የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 19


.
.
.
የከንቲባው ልጅ በጣም ተጨንቃለች ። የአባቷ ስልክ አለመስራት ፣ ደብረ ዘይት ያየነው ሰውዬ ፣ ወደ ቤት ስንመለስ መብራቶቹ በርተው ማግኘታችን ፣ በቃ ሁሉም ነገር መጥፎ መጥፎውን እንድናስብ አርጎናል ። ከዚህም በላይ ደግሞ ያሳሰባት ነገር እኔን የሷ ችግር ውስጥ ማስገባቷ ነው ። አዚህ ቤት ውስጥ መሆን ይበልጥ ስለ ችግሩ እንድናስብ እንደሚያደርገን አውቃለሁ ። ይዣት ወጥቼ እንዳላስረሳት ፤ አባቷ እንዳሉትም ዛሬ የሚመጡ ከሆነ ከቤት እንዳያጧት ስለሰጋሁ ነው ። ለፖሊስ እንዳናመለክት ስለጉዳዩ ትተው ወደኛ እንደ ሚዞሮ ግልፅ ነው ። የሚከታተለንን ሰውዬ ትተው እኛን "እናንተ ማናችሁ ፣ ይሄ ቤት የማነው ፣ ይሄን ሁሉ ንብረትስ ከየት አመጣችሁ ...?" ከማለት አያልፉም ። ለጊዜው እንደ መፍትሔ ያየሁት ፊልም ማየቱን ነውና After የሚል ምርጥ የፍቅር ፊልም ሶፋ ላይ ሆነን እያየን ነው ። በመሀል በመሀል ሲሳሳሙ እየተሳሳምን ፣ ሲተቃቀፉ እየተቃቀፍን ፣ ሲጣሉ ደግሞ በመሃላችን ክፍተት እየፈጠርን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ፊልሙ አለቀ ። በፊልሙ ላይ ቅር ያለን ነገር ቢኖር ሲያልቅ ተዋንያን ሲፅፍ የኛን ስም አለመጥቀሳቸው ነበር ። እሱን እንደ ጨረስን ቁርስም ስላልበላን በጣም እርቦን ስለነበር ተያይዘን ወደ ኩሽና ገባን ። የጊቢ ተማሪ ሞያ + የቤት ልጅ ሞያ = ሞያሽ ሞያሽ ይዘርዘርልሽ ። ቁርስን መቀነስ ፣ ምሳን መሰረዝ ፣ እራትን ማሳነስ ብዙ ዕድሜ ለመኖር ዋስትና ነው ይላሉ ከቤተሰብ የተላከላቸውን ብር በአንድ ሳምንት የሚጨርሱ የጊቢ Non cafe ተማሪዎች ። በአለማችን ላይ በረሃብ የሞቱ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው ። በተቃራኒው ግን በጥጋብ የሞቱት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ናቸው ። ስንቶቻችን ነን በምላሳችንና በጥርሳችን መቃብራችንን ስንቆፍር የምንውለው ...! ሆድ እንዳሳዩት ነው ፣ ወስፋታችንን መግታት ከብዶን ሁሉንም እችላለሁ ብለን አግበስብሰን ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ የምንበላ ከሆነ መጨረሻችን እስኪሻለን ድረስ መፆም መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል ። አንዳንድ ሰዎች "ስትበላ እንደልብ ፣ ስትጠጣ እንደልክህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላችኋለሁ 'ሲርብህ ብላ ፣ ሲጠማህ ጠጣ' ። ፈላስፋው ሶቅራጥስም በዘመኑ "እኔ ለመኖር ስበላ ፣ ሌሎች ግን ለመብላት ይኖራሉ" ብሎ ነበር ። በዚህ ዘመን ግን ሀብታም ከሆነ በፈለገ ጊዜ ፣ ደሀ ከሆነ ደግሞ በአገኘ ጊዜ ሆኗል ነገሩ ። anyways ቤት ውስጥ ስጋ ነክ ነገሮችና እንጀራ ለጊዜው ስለሌሉ ቆንጆ ፓስታ ከከንቲባው ልጅ ጋር ተባብረን ሰርተን ተባብረን በልተናል ። ከሰዓታችንን ደግሞ መፅሐፍ በማንበብና ሙዚቃ በመስማት ልናሳልፈው አቅደናል ። ከአጫጭር የልቦለድ መፅሐፍት ውስጥ የአሌክስ አብርሃም "ዶክተር አሸብር" የሚለውን በጣም ስለምወደው እሱን ተራ በተራ የምንወደውን ርዕስ እየመረጥን አንዳችን ላንዳችን እያነበብን ከልባችን እየሳቅን ሳናስበው ቀኑ ለምሽት መንበርከክ ጀመረ ። በስተመጨረሻም ካሏት የግጥም መፅሐፍት ውስጥ አንዱን መርጬ በጣም የምወደውን አንድ ግጥም እንዳነብላት ጋበዘችኝ ። እኔ ግን Control ብፌው ውስጥ የሚታየኝን ወይን ከሁለት ብርጭቆ ጋር አውጥቼ ፣ እጇን ይዤ ከሳሎን ወደ ጊቢ ውስጥ ወጣን በረንዳ ላይ ተቀመጥንና ወይን እየጠጣን ጨረቃዋን እያየን የምወደውንና በቃሌ የማውቀውን አንድ ግጥም በዜማ እልላት ጀመር እንዲህ ብዬ

"አመሻሽ ላይ ሆኜ ፡ ሳስብሽ ሳስብሽ
በረንዳ ላይ ሆኜ ፡ አንቺኑ ስስልሽ
ስላንቺ የሚያወሳ ግጥም ስፅፍልሽ
ዕምባ ከአይኖቼ ፡ ዱብ ዱብ እያሉ
አይኔና ጉንጮቼ ፡ በዕንባ ሲሞሉ
ከሰማይ ላይ ሆና ፡ ትታዘበኛለች
እጇን በአፏ ጭና ፡ ታፈጥብኛለች
ደንገጥ አልኩኝና ፡ ዕምባዬን ጠረኩኝ
እሷም ቀስ በቀስ ፡ እኔን ቀረበችኝ
ብርሃኗ ልዩ ነው ፡ ሁሉን የሚያስረሳ
ፈዝዤ ቀረሁኝ ፡ ፎቶ እንደሚነሳ
እኔጋር ደረሰች ፡ ከዋክብት አጅቧት
መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ ፡ እኔም በፍርሃት
ጠጋ አለችና ፡ አይዞህ ጨረቃ ነኝ አለችኝ
አትፍራ አትሽሽ ፡ ብላ አቀፈችኝ
ኮከብ እንዳጀባት እየነገረችኝ
እንባዬን ጠራርጋ ፡ አይኖቼን እያየች
በሹክሹክታ መንፈስ ፡ ማውራት ጀመረች
አይዞህ ጠንከር በል ምንም አትሆንም
እውነት ካፈቀርቃት የትም አትሄድም
ለፍቅርክ ምስክር ፡ እሆንልሀለው
ካለችበት ሄጄ እነግርልሃለው
ያቺ ውብ ጨረቃ ቀርባ አፅናናችኝ
ለተከፋው ልቤ ደስታን ሰጠችኝ
"ጤዛ ሞቷን ሞታ ፡ ኮከብ ባናት ስትወጣ ፣
ድምፅ ወደኔ መጣ ፡ አለኝም ጠጣ
አንተ ድንቅ ፍጡር ጠጣ ፡ ወደኔ እስክትመጣ"

የሚለውን ግጥም መረኩላትና ወይናችንን እየጠጣን የጨረቃን ውበት ማድነቅ ጀመርን አይኖቻችን ግን እሷ ላይ ለመቆየት ብዙም የፈለጉ አይመስለኝም ከኛ በብዙ ሺህ እጥፍ የምትርቅ ፣ ያውም የማናገኛት ጨረቃ ላይ ከማፍጠጥ ይልቅ የቅርባችን ይሻላል ብለን አይኖቻችን ውስጥ ያለውን ጨረቃ ለመፈለግ ይመስል እርስ በእርስ መፋጠጥ ጀመርን ብዙም ሳንቆይ ህይወት ወለላዋ ፣ ነክታኝ በስምያዋ ኑር ለዘላለም ስትል ፣ ከንፈሮቿ ነፍሴን ከአፋፍ ላይ አወጧት ፣ ባይኔ እያየሁ ወደ ጨረቃዋ አከነፏት ። መቼም የማልደርስባት ፣ ማገኛት ማይመስለኝ ፣ ያቺን እሩቅ ያለች ጨረቃ አፌን በአፏ ጎርሳ አሳየችኝ ። ከንፈሬ ከንፈሯን ፈልቅቆ ሲነካው ፣ ነፍሴ ከነፍሷ ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ነው የሚመስለኝ ። ከንፈሯ ደግሞ ለስላሳ ነው ፤ ለዘለዓለም እንድትስመው ይገፋፋል ። መሞት ካለብኝ ልሙት ፤ ሞቴ ግን ከንፈርሽ ላይ ይሁን የሚያስብል ፣ ምሽቱ ነግቶ ፣ ወፎች እስኪንጫጩ ፣ ምድርም እስክትነቃ ድረስ ልቀቁኝ የማይል ከንፈር ። (ኧረ በህግ አምላክ ልቀቃት ...
። በስንት መከራ ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን ማውራት ጀመሩ ። የከንቲባው ልጅ ከብዙ ዝምታ በዋላ "በህይወቴ አንድ የማይሰለቸኝን ነገር ልንገርህ...?" አለችኝና ቀጠለች "ካንተ ጋር #24 ሰዓት ማሳለፍ ፣ እንደውም ሰዓቱ በጣም አንሶኛል ፣ ሰዓቱም ልክ ቀናቱ #365 በሆነልኝ ። ቀናቱን ሁሉ ፣ ሳምንቱን ሙሉ ፣ ወራቱን እንዳለ ፣ ዓመታቱንም እንደዛው ካንተ ጋር በሆንኩ ። ካንተ ጋር ከሆንኩኝ ሁሉም ቀን ለኔ የፍቅር ቀናት ናቸው ። አንተኮ መውደድን የማነብብህ ደብተሬ ፣ ፍቅርን የማይብህ መስታወቴ ፣ ያለ ስጋት የምኖርብህ ሀገሬ ፣ በእስትንፋስህ የምተነፍስ ንፁህ አየሬ ነክ ። ባንተ ፍቅር እንደ ጤፍ ሺህ ቦታ ብትንትን ብልም ባንተው ፍቅር ደግሞ ይኸው እየኖርኩ ነው ። በህይወቴ ውስጥ አንተን ስላገኘሁ በጣም ደስተኛ ነኝ ። በምታደርገውና በምትለኝ ነገሮች የተለየሁ እንደሆንኩ ያክል እንዲሰማኝ ታደርጋለህ ። እናም በጣም ነው የምወድህ ፤ ሁሌም ደግሞ አደርገዋለው" ብላኝ አይኖቿን ጨፍና ከንፈሬን ድጋሜ ስትስመኝ ከውጪ በሩ ተንኳኳ ። ደንግጠን ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን በሩ ላይ አረፈ ። የልብ ምታችንም ከሚንኳኳው በር በላይ ይሰማናል ። እኔ ምናልባት አቧቷ ከሆኑ ብዬ ለጥንቃቄ ወይኑንና ብርጭቆዎቹን ይዤ ወደ ቤት ውስጥ ገባሁና ኩሽና አስቀምጬ ወደ ሳሎን ተመልሼ በመስኮት የሚሆነው ነገር መከታተል ጀመርኩኝ ።
@babusem
😘የከንቲባው ልጅ😘

ክፍል 20


.
.
.

ወደ ውስጥ አንድ ሰው ገባና በሩን ዘግቶ ከህይወት ጋር ጥምጥም ብለው ተቃቀፉ ። አባቷ ናቸው አልኩኝ በልቤ ። ደንግጬ ወዴት እንደ ምሄድ ግራ ገብቶኝ ወደዚያ ወደዚህ ስል አንዴ ከግድግዳ ጋር ተላተምኩና ግንባሬን እያሻሸው ወደ ከንቲባው ልጅ ክፍል ገባሁ ። ለማየትና ለመስማት እንዲያመቸኝ የክፍሉን በር ሙሉ በሙሉ አልዘጋሁም ። መብራት ግን አጥፍቻለሁ ። አባትና ልጅ ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ ። ደስ የሚለው አባቷ ላለሁበት ክፍል ጀርባቸውን ሰጥተው ነው የተቀመጡት ። ህይወት ደግሞ በኔ ፊትለፊት ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ከፀሀይ በላይ ፈክታ በናፍቆት ወደ አባቷ እያየች ታወራለች ። "አባቢ ደና ነህ አይደል ፡ እኔኮ ተጨንቄ ስልክህ ላይ ከጠዋት ጀምሮ ስሞክር ነበር ፤ ግን አይሰራም" አለቻቸው ። አባቷም "የኔ ህይወት አመሻሹ ላይ ነው እኮ አዲስ አበባ የገባሁት ፤ እረፍት ሳልወስድ ነው በዛው በድሬ plane ወደዚህ የመጣሁት" አሏት ። "ደክሞሀል አይደል በሙቅ ውሃ እግርህን ልጠብልክ ...?" ስትላቸው "አይ ፡ ባይሆን ሻዎር ልውሰድና ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ" ብሏት ተነስቶ ግንባሯን ሳሟትና እኔ ወዳለሁበት ቦታ አመሩ ። ደንግጬ ከበሩ ጀርባ ተደበኩኝ ። ካለሁበት አጠገብ በቀኝ በኩል ያለው ክፍል ሲከፈት ይሰማኛል ። ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ቤት ስመጣ የከንቲባው ልጅ "አባቴ ሲመጣ እዚህ ነው የሚያድረው" ያለችኝ ክፍል ነበር ። ከትንሽ ደቂቃ በዋላ ተመልሶ ተዘጋና ወደኔ እየቀረበ የሚመጣ የእግር ኮቴ እየሰማው አልፎኝ ሄደና በግራዬ በኩል ያለው ክፍል ተከፍቶ ወዲያው ተዘጋ ። በሆዴ 'አባቷ ሻዎር ገቡ ማለት ነው' ብዬ ሳልጨርስ በድጋሜ ወደኔ የሚመጣ የሰው ኮቴ ሰማሁ ። በቅስፈት ያለሁበት ክፍል መብራት ሲበራብኝ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ። ኡፍፍፍ ፡ የከንቲባው ልጅ ነበረች ። "እዚህ ነህ እንዴ ...?" አለችኝ በሹክሹክታ ። (አያይ ፡ ኩሽና ነኝ ...) ። ስናወራ ድምፃችን እንዳይሰማ ሰግተን Telegram ገብተን txt መላላክ ጀመርን ። 'እስከ መች ነው ግን ከአማቼ ጋር ድብብቆሽ የምጫወተው ...?' አልኳት ለጨዋታው ድምቀት ። አንብባ ከት ብላ ሳቀችና መልሳ ደግሞ ደንግጣ በግራ እጇ አፏን ከድና "እኔኮ ወንድ መስለኸኝ ነበር ላስተዋውቅህ እዚህ ድረስ ያመጣሁክ ፤ አንተ ግን እንደ ሴት ጓዳ ለጓዳ ትሽሎኮሎካለህ" ብላ መለሰችልኝ ። 'ተነስቼ ሻዎር ቤት ገብቼ እንዳልተዋወቃቸው' ስላት "ወንድ ነህ አ" አለችኝ ። ወንድነት ተሰማኝ መሰለኝ ከአልጋዋ ላይ ተነስቼ ወደ በሩ አመራሁ ። በሩን ከፍቼ ልወጣ ስሞክር ምንም ሳይመስላት ቁጭ ብላ ታየኛለች ። "ኧረ ተመለሰ ቀልድ አታውቅም እንዴ ...?" የሚል ልመና ነበር የጠበኩት ። (ግን ወፍ የለም ...) ። ወደ አልጋው ተመልሼ ሥርዓቴን ይዤ ተቀመጥኩ ። የከንቲባው ልጅ ለሴኮንዶች ስልኳ ላይ አቀርቅራ ቀና ስትል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ። ማንበብ ጀመርኩኝ "አየህ ፡ የብዙ ሰዎች ችግር ይሄ ነው ገላጋይን ተስፋ አድርገው ይጣላሉ ፣ ይለምኑኛል ብለው ይዳፈራሉ ፣ ይጠሩኛል የሚል አጉል ተስፋ ይዘው ይሄዳሉ አንተም እንደዛው ነው የሆንከው የኔ ጌታ የሚል ነበር (sticker እኔ ጨምሬበት አይደለም) እንዲሁ በ txt እየተበሻሸቅን ከደቂቃዎች በዋላ የሻዎር ቤቱ በር ሲከፈት ተሰማን ወዲያውኑ አባቷ "ህይወት ፣ ህይወት" እያሉ መጣራት ጀመሩ የሲሊፐር ድምፅም "ጣ ጣ" እያለ እኛ ወዳለንበት ክፍል እየቀረበ መጣ
በብርሃን ፍጥነት እኔ ከአልጋው ላይ ተነስቼ በሩ ጀርባ ስደበቅ የከንቲባው ልጅ ደግሞ ተስፈንጥራ በሩን ከፍታ ደጃፋችን ላይ የደረሱት አባቷ ወደ ውስጥ እንዳይገቡ በሩ ላይ ቆማ "አባዬ ክፍል ተሳስተሃል ቀጣዩ እኮ ነው ያንተ" አለቻቸው በፍርሃትና በሚንቀጠቀጥ ድምፅ "እሱማ መች ጠፋኝ ከሳሎን ሳጣሽ ጊዜ ነው የጠራውሽ" አሏትና ወደ ክፍላቸው ሄዱ ህይወት በረጅሙ "ኡፍፍፍ" ብላ ተነፈሰች ፤ እኔም እንደዛው "ከዚህ ክፍል ንቅንቅ እንዳትል" የሚል ማስጠንቀቂያ በጆሮዬ እያንሾካሾከች ሰጠችኝና ወደ ሳሎን ተመልሳ ተቀመጠች ያለሁበት ክፍል በር እንደ ቅድሙ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም ሳሎን ውስጥ የሚደረገውን ማየትም መስማትም እችላለሁ አባቷ ከደቂቃዎች በዋላ በለሊት ልብስ ከክፍላቸው ወተው ወደ ሳሎን ተመለሱ ። ትልቅ ሰው ናቸው እድሜያቸው በግምት ወደ #40 ዓመት ይጠጋል አሁንም እንደ ቅድሙ ጀርባቸውን ሰተውኝ ተቀመጡ "እስቲ ሂጂና ወይን አምጪልኝ!" አሏትና ወይን ከነመጠጫው ይዛላቸው ተመለሰችና እየቀዳችላቸው "አባቢ ቅድም እኮ ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ ብለህ ነበር ። ምንድነው እሱ ?" ብላ ጠየቀች ። "እይውልሽ የኔ ህይወት" ብለው ንግግራቸውን ጀመሩ "አንደኛው ነገር ፡ እንደ ምታውቂው የከንቲባነትን ስራ የጀመርኩት የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ ነበር እናም በየ #4 ዓመቱ ሌላ ዓዲስ ከንቲባ ይመረጣል በዚህም መሠረት የኔ የስልጣን ጊዜ ቆይታ ተገባዶ ወደ ሌላ ሰው የሚያልፍበት ሰዓት ላይ ደርሷል ስለዚህ ከቅርብ ቀን በዋላ እኔ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አይደለሁም ማለት ነው" ሲሏት ህይወት በደስታ ዘላ ተጠመጠመችባቸው አባቷ ንግግራቸውን ቀጠሉ ፡ "የኔ ህይወት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለስልጣን መሆን ክብደቱ ከስራው ይልቅ አንዴ ገብተውበት የስልጣን ጊዜውን ሳይጨርሱ ለመልቀቅ መሞከሩ ነው የዛሬ #4 ዓመት ያኔ ልክ አንቺላይ የግድያ ሙከራ እንዳደረጉ ስራውን ለቅቄ ይዤሽ ከሀገር ለመውጣት አስቤ ነበር ግን ስልጣኑን የተረከብኩበት ጊዜ ስለነበር ሁሉም ነገሮች በኔ እጅ ውስጥ ሆነው ስለተጀመሩና ሴኔቱ እንዳለ የኔን መልቀቅያ ወረቀት ውድቅ ስላደረገው ምንም ማድረግ አልቻልኩም ለማንኛውም አሁን እሱን ተይና ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እኔ ያንቺና ያንቺ ብቻ ነኝ ። ሁለተኛው እና ዋነኛው ነገር ደግሞ" ብለው ቀጠሉ "የኔ ህይወት አሁንም ለኔና ላንቺ እዚህ መኖር አደጋ ሊኖረው ይችላል ከሰዎቹ ጋር ችግር ውስጥ መግባት አልፈለኩም ። ክፉ ሰው የተቀጣው ክፉ የሆነ ቀን ነው እነሱን ብበቀል ያንቺ ህይወት ያሳስበኛል ትቻቸው እዚህ ብኖር ደግሞ ምናልባት ያንቺን በህይወት መኖር ካወቁ ሊነጥቁኝ ይችላሉ ያኔ አንቺን ለመግደል ብለው አቤል ላይ የተኮሱት በወቅቱ እኔ ስልጣን ላይ ከወጣሁ በዋላ በከፍተኛ የሀላፊነት ወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ይሄን ፍቅር የሆነ ምስኪን የድሬዳዋ ህዝብ እየበዘበዙ ነበር ። እነሱን ግማሹን ከስልጣን ላይ አንስቼ ሌላ ሰው ስተካና ለቀሩት ደግሞ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ስሰጣቸው ነበር ባንቺ ፋንታ አቤል ላይ ጉዳቱ የደረሰው ከቅጣት ሁሉ የበለጠ ቅጣት ጠላትሽን መግደል አ

​​ይደለም ፤ እሱ አብልጦ የሚወደውን እና የሚኖርለትን ነገር ማሳጣት እንጂ ለዛም ነበር እኔን ትተውኝ አንቺን ለማጥፋት የተነሳሱት" ስለዚህ ከዚህ ሀገር ወተን መሄድ ግድ ነው በቅርቡ ተያይዘን አሜሪካ ሄደን በነፃነት እንኖራለን" አሏት
.✎ @babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 14


