ቅንጭብጭብ
7.18K subscribers
413 photos
9 videos
5 files
502 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ኢትዮጵያ!
ምድርሽ ተቆፍሮ ዘር የተገኘበት
አፈርሽ እንደ እምነት ፈዋሽ ዕፅ ያለበት፣
ቋጥኝሽ ተባርኮ ጸበል ሲፈልቅበት
የነብያተረ ቀለም ኪታብ ሲጻፍበት
ምን ነበረ ታዲያ?
ልጆችሽ ልብ ላይ ፍቅር ቢበቅልበት።
💚💛❤️
© ሜሮን ጌትነት
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ፍትሕ

ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት እና
ብሔራዊ የአልኮልና መጠጦች ፋብሪካ እያለን የጫት እርሻ ኖሮን ጫት Export እያደረግን፤ የሺሻ ማጨሻ ዕቃ ከውጪ ሲገባ ያለ ከልካይ እየገባ፤ ወጣቶችን ከምናምን ቤት ሰበሰብን ብሎ ሕግ እንደሌለበት ሐገር ያለአግባብ ወጣቶችን ማሰር ያለ ፈቃድ ማንኛውንም ዓይነት ሥልጠና መስጠት አይቻልም!!!

ፍትሕ ለወንድሞቻችን!
ፍትሕ ለአ.አበባ ወጣቶች!
ፍትሕ ለእናት ሐገሬ ልጆች!!!
#የሕግ_የበላይነት_ይከበር!!!

#ሼር
#ኢትዮጵያ
#Bçràżýkîđ
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

፨ ጠላት ሀገር እንኳን በዚህ መልኩ አይዘረፍም!

• አዲስ አበባ ውስጥ 7 ግፍ የሚፈፀምባቸው ድብቅ እስር ቤቶች ተገኙ።
- « በአዲስ አበባ ዜጎች ከሰባት ወደማያንሱ ስውር ማሰቃያ ስፍራዎች ‘በአምቡላንስ እየተጓጓዙ!’ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይፈጸምባቸው ነበር »
በእነዚህ እስር ቤቶች ዉስጥ
- ሴቶች ይደፈራሉ
- ወንዶች ግብረሰዶም ይፈፀምባቸዋል
- ወንዶች ብልታቸዉ ላይ ሀይላንድ ይንጠለጠልባቸዋል
- አይናቸውን ታስረው በጫካ ይጣላሉ

• ፖሊስ ጣቢያ፣ ማረሚያቤት እና ስውር እስር ቤቶች ውስጥ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በአሌክትሪክ ሾክ ማድረግ፣ ብልትን በፒንሳ መሳብ፣ ዛፍ ላይ ሰቅሎ ለረጅም ጊዜ ማቆየት፣ ጫካ ውስጥ እርቃንን ማሳደር፣ ጥፍር መንቀል፣ በብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል፣ አይናቸው ከታሰረ በኋላ ከከተማ አውጠቶ ጫካ ውስጥ መጣል፣ አልፎ አልፎ ከአውሬ ጋር በማሰር ማሰቃየት ሲደረግ ነበር።

• የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ፦
ከ2004 እስከ 2010 ድረስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን 37 ቢሊየን ብር የውጭ ግዢ ፈፅሟል።
እነዚህ ግዢዎች ዓለም አቀፍ ጨረታ ሳይፈፀምባቸው የተከናወኑ ናቸው። ግዢዎቹ በጥቅም በተሳሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት መሀከል የተከናወነ ነው።

• "የሰኔ 16 ቱ የቦምብ ጥቃት የተቀናበረው በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሞ ስለሆኑ በኦሮሞ ቢገደሉ ተብሎ ነው በሙከራው ኦሮሞዎች እንዲሳተፉ የተደረገው።"

• ሜቴክ ከ2004-10 ዓ.ም ከ 37 ቢሊዬን (2.5 ቢሊዬን ዶላር) የውጭ ግዢ ያለጨረታ ከውኗል።
የሐገር ውስጥ ግዢ ሙሉ ለሙሉ ያለጨረታ ተከናውኗል። የሐገር ውስጥ ግዢም በግልፅ ጨረታ መፈፀም ሲገባው እስካሁን በዚህ መልኩ የተፈፀመ የለም። ከኮርፓሬሽኑ አመራሮች ጋር የዝምድናና የጥቅም ትስስር ካላቸው ሰዎች በብዙ እጥፍ በተጋነነ ዋጋ ይገዛ ነበር። ከአንድ ድርጅት 21 ጊዜ፣ ከሌላው ደግሞ 15 ጊዜ ግጭ ተፈፅሟል። ከአንድ ድርጅት በአንድ ጊዜ ብቻ የ2015 ሚሊዮን ብር ግዢ ያለጨረታ ተፈፅሟል።

• ከተቋሙ ተልዕኮ ውጪ የተፈፀሙ ግዥዎችም አሉ። ከዚህም ውስጥ የመርከብ ግዢ ይገኝበታል። በማይመለከተውም ስራ ገብቶ ወደ ንግድ ስራ አስገብቷቸዋል

# ከተገዙ አውሮፕላኖች መሀከል አንደኛው አውሮፕላን የት እንደገባ አልታወቀም!

• በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጣሪዎች 36 በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

• በአጠቃላይ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክና ደህንነት አመራሮች ቁጥር 63 ሲሆን እስካሁንም ያልተያዙ በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ የተደበቁ አሉ።

፨ ከአቃቤ ሕግ መግለጫ
- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ
ህዳር 3 2011 ዓ.ም

#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid

Join 👉 @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ዘመቻ አድዋ ለኔ. . .

#አዲሱ_ጉግሳ_ዘ_ኢትዮጵያ

አድዋ ለኔ

ዛሬ የምኮራበት ታሪክ ባለቤት ነኝ!
ዛሬ በራሴ አቆጣጠር ዘመኔን እቀይራለው!
ዛሬ በራሴ ቋንቋ ካሻኝ እግባባለው!

