ንቂ ኢትዮጵያ
541 subscribers
261 photos
83 videos
32 files
179 links
እዚ ገፅ ላይ የምናነሳቸዉ ነገሮች

፩ ስለ ኢሉሚናቲ
፪ ስለ 5G
፫ ኢትዮጵያ ላይ ስለሚደረጉ ሴራዎች
፬ ስለ GMO
፭ ስለ ግብረሰዶማዊነት
፮ ስለ ማይክሮ ቺፕ

1% CONTROL THE WORLD
4% ARE SELL OUT PUPPETS
90% ARE ASLEEP
5% KNOW AND ARE TRYING
TO WAKE UP THE 90%
THE 1% DONT WANT THE
5% WAKING UP THE 90%
Download Telegram
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
የኔ "ሰው"ናትናኤል ዲበና

(በታመነ መንግስቴ)

ልጁ በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ የሕትመትና በይነ መረብ(Print and Web) ጋዜጠኝነትን ይማራል።

መቼስ አስተዋይነት፣አድማጭነት፣ቅንነት እና ርቱዕ አንደበት የእሱ ናቸው።

ከናቲነት ጋር አብሮ መስራት ሲመቸኝ!አይኮሰኩስም።ጥንቅቅ ያለ ቀጫጫ ነው😁

አሁን Etv ላይ"ነገን ዛሬ"በሚሰኝ የወጣቶች ዝግጅት አፍታ እንግዳ ሆኖ አየሁት።ደስስስ አለኝ።

በዕየለቱ ሳይረግጣት በማይውላት "አረንጓዴ ሰው ይገኝባታል" በሚባልላት አራት ኪሎ ሲኳትን ምስል ቀራጩ አንስቶታል።

ሌላዋ ናቲየ የሚወዳት ቦታ ስድስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጋ ያለችዋ ፒፕሲ የጋዜጣ እና መፅሐፍ ማንበቢያ እንዲሁም መሸጫ ጓዳ ናት።እዚያ ናቲነትን መፈለግ አያከስርም።

ይሄ በብዙኃን መገናኛ ዕውቀቱ(ስለ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንና ባለሙያዎቻቸው ከዊኪፒዲያ በላይ አምኘ የምጠይቀውና የጠየኩትን የሚሰጠኝ ትጉህ ተወዳጀ ነው)የሚያስደምመኝ የዘመኔ ስጦታ በቃለ መጠይቁ አፍታ፦

"በሚዲያ ውስጥ ገብቶ እንደ ጥላ የሚያልፍ ጋዜጠኛ መሆን አልፈልግም"ብሏል።

በአስር ጣቴ ፈርሜ አምነዋለሁ።ቸር ይግጠመው!


የቀጫጫውን የEtv ቆይታ ለመታደም https://www.facebook.com/100003435445465/posts/3127578597366624/ ላይ ግቡ።

ወደ መሃል አለላችሁ!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ወደ ቤቴ ኑ!

ታመነ መንግስቴ ውቤ ነኝ።

ጊዜ፣ቦታ እና ሁኔታ ተገጣጥመው የምወደውን ሞያ ጋዜጠኝነትን ወርቅ ከሸለምኩት በሗላ ከጀግኖቹ የአገሬ ልጆች ጋር በጦር ግንባር ተገኝቻለሁ።

ይህ ጦርነት ከአስር ዓመታት በሗላ " አደይ መቀሌ"፣"እናቴ አዲስ አበባ" የሚሉ ዘፈኖች እንደሚደመጡበት ሃቅ ነው።

እስከዚያ ግን የሞት አቃቂር እያየን አለን።

ለሁሉም ከሸዋ ጣርማ በር እስከ ወሎ ጫፍ ዋጃ_ጥሙጋ፣ከሰቲት ሁመራዋ ማይጋባ እስከ አዲ አርቃይ ተጎራባች ጨው በር በጀማሪ ጋዜጠኛ ዐይን ያየሁትን፣የሰማሁትን፣ቀጥሎ በሚመጡ ጊዚያት በፈጠርኳቸው ግንኙነቶች የምፈትሻቸውን ሃቆች ለመቋደስ ወደ #እዚህ ቤት https://t.me/Gazetaw ብቅ በሉ።

በተለይ በፌስቡክ በኩል የጓደኝነት ጥያቄያችሁን ያልመለስኩላችሁ ወዳጆቸ ቤቴን ብታንኳኳት በሩስያ ሰራሹ ቴሌግራም ጥዑም ሃሳቦችን እንጋራለን።


እናም እዚህ ቤት https://t.me/Gazetaw ብላችሁ አንኳኩ።ክፍት ናት።

ታመነ መንግስቴ ከወሎ ግንባር!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
መርሳ እና ወልድያ ነፃ የወጡ ዕለት

(ከጦር ግንባር ዘጋቢው ታመነ መንግስቴ ማስታወሻ የተቀነጨበ)

ጋዜጠኝነትን እንደ እንጀራ ከቆጠርከው የተፈጨ አሸዋ የተቀላቀለበት እንጀራ ነው።እየጣመህ ይሰብርሃል።ሞያው ፍፁማዊ ነፃነት ይፈልጋል።በዚያው ልክ የባለሞያው ፍፁማዊ ምክንያታዊነት ፍቱን ነው።
እንዲህ ከሆነ ጋዜጠኝነት በፍቅር የሚያሰክር ሸሞንሟና ሞያ ቢሰኝ አልበዛበትም።

ዛሬ ሲነጋጋ ወደ ውጫሌ፣ውርጌሳ እና መርሳ ሄደን እኒያን ወሎየዎች ማየት እንዳለብን ሃሳብ አመጣሁ።ብቸኛው በእኔ ውሳኔ የሆነ ነገር ነው።ላለፉት 14 ቀናት የምሰራው ሁሉ በአለቆቸ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር።

ትናንት ማታ አሳስቄ ተሳካልኝ...!

