ቅንጭብጭብ
7.5K subscribers
408 photos
9 videos
1 file
497 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ድንቡሽ ፣ ድንቡሽቡሽ
እንትፍ ፣ ጣል የጠላን ጉሽ።

ሱራ ቢራቢሮ🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
////////////////////

#ልቤ_ልብ_እሚለው?!

ዘመን መቀየሩን በጋና ክረምቱን
ተፈራርቆ መቆም ጨረቃ ፀሐዩን
ሙቀትና ብርድን አካሌ እሚለየው
ብርሃንና ጨለማን ላይኔ የሚታየው
ከጎኔ ስትሆኝ ወይ ስትርቂ ነው
ልቤ ልብ እሚለው..
ከጎኔ ስትሆኝ በጋ፣ፀሐይ፣ሙቀትና ብርሃን
ከጎኔ ስትርቂ ጨረቃ፣ብርድና ጨለማን!!


✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

@kinchebchabi
@kinchebchabi
እስስት : ስትጎተትና : ስትቀያየር እንደምትጠላ : አታውቅም : አካሄዷም : ቢሆን ፥ አይኗ : ልቧን : ይመራዋል : እንጅ ልቧ : አይኗን : እንደሚከተለው : አታውቅም.....
ግንኮ : አይን : ያየውን : ለልብ : ካልነገረው : ልብም : አድምጦ : ካላመነበት : አይንን : ይከተለዋልን?

መቼም አንዴ ለጉዞ ፈጥሮኛልና መንገድም : እወድ የለ .....
በጉም : ላይ : እየተረማመድኩ : ሳለ ብቻዬን : አግዜሩን : አግኝቸው : ነበር : በምናባዊ : ፀዳል እንደምናስበው : አደለም : ኮስማና ነው።

እናተ : ሰዎች: ለምን : ትጠሉኛላችሁ : ስለምንስ ከክብሬ : ቁልቁል : አፈረጣችሁኝ : ማቅለላችሁ : ሳይቀር : ለሌሎች : መሳለቂያ : አረጋችሁኝ ፥ ከዙፋኔ እያለሁ : እንደሌለሁ : አበሸቀጣችሁኝ ለምን? ስለምንስ? ተጠራጣሪ : ሆናችሁ : በኔ ለምን? እንባ እንቅ እንባ እንቅ ,,,,,
እያረገው : ሶስት : የእንባ : ዘለላ :ከገፁ ፥ ሲረግፍ እየሁ።

እንባው ፥ ወደስቅለቱ : ትዝታ : እያላጋ : ወሰደን በስቅለቴ : ግዜ አንድ : ደንባራ : ወታደር : በጦር ጎኔን ሲወጋኝ : ህመሙን : አታውቅም : ይሁዳ : በከንፈሮቹ ሀሞት : ተጎንጭቶ : ጉንጨ : ላይ : ሲተፋብኝ : የተሰማኝን : አታውቅም : ጴጥሮስ : ሶስት : ግዜ : አንድ ለአብ አንድ ለወልድ አንድ ለመንፈስቅዱስ ለያንዳንዳችን : በአንድነት : የክህደትን : ኮሶ : ሲያግተን : ምሬቱን : አታውቅም።

40 ቀን 40 ለሊት ስፆም ሰይጣን በእባብ ተመስሎ ሲፈትነኝ የፈጠርኩትን መልሶ የኔ ሊያረጋቸው ሲደራደረኝ ቤተ መቅደሴን ሲሻቀጡበት እናቴን ከቁሻሻ መሀል ትቢያ እንደተደፋ ልቅላቂ ሲጠየፏት አታውቅም።

አዎ አታውቅም ........ እናት ሰዎች ህመሙን አታውቁም .........

የእግዜር እንባ ግን ምን አይነት ነው?

