ቅንጭብጭብ
7.2K subscribers
412 photos
9 videos
4 files
501 links
ካየሁት 👀 አስገራሚ
ከሠማሁት 👂 መሣጭ
ካነበብኩት 📖 አስተማሪ
ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ

እነሆ #ቅንጫቢ

ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን።

ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።
Download Telegram
ቅንጭብጭብ
እምዬ ምኒሊክ join - @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

### ከድል በኋላ _ የንጉሠ ነገሥቱ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ###

፩.

" ይለቀስለታል ሁሉም በየቤቱ
እንኳን ደህና መጣህ ዳኘው ባለቤቱ"

ዳግማዊ ምኒልክ ከዓድዋ ድል ኋላ ወደ መናገሻ ከተማቸው የተመለሱት ከዓድዋ- እንትጮ- ፈረስ ማይ- በመቀሌ በኩል ሲሆን የኢጣሊያ ወታደር ስንቅ ሰንቀው ጦር አደራጅተው ድጋሚ ቢወጉን በሚል ቅድመ ጥንቃቄ ራስ መንገሻ ዮሐንስን የትግራይ ጠቅላላ ግዛት ላይ ሾመው እና ራስ ወሌ ራስ መንገሻን እንዲያግዙ አዘው፣ አካባቢውም ሕዝቡም በጦርነቱ ሰዓት ስለተጎዳ ለርዳታ ይሆን ዘንድ 30.000 ጥሬ ብር ሰጥተው ነበር።

ንጉሠ ነገሥቱ አዲስ አበባ በገቡበት ቀን በሊቀ መኳስ አባተና በጭፍሮቻቸው ትጋት ቀደም ብለው አዲስ አበባ ደርሰው በደንብ ተጠምደው የሚጠባበቁት መድፎች የደስታ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ከዚህ ሌላ በካህናቱ በኩልም የእንጦጦ ማርያምና የራጉኤል፣የሥላሴና የዑራኤል እንደዚሁም የጊዮርጊስ ካህናት ልብስ ተክህኗቸውን እየለበሱ ቀደም ብለው በሰፊው ጃንሜዳ ተሰብስበው ይጠብቁ ስለነበረ "ወምደረኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ኢጣሊያ" እያሉ በንጉሠ ነገሥቱ ፊት እንዳሸበሸቡ የተክለ ፃዲቅ መኩሪያ " አፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት " የተሰኘው መፅሐፍ ይተርካል። ትርጉምሙ "መሬቷ በኢጣሊያ ደም ታጥባ ፋሲካ (ደስታ) አደረገች" ማለት ነው።

ሊቃውንትም ለንጉሠ ነገሥቱ ለዓድዋ ድል ተስማሚ የሆነ ቅኔ አበርክተው ነበር። የጎጃሙ ሊቅ መምህር ወልደ ሥላሴ ካቀረቧቸው መወድሶች አንዱን እናንሳ

"ሰላም ለዝክረ ስምከ መልእክተ ዂሉ ዘኮነ
ወበግርማሁ ግሩም እንተ አጥፍዓ ጣልያነ
ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ዘኢትዮጵያ መድኅነ
ቀተልኮ ለዓላዊ በምድረ ትግሬ መካነ"

ሲተረጎም...

ምኒሊክ ሆይ ከሁሉ በላይ ለሆነ ስምህ ሰላም እላለሁ፡፡
በሚያስፈራ ግርማው ጣሊያንን ላጠፋ ስምህ ሰላም እላለሁ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት /መዳኛ/ ንጉሠ ነገሥት /የነገሥታት ንጉሥ ምኒሊክ ሆይ፣ በትግሬ ምድር ዓላዊ /ጣልያንን/ ገደልከው፡፡ በባሻ ባዙቅ በታትነህም ወደ በድን ለወጥኸው፡፡

ይቀጥላል...

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ታላቁ የድል በዓላችን ሁለት ቀን ቀርቶታል።

የዓድዋ ጀግኖቻችን በምስል

1. ንጉሥ ሚካኤል
2. ራስ ዳምጠው ከተማ
3. ራስ መንገሻ ዮሐንስ
4. ደጃዝማች ጓንጉል ብሩ

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

### ከዓድዋ ድል በኋላ ሀገር ምን አገኘች? ###

ኢትዮጵያውያን ከዓድዋ ድል በኋላ የኢትዮጵያ አንድነት ተረጋግጦ የሀገር በፅኑ አለት ላይ መገንባት ተከትሎ የተለያዩ ሃገራትም ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶቻቸውን በአዲስ አበባ ተሽቀዳድመው ከፍተዋል።

