የምትሰሩት ስራ ጉዳይ
በአሁኑ ወቅት በስራ አለም ውስጥ ከተሰማራችሁና የወደፊት የስራ ቆይታችሁ ስኬታማና እድገት ያለበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ስለጉዳዩ ማሰብ ያለባችሁ ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ አእምሯችሁን ተጠቅማችሁ ካላሰባችሁ፣ ነገ ስሜታችሁ መጨነቅና መዛባት ይጀምራል፡፡
በስራው አለም ውስጥ በቆያችሁ ቁጥር በሁለት መልኩ ማደግ አለባችሁ፡-
1) በገንዘብ ብቃት፣
2) በአእምሮ እድገት
1. የገንዘብ ብቃት
የሚከፈላችሁ ክፍያ አናሳ እንደሆነ ካሰባችሁ፣ ለስራው ካላችሁ ብቃት አንጻር እየተከፈላችሁ ሊሆን ስለሚችል ብቃታችሁን የምትጨምሩበትን መንገድ ፈልጉ፡፡ ብቁ ሆናችሁ መስሪያ ቤቱ የመክፈል ባህሉ ወይም አቅሙ አናሳ ሆኖ ካገኛችሁት ደግሞ፣ የመስሪያ ቤቱን አሰራር ለማስቀየር ከመታገል ወይም ከመነጫነጭ ይልቅ የስራ መስካችሁን መቀየር ቀለል እንደሚል አትዘንጉ፡፡
2. የአእምሮ እድገት
የስራው ጸባይ አእምሮን የሚያሰራ፣ የሚሞግትና የሚያሳድግ ከመሆን ይልቅ ድግግሞሽ የሞላው ከሆነ፣ ምንም እንኳን ገንዘብን ብታገኙበትም ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚራመድ የአእምሮ እድገት እንደማይኖራችሁ አትዘንጉ፡፡ በስራው ለመቆየት ከፈለጋችሁ፣ በግላችሁ የምታድጉበትን ሌላ መንገድ መፈለግ አለባችሁ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የሚሞግት፣ አእምሮን የሚያሰራና የሚያሳድጋችሁን ስራ ወደመፈለግ ማዘንበል ወሳኝ ነው፡፡
እድሜያችሁ በጨመረ ቁጥር ቤተሰብን ከመመስረት የሚመጣ ሃላፊነትና የተለያዩ ፍላጎቶች መጨመር ሁኔታዎች አብረው ስለሚመጡ ካለማቋረጥ የማደጋችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡
Dr Eyob Mamo
@etcare_Ethiopian_Company

ጥበበኛዋ ትል
አንዲት ትል ከአንድ ራጅም ዛፍ ስር ሆና ወደ ላይ ስትመለከት ዛፉ በማፍራት ላይ ያለውን ፍሬዎች በመመልከቷ ከፍሬው ለመመገብ ወደ ዛፉ ላይ የመውጣትን ጉዞ ጀመረች፡፡ በእሷ ፍጥነት (ዝግመት) ዛፉን ወጥታ ያሰበችበት ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚፈጅ ከተሞክሮ ብታውቀውም በጣም የምትወደውን ዜማ እያንጎራጎረችና ወደላይ በወጣች ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየታያት የመጣውን የአካባቢ ገጽታ እያየች በደስታ ዳገቱን ተያያዘችው፡፡
ብዙም ሳትርቅ ከዛፉ ላይ ወደታች የምትወርድ አንዲት ምንነቷ በውል ያልታወቀ እንስሳ ቆም ብላ፣ “ወደየት ነው እንደዚህ በደስታ እየተፍለቀለቅሽ የምትሄጂው አለቻት”፡፡ ትል፣ “ዛፉ ጫፍ ላይ ያለውን ፍሬ ልበላ” አለች፡፡ እንስሳዋም፣ “በቅድሚያ እኔ ከዚያ ነው የመጣሁት፣ ፍሬዎቹ ገና አልበሰሉምና አትልፊ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ አጉል ደስተኛነትና አዎንታዊነት አያጥቃሽ ጉዞው ቀላል እንዳይመስልሽ፣ ስለዚህ ብትመለሺ ይሻልሻል” አለቻት፡፡
ትሏም፣ ቆም ብላ እዚያ ለመድረስ የሚፈጅባትን ጊዜ ካሰላች በኋላ፣ “ችግር የለውም፣ እዚያ እስከምደርስ ድረስ ፍሬዎቹ ይበስላሉ” በማለት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
ያሰብከው ከፍታ ለመድረስና የለፋህበትን ፍሬ ለማግኘት . . .