እኔም: ሆድ : ብሶኝ : የልቤን : ዘረገፍኩለት :ጌትዬ : በሁለት : አለም : ሰካር : ውስጥ: አየዳገርኩ: ለምን ዝም አልከኝ? አንተኮ: ብትታመምም : አምላክ ነህ የአምላክነትህ : ባህርይ ረቂቅ : ነው ያስችልሀል::

ግን ለምን ፈጠርከኝ? ማጥ: ረመጥ : ውስጥ : ከተትከኝ? እውነት አውጣኝ : ብዬ : ስለምንህ: ሳትሰማኝ : ቀርተህ ነው?
የህይወትስ ጣዕሙ በምን ይለካል ? በድን : አካልን አሸክመኸኝ : ለአመመታት : መክረሜን ዘንግተኸው ነውን?

እኔ : የነካሁት : ሁሉ : ርኩሰትን : እንዲላበስ : ሁሌ እንድሸሸግ : የምታረገኝ : ራሴን : በራሴው እንደ እፉኝን : ስውጥ አላሳዝንህምን?

የእናትህስ : ህመም : አንተን : ብቻ : የሚቆረቁርህ ይመስልሀል?
እሷኮ : አምጣ : አልወለደችህም : ደም : አልፈሰሳትም
ምነው_ቸሩ _መድሀኔ_አለም : የኔዋ : እናት: ወዝ ወዘናዋን : አጠንፍፋ : ባማጠች : የህመሟን ሲቃ ባስረቀረቀች : አኔን : ወልዳ : እንኳ_ማርያም : ማረችሽ ቢሏት : አንተው : የማርካት መሰለህ? በድኩም : አካሏ : ተንፏቃ : አፈር : ልሳ : ብትለምንህ : መች ምሬሻለው : አልካትና? የማርያም ልጅ...!!

አንተ : ብትፆም :ባህሪህ : ቅዱስ : ነህና : ይፈቅድልሀል እኛስ :አንጀታችን :ሲታለብ :ቆርቆሮ :ቤታችን :ውስጥ : በችጋር : ስንለበለብ :ዞር ብለህ : አይተኸናል : እንዴ?
ቅፅበታዊ : ደስታን : አሳይተህ : ዛላቂያዊ : ህመምን ከልባችን : የቸነከርከው : እውነት : ከሳዶርና ፣ አላዶር የሚተናነሱ : ይመስልሃልን?

ተው : እንጅ : ቤዛ ከሉ መድሀኔ አለም..... ተው እንጅ የማርያም ልጅ!!

ተስፋዬን : በምኞት : ደግፌ : ብጓዝ :ባንተ : አይደል የጨነገፈው : ማያዬ :መመልከቻ : አድማሴን : ባገኛት
ባንተም : አይደል : ያጣኃት? እንደኩታ : አይሽሞንሙነህ : ያለበስከኝ : ይህን :ማንነት አንተም አደል : የፈጠርከው ? ይኸው : እሷም /ወደመሸሹ አጋደለች....
እስቲ : ልወቀው : ጥፋቴን :ለምን : ግራ አርገህ ፈጠርከኝ?
ምን ትለኝ ይሆን? ምንስ ምላሽ ይኖርህ?

ግን ለምን አትወስደኝም? ኖሬ : የህይወት : ጣዕሙንስ በምን :ምላሴ : ላጣጥመው? ምላሴን : ቆርጠህብኝ ......ሳላጣጥመው : ኮመጠጠኝ።

ተፈጥሮ : ፊቱን : አጨፍግጎብኝ : ሳለ : ከነፍሴ የተጣባች : እንስትን : ወዳንተ : ልካኝ : ነበር። አንተ የምድርና ፣ የሰማይ : ጌታ : ሆይ : ቸኮሌት : ላክልኝ ብልሀለች።

ከጥሪው : መዝብ : ሳሟ :ሳይሰፍር : ወደኔ መታ የነበረችው : ማያዬን አወካት?

