ከምርጦች_ማህደር 🎧🇪🇹
127K subscribers
234 photos
14 videos
93 files
499 links
በዚህ ቻናል : የተመረጡ       አዝናኝ 😂
         አስተማሪ    ነገሮችን  ያገኙበታል።በዚህchannal የተመረጡ አስተማሪ ታሪኮች best short history ግጥሞች poem 💟 ያገኛሉ🙏
እየተዝናናን  እራሳችንን የተሻለ ሰው እናድርግ!
for paid prom or cross 50k+ @kirawajr
Download Telegram
እልህ ፣ወኔ ፣ አልበገር ባይነት ያሸናፊነት መንፈስ ሁሉንም የያዘ የሀገራችን ምርጥ እንቁ አትሌት ታምራት ቶላ!!
በስተመጨረሻም ወርቁ መጣ🥇🏆
እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬ❤️
እንኳን ደስ አለን!! እንኳን ደስ አላችሁ!! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🔥

@Kemrtochmahder
💖እቴ♥️
(በውቀቱ ስዩም)

ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ #ጫጩት ላክል እኔ፤🙌
ይስጥሽ ከጸጉሮቼ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ #ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ👨‍🦲
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
#ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤☹️

... እቴ♥️
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ🩸
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ😋
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።

እቴ
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ😊
ያስቀርልኝ አይኔን
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን #ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን😊♥️

@kemrtochmahader
ሼር አደራ🙏
እንድ #ሰካራም ታክሲ አስቁሞ ጋቢና ከገባ በኋላ ሹፌሩን አወከኝ🤔 ይለዋል
#ሹፌሩ.. ይቅርታ አላወኩህም ሲለው
#ሰካራሙ... አሁን #አስቁሜህ የገባውት ነኝ እኮ🤤😅

እሺ ምን ይባላል ይሄ🤷‍♂

😂😂🤣
@kemrtochmahader
ሼር 🙏
🌙ጨረቃ ና ናፍቆት♥️

እቱ የጥንቲቱ😊
የጥርስሽ ንጣቱ
የጉንጭሽ ቅላቱ 🥰
ውል ይለኛል ዛሬም የገላሽ ሙቀቱ
የእግሮችሽ ኮሽታ
የፍቅርሽ #ሹክሹክታ😘
ያ የሣቅሽ ዜማ የበዛው ክትክታ
ይሠማኛል ዛሬም #ናፍቆት ሲበረታ 😊

እቱ የጥንቲቱ
አንቺም ትዝ ካለሽ ካለብሽ #ናፍቆቱ
ይህ ነው መዳኒቱ 🤗
ባስለመድኩሽ ሰዓት ባለሽበት ቦታ
ቀና በይ ላንድ አፍታ
እኔም ባለሁበት ባስለመድሽኝ ሰዓት
ዓይኖቼን አቅንቼ
ጨረቃን አይቼ ልግባ ተፅናንቼ ❤️

አንቺም በዚያች አፍታ
ጨረቃዋን ፈክታ
ካየሻት ተጽናኚ
በይ ቃሌን እመኚ ❤️

ምንም ብንራራቅ ካንድ ሰማይ ሥር ነን
ነገ አብረን ለመኖር ታላቅ ተሥፋ አለን🙏😘

(ሳምሶን መኮንን)