1. ዓላማህን ከጊዜ አጣጥመህ እቅድ አውጣ
ከሁሉ በፊት ለመድረስ የምትፈልግበትን የዓላማ ከፍታ ወስን፡፡ ከዚያም፣ እዚያ ዓላማህ ጋር ለመድረስ የሚፈጅብህን የጊዜ ሁኔታ አስላና ሁለ-ገብ እቅድ አውጣ፡፡ ሁለ-ገብ እቅድ ማለት፣ እንደ አንተ ሁኔታ ገንዘብን፣ ትምህርትን፣ እድሜን . . . ያካተተ ሊሆን ይችላል፡፡
2. የሰዎችን ሃሳብ ማመዛዘን
ሁል ጊዜ ከፍ ያለ እቅድ ስታወጣና መንቀሳቀስ ስትጀምር ተቃራኒውን የሚነግሩህ ሰዎች እንደሚያጋጥሙህ አትርሳ፡፡ አንዳንዶች ለአንተ አስበው በቅንነት፣ ሌሎቹ ደግሞ በአንተ ላይ አስበው በምቀኝነት፡፡ በጭፍንነት ከሰማሃቸው ውጤቱ ው ስለሆነ ሁለቱንም ቢሆን በጥንቃቄ ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡
3. በጉዞው መደሰት
ወደ ዓላማህ በአንተ አቅምና ፍጥነት ስትጓዝ ፍጻሜው ላይ የመድረስን ደስታ እስከምታገኝ አትደበር፡፡ የጉዞ ደስታ የሚባልም ነገር እንዳለ አስብ፡፡ የመድረስ ደስታ ዓላማህ ላይ እስከምትደርስ ድረስ ያስጠብቅሃል፡፡ የጉዞው ደስታ ደግሞ አሁኑኑ በመደሰት ለጉዞው ጉልበትን ይሰጥሃል፡፡ በማንኛውም ጉዞህ ውስጥ “የምታዜመውን ዜማ” ፈልግ፣ የምትስቅበትን ምክንያት ፍጠር፣ ዙሪያህን እየቃኘህ ተደሰት፡፡ ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ ነውና፡፡
ያሰብከው ደረጃ መድረስህና ፍሬህን መብላትህ አይቀርምና፣ በፍጹም እንዳትቆም!!!

በህይወታችን የሚመጡትን መልካም አጋጣሚዎች በሙሉ መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንየቱም ያ ነገር ተመልሶ ወደኛ ላይመጣ ይችላል ወይም ደግሞ ከበፊቱ የበለጠ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ታዲያ ዛሬ ላይ ምን እየገፋን ነው ያለነው? እውነትስ ከዛ የተሻለ ነገር እጃችን ላይ ኖሮ ነው?። አንድን ነገር አልፈልግም ብሎ ለመተው እኮ እኛ ጋር ከዛ የተሻለ አማራጭ እኛጋ ሊኖር ይገባል። ካልሆነ ግን አማራጭ በሌለ ጊዜ የመጣውን መልካም አጋጣሚ አፈፍ አድርጎ ህይወትን ወደተሻለ ደረጃ ማሻገር ያስፈልጋል።
ስኬታማና የዛሬዋን መልካም አጋጣሚ
የምንጠቀምበት ቀን ያድርግልን🙏🙏
https://t.me/keyOfsuccesse
ስኬታማና የዛሬዋን መልካም አጋጣሚ
የምንጠቀምበት ቀን ያድርግልን🙏🙏
https://t.me/keyOfsuccesse
ብቃትን ፍለጋ!