ለነገሩ : አንተ : ብታቅም : አላቅም :ከማለት : ወደኃላ አትልም...... ብቻ እሷ ታቅሀለች።

በቃና : ዘገሊላ :ግዜ : ውሀውን : ወይን : ጠጅ : አድገህ : ነበር : በሰው : ሰርግ : እንደዚ : የሆክ : በራህ : ሰርግ : እንዴት: ትሆን?
በስቅለትህ : ወቅት : ጎንህን : ሲወጉህ : ውሀ፣ ደም፣ ወተት : ፈሶህ ነበር ።

በመጀመሪያ :ቀን : ማያዬን : ሳገኛት : ውሀ ጠጥታ ነበር ።
በሁለተኛው : ቀን : ስንገናኝ : በተፈጥሮ : ደም እየፈሰሳት :ነበረ ።
በሶስተኛ : ቀን : ፈጣሪ : ቸኮሌት : በኔ : በኩል እንዲልክላት : ጠይቃኝ ነበር።

በቸኮሌት: ውስጥ : ወተቱን : ለማግኘት :ፈልጋለው ይሆናላ....


ቸኮሌቷን : አንድቀን : ይዤላት: እንምመጣ :ታውቅ ይሆን?

አታውመቅም.........

የእግዚአብሄርን : ልጅ : ሰርግ : አይቼ : ከድግሱ : በልቼ ጠጥቼ : መሞቴን : እንኳን : አታውቅም..........


አዎ አታውቅመም.....

አደራ
******ንገሩልኝ******


ፀሀፊ
🦋 ሱራፌል ጌትነት
ሱራ ቢራቢሮ🦋
(🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 @kinchebchabi 🦋🦋
አታውቅም

(🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ምሽቴን በ( Ali_faraka)

ዘፈን ነውዝ


🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
አልቦ : መጋት : ምን ይሉታል? ምንስ : ይሉት ፥ የአንጀት እከክ : ቢጣባው : ነው?
ደርሶ :ግንፍል ፣ ክብልል የሚያደርገው።

መቼም : ዲያቢሎስ : ሹክ : ብሎት ነው እንጂ.... እንዲህ : ልቡ : የደነደነው።
ልጓሙን : በጥሶ : ያጠጠው .እወነት : ለመገራት : ልቡ : ባይከጅል ነው እንጂ : እውነታው : ሳይገዝፍበት ቀርቶ አደለም።

ሲናውዝ : የዋለው : በከቻ : ስጋውን : ሊያሳርፍ : ከመደቡ : ላይ ዝለታም አካሉን : ጣለው።

ሁፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ,,,, ተመስገን አለ።

ቤቱ : ግድግዳ : ላይ ኢየሱስ : በመስቀል የተቸነከረበትን : ምስል አንጋጦ : እያየ።

ልቡናው : የተሰለበው : ከእሷ ዘንድ ነበርና : የዛለውስ : ያመሰገነውስ : እሷን በማግኘቱም : አደል።

ጌታን : ያለ : መስቀል : እሷን : ያለ : ሀፍረቷ : ሊስላቸው : መቼ ፈቅዶ!!

ወትሮስ የባተሌ ነገር........

🦋ቅዱስ አርዮስ🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋

እንደ ይሁዳ ሳመችኝ.....

እንደ ጌታ ተሸጥኩላት !


🦋ቅዱስ አርዮስ🦋
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌙

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
አምሳለ ሰው አምሳለ በግ

እምበበበበበበ.......
ለተራበ
ለሞላለት ፥ ለተካበ

እሰይ! ለተከፋ ፣ የተደፋ
መጥፎ ሽታ የከረፋ!

ምናምንቲያም ፥ ምናምኒት
የዶሮ ጦስ ሽክርክሪት፣

ሽክርክር.... ሽክርክር....
ደቂቃ ሰአታት
አብረን ስንቆጥር፣
አስትንፋስ በደም ውስጥ
ዘልቆ ሲዘዋወር፣
በአራራይ ዜማ ጮህ ብዬ ስናገር
ፋታም አላቆየኝ ከህመሜ እስክሽር።

ሽክርክር...... ሽክርክር.....
አስብቶ ሸክ አንገት ክርክር
ሽክርክር...... ሽክርክር.....