ደሴ የግዷን ከ38 ቀናት የእብዱ ውሻ ንክሻ ዱካኳ እየነቃች ነው።የሚያሳዝነው ቀድማ ከከፈተቻቸው የአገልግሎት ዘርፎቿ ጫት ቤትና መጠጥ ቤት ይፈጥናሉ።"ዐለም ለምኔ"ብለው የሚቅሙት ማኘክ ጀምረዋል።ከሳምንት በፊት ደሴ _ፒያሳ ያገኘሗቸው የዕድሜ ባለሃብት"የአሁኑ ትውልድ ጫትን እንደ ባህል አደረገው"እያሉ ሲቆጩ ነበር።ብዙ ወሎየዎች በጦርነቱ መደፈራቸውን ይናገሩና ሲጨርሱ"ጫቱን ትታችሁ ለሕልውናችሁ ታገሉ"ይላሉ።

ደሴን ትተናት ወደ ሐይቅ ነዳን።ሐይቅን አልፈናት ሚሌ ወንዝ ላይ ነን።እዚህ ሐይቅን መዲናው ያደረገው የተሁለደሬ ወረዳ ያልቅና ባለ ቅኝቱ አምባሰል ይጀምራል።አምባሰል ወሎየዎቹን በምልዓት ከሚወክሉ አካባቢዎች አንዱ ነው።ዋና ከተማው ያው _ውጫሌ ናት።ውጫሌ በኢትዮጵያ ታሪክ ያላት ቦታ ከሰማይ በታች የሚገኝ ተዐምር ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክ ሀሁ የማይገባው ሁሉ አድዋን ያውቀዋል።አድዋ ጓደኛየ ሳሙኤል ታዴ"የሰው ልጆች ድል"የሚለውን የጥቁር ሕዝብ ጀብዱ የምትመሰክር ምድር ናት።እናም ስለ አድዋ ጦርነት፣ድልና ነፃነት ለማውጋት የ1881ን(?) የውጫሌ ውል መንተራስ ግድ ነው።

ያኔ የሸዋው ንጉስ ዳግማዊ ምኒልክ ጣሊያን ወደ መሐል አገር እየገሰገሰ መሆኑን ተረዱ።እንደገባቸው ልጓም ማስያዣ አንድ ውል መፈራረም ነበረባቸው።ይህም ይሆን ዘንድ ከጊዜው የኢጣሊያ መንግስት ተላላኪ ፔትሮ አንቶሎኒ ጋር እዚህ አለንበት ቀየ አካባቢ "ይስማ ንጉስ"ተብሎ ተፈራረሙ።

የውጫሌ ውል ትርጉመ ብዙ ነው።በተለይ አንቀፅ ሶስት እና አንቀፅ 17 ከዚያ ወዲህ በተፈጠረችው ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ነጭና ጥቁር ነጥብ አሳርፈዋል።

አንቀፅ ሶስት የአሁኗን ኤርትራ የዚያን ጊዜዋን ሃማሴን ከኢትዮጵያ አካል ላይ የቆረጠ ቃል አለበት ተብሎ ይታመናል።እኔ እና ትውልዴ የተማርንበት የ10ኛ ብሎም 12ኛ ክፍል መፅሐፍ እዚህ ጉዳይ ላይ በጉልህ ያሰምራል።

አንቀፅ 17ን እንኳን እኛ ሰው በሙሉ ያውቀዋል።ይህ አንቀፅ የጫረው እሳት ተቀጣጥሎ ጥቁር ሕዝቦችን በተለየ፤የሰው ልጆችን ባጠቃላይ ባለድል አድርጓል።

ለሁሉም ለሁሉም ከሌላው ጣሊያን ጋር እየተዋጋን አሁን ውጫሌ ነን።

በግራ በኩል "ውጫሌ 17"የሚሰኝ ትምህርት ቤት መግቢያው ይታየኛል።አደነቅሗቸው።ታሪክን እንዲህ ማስታወስ መቸስ ልባምነት ነው።ለነገሩ መኪናችንን የሚዘውራት ኃይሌም"...ውጫሌ እኮ ጣይቱ እምቢ ያለችበት ቦታ ነው"ሲለን ነበር።ሃቅ አለው።እቴጌይቱ ያንን መናኛ ፈረንጅ"...እኔ ሴት ነኝ።ጦርነት አልወድም።ግን የአገሬን በጠላት እጅ መውደቅ ከማይ ጦርነትን እመርጣለሁ።ከፈለግህ ጦርነቱን የዛሬ ሳምንት አድርገው።እጠብቅሃለሁ"ያሉት እዚህ ነበር።

የዛሬ ረፋዷ ውጫሌ ከእብዱ ውሻ ወያኔ እጅ ነፃ ሆናለች።እስከ ትናንት ታህሳስ 8 ቀን 2014 ዓ.ም እዚህ እንደነበሩ ያገኘናቸው ባላገሮች ነገሩን።መቸስ በመንደሩ ያልተተኮሰ የጦር መሳሪያ የለም።ቀየው ደቋል።ሰዎቹ ደንግጠዋል።ዝምታ ላይ ናቸው።

እኛ በመገስገስ ላይ ነን።የወሎ ምድር የተራራ እና ሸንተረር አወደ ርዕይ ይመስላል።ልቅረፅ ቢል የመቅረፀ ምስል(ካሜራ) ባለሞያ የሚያደክሙ ተራሮች ይታያሉ።ውርጌሳን እንዳለፍን ወደ ዝነኛዋ ኒኒ በር ተጠጋን።

ኒኒ በርን ደሴ ሆኘ ከራሴ ስም በላይ ደጋግሜ ስሟን አድምጫለሁ።ሲበዛ ስልታዊ ቦታ ናት።ይህችን ማነቂያ የያዘ ተዋጊ ልዩ ብልሃት አያስፈልገውም።ተራራ ሸንተረሩ ጠላትን ተዋግቶ አድክሞ ያቀብለዋል።በዓሉ ግርማ በኦሮማይ የናቅፋን ተራሮች"ገዳይ መሬት...እግዜር ተበሳጭቶ በክርኑ የደቆሳቸው"እያለ እንደፃፈው ኒኒ በርም እንዲያ ናት።