@kemrtochmahader
ሼር አደራ🙏
♥️አንቺ ነሽ 💓

ፍቅርን ያሳየሽኝ😊
ደስታን የሰጠሽኝ
አንገቴን #ስደፋ
ደርሰሽ ያቀናሽኝ🤗
የዝምታዬን #ጩኸት
ከልብ #ያደመጥሽኝ♥️

አንቺ ነሽ!! ❤️

የመውደድን ጥጋት
የአበባን ፍካት
የጨረቃን ውበት
የፀሀይን #ድምቀት🥰
በላይሽ ደርበሽ
ልቤንም #የሰረቅሽ😍
አንቺ ነሽ!! 🤗

ፍቅሬን የተቀበልሽ🥰
ፍቅርሽን ሰጥተሽ
ፍቅር ላንተ #ብባል
ምላሼ #አንቺ ነሽ!!♥️

ረያን አቡዲ

@kemrtochmahader
ሼር አደራ🙏
♥️🥰
ጨረቃ ስትወጣ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ
በዓይኔ አይሻለው……
ከዋክብት ሲጓዙ ከነሱ መካከል
አንቺን ፈልጋለው……😊
ከፀሃይ ጋር ብትወጪ ብዬ
ሁል ጊዜ ጠዋት እጠብቅሻለው
አንዳንዴም በህልሜ #አቅፌሽ አድራለው።🤗
ዝም ብለሽ በሀሳቤ ሁሌ ትመጪያለሽ
ምክንያቱን ባላቅም ትናፍቂኛለሽ
#ያነጫንጨኛል ላገኝሽ እሻለው…☹️
በሰበብ አስባቡ #ስላንቺ አወራለው♥️
የፅድቄ ሽልማት የኔ ገነት ውዴ
ኧረ ጉዴ ፈላ…ፍቅር #ያዘኝ እንዴ 😳

@kemrtochmahader
ሼር አደራ
⚠️ ፍትህ ለፌቨን....!!😭💔

ፌቨን የ7 ዓመት ህፃን ነች።እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘው ጌታቸው የተባለ የ3 ልጆች አባት ህፃኗን በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ደፍሮ ገድሏት ተገኘች።

የ7 ዓመት ህፃኗ ልጅን ግቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፏ ውስጥ አሽዋ በመጨመር ለመግለፅ በሚከብድ ሁኔታ አሰቃይቶ እንደገደላት እናት አስረድታለች።25 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ቢሆንም በይግባኝ ለማስወጣት እየሠሩ ነው።እኔን አስፈችው በማለት ዛቻና ማስፈራሪያው ከአቅሜ በላይ ሆኗል።ህዝብ ይፍረደኝ እያለች ነው።

!! ፍትህ ለፌቨን ..!!

ሼር እያደረጋችሁ ድምፅ ሁኗት።!
💗💔💔

መሄድ መለየትሽ ምንም እንኳን ቢያመኝ💔

ሰዉ መሆንሽ እንጂ እኔን የጠቀመኝ🤨

ፈጣሪ ሲፈጥስሽ ገና ድሮ ድሮ
ጠባቂዬ መልአክ አርጎሽ ቢሆን ኑሮ😳

እንዲህ እንዳሁኑ እንዲህ እንደዘበት
ጥለሽኝ ስትሄጂ ገንዘብ ወዳለበት😡

ያለ ዘብ ትተሽዉ ክፍቱን የነፍሴን በር
በሌሊት #መጋኛ ባስመታሽኘኝ ነበር😏

@kemrtochmahader
ሼር አደራ 🙏
#አስተውል‼️ በሌላ ሰው ውድቀት

ፍፅሞ
#አትሳቅ ጊዜ ባንተ ላይ ምን እንደሚያመጣብህ አታውቅምና !!

መልካም አዳር🙌
@kemrtochmahader
ሼር🙏
>> ስትቀርበው ለራቀ አትጨነቅ
ምክንያቱም:- ውድ ነገር ያለቦታው ርካሽ ነውና፥

>>ሥታምነው ለከዳህ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ታማኝ በመሆንህ አሸንፈሃልና፥

>> ሥትፈልገው ባጣኽው ነገር አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-እሱ አንተን ሲፈልግ ታገኘዋለህና፥

>>ሥትወደው ለጠላህ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ሥንት ምርጥ ሠዎች አንተን የሚወዱ አሉና፥

>>ሥላልሆነው ነገር አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ገና ከዚህ በኋላ የሚሆኑ ነገሮች አሉና፥

>> አጣዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ብታጣ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-አገኘዋለሁ ብለህ ያላሠብከውን ታገኘዋለህና፥

>> ያሠብከው ሳይሆን ቢቀር >>አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ፈጣሪ ያላሠብከውን ይሠጥሃልና፥

>> ፍቅር ሥትሰጠው ፍቅር ለማይሠጥክ አትጨነቅ
>>ምክንያቱም:-ምንአልባት ፈጣሪ ምርጥና ደሥ የሚል የፍቅር ታሪክ እየፃፈልክ ይሆናልና፥

እናልክ ወዳጄ አትጨነቅ!!