ከቀኝ ወደግራ ከግራ ወደቀኝ
እንዲያው ቢራራልኝ፣

ቃኘት አየት መለስ
ገረፍ ቀለስ መለስ፣

በአይነ ድምፅ በአራራይ
ላይሰማ በለሆሳስ የምሰቃይ፣

በአርምሞ
ካራ ከአንገት ተቀጣጥሞ፣

ሸክ!
ክርክር!
ብጥስ!
አንገት ቅንጥስ፣

ቀይ ደም ፍስስ
ከአፈር ልውስ፣

የገዳይ አንጀት ሲርስ
ሟች ቅልስልስ።

እምበበበበበበበበበ.....

እምበ ለተራበ


ጠኔ ሆዱን ገዝግዞት በሙክቱ ከጠረቃ በኃላ ማሰብ ጀመረ ሲያብሰለስል ከአስርቱ ትእዛዛት ውስጥ አትግደል የሚለው ትውስ አለው
አትግደል ብሎ መግደል ምን ይሉታል? አይ እግዜር ሞኝ ነህ ልበል....



እርሱም ሚስጥር መቋጠር አይችልም። ብናበላውና ብናጠጣው ካባቱ ዘንድ ያየውን ሁሉ ነገረን (የዘር ያዕቆብ ንግርት ትውስ አለው)

ከልቡ ፈገግ...... አለ

አዬ ...ሆድ አምላኩ¡


ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
Forwarded from Арбитражница dooradas (🌗የግማሽ አለም ጣኦት🌗)
ሞት ሞት ከረፋኝ

ወላዲቴን......

🌓 የግማሽ አለም ጣኦት🌗
ከምኔው !!?

ጠዋት አይደል እማማ ሩቂያ ከእንቅልፌ ቀስቅሰው ሱቅ የላኩኝ?? ከምኔው ባስ ውስጥ "አባባ እዚህ ይቀመጡ " ተባልኩኝ?

- አሁን አጠገቤ አልነበርሽ ? ከምኔው ሄደሽ ተሰወርሽኝ?

- ቡና እያቀራረብሽ አይደል የሳምኩሽ? እያፈርሽ "ሰው ቢመጣስ!" ያልሽኝ ?

- ቅድም አይደል ቤቱን የጠረግሽው ?"ቤቱን ወልዬዋለሁ እስኪደርቅ በረንዳው ላይ ሁን " ያልሽኝ ?/ከምኔው ቤቱን አቧራ ዋጠው ሸረሪት አደራበት !!

- ቅድም ከምሳ በኋላ አይደል ቡና ያፈላሽልኝ ?? ታዲያ ከምኔው ያፋሽከኛል?

- ማታ ከራታችን መልስ አይደል እንዳረገዝሽ የነገርሽኝና አብረን ያለቀስነው ?? ከምኔው ልጄ "እማዬስ" አለችኝ?

- እብዱ ታገል እንኳን ትላንት እራቱን ካበላነው በኋላ አይደል "ውይ የናንተ ፍቅር" ብሎ ሲያደንቅ አሁን በጆሮዬ የሠማሁት?? ከምኔው ፎቶሽ ያለበት የ10ኛ አመት ሙት አመት መታሰቢያን ካርድ ይዞ አየሁት "ወ/ሮ ርብቃ እኚህ ነበሩ" የሚል ያለበት
ትላንት ሌሊት አይደል እንዴ ኑኑዬ ሸንታ አቃጥሏት አልቅሳ ከእንቅልፋችን ባነን ተነስተን ስንሯሯጥ የነበረው???

- ከምኔው ኑኑዬ አድጋልኝ "እማዬስ??" አለችኝ

ከምኔው????....

ከምኔው...

ከምኔው ትዝታ ሆንሽኝ??? አልገባኝም


"(ዘምሽ ያልግዬ)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ሲርሲርታ ፥ የሚንቦለቦል ፥ እቶን ፥ ትንፋሽ። አየር ፥ቀዶ ና ሰንጥቆ ፥ ከብርሃን ፥ ተላግቶ ፥ ወደ ፥ ጨለምተኝነት ሲያዘም ፥ ዘሞም ፥ ጭልጥ ፥ ብሎ ፥ ሲነጉድ እንደገደል ፥ ማሚቱ ፥ ሲያስተጋባ።

ምላሽ ሰጪ ማን ይሆን?