ከሁለት አንገተ መለሎ ኮረብታዎች መሃል እንደ ቀዳዳ ሆና የተፈጠረችው ኒኒ ልባችን የጓጓላትን መርሳ ከተማ ለማየት ማጮለቂያ ናት።ይህችው የምድር ትዕንግርት የመዓት ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያት ወንድሞቸን ደም የማገች፣አጥንት የሳገች ቦታ ናት።ቢያንስ ላለፉት ሰባትና ስምንት ቀናት ቅልጥ ያለ ጦርነት ይካሄድባት ነበር።ደሴ አኪም ቤት(?) በገፍ እየመጡ ቁስላቸው ሲያሳቅቀኝ የነበሩ አዳጊ ወጣቶች የረገፉት እሷ ዘንድ ሳይሆን አይቀርም።

ሳይሆን ባይቀርም ልባችን መርሳ ስለሆነ እና እንደ እሷ ያሉ"ገዳይ መሬቶች"ብዙ ስለሆኑ መኪናችንን ነዳናት።መርሳም ገባን።ኮከብ የሌለባት አረንጓዴ፣ብጫ ቀይ ሰንደቃችን እንዳስከበረችን አለች።አሁን በነፃዋ የሰሜን ወሎ ፈርጥ መርሳ ከተማ በኩራት መኪናችን ላይ ሆና መውለብለብ ጀምራለች።ሕዝቡ ቤቱን ትቶ ጎዳና ወጥቷል።ሲያየን ፍቅር ያቅበጠብጠዋል።የነፃነት ጣዕም ያንቀጠቅጠዋል።የደስታ ስሜት ይንጠዋል።

ረፋድ አምስት ሰዓት ገደማ ሆነ።መሐል መርሳ መነሐሪያው ፊት ለፊት ተከስተናል።ወሎየዎቹ በደስታ ስካር ላይ ናቸው።ፍፁም ሳይኖራቸው ፍፁም ይለግሱን ጀመር።ዐይኔን በእያቅጣጫው እየወረወርኩት ነው።መከላከያው መኪናው ላይ ሆኖ እንጀራ በሚጥሚጣ ይበላል።የሚያበሉት ስድስት ወር ወያኔ የበላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው።እኛ መኪናችን ውስጥ ሳለን የብርቱካን በረዶ ወረደብን።በቃ ያዘንቡብናል።በመኪናችን መስኮት የተለገሱን ብርቱካኖች እንደ ነፃነት ጥዑም ነበሩ።ዐይኔ በጋዜጠኝነት መነፅር ይህንን ፍፁማዊ የሕዝብ ደስታ ስላየች በፍስሐ ተጥለቅልቄያለሁ።

አሁን ከመኪናችን መውረድ አለብን።የምንሰራበት ማኅበራዊ መገናኛ ግርግር ይወዳል።ቡና ቤተንዋይ(Buna Bank) መርሳ ቅርንጫፍን ለምስል መቅረጫ(Camera)ችን ዐይን ሰጥተን የኒያን ደጋግ ወሎየዎች እየየ ልንሰማ ነው።በመሐል እንዲህ ሆነ።

"ጁንታ ጁንታ"ተባለ።የተማረከ የእብዱ ውሻ ወያኔ ታጋይ አለ።ምድረ ወታደር፣የከተማ ነዋሪ ምናልባትም መለያ የቀየረ ሰላይ ሁላ ከቦታል።አንድ" መቶ አለቃ ነኝ "ያለን የመከላከያ ሰራዊት አባል መቅረጸ ምስልና የድምፅ ማጉያ(Microphone) እንደያዝን ሲያይ በትዕዛዝ መልክ፦
"ኑ ቃለ መጠይቅ አድርጉለት" አለን።ያኔ በደስታ ሰክሬ ስለነበር እንዳለው ለማድረግ ተዘጋጀሁ።አሁን ሳስበው ለካስ በወታደር ቤት ትዕዛዝ እንጅ "እባክህ"ማለት ነውር ነው።


ለሁሉም በዚህ የዘመቻ ጉዞየ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላትን ተዋጊ ቃለ መጠይቅ ላደርግ ነው።መጀመሪያ ባልደረባየ(ምስል ቀራጩ) "አይዞህ ወንድሞችህ ነን"አለው።

(የወያኔን ምርኮኛ ጉዳይ ይዠ በሁለተኛው ክፍል እመለሳለሁ።ታሪኩ የተፈጸመው ልክ የዛሬ ሁለት ወር ታህሳስ ዘጠኝ ቀን በዋለችው ዕለተ ቅዳሜ ነው!)

t.me/Gazetaw
የብልፅግና ፓርቲና የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል
የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል ቢጫ፣ሰማያዊና ቀይ ሰዎች እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው የሚዘሉ ሰዎች አናት ላይ መስቀል ከነ ፈነጠቀው ጸዳሉ ይስተዋላል፡፡ በአንፃሩ የብልፅግና ፓርቲና ሁለት እጆች ተዘርግተው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ሰዎች በሰማየ ሰማያቱ ላይ የፈነጠቀውን የፀሐይ ብርሃን አይተው ሲጨፍሩ ይስተዋላል፡፡ የሁለቱም ቀለማቶች አንድ ዓይነት መሆናቸው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት መሆናቸውና ሦስት እጃቸውን ወደላይ አድርገው የሚዘሉ ሰዎች መሆናቸው ዝም ብሎ ገጠመኝ ሊሆን አይችልም እንላለን፡፡ የብልፅግና ቤተክርስቲያን የተጀመረው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን የአዲስ ሃሳብ አፋላቂዎች ንቅናቄ ሲሆን በ1950 እኤአ በሃገረ አሜሪካ በመዳን ቅሪቶች ዘመን የብልፅግና ቤተክርስቲያን ነገረ መለኮት ተጀመረ፡፡ (www.Prosperity church logo)1 ድረ-ገፅ አይተው ትዝብትዎን ያጋሩ፡፡