አንድ ጊዜ ፈጣሪ ሰውን ያላካተተ ስብሰባን ጠራና ፍጥረትን ሁሉ ሰብስቦ አንድን ጥያቄ ጠየቃቸው፣ ይላል አንድ ምንጩ ያልታወቀ አፈ-ታሪክ፡፡
ጥያቄው እንዲህ የሚል ነበር፡-
“ለነገሩ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ አንድን ነገር ከሰው ልጆች ልሰውርባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ስለሆነም ያንን ከሰዎች ለመሰወር የምፈልገውን ነገር የት ባስቀምጠው ሰዎች ላያገኙት የሚችሉ ይመስላችኋል?” አላቸው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ብዙም የደፈረ እንስሳ ማግኘት ከባድ የነበረ ቢሆንም አራት እንስሶች የየግል ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡
ንስር እንዲህ አለ፡-
“ከሰዎች ለመሰወር የፈለከውን ነገር ለእኔ ስጠኝና ከፍ ብዬ መብረር ስለምችል ጨረቃ ድረስ ይዤው እወጣና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ “አንድ ቀን የሰው ዘር ጨረቃ ላይ የመውጣት ብቃት ስለሚኖረው ማግኘታቸው አይቀርም” አለው፡፡
አሳ እንዲህ አለ፡-
“እንደ ውቂያኖስ ጥልቅ ነገር እንደሌለለና ሰዎች እዚያ ጥልቀት ድረስ እንደማይሄዱ አውቃለሁና እኔ በዋና እዚያ ድረስ መጥለቅ ስለምችል ይዤው ልግባና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ የሰው ልጅ ወደጠለቀው ባህር የመግባት አቅም ለማዳበር ብዙ ጊዜ ስከማይፈጅበት ማግኘቱ አይቀርም” ብሎ መለሰ፡፡
አንበሳ በተራው እንዲህ አለ፡-
“እንኳን ሰው አብዛኛዎቹ የዱር እንስሶች እንኳ የሚፈሩት ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ የምደፍር እኔ ነኝ፡፡ እዚያ ወስጄ ባስቀምጠው ስለማያገኙት ለእኔ ስጠኝ”፡፡ ፈጣሪም፣ “ሰዎች ጫካን መመንጠር ብዙም ስለማይከብዳቸው ቀስ በቀስ ይደርሱበታል” አለ፡፡
ጦጣ በመጨረሻ እንዲህ አለች፡-
“ፈጣሪ ሆይ፣ ከእነዚህ ሁሉ ሃሳብ ሰጪዎች በበለጠ ሁኔታ ከሰው ጋር ቀረብ ብዬ የምኖረው እኔ ስለሆንኩኝ ባህሪያቸው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ሰዎች አብዛኛውን ነገር ፍለጋ ውጪ ውጪውን ነው የሚሉት፡፡ ውስጣቸው ያለው ነገር ትዝም አይላቸው፡፡ ስለዚህ ውስጣቸው ብታስቀምጠው በቀላሉ አያገኙትም” አለችው፡፡
የጦጣ መልስ ተቀባይነት ስላገኘ ፈጣሪ ለመደበቅ ያሰበውን ነገር በሰው ውስጥ አስቀመጠው ይባላል፡፡ ይህ የተደበቀው ነገር የራሳቸው የሰዎቹ እምቅ ብቃት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በውስጣቸው ፈጣሪ ያስቀመጠው አስገራሚና የታመቀ ብቃት እያላቸው ምንም እንደሌላቸው በከንቱ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡
በውስጣችሁ ተዝቆ የማያልቅ እምቅ ብቃት እንዳለ ታውቃላችሁ? ፈልጋችሁ አግኙት! አውጡት! አዳብሩት! ተጠቀሙበት!

