ንቂ ኢትዮጵያ
541 subscribers
261 photos
83 videos
32 files
179 links
እዚ ገፅ ላይ የምናነሳቸዉ ነገሮች

፩ ስለ ኢሉሚናቲ
፪ ስለ 5G
፫ ኢትዮጵያ ላይ ስለሚደረጉ ሴራዎች
፬ ስለ GMO
፭ ስለ ግብረሰዶማዊነት
፮ ስለ ማይክሮ ቺፕ

1% CONTROL THE WORLD
4% ARE SELL OUT PUPPETS
90% ARE ASLEEP
5% KNOW AND ARE TRYING
TO WAKE UP THE 90%
THE 1% DONT WANT THE
5% WAKING UP THE 90%
Download Telegram
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ሰው ሁሉ ቅኔ ነው፤ራሱን ይቀኛል
የእኔን ትቸዋለሁ፤የአንተ ይበቃኛል።
አያ ሙሉጌታ፦
ተቀድሰህ ንገስ፤በልባችን ዙፋን
ሁሉ እየተንጫጫ፤መሪው ገዥው ጠፋን።

ታመነ መንግስቴ

ለባለ ቅኔው ሙሉጌታ ተስፋየ
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ምሽት 12:00 ላይ "የጋራ ነው"የሬዲዮ ዝግጅት በአዋሽ FM 90.7 መደመጥ ይጀምራል።


ስለ ደግነት አርማዋ እማማ አበበች ጎበና መነጋገራችን እንደተጠበቀ ሆኖ፦


👉ሰሞነኛ የታሪክ አጋጣሚዎችን በምናወሳበት አፍታ በሐምሌ ወር ተወልዶ በሰኔ ስለሞተው "የወራሪዎች ንጉስ "ጨዋታ ይዘናል።

👉ባህልና ወግ ላይ
"አሻም አሻም"እያለ ለኢትዮጵያዊ ባህልና ጋዜጠኝነት ሲተጋ ኖሮ በጎልማሳነቱ ስላጣነው ጋዜጠኛ ካሳሁን አሰፋ ጉዳይ ይኖረናል።

👉በኪነ ጥበብ ሰዓታችንም ወደ ወሎ ተጉዘን በዚያ ከ"እሪኩም ዘመዳ" እስከ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት አዘል ግጥሞች ምጥን ዝግጅት ይዘናል።

👉በፖለቲካ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዳሰሳ ጊዜ ወደ ልበ ተራራዋ ትንሽየ አገር ኩባ እናመራለን።

👉ከእናንተ አድማጮች ጋር ለመወያየት የመረጥነውም "ዘመናዊነት እና ኢትዮጵያ ምንና ምን ናቸው?" የሚል ርዕስ አለን።

ክቡራትና ክብራን ከእናንተ ጥሞና እና ተሳትፎ እንጠብቃለን።

አጫጭሮቹን መልዕክቶቻችሁ በድምፅም እየቀረፃችሁ፦

👉6804 ላይ ላኩልን።

በቀጥታ የስልክ መስመርም፦

011 5 54 33 16 ወይም የመጨረሻውን 19 እያደረጋችሁ ደውሉልን።


ሃሳባችሁን በማህበራዊ መገናኛውም፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ትግራይ፦የታሪክ ወለፈንድነት* እና ሰሞነኛ ጣጣ

(በታመነ መንግስቴ)

እኔ በመራሄ መንግስቱ ዐቢይ አህመድ ፅሕፈት ቤት አልታደምኩም።በነዚያ ነጫጭ ወንበሮች ላይ አልተቀመጥኩም።ከሰውየው ዘንድ ፍርፋሪም አልቀመስኩም።በአሸናፊው አንደበታቸው ተረትቸም አላጨበጨብኩም።ግን ዘመኔ የመረጃ ነውና ሰውየውም ያሉትን ጋዜጠኞቹም የሆኑትን ታዝቤያለሁ።በሚከተለው መጠነኛ የልጅ ትንታኔየ ሰሞነኛውን የተከዜ ማዶ ጣጣ ከታሪክም፣ከተረክም፣ከዛሬም ከነገም አንፃር እመለከተዋለሁ።

ስሙን የደበቅሁለት ዘፋኝ ተወዳጀ እንደነገረኝ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ዳንኪራ ቤቶች"እምበር ተጋዳላይ"መቀንቀን ጀምሯል።በዚህም የተነሳ የመዲናይቱ ቀውጢ መጨፈሪያዎች ገበያቸው ተመናምኗል።ብልፅግናውን ፍራቻ የማስደለቅ ቅስማቸው ኮስምኗል።

ከተከዜ ማዶ ደግሞ ምናልባትም የቀበሮ ደስታ ቢጤ ሆኗል።በዚያ መራሔ መንግስት ዐቢይ አህመድ በገደምዳሜው"ወጋን"ያሉት ትግሬ "ታጋዮቹን"በፌሽታ እየተቀበለ ይመስላል።

የኒያ ደጋግ ሰሜነኞች እጣ ፋንታ በቀናነት ለተመለከተው እጅጉን ያሳዝናል።ያ_ምድር ላለፉት ቢያንስ 5 መቶ ዓመታት የቀውጢ ጦርነቶች ሁነኛ መድረክ ሆኗል።እናም እነ በዓሉ ግርማ እንደሚሉትና ታሪክም ደጋግሞ እንደሚነግረን ቦታው የ"አድር ባዮች"ምድር ሆኗል።

ላይኞቹ አንቀፆች መራራ መሆናቸው ይነበበኛል።ነገር ግን የሐበሻ ጀብዱ ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ መኮንን ስለ ጉዳዩ ጠይቄያቸው እንደመለሱልኝ"ተፈርቶ አይኖርም"ና ሃቅ ሃቁን ብንነጋገር ያግባባን ይመስለኛል።

በዓሉ ግርማ የሰዎቹን ስነ ልቦና ከተረዱት ጋር ተነጋግሮ ሊፅፈው ችሏል ተብሎ በሚገመተው"ኦሮማይ"የተሰኘ ታሪካዊ ልቦለዱ ውስጥ፦

"ሰለሞን ለመናገር ብሎ የሚናገር ሰው አይደለም።ከተናገረ ስለሚናገረው ነገር ካንጀቱ ስለሚናገር አድማጭ ይስባል።"ብሎ ባስተዋወቀን ገጸ ባህርይው አማካኝነት በገጽ _83_ላይ ከመረብ ማዶ ስላሉት ትግሬዎች ስነ ልቦና ሊነግረን ይሞክራል።
"___በኤርትራ ክፍለ ሀገር ታሪክ ውስጥ የበላይነትን ያገኛል ተብሎ የሚገመተውን ኃይል ተቀብሎ የማስተናገድ ዝንባሌ አዲስ ነገር አይደለም።በ400 ዘመን የትግል ታሪክ ውስጥ አንዱ ኃይል ሲሄድና ሌላው ሲመጣ ማየት የተለመደ ነገር ሆኖ ቆይቷልና አድርባይነት ሁለተኛ ተፈጥሮ ሊሆን ምንም አልቀረውም።መጠራጠር ይበዛል።የ"ቶማሶች"ቁጥር ቀላል አይደለም።"

ደራሲው ለመረብ ማዶ ሰዎች የከተበው ሃቅ ለተከዜ ማዶዎቹም የሚሰራ ይመስላል።መከላከያው መቀሌ ሲገባ "ጁንታው ጨቁኖን ነበር"ብሎ እነ ደፂ ከጫካ ወደ ከተሞች ሲጠጉ "እምበር ተጋዳላይ" ማለት ከአድር ባይነት በምን ይለያል? በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጨክኖ መተኮስ፣"አንድ ቄስ የማስተማሪያ ድምፅ ማጉያና ክላሽንኮብ"ይዘው መውተርተር ምን ይባላል? ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መጥላት ከዚህ በምን ይለያል? እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ የአራት ኪሎው ባለሟል እንዳሉትም "የጥሞና ጊዜ ያስፈልጋል!"