የብልፅግና ፓርቲና ልዩ ልዩ የኃይማኖት እምነት ተቆማት
የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት (ነገረ መለኮት) አስተምህሮት መሠረት ክርስቲያኖች ደህንነታቸው መጠበቅ አለበት ምክንያቱም መንፈሳዊና አካላዊ ህይወት የማይነጣጠሉና የማይለያዩ ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ አላቸው፡፡ የምዕመናኖች ደህንነታቸው የሚተረጎመው አካላዊ ጤና እና በኢኮኖሚ ብልፅግና ይገለፃል፡፡ የብልጽግና ነገረ መለኮት መምህሮች አትኩሮቱን ለግለሰብ ሥልጣን መስጠት በመንፈሳዊና አካላዊ ጥምረት በጎ ጎን በመገንባት ያሳልፋል፡፡ ክርስቲያኖች በተፈጥሮ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶቸዋል ምክንያቱም ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር አምሳያ ስለተፈጠሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ዓለማቸውን በማለማመድ በአካባቢያቸው የሚገኙ ቁስአካላዊ ነገሮች መጠቀም መቻል አለባቸው፡፡ የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት መሪዎች ያለ አንዳች ፀፀት ኃጢአታችንን እንዲያስተሰርይልን፣ ከበሽታ ደዌን ለመፈወስ፣ ከድህነት አረንቆ ለመላቀቅ፣ ከመንፈሳዊ እርኩስነት ለመንፃት፣ ድህነትና በሽታ በህብረተሰቡ ዘንድ እንደእርግማን ስለሚቆጠር በእምነትና በእውነት ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ መስበር እንችላለን፡፡ ”Prosperity theology teaches that Christians are entitled to well-being and, because spiritual and physical realities are seen as one inseparable reality, interprets well-being as physical health and economic prosperity.[47] Teachers of the doctrine focus on personal empowerment,[48] promoting a positive view of the spirit and body. They maintain that Christians have been given power over creation because they are made in the image of God and teach that positive confession allows Christians to exercise dominion over their souls and material objects around them.[48] Leaders of the movement view the atonement as providing for the alleviation of sickness, poverty, and spiritual corruption;[49] poverty and illness are cast as curses which can be broken by faith and righteous actions.” 2

የዘመናዊ ሽብርተኛነት ታሪካዊ አጀማመር ከፈረንሳይ አብዬት ጋር ይያያዛል፡፡ በዘመኑ የሽብርተኛነት ሥር መሠረቱ መንስዔው ሥልጣኔ አሊያም የባህል ግጭቶች፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ኃይማኖታዊ ግጭቶች፣ የእስራኤልና የፓልስታይን ግጭት፣ አሊያም የራሽያ አፍጋኒስታን መውረር በሃገራት መህል የተከሰቱ ሽብርተኞነት ያካትታል፡፡ የዘመናዊ ሽብርተኛነት በግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ብስጭት፣ የመገለል ስሜት፣ አሉታዊ የማንነት ጥያቄ፣ ራስን ማፍቀርና ማምለክ ንዴት እና ወይም የግብረገብነት ፈሪሃ እግዜብሄር ጋር ያለ ግንኙነት መላሸቅ ስሜቶች ይካተታሉ፡፡ በሃገራችን ኃይማኖታዊ ግጭቶች ወደ ዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀጆኖሳይድ) ተሸጋግሮል፡
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ውሎ አዳር በጎንደር

(ታመነ መንግስቴ ነኝ)

ስሆነው ፣ሳደርገው የዋልኩትን በሰንበት ላውጋችሁ!

ይችን እሁድ የምትሰኝ ዕለት ፈጣሪ እኛን አበጅቶ እርፍ ብሎባታል ሲባል እሰማለሁ፣አንብቤማለሁ።

"ብታምኑም ባታምኑም ጦር ግንባር ሳለሁ ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት ለኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ደውየ የግድቡን ሁኔታ እጠይቅ ነበር" እንዳሉት የአገሬ መራሔ መንግስት(ሀሳብዎ ላይ ተሳስቸ ያላሉት ነገር ብየ ተሆነ እርስዎ ተሳስተው 'የኤርትራ ጦር አልገባም' እንዳሉት ይቁጠሩት) እኔም 'ብታምኑም ባታምኑም እሁድ የእረፍት ዕለት ናት' ብያችሗለሁ።

ግን ግን ጠቅላያችን "ነገርዮሹ ስራዎት መስሎኝ? ለምን ማሳመን አስፈለገዎት_እያ!?"

ደሞስ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን የሚሉት አለማመን ነው? አሁን እኒህ የመኪናችን ዘዋሪ እስላሙ፣ጠዋት ቁርጥ ስንበላ'ቁርስ በልቻለሁ' ያሉን ኦርቶዶክሱ ጓዴ መኪና ውስጥ መተኛትን ተልባቸው መያዛቸውን ለማረጋገጥ 'ማርያምን?' ሲላቸው 'ማርያምን' ብለው የለም? ቢራስ አብረን አልጠጣንም? ይህችን እንቆቅልሽ አገር ምን ማድረግ ይሻላል? ማሳደግ😀

ውሎ አዳር በጎንደር፦

"ምን ተሰራ ፤ምን ተወራ
ጎንደር በጀግኖች ጎራ?
ይበሰራ፣
እውቀት ሐቅ ይነገራ።"

በሚል ዘፈን ተጀመረ።የመፃፍ ጸጋየን ተጠቅሜ "የጎንደር ወዳጆቸ ጋሽ ንዋይ"ጎንደር የወርቁ ልጅ ዘውዴ ናት እናቴ!" ያለላትን በሙሉ ስሟ ዘውዴ ወርቁ የምትሰኘን የጎንደር እናት ፈልጋችሁ አገናኙኝ" ብየ ለመንኩ።ልመናየን የሰማው እግዜር(እግዜር ግን ያነባል?) ቃልኪዳን(ቃልየ ብየ ስሟን አላቀልም) የዘውዴን ምትክ ፍቅርን አገናኙኝ።ፍቅር እኮ የባለከዘራው እህት ናት።እዚያ ቤት ያጎረሰችኝን ልጅ እግዜሩ መና ያውርድላት።እግዜሩ ግን ሳልሞትበት ለአፋር ሕዝብ የሚያጠግብ ውሃም ይስጠው።

ቀኑን ሙሉ ስንፈልገው የዋልነው ሰውየ ደመቀ ዘውዱ አይደለም? እኔስ ቤቱን፣ሚስቱን፣ልብሱን፣ጉርሱን አይቸ"እንደሰው ነው የምትኖር ጋሸ!?" ብየ ብደነቅበት "እህ እንደምን ልኑር?" አለኝ።

እኔማ እንደ 'ከንቲባ' አዳነች አበቤ ብየ ነበር።እናንተ 'እዳነች አበበች'የምትሉ ነገር ሰንጣቂዎች ግን ለአማራ ሕዝብ ምን አድርጋችሁለታል?