.
.
.
ብዙም አልተኛሁም ነበር ። በትካዜና በሀዘን እንደ ዳግም ምፅአት የራቀኝ ለሊት ነጋ ። የኔስ ይሁን የራሴ ችግር ነው ። የከንቲባውን ልጅ ግን ለማዝናናት ይዤ መጥቼ ቀኗን አበላሸሁ ። ጠዋት ከእንቅልፍ ሳይሆን ከአልጋው ላይ ስነሳ "ደና አደርክ የኔ ጌታ ፡ ቁርስ ቀርቧል እሺ ቶሎ ፊትህን ታጥበህ ና" አለችኝ ። ቁርሱን ከበላን በዋላ 'ትናንት እንደዛ ስለ ሆንኩብሽ በጣም ይቅርታ' ስላት "ኧረ አያሳስብም ፡ እኔ ከዛ በላይ ሆኜብህ አልነበር እንዴ ፡ ባይሆን ካሁን በዋላ እንደዛ አትሁን እሺ ፡ የሰውን እምባ ጠርገው እያሳሳቁ የምን ለራስ ማልቀስ ነው ...?" አለችኝ በአሽሙር መልክ ። ቀጥላም "ካሁን በዋላ እንደውም ከቴዲ አፍሮ ሙዚቃ #ማራኪዬ የሚለውን ሳይሆን #መማፀኔ የሚለውን መውደድ ያለብክ ይመስለኛል" አለችኝና ድምጿን ከፍ አድርጋ ዘፈኑን ታዜምልኝ ጀመር ።

"በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ ፡
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ ፣
ሳይገባኝ ለኔ ፡ የቱጋ እንደሆን እንኳን ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ ።
መማፀኔ ፡ ማሪኝ ማለቴ ፡
ለኔስ ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ፣
ታድያ እንዴት ይሆን ፡ ወዳጅን ነግሮ ፡
ልብን መመለስ ወደ ድሮ" ።

ቆሜ ነበር ያጨበጨብኩላት ። ስትዘፍን ድምጿ ስያምር ። በቃ ሴቷ ቴዲ አፍሮ ብያታለሁ ። "ከቤት ስለማልወጣ ስዕልና ሙዚቃ እቤት ውስጥ እሞክራለሁ ። እስካሁን አባቴ ከሰጠኝ ስጦታዎች መካከል በጣም የምወደው ጊታር'ን ነው ። ሲከፋኝና ብቸኝነት ሲሰማኝ በጊታሬ እዘፍናለሁ ። አንተ ከመጣህ ወዲህ ብቸኝነት ስላልተሰማኝ ነው እሺ ጊታሩን አውጥቼ ያልተጫወትኩት" አለችኝ እያሾፈችብኝ ። ከዛን "ስማኝማ ፡ ዛሬ ማክሰኞም አይደል ፡ ደብረ ዘይት ላይ የመጨረሻ ቀናችን እኮ ነው ። ታውቃለህ አባዬ ባለፈው ሀሙስ ነበር ሳምንት እመለሳለሁ ብሎ የሄደው ። እና ሳምንቱ ደግሞ ከነገ ወዲያ ስለሆነ ነገ ወደ ድሬዳዋ መመለስ ይኖርብናል" አለችኝ ። በግልጽ ባትነግረኝም ለማለት የፈለገችው ነገር ገብቶኛል ። የዙሪያ ጥምጥሙ ፍቺ ፈታ እንበል የሚል መሆኑ ነው ። ከዛ በፊት ግን ልጠይቃት ብዬ የረሳሁትን ነገር የአባትዋን ስም ስታነሳ ትዝ አለኝ ። 'ስሚማ ፡ አባትሽ ግን ለምን ይሄን ሁሉ ዓመት ለብቻሽ በአንድ ቤት ውስጥ እንዳስቀመጠሽ እኮ በግልጽ አልነገርሽኝም...? ፡ ማለቴ አባትሽ በስልጣኑ ምክንያት ከሰዎች ጋር ችግር ውስጥ ገብቶ አንቺላይ ጥቃት እንዳይደርስ ከፈራኮ አንቺን በአንድ ቤት ውስጥ ከማስቀመጥ ይልቅ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ይችል ነበር ' አልኳትና ጠየኳት ። እሷም "የመጀመርያው ፡ አባቴ ብቻውን ስላሳደገኝ ፣ ከኔ ውጪ ማንም ስለሌለውና ከኔ ተለይቶ መኖር ስለማይችል ነው ። ሁለተኛው ፡ ውጪ ቢልከኝም እዛ ማንም ስለሌለን ከፈረንጅ ነፃነት የሀገር ውስጥ እስረኛ መሆን ይሻላል ብሎ ነው ። ያው 'ከማያውቁት መላክ ፡ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል' ይባልም የለ ። ሲጀምር እሱ ሂጂም ቢለኝ ከሱ ተለይቼ ውጪ ሀገር መኖር አልፈልግም" አለችኝና ሶስተኛው ብላ ልትቀጥል ስትል 'ኧረ ይበቃል ፡ ሶስተኛ ፣ አራተኛ እያልሽ ከቀጠልሽማ ሳንዝናና መሽቶ መንጋቱ ነው' አልኳትና ይዣት ተነሳን እና ከአንዱ ምግብ ቤት ገብተን ምሳ ከበላን በዋላ "ፍቅር ግን ለአንተ ምንድነው...?" አለችኝ የከንቲባው ልጅ በልጅቷ የቅድሙ መልስ እንደኔው ተገርማ ። 'እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም ብያንስ አንድ ጊዜ አፍቅረናል ። እንደውም አብዛኞቻችን የፍቅርን ትርጉም ሳናውቅ ነው ያፈቀርነው ። anyways ፍቅር ግን ለኔ ...! አንድ ወንድና ሴት ተፈላልገው የሚመሰርቱት ግኑኝነት ...? ፡ እሱ ነው ፍቅር ...? ፡ አይመስለኝም ። እስቲ ወይ የራስሽን ወይንም ደግሞ የጓደኛሽን የፍቅር ታሪክ ለትንሽ ደቂቃ አስቢው ። እያሰብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ ። እርግጠኛ ሆኜ የምነግርሽ እራሳችንን ወደን እንጂ ሰውን አፍቅረን አናውቅም ። እንዴት...? ለምትዪኝ :- በመጀመሪያ ወንድ ከሆነ አንዲት ሴትን ፡ ሴት ከሆነች ደግሞ የሆነ ወንድ ፡ በሆነ አጋጣሚ ያገኛሉ ። የሆነ ነገሯ ይማርከዋል ፡ #90% መልኳ ፣ አካሄድ ፣ አለባበስ ፣ አነጋገር ፣ ወዘተ ። ይተዋወቃሉ ፡ ሊግባቡም ላይግባቡም ይችላሉ ። ጉዳዩ እሱ አይደለም ። ከጥቂት ቀናት በዋላ ፡ ካላገኘዋት ፣ እጄ ካላስገባዋት ፣ የኔ ካልሆነች ፣ ህይወቴ ካለሷ ባዶ ነው ፣ ወዘተ ማለት ይጀምራል ። እዚህ ጋር ልብ በይ እንግዲህ ። አነዚህን ነገሮች እያለ ያለው ለልጅቷ አስቦና ተጨንቆ አይደለም ፡ ለራሱ ፍላጎት እንጂ ። ስለናፈቀችው ፣ ደስ ስላለችው ፣ ስለምታምር ፣ ከሷ ጋር ከሆነ ደስተኛ እሆናለሁ ብሎ ስለሚያስብ ፣ ባጠቃላይ ልጅቷ ትሆነኛለች ብሎ እንጂ ፡ ለልጅቷ እሆናታለው ፣ ብሎ አይደለም ። አስተውይ ፡ መጀመሪያ ላይ አፈቀርኳት ብሎ ሲያወራ የሱ ህይወት ካለሷ ባዶ ሆኖ ስለተሰማው እንጂ የሷ ህይወት አሳስቦት አይደለም ። የሱ ጭንቀት እንጂ የሷ ፍላጎት አልታየውም ፤ አያውቅምም ። በቃ በዛ ሰዓት እሱ የሚፈልገው ነገር ቢኖር ልጅቷ የሱ እንድትሆን ነው ። የሱ ብቻ ። እሷ እንኳን የሌላ ሰው ሆና ማየቱ ይቅርና ሰላም እንኳን ቢሏት ካልገደልኳቸው ሊልም ይችላል ። እሷን ከራሱ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ለሴኮንድ እንኳን ማሰብ አይፈልግም ። እሷ አልፈልግህም ብትለው እንኳን በግድ ካልሆንሽ የሚል ጉድ ውስጥም ሊገባ ይችላል ። አስቢ ይሄን ሁሉ እያደረገ ያለው ለራሱ ሲል ነው ። ይሄንን ነው እንግዲህ ፍቅር ብለን የጠራነው ። እመኚኝ ግን ከዚህ ሰው በላይ እራስ ወዳድ ሰው በምድር ላይ የለም ። የፍቅር ትርጉም ግን ይህ አልነበረም ። ፍቅር ከራስ አልፎ ለሰዎች ሁሉ መኖርና መሞት ነው ። ቢተያዩም ባይተያዩም ፣ ብታምርም ባታምርም ፣ ለሱ ህይወት አስፈላጊ ሆነች አልሆነች ፣ እውነተኛ ልብ ካለው ያኔ የእውነት ፍቅር ከልቡ ይገባል ። በአይኑ ሳይሆን በልቡ ማየት ሲጀምር እሱ ሳይፈልገው ቤቱ ድረስ መጥቶለት ደጁን ያንኳኳል ። አፍቃሪ መሆን ከፈለገ ከልቧ ውጪ ምኗንም ሳያይ ፣ ምንም ሳታደርግለት ፣ ብትበድለው ብትክሰው ፣ ለሱ ሆነች አልሆነች ፣ ባጠቃላይ የሷ ነገር አሳስቦት እንጂ የሱ ጎዶሎነት ተሰምቶት አይውደድ ። ለጎዶሎው ብሎ ካፈቀረ አንድ ቀን እንዳልተሟላለት አስቦ ሊተዋት ይችላል ። የሷን ጎዶሎ ሊሞላ ቢሯሯጥ ግን አትራፊ ይሆናል ። ቅዱሱ መፅሐፍም "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" አይደል የሚለው ። ክርስቶስስ ከሰማይ ላይ ወርዶ የሰውን ስጋ የለበሰው ለራሱ ጥቅም ይመስልሻል ...? ፍቅር መጠቀም ሳይሆን መጥቀም ነው ። እውነተኛ አፍቃሪ በነገሮች ሁሉ ቅድምያ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ሰው ሰጥቶ የሚጠቅም እንጂ የራሱን ችግር ለማሸነፍ ብሎ በሌሎች የሚጠቀም አይደለም...
"አንተ ልጅ ግን ሰባኪ ነገር ነህ እንዴ ...?" አለችኝ ሳወራላት የነበረውን ሁሉ በተመስጦ አይን አይኔን ትኩር ብላ እያየችኝ ከሰማችኝ በዋላ ። ቀጥላም "ቆይ ግን አንተ ሴት ልጅን መተህ አታውቅም ...?" አለችኝና ብዙ ዓመት ወደዋላ እንድመለስ አረገችኝ ። 'ትዝ ይለኛል እንደ ትናንት ፡ ከ #10 ዓመት በፊት በ #2001 ዓ.ም #4ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። #6ኛውን period ተምረን ተደወለ ። ምሳ ሰዓት በመሆኑ ፣ እቤታችንም ለት/ቤቱ ቅርብ ስለነበረ ወደ ቤት ለመግባት ቦርሳዬን ይዤ ከ desk ላይ ተነሳሁ ። ነገር ግን አጠገቤ ትቀመጥ የነበረችው አቢጊያ የምት
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 17


.
.
.
"ሰዎች መሞት አይፈልጉም ነገር ግን ፣
መንግሥተ ሰማይ መግባት ይፈልጋሉ ።
ንሰሐ አይገቡም ግን ሁሉንም የሰፈር ዕድር ገብተዋል"።

ሲመስለኝ አሁን ሞት ለ #3ተኛ ጊዜ ነገር እየፈለገኝ ነው ። የከንቲባው ልጅ ከመፍራቷ የተነሳ ጥቅልል ብላ ደረቴ ውስጥ ሽጉጥ ብላለች ። ("ሞት ርስት ነው ፤ መፈራቱስ ለምንድነው ...?") ። የጠረጠርነው ሰውዬ ይመጣ ይሆን እያልን በጉጉት (ይቅርታ በፍርሃት...😬) እየጠበቅን ነው ። እስካሁን ግን ምንም ነገር ሳናይና ሳንሰማ ቀኑ ወደ ምሽት ተለወጠ ። ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል ። እኛም ድምፃችንን ብቻ ሳይሆን ትንፋሻችንን ጭምር አጥፍተን ኩርምት ብለን ተቀምጠናል ። በድንገት ሳናስበው በራችን ሲንኳኳ ሁለታችንም ከአልጋው ላይ ተስፈንጥረን ተነሳን ። ቀስ ብዬ ወደ በሩ አመራሁና 'ማ ማ ማነው...?' አልኩኝ በተንቀጠቀጠ ድምፅ ። "እኔ ነኝ" አለ ድምፁ አዲስ ያልሆነብኝ ሰው ። 'አንተ ማነህ ፡ ስም የለህም' አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ ። "እኔ ነኝ የናንተን የዕንግድነት ቆይታና መስተንግዶ የምከታተል" አለን በትህትና ። ሁለታችንም በሀይል ኡፍፍፍ አለንና በሩን ከፈትኩለት ። "ዛሬ ምነው ድምፃቹ ጠፋ ፡ ምሳ ላይም አልነበራቹም ፡ እራቱንም ልትዘልቁበት አስባቿል እንዴ ...?" አለን በተለመደው ትህትናና ፈገግታ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #01:33 ይላል ። እራት እዚው እንዲያ መጣልን ነግሬው እጅ ነስቶ ተመለሰ ። ብዙም ሳይቆይ ምግብ ከወይን ጋር ይዞ መጣ ። የምግብ ፍላጎት ባይኖረንም ነገ መንገደኛ በመሆናችን እንደ ነገሩ አድርገን ከላይ ትንሽ ወይን ከለስንበት ። በስተ መጨረሻም የእስካሁኑን ሙሉ ወጪ አስደምረን ከፍለንና አመስግነን ከአስተናጋጁ ጋር ተለያየን ። ለነገ ጠዋት #12:00 ሰዓት Alarm ሞልተን አንሶላ ውስጥ ገባን ። "ሞት ወደ ትጉህ ነፍስ ፣ እርጅናም ደግሞ ወደ አፍቃሪ ልብ አትመጣም" በሚለው ቃል እራሳችንን አሳምነን ተኛን ። ጠዋት ነግቶ Alarm እኛን ሳይሆን እኛ አላርሙን ቀስቅሰነው ከውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ወደ በረሃዋ ንግስት ድሬዳዋ ጉዞ ጀመርን ። አዲስ አበባ ፣ አዳማ ፣ አዋሽ ፣ መታሃራ እያለን ሂርና ደረስን ። ወርደን ምሳችንን ዕሮብ በመሆኑ ቆንጆ በየ አይነት በልተን ጉዞ ቀጠልን ። ከዋላችን ከተለመዱት የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና ሚኒባሶች ውጪ የተለየ አይነት መኪና ስላላየን ውስጣችን ለጊዜው ሰላም ተሰምቶታል ። ሙቀቱንና የመንገዱን አሰልቺነት ተቋቁመን ፣ የደንገጎን አስፈሪ ተራራማ zigzag ቁልቁለት መንገድ ወርደን #11:00 ሰዓት አካባቢ ድሬዳዋ ገባን ። ለጥንቃቄ ብለን ቀስ ስላለች እንጂ የሸገር ድሬ መንገድ ለትክክለኛው ሾፌር ከ #9 ሰዓት አያልፍም ። Tata የሚባሉት አውቶብሶች ግን በጣም ደካማ ስለሆኑ ጠዋት #12:00 ሰዓት ከሸገር ተነስተው ምሽት #03:00 ሰዓት ድሬ የሚገቡበት ሰዓት ይበዛል ። ለጊዜው ድሬዳዋ ራስ ሆቴል አርፈን እራት እዛው በልተን ትንሽ አምሽተን ወደ ከንቲባው ልጅ ቤት በከዚራ በኩል አድርገን አቀናን ። የቀድሞ ቤቷና የአባቷ መኖርያ ቤት አካባቢ ስንደርስ መኪናውን አቆመችና ለትንሽ ደቂቃ ትኩር ብላ በቁጭት አየችው ። እምባዋ ጉንጮቿ ላይ ሳይራመዱ ታፋዋ ላይ ዱብ ዱብ ማለት ሲጀምሩ ፤ አይኗን ከቤቱ ላይ ነቀለችና እምባዋን ዋጥ አድርጋ መኪናውን አስነስታ ወደ ራሷ ፣ ከአባቷ ውጪ አንድም ሰው ወደ ማያውቀውና ዝር ወደማይልበት ቤት አመራን...
ከምሽቱ #02:00 ሰዓት አልፏል ። የከንቲባው ልጅ ቤት ደርሰን የውጪኛውን በር ከፍተን ገብተን ፣ መኪናዋንም ጊቢ ውስጥ አቁማ ወደ ውስጥ ገባን ። የሳሎንና መኝታ ክፍሏ መብራቶች በርተው ነበር የጠበቁን ። ትዝ ይለኛል ስንወጣ አጥፍተን ነበር ። ህይወት ዞር ብላ በፍርሃት ታየኝ ጀመር ። "አጥፍተን ነበር አ የሄድነው ...?" አለችኝ ። እራሴን በአዎንታ ወደላይ ወደታች ነቀነኩኝና 'አባትሽ የዚህን ቤት ቁልፍ አላቸው እንዴ ...?' አልኳት ባለፈው ሲመጡ በር ላይ ነኝ ብለው ስለደወሉላት ። "አዋ አለው ፣ ባለፈው ሲመጣ ረስቼ ነው ብሎኛል" አለችኝ ። ከእሷና ከአባቷ ውጪ ቁልፉን ማንም ከሌለው ፣ በዛላይ አባቷ እንዳሉትም ሀገር ውስጥ ከሌሉ ፣ በተጨማሪም ቢሾፍቱ እያለን ካየነው ሰውዬ ጋር ሲደማመር የሆነ ችግር እንዳለ በግልጽ ተሰማኝ ። "ይሄኔ ነው መሸሽ" አለ ያገሬ ሰው ፤ አሁን ገና ፍርሀት የሚባለው ስሜት አካሌን ወረረው ። "ሞት ላይቀር ፍርሀት ፤ አመል ላይቀር ቅጣት" ። "ፈሪ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል" ፤ እኛ ግን የጦርነት ቀጠና ውስጥ ሆነን ደርቀናል ። "ፈሪ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል" ፤ እኛ ግን አልጋ ላይ የመውጣት አቅምም የለንም ። "ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል" ፤ እኛ ግን የሚያባረን እያለ ካለንበት መንቀሳቀስ ከብዶናል ። ሞት በየሁሉም ሰው በራፍ ላይ የሚቆም ጥቁር መላክ ነው ። እኛም ቤቱን ፈትሸነው ባዶ መሆኑን ስናረጋግጥ ይህ በራፋችን ላይ የቆመው የሞት መላክ እንዳይወስደን በሩን ሁለት ጊዜ ቆለፍነው ። ተስፋና ፍርሀት ሁሌም አይነጣጠሉም ። ፍርሃት ያለ ተስፋ ፣ ተስፋም ያለ ፍርሃት አይኖርም ። ፍርሃትን የሰጠ አምላክ ፡ ተስፋንም አይነፍግም ። "ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል" አሉ አበው ። እኛም ምንም እንኳን ወደሞት እየሄደን ቢመስለን በምድር ተስፋ አልቆረጥንም ። አባቷ መጥቶ ከሆነ ብለን በሀገር ውስጥ ስልኩ ላይ ስትደውልለት "የደወሉላቸውን ደምበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም..." አለች የቴሌ ሰራተኛ ። በጣም ተጨንቀናል ። ጭንቀታችን በከንቱ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም ። ከመተኛታችን በፊት ከጊቢ የዶርም ጓደኛዬ ደውሎልኝ ነገ ትምህርት እንደሚጀምር እና class ባልገቡት ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደ ሚወሰድ ነገረኝ ። ስልኩ speaker ላይ ስለነበር ያለኝን ነገር የከንቲባው ልጅም ሰምታለች ። አንድ ሶፋ ላይ ሆነን የመረቀነ የድሬ ልጅ መስለን አይናችንን አፍጥጠን እየተያየን የዕሮቡ ለሊት ለሀሙሱ ጀምበር እጁን ሰጠ ። ስንት ሰዓት እንደ ተኛን አላውቅም ። እራሳችንን እዛው ሶፋ ላይ ተቃቅፈን አገኘን ። አዲስ ነገር ካለ ብለን ቤቱንና ጊቢውን ፊትሽነው ። ሁሉንም ነገር ግን ትተነው እንደ ተኛን አገኘን ። ትንሽም ቢሆን ተረጋግተን "በቃ አንተ ወደ ጊቢ ተመለስ ፡ በኔ ምክንያት ትምህርትህን እንድታጣ አልፈልግም ። እስካሁን ድረስ ለኔ ያደረከው እራሱ ከበቂም በላይ ነው" አለችኝና ልትሸኘኝ ወደ ጊቢው ወጣን ። እኔም እቅፍ አረኳትና 'አይዞሽ እሺ ምንም አይፈጠርም ። ደግሞ ብዙም አልቆይም ፡ ፍቃድ ብቻ ጠይቄ ነው የምመልሰው እሺ' አልኳትና ስታለቅስ ላለማየት ብዬ በፍጥነት ወደ ውጪኛው በር አመራሁ ። ልክ በሩን ስከፍት "ትተኸኝ በዛው እንዳትቀርብኝ እሺ የኔ ጌታ ፣ ብቻዬን እፈራለሁ ፣ ደግሞም ማንም እንደሌለኝ ታውቃለህ አይደል...?" አለችኝ ልክ የመጀመሪያው ቀን ስንገናኝ "ትተኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" ባለችኝ ዜማ ። ዞር ብዬ ሳያት ፊቷ በዕምቧ እየታጠበ ነው።
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 22
.
.
.
ቶኒ በር ላይ ፈታሾቹ ከኔ ምንም ላያገኙ ፈትሸውኝ ፣ በርብረውኝና ዘቅዝቀውኝ ምንም ነገር ሲያጡ ወደ ውስጥ አስገቡኝ ። እና አሁን ያ አመዳም ጊቢ ውስጥ ነኝ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላኝ አጠይቁኝ ። (እንግዲህ በግድ ከጠየቃችሁኝ ምን ይደረጋል...🙆) ። ገና በቶኒ በር ስገባ ጀርባዬን ያሳክከኛል ። ብታዩት Campus ሳይሆን የአዋራ ፋብሪካ ነው የሚመስለው