ከዚህ በኋላ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሙሉ ትኩረታቸውን ያደረጉት ዘመናዊውን የአውሮፓ ስልጣኔ ወደ ሃገራቸው ማስገባትና ህዝቡንም እንዲሠለጥን ማድረግ ነበር። ይህም እምዬ ለስልጣኔ ምን ያህል ቀናኢ እንደነበሩ ያሳያል። የመጀመሪያዎቹ አማካሪዎቻቸውም የአውሮፓ ዜጎች ነበሩ።በተጨማሪም ውጭ ሃገር ሄደው የነጮቹን ስልጣኔ ቀስመው የመጡ ኢትዮጵያውያንን እውቀት በማከል ስልጣኔን ለማስፋፋት ቆርጠው ተነሡ።

በእርግጥ በወቅቱ የነበረው ባህልና ኃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ህዝቡን ለስልጣኔ በሩን ክፍት እንዳያደርግ መንገዱን ቢዘጋም ንጉሡ ግን ወደ ሃገር ያስገቧቸውን ስልጣኔዎች መጀመሪያ ራሳቸው በመሞከር በመቀጠልም መኳንንቱና መሳፍንቱ የእርሳቸውን አርአያ እንዲከተሉ በማድረግ ቀስ በቀስ ወደታችኛው የህብረተሰብ ክፍል እንዲዛመቱ ሆኗል።

ተክለጻዲቅ መኩሪያ አጼ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት በሚለው መጽሃፋቸው ".....ምናልባትም የስልጣኔው ውጥን ከዓድዋ ድል በፊት ቢሆን ኖሮ የገሃድ ተቃዋሚ ባልጠፋ። አሁን ግን "ጣልያንን ያህል ጠላት በቅዱስ ጊዮርጊስ እርዳታ አሸንፈው ከውጭ ጠላት አዳኑን" የሚለው ዝና ከመበርከት ጋር በፍርድ ትክክለኛ ዳኝነታቸው፣ ዘወትር እየተደገሠ በሠፊው ለወታደር ግብር በማብላት ቸርነታቸው፣ ለግላቸው ጥሬ ሀብት ወይም ርስተ ጉልት ልሰብስብ አለማለታቸው በሁሉ ዘንድ ስለታወቀ መወደድን፣ መከበርን ስለሠጣቸው የሚያደርጉት ሁሉ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት አገኘ።" በማለት በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ገልጸውታል።

በዓድዋ ጦርነት ጊዜ የመጓጓዣን አስቸጋሪነት የተመለከቱት እምዬ የምድር ባቡር፣
የመንገድና የመገናኛ መስመር ዝርጋታ አድርገዋል በመቀጠልም የስልክ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም አውቶሞቢል ወደ ሃገራችን እንዲገባ አድርገዋል። የመጀመሪያው ሹፌርም ራሳቸው እምዬ ነበሩ።

አዲስ ሥልጣኔ ቀጥታ ወደ ህዝቡ አልሰረፀም። ይልቅ ስልጣኔውን የሰይጣን ስራ ነው በማለት እምዬን ብዙዎች ተቃውመው ነበር። ኋላ ግን እራሳቸው ዳግማዊ ምኒልክ ሥልጣኔ ሰይጣን እንዳልሆነ በተግባር እያሳዩ ፣ የሚሠጡትም ጥቅም አሳይተው ሌላው ሲያደንቅ የእነርሱ መቃወም ጥቅም እንደሌለው በመረዳት በመጨረሻም የስልጣኔ ስራው ተባባሪ ሆነዋል።

አዝማሪም በወቅቱ እንዲህ ተቀኝቶላቸዋል....

ባቡርም ተጫነ ስልክም ተናገረ
ይኽ በማን ጊዜ ተደርጎ ነበረ
ምኒልክ ነብይ ነው ሆዴ ጠረጠረ
የሐበሻው ንጉሥ ምኒልክ ነቢይ ነህ
ኃላፊውን ትተህ መጪውን ታውቃለህ።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
ቅንጭብጭብ
Photo
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

### ከድል በኋላ _ ዳግማዊ ምኒልክ እና የኢጣልያ ምርኮኞች ###

፪.

በዓድዋ ጦርነት ላይ 13,300 ኢጣሊያኖች ሲሞቱ 700 ተማርከዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጦርነቱን የመሩት 2 ጄኔራሎች አሪሞንዲና ዳቦርሚዳ ሲገደሉ፤ ጄኔራል አልቤርቶኒ ደግሞ ተማርኳል። የእስረኞቹ በብዛት መማረክ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለወደፊት የክርክር አቋም በጣም ረድቷል። ጣልያኖች ቀድሞ እምቢ ያሉትን የውጫሌን ውል ለመሰረዝ የተገደዱትና አዲስ የመጣውን የጄኔራል ባልዲሠራ ጦር መረብ አልፎ እንዳያጠቃ ከመንግሥቱ መሪ ትእዛዝ የተቀበለበት ሰበብ አንዱም በምርኮኞቹ ምክንያት ነው። ለዚህም ነበረ ኢጣሊያ ኢትዮጵያ ነፃ ሀገር መሆኗን ለዓለም መንግሥታት አምና እስክታሳውቅ ድረስ ዳግማዊ ምኒልክ እስረኞቹን እንዲለቁ የቀረበላቸውን ተማፅኖ ያልተቀበሉት።