"አማራው ያጣው መሪ ነው።መሪዎች ለራሳቸው ክብር እንጅ ለሕዝቡ አይጨነቁም።"ብላችሁስ 'ማን አለህ'? ልትሉኝ አይደል?

'ደመቀ ዘውዱ' ልበላችሁና ዳግም አስከብቡት! እናንየ 'ጎንደር ባለ ማተብ ነው፤በደመቀ ዘውዴ እና ወልቃይት ጠገዴ አይደራደርም።'

የልቅ እንየ ታከለ የባህል አዳራሽ ብቅ ብለን እንመለስ። እዚያ 'ዶፔል ቢራ 22 ብር' ተብሎ ዋጋው በር ላይ የተፃፈለት ምን ያህል አስቀያሚ መጠጥ ቢሆን ነው? ጣፋጭ መጠጥና ልባም ጎንደሬ እማ 'ሽሽግ' ተደርገው እንደ መይሳው ካሳ ላለው የአገር ዋልታ ይሰጣሉ።የራስ አሊ እናት ተዋበችን ለዳግማዊ ቴዎድሮስ የዳሩለት እኮ ዋጋዋን ለጥፈው አይደለም!

'አንች በቀሚስ የምትዋቢው ጎንደሬ ወዳጀ እነበብሻለሁ!?"

"እኔን ጎንደር ጎንደር እኔን ጎንደር ያርገኝ
የበሉት ሲስማማ የፈለጉት ሲገኝ"

የባለከዘራው እህት ቤት የበላሁት እዚህ የማይፃፍ ነገር ተስማምቶኛል።እንደምሳ በልቸው እነሆ ራትም ሆኖኛል።ኤርምያስ አመልጋ ለምን በ24 ሰዓት አንዴ ብቻ እንደሚበላ ተገለጠልኝ ልበል እንዴ? ይልቅስ 'ከኤርምያስ አመልጋ ጋር ማዕከላዊ እስር ቤት ነበርኩ" ያለኝን መኩሪያ የሆነ ፋኖ_ሻለቃ ጠዋት ቃለ መጠይቅ አድርጌ አለሁ።

አዝማሪ አማረን...!

እንየ ታከለ ቤቷ ሞልቶባታል።ባልደረባየ"እናንተ ፈስሳችሁ ነው?" ያላቸው ጎንደሬዎች(ተሌላም አገር ሊመጡ ይችላሉ።አርብ ዕለት አዘዞ ጥይቱ እንደፈነዳ ዘብ(Police )ጣቢያ ተመቶ ሁለት ሰውም ሞቶ ገብተን ወላ ሐድያ ወላ ወላይታ ብቻ ሴቶች ለስደት ሊያመልጡ ሲሉ ተይዘው አላየንም እንዴ?) በሩን አልፈው መንገዱን እየዘጉት ነው።

ተስፋ ቆርጠን('ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም'ሲባል እሰማለሁ።እስላምስ? እሱም አይቆርጥም።አብሮን የነበረው ሰውየ እስላም መሆኑን ተላይኛው አንቀጽ ጥፌ የለም እንዴ?) ስንጓዝ "ባላገሩ " የሚሉት የአዝማሪ ቤት አገኘን።

"እኔን ጎንደር ያርገኝ"

እዚያ ቤት ገብተን የገበየነውንስ ታልሞትኩ ተድሉ በሗላ አወጋችሗለሁ።ተሞትኩም አትደነቁ ሌላ ታመነ ወይም ሌላ እገሌ ያወጋችሗል።

"ከሰማይ በታች አዲስ ነገር የለም።" ጎንደርም በላሊበላ ዘመን ዝም ብላ ጋራ እና ሸንተረር ነበረች።ሗላ "እሽሩሩ ጎንደር"ተባለች።የፋሲል ግቢን አሃለች።አሁንም ደርግና ወያኔን ተቋቁማ እየቆዘመች፣እያስቆዘመችኝ አለች።

t.me/Gazetaw
Forwarded from ሀser
ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