>>አንተ ለሁሉም ተፈጠርክ እንጅ ሁሉም ላንተ አልተፈጠረም!
>> ፈጣሪ ላንተ የሚያሥፈልግክን ያውቃል ያሠብከውን አሥጥሎክ ያላሠብከውን ይሠጥካል!

>>ሥላለፈው ብዙም አታሠላሥል፣
>>ሥለ ወደፊቱም አብዝተህ አትጨነቅ፣
>>ከዚህ ይልቅ ዛሬን ጠበቅ አድርግ፤

አትጨነቅ!

ይችም ቀን ታልፍና ድሮ ትባላለች!
ሠአቷ ታልቅና ታሪክ ትባላለች!
ሥለዚህ አትጨነቅ በደሥታ እለፋት!
ነገም ሌላ ቀን ነው፣ህይወትህ ተሥፋ አላት።

@kemrtochmahader
ሼር አደራ🙏
💝ሰላም ቤተሰቦቼ ሰላማች በያላችሁበት ይብዛልኝ🙏
ስለጠፋን ይቅርታ🙌

📚አንባቢ ካለ አሪፍ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ልንጀምር አስበናል🤗
እስቲ ፍላጎታችሁን በreaction አሳዩን❤️

አብራችሁን ስለምትሆኑ ሁሌም አመስጋኝ ነን🙏
ፈጣሪ ያክብርልን♥️
@Kemrtochmahder
አንዱ ሱቅ ሄዶ ሊገዛ ከባለሱቁ ጋ እያወሩ ነው ..

👨‍🦲ባለሱቅ

👱‍♂አቤት

👨‍🦲አስታወስከኝ

👱‍♂ኧረ አላወኩህም አባቴ

👨‍🦲በደንብ እየኝ እና አስታውስ

👱‍♂በርግጥ ፊትህ አዲስ አሎነብኝም ግን ይቅርታ አላወኩህም

👨‍🦲ባለፈው ጊዜ የዛሬ #አመት የፍቅረኛሞች ቀን ኮንድም ስጠኝ ብየህ #አልቋል ብለኸኝ ነበር ትዝ አልኩህ🤔

👱‍♂እእእእ😄 አዎ አስታወስኩሽ ብሮ ሰላም ነው😄

👨‍🦲በቃ ዝም በል 😡😏 #ዳይፐር ስጠኝ😟


😁😂🤣
@kemrtochmahader
ሼርር🙏
🥀የፍቅር ማዕበል ❤️‍🔥
ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

በቀጣይ የምንጀምረው ታሪክ ነዉ 🤗
@Kemrtochmahder
💔የማይሽር...ጠባሳ💔
፨።።።💘💘💘።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ😥
ከልብ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ❤️‍🔥
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ😔💔
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ😒
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ🙍‍♂
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን😟
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።
🥺

@kemrtochmahader
#ሼር አደራ🙏
​​❤️‍🔥❤️‍🔥የፍቅር ማእበል💖💞💞

💝ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ በከምርጦችማህደር
የቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💝
     
  ክፍል
1⃣
ሰላም እባላለሁ።   ብዙዎች እንደ ስሜ ሰላም የሆንኩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል...
ቅብርር ያልኩ የድሀ ልጅ ነኝ እናቴ እንደወንድም እንደሴትም ሆና ነው ያሳደገችኝ ፈጣሪ ይመስገን እንደማንኛውም ኢትዮጽያዊ ተመርቄ ስራ ይለኝም ።
     በወጣትነት እድሜ ቤተሰብ ለፍቶ ስንት መስዋትነት ከፍሎ አስተምሮ ሲጨርስ ስራ አቶ ቤት ቁጭ ብሎ የነሱን እጅ እንደመጠበቅ የሚያም ነገር የለም ።
    በዚህ ህይወት ውስጥ ብቸኛ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ፍቅረኛዬን ማክቤልን ነው ።
 