ሆኖም ምርኮኞቹ ከሹሞቹ ጋር እንክብካቤ ሳይጎድልባቸው ነበር የከረሙት። ይህንንም ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ ዐፄ ምኒልክ እና የኢትዮጵያ አንድነት በተሰኘው መፅሐፋቸው እንዲህ ያስነብባሉ

" የተቀሩት ወታደሮች በያገሩ ተመሩ። ምግቡንም እንደጠገበ አብሉ ብለው ምኒልክ አዘዙ። ዛሬ ከባላገር ጋር በጣም ተስማምቷል። ልብሱንም እንዳገሩ እየተሰፋ ሰጡት። ሹማምንቱም አዲስ አበባ በገባን ጊዜ በየሹማምንቱ ቤት ተመሩ። ሰባት ሰባት ብር ደመወዛቸውን ሰጧቸው። ቀለባቸውን ከጎተራ እያወጣ ሥጋ ሳይቀር መኳንንቱ እየተቀበለ ተጠንቅቆ ይቀልባል..... "


እምዬ በመንግስታት የቀረበላቸውን ተማፅኖ ባይቀበሉም ለተራ ምርኮኛ ወታደር እናት ተማፅኖ ግን ርህራኄ አሳይተዋል። ይህንንም ፕሮፌሰር ራይመንድ ጆናስ " አፄ ምኒልክ እና የዓድዋ ድል " በተሰኘው መፅሀፋቸው ላይ እንዲህ ያስነብቡናል ....

አፄ ምኒልክ የጳጳሱን ምልጃ ባይቀበሉም ለእናቶች ጥያቄ ግን ርኅራኄ አሳይተው ነበር:: ከበርካታ ደብዳቤዎች መካከል አንዲት እናት 'በአቢሲኒያ ለታሠርከው ልጄ አንቶኒዮ' የሚል ፅሑፍ ያለው ፖስታ ወደ ኢትዮጵያ ልከው ነበር:: ፖስታውን የተመለከቱ ጣልያንውያን በአልፍሬድ ኢልግ አማካኝነት ደብዳቤውን ለምኒልክ አደረሱ::

ደብዳቤው ሲነበብ "ውድ ልጄ ዘወትር ወደ ፓምፔይ በመሔድ በቅድስት ፓምፔይ ሐውልት ሥር ተምበርክኬ በመፀለይ ሻማ አበራለሁ:: ወደ አገርህ በሰላም እንድትመለስ እየፀለይኩ ነው::" የሚለው መልዕክት የምኒልክን ልብ ነካው:: ንጉሡም አንቶኒዮን ወደ ቤተመንግስታቸው አስጠርተው የሚከተለውን በመናገር ወደ አገሩ ሸኝተውታል::

"በእናትህ ዕምነት እና ፀሎት ልቤ ተነክቷል:: እናትህ ንፁህ ሴት እንደሆነች ይሰማኛል:: ፀሎቷ ምላሽ እንዲያገኝም እፈልጋለሁ:: ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ነፃ ነህ:: ለጉዞ የሚበቃ ገንዘብ እና በቅሎ ይዘጋጅልሃል:: ከመጀመሪያው መንገደኞች ጋር ትሔዳለህ::"

በመጨረሻም ከዚህ ድልና ምርኮ በኋላ ለኢጣልያ መንግሥት ያለው ምርጫ " እስከ አሸንጌ ሐይቅ ድረስ ያለው አገር ያስፈልገኛል፣ ኢትዮጵያን በበላይ ሆኜ በጠባቂነት ስም እገዛለሁ" የሚለውን ሕልም በግድ ሰርዞ ይንቀው ከነበረው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ራሱን በማስተካከል በእኩልነት እግር ቆሞ ውልና ስምምነት ማድረግ ነበርና ስምምነቱን በጥቅምት 15 ቀን 1989 ዓ.ም ፈፅመው ኢትዮጵያ ነፃ ሀገር መሆኗን ተቀብለው በጦርነቱ ላደረሱት ኪሳራም ከፍለዋል።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
ቅንጭብጭብ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ዓድዋ ማለት #ነፃነት ኢትዮጵያ ማለት #አሸናፊነት Join 👉 @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ዓድዋ ማለት ነፃነት
ኢትዮጵያዊነት ማለት አሸናፊነት ነው።

