.....
30 subscribers
9 photos
3 videos
5 files
3 links
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
ቀን 8 / 4 / 2013 ዓ.ም


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ4ኛ ዙር ከፊታችን ሰኞ ከታህሳስ 12/4/2013 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይፋ አደረገ፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ደሙ በዛሬዉ እለት በሰጡት መግለጫ እንዳሳወቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከሉ የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራዉን በከተማዉ ለማስጀመር በተቀመጠዉ ውሳኔ መሰረት ቀደም ሲል ህዳር 16 የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቸ በክለሳ ትምህርት ውስጥ እንዳልፉ ፣ ህዳር 28 በግል ትምህርት ቤቶች ከ1 ክፍል ጀምሮ እና በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ በሶስት ዙሮች መጀመሩን ገልጸዉ ከፊታችን ሰኞ ከታህሳስ 12/4/2013 ዓ/ም ጀምሮ በ4ኛ ዙር ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ስራ የሚገቡ የክፍል ደረጃዎች በግል ትምህርት ቤቶች የቅድመ መጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች መሆናቸዉን ሀላፊዉ አሳውቀዋል፡፡


ሀላፊዉ በመግለጫቸዉ አክለዉም ህጻናት ተማሪዎችን ወደ ገጽ ለገጽ የመማር ማስተማሩ ስራ እያመጣን በመሆኑ የተዘጋጀዉን የኮቪድ ፕሮቶኮልን በአግባቡ መተግበር እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን ሚና እንዲወጡ ጥራቸዉን አቅርበዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
ለተወደዳችሁ የማርክ ቪዥን አካዳሚ ወላጆች የቅድመ መደበኛ ትምህርት ሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2013 የሚጀመር መሆኑን እያሳወቅን አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ አሟልታችሁ በወጣው መርሀ ግብር ተማሪዎችን አንድትልኩልን አናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ የፅዳት እቃዎች ያላስገባችሁ ወላጆች አስቀድማችሁ በማስገባት ኮሮናን በጋራ እንከላከል፡፡
Forwarded from Addis Ababa Education Bureau (Abebe Chernet)
ቀን 13 / 4 / 2013 ዓ.ም


ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተብሏል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ መክረዋል።

ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አሳስበዋል።
ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላትና ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

"ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም ይጀመራል።መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የዩቲዩብ ፣ የቴሌግራም ፣ የፊስቡክ እና የትዊተር ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
ውድ የማርክ ቪዥን አካዳሚ ወላጆች እና አሣዳጊዎች በሙሉ  ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መስረት ነገ ሰኞ መስከረም16/2015 ዓ.ም ትምህርት እንዳማይኖር  እናሳውቃለን፡፡ መደበኛ  ትምህርት ረብዕ መስከረም 18 ይጀምራል ።  
 
                                                 ት/ቤቱ
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 18 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
Channel name was changed to «.....»