ባለፉት የታሪክ ገጽታዎቻችን ውስጥ በጉልበትና በይፋዊ ተቃርኖ ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ኹሉ አልተሳኩም፤ እንዲያውም የበለጠ ሲያጠናክሯትና ሲያስፋፏት ተስተዋሉ እንጂ፡፡ ለምሳሌ፡- በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመን
ኦርቶዶክሳውያኑን በግዳጅ የማስለም ድርጊቶች ተፈጽመው ነበር፤ ሕዝቡም ወደ እስልምና ሲገባ አምኖበት ሳይኾን ተገዶ ስለነበር ጊዜ እስኪያልፍ በትዕግሥት ሲጠባበቅ ቆይቶ ነበር፡፡ እናም፥ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እነዚያ የመከራ ዘመናት ሲያልፉ ሃይማኖታቸውን እንዲክዱ
ተገደው የነበሩ ምእመኖቿን መልሳ ወደ ጉያዋ ለመሰብሰብ እንዲያስችላት ‹‹አንቀጸ አሚን›› የተባለ የማስተማሪያ መጽሐፍ አዘጋጅታ፣ ‹‹መጽሐፈ ቄዴር›› የተባለ የማጥመቅያ ሥርዓትም
ሠርታ ተልእኮዋን መልሳ ለማጠናከር ችላለች። ኦርቶዶክሳዊነትን ለማክሰም የተሠራ ሴራ ጭራሹን እንዲጠናከር ዕድል መፍጠሩን ይኽ አንዱ የታሪክ ምስክርነት ነው፡፡
በኋላ በጣልያን ወረራ ጊዜም ካቶሊኮች የእስልምናውን ክንፍ በመደገፍ ሁለቱ ‹‹የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው›› በሚመስል መርሕ ተባብረው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ሲሠሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- በካቶሊኮቹ ሴራ ‹‹ሁለቱ እሾሆች›› የተባሉ ቅባትና ጸጋ በኢትዮጵያ ምድር በተተከሉ ጊዜ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እነርሱን ለመንቀል ትግል ላይ ስትጠመድ እስልምናው ደግሞ ድምጹን አጥፍቶ ውስጥ ውስጡን ሲስፋፋ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በዚኽ ታሪካዊ ተሞክሮ መሠረት ደግሞ የጋራ ጠላትን እንዴት በትብብር መዋጋት እንደሚቻል ልምድ ተቀስሞበታል፤ ይበልጥ አዘምኖና አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግም የታመነበት ይመስላል፡፡
አሁንም በግላጭ ኦርቶዶክሳውያንን አስገድዶ ለመጠምዘዝ መሞከር የማይታሰብ ነውና ሌላ ስልት አስፈለጋቸው! ይልቁንም፥ ተፈጥሯዊ በኾነ መንገድ (biological strategy) ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሷን በራሷ እንድታጠፋ ኹኔታዎችን ማመቻቸት አዲሱ ስልት ተደርጎ የተያዘ ይመስላል፡፡ ይኽ ስልት አንድ እንዲጠቃ የተፈለገው ተቋም ራሱን በራሱ እንዲያጠፋ መርዳት (helping the institution to self-suicide) የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይኽ ተፈጥሯዊ
የመባሉም ምስጢር ችግሩን በሚመስል መፍትሔ የመከላከል ስልትን ስለሚከተል ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በሥነ-ሕይወታዊ የጥናት ዘርፍ ትላትሎችን ከግብርና ሰብል ጥቃት ለመከላከል ሲፈለግ ለሰብሉ ጎጂ ያልኾኑ፣ ነገር ግን ትላትሎቹን የሚበሉ ሌሎች እንስሳት የማርባት ዘዴ
ማለት ነው፤ በዚኽ የተፈጥሮ ሚዛን (ecological balance) ይጠበቃል፡፡ ከሌሎች ስልቶች የበለጠም ውጤታማ ነው (ኬሚካልን የመሰሉ መፍትሔዎች ለጎጂ ተባዮች ተረጭተው
ጠቃሚዎቹንና ሰብሎችን ጭምር የሚያደርቁ ‹‹ጅምላ ጨራሽ›› ከመኾናቸውም በላይ ለአየር
ብክለት ስለሚያጋልጡ አይመከሩም)፡፡ ተባዮቹን የሚመስሉ ሌሎች ተጻራሪ ተባዮች ሲኾኑ ግን ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ስላላቸው በቀጥታ ከመገናኘታቸውም በላይ ጎጂዎቹ ተባዮችን አዘናግተው (ዘመድ መስለው) እንዲያጠቁአቸው ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡
ይኽንኑ ኹኔታ ወደ ተቋም ስናመጣው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ፊት ለፊት በመንግሥታዊ ሥልጣን ተጠቅመው፣ በሰይፍ አስፈራርተውና በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ተከራክረው ማሸነፍ
እንደማይቻል ከታሪክ የተረዱት አካላት አንድነቷን ለመክፈል መጠቀም የጀመሩት አዲሱ ስልት መኾኑ ነው፡፡ ይኽ ስልት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ በቀጥታና በይፋ የሚሰነዝረውን ጥቃት በይፋ ሳያሳውቅ (ለትችት በማያጋልጠው፣ ነገር ግን የተሻለ ውጤታማ በሚያደርገው መልኩ) እንዲያዳክማት የሚያስችላቸው ነው፡፡
ይኽ ተፈጥሯዊ ስትራቴጂ ‹‹ራስን በራስ እንዲያጠፋ የመርዳት›› መርሕን ስለሚከተል ቤተ ክህነቱ እንደተጻራሪ ክንፍ በፈረጃቸው የእስልምናና ሌሎች የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ከመገዳደር ይልቅ በውስጡ ባሉት ሰዎቹ ተጠቅሞ፣ ስያሜውን በሚመስል ዘዴ፣ የራሱን ተልእኮ
የሚያፋጥንለት የሚመስለውን አሠራር መዘርጋት ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል፡፡ መዋቅርን በመዋቅር፣ ጳጳስን በጳጳስ፣ ቤተ ክህነትን በቤተ ክህነት፣ ሲኖዶስን በሲኖዶስ፣ ማኅበራትን በማኅበራት፣ አሠራርን በአሠራር ተክቶ ከመጀመሪያው አቅጣጫዋ ወደ ሚፈለገው መሥመር ማስቀየስ፤ በሒደትም ግብዓተ መሬቷን ለመፈጸም እንደማለም ያለ ስልት ነው፡፡
ይኽ ከሰሞንኛ ኹኔታዎች አንጻር ምን ምን ነገሮችን እንድናስተውል ያደርገናል?

(1) ትናንት ‹‹የኦሮሚያ ቤተ ክህነት›› እያሉ ሲያጨናንቁን የነበሩ ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› ወንድሞቻችን ዘግይተው ደግሞ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ፥ ‹‹ሙስሊም ወንድሞቻችን
ቢያፈጥሩበት ምን ችግር አለበት?›› እያሉ ሲከራከሩን አስተውለናል፡፡ የገዛ ወገኖቻችን ከተቀናቃኞቻችን ጎን ኾነው ሞገቱን፤ ኦርቶዶክሳውያንን በኦርቶዶክሳውያን መዋጋት ይሏል ይኽ
ነው!

(2) ይኽንኑ ጉዳይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነቷ አማካይነት ተቃውሞ ስታቀርብ መንግሥት ደግሞ የእርሷኑ ሌላ መዋቅር (የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን) ተጠቅሞ
‹‹ይቅርታ›› አስጠየቀ፤ በመዋቅራችን አማካይነት መዋቅራችንን አጠቃው ማለት ነው!

(3) ለኦርቶዶክሳዊ ቀኖናት ደንታ የሌላቸውና ከመሰል እሴቶች ሊያንሸራትቱን የሚሹ ተሓድሶዎች ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› መስለው፣ ለትግራይ ሕዝብም እንደተቆረቆሩ አስመስለው
በበዓለ ሃምሳ ጾም ዐወጁ፡፡ ይኽንን ሲያደርጉ ግን ‹‹የገዳም አባቶችና የትግራይ ሊቃነ ጳጳሳት አዘዋል›› እያሉ ነው፡፡ ከእኛው ጾምና ትእዛዘ አበው ጋር ታክከው የእኛኑ ቀኖና ለመናድ የሚደረግ ሌላኛው እንቅስቃሴ!