ለኢትዮጵያውያን ጠላትን ገጥሞ ድል ማድረግ የለመዱት ሙያ ነዉ። በሺህ ዓመታት ታሪካቸዉ ሊወሯቸዉ የመጡትን ጠላቶቻችን ሁሌም ድባቅ እየመቱ ሲመልሱ ኖረዋል። ከታላቁ የዓድዋ ድል ቀደም ብሎ እንኳን በሰሐጢና በዶጋሊ ወራሪን ለወሬ ነጋሪ እንዳይቀር አድርገዉ የአገራቸዉን ነፃነት አስከብረዋል።
.
የዓድዋ የሚለየዉ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸዉን ድንበር ከማስከበርም የላቀ አደራ ተሸክመው መጓዛቸዉ ነዉ። በቅኝ ግዛት ሥር የሚማቅቁ፣ በቆዳ ቀለማቸዉ ብቻ ከሰዉነት ተራ በታች የተደረጉ ፣ የተጨቆኑ ፣ የተገፉ፣በነጭ ወራሪዎች ነፃነታቸዉን በግፍ የተነጠቁ የዓለም ሕዝቦችን አደራ ነበር ኢትዮጵያዊን አባቶቻችን በጫንቃቸዉ ተሸክመዉ ነበር ወደ ዓድዋ ተራሮች የዘመቱት።
ድል ቢያደርጉ "ነፃነትን ማስከበር" ብቻ ተብሎ የማይተዉ፤ ድል ቢሆኑ "የኢትዮጵያ ሽንፈት" ብቻ ተብሎ የማይጠቀስ ነበር ዓድዋ።
"አደራ" መብላት የእርም ሥጋ መብላት ለሚለዉ ኢትዮጵያውያን ድሉ የግድ ነበር። ድል አድርጎ፡
የዓለምን ታሪክ ለመለወጥ፣ የሰዉ ልጅ ክቡር እንደሆነ ለማሣየት፣ ሰዉ መሆን ክቡር እንደሆነ ለማስተማር፤ የተጣለበትን የግፉዓን አደራ ለመወጣት ነበር ሙቀትና ቁር፣ ሜዳና ዱር፣ አፈርና ጠጠር ሳይበግረዉ ፣ ረሃብና ጥማቱ፣ በሽታና ሞቱ ሳያንበረክከዉ ሆ! ብሎ ወደ ዓደዋ ዘመተ።
በሞቱ ሰዉን ሊያድን ፣ በሞቱ ሰዉን ሊያከብር... በጀግንነት በክብር ተዋጋ። ተዋደቀ። አደራ የማይበላዉ ኢትዮጵያዊ ዓድዋ ላይ አደራዉን ተወጣ።
በጀግንነቱና በድሉ
- የቅኝ ግዛት መሠረትን አናወጠ ።
- የሠዉ ልጅ ክቡር መሆንን አረጋገጠ ።
-በቅኝ ግዛትና ጭቆና ሥር አንቀላፍተዉ የነበሩ ግፉዓንን ዐይን ገለጠ።
-የነጭ የበላይነት እሳቤን ከሥሩ ገለባበጠ።
- የዓለም ታሪክ አካሄድ ተለወጠ።
......
የሰዉ ልጅ ክቡር
ሰዉ መሆን ክቡር
ሰዉ ሞቷል ሰዉ ሊያድን
በጀግንነት በክብር

ክብር ለጦሩ መሪ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ!

ክብር በሞታቸው ነፃነት ላጎናፀፉን አያቶቻችን!


#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

#### ምኒሊክ !!!!!!!!!!!!!!!!!! ####
(ጃኖ መንግስቱ ዘገየ )

ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባይተኩስ ናስማሰር ፤ ባያነሳ ሞይዘር ፤
ባንዳና ሰላቶ ፤
ፓስታ እያስቀቀለ፤ ተጫውቶብን ነበር ።

ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል ነፍጠኛ ፤
ተሸከም እያለ ፤
ተጫውቶብን ነበር ባንዳና ጎጠኛ ።

ምኒሊክ ተወልዶ ባይባል እምዬ ፤
መይሳው ጃሎ ሲል ባይመጣ ገብርዬ ፤
አገር ሞታ ነበር ኧረ እናንተ ሆዬ ።

ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ዘገር ፤
ሹምባሻና ባንዳ፤
እንደዝክር ቂጣ፤
ቁርስርስ አድርጎ በጨረሰን ነበር ።

ምኒሊክ ተወልዶ ፤
ባድዋ ሰማይ ላይ ፤
ደመቅመቅ ብላ ፤ ባትወጣ ጠሃይ ፤
ጦቢያን ያህል ሃገር ፤ ይገኝ ነበር ወይ? ???

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

ሠላም ውዶች በእምነት ነኝ...

የዓድዋ ድል ለኔ፦ ማንነት፣ ነፃነት፣ አልበገር ባይነት፤ አሸናፊነት ማለት ነው።
ቀና ብዬ በክብር እና በኩራት እንድሄድ የሚያደርገኝ ክቡር ገድል ነው!!!