​​። በዛላይ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ከዶርም ወደ cafe ስንሄድ ከመኝታ ቤት ወደ ሳሎን የሄድን ነው የሚመስለኝ ። ዶርም ሆነን ከሴቶች ጋር ማውራት ከፈለግን እኮ መስኮት መክፈት ብቻ ነው የሚጠበቅብን ። መሀል ላይ በቆርቆሮ አጥር ቢለያዩንም ከወንዶች ዶርም ጋር face to face ስለሆኑ ጎረቤቶቻችን ናቸው ብል ማጋነን አይሆንም ። እንደውም አንዳንድ ጊዜ ቺኮቻችን ሲደብራቸው መስኮት ከፍተው ይደበሩብናል ። professional የሆኑ የ GC ወንድ ተማሪዎች ደግሞ ጭራሽ micraphone ገዝተው ለሁሉም ዶርሞች እንዲዳረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ። አልፎ አልፎ ግን ወደ ሴቶቻችን ዶርም ስንመለከት ከ #18 ዓመት በታች ለሆኑ የተከለከለ ነገር እናያለን ። ከሙቀቱ የተነሳ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዶርም ውስጥ ልብስ መልበስ አቁመዋል ። ለነገሩ የድሬ ሙቀት እንኳን ልብስ ቆዳም ያስገፍፋል ። ሻዎር ውስጥ ስትገባ እንኳን fan ያስፈልግሃል ። አየሩ ፣ ውሃው ፣ መሬቱ ፣ ከሰው በስተቀር ሁሉነገሩ የተመታ ከተማ ። በቶኒ በር ገብቼ ፣ ፍቅር cafe ፣ cenrtal library ፣ የሴቶች ዶርም እና senior cafe'ን አልፌ ፣ ወደ ወንዶች ዶርም ዘለኩኝ ። ጊቢው ያለወትሮው ጭር ብሏል ። ጥሎበት ደግሞ ተማሪ ከሌለበት ሲኦል ነው የሚመስለው ። (አንተ ልጅ ደግሞ አንዳንዴ ታበዛዋለህ ፡ ሲኦልን ደግሞ መች አየሃት ...?) ። የተመደብኩበት block ደርሼ ፣ የዶርሜን በር (white house F #45) ከፍቼ ገባሁ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላ idea'ው የላቹም ። ተሳስቼ ሽንት ቤት የገባሁ ነበር የመሰለኝ ። ዶርም መሆኑን ያወኩት አልጋና ሎከር በመኖራቸው ነው ። ከሁሉም ግን ድንቅ የሚለኝ ፡ ሽንት ቤቶቹ እንዳለ ቀለም ተቀብተዋል ። የምናድርበት ዶርም ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቀለም የተቦረሸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄ ጊቢ ሲመሠረት ነው ። ግድግዳው የወፍጮ ቤት ይመስላል ፣ ፍራሾቹ ደርቀው ከድርቆሽ በላይ ጠንክረዋል ፣ ሎከሮቹ ተሰባብረው የማገዶ እንጨት መሥለዋል ፣ ኮርኒሱ ኩሽና ይመስል ጠቁሮ የጨለመ ሰማይ ሆኗል ፣ ሊሾው አፈር ለብሶ ወደ መሬትነት ተለውጧል ። በቃ ምን ልበላችሁ ...? ፡ ዶርሙ ከዶርምነት ተራ ወጥቶ ዱሪዬ ዶርም ሆኗል ። እዚህ ውስጥ እየኖርኩማ እንኳን ትምህርት ሊገባኝ ቀርቶ እንቅልፍ እራሱ የሚወስደኝ አይመስለኝም ። አማራጭ የለኝም ፤ ጠልቼ በግድ አንዴ ገብቼበታለሁ ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ፣ በዛላይ ጊቢው ስለዘገነነኝ ዶርሜን ዘግቼ አልጋ ላይ ፌንት ሰራሁ ። (ፌንት ግን ይሰራል ወይስ ይወደቃል ...?) ። ይሄን የመሠለ ዶርም ውስጥ ሆኜ በየት በኩል እንቅልፍ ይውሰደኝ...? ። anyways ቤት ሳይሆን ዱር እንዳደርኩ እቆጥራለሁ ። ኧረ ዱር እራሱ በስንት ጣዕሙ ። እውነት አያ ጅቦ እዚህ ቢመጣ "እኔን ፡ እኔን ፡ ምን ሆነክ ነው ጎዳና ላይ የምታድረው...? ፡ በል ተነስና ወደ ቤቴ ልውሰድክ" እንደ ሚለኝ አልጠራጠርም ።

የዶርም ልጆች class ሄደዋል መሠለኝ ሁሉም የሉም ። ሙሉ ብሎኩም ባዶ ነው ። አንዳንዴ ግን ከጦርነት በላይ ፀትታም ያስፈራል ። እንደዚህ አይነቱ ቀንማ ዳዊት ካልደገሙበት በስተቀር የሚያልፍም አይመስልም ። (እሺ ሊቀ ጠበብት ተስፋዬ ...) ። anyways የዛሬው እቅዴ እስከ ከሰዓቱ ፈተና ድረስ መተኛት ነው ። በህልሜ የማቴሪያል ትምህርት መፃፍ ካገኘሁ አጠናለሁ ። ካልሆነ ግን በፈተናው ላይ ለሚ ብዛት ሀላፊነቱን አልወስድም ። ብዙም ሳልቆይ ግን ዶርም የነበርኩኝ ልጅ ማን እዚህ ቦታ እንዳመጣኝ ሳላውቅ ሌላ ቦታ ላይ እራሴን አገኘሁ ። ለመጨረሻ ጊዜ ትዝ የሚለኝ ነገር ቢኖር 'የሰላም እንቅልፍ ጣልብኝ ፈጣሪዬ' ብዬ መተኛቴን ነው ። አሁን ግን አልጋ ሳልሆን መሬት ላይ በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ እግሮቼን አጣምሬ ፤ በብዙ ወንዶችና ሴቶች ተከብቤ ነው ያለሁት ። ጆሮ ደግፍ የያዛቸው ይመስል ጉንጫቸው የሌለ አብጦ ፣ አይናቸው ቆንጆ ኮረዳ የሾፈ ይመስል ተጎልጉሎ ወጥቶ ፣ ጥርሳቸው ሳር የጋጡ ይመስል የላይኛው የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለም መስሎ ፣ ባጠቃላይ የሀገሪቱን የመብራት መቆራረጥ ችግር ይፈቱ ይመስል ባንድላይ እየጮኹና እያሽካኩ ያቺን ጠባብ ቤት ሊያፈርሷት ምንም አልቀራቸውም ። የአንዳንዶቹ ፊት ለኔ አዲስ አይደሉም ። እንደውም ወደ ቀኝ ዞር ስል በታሪክ እዚህ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ ብዬ የማላስበውን ልጅ አይቻለሁ ። ያው እኔም እዚሁ ከሱጋ ስለሆንኩኝ አላዘንኩለትም ። እዚህ ቦታ ላይ መተፋፈር የለም ። አሜሪካ በሏት ። ጫት ፣ ሲጋራ ፣ ሺሻ ፣ ሴት ፣ ወንድ ፣ ዊድ ፣ ጋንጃ ፣ ከቦብ ማርሌይ ውጪ ምን የሌለ ነገር አለ...? ። እየቃምኩ መሆኔን እስካሁን አላመንኩም ። እያጨስኩ መሆኔን ደግሞ ላምንም አልፈልግም ። አንዲት የማላውቃት ሴት ተገላልጣ ወደኔ እየተወላገደች ስተመጣ 'አንተ ክፉ ሰይጣን ፡ ከኔ ራቅ' ብዬ #3 ጊዜ ላማትብ ስል እጄን ይዛኝ ከተቀመጥኩበት አስነሳችኝ ። ይዛኝ ወደሆነ ክፍል ወሰደችኝ ። ቀለል ብላ ደስ የምትል መኝታ ቤት ውስጥ ነን ። እኔና እሷ ብቻ ። እንዲህ ውብ ሆኗ እዚህ ቦታ ላይ መገኝቷ ሲገርመኝ ገፍትራኝ አልጋው ላይ ወደኩኝ ። ምን አስባ እንደሆነ እስቲ ልየው ብዬ ዝም አልኩኝ ። ቀስ ብላ ወደ አልጋው ላይ መውጣት ጀመረች ። ለነገሩ እኔ ላይ ነው እየወጣች ያለችው ። ምክንያቱም አልጋው ያለው ከኔ ስር ነውና ። ወደኔ ይበልጥ በ slow motion እየተጠጋች ከንፈሯን ከከንፈሬ ጋር ልታገጣጥም ስትል በሩ ተንኳኳ ። (ምናለበት እስኪ ነገ ቢያንኳኩ ...?) ። ኳ ኳ ኳ ... ። 'ማነው...?' አልኩኝ ጮክ ብዬ በምሬት ። "አንተ አዝግ የፈተና ሰዓት ደርሷል ተነስ" የሚል የዶርሜ ልጅ ድምፅ ተሰማኝ ። ለካ የዶርሜ በር እስኪንኳኳ ድረስ የነበረው ሁሉ በህልሜ ነው ። እኔ ግን 'ማነው' ያልኩት እኮ ከህልሜ ጓደኛ ጋር እያለሁ የተንኳኳ መስሎኝ ነው ። የዶርሜ ልጅም "ጠዋት እኮ ወደ class ስሄድ ከሩቅ አይቼህ ነበር ። ከዛን #2 period ተምረን ምሳ በልቼ መጣሁ ። እንዳጋጣሚ ደግሞ ቁልፌን ምግብ ቤት ስበላ አስቀምጬ ሳላነሳው ረስቼ መጣሁ ። ለዛ ነው ያንኳኳሁት" ብሎኝ ተያይዘን ወደ መፈተኛ ክፍል ጉዞ ጀመርን ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 18


.
.
.
በሩን አልፌ የመሄድ አቅም አልነበረኝም ። ዘጋሁትና ወደሷ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ፤ ሁለመናዋም ይንቀጠቀጣል ። 'እሽሽሽ ፡ በቃ አታልቅሺ ፣ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ካንቺ ጋር ነኝ ። ትቼሽ የትም አልሄድም ። ሁሉንም ችግሮችሽን ላላስወግድልሽ እችላለሁ ፤ ነገር ግን ብቻሽን እንድትጋፈጪው በፍፁም አላደርግም' አልኳትና ዕምባዋን ጠራርጌ ፡ ግንባሯን ፣ አይኗን ፣ ጉንጯንና አንገቷ ስር ስሜያት ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዘንድሮ ባወጣው ህግ መሠረት የ #3 ቀን ቀሪ ከጊቢው ያሰናብታል ። የኔ ቀሪ ደግሞ ከዚያ እያለፈ ስለሆነ ትንሽ አሳስቦኝ እንጂ መጀመሪያውኑ የትምህርት ፍቅር ኖሮኝ አይደለም ወደ ጊቢ ለመመለስ የተነሳሁት ። ይሄው አሁን ትምህርቱ ላይ ፈርጄ የከንቲባው ልጅ ቤት ቀርቻለሁ ። ትውልድ ይዳን ፤ ትምህርት በኔ ይብቃ ። ሳስበው ግን ህይወት በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለች ወደፊት ልጄን ትምህርት ቤት ወስጄ የማስተምረው አይመስለኝም ። ለነገሩ ልጄ እንደኔ ደደብ ፣ ደነዝ እና ሰነፍ የሚሆን አይመስለኝም ። በኔ ከወጣ ግን ውሃ በላው ። Campus ባይገባ ነው የሚሻለው ። ልግባ ቢል እራሱ ማን ሲያስገባው ...? ከኔጋር እየኖረ ትምህርቴን ማቄን ምናምን የሚል ከሆነ #18 ዓመት እስኪሞላው ደረስ አልጠብቅም ። ልክ ይቺን ጥያቄ ስያነሳ በሬን ከፍቼ ካለኝ ንብረት ላይ የድርሻውን ሰጥቼው አሰናብተዋለው ። (ንብረት ግን የሚኖረኝ አይመስለኝም ... ። የኔ ነገር ፡ ለራሴም ሳልሆን የልጄን ፈተፈትኩ አይደል ። (አንተ ልጅ ግን ልጅ አለህ እንዴ ...?። ምን ላርግ ፡ ከ #3 ወር በፊት የተፈተነው Applied Maths final ፈተና ትዝ ብሎኝ እኮ ነው ። On time #02:00 ሰዓት ሻርፕ (flat ...) ላይ class ተገኘሁና አሰላለፍ አሳምሬ አስተማሪውን ጠበቅነው ። ዛሬማ ካልደፈንኩት ከዚህ ክፍል ውስጥ ንቅንቅ አልልም ብዬ ቆረጥኩ ። በስተ ሰሜን ጎበዙ የዶርሜ ልጅ ፣ በስተ ደቡብ ከዋላዬ ስለሆነ አይመቸኝም ፣ በስተ ምስራቅ ከክፍል #1ኛ ውጤት ያለው ልጅ ፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ከዲፓርትመንታችን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ልጅ ተቀምጠዋል ። Morino እራሱ አሰላለፍ እንዲህ አይችልበትም ። የተከተልኩት የጨዋታ ስልትም ፡ ትንሽ ማንበብ + ብዙ መኮረጅ = #50/50 የሚለው ነው ። ኩረጃ ላይ ብዙም ልምድ የለኝም ። እንግዲህ የኔ ጉድ ዛሬ ይታያል ። (ጉድ = Good ...) ፈታኙም ፈተናውን ይዞ ከተፍ አለ ። (ምናለበት አሁን ቢቀር ይሞታል ...?) ። ፈተናውን ጠረጼዛ ላይ አስቀመጠና እንዲህ አለን "Continous ከ #50 ሁላችሁም ከ #40 በላይ ስላመጣችሁ አይያዝም ። ስለዚህ የዛሬው ፈተና የሚያዘው ከ #100% ነው ። #90 ጥያቄ ተዘጋጅቷል ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ #3 pharagraph ትፅፋላችሁ ። ሁሉም ጥያቄ የወጣው ከተማራችሁት ውጪ ሲሆን ፤ ጥያቄዎቹ እንኳን ለእናንተ ለኛም አዲስ ናቸው ። የቀረው #10% ነጥብ ደግሞ ስማችሁን በቻይንኛ መፃፍ ይሆናል ። አሁን ፈተናውን እንጀምራለን ልክ ጀምሩ እንዳልኳችሁ pencil down እላቹዋለው ታቆማላችሁ ። ፈተናው ላይ #1 ኤክስ የገባበት ተማሪ ከጊቢው ይሰናበታል ። መልካም ፈተና ። ነጮች "ስለ ሰው ይበልጥ ባወክ ቁጥር ውሻህን ትወደዋለህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላቹዋለው 'ስለ Maths ይበልጥ ባወክ ቁጥር አለመማርን ትወዳለህ' ።...

ከከንቲባው ልጅ ጋር ቲቪ ከፍተን እያየን እያለ ስልኬ ላይ Msg ገባና አውጥቼ ሳየው Cost ገብቶልኝ ነው ። Non cafe ስለሆንኩኝ እንደ ተለመደው መንግስት #450 የኢትዮጵያ Dollar ባንክ account ላይ አስገብቶልኛል ። እኔ የምለው ግን ፡ መንግስት ለካ እንዲህ ቋጣሪ ነው ። cost መግባት የነበረበት በየወሩ በ #28 ነበር ። የዚህኛው ወር ግን በ #36ኛው ቀን ነው የገባው ። ቆይ ግን #450 ብር ለ #1 ወር በዚህ ኑሮ ፡ ብር ሆና ነው የምትበላው ...? ያውም ከተማሪ ። እኛኮ ለምሳ እና እራት ብቻ #1200 ብር ነው የምንከፍለው ። እነሱ ግን የ #5 ሚሊዮን ብር እራት በልተው ፤ በ #450 ብር መፋቅያ ጥርሳቸውን ይፍቃሉ ። Bisrat tv እያየን ነው ። ፕሮግራሙም ስለ ሶሪያ ህፃናት ነው ። አንድ የ #7 ዓመት ህፃን እንዲህ እያለ ነው "በሽር አል አሳድ'ን (የሶርያ president) ምን አደረግነው ...? ዝምብለን እየኖርን ነበር ። ምንም ሳናደርገው ቤታችንን አፈራረሰብን ፣ ቤተሰቦቻችንን እንዳለ ገደላቸው ። ቆይ ግን ምን አድርገነው ነው ...?" ። ይሄንን ሲናገር ፊቱ እንደ ጎርፍ ዝናብ በዕምባ ተሞልቶ ነበር ። ሶሪያ ውስጥ የሞቱት ህፃናት ብቻ ከ #50,000 በላይ ናቸው ። አብዛኛዎቹ ሀገር ሰላም ብለው የትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው ። በራሳቸው ጥፋት ሳይሆን በአባቶቻቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ነገን ሳያዩ ዛሬን ሳይኖሩ በአጭር የተቀጩ ህፃናት ። ዛሬም ድረስ ጦርነቱ ቀጥሏል ፣ ሀገሪቷ ምድረ በዳ ሆናለች ፣ የሶሪያ ህፃናትና ህዝቦችም ስደት ላይ ናቸው ። አሸናፊ የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት መጨረሻው እንግዲህ ይህ ነው ። ከወር በፊት ሳቢያን ፡ ድሬዳዋ ብር ለማውጣት ባንክ ቤት ስሄድ መንገድ ላይ የሶሪያ ስደተኞች ተቀምጠው ሲለምኑ አይቼ ነበር ። ባልና ሚስት መሀላቸውን ልጃቸውን አስቀምጠው ፊትለፊት ደግሞ በአማርኛ ፊደል የተፃፈ "የሶሪያ ስደተኞች ነን ፡ እባካችሁን እርዱን" የሚል Copy ወረቀት ተቀምጦ ፣ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሰው ደግሞ ከንፈሩን እየመጠጠላቸው ያለውን #1 ፣ #5 ፣ #10 ብር እየሰጣቸው ያልፍ ነበር ። እኔም ሳያቸው አንጀቴን ነበር የበሉኝ ። በተለይ ደግሞ መሀላቸው የተቀመጠው ፣ ምንም የማያውቀው ፣ #4 ዓመት እንኳን ያልሞላው ህፃን ልጅ እንዴት እንደ ሚያሳዝን ። anyways አያድርገውና ኢትዮጵያን ሳስባት እንደ ሶሪያ ካልሆንኩኝ ሞቼ እገኛለሁ ያለች ትመስላለች ። ሰላም ስልችት ብሏት ደም ደም ከሸተታች ሰነባብታለች ። ሰላም ሲሆን ጀርባዋን ይበላታል መሰለኝ ግደል ግደል ፣ ሰልፍ ውጣ ሰልፍ ውጣ ፣ ኮብል ኮብል ፣ አፍርስ አፍርስ ፣ ረብሽ ረብሽ ፣ ወዘተ ወዘተ ይላታል ። (ወዘተ ወዘተ እንኳን አይላትም ...) ። ከሶሪያ እንኳን መማር አልቻለችም ፤ የሰላም ዋጋ ምኑም አልገባትም ። ዛሬ ሁላችንም በየቤታችን ሆነን የምናየው የሶሪያ መጨረሻ የሌለው ዕልቂት ፣ መድረሻው የማይታወቅ ስደት ፣ መልስ የማያገኝ ጥያቄ ፣ ቀስ በቀስ የኛው ታሪክ ሆኖ ዓለም በየቤቱ ቁጭ ብሎ ይታዘበናል ። ልክ ዛሬ ለነዚህ ስደተኞች ከንፈር እየመጠጥን ሳንቲም እንደ ወረወርን ፤ አንድ ቀን ደግሞ ለኛም በባዕድ ሀገር ይወረወርልን ይሆናል ። ይሄ እንዳይሆን ከፈለግን ሁሉን ነገር የመንግስት ስራ ነው ማለቱን ትተን ለሰላማችን ስንል እራሳችን ፣ ቤተሰባችን ፣ ጓደኛችን ፣ ጎረቤታችን ፣ ሰፈራችን ፣ ቀበሌያችን ፣ ወረዳችን ፣ ዞናችን ፣ ክልላችን ፣ ምናምን ሳንል ለአንዲት ሀገራችን በጋራ ብንሰራ የተሻለ ብቻ ሳይሆን ተመራጭም ይሆናል ።....
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 21