(4) በውስጣችን ኾነው፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያንን አሁናዊ ጭንቀት መፍትሔ እንዳገኙ አስመስለው ‹‹ደጉ ንጉሥ ቴዎድሮስ ይገለጣል!›› የሚሉንም በዝተዋል፡፡ ለዚኽ ማሳመኛቸው
ደግሞ ‹‹ፍካረ ኢየሱስ›› እና ‹‹የገዳም አባቶች መልእክት›› የሚሉ የማግባቢያ አካሔዶችን ይጠቀማሉ፡፡ ገዳማውያኑ ግን በአንድነት ኾነው ‹‹መልእክቱ ከእኛ አይደለም!›› ማለታቸውን ልብ ይሏል፡፡

ይቀጥላል...
Forwarded from ሀser
ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት!

....የቀጠለ

(5) ከዚኽን በፊትም በተለመደው የፖለቲካ ሴራ አካሔድ መሠረት ቅዱስ ፓትርያርኩን ከመንበር አውርደው በሌላ ተረኛ ለመተካት ባለሥልጣናቱ ፊት ለፊት መምጣቱን አልፈለጉትም፡፡ እናም፥ መጀመሪያ ቅዱስነታቸውን እነርሱ ‹‹ጁንታ›› ከሚሉት አካል ጋር ፈርጀው ለማሸማቀቅ፣ በምእመኑ ዘንድ ለማስጠላትና ‹‹በፈቃዳቸው ለቀቁ›› ለማስባል ሞከሩ፡፡ ‹‹እኔም ኦርቶዶክሳዊ
ነኝ›› የሚሉ፣ በተግባር ግን ያልኾኑ ‹‹መምህራን›› እና አክቲቪስቶችን ከጀርባ ‹‹አይዟችሁ!›› እያሉ በጸያፍ አገላለጾች አስሰደቧቸው፤ ከልክ በላይም አፍ አስከፈቱባቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን
ዋና ጸሐፊ ‹‹አይወክሉንም!›› የሚል መግለጫ አስሰጡ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ኹሉ ግን በሚገርም ኹኔታ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ ኾኖ ‹‹ከአባታችን ጎን ነን!›› ብሎ አሳፈራቸው፡፡ ይኽንን የሕዝቡን ሥነ ልቡና ያስተዋሉት ፖለቲከኞቹ ከቅዱስነታቸው ጋር የ ግል ቅራኔ ያላቸውንና የሥልጣን ጥም ያሰከራቸውን ‹‹ጳጳሳት›› በኅቡዕ አደራጅተው መንቀሳቀስ ይዘዋል፡፡ ‹‹ደኅንነቶች ነን›› በሚሉ ሰዎችና ለተረኛው መንግሥት እንቀርባለን በሚሉ ‹‹አባቶች›› አማካይነት ‹‹መንግሥት የሚፈልገው ይኽንን ነው›› ብለው እያስወሩ በአባቶችን ውሳኔ ላይ ከወዲሁ ጫና ለማሳደር እየተሞከረ፣ ቤት ለቤትም ቅስቀሳዎች እየተደረጉ መኾኑ እየተሰማ
ነው፡፡ ገና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳይሰበሰብም፡- ‹‹ቅዱስ ፓትርያርኩ በሌሉበት ምልዓተ ጉባኤ እንደሚካሔድ፣ እንደራሴ እንደሚሾም›› ማስወራት ይዘዋል፡፡ የእኛን አባቶች እየተዋጓቸው ያሉት በእኛው አባቶች ነው የሚያስብለውም ይኸው ነው!

(6) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን በማርቀቅና በማጽደቅ ሒደት ውስጥም የግለሰቦች ፍላጎትና የውጭ አካላት እጅ እየገባ እንደኾነ ተሰምቷል፡፡ ገና ሕጉ በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ ሳይጸድቅ ‹‹የማስፈጸሚያ ሰነድ›› የሚል ረቂቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ባሉት የወቅቱ ፈላጭ
ቆራጮች አማካይነት ሌላ አጀንዳ ማስቀየርያ መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡ ስሙን ‹‹ሕገ ቤተ ክርስቲያን›› እያሰኙት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለግለሰቦች ፍላጎት አሳልፎ የሚሰጠውን አካሔድ ግን ‹‹ሕጋዊ›› ለማስመሰል የሚሔዱበት ርቀት ያስተዛዝባል! ሌላው ቀርቶ ‹‹እኛ
መነኮሳት ነን፤ ንብረታችን ኹሉ የቤተ ክርስቲያን እንጂ የእኛ መኾን የለበትም›› የሚል ሐሳብ የሰጡ ሊቃነ ጳጳሳትን እንኳን ምን ያኽል ሲያገልሏቸው እንደነበር የምናስታውሰው ነው!

(7) የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊ አንድነትና መዋቅራዊ ጥንካሬ ለጎሣ ፖለቲካቸው የመከፋፈል ሴራ አልመች ሲል የ16ኛውን መቶ ክፍለ ዘመን እሾኽ (‹‹ቅብዓት›› የሚባል ኑፋቄ)
በ21ኛው ክፍለ ዘመን መልሰው ለመትከል ምሥራቅ ጎጃምን የሚያስጨንቋትም አሉ፡፡
በየትኛውም የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሥርዓት ‹‹ጳጳሳት›› እንደተሾሙ ተነገረ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባኤ ትኩረት ለመሳብና አጀንዳውንም ለማስቀየርም ሲሉ ‹‹የጳጳሳቱ በዓለ ሢመት ተዘጋጅቷል›› ብለው የጥሪ ካርድ በተኑ፡፡ ይኽ ኹሉ ሲኾንና ከመደበኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ተደጋጋሚ አቤቱታ ለመንግሥት መዋቅሮች ሲቀርብ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል፤ በአጥፊው ፋንታም ሰላማውያኑ ታስረዋል፡፡ ‹‹ተለያይቶ
የነበረውን ሲኖዶስ አንድ አደረግሁ›› ብለው የሚመጻደቁት አካላት ‹‹ሌላ ሲኖዶስ›› ለመፍጠር ለምን እንደሚሯሯጡ ግን ግልጽ አይደለም!
ኦርቶዶክስን በራሳቸው በኦርቶዶክሳውያን አማካይነት የማዳከም ስልት፤ አዲሱ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሴራ!