እንደ ኩሩ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከማደንቃቸውና ከሚያሳዝኑኝ ነገስታት መካከል ትግሬው ቆራጥ መሪ ዮሐንስ አራተኛ ይገኙበታል።የእሳቸው በድልም በእድልም የተዋዛ የግዛት ዘመንና በመጨረሻ ለኢትዮጵያ ቁራሽ መሬት ሲሉ አንገታቸው በመሃዲስት እጅ መቆረሱ ከጥፋታቸው በላይ እጅጉን ይጎላብኛል።

ይሄንን እያሰላሰልኩ በትግራዋይ ጀግንትና የኢትዮጵያ ስልጣኔ እምብርትነት ስኮፈስ አስቀያሚዎቹ የከሃዲነት አጋጣሚዎች እንደ ሰኔ መብረቅ ብልጭ ይሉብኛል።

የሐበሻ ጀብዱ መፅሐፍ ተርጓሚ ተጫነ ጆብሬ መኮንን በተገኙበት የአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ የመፅሐፍት አውደ ርዕይ መድረክ ላይ አስተናባሪ የነበሩት ታላቁ የስነ ፅሁፍ አስተማሪ ሊቀ ምሁሩ ደረጀ ገብሬ በዕለቱ ሲመክሩን"ታሪክ መማሪያ እንጅ መማረሪያ"ስላልሆነ በዚሁ መፅሐፍ ገጽ_307 ላይ ተከትቦ ብዙ ያነጋገረን አንቀፅ ከዚሁ የተከዜ ማዶ ሰዎች ጣጣ ጋር በእጅጉ ይቆራኛል።

የዚህ ተወዳጅ መፅሐፍ ደራሲ አዶልፍ ፓርለሳክ የኢትዮጵያው የገበሬ ጦር በብዙ አጋጣሚዎች ድልን በጣሊያን ላይ ተቀዳጅቶ ዳግማዊ አድዋን ሊያበስር ሲል እንከን እየሆኑ በአገራቸው ታሪክ ላይ ቀፋፊ ቀለም ያስቀመጡትን ሰዎች በስም ይጠቅሱና

"___በማይጨው ጦርነት በዚያች ቀውጢ ሰዓት በሰሩት ስራ እኔም "አረመኔዎች" ናቸው ከማለት ወደሗላ አልልም።" ሲሉ እጅጉን ያዝኑባቸዋል።

በጉዳይ ላይ ብቻ ከተርጓሚው ጋሽ ተጫነ ጆብሬ ጋር መጠነኛ ክርክር ለማድረግ ሞክረናል።በዚያች አፍታ ከተሰነዘሩ የታዳሚያን ዕይታዎች መካከል የማረከኝና በዚህ ፅሁፍ ውስጥም ጎልቶ ቢነበብ የሚያግባባን "ባንዳነት ከGeographical Location አንፃር"ቢታይ ሲሉ አንድ ሰው ያነሱት ሃሳብ ተመችቶኛል።

የነገሩን ሁነኛነት ለመፈተሽ ባደረግሁት ጥረት የዚሁ መፅሐፍ ደራሲ በተጠቀሰው ገጽ ላይ ከብስጭታቸው ቀጥለው"ራያዎች በዘር ኦሮሞዎች ናቸው ይባላል"ያሉበት አገላለፅ ቀን የከፋ ለታ የትኛውም "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው"የሚል ብሔር አገሩን አሽቀንጥሮ ከመጣው ጋር አሸሸ ገዳሜ ሊል እንደሚችል ማሳያ ይሆናል።

"ቀን ዘመድ እኮ ልዠ
እናትና ልዡን የሚያስተቃቅፈው የቀኑ ማማር ነው።"ስትል የአያቴ ምሽት የነገረችኝ በኑረት የተፈቸነ ሃቅም በእንዲህ ያሉ ተጠየቆች ይሰራል።

"ብሔርም ባዕዳ ነው፤ይገለባበጣል

አብሽሪ ኢትዮጵያ፤የአንች ቀን ይመጣል።"**


በዚህም ተባለ በዚያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ መውጣቱ በአንፃራዊነት ለሁሉም ይበጃል።መራሔ መንግስት ዐቢይ አህመድ ለጋዜጠኞቹ ሲነግሩ እንደሰማነው ሕዝበ ትግራዋይ የመከላከያን ጣዕም" ቢያንስ በወር ውስጥ ቢበዛ በሁለት"ሊረዳው ይችላል።እስካሁን ግን ለብዙ ክፍለ ዘመናት ታሪክ እና ዕድል ፊታቸውን አዙረውበት መጠነኛ የአገር ክህደቶችና በትህነግ(TPLF) ስብከቶች የተማረከ ይመስላል።

"ከድህነት ነፃ እስካልወጣን ድረስ ባንዳነት አይጠፋም።"የሚለው የጋሽ ተጫነ ጆብሬ መኮንን ሃሳብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ይሰራል።የራበው ታማኝ ውሻ ጎን ሲርቀው ማጀት ማማተሩ ወይም ጎረቤት ሄዶ ተከርቸም መሆኑ መች ይቀራል?

ስለዚህ ዘመቻችን ድሕነት በሚባል ሁነኛ ጠላት ላይ ቢሆን ይሻላል።ጠብመንጃው ስራ ይባላል።ስራ ሰውን ሳይሆን እንጀራን ያበላል።

ይቆየን!


*.ወለፈንድነት___Paradox ለሚለው ቃል አንፃራዊ ፍች እና ግራ አጋቢ፣የሚያምታታ
ማለት ነው።

**.ግጥሙ ፦ሰውነት ባዕዳ ነው፤
ይገለባበጣል
አብሽሪ ቲኑየ፤
የአንች ቀን ይመጣል"

ከሚለው የትህትና መኩሪያ ግጥም ቃላት ብቻ ተቀይረው የተወሰደ ነው።



ሃሳባችሁን ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ልባሽ አለበሱን

(በታመነ መንግስቴ)

ከአፄ ፋሲል በፊት፤እንደዋዛ አሰሱን
በምኒልክ ዘመን፤ዳግመኛ ከለሱን
ፋሽስት ሆኑና፤ያው ትንሽ ቀመሱን
አሁን ሰምሮላቸው፤ ልባሽ አለበሱን።

ግጥሙ ግጥም ነው።ተውት!