  ከልጅነታችን ጀምሮ አብረን ነው ያደግነው የፍቅር ስሜት በመላችን አልነበረም  እኔ 12 ስገባ እሱ ቀድሞኝ ተፈትኖ ውጤት አልመጣለትም ነበር 
እና የዛን አመት ነው አፈቅርሻለሁ አፈቅርሀሉ ሳንባባል እራሳችንን relationship ውስጥ ያገኘነው ።
 
  ይኸው አሁን 5 አመታችንን ጨርሰን ወደ 6 እየሄድን ነው ፈጣሪ ከፈቀደው እኔ ልክ ስራ እንዳገኘሁ እናቴን የተወሰነ የሰርግ ወጪ ማገዝ ከቻልኩ ለመጋባት ነው እቅዳችን 
ቢያንስ ካገባሁ ቡሀላ ከናቴ ላይ ሸክም ከመሆን እድናለሁ በራሴም እፍጨረጨራለሁ ብዬ አምናለሁ።
    

ከናቴጋ  ቡናችንን እየጠጣን የሞቀ ጨዋታ እያለን ማክቤል ደወለ አነሳሁት
ሄሎ ሰላም

ወዬ ማክ 
ሰፈር ነኝ የተለመደው ቦታ እየጠበኩሽ ነው ቶሎ ነይ !!!
እሺ መጣሁ ብዬ እናቴን መጣሁ ቆይ ማክቤል ፈልጎኝ ነው ከቆየሁብሽ ወደ ስራሽ ሂጂ እሺ እናቴ
ስሚያት በዛው በለበስኩት ቱታና በነጠላ ጫማ ወደ ማክቤል አመራሁ  (ነፍቅር አጋራችሁን በጣም ስትቀርቡት ስለለበሳችሁት ልብስ ግድ አይሰጣችሁም እዚጋ ዋናው ነጠብ እሱን ማግኘታችሁ ማውራታችሁ ለናንተ ከበቂ በላይ ነው)
ማክ የተለመደው ቦታችንጋ ቁጭ ብሏል እንደለመድኩት ከኋላው ሄጄ ጥምጥም ብዬበት ሳምኩት ፍፁም የማቀው ማክቤል አልነበረም እጄን ከሰውነቱ ላይ መንጭቆ አነሳው በስማም እንዴ ምናባህ ሆነሀል መነጨከኝኮ አልኩት 😒
  ካሁን ቡሀላ መተዛዘሉ አስፈላጊ አደለም ለትልቅ ጉዳይ ነው የፈለኩሽ አለኝ ፊቱ ደም መስሏል ደም ስሩ ሁላ ተወጣጥሯል አረ እያስጠነከኝ ነው የተፈጠረ ነከር ካለ በቀጥታ ተናገር ምን ሆነሀል ቆይ??

ከዛሬ ጀምሮ እኔና አንች መለያየት አለብን ካሁን ቡሀላ አጠገብሽ አልደርስም አጠገቤ እንዳትደርሺ  አለኝ።
   ከት ብዬ በረጅሙ ሳኩበት አንተ ያምሀል እንዴ እኔኮ ምን ተፈጥሮ ነው ብዬ ደነገጥኩ አንተ ትቀልዳለሀ ደነዝ ጌታን ፊትህ ሁላኮ ተቀያይሯል እጄን ወደጉንጩ እያስጠጋሁ  
በደጋሜ አጄን ከፊቱ ላይ አነሳና መስፍን ይሙት አልቀለድኩም ለምን ብለሽ እንዳጠይቂኝ ዝም ብለሽ ከህይወቴ ውጭልኝ አለ አይኑ አዝሎት የነበረውን እንባ አፈሰሰው
  