Telegram
የስኬት ሚስጢር
✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

⏱ጊዜ
▫️▫️▫️
ህይወት ጊዜ በሚባል መለኪያ ተሰፍሮ ለሁሉም እኩል ተሰጥቷል። በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን በአመት 365 ቀናት ።
እያንዳንዷን ቀን እንደ ባንክ አካውንት አስበው ጊዜን ደግሞ እንደ ከረንሲ ( ገንዘብ) በጊዜ ማንም ደሃ ማንም ሃብታም የለም፤ ለሁሉም እኩል 24 ሰዓት ተሰጥቶታል።
በህይወት የሃብት ልዩነት የሚፈጠረው በጊዜ አጠቃቀም ልዩነት ነው።
ጊዜውን በአግባቡ ለተገቢው ተግባር የተጠቀመ የፈለገውን ና በህይወት አላማው ይኖራል። ጊዜውን በአግባብ ያልተጠቀመ ደግሞ በትችት ና በህይወት ሩጫ ( ሲደክም) ይኖራል።
ሽርፍራፊዋ ሰከንድ ከህወትህ ላይ ተሸርፋ የተሰጠችህ ናት፤ በአግባቡ ተጠቀምባት።
አሁን ማድረግ ለሚገቡህ ነገሮች ሁሉ: በኋላ፣ ነገ፣ ቀጣይ ሳምንት የሚቀጥለው ወር የሚባል ሰበባ ሰበብ አትስጥ ምክንያቱም ምድር ላይ ያለውን እጅግ በጣም ውዱን ጊዜህን እያባከንክ ነው።
ማድረግ ካለህ አሁኑኑ አድርገው።
ማድረግ ከሌለብህ ደግሞ ማድረግ የሌለብህን ነገር በማሰብ እንቁ ሃብትህን አታባክን።
መልካም ቀን

Audio
ሚስጢሩ (The secret)
(#documentary_Audio በትርጉም በቅርብ ቤተሰቤ የተሰራ አድምጡት ትወዱታላችሁ። ለህይወት ያላችሁን እይታ ይቀይርላችኋል። 👌👌👌
⏱1:32:19⏱
https://t.me/keyOfsuccesse
https://t.me/keyOfsuccesse
(#documentary_Audio በትርጉም በቅርብ ቤተሰቤ የተሰራ አድምጡት ትወዱታላችሁ። ለህይወት ያላችሁን እይታ ይቀይርላችኋል። 👌👌👌
⏱1:32:19⏱
https://t.me/keyOfsuccesse
https://t.me/keyOfsuccesse
የአንተም ጊዜ አለ!
ፀሀይ እና ጨረቃ እኩል አያበሩም፤
እኩል እናብራም ቢሉ ተፈጥሮ አትፈቅድላቸውም።
ግን ሁለቱም በራሳቸው ጊዜ ማብራታቸው አይቀርም።
አንተም አጠገብህ ያለ ሰው ሲሳካለት አይተህ የእኔስ ቀን መቼ ነው ?
ምነው ፈጣሪ ዘገየ ካልክ እንደፀሀይ በቀን እንደጨረቃም በጨለማ የምታበራበት ቀን አለ።
በተስፋ ተራመድ !
https://t.me/keyOfsuccesse
ፀሀይ እና ጨረቃ እኩል አያበሩም፤
እኩል እናብራም ቢሉ ተፈጥሮ አትፈቅድላቸውም።
ግን ሁለቱም በራሳቸው ጊዜ ማብራታቸው አይቀርም።
አንተም አጠገብህ ያለ ሰው ሲሳካለት አይተህ የእኔስ ቀን መቼ ነው ?