.
.
.
ህይወት ልታለቅስ ነው መሠል ደንግጣ ፍዝዝ ብላለች ። ዋነኛው ምኞቷ በነፃነት መኖር እንደሆነ ነግራኝ ነበር ። ታድያ ጊዜው ሲደርስ ምን አሸበራት ...? ነው ወይስ ደስታው ነው ባለችበት ደርቃ እንድትቀር ያደረጋት ...! የሷ ይቆየኝና ግን እኔም ልክ አባቷ "ተያይዘን አሜሪካ ሄደን በነፃነት እንኖራለን" ሲሏት የልብ ምቴ ፈጥኖ ፣ ፊቴም ተለዋውጦ ነበር ። ከውስጤም ልክ የሆነ አካል እንደጎደለ ተሰምቶኛል ። "ምነው የኔ ህይወት ፡ ደስ አላለሽም እንዴ ...? እኔኮ ይሄን ስነግርሽ ከምንጊዜውም በላይ የምትደሰቺ መስሎኝ ነበር" አሏት አባቷ ። ህይወትም ድምጿ እየተቆራረጠ "አያይ አባቢ ፡ ደስ ብሎኛል ፡ ግን በቃ የአቤል ደም ፍትህ ሳያገኝ እንደ ውሃ ፈሶ ቀረ ማለት ነው ...?" አለቻቸው ። አባቷም በረጅሙ ተነፈሱና "አይደለም የኔ ህይወት ፡ አንቺን ለ #4 ዓመት እዚህ በድብቅ አስቀምጬሽ ስራ ላይ ጊዜዬን ያጠፋሁትም ለዚሁ ነበር ። የአቤልን ደም ያፈሰሱትን ሰዎች ህግ ቦታ ይዤ ሄጄ እነዚህ ናቸው ገዳዮቹ ብል የሬሳ ምርመራ ብለው መቃብር ስለሚቆፍሩ ሟቹ አቤል እንጂ አንቺ እንዳልሆንሽ ለጠላቶቼ መንገር ስለ ሚሆንብኝ እሱን መንገድ አልተከተልኩም ። ሁሉም ሰው የሚያውቀው አንቺ እንደሞትሽ እንጂ ስለ አቤል ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ። ፖሊሶቹን ጭምር ለምርመራ ሲመጡ 'ሲገድሏት የት ነበራችሁ ...? አሁን ወሬ ለቀማ ነው የመጣችሁት...?' ብያቸው ስለ ጮኹኩባቸው ፣ በዛላይ የከተማችን ከንቲባም ስለነበርኩ ሬሳውን ለማየት አልደፈሩም ። ስለዚህ የነበረኝ ብቸኛው አማራጭ ሰዎቹን በለመዱት የወንጀል ስራቸው ሲጨማለቁ በጥብቅና በቅርበት ተከታትሎ በቂ ማስረጃ ማሰባሰብ ነበር ። ሰዎቹ በዋዛ የሚያዙ ባይሆኑም በስተመጨረሻ ግን በእጄ ወድቀው ለዘላለም እስር ቤት ውስጥ እንዲማቅቁ አድርጌያቸዋለው" አሏት ። ህይወትም "ታድያ እነሱ ከታሰሩ የኛ መሸሽ ከማነው ...?" አለቻቸው ። እሳቸውም "የኔ ህይወት ፡ እነዚህ ሰዎች እስር ቤት ገቡ ማለት የተንኮል ስራቸውን አቆሙ ማለት አይደለም ። እንደውም እዛ በመግባታቸው ሰይጣንነታቸው ቢብስ እንጂ አይቀንስም ። ፍርድ ቤት ሲፈረድባቸው እንዴት ገላምጠው እንዳዩኝ አታቂም ። በዚህም በዚያም የኔ ህይወት ፤ አሁን ስለነሱ የምናስብበት ጊዜ አይደለም ። ማሰብ ያለብን አሜሪካ ስንሄድ ስለሚጠብቀን አዲሱ ህይወት ነው ። ባለፈው መጥቼ ፋይሎችሽን እንዳለ የወሰድኩትም ለዚሁ process ነበር ። አሁን ሁሉም ነገር አልቋል ። መሄድ ብቻ ነው የቀረን ። አዲስ አህጉር ፣ አዲስ ሀገር ፣ አዲስ ከተማ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ ት/ቤት ፣ አዲስ ጓደኞች ጭምር ይኖሩሻል" አሏትና ፊት ለፊታቸው የተቀመጠውን ወይን አንስተው ተነሱና አንዴ ከተጎነጩ በዋላ ግንቧሯን ሳሟትና "በጣም ደክሞኛል እሺ የኔ ህይወት ፡ ቀሪውን ነገ እናወራለን ፡ አሁን ገብቼ ልተኛ" አሏትና እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ መራመድ ጀመሩ ። በሩ ጀርባ ተሸሸኩኝ ። የክፍላቸውን በር ከፍተው ገብተው ሲዘጉት ተመልሼ በበሩ ወደ ሳሎን ማየት ቀጠልኩኝ ። በህይወት ፊት ላይ ምንም አይነት የደስታ ስሜት አይታይም ። ፊቷን ደመና ያዘለ ሰማይ አስመስላ ከሶፋው ላይ ተነስታ ወደኔ መጥታ ገባችና በሩን በቀስታ ቆለፈችው።
ምንም ሳትለኝ አልጋ ውስጥ ገብታ ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች ። ምን ሆነሽ ነው ...? ልላት አልፈለኩም ። አባቷ የተኙት ከአጠገባችን ባለው ክፍል ውስጥ ስለሆነ ለማውራት አይመችም ። በተጨማሪም በራሷ ፍቃድ እንድትነግረኝ ነው የፈለኩት ። እኔም ያወሩትን ነገር እያንዳንዷን እንዳልሰማሁ ምንም እንዳል ተፈጠረ በማስመሰል አልጋው ውስጥ ገባሁና ጀርባዬን ሰጥቻት ተኛሁ ። አይኖቼ ግን አልተከደኑም ። ብዙም ደቂቃ ሳይቆይ ግን ህይወት በጀርባዬ በኩል ተለጥፋብኝ በታፈነ ድምፅ ማልቀስ ጀመረች ። ቀና ብዬ መብራቱን አብርቼ ዞሬ ሳያት በዕምባዋ አንሶላና ትራሱን አረስርሳለች ። እቅፍ አድርጌያት እምባዋን መጠራረግ ጀመርኩኝ ። ግን ማስቆም አልቻልኩም ። ዕምባ ከአይኖቿ ሲፈስ ፡ በእጆቼ ስጠርግ ፣ አሁንም ሲፈስ ፡ ደግሜ ሳብስ ፣ መላው ሲጠፋኝ 'እሽሽሽ በቃ ፡ በቃ ፡ ስወድሽ አታልቅሺ ፡ የዕምባሽ መፍሰስ ትክክለኛውን ምክንያት ባላውቅም ፡ ምናልባት ግን ሊያስቆመው የሚችለውን ጉዳይ ንገሪኝና መፍትሄ እንፈልግለት' አልኳት በለሆሳስ ። እየተንሰፈሰፈች ፣ ከዕምባዋ ጋር በአፍንጫዋ የሚወርደውን ውሃ መሠል ንፍጥ ወደላይ አየመለሰችና እየጠራረገች "ለምን እንደማለቅስ ከነገርኩህ ራስ ወዳድ ነሽ አትለኝም ...?" አለችኝ ። 'አልልሽም ፡ በይ ንገሪኝ' አልኳት ማቆምያ የሌለውን ዕምባዋን እየጠረኩላት ። "እንደውም እርሳው በቃ" ብላኝ እንደ ቅድሙ ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች ። እኔም "ዛሬ እንጂ ነገ የት ይሄዳል ...?" ብዬ መብራቱን አጠፋሁና ለመተኛት ሞከርኩኝ ። ግን አይኔ አልከደን አለኝ ። ስልኬን አወጣሁና data አብርቼ Telegram ገባሁ ። የክፍሌ group ላይ ነገ Material ፈተና አለ ተብሎ ተለቋል ። በልቤ ችግር ላይ ሌላ ችግር አልኩና data አጥፍቼ ፣ አባቷ ቀድመውን እንዳይነሱ Alarm ሞልቼ ተኛሁ ። እንቅልፍ ባይኔ ስላልዞረ ጠዋት አላርሙን እራሴው ቀሰቀስኩትና ተነሳሁ ። ልጅቷንም ቀስ ብዬ በእጄ ትከሻዋን ነካ ነካ እያደረኩ በሹክሹክታ 'ህይወት ፡ ህይወት' እያልኳት ስጣራ ተነሳችና ወደ ጊቢ መመለስ እንዳለብኝ ከነምክንያቱ ነገርኳት ። አባቷ ቤት እንዳሉ ረስታለች መሠለኝ "ሂድ በቃ" አለችኝ በደከመ መንፈስ ። 'መሄዱማ የት ይቀራል ፡ ግን እኮ አባትሽ እቤት ናቸው እንዴት ነው የምወጣው ...?' አልኳት ። ሴት ልጅ መለኛም አይደለች ። እኔ የቤቱንና የአጥሩን በር ከፍቼ ስወጣ አባቷ እንዳይሰሙ እሷ ክፍላቸው ገብታ ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርጋ እንደምትከፍት ነገረችኝ ። ከአባቷ ጋር ጓደኛም ጭምር ስለሆኑ በዛን ሰዓት የሚያስቡት እሳቸውን ለመረበሽ የፈጠረችው ነገር እንደሆነ ነው ። ያለውን ነገር በስልክ እርስ በርስ እንድናሳውቅ ተነጋግረን እሷ ጉንጬን እኔ ደግሞ አይኖቿን ሳምኩኝና ተሰነባብተን እንደ ተባባልነው ልክ እሷ ከሳሎን በጂፓስ የሙዚቃውን ድምፅ መጨረሻ ላይ አድርጋ ስትከፍት በሩን ከፍቼ ሸመጠጥኩት ። ከጊቢው ስወጣ በረጅሙ ተነፈስኩና ቁልፎቹን በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አቀናሁ ። የሙዚቃው ድምፅ ውጪ ድረስ ይሰማ ነበር ። ቤት ውስጥ እያለሁ ሲከፈት ...

"ቀኑ መሽቶ ጨላለመ ፡ ብሎ
ተስፋ ቆርጦ ከደከመ ፣
ደስታውን ያራቀው ለታ ፡
ያኔ ነው ሰው የሚረታ" ።

እያለ ነበር ። አሁን ግን ድምፁ ቀስ በቀስ እንዲህ እያለ እየራቀኝ መቷል ...

"እኛ ከሌለን ባዶ ፡ እኛ ከሌለን ባዶ ፣
እኛ ከሌለን ባዶ ፡ አዎ
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................

🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 23


.
.
.
ሁሉም ተማሪዎች calculator ይዘው ነው የመጡት ። እኔ ግን በህልሜ የመረቀንኩት አለቀቀኝም መሰለኝ ብዕር እንኳን አልያዝኩም ። ብዕሩን እንደምንም ከመምህር አግኝቻለሁ ። calculator ቀድሞውኑ ለድምር አያስፈልገኝም ፤ አየር ላይ አጫውተዋለሁ ። ብዙ ጊዜ ተማሪ ፈተና ሲደርስ ሲጨናነቁ አያለሁ ። እኔጋር ግን እሱ የለም ። የምችለው ከሆነ እሰየው ፤ ካልሆነ ግን ሲፈልግ ገደል ይግባ ። (ፈተናው ሳይሆን አንተ ነህ ገደል የምትገባው...🙆) ። ፈተናው ተሰጠንና አየሁት ። #5 ጥያቄ ነው ። ከነሱ ውስጥ ግን እኔ ከአንደኛው ጥያቄ ውጪ አንድም info የለኝም ። እያንዳንዳቸው #4 ፣ #4 ነጥብ አላቸው ። ስለዚህ ከ #20% ውስጥ #4% ነው የማገኘው ማለት ነው ። የማውቃትን #1 ጥያቄ ሰርቼ የቀሩትን ደግሞ ከልጆች copy paste ላደርግ ብዬ ቀና ስል #2 አስተማሪዎች አንዱ ከፊት ሌላኛው ደግሞ ከዋላ ሆነው ድምበር እየጠበቁ ነው ። ጥሎብኝ ፈተና ሲከብደኝ መጨናነቅ አልፈልግም ። የቀሩትን #4 ጥያቄዎች በመሰለኝና ደሳለኝ ሞልቼ ወጣሁ ። ከሳምንታት በፊት "ምነው አንተ ልጅ እያሽቆለቆልክ እኮ ነው ፣ በጣም ከስተሃል" ባሉኝ አንደበታቸው ዛሬ ግን class ውስጥና መንገድ ላይ ያገኙኝ ልጆች እንዳለ "ምን ተገኘ ደግሞ ፡ በጣም ተስማምቶሃል" እያሉኝ ያልፉኝ ጀመር ። እንደውም የተመልካች አይን ሲበዛብኝ ሰግቼ ትፉልኝ ማለት ጀመርኩኝ ። እነሱ ግን ትፉልኝ እና ትፉብኝ መለየት ስለከበዳቸው በዋላ ላይ ማስታጠብያ ገዛሁና እሱ ውስጥ እንዲተፉልኝ አደረኩ ። ሁሉም የውፍረቴን ምክንያት ቢጠይቁኝም ፡ እኔ ግን ትንፍሽ አላልኩም ። ምክንያቱም ከዚህ በፊት ስከሳ አንድም ሰው የክሳቴን ምስጢር አልጠየቀኝምና ። ዶርም መሄድ ስላስጠላኝ ወደ Library አቀናሁ ። የተባረከው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ንሰሐ ይገባል ፤ እንደኔ አይነቱ ደግሞ ቤተ መፅሐፍት ገብቶ ላይገባው ግራ ይጋባል ። Final ፈተና እየደረሰ በመሆኑ ሶስቱም የጊቢው Library እንደ አባይ ሞልተው ተማሪዎች ወደ ግብፅ እየፈሰሱ ይገኛሉ ። አሁን ያለሁት ከሶስቱ አንዱ በሆነውና ዘንድሮ ተመርቆ ስራ በጀመረው Central Science and technology Library ውስጥ ነው ። ይሄ ቤተ መፅሐፍት ግን በጣም ዕድለኛ ነው ። ስንቱ ተምሮና ተመርቆ ስራ ባጣበት ዘመን ላይ ነው ሳይማር ተመርቆ ስራ የጀመረው ። anyways እኔ እንኳን የገባሁት እንደ ሌሎቹ የትምህርት መፃፍ ላነብ አይደለም ። ላይብረሪው ከትምህርት መፅሐፍ ውጪ ፡ ጋዜጣ ፣ መፅሔት ፣ FB ፣ Telegram ፣ ወዘተ መጠቀምያ ቦታ አለው ። ያውም እንደ ሳሎን በሶፋ የተሽቆጠቆጠ ቦታ ። እና ብዙ ጊዜ እዚህ እየመጣሁ Telegram ስለምጠቀም ላይብረሪስቶቹ ጭምር ሸምድደውኝ እንደ ድንገት እንኳን አርፍጄ ቦታው ላይ ሰው ሊቀመጥ ሲመጣ "ሰው አለው" ማለት ጀምረዋል አሉ ። እዚህ የሚገኙ ጋዜጦች ግን አይመቹኝም ። ከነሱ ይልቅ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሽንት ቤቶች ግድግዳ ላይ በተለያዩ የጊቢው Activist ተማሪዎች የሚፃፉት ሺህ እጥፍ ይማርካሉ ። ብዙ ጊዜ እንደውም የETV ዜና ሲናፍቀኝ ወደ ሽንት ቤት ጎራ እልና አነባለሁ ። ወደ ውስጥ ሳትዘልቅ ገና ከበሩ መግቢያ ላይ ይጀምራል ። "እንኳን ወደ ተመስገን በየነ የምግብ ማስወገጃ አዳራሽ በደህና መጣችሁ ። እናንተ ብቻ ጠንክራችሁ ብሉ እንጂ እኛ የናንተን የከበሩ ማዕድናት ለመቀበል #24 ሰዓት ዝግጁ ነን ። ለደንበኞች ቦታ ይያዛል ፣ በተጨማሪም በራሳችን ጉልበት ውሃ ወደ ሽንት ቤቱ እንደፋለታለን" ። ወደ ውስጥ ገብታችሁ ሱሪ አውልቃችሁ ቁጭ ስትሉ ደግሞ በአምስቱም አቅጣጫ (ከፊት በር ላይ ፣ ከዋላ ፣ በቀኝ ፣በግራ እና ኮርኒስ ላይ) ከሽንት ቤቱ ውጡ የማያስብሉ ምርጥ ምርጥ ቀልዶችን ያገኛሉ ። ከሁሉም ግን እኔን የምትመቸኝ "ለዚሁ ነበር እንደዛ የበላሁት ...?🙆" የምትለዋ ነች ።

ምሽት ላይ እራት ከጓደኞቼ ጋር በልተን ቶኒ ላይ ሻይ ጠጥተን #01:30 ወደ ዶርም ስንመለስ ህይወት ደውላልኝ telegram እንድገባ ነገረችኝ ። ቀኑን ሙሉ ያልደወለችልኝ አባቷ እቤት ስለዋሉ እንደሆነና በቅርቡ ደግሞ ከሀገር እንደሚወጡ ነገረችኝ ። አብዛኛው ወሬዋ ግን ናፍቆት ነክ ነበር ። እንደውም በ voice ጭምር እየዘፈነች ልካልኛለች ። Studio ሳትገባ ዝምብላ እንደ ቀልድ የምትልክልኝና እቤቷ እያለሁም የምታዜምልኝ ሙዚቃዎች ህይወት አላቸው ። እሱ ብቻ አይደለም ፤ የምትፅፍልኝ መልዕክቶች ጭምር ልቤን ያቆሙታል ። "ቀኑን ሙሉ ስላንተ ሳስብና ስፅፍልህ ነበር የዋልኩት" ብላኝ ይሄን መልዕክት ላከችልኝ ። "ከዋክብትንና የምድር አሸዋን መቁጠር ከሚሳንህ በላይ ላንተ ያለኝን ስሜት በቁጥር ማወቅ ያዳግትሀል ። በዚች ምድር ላይ ለመኖር #1ሺህ ምክንያቶች ላያስፈልጉኝ ይችላሉ ። ባይሆን ያንተ መኖር ብቻ በራሱ በቂዬ ነው ። አንተ የቀኔ ፀሀይ ነህ ፤ ብሩህ ታደርግልኛለህ ። የምሽቴም ጨረቃ ነህ ፤ ጨለማዬን ትገፍልኛለህ ። ልቤ ፣ ደምስሬ ፣ አይምሮዬ ፣ ንግግሬ ፣ ልብ ምቴ ፣ ህይወቴ ፣ ሁሉ ነገሬ ውስጥ ገብተሃል ። ሌላው ይቅር ፡ አይኔን እንኳን ስጨፍን የምትታየኝ አንተ ነህ ። ብዙ ጊዜ ስትጎጂ እና ስታለቅሺ ማየት አልፈልግም ብለኸኛል ። የኔ ጌታ እየተጎዳሁና እያለቀስኩ ነው የዋልኩት ። አውቃለሁ አጠገቤ መሆን ስላልቻልክ እንጂ እኔን ለመጉዳት እንዳልራከኝ ። ቢሆንም ግን በጣም እየፈራሁ ነው ። ህይወት ላንተ ናት ፡ ሞት ግን ለኔ ፣ ደስታ ላንተ ነው ፡ ሀዘን ግን ለኔ ፣ አብሮ መሆን ላንተ ፡ ብቸኝነት ግን ለኔ ፣ ሁሉ ነገር ላንተ ፡ አንተ ግን ለኔ ነህ ። አንተን መናፈቅ ያስደስታል ፤ ለዛም ነው ቀኑን ሙሉ የማስብህ ። ምሽት ላይ ሆኜ አንተኑ ሳስብህ ከዋክብት አዝነውልኝ ሊያፅናኑኝ ከሰማይ ላይ ይረግፋሉ ። ምናልባት ሰማይ ባዶ ሆና ካገኘሀት ብዙም አትደነቅ ። ምክንያቱም በደምብ እንዳስብህ አድርገህኛልና ። ቀኑን ሙሉ ድምፅህን ሳልሰማ ፣ አይኖችህን ሳላይ ፣ በናፍቆት አሳለፍኩኝ ። ረስተኸኝ ይሁን እያልኩ እጨነቃለሁ ። የኔን ስሜት ሳልነግርህ ከማንም በላይ ታውቀዋለህ ብዬ አስባለሁ ። አብጄ አማኑኤል ብገባ እራሱ አንተን መርሳት የሚቻለኝ አይመስለኝም ። ደግሞ ህይወት መልሳ እንደምታገናኘን እና ወደፊት አንድ ቀን አብረን እንደ ምንህን ተስፋ አደርጋለሁ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ፤ ጉዞው ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። ለኔ ግን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የኔ ጌታ ፡ ያንተ አለመኖር ያማል ። ከአለም ጋር ከተለያየን ቆየን ፤ ምክንያቱም የኔ አለም አንተ ነህ ። ፀሀይ ፊቷን አዙራብኝ ብርሃን ካጣሁ ቆይቻለው ፤ ምክንያቱም የኔ ፀሀይ አንተ ነህ ። ጨለማ ውስጥ ነኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ነኘ ፤ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፤ በውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑንና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። በቶሎ ላገኝህ ብዬ ተኝቼ አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልማል ። እኔ አንተን ሳጣህ እንኳን ቀኑን እራሴንም እረሳለሁ ። ግን የኔ ጌታ እስካሁን ድረስ ያልረሳሁት #

1 ነገር አለ ። እሱም አንተ ነህ ። ምክንያቱም አንተን እረሳሁ ማለት በህይወት የለሁም ማለት ነው" ። ይሄን ሁሉ ብላኝ ፣ በድምጿም እየዘፈነች ልቤን ብታቆመውም የኔ መልስ ግን ዝምታ ነው ። ዝም ....ይቀጥላል
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 24