ምን አልክ መስፍን ይሙት እእ በአባትህ ማልክኮ እንዴ ምንድነው የተፈጠረው ያምሀል እንዴ ቆይ ምን አጠፋሁ ንገረኝ እንዴ ቆይ አቶደኝም አታፈቅረኝም 6 አመት ይቅርና 6 ወር የለፉበት ፍቅርኮ ያሳዝናል እእእ እንዴት ከመሬት ተነስተህ እንለያይ ትለኛለህ እናቴ የሰርጋችንን ቀን በጉጉት እየጠበቀች እኔ የምንጋባበት ቀኑ እርቆብኝ ሳለ እንደቀላል እንለያይ ትለኛለህ እእእእ ።( ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ነበር ልቤ ተከፍታ ለመውጣት ምንም አልቀራትም አንድ ቀን እንኳንኮ በመሀላችን አስታራቂ ገብቶ አያቅም ከፍ ያለ ፀብ ተጣልተን አናቅም አንድም ቀን ስለመለያየት አስበን አናቅም የመጀመሪያው ነኝ የመጀመሪያዬ ነው)
  
  የተፈጠረውን ነገር እንኳን አላብራራልኝም ፊቴን ቀና ብሎ አላየውም መናገር ሚፈልገውን ተናግሮ ሲጨርስ ሄደ ጥሎኝ እራሴን ችዬ መቆም እንኳን ስለከበደኝ እዛው ደገፍ ብዬ ቁጭ አለኩ
መጮህ አማረኝ ማልቀስ አማረኝ አነዱ ልቤም አውቆ ነው አሁን ይመጣል ይለኛል አንዱ ልቤ ደሞ መቼም የውሸት በአባቱ አይምልም ይለኛል ግራ ገባኝ እንደምንም ተሟሙቼ ቤቴ ደረስኩ እናቴ ወደስራዋ ሄዳለች ማንም የለም እህቴም ብትሆን ውሎዋ ትምህርት ቤት ነው ቀጥታ ክፍሌ ገበሁ በቁም አልጋው ላይ ወደኩኝ አፌን በትራሴ አፍኜ ጮኩ ትራሴን ነከስኩት ምንም መፍትሄ የለም ስልኬን አነሳሁ ደወልኩኝ በሁለቱም ስልኩ block አድርጎኛል ...

ክፍል ሁለት ከ
200like👍በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ🙏

@Kemrtochmahder
ሼር🙏
      
በውሸት ተከባ በታጠረች አለም
#መታመን ነው እንጂ #መካድ ብርቅ አይደለም‼️

💛ለራሳችን እንታመን በዚኛዉ አለም ጥቅም ባይኖረዉም ለላይኛዉ ስንቅ ይሆነናል እና🙏

@kemrtochmahader
#Share 🙏❤️
ከምርጦች_ማህደር 🎧🇪🇹 pinned «​​❤️‍🔥❤️‍🔥የፍቅር ማእበል💖💞💞 💝ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የፍቅር ታሪክ በከምርጦችማህደር የቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ💝         ክፍል1⃣ ሰላም እባላለሁ።   ብዙዎች እንደ ስሜ ሰላም የሆንኩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል... ቅብርር ያልኩ የድሀ ልጅ ነኝ እናቴ እንደወንድም እንደሴትም ሆና ነው ያሳደገችኝ ፈጣሪ ይመስገን እንደማንኛውም ኢትዮጽያዊ ተመርቄ ስራ ይለኝም ።      በወጣትነት…»
​​  
💛የፍቅር ማዕበል💞

💝ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የ ፍቅር ታሪክ በከምርጦችማህደር የ ቴሌግራም ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ
❤️‍🔥

          ክፍል
2⃣

ምሽቱን ሙሉ አይኔ ደም እስኪመስል ሳለቅስ አመሸሁ አንድም ቀን ካፉ ክፉ ቃል አውጥቶ አስቀይሞኝ አያቅም ይሄ ነው የምለው መጥፎ ፀባይ የለበት በድንገት እንደዚህ ያደረገው ነገር ግራ ገባኝ አልቅሼምም አልወጣ አለኝ::