ምነው ፈጣሪ ዘገየ ካልክ እንደፀሀይ በቀን እንደጨረቃም በጨለማ የምታበራበት ቀን አለ።
በተስፋ ተራመድ !
https://t.me/keyOfsuccesse
Telegram
የስኬት ሚስጢር
✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።
#እርምጃ_መውሰድ!
ሃብታምነት ከእውቀት ጋር ቀጥታ ግንኙነት የለውም። እንደውም የማሰብ አቅማቸው አነስተኛ የሆነ ወይም ያነሰ የ IQ መጠን ያላቸው ሰዎች፣ ከፍተኛ IQ ካላቸው በተሻለ ሃብታም ይሆናሉ። እንዴት የሚለውን እንመልከት፦
ለምሳሌ ኢንጂነር ከሆንክ የምትማረውም ሆነ የምትሰለጥነው ስህተትን እንዳትሰራ ሆነህ ነው፤ ድልድይ ስትገነባ፣ መኪና ዲዛይን ስታደርግ... በአንተ አንዲት ስህተት የብዙሃን ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃልና ነገሮችን ሁሉ በሚገባ እንድትመረምር ሆነህ ትሰለጥናለህ። በተቻለህ አቅም የአደጋዎችን የመከሰት እድል (Risk) መቀነስ ይኖርብሃል።
ይህ መሆኑም ከመጠን በላይ እንድታስብ ያስገድድሃል። በምርጫዎች መሃል ስትኳትንም መደንዘዝ ትጀምራለህ (Paralysis by analysis)
ህይወትህንም እንደዚሁ አስበው... ከፊት ለፊትህ የቆመ አንበሳ አለ ሆኖም ግን ብዙ ነገሮችን በሃሳብህ ስታወጣና ስታወርድ የሽጉጡን ቃታ ሳትስብ ፈዘህ ቆመሃል።
ነገሮችን ከመከወንህ በፊት ምን ምን መጥፎ ውጤቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ቀድመህ ታስባለህ። ይህን ባደርግ ይህ ይሆናል ስለምትልም ወደፊት ላለመራመድና እርምጃ ላለመውሰድ የሚያግዱህ ሺ ምክንያቶችን ትደረድራለህ።
ከዚህ በተቃራኒ ብዙ ማሰብ የማይወዱና ካንተ በእውቀት ደረጃቸው ያነሱ ሰዎች የተሻለ እርምጃ ወሳጆች ናቸው።
እርምጃ መውሰድ ማለት አንድ ሺ መጽሐፎችን ማንበብ ማለት አይደለም፤ እርምጃ መውሰድ ማለት ብዙ ሰአታትን ስልጠና መውሰድ ማለት አይደለም።
#እርምጃ_መውሰድ_ማለት_እርምጃ_መውሰድ_ብቻ_ነው_አለቀ!

‹‹አዲስ ዓመት መልካሙን የምንሰራበት ይሁንልን!››
:
☞ዘመናትን የሚያቀያይርና አዲስ ዓመትን የሚሰጠን እርሱ
ፈጣሪ ነው።
:
ይህንን የፈጣሪን ምህረትና ቸርነት የምናስብ ስንቶቻችን
ነን?
:
ሰው ደግሞ ተጨማሪ አዲስ ዓመትና እድሜ ካልተሰጠው
ምንም ማድረግ አይችልም፡፡
:
ፈጣሪ እንድንኖር ካልፈቀደልን አዲሱን ዓመት ካልሰጠን
ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡
:
# ሌላው ቀርቶ፦
፡
➊.ወጥተን→የምንገባው፣
:
➋.ተቀምጠን→የምንነሣው፣
:
➌.ተምረን ለውጤት→የምንበቃው፣
:
➍.ሠርተን→የምናገኘው፣
:
➎.ነግደን→የምናተርፈው፣
:
➏.ወልደን→የምንስመው፣
:
➐.ለመጪው ዓመት ብለን እቅድ→የምናቅደው ፈጣሪ እንደ
ቸርነቱ ወደ አዲሱ ዓመት እንድንሸጋገር ሲፈቅድልን ነው፡፡
:
√ብዙ ሰዎች ግን የፈጣሪን ቸርነት ረስተዋል፡፡
:
√አዲስ ዘመን ሲሰጠን ዋጋ የሚከፈልበት ቢሆን ኖሮ ዋጋውን
ማን ይችለው ነበር?