የዛሬው ጨዋታችን በአንዲት የደቡባዊ አፍሪካ አገር ላይ የተሰራን ትዕይንተ ዶሴ(Documentary Film) መሰረት አድርጎ የተዋዛ ነው።

ርዕሱ በፈረንጅ አፍ"T_Shirt Travels"ይላል።በእኛ አፍ መተርጎሙ አስፈላጊ አልመሰለኝም።ለነገሩ መተርጎሙም ከባድ ነው።ብዙዎቹን የእንግሊዝኛ ቃላት በማደንቀው የአማርኛ ቋንቋ ለመክተብ ስታትር እንዲህ ተራራ የሆኑ ቃላት ይገጥማሉ።"Shirt"ን "ካናቴራ" ማለት ባይሳነኝም "T"ን "ቲ"ማለት ተገቢ አይመስለኝም።ነገሩ ከነገሬ ጋር ስለሚገናኝ እንጅ በቋንቋ ላይ አንድ ቀን እንደምንጨዋወት አልዘነጋሁኝም(አትርሱብኝና ቋንቋ መደባለቅ ለማይምነት መቅረብ መሆኑን በሆነ አፍታ አሳያችሗለሁ)!

እንዳልኳችሁ ትዕይንተ ዶሴው የተሰራው በደቡባዊት አፍሪካ ውስጥ ባለች አንድ እባብ የመሰለ ካርታ ያላት አገር ነው።በልጀነታችን ከምንሰማቸው አስቂኝ ቀልዶች መካከል የሆነ ተማሪ ዋና ከተማዋን ሲጠራ "ልዑል ካሳ" ማለቱ ነበር።ለስሟ የቀረበ መጠሪያ ያለው ወንዝ ያጠጣታል።ምናልባትም የአፍሪካ ትልቁ ፏፏቴ በዚያ ይገኛል።ስሟን መንገር "አታውቁም"ማለት ይሆንብኛል😀

አገሪቱና ዋና ከተማዋ ብሎም ወንዟ ማን እንደሆኑ እየገመታችሁ መጨዋወታችንን እንቀጥልማ__

"ኧረ እርየ እርየ _ኧረ እርየው መላ
ጎጃም ተገበየ__ፍቅርና ተድላ"ይላል ቆምጫጫው ጎጀ።
(ተነገሬ ጋር ምን ያገናኘዋል? ምንም😀)
ትዕይንተ ዶሴው ሲጠቃለል"አፍሪካ ማለት ነፃነቷን መልሳ በማጣት ላይ ያለች የምዕራቡም የምስራቁም ዐለም የቆሻሻ ማራገፊያ ናት።"ማለት ይመስለኛል።

ጉድ እኮ ነው ሰዎቸ__
አሜሪካዊያን ለብሰውትም፣አጥበውትም፣ጥለውትም ፣አንስተውትም፣መልሰው ጥለውትም ቤት እያጣበበ ያስቸገራቸውን "ውራጅ"ጨርቅ በየ መንገዱ"ስጡን"ለሚሏቸው ሰዎች ይቸሯቸዋል።በትዕይንተ ዶሴው ላይ እንደሚሉት"ምንም ልብስ ለሌላቸው ሰዎች የሚሰጥ፣ለአሜሪካ የጦር ኃይል በነፃ የሚለገስ "ይመስላቸዋል።በአፍሪካ ምድር ሁነኛ የገንዘብ መከመሪያ መሆኑን ማን ይነግራቸዋል?

የማወጋው ወግ ግር ያላችሁ በስድስት ኪሎና አካባቢዋ፣በመገናኛ መንገድ፣በሜክሲኮ አካባቢ፣በዚህ በአራዳ መንደር(Piazza)"በረረች፣በረረች፣ሱሪ በሞቶ፣ጫማ በሞቶ "የሚሉ ቀማኞችን ታውቃላችሁ? በቃ ይሄንን ነው የምላችሁ።

እናንተ ሆየ(ራሴ እንዴት እንደተንገላታሁ ልንገራችሁ።ከቴስ ከጎዳና ገዝቸ መሰላችሁ? ከመርካቶ ዘግኘ እኮ ነው ጉድ የሆንኩላችሁ።ተምወደው ተወዳጀ ጋር አንድ መልከ መልካም ኮት_Jacket_[ኮት =ኩታ__ይችንም አንድ ቀን እናወጋታለን] ገዛሁላችሁ።ተዚያማ ሲያቀብጠኝ በምናምን ቀኑ አጠብኩላችሁ።ተዚያ ቀለሙ ምን ሆነ ልበላችሉ? ነጭ፣ቀይ፣ቢጫ፣ጥቁር፣የማላውቀው በቃ ጉድ ሆንኩላችሁ።)

"ዋጋው በጣም ተራ ሆኖ ነው" ታላችሁ።አባ ይሙት ትሳሳታላችሁ።ማነው 900(ዘጠኝ መቶ) ብርን ተራ ነው ያላችሁ? ይሄ ብር የብዙ አዲስ አበቤ ተቋማት ጥበቃዎች ደመዎዝ መሆኑን ለማታውቁ ልንገራችሁ።አንዳንዶቹ ግን ሲበዛባቸው ነው(ስለነሱም አንድ ቀን እናወጋለን😁)

ተዚህ ጉደኛ ኮት በሗላ ልብስ ማመን ተሳነኝ(በቃ ጥቁር ሱሪ ገዝቸ ከማጠብ ወያኔ ተሸንፋለች፣መቀሌም አትገባም የሚለውን የባጫ በደሌ😁 መግለጫ ማመን ቀለለኝ።)

ሰዎቸ እየቀለድኩ አይደለም።"ቀልድና ቅዘን"አገራችንን ሲያበላሽ እያየሁ አልቀልድም።መራሄ መንግስት ዐቢይ አህመድ በመደመር መፅሐፋቸው ገጽ_66 ላይ፦
"ብዙ በጭቆና ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች የጭቆናቸውን ሕመም የሚቋቋሙትና ኑሯቸውን የሚያስቀጥሉት ራሳቸውን በቀልድ እየደለሉ ነው።"ይላሉ።እስማማለሁ።

ካስፈለገ"ዐለምን ለመለወጥ የሚሰሩ ሰዎች አይቀልዱም።እነማን ናቸው ዐለምን የለወጧት
ታውቃለህ? ስሚዝ አዳምስ፣ሪካርዶ፣ካርል ማርክስ እነዚህ ዓለማዊ ፈላስፋዎች ናቸው።እና አይቀልዱም።ያለ ጩኸት ዝም ብለው ዐለምን ይለውጣሉ።"የሚለንን የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ ላይ የተሳለ ገጸ ባህርይ እጨምርላችሗለሁ።እናም 'ቀልድና ንቅዘት(ቅዘን ላለማለት) አገር ያበላሻል'እላችሗለሁ።

ጨዋታችን እንደ አገሬ ቦተሊካ የተሳከረበት እንዳይሆን እንዲህ እንጠቅልለውማ

"ዘመነ ሉላዊነት ብዙ ሕዝቦችን እያገለለ፣ዳር እየጣለ እና ካላቸው ነገር እየነጠለ ነው"ሲሉ በቁጭት የሚናገሩት የ"T_Shirt Travels" ትዕይንተ ዶሴ ቃለ መጠይቅ ተደራጊ ኡርባን ጆሃንሰን ናቸው።እሳቸው የUNICEF የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ሃላፊ እንደሆኑ ልብ ይሏል።

በዚሁ ትዕይንት ውስጥ እንግዳ የሆኑ አንዲት ሳተና ሴት አፍሪካዊትም"ነፃ ገበያ ነፃ ገበያ ይላሉ(ምዕራባዊያንን ነው) ግን ነፃው ገበያ ለማን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ።