ከዚህ ሁሉ ግን ሐበሻ የሚባል የነፃነት አየር እተነፍሳለው ሁሌም ግን የሚሰሙኝን የሠውነት ህሳቤዎችን እንደ ዕውቀቴና እንደ ወጌ ተለጥጬ እንዳስብ አድዋ አስችሎኛል
በራስ መተማመኔን አድዋ ሰጥቶኛል
ዛሬም ነገም እኔ ከማንም የተሻልኩ እንደሆንኩ ሳስብ አድዋ ምክንያቴ ነው
እኔ ሁሌም እላለው #ኢትዮጵያዊ መሆን መሆን ከምንፈልገው በላይ ነው። ይሄ ማለት ነፃ! ኩሩ! ጀግና! ኃያል! ሕዝብ ነኝ አሁንም ግን ምክንያቴ አድዋ ነው።
አድዋ ማለት ለኔ ከፈጣሪ በታች ሠው እንድሆን ያረገኝ ታሪኬ ነው።
አድዋ ቀለሜ ነው ኢትዮጵያዊ የሚያሰኘኝ ቀለሜ
የጀግንነት
የክብር
የእምቢ ባይነት
የራስን ቻይነት
የልዩነኝ ባይነት
አረ ምን ልበለው ብቻ #ማርያምን አድዋ ስሜ ነው

#ኢትዮጵያ_ከነክብሯ_ለዘላለም_ትኑር!!!

@kinchebchabi @roviben
ቅንጭብጭብ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ #ዝክረ_ካራማራ_ድል ይህ ድል ከ 40 ዓመት በፊት የተገኘ ሌላኛው የኢትዮጵያውያን የቅርብ ግዜ ድል ነው። #ካራማራ_ድል እ.ኢ.አ፦ የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም በ #ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ብቻ "ድንበራችንን በደማችን እናስከብራለን!" 💚💛❤️ ኢትዮጵያ ትቅደም 💚💛❤️ ሌሎች ታሪኩን ያነቡ ዘንድ ለታሪክ ጠያቂዎች ገፃችንን አጋሯቸው Join.us @kinchebchabi…
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

እንኳን ለ 41ኛው የካራማራ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ካራማራ ተራራ ነው። ልክ እንደ ሶሎዳ። በዓሉም ልክ እንደ አድዋ ብሔራዊ የድል በዓል ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ውስጣዊ ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተውና በአንድነት በመቆም ሀረርጌን፣ ሲዳሞንና ባሌን በግዛቴ አስገባለው በማለት የቃዠውን የሶማሌውን የኮሎኔል ዚያድባሬን ጦር ልክ አስገብቶ ዳር ድንበሩን ያስከበረበት ታሪካዊ ቀን። የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም።

💚💛❤️

"ክብር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ወደ ኋላ ለማይለው #የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ሰራዊት! እና በዚህ ጦርነት የአገራችን ዳር ድንበር እንዳይደፈር አብረውን ለወደቁት ለሶሻሊስቷ አገር ኩባና የቀድሞዋ ደቡብ የመን ወታደሮች!"

🏵 ክብርና ሞገስ ለሰማዕታቱ! 🕯
🇪🇹 #ኢትዮጵያችን_ለዘላለም_ትኑር! 🙏

"ውርደት ድንበሯን ላስደፈሩ፣ ከጠላት ጋር ላበሩና የከበረችውን አገር ላወረዱ ሁሉ!"

"ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም በአባቶቻችን ደም፤ #እናት_ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም! የደፈረሽ ይውደም!"

#ካራማራ ብሔራዊ የድል በዓል
"ድንበራችንን በደማችን እናስከብራለን!"
💚💛❤️ #ኢትዮጵያ_ትቅደም 💚💛❤️


ሐገራችን ኢትዮጵያን ዳር ድንበሯን ለማስከበር በዱር በገደል ለተወዋደቁ ጀግኖች።

በአድዋ ሠርግ በካራማራ መልስ ጥሪ የ 41ኛውን የድል በዓል እንደአቅማችን በዚህ መልኩ ዘክረናል በሚቀጥለው በመንግሥት ደረጃ እንደሚከበር ተስፋ እናደርጋለን።


(የድል በዓሉን ታሪክ https://t.me/kinchebchabi/1700 ይህን ሊንክ በመጠቀም ማንበብ ይቻላል።)

join 👉 @kinchebchabi
ለመፃፍ እየፈለኩ እጄን የያዘኝ የማደርገው ግራ የገባኝ ልፍስፍስ ያልኩበት አማራጭ ያጣሁበት ባወራ ምን ልጠቅም ብዬ ዝም ብዬ በውስጤ ያረርኩበት እና የክልሉ መንግሥት ሆነ ሕዝብ ከሰብዓዊነት የዘቀጠ ነገር የታየበት

የጌዴኦ ሕዝቦች መፈናቀል እና በረሃብ ማለቅ ነው። ይሄ ኹሉ ሕዝብ ተርቦ ሜዳ ወድቆ እንዴት በሚሊየን በተመደበ ገንዘብ የዘመን መለወጫ ልናከብር ነው ይባላል??? (ደቡብ - ጌዴኦ)

ኧረ እየተሳሰብን - ኧረ እንደሰው እየተሰማን - ነግ በኔ ነው
የጌዴኦ ሕዝቦች ተፈናቅለዋል! ተርበዋል እናቶች ጡት ደርቆባቸው የሚያጠቡት አጥተዋል...

ከለገጣፎ ሲፈናቀሉ መንግሥት መረጃ የለኝም
ከጌዴኦ ሲፈናቀሉ የሚዲያ ሽፋን የለም
ተረኛ ደግሞ #ሱሉልታ ነው ሊያፈናቅሉ ውጡ ማለት ጀምረዋል...

ሕዝብ እያየ ዝም መንግሥት እየሰማ ዝም

አንድም ሰው አይፈናቀልም ተብሎ አልነበር እንዴ?!
የሚያወራ ብቻ ሳይሆን የሚሰማ የውጪውን ሳይሆን ቀድሞ የቤቱን የሚሰራ መንግሥት እፈልጋለሁ!!!
አከተመ!!!