.
.
.
ድሬዳዋ ግን UNESCO ላይ አልተመዘገበችም ...? ማለቴ ባላት በቂና አስተማማኝ የአዋራ ክምችት መመዝገብ ያለባት ይመስለኛል ። (#10 09 2011) ከእንቅልፋችን ስንነቃ ያየነውን ግን እንኳን ዩኔስኮ ፡ ቅዱስ ገብርኤል እራሱ በህይወት መፃፍ ላይ ይከትበዋል ። (የከተሜ ልጆች ፡ ይከትበዋል የምትለዋ ቃል ደግሞ ክትባት እንዳት መስላችሁ ...) ። ተቀርፆ አለም ሁሉ በቲቪ ቢያየው ደስ ይለኝ ነበር ። anyways እኛ በስልክም ቢሆን ቀርፀናል ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ተፈጥሮ ሲቀየር አየሁ ። አዋራ እንደ ጉም ሙሉ ድሬዳዋን ሲሸፍናት ሳሉት ። እንኳን ሰውን ከሰው ለመለየት ይቅርና ፤ አንተ እራሱ የት እንዳለህ አታውቅም ። ብቻ ወደ ውስጥ እራሱ የምናስገባው oxygen ሳይሆን ክሽን ያለች ንፁህ አዋራ'gen ነው ። (ቅቤ አለው እንዴ ይሄ ነገር ...?) ። ወደ ውጪ ደግሞ በ carbondioxide ፋንታ የምናወጣው አፈር'dioxide ነው ። (እዚጋ chemistry ሲፎርፍ የነበረ ተማሪ ምን እያወራሁ እንደሆነ አይገባውም ...) ። በጠራራ ፀሀይ ድሬዳዋ ከተማ ሙሉ በሙሉ ጨለመች ። የመንገድ ዳር መብራቶች እራሱ ሶላር ናቸውና ሲመሽ በራሳቸው system ነው የሚበሩት ። ዛሬ ግን በቀን የጨለመ መስሏቸው ሲበሩ ውለዋል ። ምሳ ከጓደኞቼ ጋር በልቼ ወደ bank ቤት አመራሁ ። እቅዴ ባንክ ውስጥ ያለኝን ሙሉ capital ማውጣት ነው ። (ይቅርታ small ለማለት ነው...) ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ ሁሌም የማሰለፉበት ባንክ ደረስኩኝና ሰልፉን ተቀላቀልኩ ። የባንክ ቤቱ ጊቢ ባዶ ኪሳቸውን ባሉና ሙሉ ፌስታል ብር በያዙ ሰዎች ተሞልቷል ። ባዶውን የመጣ ኪሱን ሞልቶ ይሄዳል ። ፌስታል ሙሉ ብር ይዞ የመጣ ደግሞ ባዶ ኪሱ ውስጥ ፌስታሉን አስቀምጦ ይመለሳል ። ይሄ ነው እንግዲህ ቁጠባና ቁንጠራ ማለት ። ያለው ሲቆጥብ የሌለው ይቆነጥራል ። ተራዬ ደርሶ ባለፈው የገባልኝን cost #450 ብር አውጥቼ ቀሪውን ብር ሳይ ልቤ በሀሴት ተሞላች ። የማታሳፍር ንፁህ የኢትዮጵያ #27.50 ዶላር አለችኝ ። ቀጣይ ወር ስመጣ ወልዳልኝ #28 ብር እንደ ምትሆንልኝ ተስፋ አለኝ ። ይቺም ብር ሆና ይዣት ወደ አሸዋ አቀናሁ ። (ማነሽ ድሬዳዋን የማታውቂዋ ፡ አሸዋ ደግሞ የሰፈር ስም እንጂ ድንጋይ አይደለም ...) ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ባዶ ሆኖ ካገኛችሁት ብዙም አትደንግጡ ። ምክንያቱም አዳሜና ሄዋኔ የወር አስቤዛዋን ለመሸመት እዚህ አሸዋ ውስጥ ናቸውና ። ተማሪ ፣ አስተማሪ ፣ ነዋሪ ፣ ዘዋሪ እንዳለ ከዚህ ነው የሚሸምቱት ። ኧረ ባለፈው ዘፋኙ Sancho (ታናሞ ካሻሞ ...) እዚህ መጥቶ ለ clip የሚሆኑትን ጫማዎች ገዝቶ ሄዷል አሉ ። ደግሞ ለራሱ ብቻ አይደለም ። ለኔ ጊልዶ እና ያሬዶ ጭምር ይዞ ሄዷል ይባላል ። (አሉባልታ አይደለም ደግሞ ፤ አሉ ብሎ የነገረኝን ልጅ አምነዋለሁ ...) ። brand ጫማ ፣ ልብስ ፣ electronics ፣ ወዘተ እዚህ በርካሽ ዋጋ ይገኛል ። (ኧረ ጀለሴ ፡ ማስታወቂያ ውስጥ ገባሽ እኮ ...። አይኔን ጨፍኜ cost ላይ #250 dollar ጨምሬ vans ጫማ ገዛሁ ። ምሽት ላይ እራት ከጓደኞቼ ጋር በልተን ወደ ዶርም ተመልሰን telegram ገብቼ ከህይወት ጋር ማውራት ጀመርን ከኔ ጋር የምታወራቸው እያንዳንዷ ቃላት ሀይል አላቸው የዋህነቷ ፍቅሯ ፣ ድምጿ ፣ ሁሉ ነገሯ ከአቅሜ በላይ ናቸው ። ደግሞ ነገ አባቷ የሆነ ቦታ እሄዳለው ስላሏት እቤታቸው መምጣት እንደ ምችል ነግራኛለች "ና ናፍቆኛል ትያለሽ አሉ ፡ የኔንም ላንቺ ባወሩ ፣ ካንቺ ብቻ ሰምተው መጡ ፡ ሳይነግሩሽ የኔን በቅጡ ።ሊመሻሽ ሲል #11 ሰዓት አካባቢ ከህይወት "አባዬ ወቷል መምጣት ትችላለህ" የሚል txt ገባልኝ ደቂቃ ሳላባክን ከዶርም ተነስቼ ፣ በቶኒ በር ወጥቼ ሰፈራቸው አካባቢ ደረስኩኝ ። ወደ ቤታቸው በር ቀርቤ ላንኳኳ ስል መሬት ላይ ፖስታ አገኘሁ ማንኳኳቱን ትቼ እሱን አነሳሁትና ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩኝ "የፃፍኩልህን አቅጣጫ ተከትለህ ና አታስጠብቀኝ እሺ የኔ ጌታ" ይላል ህይወት እንደሆነች ተረዳሁና ሰፈሩን አንድ ጊዜ ዞር ዞር ብዬ ከቃኘሁ በዋላ በፃፈችልኝ GPS መሠረት መጓዝ ጀመርኩኝ ቤታቸው የተሰራው ወደ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ፡ ከቤታቸው በታችኛው በኩል ትንሽዬ ጫካ መሳይ በዛፎች የተሸፈነ ቦታ አለ አቅጣጫውን ስከተል በስተመጨረሻ ጫካው ውስጥ እራሴን አገኘሁ ፀጥታው ድምፅ አውጥቶ ጆሮዬ ላይ መጮህ ጀመረ ልቤ ከልክ በላይ ይመታል እየመሸም ስለሆነ በጣም ያስፈራል ወዲያው የኮሽታ ድምፅ ከጫካው ውስጥ ይሰማኝ ጀመር የረገፉ የዛፎች ቅጠል በእግር ሲረገጡ የሚፈጠረው ድምፅ ከደቂቃ ወደ ደቂቃ በደንብ ይሰማኝ ጀመር ስለመሸ ብዙ ነገሩ በደንብ አይታይም ኮሽታው በጀርባዬ በኩል እንደሆነ ተረዳሁና ድምፁን ወደ ሰማሁበት አቅጣጫ ስዞር ጭንቅላቴን ምን እንደሆነ የማላውቅ ነገር በሀይል መታኝና ተዘረርኩኝ ለስንት ደቂቃ ወይንም ሰዓት እራሴን እንደሳትኩ አላውቅም ግን እራሴን ጨለማ ክፍል ውስጥ ወንበር ላይ ተቀምጬ ፣ እግሮቼና እጆቼ ወደዋላ ታስረው ነው ያገኘሁት ሳላስበው ፊቴ ላይ የእጅ battery ብልጭ አለብኝና አይኔን አቃጥሎኝ ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ ብልጭ የሚሉ የተለያዩ የመብራት ቀለሞች ይመላለሱ ጀመር ከላይ እስከ ታች በያዘው ባትሪ scan አደረገኝ ወይ ቤቱ ስለጨለመ ይሁን ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሷል መሠለኝ በደንብ አይታይም ባትሪውን እንዳበራብኝ በቀኝ እጁ ግንባሬ ላይ ሽጉጥ ደቀነብኝ አይኔ ላይ ስላበራው ማን እንደሆነ እንኳን አይታወቅም ። ወፈር ባለና በሚያስፈራ ድምፅ "በዚህ ዕድሜ ፡ መሞት ትፈልጋለህ ?" አለኝ አልፈልግም' ስለው "መኖር የምትፈልግ ከሆነ የምልህን ነገር ማድረግ ይኖርብሃል" አለኝ ። ፈራ ተባ እያልኩ 'ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልገው ?' አልኩት እሱም "ህይወትህን የምትፈልግ ከሆነ የማዝህ ነገር በጣም ቀላል ነው" ሲለኝ 'የምትለኝን ባላደርግስ...?' አልኩት በንዴት ። እሱም "ወይ እዚሁ ግንባርህን ብዬክ ፤ ወይም ደግሞ እስር ቤት ለዘላለም እንድትማቅቅ አደርግሃለሁ" አለኝ የእስር ቤቱ ገርሞኝ 'እንዴት አርገህ ነው ደግሞ እስር ቤት የምታስገባኝ ?' አልኩት የስላቅ ሳቅ እየሳኩኝ ። እሱም እየተሳለቀብኝ "እረሳህ እንዴ ደፍረህ የገደልካትን ልጅ" ሲለኝ ደንግጬ 'የምን ልጅ አልኩት ?' እሱም "አቅጣጫውን ተከትለህ ወደ ጫካው ስትገባ ከዋላህ ሆኜ በካሜራ ሳነሳህና ስቀርፅህ ነበር ። ጫካው ውስጥ ደግሞ የሆነች ልጅን እራሴው ደፍሬ ገድያታለሁ ለማስረጃ ደግሞ የእጅ ሰዓትህንና የአንገት ሀብልህን ቦታው ላይ አስቀምጫለሁ ። ስለዚህ አሁን የምልህን ነገር ካላደረክ በአንድ የስልክ ጥሪ ለፖሊስ አሳልፌ ልሰጥህ እችላለሁ" ሲለኝ በድንጋጤ ፈዝዤ ቀረሁ ። በዚህ መሀል ግን ህይወት የሆነ ቀን ከዲያሪዋ ላይ ያነበበችልኝ ትዝ አለኝ


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 25

.
.
Notice : በትላንትናው ክፍል ላይ ማለትም ክፍል 25 ላይ የመጨረሻዎቹ አከባቢዎች ተስፋዬ እንደታገተ ህይወት ከዲያሪዋ የነገረችው ትዝ እንዳለው ገልጾልን ነበር ያለቀው! ስለሆነም ተስፋዬ ትዝ ያለውን ዲያሪ ከራሷ በህይወት አንደበት በሪከርድ ድምጽ ቀርቦላችሁዋል..ከስር ከዚህ ክፍል ጋር ዲያሪውን በድምፃ አታች ስላረግንላችሁ አዳምጡት የታሪኩ አንድ አካል ነውና!🔥
.
.
በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሽጉጥ ተደቅኖብኝ እየተዛተብኝ ነው።ከዚህ ለማምለጥ ደግሞ ሰውዬው የሚለኝን ነገር ማድረግ የግድ ነው ። 'እሺ ምንድነው እንዳደርግልህ የምትፈልገው ...?' አልኩት በብስጭት ። "አንድ ነገር ብቻ ነው የማዝህ ፣ እሱም የከንቲባውን ልጅ እኔ ወደ ምልህ ቦታ ይዘሀት ትመጣለህ ። ከዛን ልጅቷን በሰላም ተረካክበን ፣ አንተ ደግሞ በምላሹ ወደ ጫካ ስትገባ የተቀረፅከውን ፣ እንዲሁም የእጅ ሰዓትህና የአንገት ሀብልህን ከነ ህይወትህ ይዘሀቸው ትመለሳለህ ። አለቀ ፤ በቃ ይኸው ነው" አለኝ ቀለል አድርጎ ። የመጀመሪያ ቀን ከህይወት ጋር ስንገናኝ "የከንቲባ ልጅ ነኝ" ብላኝ ስትተዋወቀኝ ያን ቀን በልቤ ለራሴ 'በቃ ተስፍሼ ቁርጥህን አወቅ ፡ ነገ ወይ ከርቸሌ ፡ ወይም ደግሞ ሲኦል ትገባታለህ' ያልኩት ትዝ አለኝ ። 'ቆይ ግን ከሷ ምንድነው የምትፈልገው ...?' ስለው "እሱ ያንተ ጉዳይ አይደለም" አለኝ በሽጉጡ ግንባሬን እየተጫነኝ ። ባይታየኝም ወደላይ ቀና ብዬ እያየሁት 'ቆይ አንተ ማነህ ፡ ለምንስ ነው እንደዚህ የምታደርገው...?' አልኩት በልመና አይነት ድምፅ ። "እኔ ማለት የናንተ ጥቁር ጠባቂ መላክ ነኝ ። በሄዳችሁበት ሁሉ አለው ። ደብረዘይት ብትል ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ብትል ፣ ሌላው ይቅር ፣ የከንቲባውን ልጅ ቤት መብራት ማጥፋትና ማብራት እንኳን የኔ ስራ ነው" ሲለኝ ሙሉ ነገር ጭልምልም አለብኝ ። ከዚህ በፊት ሲከታተለን የነበረውና በፍርሃት ስንጠብቀው የነበረው ሰውዬ እንደሆነ ተረዳሁ ። ግን ጥያቄ የሆነብኝ ነገር ነበር ። ህይወትን ከሆነ የሚፈለገው ፡ ለምን ከዚህ በፊት ያገኛቸውን አጋጣሚዎች እንዳልተጠቀመ ጠየኩት ። እሱም "ደብረዘይት ፡ ኩሪፍቱ ሪዞርት ውስጥ ሁሉ ነገር አልመች አለኝ ። ከዛ ስትወጡ ልይዛት አቅጄ ነበር ። ግን እኔ ባላሰብኩበት ቀን ከዛ ለቃችሁ ወጣችሁ ። እዚህ ደግሞ እንዳልይዛት ልጅቷ ከቤት አትወጣም" ። ሲለኝ 'ታድያ ምን ይሳንሀል ፣ መብራቶቹን ያበራኻቸው በፀሎት ነው እንዴ ፣ ልክ ገብተህ እንዳበራኻቸው ልጅቷንም ገብተህ መውሰድ እኮ ትችላለህ' አልኩት ። እሱ ግን ይበልጡኑ በሽጉጡ እየተጫነኝ "ስማ አንተ ወጠጤ ፡ እዚህ ያመጣውክ እንድትመክረኝ አይደለም ። ለመጨረሻ ጊዜ ደግሜ እጠይቅሃለሁ ። ልጅቷን እኔ ወደ ምልህ ቦታ ይዘሀት ትመጣለህ ወይስ እዚሁ ግንባርህን ለሁለት ልክፈልልህ...?" አለኝ እየደነፋብኝ ። በጣም ጨንቆኛል ፤ እሱ ባይተኩስብኝም ጭንቅላቴ አሁን እራሱ ለሁለት ክፍል ብሏል ። አንደኛው 'ተው ተስፋዬ ለማታውቃት ልጅማ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋዕትነት መክፈል የለብህም ። ባይሆን ላንተ ሲሉ ቀን ከሌሊት የሚለፉ ቤተሰቦችህን አስባቸው ። ደግሞስ እሷ የከንቲባ ልጅ እንጂ ማራኪክ አይደለች' ይለኛል ። ሁለተኛው ደግሞ 'አይዞህ ፡ በርታ በል ፡ ይሄ የህይወት ፣ የህሊናና የሰውነት ጉዳይ ነው ። ልጅቷ ፡ እህትህ ፣ ፍቅረኛህ ፣ እናትህ ወይንም ደግሞ ወደፊት የምትኖርህ ሴት ልጅህ እንደሆነች አስብና የሰውዬውን ጥያቄ ውድቅ አድርግ' ይለኛል ። ሰውዬው በሀይል "አንተን እኮ ነው የማወራው" ብሎኝ ከሀሳቤ አነቃኝ ። ትዕግሥት የሚባል ነገር አልፈጠረበትም ። ቀጠለና #10 second እሰጥሃለሁ ። ካንተ መስማት የምፈልገው 'እሺ' የሚለውን ቃል ብቻ ነው አለኝና መቁጠር ጀመረ ። #10 ፣ #09 ፣ #08 ፣ #07 ፣ #06 ፣ #5 አለና #4 ላይ ሲደርስ ሽጉጡን አቀባብሎ መቁጠሩን ቀጠለ ፣ #03 ፣ #2 ፣ #1 ...

'እሺእእእ ...' አልኩት ቅልጥ ባለ ድምፅ ። የሱ አንድ እና የኔ እሺ ማለት እኩል ከአፋችን ሲወጣ የሽጉጥ ድምፅ ሳይሆን "አንድ ሺ" የሚል ቃል ነበር የተሰማኝ ። በእጆቹ እያጨበጨበ "ጎበዝ ልጅ ፤ ጥሩ ምርጫ ነው" አለኝ የፌዝ ይሁን የደስታ የማላውቀው የሳቅ አይነት እየሳቀ ። ቀጠልኩና 'እሺ ለምን እንዳልኩህ ግን ገብቶሃል ...? ሳታስጨርሰኝ ነው እኮ ማጨብጨብ የጀመርከው' ስለው "ያልኩህን ለመፈፀም ነዋ ፣ ሌላ ለምን ሊሆን ይችላል...?" አለኝ ። እኔም 'አይደለም ፡ አላስጨርስ አልከኝ እንጂ ልልህ የፈለኩት እኮ ፡ እሺ ከምትገለኝ ምናለበት እስር ቤት እንድገባ እንኳን ብትፈቅድልኝ ለማለት ነበር' አልኩት የማላገጥ ሳቅ እየሳኩበት ወኔዬ ከየት እንደመጣ ሳላውቅ ። ወዲያው መልስ ምት ነው መሰለኝ አይቼውም ቀምሼውም የማላውቀውን ጥፊ ድርግም ሲያደርግብኝ ለአስር ሴኮንድ ምድር ጨለመችብኝ ። ቀጥሎም አንገቴን አንቆኝ "ቆይ ማነኝ ነው የምትለው ...? ለልጅቷስ ይሄን ያክል እራስህን ለሞት አሳልፈህ የምትሰጠውስ ለምንድነው ? ልጅቷ ምንህ ነች .?" አለኝ ሀይል በተቀላቀለበት ድምፅ 'ስሟን አታውቅም እንዴ ? ህይወቴ ናት እኮ' አልኩት እንደ ማይገለኝ ስለታወቀኝ ደፋር ሆኜበት የሚለኝን እሺ ካላልኩት የሚገድለኝ ቢሆን ኖሮ መጀመሪያውኑ ወደ ጫካው ስገባ Video መቅረፅ አይጠበቅበትም ነበር video ሊቀርፀኝ የፈለገበት ምክንያትም እሺ ካላልኩት ለማስፈራሪያነት ሊጠቀምበት አስቦ እንደሆነ ግልፅ ነው ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሚገድለኝም ከሆነ ግን የጀግና ሞት ልሙት ብዬ እንጂ ለመሞት ዝግጁ ሆኜ እንኳን አይደለም በዚች ምድር ላይ የምንሞትለት ሰው ከሌለ የምንኖርለትም ሰው አይኖርም አለውልሽ የሚለው ቃል ትርጉም የሚያገኘው ስትሞትላትም ጭምር ብቻ ነው በአፍ ብቻ አለውልሽ ከጎንሽ ነኝ ፣ ምንጥሴ ቅብጥርሴ ማለት እራስን ማታለል ነው ለሰው ልጆች ሁሉ መኖር ብቻ ሳይሆን መሞትንም ጭምር ከክርስቶስ ተምሬያለሁ እየሰቀሉት እንኳን "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" እያለ ለገዳዮቹ ይፀልይ ነበር እኔ ደግሞ እንደ እርሱ ለጠላቶቼ ጭምር የምሞትበት አቅም ባይኖረኝ እንኳ ፤ ብያንስ ለወዳጆቼ መሞት አይከብደኝም ህይወት ደግሞ ለኔ ከወዳጅም በላይ ናት አይኖቿ እንዴት በስስት እንደሚያዩኝ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ወደ ጊቢ ለመመለስ ከቤታቸው ስወጣ እንኳን ፀሀይ የሚመስለው ፊቷ በአንዴ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ይሆናል እርግጠኛ ነኝ በኔ ቦታ ብትሆን ሳታንገራግር ህይወቷን ትሰጠኛለች በዚህም በዚያም ግን እኔ ለሰዎች መሞትን እንጂ ሰዎች እንዲሞቱልኝ አልፈልግም ከጥቂት ደቂቃ በዋላ የቤቱ መብራት ሲበራ አይኖቼ ሰውዬው ላይ ፈጠው ቀሩ ፊቱ አዲስ አልሆነብኝም አይኖቼን ጨፍኜ ለማስታወስ ሞከርኩ አይምሮዬ ይህ የህይወት አባት አይደሉም እንዴ ? ይለኛል አይኖቼን ገልጬ ድጋሜ ትኩር ብዬ ተመለከትኩት አዎ ልክ ነኝ ፤ እራሳቸው ከንቲባው ናቸው ሀሙስ ምሽት እነ ህይወት ቤት ግንባሯን ስሟት ወይናቸውን ይዘው ወደ መኝታ ክፍላቸው ሲሄዱ በትንሹም ቢሆን ፊታቸውን አይቼ ነበር ታድያ ምን እየተካሄደ ነው ? ምንስ ለማድረግ እየሞከሩ ነው ?

💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 26
.
.
.
ሽጉጡን አስቀመጡና ወደኔ ቀርበው እጄንና እግሬን ፈተው ወንበር አመጡና ፊትለፊቴ ተቀመጡ ።

​​እኔ በሁኔታው ስለ ተገረምኩኝ ምን ማለት እንዳለብኝ እራሱ ጠፍቶኝ ዝም ብዬ ተቀምጫለሁ ። እሳቸውም ትንሽ እንደ ማሰብ አረጉና "እየውልህ" ብለው ማውራት ጀመሩ።"እየውልህ በመጀመሪያ ምናልባት ካላወከኝ እኔ የህይወት አባት ነኝ።በዚህች ምድር ላይ ያለችኝ ብቸኛዋ ልጄና ሁሉ ነገሬ ናት።የሷ ነገር ከማንም እና ከምንም ነገር በላይ ስለሚያስጨንቀኝ ነው አንተ ላይ እንደዚህ ያደረኩት" ሲሉኝ 'ቆይ ፡ የእርሶ ለሷ መጨነቅ እና እኔን እንደዚህ ማድረግ ምን ያገናኘዋል ...?' አልኳቸው ። ቀጥለው "ሲመስለኝ ህይወት ስለራሷ ብዙ ነገር ነግራሃለች ። ከአራት ዓመት በፊት በተፈጠረ አደጋ ምክንያት ከቤት ወጥታ አታውቅም ። እኔ ደግሞ በስራዬ ምክንያት በየቀኑና በየሰዓቱ ከሷ ጋር መሆን ስለማልችል ደህንነቷን ለማረጋገጥ ብዬ በቤቱና በጊቢው ውስጥ security camera እና ድምፅ መቅጃ መሳሪያ ገጥሜ ነበር ። በዚህም መሳሪያ ለተከታታይ አራት ዓመታት ሁሌም የማየው እና የምሰማው ነገር ተመሳሳይ ነበር ። ታነባለች ፣ ትተኛለች ፣ ትንሽ ትበላለች ፣ ፊልም ታያለች ፣ በጊታር ትዘፍናለች ፣ ታለቅሳለች ፣ ትፅፋለች ። ነገር ግን በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ከኔ በስተቀር አንድም ሰው እቤት እሷጋ የሚመጣ ሰው አልነበረም ። ሁሌም የምታደርጋቸው ነገሮች ተመሳሳይ ከመሆናቸው የተነሳ ፣ በዛላይም በየ ሰዓቱ ስለምንደዋወል check ማድረግ እራሱ አቁሜ ነበር ። ነገር ግን ከሳምንታት በፊት አሜሪካ ሄጄ ስመለስ ጠረጴዛ ላይ የወንድ ልጅ የእጅ ሰዓት እና የአንገት ሀብል ተቀምጦ አየሁኝ ። (ስልክ ተደውሎላት ፡ አባቢ በር ላይ ነኝ ብሎኛል ብላኝ በጓሮ በኩል የደበቀችኝ ቀን እንደሆነ ትዝ አለኝ ። ከዛ ቀን በፊት ሶፋ ላይ ስተኛ አውልቄያቸው እዛው እንደረሳዋቸው ትዝ አለኝ) ። አባቷ ማውራታቸውን ቀጥለዋል ። "በሁኔታው ብደናገጥም እሷ እንዳታውቅብኝ ብዬ ሳምንት እመለሳለሁ አልኳትና ተሰናብቻት ወጣሁ ። በዛ ጊዜ እቅዴ የነበረው ወደ ውጪ ይዣት ለመሄድ የመጨረሻውን process ለማስፈጸም ነበር ። ግን ጠረጴዛው ላይ ያገኘሁት ነገሮች ስለረበሹኝ ወደ ውጪ መሄዱን ትቼ ወደ ቢሮዬ በረርኩኝ ። እቤት ውስጥ የሚፈጠረውን ነገር እየቀዳ የሚያሳየኝን screen ከፍቼ ከሳምንት በፊት እስከ ዛሬ የተቀዳውን ማየት ጀመርኩኝ ። ትኩረቴን የሳበው ግን ከሚያዝያ #30 ፡ ጀምሮ ያለው ነበር ። ህይወቴ በመኪና ከጊቢ ስትወጣ ያሳያል ። ከሰዓታት በዋላ ደግሞ ይበልጡኑ ትኩረቴን መሳብ ቀጠለ ። መኪናውን ይዛ ከወንድ ጋር ተመለሰች ። እኔ ሳላውቅ የኔ ልጅ ከአራት ዓመት በዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤት ወጥታ ከማላውቀው ሰው ጋር ተመለሰች ። ልጁም አንተ ነበርክ ። ስታወሩ የነበረውን ሁሉ አዳመጥኩኝ ። በንጋታው ምሽት እኔ መጣሁ ። በቀጣዩ ቀን ወደ ጊቢ ልመለስ ብለሃት ሄድክና ከሰዓታት በዋላ ተመልሰህ መጣህ ። ከዛን ወደ ደብረ ዘይት ለመሄድ አቅዳችሁ በንጋታው ከቤቱ ለቃችሁ ወጣችሁ ። እኔም ልክ እንደወጣችሁ ወደ ቤት ገባሁና እንዳልታወቅ ሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሼ ፣ መብራት ሳላጠፋ ከቤት ወጣሁኝ ። አዲስ አበባ ፣ ደብረዘይት ፣ በሄዳችሁበት ሁሉ ተከትያችሁ በስተመጨረሻም ኩሪፍቱን በጠዋት ለቃችሁ እንደወጣችሁ አወኩና እኔም ተመለስኩኝ" ብለው በረጅሙ ተነፈሱ ።