ለዚህ ነው የአፍራካ ነፃነት ከብዙ አስርት ዐመታት በሗላም አጠራጣሪ የሆነው።ዛሬም ዳግማዊ ኃይለሥላሴ፣ዳግማዊ ኩዋሚ ንኩርማህ፣ዳግማዊ ከተማ ይፍሩ፣ዳግማዊ ጁሊየስ ኒሬሬ፣ዳግማዊ ጸጋየ ገብረ መድኅን ያስፈልጋሉ።"አፍሪካ ቀዳሚውን የሰው ልጅ ስልጣኔ በዐባይ ሸለቆ ላይ የጀመረች የካም እና ኩሽ ምድር፣በሗላም እናንተ ባሪያ እያደረጋችሁ እስከምትፈነግሉት ታላቁ ቄስ ዮሐንስ(Priester John) የነገሰለት፣መንሳ ሙሳ በቲንቡክቱ ቀየ ወርቅ የነሰነሰለት፣ለሾና ሕዝብ አገሩን "ታላቋ" ዚምባቡየ እያለ ታሪክ የሰገደለት ኃያል ዘውግ የሚኖርባት የምድር ዕምብርት ናት እንዲሉ።

አፍሪካና አፍሪካዊያን(ኢትዮጵያዊያንም መጠነኛ ኩራታችንን ተወት አድርገን እንደ አፍሪካዊ ማሰብ አለብን።ከሰሞኑ ስማቸውን የዘነጋሁት ምሁር'ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ቅኝ ያልተገዛች አገር ምናምን ስንልኮ በተገዙት የአፍሪካ ወገኖቻችን ቁስል ላይ እንጨት እየሰደድን ነው'ያሉበትን ንግግራቸው በጣም ወድጀዋለሁ።በተቻለን መጠን አፍሪካን አክብረን ልንመራት ይገባል።ታላቁ ንጉስ ቀኃሥ በመንግስታቱ ማህበርና የተለያዩ አገሮች ዞረው ዞረው በመጨረሻ እንደማይሆን ሲረዱ "የአፍሪካ አባት"መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም።)

ስለሆነም አፍሪካና አፍሪካዊያን በሚያኮራው ማንነታችን ሊያሳፍሩን ቢጥሩም ልናፍርላቸው ፈፅሞ አይገባም።ልባሻቸውን እና በቅንዝር የተሞላ ጥቅስ ያጥለቀለቀው ሹራባቸውን አውልቀን ጥለን የእኛን ባህላዊ ልብሶች በብዛት በማምረት መልበስ እንችላለን።

እኛን የጎደለን ስነ ልቦናዊ ብስለት ነው።እንመልከት፣እናንብብ፣እንጠይቅ፣እምቢ እንበል።
(ኤዲያ ላወጋችሁ ያሰብኩት ብዙ ነበር።አሁን ባስበው ረጅም ጡፍ አታነቡም።ደሞ ይሄ ወንፊት የመሰለ ማህበራዊ መገናኛም ተረዘመ ያፈሰዋል።ዴሞ "ነገር ቢያበዙት በአህያ አይጫንም"ና ለዛሬው ይበቃናል።ትዕይንተ ዶሴውን ተመልከቱት፣የአገሪቱን፣የዋና ከተማዋንና የወንዙን ስም አሁኑኑ ምንም ነገር ሳታዩ እዚሁ ላይ ገምቱና ከሃሳቦቻችሁ ጋር በተለመዱት አድራሻዎቸ ላኩልኝ!
የምወዳችሁ ነኝ!)


የሻታችሁን ሁሉ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ@Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
የዛሬ ዓመት ገደማ የተከተበ___

'ጉራ ብቻ'
(በታመነ መንግስቴ)

ያው የማከብረው ወዳጀ መምህር ሀብታሙ አለማየሁ አንድ ማስፈንጠሪያ(Link) ላከልኝ።Egypt Independant የተሰኘ ገፀ ድር ጉራ ተሸክሟል።"ኢትዮጵያ እና ግብፅ ጦርነት ቢገጥሙ ማን ያሸንፋል?" ዓይነት የሰይጣን ንፅፅር ውስጥ ለመግባት ሲንደረደር የአገሩ ርዕሰ ብሔር አብደል ፈታህ አል ሲሲ የአየር ኃይል መኮነኖቻቸውን "ለየትኛውም የአገር ውስጥ ወይም የድንበር ባሻገር ተልዕኮ ተዘጋጁ"እያሉ ማሟሟቃቸውን ወሽክቷል።

ይቀጥልና የግብፁ ውጭ ጉዳይ ምሉክ ሳሚ ሽኩሪ ስለ እኛው አቻቸው አቶ ገዱ ዓረፍተ ነገሮች"ጠብ አጫሪነትና"እና "አበሳጭነት" መናገራቸውን ፅፏል።ከዚያም ከዓለም ዐቀፉ የጦር መሳሪያ ሃይል ድረገፅ አገኘሁት ያለውን የኢትዮጵያና ግብፅ ንፅፅሮሽ ያስቀምጣል።ለአብነት፦

ሀ.የግብፅ ዓለም ዓቀፍ የጦር አቅም ዘጠነኛ ሲሆን የኢትዮጵያ 60ኛ ተብሏል።

ሁ.የግብፅ ዓመታዊ የጦር ኃይል ገንዘብ ድልድል(በጀት) 11.2 ትዕልፊት(ቢሊዮን) ሆኖ የኢትዮጵያው 350 አዕላፍ(ሚሊዮን) ተገምቷል።

ሂ.የግብፅ ወታደሮች ቁጥር 920ሺ ተገምተው የእኛዎቹ 160ሺ ላይ ተቀምጠዋል።

እንግዲህ ነፃነትን ለ2ሺህ ዓመታት ተነፍጋ በቱርክ፣እንግሊዝ፣ሮማ፣ፋርስ፣እና ኢትዮጵያ ስትገዛ በኖረችውና ነፃነትን በማታውቀው አገረ ግብፅ ያለ የሚመስለው 'Egypt Indepndant' የፃፈውን እንመነውና ወደ እኛ ጉዳዮች እንምጣ፦

'ከነገራችን ጋር' የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ምሉክ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የያዙት መንገድ አይከፋም።ግብፅን እንደማንፈራትና በተለይ በሁለት እጆቿ ልታፍስ መቃጣቷን መቃወማቸው ያስመሰግናቸዋል።_ ሰውየው ደመ ሞቃት ስለመሆናቸው ራሳቸው ለዘመን መፅሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ውስጥ አንብቤያለሁ።

ቢሆንም ከዘመን አይሽሬው የኢትዮጵያ ላዕከ መንግስት(Diplomat) አክሊሉ ሃብተወልድ ጋር የሚነፃፀር ብልጠት ያስፈልጋል።አክሊሉ በማስታወሻቸው እንደፃፉልን ኤርትራን ለማስመለስ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ረፍት አልባ ሆነው ለህመም ሳይቀር ተዳርገዋል።የዚያኔ ኢትዮጵያን በስም እንኳ በደንብ ከማያውቋት አገራት መሪዎች ጋር በፈጠሩት መልካም ግንኙነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኤርትራን ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል ደግፈው እጅ እንዲያወጡልን አድርገዋቸዋል።

ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ዛሬ "የጥቁር እንቁ" የምንለውን የጋምቤላ ምድር ወደ እናት አገሩ የመለሱት በጥበብ ነው።ኦጋዴንን፣የባቡሩን ባለቤትነት፣ ኢትዮጵያን ራሷን ያስረከቡን በከፍተኛ የተግባቦት ብቃት ነው።ከእነ አቶ ገዱ ይሄ እና ከዚህ በላይ ይጠበቃል።

የእኛ ትውልድ ሃውልት የህዳሴ ግድብ ነው።ግብፅ "ጦርነት" የምትለው 'ጉራ ብቻ' ነው።ምክንያቱም ዘመኑ አይፈቅድማ! የምወደው ነገራተሰብ(ጋዜጠኛ) ዮርዳኖስ አበበ እንደሚለው "በዚህ ዘመን በአንድ ጦርነት የሚመጣን ኪሳራ 20 ዓመት አይመልሰውም።" ጦርነቱ ከሆነም እንዲሁ በጉራ ደረጃ እና የአገር ውስጥ ባንዳዎቻችንን በመመልመል ነው።ስለዚህ ለጊዜው በአጥንት መናከሱን ትተን ወደ ጅቡ መጮህ አለብን።

ጅቡ ብዙ ነው።እነ አሜሪካም የእኛን ጉዳይ ለራሳቸው ይፈልጉታል።ያ ታላቅ ሰው-አክሊሉ ሃብቴ እንደፃፉት"ሁሉም ለየራሱ ጥቅም እንጅ በፖለቲካ 'ጀስቲስ'(ፍትሕ) እንደሌለ የታወቀ ነው።"

በዚህም ተባለ በዚያ እኛ መራብ አንፈልግም።ግዮን ኢትዮጵያን "ይከብ" ዘንድ በአምላኩ ታዝዟል።አሁንም ጋሽ አክሊሉ ሃብቴ ኦጋዴንን ሊነጥቋቸው ለቋመጡ እንግሊዞች"ሳንዋጋና ሳንሸነፍ ልትወስዱት አትችሉም!" እንዳሏቸው እኛም "ሳንዋጋና ሳንሸነፍ የዓባይን ግድብ ውሃ ሙሌት ልትከለክሉን አትችሉም!" ብለናል።

"ጉራ ብቻ'' የለቀቀብኝን ገፀ ድር ማስፈንጠሪያ እነሆ፦https://egyptindependent.com/is-an-egypt-ethiopia-war-an-option-a-comparison-between-the-egyptian-and-ethiopian-armies/
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
መንገሪያ!


ከነገ ቅዳሜ _ሐምሌ 3 /2013 ዓ.ም ጀምሮ በእዚህ ቤት ይተላለፍ የነበረው የደብዳቤና ጦማር ቀን እንደተጠበቀ ሆኖ ከዘ_ፍጥረት እስከ ምፅዓት ከኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ጋር የተቋጠረው የዓባይ ጉዳይ የሚዳሰስበት "የዓባይ ነገር"የተሰኘ ዝግጅት እንደምንጀምር እናሳውቃለን።

እናንተ የቤቱ ሰዎችም በዚህ አምድ ስር ታላቁን ወንዝና ተፋሰሱን ከየ አንፃሩ እየተመለከታችሁ መሶባችንን ሙሉ እንድታደርጉ ትለመናላችሁ!


ሐምሌ_2_ቀን_2013 ዓ.ም

ታመነ መንግስቴ ፤አዲስ አበባ _ኢትዮጵያ



የሻታችሁን ሁሉ፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
#.. እመ.... #

ያደኩበት ቀበሌ.. የአባቴን ጠቦቶች ለቅሞ የወዳጆቼን ሀገር ሊረሽን ወረደ ፡፡
አዬ እመብርሃን....
እዛም ስለት አለብሽ ፡ እዚም ፀሎት አለብሽ ... ታቦት ስመው ከወጡ ልጆችሽ መሃል ሁለት ቡድን እንጂ ሁለት አምላክ የለም አይደል ?
እንግዲህ ለማን ትለመኛለሽ ፡ እንግዲህ ለማን ትጠየቂያለሽ .....
ሳይነጋ መሸብን ፡፡
ሰሜን ሊጀግን ፡ ደቡብ ሊረሽን ፡ ምስራቅ ሊፋለም ይወርዳል ፡፡ ሰው ሳያንስ እንስሶች በካራ ስለት ያልቃሉ፡፡
በለምለም ሳር መማለድ ቀረ ፡፡ ደናቁርትን የሚታገል ህዝብ ፊት ለስርየት የሚታረድ ቄስ ጠፋ ፡፡ ለሽንገላ የቆመ ሼህ ናፈቀን ፡፡ በቃ... ሁሉም ስለ ጎጡ ፆመ ፡፡

...ዝንት ዓለም ዱላ ፡ ዝንት ዓለም ካራ ፡፡
የመቆም ጥቅም ሳይገባን የምንወድቅለት ሀገር ይናፍቀናል ፡፡
አየሽ ድንግል... ታመን አልጨረስንም ፡ ዘፍነን አልታደስንም ፡፡
" በሉ እንሂድ !! " .... እንላለን
" እንውጋቸው !! እንበላቸው !! " አይደርስብን ዘመን የለም ፡፡ ይኸው... ይመጣል ያልነው ምፅዓት በኛ ክፋት ተቀደመ ፡፡ አፈ ሙዝ እሩምታው እስኪንጠፈጠፍ ብንጀግንም.. አሻግረሽ የነገን ለቅሶ አሳዪን .... በቃ በይን እመብርሃን ፡፡ በቃን............ ሰው ማስታረቅ ትቷል ፡ ሰው መሸነፍ ትቷል ፡፡ በቃን....
አምና ለሳቀው ብላቴ .. ፡
አምና ለሳቀው ወታደር.. ... ለሀገሬው ... ለተገፋው ፡ ለሚገፋው!! ... ይማማር ዘንድ ፊደል ሁነሽ ድረሽለት ፡፡
በቃ በይን እመብርሐን ፡፡
የትግራይ ወዳጆቼ... ሳሚ ፡ ሀዱሽ ፡ ገሬ ፡ ክብሮም ፡ ኤልሳ ፡ አንድ ቀን በደህናው ቀን እንገናኛለን ፡፡
#ጌታነህ ደጉ
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
"ውድ አንባብያን!

"ክረምት እና ንባብ" በሚል መሪ ቃል ዋልያ ኢቨንትስ ከሐምሌ 15_ነሀሴ 10 ድረስ የሚቆይ የመጻሕፍት አውደ ርእይ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።

በዚህ መሰናዶ ነባርና አዳዲስ መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ ከመገኘቱ በተጨማሪ በእያንዳንዱ ውሎ/ምሽት ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶች ይከናወናሉ።

ከእነዚህ ክንውኖች አንዱ አንጋፋ ደራስያን ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ነው። ስለሆነም ሐምሌ 29:2013 ዓ.ም በዕለተ ሐሙስ ከአስራ አንድ ሰዓት ጀምሮ ደራሲ አንዳርጌ መስፍን ተጋባዥ እንግዳ ሆነው የሕይወት ልምዳቸውን ያካፍላሉ።

ኑ! ከ "ጥቁር ደም" እና ከሌሎችም ልቦለዶች ደራሲ ጋር ማለፊያ ወግ እናውጋ!