መላው የጥቁር ሕዝብ በባርነት ቀንበር ሥር ወድቆ ሲማቅቅ፤ የሰውነት ማዕረግ ተዋርዶ፣ ነፃነት ተገፎ፤ ተስፋ ጨልሞ በነበረበት በዚያ ዘመን ነፃነትን ሊያበስር፣ ሰውነትን ሊያከብር ፣ ተስፋን ሊያለመልም የተለኮሰ የድል ችቦ ነዉ ዓድዋ ።

የዓድዋ ድል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘር ሳይቋጠር ሃይማኖት ሳይለይ ንጉሡን ምኒልክን ተከትሎ ለአገሩ ነፃነት፣ ለድንበሩ ክብር ደሙን ያፈሰሰበት፣ ሕይወቱን የገበረበት፣ አጥንቱን የከሰከሰበት...
የጨለመውን የጥቁር ሕዝብ ሰማይ የነፃነት ጮራ የፈነጠቀበት... የማንነት ሚዛን የተለካበት የመስዋዕትነት አውድ ነው።

ዓድዋ ኢትዮጵያ በሰው ልጆች የነፃነት ትግል ታሪክ ላይ በትልቁ ማኅተሟን ያተመችበት፤ ለመላው ጥቁር ሕዝብና የነፃነት ታጋዮች የማንነት፣ የነፃነት፣ የአርበኝነት፣ የጀግንነት፣ የአልበገር ባይነት ምሳሌ የሆነችበት ደማቅ ድል ነው!!!

(ለእናንተስ? ዓድዋ ለኔ...
ሃሳባችሁን በ @bcrazykid ላኩልን)

#ዓድዋ 123
#የኢትዮጵያ_ድል
#የጥቁር_ሕዝብ_ኩራት

💚💛❤️
#Ethiopia
#VictoryOfAdwa

👉 @roviben @kinchebchabi
ቅንጭብጭብ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ የአድዋ ድል አከባበር join 👉 @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

### ዓድዋ ድል በዓል አከባበር ###

፩.

"ዐፄ ምኒልክ የአስተዳደር ብቃታቸዉ የላቀ ፤ በባሕሪያቸውም ልባቸው ከተንኮል፣ ከቅናትና ከምቀኝነት ንፁሕ ስለሆነ ሰው ይዋጣላቸዋል። አለቆችን በሙያና ባገልግሎት መመረጥ፣ የተመረጡትንም ያለ አድልዎ በሹመት፣ በሽልማትና በማዕረግ ማሳደግ ልማዳቸው ነበር። ታላላቆቹ ቢሞቱ የሚተኩ ታላላቅ ባለ ሥልጣኖች በፍፁም አይገዳቸውም። በየሥፍራው የሚተኩ የጎደለውን የሚሞሉ በየክፍሉ በየቅርንጫፉ በቁም ነገር በታማኝነት የሚያገለግሉ ግርማ ሞገስ የተዋሐዳቸው አገር አቀፍ ባለሥልጣኖች የሞሉበት ዘመን ነበር። የሠለጠነው የአውሮፓ ኃይል በጦርነት የተንበረከከውና ኢትዮጵያ የጥንቱን ስፋቷንና ገናንነትዋን መልሳ የተቀዳጀችው እነዚህንና ሌሎች መሰሎቻቸው በሰጡት አመራር ኅብረትና ታዛዥነት ነው።" በሚል ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ አፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት በተሰኘው መፅሀፋቸው ይተርካሉ።

ዳግማዊ ምኒልክ በዚሁ የአመራር ጥበባቸውና ስልት አዋቂነታቸው ዓድዋ ላይ ኢጣልያን ድል ካደረጉ እና የውጫሌውን ውል የአዲስ አበባ ውል በሚል በሚታወቀው ውል አሽረው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ኢጣሊያ ከተቀበለች ኋላ ፊታቸውን ወደ ሥልጣኔና የውጭ ግንኙነት ላይ አተኩረው እስከሰባተኛ ዓመት ድረስ ዓድዋን አላከበሩም ነበር።

በዓሉን በ1895 ዓ.ም በአዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ሲዘጋጁ አዲስ አበባ ላሉትም፣ ከየአውራጃው ለተሰበሰቡትም ለየመኳንንቶቻቸው መልዕክት አስተላልፈው ነበር። መልዕክቱ ሰባተኛ አመት ላይ ለምን እንደተከበረ የሚያመላክት ነው። መልዕክቱም እንዲህ ይላል...

" ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባውና እኔም ይኸንን በዓል እንዲህ አድርጌ ማክበሬ እናንተንም ማድከሜ እግዚአብሔር በቸርነቱ ሰባት ዓመት ሙሉ በዕረፍትና በጤና ስላኖረን ስለዚህ ነገር ማክበር ይገባል ብዬ ነው። እንጂ ለጥጋብና ለትዕቢት ሠራዊት በዛ ነፍጥ ( የጦር መሳሪያ) በረከተ ለማለት አይደለም። ነገር ግን በዚህ በየሥራው ነገር በእንጨት፣ በድንጋይ የማደክማችሁን አትመልከቱ
( ለሕንፃ፣ ለመንገድ፣ ለልማት ሥራ በማስጋዝና አቅርቡ በማለት)። ይልቁንም እኔን ስታጡ (ስሞት) ብርቱ ኃዘን ያገኛችኋል። አሁንም ወንድሞቼ ወዳጆቼ የማናውቀው መከራ እንዳያገኘን እንዳይመጣብን በዚህ ነገር ደስ አይበላችሁ። ( በዚህ ሰልፍ በመመካት ልባችሁ አይታበይ)። እግዚአብሔር እንዳይለየን አብሮ እንዲያስበን እኔም አዝናለሁ፤ እናንተም እዘኑ" ብለዋል

ከዚህ መልዕክት እንደምንረዳዉ እምዬ ምኒልክ የዓድዋን ድል በዓል ለማከበር የተነሱበት ዋነኛ ዓላማ በተገኘው ሰላምና እረፍት ምስጋና ማቅረቢያ እንጂ በድሉ ታብየው ደስታ ለማድረግ አለመሆኑን ነው። ይህንንም ከድሉ ኋላ ለሙሴ ሽፍኔ "በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ። እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግኋቸው ብዬ ደስ አይለኝም" ሲሉ የፃፉላቸው ደብዳቤ በድሉ አለመኩራራታቸዉን እንደዉም በጦርነቱ በሞቱት ሰዎች ምክንያት ምን ያህል ልባቸዉ በሐዘን እንደተመታ ማሣያ ሌላ ማስረጃ ነዉ።

ይቀጥላል...

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
ቅንጭብጭብ
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ የአድዋ ድል በዓል አከባበር join 👉 @kinchebchabi
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

### የዓድዋ ድል አከባበር ###

፪.

የንጉሠ ነገሥቱን የበዓል ጥሪ ተከትሎ መኳንንቱ፣ የየክፍለ ሀገራቱ ገዢ፣ ወጣቱ፣ ሽማግሌው ከነቤተሰቡ ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ ለብሶ አዲስ አበባ ላይ የበዓሉ ማክበሪያ ቦታ ሆኖ በተመረጠው ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ባለ ሰፊ ሜዳ ላይ ተገኘ። ይህ ሁሉ አጀብ ለጦር አለቆቹ እና ለንጉሠ ነገሥቱ ምስጋና ለማቅረብ ብሎም ንጉሡን ለማየት ነበር። ህዝቡ ከተሰበሰበ ኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀን 6 ላይ ወደ ቦታው ደርሱ። ንጉሡ ሲደርሱ የነበረውን ሁኔታ ሥርገው ሐብለ ሥላሴ በመፅሀፋቸው እንዲህ ይተርካሉ....

" ከተማይቱን ከሚከቧት ብዙ ኮረብታዎች ጫፍ ላይ ድንገት የመድፍ ጩኸት አጓራ። እንደገና ተደጋግሞ ነጋሪቱ ተጎሰመ፣ እምቢልታው ተነፋ። የነጋሪቱ ምትና የእምቢልታው ቃና የንጉሠ ነገሥቱን መድረስ ለማብሰር ነበር። በመጨረሻም ከኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት የመጡ ልዑላን በእነርሱ መካከል ከሁሉኝ ላቅ ብሎ የሚታየው በአንድ የተንቆጠቆጠ የተገራ ነጭ ፈረስ ላይ ንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ ምኒልክ ነበር።

ሰልፉ በዚያ ሰፊ አደባባይ ላይ መስመሩን ይዞ ቆመ። ሰው ሁሉ ከከብቱ ወረደ። ንጉሠ ነገሥቱ ብቻ ከፈረስ ጀርባ ላይ እንደተቀመጠ ቀረ። ነጋሪቱና እምቢልታው እንደገና አጓራ። ያ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለው ሕዝብ የጌታውንና የመሪውን ንግግር ለመስማት ቋምጧል። ትንሽ እንኳ ትንፋሽ ርጭ ባላለበት ፀጥታ ንጉሠ ነገሥቱ ንግግር ጀመረ። በምርጥና በሰመሩ ቃላት የጦር አበጋዞቹን፣ ጀግናውንና በእውነትም መመስገን የሚገባውን ሠራዊት አሞገሳቸው። ምኒልክ ለተሰበሰበው ሕዝብ ትልቁንና ብቸኛ የሆነውን ድል የተወጣውን የዓድዋውን ጦርነት ሀለፀ። እስካሁን ድረስ አንድ አፍሪቃ ሕዝብ አንድን የአውሮጳ ኃይል ማሸነፍ እንዳልቻለ ምኒልክ አወሳ። ....