👉ከ ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፣ ምዕ.4፥ ገጽ.89-92 ላይ ባለው ሐሳብ መነሻነት የተጠናቀረ
ንቂ ኢትዮጵያ pinned «ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት! ባለፉት የታሪክ ገጽታዎቻችን ውስጥ በጉልበትና በይፋዊ ተቃርኖ ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ኹሉ አልተሳኩም፤ እንዲያውም የበለጠ ሲያጠናክሯትና ሲያስፋፏት ተስተዋሉ እንጂ፡፡ ለምሳሌ፡- በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመን ኦርቶዶክሳውያኑን በግዳጅ የማስለም ድርጊቶች ተፈጽመው ነበር፤ ሕዝቡም ወደ እስልምና ሲገባ አምኖበት ሳይኾን…»
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ዋና ስር መሠረታዊ ችግር - አንቀጽ 39

ምዕራባውያኑ ስለ አንቀጽ 39 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም የሰጡት የሴራቸውን ማብራሪያ አድምጡት። ሀገሪቱን በብሔር ብሔረሰብ መብት ማስከበር ስም በህገመንግስቱ እንዲካተት የተደረገው በማር የተለወሰ መርዝ አንቀፅ አደገኝነት በሰፊው ተብራርቶበታልና አድምጡት ሼርም ተደረጋጉት። አዲሱ ትውልድ ሊነቃና ካለፈው ታሪኩ ሊማር ይገባዋልና።
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
ስለ NIKE ጫማ ማወቅ ያለብን

Nike በአለማችን ተወዳጅ የሆነው Brand ጫማ ስያሜውን ያገኘው ከጥንት የግሪክ አማልክት የ Pallas(Titan) እና የStyx ልጅ ከሆነችው Nike ነው ፡፡Styx መሬትንና የሲዖልን መግቢያ የሚከፍል ወንዝ ነው ብለው ግሪኮች ያምኑ ነበር፡፡
Nike የጥንታዊ ግሪኮች ጣዖት የነበረች ሲሆን የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ብለው ያመልኳት ነበር፡፡መመለኳም አሁን ድረስ ቀጥሏል፡፡

Nike በ Zeus(የጥንት ግሪክ ዋና አምላክ) የፍጥነት የጥንካሬና የድል አምላክ ለዘላለም እንደሆነች ቃል ስለተገባላት አምላክነቷ አሁንም ድረስ ቀጥሎ በእሷ ስም የተሰየሙት ምርቶች የሚከተሉት ናቸው፡
1.Honda motor cycles የ Nike'ን ምልክት እንደ አርማ/logo ይጠቀማል፡፡
2.በአሜሪካ anti aircraft missile system የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል፡፡
3.በዋነኛነት የ nike ጫማ አምራች የ nike'ን ምልክት ይጠቀማል፡፡

ስለዚህ አብዛኞቻችን የምንጠቀመው Nike ጫማ ሰይጣንን የሚወክል ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡በዙ ሰወች "ካላመለኩት ምን ችግር አለው" ይሉ ይሆናል ነገር ግን እኛ የእግዚአብሔር ተከታዮች እንጂ የሰይጣን አደለንም፡፡ ሰይጣን አምላኪዎቹ ኢሉሚናቲዎች ብዙ በጀት መድበው ይህንን ሁሉ የሚከውኑት የሚያመልኩትን ሰይጣን ከፍ ከፍ ለማረግና የዓለም ህዝብን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሱ አቀንቃኝ ለማረግ ነው።

አሁን አሁን ላይ ለእኛ ለክርስቲያኖች ጊዜው ከባድና በፈተናዎች የተሞላ ነው::እያንዳንዷን እርምጃችን ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል፡፡ምክንያቱም እኛ ግሎባላይዜሽን በሚባል በዘመናዊ ባርነት የታጠርን ሰወች አብዛኛው እንቅስቃሴያችን በእኛ ሳይሆን የሰይጣን ጭፍራ በሆኑ ሀገሮች የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡የሚሰጡንን ቀጥታ እንቀበላለን ለምን ብለን አንጠይቅም። የእነሱን እንቀበላለን የእኛን እንንቃለን የእነሱ የሆነው ሁሉ ይጥመናል፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ስለምንከተላቸው ሰወች ፣ ስለ አለባበሳቸው ፣ ስለምንመገበው ምግብ ፣ ስለምንጠቀመው ቴክኖሎጂ እናውቃለን?

አሁንም ለመንቃትና ለማስተዋል ጊዜው አረፈደም!

#ፀረ_ኢሉሚናቲዝም
Forwarded from ኖህ ኢትዮጵያ
ቅዱስ ጊዮርጊስ - ቢራ ወይስ ሰማዕት?

የቅዱሳን ስዕል አድህኖ በክብር መቀመጥ ሲገባው የቅዱስ ገዮርጊስ ስዕል ግን

1/ በየጠርሙሱ ተለጥፎ የሰካራም እጅ ያለ ንጽህና በድፍረት ይጨብጠዋል።

2/ ስዕል አድህኖው በየመጠጥ ቤቱ እየወደቀ ይረገጣል። ከቆሻሻ ጋር ተጠርጎ ይጣላል።

3/ በስሙ ታቦት መቀረጽ ሲገባው የሚያሰክር መጠጥ ሆኖ ስሙን ለማርከስ ተሰርቷል

4/ ኢትዮጵያ ከሰማዕቱ የምታገኘውን ክብርና ጥበቃ ለማሳጣት በ1915 ዓ.ም ጣሊያኖች አቅድው አቋቋሙት።

የሚገርመው መጠጡን የሚጠጣው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዩ ነው።
አንዳዴ እንደቀላል የምናያቸው ነገሮች ከፍተኛ የሆነ ጥፋቶች ናቸውና እንንቃ።

ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!