አድራሻ:- አራት ኪሎ ከቱሪስት ጀርባ ኢክላስ ህንጻ። ለበለጠ መረጃ 0966252525::"

ይሄ መድረክ ከተዓምር በታች ያለ ተዓምር ነው ሰዎቸ!

እኔ ዕድሜ ለባምላኩ ገዛኸኝ ይሁንና ሁለት ምሽቶችን ታድሜ እየተፈወስኩ ተመልሻለሁ።

ነገም አብራችሁን ማዝገም ለምትሹ
መልዕክቶቻችሁን፦

በጓዳ @GazetawBot ላይ

ለእኔ ለአባወራው @Tamen1234 እያላችሁ ላኩልኝ።

የቤታችንን በር @Gazetaw አንኳኩ፤ክፍት ናት!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
የኔ "ሰው"ናትናኤል ዲበና

(በታመነ መንግስቴ)

ልጁ በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ የሕትመትና በይነ መረብ(Print and Web) ጋዜጠኝነትን ይማራል።

መቼስ አስተዋይነት፣አድማጭነት፣ቅንነት እና ርቱዕ አንደበት የእሱ ናቸው።

ከናቲነት ጋር አብሮ መስራት ሲመቸኝ!አይኮሰኩስም።ጥንቅቅ ያለ ቀጫጫ ነው😁

አሁን Etv ላይ"ነገን ዛሬ"በሚሰኝ የወጣቶች ዝግጅት አፍታ እንግዳ ሆኖ አየሁት።ደስስስ አለኝ።

በዕየለቱ ሳይረግጣት በማይውላት "አረንጓዴ ሰው ይገኝባታል" በሚባልላት አራት ኪሎ ሲኳትን ምስል ቀራጩ አንስቶታል።

ሌላዋ ናቲየ የሚወዳት ቦታ ስድስት ኪሎ አንበሳ ግቢ ጋ ያለችዋ ፒፕሲ የጋዜጣ እና መፅሐፍ ማንበቢያ እንዲሁም መሸጫ ጓዳ ናት።እዚያ ናቲነትን መፈለግ አያከስርም።

ይሄ በብዙኃን መገናኛ ዕውቀቱ(ስለ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንና ባለሙያዎቻቸው ከዊኪፒዲያ በላይ አምኘ የምጠይቀውና የጠየኩትን የሚሰጠኝ ትጉህ ተወዳጀ ነው)የሚያስደምመኝ የዘመኔ ስጦታ በቃለ መጠይቁ አፍታ፦

"በሚዲያ ውስጥ ገብቶ እንደ ጥላ የሚያልፍ ጋዜጠኛ መሆን አልፈልግም"ብሏል።

በአስር ጣቴ ፈርሜ አምነዋለሁ።ቸር ይግጠመው!


የቀጫጫውን የEtv ቆይታ ለመታደም https://www.facebook.com/100003435445465/posts/3127578597366624/ ላይ ግቡ።

ወደ መሃል አለላችሁ!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
ወደ ቤቴ ኑ!

ታመነ መንግስቴ ውቤ ነኝ።

ጊዜ፣ቦታ እና ሁኔታ ተገጣጥመው የምወደውን ሞያ ጋዜጠኝነትን ወርቅ ከሸለምኩት በሗላ ከጀግኖቹ የአገሬ ልጆች ጋር በጦር ግንባር ተገኝቻለሁ።

ይህ ጦርነት ከአስር ዓመታት በሗላ " አደይ መቀሌ"፣"እናቴ አዲስ አበባ" የሚሉ ዘፈኖች እንደሚደመጡበት ሃቅ ነው።

እስከዚያ ግን የሞት አቃቂር እያየን አለን።

ለሁሉም ከሸዋ ጣርማ በር እስከ ወሎ ጫፍ ዋጃ_ጥሙጋ፣ከሰቲት ሁመራዋ ማይጋባ እስከ አዲ አርቃይ ተጎራባች ጨው በር በጀማሪ ጋዜጠኛ ዐይን ያየሁትን፣የሰማሁትን፣ቀጥሎ በሚመጡ ጊዚያት በፈጠርኳቸው ግንኙነቶች የምፈትሻቸውን ሃቆች ለመቋደስ ወደ #እዚህ ቤት https://t.me/Gazetaw ብቅ በሉ።

በተለይ በፌስቡክ በኩል የጓደኝነት ጥያቄያችሁን ያልመለስኩላችሁ ወዳጆቸ ቤቴን ብታንኳኳት በሩስያ ሰራሹ ቴሌግራም ጥዑም ሃሳቦችን እንጋራለን።


እናም እዚህ ቤት https://t.me/Gazetaw ብላችሁ አንኳኩ።ክፍት ናት።

ታመነ መንግስቴ ከወሎ ግንባር!
Forwarded from Tamene Mengste Wube (ታመነ መንግስቴ ውቤ)
መርሳ እና ወልድያ ነፃ የወጡ ዕለት

(ከጦር ግንባር ዘጋቢው ታመነ መንግስቴ ማስታወሻ የተቀነጨበ)

ጋዜጠኝነትን እንደ እንጀራ ከቆጠርከው የተፈጨ አሸዋ የተቀላቀለበት እንጀራ ነው።እየጣመህ ይሰብርሃል።ሞያው ፍፁማዊ ነፃነት ይፈልጋል።በዚያው ልክ የባለሞያው ፍፁማዊ ምክንያታዊነት ፍቱን ነው።
እንዲህ ከሆነ ጋዜጠኝነት በፍቅር የሚያሰክር ሸሞንሟና ሞያ ቢሰኝ አልበዛበትም።

ዛሬ ሲነጋጋ ወደ ውጫሌ፣ውርጌሳ እና መርሳ ሄደን እኒያን ወሎየዎች ማየት እንዳለብን ሃሳብ አመጣሁ።ብቸኛው በእኔ ውሳኔ የሆነ ነገር ነው።ላለፉት 14 ቀናት የምሰራው ሁሉ በአለቆቸ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሠረተ ነበር።

ትናንት ማታ አሳስቄ ተሳካልኝ...!

ደሴ የግዷን ከ38 ቀናት የእብዱ ውሻ ንክሻ ዱካኳ እየነቃች ነው።የሚያሳዝነው ቀድማ ከከፈተቻቸው የአገልግሎት ዘርፎቿ ጫት ቤትና መጠጥ ቤት ይፈጥናሉ።"ዐለም ለምኔ"ብለው የሚቅሙት ማኘክ ጀምረዋል።ከሳምንት በፊት ደሴ _ፒያሳ ያገኘሗቸው የዕድሜ ባለሃብት"የአሁኑ ትውልድ ጫትን እንደ ባህል አደረገው"እያሉ ሲቆጩ ነበር።ብዙ ወሎየዎች በጦርነቱ መደፈራቸውን ይናገሩና ሲጨርሱ"ጫቱን ትታችሁ ለሕልውናችሁ ታገሉ"ይላሉ።