የህይወት አባት ሳያቋርጡ ሁሉን ነገር ለኔ መተረካቸውን ቀጥለዋል ። "ከደብረ ዘይት ስትመለሱ የቤቱ መብራቶች በርተው ስለጠበቋችሁ መረበሻችሁን በ security camera'ው አይቻለሁ ። ግን እኔ ነበርኩ ሳላጠፋ ረስቼ የወጣሁት ። በዛም ምክንያት የኔን ልጅ በችግሮቿ ቀን እንዳልተለየሀት አየሁኝ ። ልጄ ሁሉን ነገር እንደማውቅ እንዳታውቅብኝ ብዬ ባልኳት ቀን መሠረት ሀሙስ ከአሜሪካ የመጣሁ አስመስዬ ቤት ገባሁ ። ወደ ቤት ስመለስ እንኳን አንተ እቤት ውስጥ እንደነበርክ አውቅ ነበር ። ግን ሁሉን ነገር ከልጄ መስማት ስለፈለኩኝ ምንም አይነት ጥያቄ አላነሳሁባትም ። እሷ ግን እንኳን ልትነግረኝ ቀርቶ ጭራሽ ደበቀችህ ። ምስጥረኛዬ ፣ ሁሉ ነገሬ ፣ ህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኔ ከአባቷ ምስጢር ደበቀች ። ቢሆንም ግን አልተቀየምኳትም ። ሁሉም ነገር የኔ ጥፋት ነው ። እንዳንተ ሙሉ ጊዜዬን ፣ ሁሉ ነገሬን አልሰጠዋትም ። የኔ ልጅ ከኔ ለመደበቅ የፈለገችው ለክፋት አይደለም ። ምናልባት እኔ ካወኩኝ ካንተ ጋር የምትለያይ መስሏት ወይንም ደግሞ ፈርታኝም ሊሆን ይችላል ። ሴቶች ካፈቀሩ ምስጥረኛዬ ከሚሉት ሰው ጭምር ምስጢር መደበቅ ይጀምራሉ ። ይህ ደግሞ ምናልባት የወደዱት ሰው ላይ የሆነ ነገር እንዳይደርስ ከማሰብ የመነጨ ተፈጥሯዊ ቅድመ ጥንቃቄያቸው ይሆናል ። ባለፈው አርብ ጠዋት እንኳን ሙዚቃ እንደዛ አስጩሀ ከፍታ አንተን በዘዴ ከቤት እንዳስወጣችህ አውቃለሁ ። ይሄን ሁሉ እያየሁ ግን ዝም ያልኩት በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው ። አንደኛው ልጄን ከማንም በላይ ስለምወዳትና ከኔ የሚጠበቅብኝን ነገር ስላላደረኩላት ስሜቷን መጉዳት ስላልፈለኩ ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ያንተ ጥሩና መልካም ፀባይ ነው ። እኔ ይሄን ያክል ቀርቤያት ፍቅር ስሰጣት ፣ ስጨነቅላት እና ስንከባከባት ትዝ አይለኝም" ብለው በትካዜ ተውጠው ዝም አሉ ። ከዛን እኔም 'እሺ ፡ የሆነው ሁሉ ይሁን ፤ ግን የዛሬው ድርጊታችሁ ምንም አልገባኝም' አልኳቸውና መልስ ሊሰጡኝ ተዘጋጁ ። "ምን መሰለህ ፡ የህይወቴ ፀባይ ሀሙስ ወደ ቤት ከተመለስኩ በዋላ ሙሉ በሙሉ ተቀየረብኝ ። በተለይ በቅርቡ ወደ አሜሪካ እንሄዳለን ካልኳት በዋላ ከኔጋር ማውራት እራሱ አቁማለች ። ትካዜ ታበዛለች ፣ እየዘፈነች ታለቅሳለች ፣ ለብዙ ሰዓታት በሯን ዘግታ ብቻዋን ትሆናለች ። ቃል አውጥታ ባትነግረኝም ሁኔታዋ ሁሉ ከዚህ ሀገር ለቃ መሄድ እንደማትፈልግ ነው ። ምክንያቷ ደግሞ አንድና አንድ ብቻ ነው ። እሱም አንተ ነህ ። ወይ ካንተ ጋር ሀገር ለቆ መሰደድ ወይም ደግሞ እዚሁ ካንተ ጋር ሆና ሞቷን እንደምትመርጥ አውቃለሁ ። እኔ ደግሞ ልጄን እዚሁ ትቻት እንድትሞት መቼም አልፈቅድም ። ለዚህ ነበር አንተን ይዤ እሷን እንድትከዳትና ለሞት አሳልፈህ እንድትሰጣት መንገድ ያመቻቸውልክ ። ሞትን ወይንም እስር ቤትን ፈርተህ የምትሸጣት መስሎኝ ነበር ። እዚህ እያወራን ያለነው በሙሉ በድምፅ እየተቀዳ ነው አና ሞትን ፈርተህ እሷን እኔ ወዳልኩህበት ቦታ አመጣታለሁ ብትል ኖሮ ይሄንን ድምፅ መቅጃ ይዤ ሄጄ እሷም ባንተ ተስፋ ቆርጣ ትሄድልኝ ነበር ። አሁን ግን ነገሩ ጭራሹኑ አየከረረ መጣብኝ ። እንሂድ ብላት እምቢ እንደማትለኝ አውቃለሁ ። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና ብትሄድ በጣም ትጎዳብኛለች ። ከዚህ በፊት ብቻዋን ለአራት ተከታታይ ዓመታት ያሳለፈችው አስቀያሚ ህይወት እራሱ ይበቃታል" አሉኝ በጣሙን እያዘኑ



ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 27

.
.
.
ሀዘናቸው ሲጨንቀኝ ጊዜ 'እና አሁን እኔ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጉት ...?' ስላቸው "አሁንማ ያለኝ አንድ አማራጭ ብቻ ነው ። እሱ ደግሞ ካላንተ ፍቃድና ውሳኔ ውጪ መቼም የሚሆን አይነት አይደለም" ሲሉኝ 'ግድ የለም ይንገሩኝ ፤ ምንድነው እሱ...?' አልኳቸው ። "ምን መሰለህ ፡ ቅድም እንዳልኩህ የኔ ልጅ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆና የኔ እሷን ከዚህ ሀገር ይዞ መሄድ ከሞት ለማዳን ቢሆንም ግን ለሷ ስሜት ጥሩ ላይሆን ይችላል ። እናም ፍቃድህ ቢሆንና አብረኸን ወደ አሜሪካ ብትሄድ ምን ይመስልሃል...? ፡ አውቃለሁ እዚህ ደስ የሚል ህይወት ሊኖርህ ይችላል ። ቤተሰብ ፣ ጓደኛ ፣ ትምህርት ፣ ብዙ ነገሮችን ማጣትና መራቅ አትፈልግ ይሆናል ። ግን ምን ላድርግ...? ፡ በኔ ምክንያት ለአራት ዓመታት በአንድ ቤት ውስጥ ብቸዋን የሰቆቃ ህይወት ማሳለፏ ሳያንስ ፤ አሁን ደግሞ ነፃ ላወጣት ነው ባልኩበት በመጨረሻዋ ሰዓት ካንተ ጋር በፍቅር ወደቀችብኝ ። እሺ እኔ ብቻዬን ምን ላድርግላት ...? ፡ ሱቅ ሄደህ አትገዛው ነገር ፍቅር ነው ። በጣም ስለጨነቀኝ እና የልጄ ጉዳት ከአቅሜ በላይ ስለሆነብኝ ነው አንተንም የማስጨንቅህ" አሉኝ አይኖቻቸው በዕምባ ተሞልተው ። ጥያቄውን ለመመለስ ስጨነቅ አይተውኝ ነው መሠለኝ "ግድየለም ፡ በደንብ የምታስብበት በቂ ጊዜ እሰጥሃለሁ ። እንዳልኩህ እናንተን ለመከታተል ብዬ የአሜሪካ ጉዞዬን ሰርዤ ነበር ። እና እሱን process ለማስጨረስ ግዴታ ነገ ወደዛው በረራ ማድረግ ይኖርብኛል ። እናም በዚሁ ምክንያት ለአንድ ሳምንት እዛው ስለምቆይ አሁን የጠየኩህን ከዛ እስክመለስ ድረስ በደንብ አስበህበት መልስ እንደ ምትሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ ። ይቺን አንድ ሳምንት ህይወቴን ላንተ ነው አደራ ሰጥቼ የምሄደው ። ቢቻልህ ከትምህርት ሰዓትህ ውጪ ያለህን ጊዜ ከሷ ጋር ብታሳልፍ ደስ ይለኛል ። ደግሞ ዛሬ ስለሆነው ነገር ሁሉ እሷ ማወቅ የለባትም ። በቃ በጣም ስለመሸ ወደ ጊቢ ልመልስህና ከነገ ጀምሮ እስከ ምመለስበት ቀን ድረስ ህይወት ጋር እየመጣህ ከጎኗ መሆን ትችላለህ ። ምናልባት በወቅታዊው ጉዳይ ትምህርት የማይኖርህ ከሆነ ለደህንነታችሁ ሲባል እስክመጣ ድረስ ሀረር ብትሄዱ ለሷም ጥሩ ይመስለኛል ። ግን የሚመችህ ከሆነ ብቻ ነው ። እና ደግሞ ስልክህን ቅድም ለጥንቃቄ ብዬ ከኪስህ ወስጄ ነበር ። ልጄ በመቅረትህ እንዳታስብ በራሴ ስልክ ተመልሼ እየመጣሁ ነው ብዬ txt አድርጌላት ነበር ። እሷም "የኔ ጌታ እንዳትመጣ በቃ ፤ አባቢ እየተመለሰ ነው" የሚል txt ልካልሀለች" ብለውኝ ስልኬን መለሱልኝና መልዕክቱ እንደገባ አረጋግጬ ወደ ጊቢ ለመመለስ ተነሳሁኝ ። ከነበርንበት ክፍል ወጥተን ወደ ታች በደረጃ ወርደን በጣም የሚያምር ሳሎን ውስጥ አልፈን ደጃፍ ላይ ወደ ቆመው መኪና ገብተን የጊቢውን በር በሪሞት ከፍተው ወጣንና መልሰው በሪሞቱ ዘግተውት ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጉዞ ጀመርን ። ሌላ ነገር እንዳይመስል ዩኒቨርስቲው በር ጋር ሳንደርስ በቅርብ ርቀት ላይ መኪናውን አቁመው "አደራህን ፡ ያልኩህን በደንብ አስብበት ። ደግሞ እራስ ወዳድ ነህ እንዳትለኝ ፤ የልጄ ጉዳይ ሆኖብኝ ነው ። ስለሁሉም ግን በጣም ይቅርታ" አሉኝ ። ከልባቸው እንደሆነ ያስታውቃል ። እኔም 'ፈጣሪ ይቅር እንዲለንና ፣ በሰላም ሄደው በሰላም እንዲመለሱ መልካም ምኞቴን ገልጬላቸው ፣ በቶኒ በር ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዘለኩኝ ።ብቻዬን እራት በልቼ ወደ ዶርም ገባሁ ። የኛ ጊቢ ሰሞኑን ከሶሪያ በላይ ስለሚያስፈራ የዶርሜን ልጆች ጨምሮ አብዛኛው ተማሪ ጊቢ ውስጥ አያድሩም ። ውጪ ሶስት ሶስት ተማሪ ሆነው ቤት ተከራይተው ነው የሚኖሩት ። በዛ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ብቻዬን ዶርም ጋደም ብያለሁ ። #03 ሰዓት ላይ የኛ block አካባቢ ቅልጥ ያለ ጩኸት ሰምቼ በፍጥነት ከአልጋዬ ላይ ተነሳሁና በሁለተኛው በር በኩል የሚሆነውን ማየት ጀመርኩኝ ። አንድ የፋሲል መለያ የለበሰ ልጅ ከአምስት በላይ በሚሆኑ ልጆች እየተደበደበ ፣ እየጮኸ ፣ በስተመጨረሻ እንደምንም አምልጧቸው ወደ ዶርም ኡኡኡ እያለ ሮጦ ገባ ። ደብዳቢዎቹ የ turk ልጆችም ወደ ዶርማቸው ተመልሰው ገቡ ። እኔም ወደ አልጋዬ ተመልሼ በልቤ 'ወይ ዘንድሮ' እያልኩኝ ተኛሁ ። ከደቂቃዎች በዋላ ግን የቅድሙ ጩኸት በእጥፍ ጨምሮ ቅልጥልጥ ያለ ኡኡታ ይሰማኝ ጀመር ። የአንድ ሰው ድምፅ ሳይሆን የብዙ ሰዎች እሪታ ነው ። እንደ ቅድሙ ማየቱን ተያያዝኩኝ ። ለካ የቅድሙን ልጅ መመታት ሰምተው Wolfsburg'ኦቹ ከዋና በር ተጠራርተው በጀማ ሆነው ጊቢ ገብተው turk'ኦቹን በየዶርሙ እየገቡ መሸክሸክ ጀምረዋል ። ጥቁር ልብስ ለብሰው ፣ በእጃቸው ላይ ደግሞ ለምልክት ቀይ ጨርቅ አስረው ነበር የመጡት ። ጩኸቱና ኡኡታው ለደቂቃዎች ቀጥሎ በስተመጨረሻ turk'ኦቹ የድረሱልን ድምፅ እያሰሙ ከየዶርሙ መሰባሰብ ጀመሩና ጊቢውን ሞሉት ። ወዲያውኑ ግን federal ከዚህ በፊት ሰምቼው የማላውቀውን የጥይት ድምፅ አከታትሎ ወደላይ ተኩሶ ካለሁበት አነጠረኝ ። ሁሉም ተበታትነው ወደየ ዶርማቸው በሩጫ ገሰገሱ ። ይሄን ሁሉ ብቻዬን ዶርም ውስጥ ሆኜ በሁለተኛው የዶርሙ በር መስታወት ስከታተል ነበር ። ጠዋት ነግቶ አብዛኛው ተማሪ class የሚጀመር መስሎዋቸው ወደ ጊቢ ተመልሰው ነበር ። ግን አሁንም በማታው ረብሻ ምክንያት ትምህርት ሊጀመር አልቻለም ። ምሳ ሰዓት ደርሶ ልንበላ ከጊቢ ልንወጣ ስንል ሶስቱም የጊቢው በሮች ተዘግተው ጠበቁን ። መግባት እንጂ መውጣት አይቻልም ። ተማሪ አንዴ ከጊቢ ከወጣ እንደ ማይመለስላቸው ስላወቁ ነው በሮቹን የዘጉት ። አብዛኛው ተማሪ ፍቅር cafe ተሰብስበው የበሮቹን መከፈት በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል ። እያስፈራሩን ነው መሠለኝ ፌደራሎቹ patrol መኪና ላይ ሆነው ጊቢውን እያሰሱት ነው ። ምሳ ሰዓት አልፎ ተማሪ በጠኔ ተመቶ ፌንት ሊሰራ ሲል ልክ #09 ሰዓት ላይ የጊቢው የተማሪዎች president መጥቶ ሰበሰበንና በዛው ሄደንባቸው እንዳንቀር ID card አስይዘን እንድንወጣ አሰፈቅዶልን ፣ በዛው ወጥቶ የሚቀር ተማሪ ላይ ግን እርምጃ እንደሚወሰድ ነገረን ። በጣም እርቦን ስለነበር መታወቂያችንን ፊታቸው ላይ ወርውረን ከጊቢ ወጣን ። (ፊታቸው ላይ ወርውረን የምትለዋ ሳክስ ናት ...🙆) ። ምሳ በልተን ወንጀለኛ ላለመባል ወደ ጊቢ ተመልሰን ID card ወስደን የህንድ ፊልም ለመስራት ከ #20 ተማሪዎች ጋር strategy መንደፍ ጀመርን ። ጊቢ ውስጥ መቆየቱ ለኛ በጣም መጥፎ ሊሆን ስለሚችል በአጥር ለመውጣት set up አዘጋጅተን እቅዱን አሳክተን ተደብቀን በአጥር ዘለን ወጣን ። የስራ ባልደረቦቼን አመስግኜ ጉዞዬን ወደ ከንቲባው ልጅ ቤት አደረኩኝ

ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................

💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 28


.
.
.
እቤታቸው በር ላይ ደርሼ ስልኳ ላይ ደውዬ በሩን ከፍታልኝ በናፍቆት እንደ እባብ ተጠመጠመችብኝ ። እንደውም ናፍቆቱ አልወጣ ስላላት እንደዛው እንዳቀፈችኝ ነው ተሸክሜያት ወደ ውስጥ የገባነው ። አባቷ እንዳሉኝ ነው ፤ መልኳ እንደበፊቱ አይደለም ። ፊቷ እኔን ስታገኘኝ ፍክት ቢልም አልቅሳ እንደነበር ያሳብቃል ። አርብ ዕለት speaker አስጩሀ ከቤት በዘዴ ካስወጣችኝ በዋላ ሳንተያይ ይኸው በሶስተኛው ቀን ሰኞ ላይ ተገናኝተናል ። ለኛ ግን ሶስት ቀን ብቻ አይደለም ። ሶስት ዓመትም ርዝመቱን አይገልፅልንም ። ትምህርት ስለሌለኝ አባቷ እንዳሉኝ ማድረግ ይኖርብኛል ። ነገ በጠዋት ወደ ሀረር ይዣት ሄጄ አባቷ እስኪመለሱ ድረስ ለአንድ ሳምንት እንደልቧ እንድትቦርቅ አደርጋታለሁ ። ማታ ላይ እንደ ተለመደው አብረን እራት ሰርተን ጥግብ እስክንል በላንና ነገ ሀረር እንደ ምንሄድ ነግሬያት በደስታ ተስማምታ ፤ እሄድባት ይመስል ጥብቅ አርጋ አቅፋኝ አንድ አልጋ ላይ ተኛን ። ለመሄድ ምን ያክል እንደቸኮለች የገባኝ በጠዋት ተነስታ ሞልተን የተኛነውን Alarm ስትቀሰቅሰው ነበር ። የሀረር ከተማ ለድሬዳዋ በጣም ቅርብ ስለሆነች በለሊት መነሳቱ አስፈላጊ አልነበረም ። ለዛም ነው ሁለት ሰዓት ላይ ከድሬ ጉዞ የጀመርነው ። አስፈሪውን የደንገጎ ጠመዝማዛ ተራራማ መንገድ አልፈን አንድ ሰዓት ሳይፈጅብን አዴሌ ደረስን ። ከዛን ሀሮማያ ፣ አራተኛ እያለን የሰላም ተምሳሌት የሆነችውን የሀረር ከተማ ምድር በሰላም ረገጥን ። እኔ ስመጣ ለአራተኛ ጊዜዬ በመሆኑ ውስጥ ለውስጡ ምንም አያስቸግረንም ። ጊዜያዊ መኖሪያችንን ከአንዱ ሆቴል ጎራ ብለን ይዘን ገና ከጠዋቱ #04:00 ሰዓት በመሆኑ (ቁርስ + ምሳ = ቁምሳ) ቁምሳችንን በልተን የሰላም አየር እየተነፈስን ዞር ዞር ማለት ጀመርን ። ስማቸውና መገኛቸው ሁለት ቦታ ሆነ እንጂ ለኔ ድሬ እና ሀረር ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ባልና ሚስት ነው የሚመስሉኝ ። አንድ አይነት ህዝብና ከተማ ። ሁለቱም የሆነ ዘመን ላይ በጣም አድገው የኢትዮጵያ ከፍታ ሆነው ፤ በአሁኑ ዘመን ግን አስታዋሽና ውለታ መላሽ ትውልድና መንግስት አጥተው ወደ ማርጀት እየተቃረቡ ያሉ ከተሞች ናቸው ። ለሰው ልጅ ያላቸው ፍቅርና ክብር የትም አለም ላይ አይገኝም ። አንዳንዴ የህዝባቸው ፍቅር ሲገርመኝ ከድሮዋ ኢትዮጵያ የተረፉ ዘሮች እነዚህ ሁለቱ ከተሞች ይመስሉኛል ። ጭንቀት እና ጥላቻ የሌለባቸው ልዩ ፍጡራን እነሱን አየሁ ። ቢሆንም ግን አየር ሁኔታቸው የሰማይና የምድር ነው ። ድሬዳዋ ከፀሀይዋ የተነሳ ፍሪጅ ውስጥ ብንገባ እንኳን ሞቆን ያልበናል ። ሀረር ደግሞ በተቃራኒው ከብርዱ የተነሳ ከውጪው ይልቅ ፍሪጅ ውስጥ መሆኑ ሳይሻል አይቀርም ። በተለይ ሲመሻሽ ደብረ ብርሃን እራሷ በብርዷ የምትቀና ይመስለኛል ። ከጀጎል በር ተነስተን እስኪሰለቸን ድረስ ሀረርን በወክ አካለስናት ። ቁምነገር ግን መሽቶ ከብርዱ የተነሳ ስልኬ ደንዝዛ አልታዘዝ አለችኝ ። ከሙቀት ይልቅ የብርድ አፍቃሪ ብሆንም ግን የሀረር በዛ ። ምሽት ላይ አልጋ ከያዝንበት ሆቴል ቆንጆ እራት በልተን ለብርዱ ማስታገሻ እኛው ለእኛው አናንስም ብለን ተቃቅፈን ተኛን ።

"ነይ በክረምት ፡ ነይ በብርዱ ፤ ሰው አይችልም ሆዱ
ነይ በሀምሌ ፡ ነይ ነሐሴ ፤ እንዳረግሽ የራሴ ።"