:
√ግን ፈጣሪ አዲስ ዓመት የሰጠን ያለዋጋ በነፃ ነው።
፡
√ለምንኖርበት ዕድሜ ለሰጠን ተጨማሪ ዓመት የጠየቀን ዋጋ
የለም፡፡
:
√ታዲያ ጊዜ የሰጠን ፈጣሪ ደግሞ ጊዜ እንድንሰጠው
እንድናመሰግነው ይፈልጋል።
:
❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀
:
# አዎን ወዳጆቼ፥
፡
☞አንዳንድ ሰዎች እንዲኖሩ፣ እንዲወጡና እንዲወርዱ አዲስ
ዓመትና ጊዜ ፈጣሪ ሰጥቷቸው ሳለ አዲስ ዓመት ለሰጣቸው
ለፈጣሪ ግን ጊዜ መስጠትና ማመስገን ተስኗቸው
ይስተዋላሉ፡፡
:
♡ይህቺን ቀን አስበው እዚህች ቀን ላይ፣ ለዚህች ዓዲስ
ዓመት ያልደረሱ ብዙ ሰዎች አሉ።
፡
♡አንተ እኔ ሁላችንም ግን ደርሰናልና እንደ ቸርነቱና ምህረቱ
ለዚህ ላደረሰን አምላካችን እንዲህ እያልን እንፀልይ፦
፡
➊.አምላካችን ሆይ፥ አዲሱን ዓመት ስለሰጠኸን
እናመሰግናሀለን።
:
➋.አምላካችን ሆይ፥ ከዚህ በኋላ የሚኖረን ቀሪ እድሜ
በፊትህ ያማረ ይሁንልን፡፡
:
➌.አምላካችን ሆይ፥ እድሜና ዘመናችን በቤትህ ይለቅ፡፡
:
ማለዳ ማለዳ በአዲስ ምስጋና፣
:
በአዲስ ዝማሬ፣
:
በአዲስ ሽብሸባ፣
:
በአዲስ ቅኔ፣
:
በአዲስ እልልታ ይህ በረከት የሆነው እድሜና ዘመናችን
በቤትህ ይለቅ፡፡
፡
➍.አምላካችን ሆይ፥ ሳናመሰግንህ ላለፉት የምህረት
አመታት ሁሉ ዛሬ ይቅር በለን፡፡
:
➎.አምላካችን ሆይ፥ የሚከፋፍለን የሚያለያዬንን የጥል፤
የክርክር፤ የዘረኝነት ግድግዳ አንተ አፍርስልን።
:
➏.አምላካችን ሆይ፥ በአዲሱ ዓመት ፍቅርና አንድነትን
ስጠን።
:
➐.አምላካችን ሆይ፥ ሐገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ባርክ።
:
➑.አምላካችን ሆይ፥ በሰጠኸንም እንደ ቸርነትህ
በጨመርክልን አዲስ ዓመት መልካሙን እንድንሰራበት አንተ
ይርዳን! # ለዘላለሙ አሜን!
:
♡እስኪ ተመስገን በሉት። ተመስገንንንንንንንንንንንንንንንን
:
❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀
➊.ሀጥያትን→በጽድቅ፣
፡
➋.አለመጸለይን→በመጸለይ፣
፡
➌.ስጋዊነትን→በመንፈሳዊነት፣
፡
➍.አለማገልገልን→በማገልገል፣
፡
➎.ድህነትን→በመስራት፣
:
➏.አለማንበብን→በማንበብ፣
:
➐.አለማወቅን→በመማር፣
:
➑.ጥላቻን→በፍቅር፣
:
➒.ክፉን→በመልካም፣
:
➓.ንፉግነትን→ በመስጠት፣ የምንቀይርመበትና ፍቅር የበዛበት
ብሩህ ዘመን ይሆንልን ዘንድ ተመኘው!