#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid
ከሰሞኑ በአዲስ መንገሻ ሃሳብ አፍላቂነት እሁድን ቤት ወይንም ሌላ ቦታ ከምናሳልፈው ከለገጣፎ ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖቻችንን አቅማችን የፈቀደውን ይዘን እንሂድ በሚለው ተነጋግረንበት ስለነበር ትናንት ከቀኑ አምስት ሠዓት ሲሆን ስምንት ሆነን ጉዟችንን ወደ ቦታው አደረግን። አያት ከደረስን በኋላ የት እንዳሉ ስንጠይቅ በአራት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም ዮሐንስ፣ ፍሉ መድኃኒዓለም፣ ዳሌ ገብርኤል እና ዋሻው ሚካኤል እንዲሁም አንድ ሚሽን የሚባል ቦታ ተጠልለው እንደሚገኙ ሠማን።

እኛም ብዙም ሠው ያላያቸውን ማየቱ ይሻላል ብለን የካ ጣፎ ዋሻው ሚካኤል የተባለ ደብር የተጠለሉትን ለማየት ወደዚያው አቀናን።

ከአያት ማዞሪያ ወደ ጣፎ የሚየመራው መንገድ መሀል ላይ ከታክሲ ወርደን በጋሪ ተሳፍረን ወደ ቤተክርስቲያኑ አመራን፡፡ቦታው ላይ ያለው ነገር እጅግ ይረብሻል። ተፈናቃዮቹ የፈረሠውን መኖሪያቸውን 20 እርምጃ በማይሞላ ርቀት ላይ ተቀምጠው ያዩታል። በተጠለሉበት ቤተክርስቲያንና በቀድሞው ቤታቸው ፍራሽ መሃል የወንዝ መውረጃ አለ፤ አባኪሮስ ወንዝ ይባላል።በእርግጥ አሁን ደርቋል። ከወንዙ ወዲያ ኦሮሚያ ወደዚህ ደግሞ አዲስ አበባ ነው አሉን። ቤታቸው የፈረሰበት አካባቢ ደግሞ ገዋሳ ጃላ ዋሻ ይባላል። ተፋናቃዮቹ ቤቱን ከዛሬ 12 ዓመት በፊት ከገበሬዎች ላይ ነው ገዝተው የገቡት። የአፈር፣ የመብራት፣ የውሃ ግብር የከፈሉባቸው ህጋዊ ደረሠኝም አላቸው።

በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት 56 አባወራዎች በአጠቃላይም 208 ሠዎች ሲኖሩ ከነዚህም ውስጥ 6ቱ ነፍሠ ጡሮች እና 84ቱ ደግሞ ህፃናት ናቸው። ህፃናቱ እድሜያቸው ከ3-8 ሚሆን ነው።

ቀይ መስቀል ያሉኝ ድንኳኖች ትንንሾች ናቸው በማለቱ 25×10 ሜትር የሚሆን ሠማያዊ የሸራ ላስቲክ ወጥረው ቀይመስቀል በሠጣቸው ፍራሽ ላይ ብርዳማውን ሌሊት ያሳልፋሉ።

እስካሁን ያደረጉትን እንቅስቃሴ ስንጠይቃቸው የኦሮሚያ ክልል መስተዳደርን አነጋግረን ነበር ሆኖም ግን እንኳን እኛን ሊሠሙን በአካባቢው የሚገኙትን ሌሎች ቤቶች እያሳዩን "እነዚህም ይፈርሳሉ እናንተ ቦታ እስክትለቁ ነው የምንጠብቀው። እኛ የምንፈልገው መሬቱን ነው።" የሚል ምላሽ በምክትል አስተዳዳሪው በኩል እንደሰጧቸው ነግረውናል። በተጨማሪም እኚሁ ምክትል አስተዳዳሪ "ኦሮሚያን ሙሉ በሙሉ የማፅዳት ሥራ ነው የምንሠራው" የሚል አሳፋሪ የሆነ ምላሽ እንደሰጧቸውም ነግረውናል።

ተስፋ ባለመቁረጥ ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቢሄዱም "እኛ ስለ ኦሮሚያ ክልል አይመለከተንም" የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል (ማንን ይሆን የሚመለከተው??? ስራቸውስ ምንድነው??? ኦሮሚያ ክልል ከሃገር ውጪ ነው???)

እስካሁንም ትንሽ ተስፋ የሰጣቸው ሠብዓዊ መብት ኮሚሽን ብቻ ነው። ህፃናቱ በመሳቀቅ ትምህርት ቤት መሄፍ አቁመዋል። ይሄ ሁሉ ግን ለመንግስት ምንም ነው።

እዚህ ያሉትን በማየት እኛ የመጀመሪያዎቹ ነን። ከአሁን በፊት ማንም ወደዚህኛው ጣቢያ አልሄደም የህፃናት ምግብ፣ ልብሶች፣ ደረቅ ምግቦች፣ የንፅህና መጠበቂያ..... ያስፈልጋል (ሄዶ አይዟችሁ ማለትም፣ ከህፃናቱ ጋር መጫወትም አንድ ነገር ነው)

በሠላም ሰርቶ የሚገባን፤ ግብር እየከፈለ የሚኖርን ዜጋ ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቅሎ፤ ህፃናትን ከትምህርት ማዕድ አጉድሎ ሃገር መገንባት ከቶ እንዴት ይቻላል???

በመጨረሻም ስንመለስ አንድ አባት እንዲህ ሲሉ ሠማኋቸው "ፋሽስት የሚባለው ጣሊያን እንኳን ወገናችን ላይ ይሄን ያህል አልጨከነም"

ስንወጣ አንድ ህፃን ልጅ ተከተለን 3 ዓመት ቢሆነው ነው፡፡ "ነገም ምግብ አምጡልኝ እሺ" አለን፡፡ ይሄን እየሰማን እንዴት ይሆን ዝም ማለት የሚቻለው? የአቅማችሁን
1፡ ምግብ፡- ፓስታ፣ መኮረኒ፣ወተት፣ ዱቄት፣ የህፃናት ወተትና ተጨማሪ ምግቦች
2፡ አልባሳት፡ የህፃናት፣ ወጣትና ጎልማሶች
3፡ የንፅህና መጠበቂያ ፡ ሳሙና፣ ሞዴስ፣ ዳይፐር
4፡ ከምንም ነገር በላይ አለሁ የሚላቸው ወገን እንዳላቸው እናሳያቸው፡፡