ደሴን ትተናት ወደ ሐይቅ ነዳን።ሐይቅን አልፈናት ሚሌ ወንዝ ላይ ነን።እዚህ ሐይቅን መዲናው ያደረገው የተሁለደሬ ወረዳ ያልቅና ባለ ቅኝቱ አምባሰል ይጀምራል።አምባሰል ወሎየዎቹን በምልዓት ከሚወክሉ አካባቢዎች አንዱ ነው።ዋና ከተማው ያው _ውጫሌ ናት።ውጫሌ በኢትዮጵያ ታሪክ ያላት ቦታ ከሰማይ በታች የሚገኝ ተዐምር ነው።

የኢትዮጵያ ታሪክ ሀሁ የማይገባው ሁሉ አድዋን ያውቀዋል።አድዋ ጓደኛየ ሳሙኤል ታዴ"የሰው ልጆች ድል"የሚለውን የጥቁር ሕዝብ ጀብዱ የምትመሰክር ምድር ናት።እናም ስለ አድዋ ጦርነት፣ድልና ነፃነት ለማውጋት የ1881ን(?) የውጫሌ ውል መንተራስ ግድ ነው።

ያኔ የሸዋው ንጉስ ዳግማዊ ምኒልክ ጣሊያን ወደ መሐል አገር እየገሰገሰ መሆኑን ተረዱ።እንደገባቸው ልጓም ማስያዣ አንድ ውል መፈራረም ነበረባቸው።ይህም ይሆን ዘንድ ከጊዜው የኢጣሊያ መንግስት ተላላኪ ፔትሮ አንቶሎኒ ጋር እዚህ አለንበት ቀየ አካባቢ "ይስማ ንጉስ"ተብሎ ተፈራረሙ።

የውጫሌ ውል ትርጉመ ብዙ ነው።በተለይ አንቀፅ ሶስት እና አንቀፅ 17 ከዚያ ወዲህ በተፈጠረችው ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ነጭና ጥቁር ነጥብ አሳርፈዋል።

አንቀፅ ሶስት የአሁኗን ኤርትራ የዚያን ጊዜዋን ሃማሴን ከኢትዮጵያ አካል ላይ የቆረጠ ቃል አለበት ተብሎ ይታመናል።እኔ እና ትውልዴ የተማርንበት የ10ኛ ብሎም 12ኛ ክፍል መፅሐፍ እዚህ ጉዳይ ላይ በጉልህ ያሰምራል።

አንቀፅ 17ን እንኳን እኛ ሰው በሙሉ ያውቀዋል።ይህ አንቀፅ የጫረው እሳት ተቀጣጥሎ ጥቁር ሕዝቦችን በተለየ፤የሰው ልጆችን ባጠቃላይ ባለድል አድርጓል።

ለሁሉም ለሁሉም ከሌላው ጣሊያን ጋር እየተዋጋን አሁን ውጫሌ ነን።

በግራ በኩል "ውጫሌ 17"የሚሰኝ ትምህርት ቤት መግቢያው ይታየኛል።አደነቅሗቸው።ታሪክን እንዲህ ማስታወስ መቸስ ልባምነት ነው።ለነገሩ መኪናችንን የሚዘውራት ኃይሌም"...ውጫሌ እኮ ጣይቱ እምቢ ያለችበት ቦታ ነው"ሲለን ነበር።ሃቅ አለው።እቴጌይቱ ያንን መናኛ ፈረንጅ"...እኔ ሴት ነኝ።ጦርነት አልወድም።ግን የአገሬን በጠላት እጅ መውደቅ ከማይ ጦርነትን እመርጣለሁ።ከፈለግህ ጦርነቱን የዛሬ ሳምንት አድርገው።እጠብቅሃለሁ"ያሉት እዚህ ነበር።

የዛሬ ረፋዷ ውጫሌ ከእብዱ ውሻ ወያኔ እጅ ነፃ ሆናለች።እስከ ትናንት ታህሳስ 8 ቀን 2014 ዓ.ም እዚህ እንደነበሩ ያገኘናቸው ባላገሮች ነገሩን።መቸስ በመንደሩ ያልተተኮሰ የጦር መሳሪያ የለም።ቀየው ደቋል።ሰዎቹ ደንግጠዋል።ዝምታ ላይ ናቸው።

እኛ በመገስገስ ላይ ነን።የወሎ ምድር የተራራ እና ሸንተረር አወደ ርዕይ ይመስላል።ልቅረፅ ቢል የመቅረፀ ምስል(ካሜራ) ባለሞያ የሚያደክሙ ተራሮች ይታያሉ።ውርጌሳን እንዳለፍን ወደ ዝነኛዋ ኒኒ በር ተጠጋን።

ኒኒ በርን ደሴ ሆኘ ከራሴ ስም በላይ ደጋግሜ ስሟን አድምጫለሁ።ሲበዛ ስልታዊ ቦታ ናት።ይህችን ማነቂያ የያዘ ተዋጊ ልዩ ብልሃት አያስፈልገውም።ተራራ ሸንተረሩ ጠላትን ተዋግቶ አድክሞ ያቀብለዋል።በዓሉ ግርማ በኦሮማይ የናቅፋን ተራሮች"ገዳይ መሬት...እግዜር ተበሳጭቶ በክርኑ የደቆሳቸው"እያለ እንደፃፈው ኒኒ በርም እንዲያ ናት።

ከሁለት አንገተ መለሎ ኮረብታዎች መሃል እንደ ቀዳዳ ሆና የተፈጠረችው ኒኒ ልባችን የጓጓላትን መርሳ ከተማ ለማየት ማጮለቂያ ናት።ይህችው የምድር ትዕንግርት የመዓት ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያት ወንድሞቸን ደም የማገች፣አጥንት የሳገች ቦታ ናት።ቢያንስ ላለፉት ሰባትና ስምንት ቀናት ቅልጥ ያለ ጦርነት ይካሄድባት ነበር።ደሴ አኪም ቤት(?) በገፍ እየመጡ ቁስላቸው ሲያሳቅቀኝ የነበሩ አዳጊ ወጣቶች የረገፉት እሷ ዘንድ ሳይሆን አይቀርም።

ሳይሆን ባይቀርም ልባችን መርሳ ስለሆነ እና እንደ እሷ ያሉ"ገዳይ መሬቶች"ብዙ ስለሆኑ መኪናችንን ነዳናት።መርሳም ገባን።ኮከብ የሌለባት አረንጓዴ፣ብጫ ቀይ ሰንደቃችን እንዳስከበረችን አለች።አሁን በነፃዋ የሰሜን ወሎ ፈርጥ መርሳ ከተማ በኩራት መኪናችን ላይ ሆና መውለብለብ ጀምራለች።ሕዝቡ ቤቱን ትቶ ጎዳና ወጥቷል።ሲያየን ፍቅር ያቅበጠብጠዋል።የነፃነት ጣዕም ያንቀጠቅጠዋል።የደስታ ስሜት ይንጠዋል።

ረፋድ አምስት ሰዓት ገደማ ሆነ።መሐል መርሳ መነሐሪያው ፊት ለፊት ተከስተናል።ወሎየዎቹ በደስታ ስካር ላይ ናቸው።ፍፁም ሳይኖራቸው ፍፁም ይለግሱን ጀመር።ዐይኔን በእያቅጣጫው እየወረወርኩት ነው።መከላከያው መኪናው ላይ ሆኖ እንጀራ በሚጥሚጣ ይበላል።የሚያበሉት ስድስት ወር ወያኔ የበላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው።እኛ መኪናችን ውስጥ ሳለን የብርቱካን በረዶ ወረደብን።በቃ ያዘንቡብናል።በመኪናችን መስኮት የተለገሱን ብርቱካኖች እንደ ነፃነት ጥዑም ነበሩ።ዐይኔ በጋዜጠኝነት መነፅር ይህንን ፍፁማዊ የሕዝብ ደስታ ስላየች በፍስሐ ተጥለቅልቄያለሁ።