:
[☞መልካም አዲስ ዓመት☜]
:
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
:
"ሰላማችሁ ይብዛ"
:
☞ዘመናትን የሚያቀያይርና አዲስ ዓመትን የሚሰጠን እርሱ
ፈጣሪ ነው።
:
ይህንን የፈጣሪን ምህረትና ቸርነት የምናስብ ስንቶቻችን
ነን?
:
ሰው ደግሞ ተጨማሪ አዲስ ዓመትና እድሜ ካልተሰጠው
ምንም ማድረግ አይችልም፡፡
:
ፈጣሪ እንድንኖር ካልፈቀደልን አዲሱን ዓመት ካልሰጠን
ምንም ነገር ማድረግ አንችልም፡፡
:
# ሌላው ቀርቶ፦
፡
➊.ወጥተን→የምንገባው፣
:
➋.ተቀምጠን→የምንነሣው፣
:
➌.ተምረን ለውጤት→የምንበቃው፣
:
➍.ሠርተን→የምናገኘው፣
:
➎.ነግደን→የምናተርፈው፣
:
➏.ወልደን→የምንስመው፣
:
➐.ለመጪው ዓመት ብለን እቅድ→የምናቅደው ፈጣሪ እንደ
ቸርነቱ ወደ አዲሱ ዓመት እንድንሸጋገር ሲፈቅድልን ነው፡፡
:
√ብዙ ሰዎች ግን የፈጣሪን ቸርነት ረስተዋል፡፡
:
√አዲስ ዘመን ሲሰጠን ዋጋ የሚከፈልበት ቢሆን ኖሮ ዋጋውን
ማን ይችለው ነበር?
:
√ግን ፈጣሪ አዲስ ዓመት የሰጠን ያለዋጋ በነፃ ነው።
፡
√ለምንኖርበት ዕድሜ ለሰጠን ተጨማሪ ዓመት የጠየቀን ዋጋ
የለም፡፡
:
√ታዲያ ጊዜ የሰጠን ፈጣሪ ደግሞ ጊዜ እንድንሰጠው
እንድናመሰግነው ይፈልጋል።
:
❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀
:
# አዎን ወዳጆቼ፥
፡
☞አንዳንድ ሰዎች እንዲኖሩ፣ እንዲወጡና እንዲወርዱ አዲስ
ዓመትና ጊዜ ፈጣሪ ሰጥቷቸው ሳለ አዲስ ዓመት ለሰጣቸው
ለፈጣሪ ግን ጊዜ መስጠትና ማመስገን ተስኗቸው
ይስተዋላሉ፡፡
:
♡ይህቺን ቀን አስበው እዚህች ቀን ላይ፣ ለዚህች ዓዲስ
ዓመት ያልደረሱ ብዙ ሰዎች አሉ።
፡
♡አንተ እኔ ሁላችንም ግን ደርሰናልና እንደ ቸርነቱና ምህረቱ
ለዚህ ላደረሰን አምላካችን እንዲህ እያልን እንፀልይ፦
፡
➊.አምላካችን ሆይ፥ አዲሱን ዓመት ስለሰጠኸን
እናመሰግናሀለን።
:
➋.አምላካችን ሆይ፥ ከዚህ በኋላ የሚኖረን ቀሪ እድሜ
በፊትህ ያማረ ይሁንልን፡፡
:
➌.አምላካችን ሆይ፥ እድሜና ዘመናችን በቤትህ ይለቅ፡፡
:
ማለዳ ማለዳ በአዲስ ምስጋና፣
:
በአዲስ ዝማሬ፣
:
በአዲስ ሽብሸባ፣
:
በአዲስ ቅኔ፣
:
በአዲስ እልልታ ይህ በረከት የሆነው እድሜና ዘመናችን
በቤትህ ይለቅ፡፡
፡
➍.አምላካችን ሆይ፥ ሳናመሰግንህ ላለፉት የምህረት
አመታት ሁሉ ዛሬ ይቅር በለን፡፡
:
➎.አምላካችን ሆይ፥ የሚከፋፍለን የሚያለያዬንን የጥል፤
የክርክር፤ የዘረኝነት ግድግዳ አንተ አፍርስልን።
:
➏.አምላካችን ሆይ፥ በአዲሱ ዓመት ፍቅርና አንድነትን
ስጠን።
:
➐.አምላካችን ሆይ፥ ሐገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ባርክ።
:
➑.አምላካችን ሆይ፥ በሰጠኸንም እንደ ቸርነትህ
በጨመርክልን አዲስ ዓመት መልካሙን እንድንሰራበት አንተ
ይርዳን! # ለዘላለሙ አሜን!