መፅሐፉ በመቀጠልም ዳግማዊ ምኒልክ ስለ ጦር አበጋዞቻቸውና አጠቃላይ ስለጦርነቱ የተናገሩትን እንዲህ ያስነብበናል ...

" የጦር አበጋዞቼና ሠራዊቴ ትልቅ ድርጊት ነው የፈጸሙት። ትግሉ አቻ አልነበረም። ስለዚህ ነው ለዚህ ድል ይበልጥ ዋጋ የምንሰጠው። የእኛ ጦረኞች ከጥንት እንደቆየን ይበልጦቹ ጦር፣ ጎራዴ፣ ቀስትና ፍላፃ ነበር የታጠቁት። ለማንኛውም መከላከያቸው ጋሻ ነበር። ጠላት የሚዋጋበት ዘመናዊ የአውሮጳ መሳሪያ ነበር። በጠመንጃ በሩቅ የእኛን ሰራዊት አደባየው። በመድፍ ጥይት ሰፈራችንን በታተነው። ሆኖም ይሄን ሁሉ የመሳሪያ ዶፍ ምንም አይነት መከላከያ የሌለውን የጀግኖችን ድፍረትና ኃይል አላዳከመውም። የሠራዊታችንን ጀግንነት በሚገባ ተቋቋመው። በመጨረሻም የሚመሰገንና ብቸኛ የሆነ ድል ለእኛ ሆነ"...

በዓሉ በደማቅ ትርኢትና አጀብ ማለፉንና 12 ሰኣት ላይ ዳግማዊ ምኒልክ ወደ እልፍኛቸው እንደተመለሱ ፀሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ፅፈዋል። አክለውም ይህን ሁሉ ባለ አስፈሪ ግርማ ትርኢት ለሕዝባቸው ማሳየታቸው " እግዚአብሔር አያምጣብን እንጂ ሌላም ጠላት ቢመጣ እንደዚህ አድርጌ እረዳችኋለሁ፣ አጠቃላችኋለው" ብለው ለሕዝባቸው ለማስረዳት መሆኑን ይገልፃሉ።

ይኸው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዓሉ ከትውልድ ትውልድ አንዴም እየደበዘዘ፣ ሌላ ጊዜም እየፈካ እስካሁን እየተከበረ አለ። ወደፊትም ሲከበር ይኖራል።

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@kinchebchabi @kinchebchabi
Forwarded from Ibex Events & Hiking
ወደ ቡልጋ - የለኝ ገደል የምናደርገው ጉዞ 4 ቀናት ብቻ ቀሩት

እሁድ - ሕዳር 18

ክፍያው ምንን ያጠቃልላል?
የቁርስ፣ ምሳ፣ የታሸገ ውኃ፣ የመግቢያ ክፍያዎች፣ የአስጎብኚ፣ የፎቶግራፍ የሻይ ቡና መጠጥ... ክፍያዎችን በሙሉ

በዚህ ጉዞ ለመሳተፍ እርግጠኛ ሲሆኑ በ telegram @ibexet , @yoti27 "አለሁ" ይበሉ ወይም 0945965456 / 0928412796 ይደውሉልን።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን በውስጥ መስመር የምንልክ ይሆናል

በ Telegram t.me/ibexevents
በ facebook m./facebook.com/ibexevent ይቀላቀሉን።

መልካም ቀን!

ሰላም ለኢትዮጽያ! 💚💛
#Ethiopia #LandOfOrigins #hikinglovers #VisitAmhara #Bulga #Travel
ቅንጭብጭብ
ከ112 ዓመታት በፊት በዛሬው ዕለት የሰጠመችው ግዙፏ የታይታኒክ መርከብ ታይታን (ታይታኒክ) - Unsinkable Ship ...
#Ethiopia | ታይታኒክ የተገነባችው ሰሜን አይርላንድ ውስጥ “White Star Line” በተባለ ካምፓኒ ነው፡፡

ታይታኒክ 269 ሜትር ርዝመት፣ 28 ሜትር ስፋት፣ 32 ሜትር ቁመት እንዲሁም ከ47 ሚሊዮን ኪ.ግራም በላይ ክብደት ነበራት፡፡

ታይታኒክ የተሰራችው በ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ እ.አ.አ በ1997 ለእይታ የበቃው የጀምስ ካሜሮን ፊልም ታይታኒክ 200 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶበታል፡፡