የሲቃ ፥ ናዳ ፥ ሲግተለተል። ራስ ፥ ከራስ ፥ ሲጣረስ ማንስ ወደ ማን ሊጮህ? የጮኸስ ምን አግኝቶ?

ካለ ንገሩ እንጂ? በእግዜር.....

እንጃ እኔስ ሞት ሞት ከረፋኝ
አይኖቼ ደም ሰቀዙብኝ፣

እንጃ የሞት ጠረኑንን
ውል እያለ ማፍገምገሙን፣

አልወደድኩት......አልተመቸኝ

እንጃ.....



ቅዱስ አርዮስ(🦋 )
🌗የግማሽ አለም ጣኦት 🌗

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ሲርሲርታ

ቅዱስ አርዮስ(🦋 )
🌗የግማሽ አለም ጣኦት 🌗

አንባቢ ጆጆ አሌክስ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
////////////////////////
.
.
.
ቅድመ ሰው አዳም ያኔ በብቸኝነት ብርዱን ለመቋቋም መላ ሰዉነቱን ጨርቅ ሊጥልበት ጥጥ ሲባዝት ኩታ ሲጠልፍ ጋቢ አብጅቶ ሲጨርስ ብርዱን ለመደው..!
እኔ ግን በቀዝቃዛ ሐገር በደጋማ ቦታ መልመድን አልሻም የብቸኝነትን እዳ አንዳች ብርሃንን አንዳች ሙቀትን ሚቸር የተዘረጋ እጅሽን ይሄው እጠብቃለሁ አቅፎ እስኪሸሽገኝ ብርዱን ሳልላመድ ቀድሞ እንዲላመደኝ..!

መስከረም 2/2014 ዓ.ም

Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

@kinchebchabi
@kinchebchabi
ምን ነካሽ ?!
©ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣
ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ !
ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣
የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤
ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣
ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣
' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ?

ለምን ነው አካሌ ??....
ሰውነት እርስቱን ፥ ቀን ሲገፋው ማልዶ ፣
በእምነት የካቡት ቃል ይወድቃል ተንዶ ፤
ፍቅርን ባነፁበት ፥ በቀየዱት ቀዬ ፣
እንዴት መልስ ይሆናል ፥ ለየምን እዬዬ?

ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም ተከናንቦሽ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፣
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
' ምን ነካት? ' ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን።

እውነትም ምን ነካሽ ? ፥ ምን አየሽ እርግቤ
የሀሴቴ ደንገል ፥ የነብስ ረሀቤ
ምን ነካሽ? ፥ የኔ ወርቅ
የህይወት ውቧ ሰንደቅ
የናፍቆት ዶሰኛ
የቀን አመለኛ
የአይኔ ስር መሀረብ
የትዝታ ቀለብ
የሳቅሽ መስክ ላይ ፥ መከፋት ሳር ግጦ ፣
አዛኝ አንጀትሽን ያ ጭካኔሽ በልጦ ፤
በአይንሽ ስትገርፊኝ ፣
በኩርፊያሽ ስታስሪኝ ፣
በእምባሽ ልቤ ወልቆ ፥ ዝምታሽ ሲያደቀኝ ፣
' ያቺ ሴት ናት! ' ብሎ ማመኑ ጨነቀኝ።