:
♡እስኪ ተመስገን በሉት። ተመስገንንንንንንንንንንንንንንንን
:
❀︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵♔︵♡︵❀
➊.ሀጥያትን→በጽድቅ፣
፡
➋.አለመጸለይን→በመጸለይ፣
፡
➌.ስጋዊነትን→በመንፈሳዊነት፣
፡
➍.አለማገልገልን→በማገልገል፣
፡
➎.ድህነትን→በመስራት፣
:
➏.አለማንበብን→በማንበብ፣
:
➐.አለማወቅን→በመማር፣
:
➑.ጥላቻን→በፍቅር፣
:
➒.ክፉን→በመልካም፣
:
➓.ንፉግነትን→ በመስጠት፣ የምንቀይርመበትና ፍቅር የበዛበት
ብሩህ ዘመን ይሆንልን ዘንድ ተመኘው!
:
[☞መልካም አዲስ ዓመት☜]
:
«ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ»
:
"ሰላማችሁ ይብዛ"
A struggle is a struggle
.
ሽንኩርት ሲከትፍ ቢላዋ የቆረጠዉ እና እንጨት ሲፈልጥ እጁ የተቆረጠ ሰዉ ሁለቱም “ምን ሆነህ ነዉ?” ቢባሉ “እጄ ተቆርጦ ነዉ” ይላሉ፥
.
ባለ ሽንኩርቱም፡ ባለ መጥረቢያዉም ይደማሉ፣ ይቆስላሉ፡ ቁስላቸዉን ያስታምማሉ፥
A struggle is a struggle
መልካም ቀን
https://t.me/keyOfsuccesse
.
ሽንኩርት ሲከትፍ ቢላዋ የቆረጠዉ እና እንጨት ሲፈልጥ እጁ የተቆረጠ ሰዉ ሁለቱም “ምን ሆነህ ነዉ?” ቢባሉ “እጄ ተቆርጦ ነዉ” ይላሉ፥
.
ባለ ሽንኩርቱም፡ ባለ መጥረቢያዉም ይደማሉ፣ ይቆስላሉ፡ ቁስላቸዉን ያስታምማሉ፥
A struggle is a struggle
መልካም ቀን
https://t.me/keyOfsuccesse
#አትሁን!!!
ሁሉም ሰው አንተን ለማሞኘት ጭንብል ለብሶ በሚመጣበት ዓለም ውስጥ ነውና የምትኖረው ፣
እጅግ በጣም የበዛ ጥሩ ሰው አትሁን!!!
#የኃያልነት_ሕጎች መጽሐፍ
48 LAWS OF POWER የተሰኘው መጽሐፍ ሳይቆራረጥ በጥንቃቄ የተተረጎመው #የኃያልነት_ሕጎች በሚለው መጽሐፍ ነው፤
ሲገዙ #የኃያልነት_ሕጎች ብለው በእንግሊዘኛው ሽፋን የታተመውን መጽሐፍ ይግዙ!