አሁን ከመኪናችን መውረድ አለብን።የምንሰራበት ማኅበራዊ መገናኛ ግርግር ይወዳል።ቡና ቤተንዋይ(Buna Bank) መርሳ ቅርንጫፍን ለምስል መቅረጫ(Camera)ችን ዐይን ሰጥተን የኒያን ደጋግ ወሎየዎች እየየ ልንሰማ ነው።በመሐል እንዲህ ሆነ።

"ጁንታ ጁንታ"ተባለ።የተማረከ የእብዱ ውሻ ወያኔ ታጋይ አለ።ምድረ ወታደር፣የከተማ ነዋሪ ምናልባትም መለያ የቀየረ ሰላይ ሁላ ከቦታል።አንድ" መቶ አለቃ ነኝ "ያለን የመከላከያ ሰራዊት አባል መቅረጸ ምስልና የድምፅ ማጉያ(Microphone) እንደያዝን ሲያይ በትዕዛዝ መልክ፦
"ኑ ቃለ መጠይቅ አድርጉለት" አለን።ያኔ በደስታ ሰክሬ ስለነበር እንዳለው ለማድረግ ተዘጋጀሁ።አሁን ሳስበው ለካስ በወታደር ቤት ትዕዛዝ እንጅ "እባክህ"ማለት ነውር ነው።


ለሁሉም በዚህ የዘመቻ ጉዞየ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠላትን ተዋጊ ቃለ መጠይቅ ላደርግ ነው።መጀመሪያ ባልደረባየ(ምስል ቀራጩ) "አይዞህ ወንድሞችህ ነን"አለው።

(የወያኔን ምርኮኛ ጉዳይ ይዠ በሁለተኛው ክፍል እመለሳለሁ።ታሪኩ የተፈጸመው ልክ የዛሬ ሁለት ወር ታህሳስ ዘጠኝ ቀን በዋለችው ዕለተ ቅዳሜ ነው!)

t.me/Gazetaw
የብልፅግና ፓርቲና የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል
የብልፅግና ቤተክርስቲያን ምስል ቢጫ፣ሰማያዊና ቀይ ሰዎች እጃቸውን ወደ ላይ ዘርግተው የሚዘሉ ሰዎች አናት ላይ መስቀል ከነ ፈነጠቀው ጸዳሉ ይስተዋላል፡፡ በአንፃሩ የብልፅግና ፓርቲና ሁለት እጆች ተዘርግተው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ሰዎች በሰማየ ሰማያቱ ላይ የፈነጠቀውን የፀሐይ ብርሃን አይተው ሲጨፍሩ ይስተዋላል፡፡ የሁለቱም ቀለማቶች አንድ ዓይነት መሆናቸው ሰማያዊ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት መሆናቸውና ሦስት እጃቸውን ወደላይ አድርገው የሚዘሉ ሰዎች መሆናቸው ዝም ብሎ ገጠመኝ ሊሆን አይችልም እንላለን፡፡ የብልፅግና ቤተክርስቲያን የተጀመረው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን የአዲስ ሃሳብ አፋላቂዎች ንቅናቄ ሲሆን በ1950 እኤአ በሃገረ አሜሪካ በመዳን ቅሪቶች ዘመን የብልፅግና ቤተክርስቲያን ነገረ መለኮት ተጀመረ፡፡ (www.Prosperity church logo)1 ድረ-ገፅ አይተው ትዝብትዎን ያጋሩ፡፡

የብልፅግና ፓርቲና ልዩ ልዩ የኃይማኖት እምነት ተቆማት
የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት (ነገረ መለኮት) አስተምህሮት መሠረት ክርስቲያኖች ደህንነታቸው መጠበቅ አለበት ምክንያቱም መንፈሳዊና አካላዊ ህይወት የማይነጣጠሉና የማይለያዩ ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ አላቸው፡፡ የምዕመናኖች ደህንነታቸው የሚተረጎመው አካላዊ ጤና እና በኢኮኖሚ ብልፅግና ይገለፃል፡፡ የብልጽግና ነገረ መለኮት መምህሮች አትኩሮቱን ለግለሰብ ሥልጣን መስጠት በመንፈሳዊና አካላዊ ጥምረት በጎ ጎን በመገንባት ያሳልፋል፡፡ ክርስቲያኖች በተፈጥሮ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶቸዋል ምክንያቱም ክርስቲያኖች በእግዚአብሄር አምሳያ ስለተፈጠሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ዓለማቸውን በማለማመድ በአካባቢያቸው የሚገኙ ቁስአካላዊ ነገሮች መጠቀም መቻል አለባቸው፡፡ የብልጽግና መንፈሳዊ ትምህርት መሪዎች ያለ አንዳች ፀፀት ኃጢአታችንን እንዲያስተሰርይልን፣ ከበሽታ ደዌን ለመፈወስ፣ ከድህነት አረንቆ ለመላቀቅ፣ ከመንፈሳዊ እርኩስነት ለመንፃት፣ ድህነትና በሽታ በህብረተሰቡ ዘንድ እንደእርግማን ስለሚቆጠር በእምነትና በእውነት ይህን የተሳሳተ አስተሳሰብ መስበር እንችላለን፡፡ ”Prosperity theology teaches that Christians are entitled to well-being and, because spiritual and physical realities are seen as one inseparable reality, interprets well-being as physical health and economic prosperity.[47] Teachers of the doctrine focus on personal empowerment,[48] promoting a positive view of the spirit and body. They maintain that Christians have been given power over creation because they are made in the image of God and teach that positive confession allows Christians to exercise dominion over their souls and material objects around them.[48] Leaders of the movement view the atonement as providing for the alleviation of sickness, poverty, and spiritual corruption;[49] poverty and illness are cast as curses which can be broken by faith and righteous actions.” 2

የዘመናዊ ሽብርተኛነት ታሪካዊ አጀማመር ከፈረንሳይ አብዬት ጋር ይያያዛል፡፡ በዘመኑ የሽብርተኛነት ሥር መሠረቱ መንስዔው ሥልጣኔ አሊያም የባህል ግጭቶች፣ ዓለም አቀፋዊ ትሥሥር፣ ኃይማኖታዊ ግጭቶች፣ የእስራኤልና የፓልስታይን ግጭት፣ አሊያም የራሽያ አፍጋኒስታን መውረር በሃገራት መህል የተከሰቱ ሽብርተኞነት ያካትታል፡፡ የዘመናዊ ሽብርተኛነት በግለሰብ ደረጃ በስብዓናችን ላይ የሚከሰት ብስጭት፣ የመገለል ስሜት፣ አሉታዊ የማንነት ጥያቄ፣ ራስን ማፍቀርና ማምለክ ንዴት እና ወይም የግብረገብነት ፈሪሃ እግዜብሄር ጋር ያለ ግንኙነት መላሸቅ ስሜቶች ይካተታሉ፡፡ በሃገራችን ኃይማኖታዊ ግጭቶች ወደ ዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጀጆኖሳይድ) ተሸጋግሮል፡