ሀረርን በጣም ወደናታል ። ከሁሉ በላይ ግን ህዝቦቿን ነው የወደድናቸው ። ከተማዋን እና መንደሮቿን ለአምስት ተከታታይ ቀናት እየዞርን ከእግር ጥፍራ እስከ እራስ ፀጉሯ ድረስ ዋና ዋናዎቹን ቦታዎች ጎብኝተን ጨረስን ። ከሁሉም ግን መቼም የማንረሳው ፣ በጣም አስፈሪውና አስደሳቹ ጉብኝታችን ከጅብ ጋር face to face ተቀራርበን ምግብ ተጎራርሰን ያሳለፍነው የአርብ ዕለት ምሽቱ ነው ። ከዚህ በፊት ጅብን ብዙ ቀን ቀሩቅ አይቼ አውቃለሁ ። ነገር ግን አጠገቤ ቆሞ ፣ ትከሻዬ ላይ ሆኖ ፣ ስጋ ከእጄ ጎርሶ ፣ ፍጥጥ ብሎ አይን ለአይን ስንተያይ ይህ የመጀመሪያዬ ነው ። ለህይወት ግን ይህ የመጀመሪያዋ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻዋም ሳይሆን አይቀርም ። በስንት መከራ ነበር መሬት ላይ ጎትቻት ከጅቡ አጠገብ ያደረስኳት ። እሱንም አይኗን ጨፍና ነው ። በእጇ ስጋ ይዛ ጅቡ ዘሎ ከእጇ ላይ ሲነጥቃት እንዴት በድንጋጤ ዘላ እኔ ላይ እንደወጣች እሷ እራሱ አታውቀውም ። እንደዛው ድንግጥ ፣ ፍዝዝ እንዳለች ነበር ተሸክሜያት ወደ መኪናችን የሄድነው ። በስተመጨረሻ ግን እንደምንም ፀበል ማነው ሀይላንድ ውሃ ረጨውባትና ወደ ቀልቧ ተመልሳ ወደ ሆቴላችን ተመልሰን እራት በልተን ተኛን ። ጅቡ እንዳይበላት ሰግታ ነው መሠለኝ ደረቴ ውስጥ ሽጉጥ ብላ በብርድ ልብሱ ተሸፋፍና ነበር የተኛችው ። እኔ ግን ውሏችንን በጣም ነበር የወደድኩት ። እንኳን ሰው እንስሳው ጭምር ከሰው ተላምዶ ፍቅር የሆነባት ብቸኛዋ የአለማችን ከተማ ሀረር ። ቅዳሜን ግን ልክ ፈጣሪያችን በቅዱሱ መፅሐፍ ላይ #6 ቀናትን ፍጥረታት በሙሉ ፈጥሮበት በሰባተኛው ቀን ላይ ከስራው ሁሉ እንዳረፈ ፤ እኛም ከጉብኝታችን አርፈን የራሳችን የሆነ ጣፋጭ ጊዜ ለማሳለፍ ተዘጋጀን ። ነገ የአባቷ የመመለሻ ቀን በመሆኑ ነገ በጠዋት ወደ ድሬዳዋ መመለስ ይኖርብናል ። ስለዚህ ዛሬ በሀረር የመጨረሻ ቀናችን በመሆኑ የማይረሳ የብቻችን ቀን ለማሳለፍ አስበን እንደዚያው እያደረግን ነው ። በመሀል ግን ህይወት አንድ ያልጠበኩትን ጥያቄ አቀረበችልኝ ። በስስት አይኖቼን እያየች "ለምን ይዘኸኝ አጠፋም ...?" አለችኝ ። አባቷ ከጠየቁኝ በተጨማሪ ሌላ ነገር መጣብኝ ። የአባቷን ቃል ተቀብዬ ከነሱ ጋር ወደ አሜሪካ መሄድ ወይስ የልጅቷን ጥያቄ በፀጋ አምኜ ወደ ማናውቅበት ቦታ መጥፋት ...? ለኔ ግን እሷን ይዞ መሸሹ ምንም አልታየኝም ። ምክንያቱም ከምንጠፋ በሰላም አሜሪካ መሄዱ በጣም የተሻለ ነው የሚሆነው ። በእርግጥ ህይወት ይሄን የጠየቀችኝ አባቷ ከኔጋር ግኑኝነት እንዳሏቸው ስለማታውቅ ይሆናል ። ሆኖም ግን እኔ ከሀገር የመውጣት ምንም ፍላጎቱ የለኝም ። ቢኖረኝም አባቷ ስለጠየቁኝ ብቻ ብድግ ብዬ መሄዱ ምንም አልታየኝም ። ከነሱ ጋር የምሄድበት በቂ ምከንያት የለኝም ። ምንም እንኳ ህይወት በጣም ብታሳዝነኝም እዚህ ባለኝ ነገር ደስተኛ ነኝ ። ቤተሰቦቼ ፣ ጓደኞቼ ፣ የለመድኳቸውን ሰዎችና ነገሮች ትቼ መሄድ አልፈልግም ። ይሄን ደግሞ እንዴት ብዬ ለህይወትና ለአባቷ እንደ ምነግራቸው በጣም ጨንቆኛል ። ጭንቅላቴ በነዚህ ሁለት ሀሳቦች መካከል ሆኖ ግራ ተጋብቷል ። ለማንኛውም ነገ የልደቴ ቀን ነው ። ሁሉን ነገር ነገ አባቷ ሲመጡ ወስኜ አሳውቃቸዋለሁ ። በህይወቴ ትልቁና ወሳኙን ውሳኔ የወሰንኩበት ዕለት ሆኖም ያልፋል።

ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​😘የከንቲባው ልጅ😍

🔥ክፍል 29


.
.
.
በሀረር የመጨረሻ ቀናችን በመሆኑ ህይወት ፈታ ፣ ፏ ብልጭ ብለን ምሽታችንን እንድናደምቅ ጠይቃኝ አለ የተባለውን ጭፈራ ቤት አፈላልገን ከጥቂት ድካም በዋላ አግኝተን ወደ ውስጥ ገባን ። ለዚሁ ቅድመ ሁኔታ ብለን እራታችንን ጥግብ እስክንል ድረስ ጠቅጥቀን በልተናል ። ሆድን ከመጠጥ በፊት አስቀድሞ መሙላት የሰካራም ደምቡም አይደል ...? ። ጭፈራ ቤቱ እስከ መውጫ በሩ ድረስ በሰዎች ተሞልቷል ። በቁጥር ግን ከአዋቂዎች ይልቅ ወጣቱ ትውልድ ይበዛል ። ልክ እንደ እኔና እንደ ህይወት አይነቱ ። እኛስ ይሁን ሽር ሽር ላይ ነን ፤ ሌሎቹስ በዚህ ሰዓት እዚህ ቦታ ላይ መገኘት ነበረባቸው ...? ብዬ ለነሱ መቆርቆር አልፈለኩም ። እኔም ባለሁበት ነገር ላይ አስተያየት መስጠትና ወቀሳ ማቅረብ ደስ አይለኝም ። እየጠጣን እያለ በመሀል ህይወት "ቆይማ አንዴ መጣሁ" ብላኝ ከጭፈራ ቤቱ ወጣችና ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ኬክ ይዛ ተመለሰች ። ለዲጄው ሙዚቃውን እንዲያቆመው ምልክት ሰጠችና ለህዝቡ ሰላምታ ሰጥታ ማውራት ጀመረች ። በእጆቿ ወደኔ እየጠቆመች "እዛጋ የምታዩት አስጠሊታው ልጅ ጓደኛዬ ነው ። እና ከተዋወቅን እልፍ አዕላፍ ዘመናት አልፈውናል ። የሚገርማችሁ የተወለደው ልክ የዛሬ #21 ዓመት ከለሊቱ #06 ሰዓት አካባቢ ነው ። እንዴት እንዳወኩኝ ታውቃላችሁ ...? ቁጭ አድርጎ ዝክዝክ አርጎ ነግሮኝ ነው ። (እኔ ግን ስለ ልደቴ ቀን ምንም ያልኳት ነገር የለም ።) እንደ ምታዩት መልኩ በጣም ያስጠላል ። ልክ እንደ መልኩ ፀባይም ምንም የሚወደድ ነገር አልፈጠረበትም ። በጣም ነው የምጠላው ። እሱ ግን ከልቡ ነው የሚወደኝ ። ነፍሱ እስኪጠፋ ድረስ ያፈቅረኛል ። እንደውም እዚህ ከመምጣታችን በፊት ይዤሽ ልጥፋ ብሎኝ እምቢ አልኩት እንጂ ከኔጋር ብቻ ለመሆን የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም" ። ህይወት ወደኔ እያየች ማውራቷን ቀጥላለች ። ብዙ ብትጠጣም እያወራች ያለው ነገር ግን ከስካር የመነጨ አይመስለኝም ። በቃ ሆዷ ውስጥ የቀረውን ነገር በቅኔ መልክ እያሳወቀችኝ መሆኑ ነው ። "እና ይዤሽ ልጥፋ ሲለኝ ፡ እኔ ግን በጣም የምወደው ለጊዜው በመሀላችን በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ብንለያይም የልቤ ሰው ማራኪዬ የሚባል ፍቅረኛ ስላለኝ እምቢ አልኩት ። እምቢ ስላልኩት እንኳ ተቀይሞኝ አልተወኝም ። በኔ መቼም ተስፋ ስለማይቆርጥ እስካሁን ድረስ አብሮኝ አለ ። አሁን ግን ሳየው በኔ ላይ ያለው ተስፋ እየተመናመነ እየመጣ ነው ። እንደውም በቅርቡ የህይወት ጉዳይ ሆኖበት ጥሎኝ ወደ አሜሪካ ሊሄድ ነው ። plane ላይ ወጥቶ ይቺን ሀገር እስኪለቅ ድረስ በኔ ተስፋ የሚቆርጥ አይመስለኝም ። እስከዚያች ቀን ግን አብሬው እንድሆንና እንድሄድ ዕድል ሰጥቶኛል ። እኔ ግን ከማራኪዬ እና ከእሱ መምረጥ አቅቶኝ መጨረሻ ላይ ብቻዬን እንዳልቀር እሰጋለሁ" አለችና ዕምባዋን እየጠራረገች "በልደቱ ቀን ምንድነው የምቀባጥረው ...? በቃ ሁላችሁም እንኳን ተወለድክ በሉልኝ እስኪ" ብላ ዲጄውን የሆነ ነገር አለችው ። እሱም "ልዩ ፡ ልዩ ፡ ልዩ ቀን ነው ልዩ" የሚለውን ሙዚቃ ከፍቶ ቤቱ ውስጥ ያሉትም በጭብጨባ ተቀብለውት መልካም ልደት brother ፣ መልካም ልደት ባባ ፣ happy birthday አባቴ ፣ እያሉኝ ይጨብጡኝ ጀመር ። ኬኩንም እንድቆርሰው ዕድል ተሰጥቶኝ በመስቀል አምሳያ ለአራት ሰነጠኩት ። ተበላ ፣ ተጠጣ ፣ ተጨፈረ ፣ ተሰከረ ፣ በስተመጨረሻም እኔና ህይወት ተያይዘን ዚግዛግ እየሰራን ዕዛው ጭፈራ ቤት ካሉት አንዱን መኝታ ቤት ይዘን አልጋው ላይ ፌንት ሰራን ።
የተቀባችው ሽቶ በጠጣነው አልኮል ላይ ተጨምሮ ይበልጡኑ አጦዘኝ ። ለነገሩ የገላዋ መዐዛ ለብቻው እራሱ ናላ አዙሮ ያንበረክካል ። ከሱ በተጨማሪም የሰውነቷ ግለት ተላልፎብኝ ላብ በላብ ሆኛለሁ ። የፍቅር ያለህ ፡ የእሳት ያለህ ፡ የፀሃይ ጮራ ጤዛን እንዲመጣት ፤ እንዲሁ ደግሞ የሷ ረጅም ስምያ በከንፈሯ አድርጎ ነፍሴን መነጠቃት ። ከሙቀቱ ለመሸሽ ብለን ሁለታችንም ልብሶቻችንን አውልቀን ልክ አዳምና ሄዋን ዕፀ በለሷን በልተው ራቁታቸውን እንደቀሩት ፡ እንደዛው ሆነናል ። ልክ ከእናታችን ሆድ ወጥተን ይቺን ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ ስንቀላቀል እንደነበርነው አይነት እኛም መለመላችንን ቀርተናል ። ከዚያ በዋላ የተፈጠረው እንግዲህ ቅዱሱ መፅሐፍ እንደሚለው አወቀችኝ ፡ አወኳት ፡ ተዋወቅን ። ብቻ ለጥቂት ደቂቃም ቢሆን ነፍሴ የሰማይ ጫፍ ላይ ደርሳ ስትመለስ ታይቶኛል ። ሁለታችንም ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ አልጋ ላይ ሁለት አካላችንን በአንድነት አጣምረን ተኛን ። እኔና አንቺ የሚለውን ግለኝነት ገፍተን እኛ የሚለውን ህብረት መርጠን አቀፍን ።

"ወፎች እስኪንጫጩ ፡ እስኪነቃ ምድሩ ፣
ቃላት ያልቻሉትን ፡ ያን ዝርዝሩን ሁሉ ፣
ከናፍሮቻችን ፡ ማልጎምጎም ቀጠሉ" ።

ጠዋት ነግቶ ካንቀላፋንበት ስንነቃ የትናንቱን ምሽት ድፍረት አልነበረንም ። ልክ አዳምና ሄዋን ዕፀ በለሷን ከበሉ በዋላ ራቁታቸውን እንደሆኑ አውቀው ዛፍ ስር ከፈጣሪያቸው እንደተደበቁ ፤ እኛም እርስ በእርስ ተፈራርተን ልብሶቻችን ውስጥ ተደበቅን ። በዝምታ ከአልጋ ላይ ተነሳን ፣ በዝምታ ቁርሳችንን በላን ፣ በዝምታ ሀረርን ተሰናብተናት ወደ ድሬዳዋ ጉዞ ጀመርን ። የደንገጎ መንገድ ላይ ስንደርስ ህይወት "ፀፅቶሀል አይደል...?" አለችኝ ። እኔም 'የሆነው ሁሉ መሆን ስላለበት ሆኖ አልፏል ። ነገሩ ልክ ነው ፡ ልክ አይደለም ብዬ አንቺንም እራሴንም ማስጨነቅ አልፈልግም ። ለውጥ ላናመጣ ነገር ወደዋላ ተመልሰን ስለሱ ማሰብና መጨነቅ ጥቅሙ ጉዳት ነው' አልኳት ። እሷም ቀጠለች "ዝም ያልከው ነገሩ አሳስቦክ ይሆናል ብዬ ነው የጠየኩህ ። በነገራችን ላይ እኔ በተፈጠረው ነገር መቼም አልፀፀትም ። በልደትህ ቀን እንደ ሌሎቹ የአንገት ሀብል ፣ የተለያዩ ስጦታዎችን ልሰጥህ አልፈለኩም ። ላንተ የሚገባው እሱ አይደለም ። እኔ የራሴ አይደለሁም ። ሁለመናዬ ሁሉ ያንተ ነው ። ያንተኑን ነገር ነው መልሼ የሰጠሁክ ። ክብሬንና ንፅህናዬን ብቻ አይደለም ፤ አንዲቷንም ነፍሴን ላንተ ለመስጠት ሁሌም ዝግጁ ነኝ ። ታውቃለህ የልደቴ ቀን የእናቴም የሞት ቀን በመሆኑ አንድም ቀን አክብሬው አላውቅም ። ከአሁን በዋላ በዛ ፋንታ አንተን ያወኩበትን ዕለት እንደ ልደቴ ቀን አከብረዋለሁ ። አውቃለሁ አንተ ከእኔ በላይ የምትኖርላትና የምታፈቅራት ልጅ አለች ። እሱን እያወኩኝም ላንተ ያለኝን ስሜት ማጥፋትና መተው እንኳን አልቻልኩም ። በቃ አባቴ ልክ እኔን ህይወቴ እንደሚለኝ እኔም አንተን ህይወቴ ብዬሃለሁ ። ላጣህ አልፈልግም ፤ ግን እንደማጣህ አውቃለሁ ። ባውቅም ግን አልተውህም" አለችኝ ትክዝ ብላ ። በጣም ይጨንቃል ። በጣም የሚወዱት ሰው ከልብ ሳይጠፋ ሌላ ሁለተኛ ሰው ልክ እንደ መጀመሪያዋ አይነት ልብና ስብዕና ያላት ሴት ወደ ልብህ ልትገባ ስትመጣ ምንድነው የሚደረገው ...? በኔ ተስፋ ትቁረጥ አትቁረጥ የማላውቀውን ፣ ስልኬን ለማንሳት እንኳን ፍቃደኛ ያልሆነችውን ፣ ከራሴ በላይ የምወዳትን ማራኪዬን ብዬ ህይወትን ወደ አሜሪካ ለብቻዋ ልሸኛት ወይንስ ማራኪዬ በኔ ተስፋ እንደቆረጠች በማሰብ እኔም ተስፋ ቆርጬባት እንደ ነፍሷ የምትሳሳልኝን ፣ ከአይኖቿ የፍቅር ዕምባ የሚፈሳትን ህይወትን መርጬ ከዚህች ሀገር ለፍቅር ስል ልመንን ...? የእውነት ይጨንቃል ።

ይቀጥላል....
.
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 31

.
"የኔ ሻህሩክ ፡ እኔኮ ስቀልድ እንጂ አትሆንም ብዬ አይደለም" አለችኝና ከወንበሩ ላይ ተነስታ በጀርባ በኩል ጥምጥም ብላብኝ ጉንጬን ግጥም አርጋ ሳመችኝና "ይቅርታ እሺ የኔ ጌታ ...!" ብላኝ ወደ ቦታዋ ተመለሰች ። እኔም 'አያሳስብም ፣ ደግሞም ምንም አለተቀየምኩሽም ። ቆይ ግን አንቺስ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ...? ያው ስታድጊ ያላልኩሽ already አርጅተሻል ብዬ ነው' አልኳት ። "ሙት እሺ ፡ እኔ እንኳን መሆን የምፈልገው እንዳንተ ቀላል ላይሆንልኝ ይችላል ። እንዳልከው ማንኛውንም ነገር ከተፋለምንለት ልናገኘው እንችላለን ። የኔ ህልም ግን ያን ያክል ቀላልና በዋዛ የሚኮን ነገር አይደለም ። በቃ ህልም ብቻ እንጂ እውን አይሆንም" ስትለኝ ፡ ይሄን ያክል ምን ለመሆን ብትመኝ ነው አልኩና ህልሟ ምን እንደሆነና በምችለው ሁሉ እውን እንዲሆንላት ከጎኗ እንደምሆን ነገርኳት ። እሷም "የወደፊቱን ህልሜን ብነግርህ እንዲሳካልኝ ከጎኔ እንደ ማትቆም አውቃለሁ ። ይሄን የምታደርገው ደግሞ እኔን ለመጉዳት እንዳልሆነም አውቃለሁ ። የኔ ህልም ያንተ ሚስት መሆን ነው ። እና እውን እንዲሆንልኝ ትረዳኛለህ ...?" አለችኝ ። 'እኔኮ እየቀለድኩ አይደለም የምሬን ነው' ስላት "በቃ እንደውም እሱን እርሳውና አንድ ነገር አምሮኛል" አለችኝ ። 'በአንድ ቀን አርግዘሽ እንዳይሆን ያማረሽ' ስላት "እኔም እየቀለድኩ አይደለም የኔ ጌታ ። ስወድህ ግን እምቢ እንዳትለኝ ። ዋና በጣም አምሮኛል ፤ በእናትህ የምታውቀው ቦታ ካለ እዛ ውሰደኝ" አለችኝ በነዚያ መንግስትን እንኳን ሀሳብ ለማስቀየር ሀይል ባላቸው አይኖቿ ጭምር እየተማፀነችኝ ። የለስላሳውን ሂሳብ ከፍለን በመኪናችን እዛው ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው #MA ሆቴል በረርን ። ደርሰን ልብሳችንን አውልቀን የዋና ልብስ ከዛው ተከራይተን ለመዋኘት ተዘጋጀን ። ደግነቱ ከኛና ከሚያስዋኘው ልጅ ውጪ ማንም ሰው በቦታው የለም ። "ስማኝማ ፡ ለምን ደብረ ዘይት ያለማመድከኝን ዛሬ ከ #10 test አትፈትነኝም ። ከፈለክ እንደውም final አርገው" አለችኝ ህይወት እየሳቀች ። እኔም 'በዋላ ከከበደሽ ግን የለሁበትም' አልኳትና ወደ ዋና ገንዳው ገፈተርኳት ። አንዴ ጠጥታው ስትወጣ ፣ ሌላ ጊዜ ወደ ውስጥ ስትሰምጥ መጨረሻ ላይ እንደምንም ተረጋጋችና ውሃውን ተቆጣጠረች ። ቀና ብላ ወደላይ እያየችኝ "ጨካኝ መምህር ነህ እሺ" አለችኝ ። 'እሺ የኔ ጉረኛ ተማሪ' አልኳትና ወደ ውሃው ውስጥ ዘልዬ dive ገባሁ ። ብዙም perfect ስላልሆነች ትንሽ አለማመድኳት ። ለመልመድ ብዙም አልተቸገረችም ። እንደውም ከባለፈው ይልቅ በጣም ተሻሽላ ከኔም ጋር ፉክክር ጀምራለች ። ዕረፍት እየወሰድን እየዋኘን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። "ካሁን በዋላ እንደውም እኔ እራሴ እንዳላለማምድህ" አለችኝ እዛው ውሃ ውስጥ የገንዳውን ጫፍ ግድግዳ ተደግፈን እንደቆምን ። make up ስለማትጠቀም ውሃ ነክቷትም መልኳ እንደዛው ውብ እንደሆነ ነው ያለው ። እንደውም ውሃ ሲነካው ይብስበታል ። እጆቼን በእጆቿ ስትይዘኝ ውሃ ውስጥ ቆሜ ሙቀት ይገለኛል ። መላ ሰውነቴን የሆነ ነገር ውርር ያደርገዋል ። አይኖቿን አይኖቼ ላይ ከጣለች ደግሞ በቃ ልቤ ወጥቼ ከሷ ልብ አጠገብ ካልተቀመጥኩ ይላል ። "እኔን ውሃ ውስጥ አቁመህ ስለምን እያሰብክ ነው ...?" አለችኝና ከሃሳቤ ባነንኩኝ ። 'ስላንቺ ነዋ ፣ ሌላ ስለማን አስባለሁ' ስላት "ስለኔ ምን የኔ ጌታ" ብላኝ ይበልጡኑ ወደኔ ተጠግታ አይን አይኔን ማየቱን ቀጠለች ። የሆነ ነገር ልነግራት እፈልጋለሁ ። ግን ይተናነቀኛል ። አፌ ለመናገር ሲጨናነቅ አይኖቼ አውቀውበት ከንፈሯ ላይ ጣሉኝ ። ያ የማይፋታኝ የቴዲ አፍሮ ዘፈን ፊቴ ላይ ድቅን ሲል ከንፈሬን ከከንፈሯ ጋር አዋሀድኩት ። መቼም ልቀቁኝ የማይል ጣፋጭና ስስ ከንፈር ።

"ሳማት ሳማት አለኝና ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣
ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር...