#ሰብዓዊነትይቅደም
#ኢትዮጵያ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ከለገጣፎ ተፈናቅለው አያት አካባቢ ዮሐንስ፣ ፍሉ
መድኃኒዓለም፣ ዳሌ ገብርኤል እና ዋሻው ሚካኤል አብያተ
ክርስቲያናትና ሚሽን የሚባል ቦታ የተጠለሉ ኢትዮጵያውያውያኖች አሉ፡፡ የቻላችሁ ቦታው ድረስ ዘልቃችሁ
ብታዩዋቸውና ብርታበረታቷቸው መልካም ነው፡፡

አሁን ላይ በቅድሚያ የሚስፈልጋቸው፦
1፡ ምግብ፡- ፓስታ፣ መኮረኒ፣ ዱቄት፣ ዘይት የህፃናት ወተትና
ተጨማሪ ምግቦች
2፡ አልባሳት፡ የህፃናት፣ ወጣትና ጎልማሶች (ለወንድና ሴት)፤
3፡ የንፅህና መጠበቂያ ፡ ሳሙና፣ ሞዴስ፣ ዳይፐር
4፡ እንደ ድንኳን የሚጠቀሙበት ሸራ ሲሆን፤ ሄዶ ለመጠየቅ
ያልቻላችሁ የአቅማችሁን ያህል ቁሳቁስ ከታች በተመለከቱት
አድራሻዎች እየደወላችሁ ብታስቀምጡልን እኛ ሰብስበን
እናደርስላቸዋለን።

1, እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ፦
በላይ 0922160672

2፡ ሰሜን ሆቴል, ቀጨኔ መድኃኒዓለም እና አዲሱ ገበያ አካባቢ፦
ዳንዔል
+251900021888፤ +251921019518

3፡ ፒያሳና ጊዮርጊስ፦
በእምነት +251922876160

4፡ መሳለሚያ ፡ ማርታ 0920680045

5፡ ስድስት ኪሎ፡ ቅድስት 091873363

6፡ መገናኛ አካባቢ፡ ሀይማኖት 0913670905

ከምንም በላይ
#ሰብዓዊነት_ይቅደም
#ኢትዮጵያ

እባክዎ መርዳት ባይችሉ ለሌሎች ሼር በማድረግ ይተባበሩ

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ይህንን ልትመለከቱ የምትችሉት #ኢትዮጵያ ብቻ ነው! 💚💛❤️

በዓለ ስቅለት - ስግደት
ጁምአ ሶላት - ስግደት

#ኢትዮጵያዬ 💚💛❤️

"ቅዳሴና አዛን አጥር ቢለያቸው
ፈጣሪ ከሠማይ አንድ ሆኖ ሰማቸው"

#መልካም_በዓል

Join - @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ነገ እሁድ ሚያዚያ 27 ጠዋት 12፡45 ምንሊክ አደባባይ እንገናኛለን፡፡ ከዚያም በዓሉ እስከሚከበርበት የድል ሀውልት (አራት ኪሎ) ድረስ በእግር እንጓዛለን፡፡ በዚያም ፉከራና ሽለላ እንዲሁም ህብረ ዝማሬዎችን እናቀርባለን፡፡ እሱን ስንጨርስ ወደ ስድስት ኪሎ በማምራት የሰማእታት ሀውልት ስር በመገኘት በግራዚያኒ በግፍ የተጨፈጨፉብንን ኢትዮጵያውያንን እንዘክራለን፡፡ የአለቱ ዝግጅታችን በሰማዕታቱ ሀውልት ስር እናጠቃልላለን፡፡ የወደዳችሁ ተቀላቀሉን፡፡
#78ኛው #የድልበዓል
#ኢትዮጵያ

@Bcrazykid @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ሚያዝያ 27
እሁድ | የድል በዓል
ዳግም ትንሳኤ | ረመዳን

እንኳን አደረሳችሁ | መልካም በዓል

አዲስ አበባ | #ኢትዮጵያ
78ኛው የድል በዓል አከባበር
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

78ኛው የድል በዓል አከባበር
@ አርበኞች አደባባይ (4 ኪሎ)

አንድነት! ውበት! #ኢትዮጵያ!

"ኢትዮጵያዊነት ከዘር ከቀለም ከሃይማኖትም በላይ ነው!"

@Bcrazykid @kinchebchabi
ቅንጭብጭብ
#B ዛሬም ልደቴ ነው፤ አዎ ድፍን ፳፫ አመቴ #Bcrazykid የቤቱ አባወራ ® (ማነው መልካም ልደት የሚለኝ፤ መልካም የሚመኝልኝ 😊)
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ከዓመታት በፊት በግንቦት 1988ዓ.ም በጳውሎስ ሆስፒታል በተነሳ መውለጃቸው በደረሰ የእርጉዝ ሴቶች ሰላማዊ የጭንቅ (የሕመም) ጩኸት (ምጥ) ንፁሀን ጨቅላዎች ከሞቀ የዘጠኝ ወር የእናት ቤታቸው በዶክተሮች አፈናቃይነት ብዙ ጨቅላዎች ወደዚች ምድር ወጡ ከነሱም መሀል አንደኛው 52cm የሚረዝም 3.2 ኪ.ግ የሚመዝን ጨቅላ ነበር።

ጨቅለው ዛሬ ትልቅ ሰው ሆናል ብዙ መጠየቅ ብዙ ማወቅ ደስ ይለዋል፤ መሳቅ ሱሱ ነው በቁም ነገሮች ላይ ኮስተር ማለቱን ቢያውቅበትም ፈገግታው ታግላ ትወጣለች፣ ሰው ማናደድ ይወዳል ሲከፋቸው ግን ፍፁም ይከፋዋል ይቅር በሉኝ ብሎ አይጠግብም፣ ፍፁም ሰላም ይሠማዋል በሕይወቱ ሲበዛ ደስተኛ ነው። አጣሁ ብሎ የማይወፋው ይሉቁንም ደግ አረገ ብሎ የሚስቅ አገኘሁ ብሎ የማይመጻደቅ ሕይወትን እንደ ጨዋታ ቀለል አድርጎ የሚጫወት ሰው ነው።

በተገኘው አጋጣሚ ስለሐገሩ መደስኮር ይወዳል የልጅነት ሕልሙ ቢሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወጣትነት ዘመኑ በተለያዩ መድረኮች፣ ራዲዮና ቴሌቭዥን ጣብያዎች፣ በአደባባይ እንዲሁም በማሕበራዊ ትስስር ገጾች ኢትዮጵያዊነትን ለመንገር እድሉን አግኝቶ ተጠቅሞበታል።