ታይታኒክ በቀን 600 ሺህ ኪ.ግራም ከሰል ትጠቀም ነበር፡፡

ታይታኒክ ከእንግሊዝ ሳውዝ ሀምፕተን ከተማ ወደ ኒውዮርክ ጉዞ የጀመረችው እ.አ.አ ሚያዚያ 10 ቀን 1912 ነው፡፡

መርከቧ ለ4 ቀናት የተሳካ ጉዞ ካደረገች በኃላ 30 ሜትር ቁመት ካለው የበረዶ ግግር ጋር የተላተመችው ሚያዚያ 14 ቀን 1912 ከሌሊቱ 5 ሰዓት ከ40 አካባቢ ነው፡፡ መርከቧ ሙሉ በሙሉ ለመስጠም 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ፈጅቶባታል፡፡

በአደጋው ወቅት ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች መርከቧ ውስጥ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በህይወት የተረፉት 706 ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

ታይታኒክ ውስጥ 20 ህይወት አድን ጀልባዎች ነበሩ፡፡ ጀልባዎቹ እያንዳንዳቸው እስከ 64 ሰው የመያዝ አቅም ቢኖራቸውም መርከቧ ውስጥ በተፈጠረው ትርምስ ጥቂት ሰዎችን ብቻ ነበር እየያዙ የወረዱት፡፡

በታይታኒክ አደጋ የሞቱት አብዛኞቹ ወንዶች ናቸው፡፡ ይህም የሆነው ወደ ማምለጫ ጀልባዎች እንዲገቡ ቅድሚያ ለሴቶች እና ለህጻናት በመሰጠቱ ነው፡፡

ከሟቾች ውስጥ 26ቱ ጫጉላ ላይ የነበሩ ጥንዶች ናቸው፡፡

የታይታኒክ የሙዚቃ ባንድ አባላት መርከቧ እስክትሰጥም ድረስ ሙዚቃ መጫወት አላቆሙም ነበር፡፡

መርከቧ ውስጥ የነበሩ አንድ ቄስ ሁለት ጊዜ ወደ ህይወት አድን ጀልባዎች እንዲገቡ ተጠይቀው እሺ ሳይሉ ቀርተዋል፡፡ ቄሱ እስኪሰጥሙ ድረስ ከሞት ጋር የተፋጠጡ ክርስቲያኖችን ኑዛዜ (ንስሐ) ሲሰሙ እና ስርየት ሲለምኑ ነበር፡፡
የታይታኒክ ዋና ካፒቴን ኤድዋርድ ስሚዝ ለመርከቧ ሰራተኞች ያስተላለፉት የመጨረሻ መልዕክት እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ወድ ሰራተኞች የሚጠበቅባችሁን ሁሉ አድርጋችሁል፡፡ ከዚህ በላይ እንድታደርጉ የምጠይቃችሁ ምንም ነገር የለም፡፡ የባህር ላይ ህግን ታውቃላችሁ፡፡ አሁን ሁሉም ሰው ለራሱ ነው፡፡ ፈጣሪ ይባርካችሁ”፡፡

ታይታኒክ ከባህር በታች በ3 ሺህ 840 ሜትር ጥልቀት ነው የሰጠመችው፡፡

ታይታኒክ ከመስጠሟ ከ14 ዓመታት በፊት በ1898 ሞርጋን ሮበርትሰን የተባለ እውቅ ደራሲ ‘ሊሰጥም የማይችለው መርከብ (unsinkable ship) ከበረዶ ግግር ጋር ተላትሞ ሰጠመ’ የሚል ጭብጥ ያለው መጽሐፍ ለንባብ አብቅቶ ነበር፡፡ ደራሲው በምናብ ለፈጠራት መርከብ የሰጣት መጠሪያም “ታይታን” የሚል ነበር፡፡

የታይታኒክ መርከብ ፍርስራሽ የተገኘው አደጋው ከደረሰ ከ73 ዓመታት በኋላ ዶ/ር ሮበርት ባላርድ በተባለ አሜሪካዊ የስነ ውቅያኖስ ተመራማሪ ነበር፡፡ ጊዜውም እ.አ.አ 1985 ዓ.ም ነበር፡፡

የታይታኒክ ፊልም መሪ ተዋናይት ኬት ዊንስሌት “ማይ ኸርት ዊል ጎ ኦን” የተሰኘውን የፊልሙን ማጀቢያ ሙዚቃ እንደምትጠላው ተናግራ ነበር፡፡ ኬት “ሙዚቃውን ስሰማው ሊያስመልሰኝ ይደርሳል“ ነበር ያለችው፡፡

ታይታኒክ ፊልም በ11 ዘርፎች ኦስካር (አካዳሚ አዋርድ) አሸንፏል፡፡ ከሽልማቶቹ ውስጥ ግን አንዱም በተውኔት ዘርፍ የተገኘ አይደለም፡፡ የፊልሙ መሪ ተዋናዮች ኬት ዊንስሌት እና ሊዮናርዶ ዲ ካፔሪዮ በምርጥ ትወና አልተሸለሙም፡፡

© ኢዮብ መንግስቱ - በአብሮነት እንቆይ
@kinchebchabi