እናልሽ ገላዬ ፥ አንቺ የነፍሴ ኩሬ
ድክምክም አድርጎ ፥ ፍዝዝ ትክዝ ትክዝ ፣
አዚም በገባሩ ፥ ቀንሽን ሲበርዝ ፤
በጣት ያልጠለቀ ፥ የልባችን ኪዳን ፣
'ምን ነካት? 'ይለኛል ፥ ገፅሽ ሲደማምን ።
ምን ነካሽ በእኔ ሞት??
.
.................... //// ....................
መስከረም ፳፻፲፫ ዓ.ም
@kinchebchabi
@kinchebchabi
ቅንጭብጭብ pinned «ምን ነካሽ ?! ©ሲራክ ወንድሙ @siraaq . ' ጥፋቱ የማን ነው? ' ፥ ብዬ እንዳልጠይቅሽ ፣ ቃልሽን ሳልሰማ ፥ እንባ ነው ሚቀድምሽ ! ምንድነው ገላዬ? ፥ ውስጥሽን በርዞ ፣ የልብሽን ደጀን ፥ መሻከር ወዝውዞ ፤ ቂም አይሉት እልህ ፥ በነፍስሽ ተረግዞ ፣ ዜማሽ ቅኝት አጥቶ ፥ በሀዘን እንጉርጉሮ ፣ ' ተወኝ ! ' የሚያስብልሽ ፥ ለአይን እንኳን አቅሮ ? ለምን ነው አካሌ ??.... ሰውነት እርስቱን…»
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ፀሐይ ስትወጣ.. በዳመና የተሸፈነው ሰማይ ብርሃን ሲጎናፀፍ ከጠባብ ደረቴ ከአጭሩ አንገቴ ስር ከእቅፌ ዉስጥ ሁነሽ በረንዳ ላይ ቁመን አንችን ተጎናፅፌ ጀንበሯን እያየን ቀኑ ይጀምራል ታዲያ ከዚህ በላይ ምንስ ያስደስታል..?!


✍️ Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

@kinchebchabi
@kinchebchabi
በአይን : ቋንቋ : የሆዳችንን : እናወራለን። ቃላት : ልምሻ : ሆነው :ሲድሁ : በአትኩሮት : ለተመለከተን የኔና ፣ እሷ ነገር : እጅን ከአፍ : ማስደፋቱ : አይቀሬ ነው። አንዳንድ : እያዩ : የማያምኑ : ሙዠሌያም : ሰዎች : አውነት : እውነት : ኩነኔ : አይገባቸውምን?

በእሷነቷ : ጎምዥተው : ከስሯ: የሚርመሰመሱት : ጀሌዎቿ : ምኗ እንደሆንኩ : እያወቁ : ምንሽ ነው? ይሏታል

እሷስ ምኗ ሞኛ

አባባኝ አባባኝ
ወይም አላገባኝ!! አለቻቸዋ....

እነሆ : ከዛን ግዜ : ጀምሮ : ነው አሉ ውሽምነት : በነቂስ : የተስፋፋው¡

እሱም : እያየ እንዳላየ : የሚያደርግ ሙዠሌ : አይንና ፣ ልቡን : በልቶት ኑሮ
ዘለአለሙን: ያካል : እስከ : ህቅታው ይፎክታል : በማከክና : በመፎከት መች ፍቅር : ይወጣና።


ምኑ ሞኝ ነው ጃል¡


ቅዱስ አርዮስ
🌗የግማሽ እለም ጣኦት🌗


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
ቀኖቼ...
<unknown>
ቀኖቼ

#ዝብርቅርቅ
(ፀፀተ ጼጥሮስ)

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋 t.me/kinchebchabi 🦋🦋
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
?!?!?!?!?!?!?!?!?!?!?!?!?!?!
.
.
.
እኛ..
ሁለት አንድ አካሎች ፍቅር ያቆራኘን
ሃገር ሞልቶ እያለ ቦታ ያላገኘን
እኛ..
ክንፋችን እረጅም ህልማችን መብረር
ጎጆ ያልቀለስን ተጠግተን ምንኖር
እኛ..
ሁለት አንድ ነብሶች ናፍቆት ያንገላታን
ጊዜ ሞልቶ እያለ ለእፎይታ አፍታ ያጣን
እኛ..
አንድ አካል አንድ ነብስ
ናፍቆት የፍቅር ቁስ
እኛ..

መስከረም 27/2014 ዓ.ም

✍️Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

@kinchebchabi
@kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

#ቃል < #ስሜት!
.
.
እንዲህ ነው እምወዳት
እንዲያ ነው እሚያደርገኝ
ብየ ለማስቀመጥ
ቃላት ባመራርጥ
ስሜት ነው እሚተርፈኝ
ቃል ሁሌ ነው እሚያንሰኝ..

መስከረም 27/2014 ዓ.ም

✍️ Aman😑 YTZ
@amanYTZ23

@kinchebchabi
@kinchebchabi