ኢትዮጵያ ሲባል ደስ ይዋል፤ ሰንደቋን ሲያይና ሲዘምርላት አይኑ እምባ ያቀራል ከሰዎች ተሠባስቦ መለየት አይሆንለትም፤ ሲለያዩ ይከፋዋል። መዞር ይወዳል ሐገር ዞሮ ለማየትማ ማ ብሎት... በትንሽ ብር ሐገሬ ላይ ነኝ ምን እሆናለሁ ብሎ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ይሄዳል። ባገኘው አቀባበል ረክቶ ይመለሳል።

ከኦሮሞው በአምቦ ረብሻ ቤ/ክ ተጠልሎ ገበታ መጥቶለት ከእጃቸው በልቷል፤ ከአማራው ባሕርዳር ላይ እንጀራ ማር ያለ ወቅቱ ተቆርጦለት አጣጥሟል ፤ በጢስ አባይ ፏፏቴ ተደምሞ ሳይጨርስ በላሊበላ ፍልፍል ቤ/ክ ተደንቋል፤ በጎንደር ፋሲለደስ ግንብ ፎቶ ተነስቷል ወዳጆቹ ከፈተና ሰዓት ጊዜ ተሻምተው አዝናንተውታል፤ ከትግሬው በመቀሌ እንግዳ ነህ ተብሎ አልጋ ተለቆለት ባለቤቱ መሬት ተኝቶ እንግዳው ተከብሯል ፤ በሐረር ፍቅር በዝቶለት በተጣበበ ሰዓት ከስራ ሰዓት ተሻምታው የምሳ ግብዣ ተደርጎለታል፤ በሐዋሳና አርባምንጭ ለም መሬት ሽር ብትን ብሎ ሰለቸን ሳይሉ ለወራት ተንከባክበውት ተመልሷል፤ በድሬ-ደዋ ጣፋጭ ባቅላትና ሙሸበክ በቁሙ ጎርሶ ሲበቃው ገዝቶ ተመልሷል፤ አክሱም ጽዮንን ተሳልሞ በአክሱም ሐውልት ቅርስ ፈዟል፣ ከሰሜን ከደቡብ ከምስራቅ ከምዕራቡ ተደመሩ ሳይባል ከእጃቸው በልቶ ጠጥቶ ተዋህዷል።
(jo, ግርማይ, ፋሲካው, ግርማ, ሳምሪ, ሕይወት... ምሥጋና ለእናንተ)

ይህ ሰው ዛሬም ይዞራል ለደቂቃ ያወቀውን ሰው ለሰዓታት ይናፍቃል፤ በነገሮች ሁሉ ስቆ ያልፋል ሰዎች ሊያናድዱት ሲፈልጉ ይብስበታል ከልክ በላይ ይስቃል። ስቀን ዓለምን እናስቃለን ይላል፤ ቆሞ ለመሄድ ከእግሩ ይልቅ የቆመበትን መሬት ያመሠግናል።

ፍላጎቱ የተገደበ አይደለም፤ ማስቀደም ያለበትን ግን ያስቀድማል ተፈጥሯዊ ነገሮች ይሥቡታል የእግር መንገድና ሙዚቃ ሃኪሞቹ ናቸው ሳቁ ለሁሉ መድኃኒቱ ናት በቃ ዝምብሎ መሳቅ ይወዳል። ሲከፋው መሳቅ፣ ሲደሰት መሳቅ፣ ሲያጣ መሳቅ፣ ሲያገኝም መሰቅ . . . ከሳቅ ውጪ አያውቅም
"በምኒ ምን ያውቃል፤ ሲሰድቡት ይሥቃል።" ወዳጁ የተረተበት ተረት ነው። (ሮቤል)

ይህ ሰው አሁን አድጓል ባለ ጢም ባለ ጎፈሬ ነው ዞሮ ማየት ከሚፈልጋቸው የሐገሩ ከተሞች ሐመር፣ አፋር፣ ባሌ ቢቀሩትም በቅርቡ መጣለሁ ይላቸዋል ከ 1 ዓመት በፊት እመጣለሁ ያላቸውን ሄዶ አይቷቸዋል ደስ ብሎታል ኧረ ጭራሽ ሊደግማቸው ነው። ጉራ የለበትም የሆነውን ነኝ ማለትም አያፍርም፣ ከባድ የሚባሉ ኃላፊነቶችን መውሰድ ያስደስደስተዋል፤ በድል እንደሚወጣው ያምናል! ካልሆነም በብልሃት አልፎት መማሪያው ያደርገዋል። [ይልቅ እቆምለታለሁ ብሎ ያሰበው የጾታ ትንኮሳ ጉዳይ ባይሳካለትም አንዳንድ ሃሳቦቹ በሌሎች ሰዎች ስለተሰሩ ደስተኛ ነው። (መሠራቱ እንጂ የግድ እኔ ካልሰራሁት አይልም) መሥራት የሚፈልገው ጥግ ድረስ ግን ይሰራዋል።]

ገና ለገና በዶክተር አፈናቃይነት ከእናቴ ማኅፀን ከወጣሁ 23 ዓመት ሆነኝ ብሎ እንዲህ ከደሰኮረ ይሄን ሰው በድጋሚ ከ 23 ዓመት በኋላ አስቡት ምን ያህል ተረት/ታሪክ ሊደሰኩር እንደሚችል 😊😁

ለማንኛውም ይህ ሰው ዛሬ ልደቱ ነው፤ ይህ ሰው እኔ ነኝ ይኸው 23 ዓመቴን ቀብ አደረኳት። ስወለድ የነበረኝ አልቃሻነት ዛሬ በሳቅ እና ሳቅ ብቻ ተቀይሯል።

ስትስቁ ዋሉ፤ መወለድ ብርቅ አይደለም ለምን ተወለድኩ ማለትና አውቆ መኖር ግን መልካም ነው።

እዚህ ለመድረሴ መጀመሪያ ለፈጠረኝ እርሱ እንዲህ ለመሆኔ በመልካምም በመጥፎም ለሠራችሁኝ ሁሉ ክብርና ምሥጋና ለእናንተ. . .

