ቅንጭብጭብ
7.2K subscribers
411 photos
9 videos
4 files
500 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ጭላንጭል ብርሀን : በጨቅላ : አእምሮ : ላይ ተስሎ የቀረ። ስዕሉ በልቡ ውስጥ የተሞነጫጨረ : ተሞነጫጭሮም : በከፊል የደማ ፣ ደምቶም የረጋ : የረጋውም ደም ቀይ ቀለምን ይረጫል። በእስራስ : የሞነጨረውን ስዕል : በደሙ ጠብታ እየነከረ ትላንቱን ይጭራል : ዛሬውን ይተልማል : ነገውን ግን እንጃ : እሱም አያውቀው........

ዘመም : እንዳለ የልጅነት : ገጿን ይስላል አዎ : ክብ ፊት : ፀጉሮቿ የተዘናጠፉ : የአይኗቿ ሽፋሽፍት መስለምለም : የሚያሳሳ : ምጥን ጎራዳ አፍንጫ ያላት
: ከናፍርቶቿ የኖህ : መርከብን ይመስላሉ : ንፍር ውሀውን : ለማምለጥ : ብለው የተከደኑ ሲከፈቱ : ግን ነጭ : ርግብን : ይዘዋል የሷም ከናፍር ሲገለጥ : ነጭ ጥርሷን : ስትፈለቅቀው ድንቡሽቡሽ : ያሉ ጉንጮቿ ውብ የተፈጥሮ ስርጉዷ : ወይም ዲምፕሏ : ጎሎቶ ይታያል።
ያ የልጅነት መልኳ: ናፈቀኝ የምር የምር : የልቤን በልቤ ሰድሬ በፍቅሯ ክታብ ተንሳፈፍኩ

አይ ልጅነት ግን እንደ ዥረት ይነጉዳል
እንደ ብራና :በጭንቀት የተወጠረው የጨቅላ አምሮዬ :እንደምወዳት ለመንገር ከልቤጋ ሙግት ይገጥማል
ምሳ ሰአት ላይ ለ ጓደኛዬ : ሚስጥሩን ብነግረውጭራሽ ሆዱ መቋጠር አቅቶት ጉድ አረገኝ ለምወዳት ልጅ : ጓደኛ ነግሮ አሸማቀቀኝ

9 ሰአት ላይ : ወደ ጓሮ ሄደን ለምወዳት ልጅ ሁሉንም : ነገሩአት
በነገሩም ተቆጣች :ያን ሰአት ጨዋታና ትምህርት : እንጅ ፍቅርን የት : እናውቀውና ገና በ
#3ተኛ ክፍል አይታሰብም ነበር በእውነቱ

የምወዳት ልጅም : በቁጣ ነገ ለ English : አስተማሪያችን እንደምትናገር ነግራኝ ተለያየን አቤት ያን ማታ የልጅነት : ልብ ሲጨነቅ ና ሲርድ አደረ
መቸም መሽቶ : አይቀርም ነጋ
እየፈራሁ ሄድኩኝ ከወትሮ በተለየ :
ሁሉም ፊት ነስቶኛል

ከሰውነት ተራ የዘቀትኩ ያህል ተሰማኝ
#english አስተማሪያችን #መምህርት_አልማዝ ክፍላችን ገብታ ትምህርት : ከመጀመሯ በፊት : ጠርታኝ ከተማሪዎች ፊት : አስቆመችኝ
የሰው : አይን ምንኛ ይከብዳልን?

በትንሽ ሰው : የሚታወቀው የማፍከር : ኩነኔ ይፋ ወጣ ምን ቃል አለኝ ፍቅሬንም : ስሜንም በማጣጤ : ሆድ ቢብሰኝ የልጅነት : እንባ ከአንጀቴ አነባሁ : ያቺን እንባ አፈር እስኪጫነኝ ድረስ : ምረሳት አደለችም : ሁሉም መሳቂያ አርጎኝ ነበር ሳልፈልግ ፌመስ ሆንኩ : ብወዳትም ግዴታ መራቅ : አለብኝ የግድ : መራራዋን ፅዋ : ቢመረኝም በልጅ አንጀቴ ተጋትኩት

የሚገርመው : ነገር ስጠጋት : ትጠጋኛለች ስቀርባት : ትቀርበኛለች በቃሏ : ምሳሌን አሳየችኝ : ለፊደል "ሀ",
ለአሳር "ዋ" ይሉት ነገር።

እሷኮ ያኔ : ፍቅርን አታውቅም : እኔ ድኩም : አካሌን ይዤ : እባዝናለሁ ትምህርት ቤት : በጠዋት ሄጄ ጠብቄያት : ስትዘገይ ስብር እላለው : አረፋፍዳም ቢሆን ስትመጣ : የልጅነት ተስፋዬ : ይለመልማል የነፍስ ምግቤ ናታ።

ግንኮ አሁን ላይ እሷ : የለችም መፈቀሯን አላወቀች ሞኝነቷ.....
ያወቀች ግዜናስ?
ብን ትላለች ልክ እንደድሮው
በጭላንጭል ገፅ ትከሰታለች ልክ እንደ አሁኑ

1... 2.. 3 ... 4 ..16 አመት ሙሉ ስዕሏ በልቤ ላይ እንደተቀረፀ : ነው ንግግሯንና : ሳቋ በፅልመት ምልክ እየተደጋገመ : ያቃጭልብኛል።

አሁን ላይ ጨለማ ውስጥ ነኝ ላምባ ዲናዬ ሰምታኝ ትመጣ ይሆን? እንጃ ....

#ግንኮ_መፈቀሯን_አታውቅም

የተኖረ እየተኖረም ያለ

ሱራፌል ጌትነት🦋
🦋ሱራ ቢራቢሮ🦋
🦋
@surabirabiro🦋


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋
🦋🦋
t.me/kinchebchabi 🦋🦋