  ማታ መሽቶ እናቴ ወደቤት መጣች ከእህቴጋ ሲያወሩ እየሰማኋቸው ነው እህትሽ ምን ሆና ነው በጊዜ ወደመኝታ ቤት ያመራችው ??
እኔጃ እማዬ ከመጣሁ ጀምሮ አላናገረችኝም እስቲ አንቺ አናግሪያት አለቻት።
እኔም ምንም እንዳልተፈጠረ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ እናቴ አይታኝ ተያት በቃ እንቅልፍ ወስዷታል ብለው ከክፍሌ ወጡ።
   ሌሊቱን ሙሉ አንዴ ስነሳ አንዴ ስቀመጥ አንዳንዴም እንደ ህንድ አክተር ልግደለው እንዴ እላለሁ አንዳንዴ ደሞ በድንገት ቢሊየነር ሆኜ በየቲቪው ብታይኮ እራሱ እየለመነ ይቅርታ ይጠይቀኛል ብቻ ሌሊቱ እንዲሁ ነጋልኝ በሀሳብ ስብሰለሰል ።
  
   በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ላይ ስነሳ ቤት ማንም የለም ከነጋ ቡሀላ ስለሆነ እንቅልፍ የወሰደኝ አርፍጄ ነው የተየሳውት ቀጥታ ከእንቅልፌ እንደተነሳሁ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ድፍት ብዬ አለቀስኩ የሆነ ሸክም ከላዬ ላይ እንደቀለለ ነገር ተሰማኝ ወደ ቤቴ ተመልሼ ምሳ ሰአት ሳይደርስ ቤቱን ፏፏ አድርጌ እናቴን ጠበኳት ተጨዋውተን ወደ ስራዋ ተመልሳ ሄደች ።
እኔም ለባብሼ ወደነማክቤል ሬስቶራንት ሄድኩኝና አስጠራሁት ገና ሲያየኝ ፊቱን ቅይይር አደረገው ።

ምንድነው??
ማክቤል መለያየታችን ይሁን እሺ  ቢያንስ ግን ይሄ ነው ጥፋትሽ በለኝና ልወቀው እኔም ጭንቅላቴ እረፍት ያግኝ አልኩት።
        በቃ መለያየት ፈለኩ ተለያየን ሌላ ምክንያት መደርደር አያስፈልገኝም እየመጣሽ እንዳትበጠብጪኝ ክብርሽን ጠብቂ ።   
ይሄን ተናግሮ በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ
እንባ እየተናነቀኝ ፊቴን አዙሬ ወደ ቤቴ ሄድኩኝኝኝ ምሽቱን በሙሉ ከራሴጋ ሳልሆን መምሸቱም መንጋቱም ስለማይቀር መሽቶ ነጋ ዛሬም በጠዋት ተነስቼ ወደቤተክርስቲያን ሄድኩኝ ።
ቅዱስ ሚካኤል አባቴ ለኔ ካላልከው በቃ ከልቤም ከህይወቴም አውጣልኝና አንተ የተሻለውን እንደምታዘጋጅልኝ ስለማምን አንተን እጠብቅሀለሁ የራሴን ሰው እስክሰጠኝ አሱን ግን አባቴ ከነትዝታዎቹ ከሀሳቤም ከኔ ህይወት አውጣልኝ ብዬ ፀለይኩ።።
ወደ ቤቴ ተመልሼ እንደተለመደው እናቴን ምሳዬን ሰርቼ ቤቴን አፀዳድቼ ጠበኳት ከሷጋ ተሳስቀን የልብ የልባችንን አውርተን ወደስራዋ ሄደች ።
  ልክ እናቴ ሄዳ ለብቻዬ ቁጭ ስል ቀጥታ ሀሳቤ ውስጥ ይመጣል ። አልጋዬ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ እንዴት ነው እሱን መበቀል ምችለው ????????
ከብዙ ሀሳብ ቡሀላ ጭንቅላቴ ውስጥ 1 ሰው መጣ ነዛሬ ሳምንት ሆዴን በጣም እያመመኝ ተቸግሬ ነበር ።
ለመታየት ወደ ሆስፒታል አመራሁ ልክ ከtaxi ወርጄ የሆስፒታሉ በር ላይ ስደርስ ከአንድ ልጅ ይሁን ሰውዬ ብቻ አላትሞ መሬት ላይ ዘረረኝ ። በጣም ደንግጦ ወይኔ ይቅርታ በሀሳብ ተውጬ ነው ተጎዳሽ የኔ እናት እእ በፈጣሪ ስም ደና ነሽ  ብቻ ምን ልበላችሁ ተርበተበተ ከወደኩበት አነሳኝ ለጊዜው ትንሽ ቢያዞረኝም ያን ያህል ህመም አልተሰማኝም ነበር። ወዴት ነሽ እ ምን ልርዳሽ አለኝ ወደ ሀኪም ቤት ልገባ የነበርኩት ልጅ ወደ ቤቴ ነኝ አልኩት ።
እሺ ነይ እኔ ልሸኝሽ  አለኝ እንኳን ለመንዳት ለማየት ወደምታታሳሳው መኪናው ውስጥ አስገባኝ ።
ይቅርታ አላየሁሽም ነበር እሺ ካመመሽ ወይ የሆነ የጉዳት ስሜት ከተሰማሽ ደውይልኝ ብሎ ቁጥሩን ሰጠኝ ወደ ቤቴ ሸኝቶኝ ተመለሰ ። ይኸው 1 ሳምንት ሙሉ ትዝ አላለኝም ነበር ዛሬ ግን ማክቤልን ለማስቀናት ለአንድም ይሁን ሁለት ቀን ይተባበረኝ ይሆናል ብዬ አሰብኩ።
 