® አባወራው
እንኳንም ተወለድኩ
#መልካም_ልደት ለኔ!
#ኢትዮጵያ | @Bcrazykid
@kinchebchabi @roviben
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

"ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ"

ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ፤ መልካም የገና በዓል።

#ገና
#ኢትዮጵያ
@kinchebchabi @kinchebchabi
ሰላም...
እንዴት ናችሁ?

ከረዥሙና አድካሚው የ 46 ቀን የዓድዋ ጉዞ በኋላ ተመልሰናል። በነዚህ ቀናት ውስጥ ለቤቱ ጭር ማለት ይቅርታችሁን እንጠይቃለን 🙏

ሰላም ተመልሰናል ሐገሩ መንደሩ ቀዬው ኹሉ ሰላም ነው። በ facebook የምታዩት በወሬ የምትሰሙት ረብሻ ነው፤ መንገድ ዝግ ነው፤ ሰዉ ክፉ ነው.... የሚሉት ኹሉ ውሸት ስለመሆኑና ምድር ላይ ያለው እውነት ከዚህ ወሬ ፍፁም ልዩ ስለመሆኑ የሐገሬ ሕዝብ ፍቅር፣ የዋህ፣ አልባሽ፤ አጉራሽ ስለመሆኑ ከእኛ በላይ ምስክር አይገኝም!!

ሰላም ፍቅር አንድነት ለኢትዮጵያ...

ተከታታይ ጠቃሚ ሐሳቦችን፣ ታሪኮች፣ ግጥሞች እና ሌሎችም መረጃዎች ይቀጥላሉ.... አብራችሁን ስላላችሁ በእጅጉ እናመሰግናለን 🙏

የተለያዩ ሐሳቦችና ጽሁፎቻችሁን በ @bcrazykid አጋሩን

#ሻሎም
#ኢትዮጵያ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ
አለ ቂል ሰው 'ሁሉም አከተመ'
ደቂቅ ተስፋን ካየናት አርቀን
ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን!

ጨለማው በብርሀን ይለወጣል!
ሕይወት በብርሀን ጊዜ ብቻ የምንደሰትባትና የምንፈነጥዝባት አይደለችም። ይልቁኑም በጨለማውና ግራ በገባን ጊዜ ጭምር ከጨለማውና ከውጥንቅጡ ለመውጣት በምናደርገው ጥረት ይበልጥ ህይወታችንን ወደ በለጠ ደስታ ውስጥ እንጨምረዋለን።

በጨለማው ጊዜ በውጥንቅጡ ጊዜ በችግሩ ጊዜ ተስፋ የቆረጡ፣ህይወታችን አበቃላት ብለው ጉዟቸውን ያቆሙና ህመሙ በዛብኝ ብለው ህልማቸውን ያቋረጡት ሁሉ አስደናቂዋን የብርሀን ፍንጣቂ ለማየት አይታደሉም።

የብርሀኗን ፍንጣቂ ለማየት በህመሙ ጊዜ መጠንከር፣ በስቃዩ ጊዜ መበርታት በጨለማው ጊዜ መታገስ ያስፈልጋል፤ ያኔ ህመሙ ወደ መዳን፣ ማጣቱ ወደ ማግኘት፣ ጨለማውም ወደ ብርሀን ይለወጣል!

በጨለማው ጊዜ ጥርስህን ንከስና ጉዞህን ቀጥል ወደ ስኬትህ መጨረሻ የሚያደርስህን ትግል በፍጹም አታቁም። አዎ ፈተናው ምን ያህል ቢበዛና ሊጥልህ ቢያንገዳግድህም አንተ ግን በፍጹም አትውደቅ። ብትወድቅም እንኳ እየተንፏቀቅ መሄድህን ቀጥል። ያኔ ብርሀን ከፊትህ ይመጣል!

ይፈትናል እንጂ ድሉ ያንተ ነው!
አስተውል! አበቃ የሚባል ነገር የለም ሕይወት ይቀጥላል...

#አጉላ | #ኢትዮጵያ | @Bcrazykid

join us
@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበል የሚያሰኝ ውሳኔ... (ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ)

መጋቢት 7 ቀን ከተወሰኑት ውሳኔዎች በተጨማሪ፦

1. ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞች ሁሉ በራሳቸው ወጪ ለዚሁ ዓላማ በተወሰኑ ሆቴሎች ውስጥ ለ14 ቀናት ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ።

2. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሀገራት የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት እንዲያቆም።

3. መንግሥት የሀይማኖት ተቋማት እና የአምልኮ ስፍራዎች ላይ የምዕመናን መሰባሰብ በጊዜያዊነት መቋረጡን የሚደግፍ ሲሆን፣ የኮቪድ19 ቫይረስን ስርጭት ለመግታት ያስችል ዘንድ ንክኪን በማያስከትሉ ሌሎች አማራጮች አምልኮ ቢካሄድ ይመረጣል።

4. ማረሚያ ቤቶች ጊዜያዊ ማቆያቸውን እና ሌሎች ስፍራዎችን በመጠቀም ጭምር መተፋፈግን እንዲያስቀሩ። በተጨማሪም፣ አዲስ ታራሚዎች ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባታቸው በፊት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን እንዲያካሂዱ። ታራሚዎችን መጠየቅ ለተወሰነ ጊዜ የተከለከለ ሲሆን፣ በቀላል ጥፋት ምክንያት ማረሚያ ቤት የገቡ ወይም የእርምት ጊዜያቸው የተቃረበ ታራሚዎች እንዲፈቱ።

5. የውጪ ዜጎችን መተናኮል ተቀባይነት የሌለው እና ኢትዮጵያዊ ያይደለ ጥፋት ነው። ሕዝቡ ቫይረሱ ዘርና ዜግነትን የማይለይ መሆኑን ተገንዝቦ፣ የውጪ ዜጎች ላይ ጣት ከመቀሰር እና ከማግለል ይልቅ፣ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ቫይረሱን የመከላከል እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርበታል።

6. ላለፉት ቀናት የማስተባበር ሥራን ሲሰሩ የነበሩ ወጣቶችም፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎቻቸውን ሲቀጥሉ በተመሳሳይ መልኩ ራሳቸውን እንዲጠብቁ እና ቫይረሱን የመከላከያ እርምጃዎችን ተፈጻሚ እንዲያደርጉ።

7. ኮሚቴው ወሳኝ የነፍስ አድን ሥራዎችን በቂ መገልገያዎች እና መሣሪያዎች ሳይኖሯቸው በማከናወን ላይ የሚገኙትን የሕክምና ባለሙያዎች ያመሰግናል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ፣ ኮሚቴው በትምሕርት ላይ ያሉትን ጨምሮ፣ ሁሉም የሕክምና ባለሙያዎች ለብሔራዊ ግዳጅ እንዲዘጋጁ ጥሪውን ያቀርባል።

8. የመጀመሪያው ዙር በአሊባባ አማካኝነት በጃክ ማ የተበረከቱት የምርመራ ቁሶች፣ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎች እንዲሁም ቫይረሱን የተመለከቱ መመሪያዎች ስብስብ እሁድ መጋቢት 13፣ 2012 ይደርሳሉ። ከዚህ አንጻር፣ ኮሚቴው በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም እንዲደርሳቸው ለታሰበላቸው የአፍሪካ ሀገራት ለማሰራጨት ቅድመ-ዝግጅት እያካሄደ ይገኛል።

9. የጭፈራ ቤቶች እና የመጠጥ ቤቶች ቫይረሱን የመከላከል እና ስርጭቱን የመግታቱ አካል ሆነው፣ በጊዜያዊነት ሥራቸውን ያቆማሉ።

10. ይህንን አሳሳቢ የጤና ሁኔታ በመጠቀም ከገበያ ዋጋ ከፍ ባለ መጠን በመሸጥ ትርፍ ለማጋበስ በሚሞክሩ ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ይቀጥላል።

11. ክልሎች ከፌደራል መንግሥት ድጋፍ እየተደረገላቸው፣ ዝግጁነታቸውን ብቁ ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።

#ኢትዮጵያ
#ኮሮና #ኮቪድ19

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#ኢትዮጵያዬ.... ገስግሺ ወደፊት

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መድኃኒትን የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማጣመር እየሞከረች ነው።
ዕፀ ደብዳቤና ሌሎች መጻሕፍቶችሽ ለዛሬ መድሀኒት ናቸውና ይውጡ ያገልግሉ...
ሐኪም አበበች ሽፈራውና ሌሎች የዕፅ አዋቂዎች ትኩረት የተነፈጉ የባሕል ሐኪሞችሽ ዛሬ ተባብረው አለምን አፉን ያሲዙልኝ ዘንድ እርሱ ይራዳቸው።

#አሜን
#ኢትዮጵያ
#Bcrazykid

የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ቫይረሱን ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሂደቶችን በስኬት አልፏል፡፡

ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻ እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የሀገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለዘመን አመጣሹ ኮሮና ቫይረስ( ኮቪድ -19) ወረርሽኝ ህክምና የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

መድሃኒቱ የመከላከል አቅም የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለው እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡

የምርምር ሂደቱ ተጠናቅቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል፡፡

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
.
=> አድዋ እና ሰበቡ
©በሲራክ ወንድሙ
... ክፍል ፩
....... ይህ ፅሁፍ ኅብረ
ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በቴዎድሮስ በየነ በ2008 ዓ.ም ከታተመው የታሪክ መፅሀፍ ውስጥ የአድዋ ድል ከሚለው ምዕራፍ ላይ ለአንባቢ እንዲበጅ (እንዲገባ) በሌላ ቅንፍ በትንሹ እውቀቷን ለማስጨበጥ በሌላ ሌላ ቅንፍ ለመላው አፍሪካ የነፃነት በዓል ምክኒያት በማድረግ ከ ፌስቡክ ሆይሆይታ ና ሆያሆዬ ባሻገር ጦርነቱ ላይ በምናብ በመገኘት ለመዘካከር ነውና ሳትሰለቹ አንብቧት።

መጀመሪያ ላይ ስለአድዋ ጦርነት መንስኤ ሲነሳ የውጫሌው ውል አንቀፅ አስራ ሰባት እንደሆነ በሰፊው ሲነሳ እንሰማለን
ውሉ ችግሩ ምንድነው? መቼ ተፈራረሙ? ውጫሌ የት ነው?

....ውጫሌ በወሎ ወረኢሉ ውስጥ የምትገኝ መንደር ስትሆን ይህን ውል የኢጣልያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት በሚያዚያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም በውሉ አስተርጓሚ በግራዝማች ዮሴፍ ንጉሴ የተከናወነ ውል ነው።
ውሉ ጠቅላላ 20 አንቀፅ ሲኖረው ለጦርነቱ መነሻ የሆነው አንቀፅ 17 ነው።

እስኪ አንቀፁን በሁለቱም ትርጉም እንመልከተውና ለጥቀን ሌላውን እንቀጥል:-
#በአማረኛ_የተፃፈው
"የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከአውሮፓ ነገስታት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ የኢጣሊያ መንግስት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል።"

.... ይላል።
#በኢጣሊያኛ_የተፃፈው_ደግሞ
"የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባቸዋል።"
...የሚል ነበር።

ጣሊያኖች ይህን ውል ከተዋዋሉ በኃላ ለ12 የአውሮፓ መንግስታትና ለዩናይትድስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ጭምር October 11 ቀን 1889 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ
#ኢትዮጵያ_በኢጣሊያ_ስር_ነች እያሉ አሳወቁ።
በትምህርት ቤት መማሪያ ደብተሮችም ላይ ሁሉ
ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ጥገኝነት ስር ናት የሚል ታተመ።

ይህ ለአድዋ ጦርነት መነሳት ምክኒያት ና ዋነኛ መንስኤ የሆነው ጉዳይ ሊታወቅ የቻለው አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ የተባሉ ቋንቋ አዋቂ አፄ ምሊኒክ በሰጧቸው ትዕዛዝ መሰረት የውሉን ሰነድ በመመርመር የውሉ 17ኛው አንቀፅ የያዘውን ትርጉም መዛባት በመግለፅ ጉዳዩ
ኢትዮጵያ የምትጎዳበት ስለመሆኑ ጭምር በማስረዳት በሰጡት ቃል ነው።