በሰአቱ ስሙን አልነገረኝም ነበር ስልኬ ላይ የገፈተረኝ ልጅ ብዬ ነው save ያደረኩት ያ በደንብ ለማስታወስ ያህል ማለት ነው   

   ስልኬን አነሳሁ ደወልኩ አያነሳም
  ወዲያው ስልኬን ከጄ ላይ ሳላስቀምጠው መልሶ ደወለ ።
     ሄሎ!!!
ሄሎ ጤና ይስጥልኝ ሰላም ነህ (ምን እንዳርበተበተኝ ፈጣሪ ይወቀው)።
   አብሮ ይስጥልን ሰላም ነኝ ማን ልበል?
(ወይኔ ድምፁ ደስ ሲል ከዛ ከርከሮ ማክቤል ተብዬ አንፃርማ ይሄ)....
እእእእ ይቅርታ ሰላም ነኝ እእ ባለፈው ሆስፒታል በር ላይ ገፍትረህ የጣልከኝ ልጅ።
   እእእ አወኩሽ ምነው አመመሽ እንዴ እእ???
አረ አደለም ሰላም መሆኔን ልንገርህ ብዬ ምናልባት ተጨንቀህ ከነበር አልኩት ቀልድ ማውራቴ ነው በኔ ቤት እሱ ግን በስሬስ
እውነት ለመናገር አስቤሽ ነበር ግን በሰአቱ ስልክሽን አልወሰድኩም እና ቢያማት ትደውል ነበር ብዬ ዝም አልኩ።
   አለኝ።
አረ አላመመኝም ደና ነኝ ግን ከይቅርታጋ 1 ነገር ላስቸግርህ ነበር ማለቴ ከተመቸህ ዛሬ ላገኝህ ነበር 1 ጉዳይ ላወራህ ነበር ። (አይና አውጣነቴን ከየት እንዳመጣሁት አላቅም) 
እእ ምነው በሰላም ነው የፈለግሽኝ???
አዎ በሰላም ነው ግን ካልተመቸህ ችግር የለውም ተወው በቃ ።  አልኩት
አረ እንደዛ አላልኩም ወደማታ አካባቢ ስራ ከጨረስኩ አገኝሻለሁ ሰፈርሽ ባለፈው ያደረስኩሽ ቦታ ነው አደል???

   አዎ አዎ እዛ ነው ደውልልኝ ቀደም ብለህ ማለቴ ከተመቸህ አልኩት ።
 እሺ እደውልልሻለሁ መልካም ቀን።
ስልኩ ተዘጋ


ክፍል ሶስት ከ200👍like በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ማድረግ አይርሱ‼️
@Kemrtochmahder