............. ይህን ያህል ስለ17ኛው ውል መሳሳት አቅጣጫ ከያዝንና ካየን የትርጉሙ መጭበርበር እንዴት ከአለቃ አፅመ ጊዮርጊስ ለአፄ ምሊኒክ እንደደረሰ እንቃኝ።
አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ ባልታተመ (ይህ የወንድማችን ቅፅ አንድ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ) መፅሀፋቸው እንደገለፁት ለአፄ ለምሊኒክ እንዲህ ሲሉ በደብዳቤ አመለከቱ :-
<< የተፃፈው ውል ኢጣሊያ አገር የሚሄደው ማለፊያ ነው።
ብቻ 17ኛውን ክፍል ይመልከቱት።ዛሬ በሚዛን ብትመዘን የብር ተመን አትሆንም ካንድ ዓመት በኃላ ግን ከሺህ ቶን ፈረሱላ እርሳስ ይልቅ ትከብዳለች። >>

... ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው ምኒሊክ አንቶኔን አስጠርተው እንደገና ጠየቁት።
አሁንም ግልፅ ባልሆነ አነጋገር አጭበረበራቸው። እንዲህም አለ << ታዲያ ይህ ምን ክፋት አለበት (17ኛው ክፍል) እኛ የርስዎ አሽከርዎ ፖስተኛ መሆናችን ነው እንጂ።>>... | አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ (ያልታተመ)|

....... የውሉ ዋና ፀሀፊ ፒዬትሮ አንቶኔሊ ከአፄ ምሊኒክ ከእቴጌ ጣይቱና ከመኳንንቱ ፊት ቀርቦ ይህን የውጫሌ ውል እምቢ ካሉ ጦርነት መነሳቱን እንዲያውቁት ያስፈልጋል ብሎ ሲደነፋ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ እጥፍ ጊዜ ቱግ ብለው ተቆጡና፤
" የዛሬ ሳምንት አድርገው። በዚህ የሚደነግጥልህ የለም ሂድ የፎከርክበትን አድርግ። እኛም የመጣውን እናነሰዋለን። እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው በዚህ የሌለ አይምሰልህ።
የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም። አሁንም ሂድ አይምሽብህ የፎከርክበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገው። እኛም እዚህ እንቆይሃለን።.....
እኛ ለራሳችን እንበቃለን የሀገራችንንም ክብር እንጠብቃለን። አንፈራችሁም! በፈቀድነው ጊዜ ከመሬታችን ከሀገራችን ተራራ እንደ ድንጋይ እንፈነቅላችኃለን።" አሉት።

እርሱም ከአዳራሹ ሊወጣ ከሞከረ በኃላ እንደገና መለስ ብሎ
"የምንገጥመውኮ ጦርነት ነው፤ ወንዶቹስ በሆነላቸው እንኳን ሴቲቱ" አላቸው።
"የእኔ ሴትነትና ያንተ ወንድነት የሚለካው እዚያው ጦር ሜዳ ነውና እንዳትቀር።"ብለው መለሱለት።
እንግዲህ የአጭቤው(አጭበርባሪው)አንቶኔሊ አንቶዬ(ስምህን ቄስ ይጥራው አንተ ሰላቢ😀 ለነገሩ....😀😀)
በንቀት እና በወኔ ሙላት የተመላለሱትን ቃለ ምልልስ አይተናል።

የጣይቱን ፉከራ በጦርነቱ ውስጥ በሰራችው ገድል የምናውቀው ነው መቼስ።
ያው ዘመን እየመጣ ዘመን በሄደ ቁጥር እነእቴጌን መሰል ሴቶችን ማጣት የሀገር ህመም ነው። መቼስ ዘንድሮ እንደሆነ ፎክረውና ብልሃት ምሰው ከሚያሸንፉ ይልቅ ቁራጭ ጨርቅ በላያቸው ላይ ለጥፈው ወንዱን እያፈዘዙ አንዴ ከቆመ ዛፍና መኪና ጋር እያጋጩ አንዴ ቦይ ውስጥ እየከተቱ ሆኗል ብልሃቱ። (ቱ ደሞኮ እኛኑ ነው 😂)
እኔስ ስንቴ ነው አንገቴን እስኪያመኝ እየሾፍኩ ቆሎ በትኜ ጣቢያ ያደርኩት 😀 " መገን" አለ ወሎ።

የአንቶኔሊን ንቀት ታክል በዘመኔ ላይ መማረር ቢኖርብኝም ይሁን ይመቻቸው ብያለሁ።
የዚህችን ክፍል መዝጊያ ከመፅሀፉ ውስጥ ባገኘዋት ፈገግ በምታስብል ገጠመኝ ልዝጋና በቀጣዩ ቀን በሌላ ክፍል ልመለስ....

...... አንቶኔሊ ከስብሰባው ሲወጣ ምኒልክ ለጋሲዮን ድረስ የሚሄድበት በቅሎ ስጡት ብለው ተሰጠው። አንቶኔሊ በቅሎ ለሰጠው አሽከር አንድ መቶ ብር ሰጠ።
አሽከሩም የተሰጠውን ብር ይዞ አዳራሽ ገብቶ ለምኒልክ ነገረ።
ራስ መኮንን ነበሩና " ጉርሻ ከሆነ ይበዛል። ጃንሆይ ለሰጡት በቅሎ ከሆነም ያንሳልና ይመለስ!" አሉ። ምኒልክም ስቀው ለአሽከሩ "ጉርሻ ነውና ውሰደው" አሉት።

........... ዛሬ የአድዋን ድል መዳረሻ ቀናት አስመልክቼ በቅንጭብ ያቀረብኩት ክፍል ይህን ይመስላል በቀጣይ አንዳንድ የጦርነቱን ነጥቦች እናያለን ሀሳብ አስታየታችሁን ፃፉልኝ።
የተሳሳትኩትም ካለ አርሙኝ ያጠፋሁትም ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ።🙏

ለዚህ ፅሁፌ በዋነኝነት ኃብረ
ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በ2008 ዓ.ም በቴዎድሮስ በየነ የታተመውን ቅፅ አንድን ተጠቅሜያለሁ።
ቸር ቆይታ!!!
- ለማድብን እጅጉ ( ቃሲም )
- ለበፍቃዱ አረጋ
#እና
- ለቃለአብ ሲሳይ (ናታኒም)
ምስጋናዬ ይድረስልኝ
©
#ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@kinchebchabi
@kinchebchabi
ይህን ለምታዩ ኹሉ ሰላም ይሁን #ሰላም!
#ኢትዮጵያ @Bcrazykid