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 30


.
.
.
ድሬዳዋ በሰላም ገብተ

​​ናል ። ህይወት "ከልደትህ ቀን ላይ አንድ ሰዓት ሰጥተኸኝ ለትንሽ ጊዜ እንኳን አብረኸኝ አትሆንም ...?" አለችኝ ወደ ጊቢ እንደምሄድ ስነግራት ። ያንን አሳዛኝ ፊቷን እያሳየችኝ ስትለምነኝ ጥያት የመሄድ ምንም አቅሙም አይኖረኝም ። የድሬ ከተማ መግቢያ ላይ ወደ ሚገኘው #CCECC ሆቴል አመራን ። የቻይናዊ ሰው ሆቴል ነው ። "ከዚህ በፊት እዚህ መጥተህ ታውቃለህ እንዴ ...?" አለችኝ አየመራዃት ወደ ውስጥ ስንገባ ። 'አዎ' ስላት "መቼም የቻይና ምግብ አምሮህ እንዳልመጣህ ተስፋ አለኝ" አለችኝ እያሾፈችብኝ ። 'አይደለም ፤ ፊልም ለመስራት ነው የመጣሁት' አልኳት ። "የድሬ ልጅ ነች የከዚራ ፤ ስለ ውበቷ ስንቱን ላውራ የሚል ፊልም መሆን አለበት" አለችኝ በድጋሜ እየቀለደችብኝ ። 'ርዕሱን ለጊዜው አላውቅም' ስላት "እንዴዬ ፡ አንተ የምርህን ነው እንዴ አለችኝ" ኮስተር ስላልኩባት ። 'አዎ የምሬን ነው ። እንደውም አምስት ወር ሊሆነው #4 ቀን ይቀረዋል ። ታህሳስ #22 ነበር ። እዚሁ ሆቴል ውስጥ በአክተሮች ፣ ካሜራ ማኖች እና ሜክ አፕ አርቲስት ተከብቤ ነበር ። ቃልኪዳን ጥበቡ (የባባ ሚስት) ፣ ከዘመን ድራማ ተዋናዮቹ እነ አዩ ግርማ ፣ ሄኖክ ድንቁ ፣ እና የመሳሰሉት ነበሩ የፊልሙ ተዋናዮች ። ለካ ፊልም እንደዚህ ተቀርፆ ነው እኛ ጋር የሚደርሰው ። ብታይ የአምስት ደቂቃ ትዕይንት ለመቅረጽ ከሃያ ጊዜ በላይ ነው Cut ፣ action የተባለው ። ከስምንት ሰዓት እስከ #11 ሰዓት ቁጭ ብዬ ሲቀረፅ ያየሁት የ #10 ደቂቃ ትዕይንት አትሆንም ። ፊልሙ ድሬ ብቻ ሳይሆን ሀረርም እንደሚቀረፅ ነግረውኛል' አልኳት ። "መቼም የፊልሙ አክተር አንተ መሆን አለብህ" እያለች ትስቃለች ። 'በመጀመሪያ ደረጃ በዘመድ ነው famous የሆንከው እንዳትይኝ እንጂ ፤ የፊልሙ producer የዶርሜ ልጅ ጓደኛ በመሆኑ ነው እዛ የመሄድ እድል ያገኘሁት ። በመቀጠል ደግሞ እኔን የፈለጉኝ ፊልሙ እዚህ ሆቴል ውስጥ ሲቀረፅ በአክተሮቹ ጀርባ ከሆነች ልጅ ጋር ቁጭ ብዬ ሻይ እንድጠጣ ነው' ስላት ሳቋን በሀይል ለቀቀችውና አስተናጋጁ ሳንጠራው ደንግጦ መጣ ። ምሳ ሰዓት እስኪደርስ እስከዚያው ለስላሳ አምጣልን አልኩትና ተመልሶ ሄደ ። ማፌዟን አላቆመችም ። "እና ይሄን ሁሉ part ሸፍነህላቸው ስንት ብር ከፈሉክ ...?" አለችኝ ። 'እኔ ከጥበብ ገንዘብ አልቀበልም' ስላት "owk የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ስም መሆኑ ነው ጥበብ" አለችኝ ። ህይወት በመሆኗ ነው ዕድለኛ የሆነችው እንጂ ሌላ ሰው ፤ በተለይ ደግሞ ወንድ ቢሆን እንደዚህ የሚመልስልኝ እዚሁ ነበር ሰይፌው የምሄደው ። (ወንድ ልጅ አይኑር ያለው ማነው ...?😳) ። በኔ ላይ የመቀለድ ፣ የማሾፍና የማፌዝ መብት ያላት ብቸኛዋ ሴት እሷ ሆናለች ። እሷን የመቀየም ፣ የማኩረፍና በሷ ላይ የመናደድ አቅም የለኝም ። እራሷ ናት ያሳጣችኝ ። ስትስቅ ፣ ስትደሰት ፣ ሁሉን ነገር ረስታ ቀልቧን ሁሉ ስትጥልብኝ በህይወት በመኖሬ እደሰታለሁ ። ፈገግ ባለች ቁጥር የሷን ብቻ ሳይሆን የኔንም ዕድሜ በዕጥፍ ትጨምራለች ። በተለይ ደግሞ "የኔ ጌታ" እያለች ስታቆለጳጵሰኝ ሰማይና ምድሩን እኔው እራሴ በእጄ ጠፍጥፌ የሰራሁላት ነው የሚመስለኝ ። ስታዝን ፣ ስትጨነቅ ፣ ስታለቅስ ፣ ስታኮርፍ ፣ ህይወት ግልብጥብጥ ስትልባት ፣ በቃ ያኔ ነው በህይወት መኖሬን የምጠላው ። ከእሷ አይን የምትፈስ እያንዳንዷ የዕምባ ዘለላ ከእሳተ ገሞራ በላይ ውስጤን የማቃጠል ሀይል አላቸው ።

'ፊልም መስራት የልጅነት ህልሜ ነው ። ትዝ ይለኛል የ #1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለሁ ነበር የወሰወሰኝ ። ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ እያለሁና በትምህርት ቤትም ብዙ የመድረክ ድራማዎችን ሰርቼ ነበር ። አሁንም ድረስ የኔ የወደፊቱ ህልሜ በመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተመርቄ ስራ መስራት ይቅርታ ስራ ማፈላለግ አይደለም ። የፊልም አክተር መሆንና መሆን ብቻ ነው እቅዴ ። ከፊልም ውጪ plan B እራሱ የለኝም ። ፍላጎቴ ብሩና ዝናው አይደለም ። ፊልም መስራቱን ብቻ ነው የምፈልገው ። መንገድ ላይ የፊልም director ባገኝ እግሩ ላይ ወድቄ ከፈለክ በነፃ #10 ፊልም እሰራልሀለው ማለቴ አይቀርም' ስላት "እሺ የኛ shah rhuk Khan" አለችኝ ህይወት ትኩር ብላ ካዳመጠችኝ በዋላ ። በነገራችን ላይ የፊልም አፍቃሪ እንድሆን ያደረገኝ የህንዱ አክተር ሻህሩካን ነው ። የሱን ታሪክ በጣም ስለምወደው አጠር አርጌ ልንገርሽ አልኳትና ለትረካው ተሰናዳሁ ። "በልጅነቱ ጎበዝ ተማሪ ነበር ። ስፖርት በተለይ ደግሞ ኳስ መጫወት በጣም ይወዳል ። በልጅነቱ ትምህርት ቤት እያለ አንድ ቀን አስተማሪያቸው ወደ ፊት አወጣውና ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ ብሎ ጠየቀው ። እሱም አፉን ሞልቶ በኩራት የቦሊውድ ምርጥ አክተር እሆናለሁ አለው ። ክፍል ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች ሳቁበት ። አስተማሪውም የማይሆን ህልም እንደሆነና ሀሳቡን ቀይሮ ትምህርቱ ላይ ብቻ እንዲያተኩር ነገረው ። ለሻህሩክ ግን ይህ አልተዋጠለትም ። ህልሙን እውን ለማድረግ የ #2ኛ ዲግሪ ትምህርቱን አቋረጠና ወደ ፊልም ጉዞ ጀመረ ። ነገር ግን በዛ ሰዓት ሁለት ነገሮች ፈተና ሆኑበት ። የመጀመሪያው ወላጆቹን በሞት ማጣቱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ታላቅ እህቱ የአይምሮ ህመምተኛ መሆኗ ነበር ። በዛ ምክንያት ቤተሰቦቹን የማስተዳደር ሀላፊነት እሱ ላይ ወደቀ ። ከድህነት ጋር ትግል ገጠመ ። ስራ ለመፈለግ ወደ ሙምባይ ከተማ ሄደ ። የቤት ኪራይ የሚከፍለውን አጥቶ ከቤት ተባሮ ሁለት ቀን ጎዳና ያደረበት ቀን ነበር ። የሰዎች ሱቅ ስር ያደረበት ቀን ደግሞ ስፍር ቁጥር የላቸውም ። ሆኖም ግን በዚሁ ችግር ውስጥ ሆኖ ተዋናዮች የማይደፍሩትን ትወናዎች ይሞክር ነበር ። የሆነ ቀን ለመወዳደር ሄዶ የፊልሙ director "አንተ አርቲስት የምትሆን ሰው አይደለህም" አለው ። እሱ ግን ምንም ሳይመስለው ትቶት ሄደ ። ግን ተስፋ አልቆረጠም ፤ ወደዋላም አልተመለሰም ። ሁልጊዜ ወደ ህልሙ በሚወስደው መንገድ ላይ ይረማመድ ነበር ። ያለምንም ክፍያ ሲኒማ በር ላይ ቆሞ የመግቢያ ticket ይሸጥ ነበር ። በወረደ ሂሳብ እንደ ካሜራና መብራት ያሉ የፊልም መሳሪያዎችን ተሸክሞ ከአርቲስቶች ዋላ ይሄድ ነበር ። ነገር ግን አንድ ቀን መጣ ። የሱ ቀን ። የለውጥ ቀን ። ትንሽ ብር ተከፍሎት አንድ ፊልም (#Deewana) እንዲሰራ ተነገረው ። ከዛው ላይ ተነሳ ፣ ቀጠለበት ፣ ድህነትን ማሸነፍ ጀመረ ፣ እውቅና ትከተለው ጀመር ፣ ህልሙም እውን ይሆን ጀመር ። ለአርት አትሆንም የተባለው ሰው ምርጥ አክተር መሆን ጀመረ ። ዛሬ እንደ ህንድ ብቻ ሳይሆን እንደ አለም በጣም ታዋቂና ዝነኛ አክተር ነው ። በድህነት የሰዎች ቤት ስር ያድር የነበረው ዛሬ ላይ ከአለማችን ሀብታም አክተሮች መሀል አንዱ ነው ። ከብዙ ተቋማት ብዙ ሽልማት ያገኘ ፣ ከራሱም ተርፎ ለህዝቡ የደረሰ ጀግና ነው" ። እናም የኔ ህይወት ሰው ትሆኛለሽ ፣ አትሆኝም ስላለሽ አይደለም ። እሆናለሁ ካልሽ የማትሆኝው የለም ። ዋናው ለምንፈልገው ነገር እስከመጨረሻው ድረስ መስዋዕትነት መክፈል ነው ። ትግልሽን አሪፍ ካደረግሽ ብትወድቂ እራሱ አንድ ቀን ከላይ መሆንሽ አይቀርም ።

ይቀጥላል...
​​😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 33


ተነሳሁ አፌም ተከፈተ ። 'ለዚህ ሁሉ ነገር ሶስት አካላትን መውቀስ እፈልጋለሁ ። (ጥቅም ባይኖረውም ...😢) ። #1ኛው :- ያው ሁላችንም በስም ብቻ የምናውቀው መንግስት ተብዬው ነው ። ወንጀል በማንኛውም ሁኔታ ፣ ቦታና ፣ ጊዜ ፡ በሆነ ሰው/ቡድን ሊፈፀም ይችላል ። የመንግሥት ዋነኛ ስራው ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ፤ ካልሆነም ወንጀለኞቹን ይዞ ህግ ፊት ማቅረብ ነው ። ይህን ካላደረገ መንግስት የለም ማለት ነው ። እባክህ መንግስት ሆይ ፡ ከሰማኸኝ በጣም ናፍቀህኛል ፡ ላገኝህ እፈልጋለሁ ። ብቻህን ቢሆን ይመረጣል ስል ሁሉም ባንድነት አሽካኩ ። #2ኛው :- ከሁሉ ደግሞ የገረመኝ ነገር ፡ የሚዲያዎቹ ነው ። "በኮርያ በተቀሰቀሰው የተማሪዎች ግጭት የሁለት ተማሪ ህይወት አልፏል" EBC ። ስንቱ ምስኪን ሀገሩ ላይ እየሞተ እያለ ስለማያገባን ፈረንጅ ይተርክልናል ። ምናለበት እስኪ ብያንስ እንኳን ነፍስ ይማር ቢል ...?😢 ። ነው ወይስ ግዴታ ባለስልጣን ወይንም አርቲስት መሆን አለብን ...? ። ለስሙ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው ። እኔ ግን የመንግስት ቴሌቪዥን ብዬዋለሁ ። እስቲ እውነት የኛ ሚዲያ ከሆኑ "ተማሪዎች ላይ ስቃይ እየደረሰ ነው ፡ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል" ይበሉ ። #3ኛው :- ህዝብ ነው ። ምነው ይህ ህዝብ ለስንቱ እንዳልተሰለፈ ፡ ዛሬ ለተማሪ ሲሆን ዝም አለ ። ለዘይት ፣ ስኳር ፣ አብይ ፣ ኦነግ ፣ ግንቦት #7 ፣ ጃዋር ፣ እንደዛ በየ አደባባዩ እንዳላሽቃበጠ ፡ ምነው ዛሬ የራሱ ልጅ ባደባባይ ሲገደል ፀጥ አለ ...?😥 ። ብያውቁ ሁላቸሁም ተማሪ ሆነው አልፈዋል ። ተማሪዎች ሲገደሉ ፣ ሲሰደዱ ፣ ሲደበደቡ ፣ ሲሰደቡ እያዩ ባልሰማ ዝም ፤ በተቃራኒው ግን ለአንድ ለማይረባ ነገር ብለው #5 ሚሊዮን ሆነው አደባባዩን ይሞሉታል ። እስቲ የተማሪዎች ህመም ከተሰማቸው ለምን "እኔም ተማሪ ነኝ" ብለው አደባባይ አይወጡም ። ለማንኛውም ፡ በዚህ ዘመን ሰው አለኝ ማለት ከንቱ ነው ። መንግስትም ህዝብም ያጣ generation ...😔 ። እንደኔ የዚህ ክፉ ዘመን የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆናችሁ ተስፋችሁን እግዚአብሔር ብቻ አድርጉ ። "አሁንስ ተስፋዬ ማነው ፡ እግዚአብሔር አይደለምን ...?" አይደል ቅዱሱ መፅሐፍም የሚለው ። ይህን ስናገር ታዛቢ እንጂ ሰሚ እንደሌለኝ እያወኩኝ ነው ። ግን ብያንስ ስለተነፈስኩኝ ቀሎኛል ። እውነቱን ሸሽገህ የህሊና እስር ቤት ከምትገባ ፡ እውነቱን ተናግረህ የመንግስት እስር ቤት ብትገባ ይሻልሀል' ብዬ ስቀመጥ ሁሉም ተማሪዎች በጭብጨባ ክፍሉን አናወጡት ። እኔም 'አመሰግናለሁ ፣ ኧረ አይገባም አመሰግናለሁ' እያልኩ አሽቃበጥኩ ። ወዲያው ግን ግንባሬን የሆነ ነገር ቋ ሲያደርገኝ ደንግጬ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ ። ከዛን የ Fluid አስተማሪያችን "ምንድነው የምታመሰግነው ...?" አለኝ ኮስተር ብሎ ። ለካ ያን ሁሉ ስብሰባው ላይ ያወራሁት ክፍል ውስጥ ሆኜ ስቃዥና ሳንቀላፋ ነበር ። ውሃ በላኝ ።....

ከህይወት ጋር የልደቴ ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ከተያየን እንደ ቀልድ አምስት ቀናት ተቆጠሩ ። በጣም እንደናፈቀችኝ ያወኩት ክፍል ውስጥ ሴት መምህራችን ስታስተምረን መልኳ ወደ ህይወት ፊት ተቀይሮ ፈገግ ብዬ በፍቅር አይን ስመለከታት ተገርማ "ተስፋዬ ምን ፈገግ የሚያስብል ነገር ተገኘ ...?" ስትለኝ ነበር ። ጥቁር ሰሌዳው ላይ ፣ ደብተሬ ላይ ፣ ጠረጴዛ ላይ ፣ ግድግዳ ላይ ፣ በሄድኩበት ሁሉ የምትታየኝ እሷ ብቻ ሆናለች ። ከሷ ጋር ያሳላፍኳቸውን እያንዳንዷን ቅፅበት ሳስታውስ ነፍሴ በደስታ ትፈነድቃለች ። ለሊት ብቻዬን በዶርማችን በር በኩል ሽቅብ ከማያቸው እልፍ አእላፍ ከዋክብት ይልቅ በልቤ ውስጥ የምታንፀባርቀው እሷ ሆናለች ። ከሷ ጋር ሳሳልፍ የተሻሉ ቃላትን ተጠቅሜ ደስ ላላሰኛት እችላለሁ ። ነገር ግን በክንዶቼ መሃል አስገብቻት ፣ ደረቴ ላይ ተለጥፋ ፣ ጆሮዎቼ የሷን ድምፅ ብቻ ሲሰሙ ፣ አይኖቼም እሷኑ ብቻ እያዩ ፣ ከልቤ ሃሳቧን ፣ ጭንቀቷን ፣ ሀዘኗን ፣ ደስታዋን ፣ ሳቅና ሰቀቀንዋን ሁሉ ስካፈላት ከምን ጊዜውም በላይ ስለምትደሰት ፤ ደስታዋ ደስታዬ ሆኖ ከዋለ ካደረ ቀናቶች ተቆጥረዋል ። ከረገጠችው መሬት በላይ በኔ ላይ ዕምነት ኖሯት ሳያት ታስደምመኛለች ። እኔም ልክ እጆቿን ይዤ አይኖቿ

​​ን ስመለከት ብርሃን ይታየኛል ፤ ጉልበት ይኖረኛል ። እራሷ ደካማ ጎኔ ሆኗ እራሷ ታበረታኛለች ። በስልክ በየ ሰዓቱ እናወራለን ። አባቷ ያንኑ ዕለት እሁድ ምሽት ወደ ቤት እንደ ተመለሱና የዛሬ ሳምንት ማለትም ልክ እኔና እሷ በተዋወቅን በወሩ ግንቦት #30 ወደ አሜሪካ እንደ ሚበሩ ነግራኛለች ። ልክ ይሄንን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ብሎ ነበር ። ከአካላቶቼ መሃል አንዱ የተቆረጠ ያህል ህመም ተሰማኝ ። የመጨረሻ ውሳኔዬን ነገ እቤታቸው ሄጄ እንዳሳውቃቸው አባቷ ደውለው ነገሩኝ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ። ጉዞው ሁሉ ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። እኔን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የሷ አለመኖር ያማል ። የኔ አለም ለመሆን በተቃረበች ማግስት ከተለየችኝ ከአለም ጋር መጣላት ይሆንብኛል ። እሷን በፀሃይ ፋንታ እንደ ምትክ ሆና በተሰጠችኝ በመጨረሻዋ ሰዓት መሄጃዋ ሲደርስ ብርሃን ማጣት ይሆንብኛል ። ትታኝ መሄዷን ሳስብ ፀሃይ ፊቷን አዙራብኝ ፣ ጨለማ የዋጠኝ ያክል ተሰማኝ ። ጨለማ ውስጥ ወደኩኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ላይ ተጣልኩኝ ፣ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፣ በናፍቆት ውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑን እና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልምብኛል ። እኔ እሷን ካጣሁ እንኳን ቀኑን እራሴንም መርሳቴ አይቀርም ። የኔና የሷ ፍቅር ቀናት ስለተቆጠሩ አይደለም ። ፍቅር የጊዜ ማጠርና መርዘም አይደለም ። ፍቅር ማለት ፡ ያ በማንኛውም አጋጣሚ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ፣ በየትኛውም ቦታ ላይ ያሳለፍናት ያቺ ጊዜ ፣ ደቂቃም ትሁን ቅፅበት የማይረሳ ትዝታን ያሳለፍንባት ፣ በልቤ በልቧ የተነጋገርንባት ፣ በደስታ ሰክረን ያሳለፍናት ፣ አዎ እሷ ናት ። ልክ ፀሃይ አለምን ለማብራት እንደ ተፈጠረች ፣ ህይወትም ለመኖር ፣ ዝናቡም ሊዘንብ ፣ አበቦች ሊፈነዱ ፣ ሌሎችም ሌሎችም ለአላማቸው ልክ እንደተፈጠሩ ፣ የኔ መፈጠርም እሷን ለማፍቀር ቢሆንስ እያለ ልቤ ከራሴ ጋር ይሟገቱ ጀመር

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺
🔥ክፍል 32


"ግንቦት #17,1989 ዓ.ም ከለሊቱ #06 ሰዓት አካባቢ ። ሰማዩ ከሰይጣን በላይ ጠቁሯል ። (ቆይ ግን ሰይጣንን ማንም ሰው ካላየው ፡ መልኩ ጥቁር እንደሆነ በምን አወቅን ፣ ነው ወይስ የማይታይ ነገር ጥቁር ይመስለናል...?) ። ምድርም ያለ ፀሀይ ብርሃን የላትምና የሰማይ ተከታይ ሆናለች ። ከአንዲት እናት በስተቀር ሰፈሩ በሙሉ ፀጥ ረጭ ብሏል ። እናቲቱ ግን እያቃሰተችና እየጮኸች ትገኛለች ። እንዲህም ሆኖ ግን ማንም ሰው አልተረበሸም ። በተቃራኒው ሁሉም ሰው ተጨንቆ ወደላይ አንጋጦ ፀሎት እያደረገ ይገኛል ። በዚያች የጭንቅ ለሊት ሁሉንም ወደ ሳቅ ፣ ደስታና ዕልልታ የቀየረ አንድ ነገር ተፈጠረ ። በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ወንድ ልጅ ይቺን ምድር በሰላም ተቀላቀለ ። እናቲቱም የልጁን ስም ተስፋዬ ብላ ሰየመችው ። የወደፊት ተስፋዋን እሱ ላይ ጥላለችና" ። ይሄን ታሪክ የስልኬ Note ላይ ፅፌው ስለነበር ፣ ህይወት የልደቴን ቀን ከዛ ላይ አይታ እንዳወቀች ነግራኛለች ። በ #17 ለሊት ስለ ተወለድኩኝ ልደቴን በ #18 ነው የማከብረው ። እና ዛሬ ልደቴ ነው ፤ #22 ዓመት ሞልቶኛል ። (እና ምን ይጠበስ ...) ። ዛሬ እንኳን ጥብስ አይደለም የምፈልገው ። ልደትም አይደል ፣ ለፎቶው ድምቀት ድፎ ዳቦ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ፣ ለስላሳ ፣ ፊኛ ፣ ፈንዲሻ እና ግብዳው ሻማ ይሁንልኝ ። እንደውም #21 ዓመት ስላለፍኩኝ አንድ ሳጥን ቢራ ይዛችሁልኝ ኑ ። በነገራችን ላይ በዚህ ዓመት መምረጥ ብቻ አይደለም ፤ መመረጥም እችላለሁ ። እንደውም በቀጣዩ ምርጫ ላይ መሳተፍ እፈልጋለሁ ። በዚሁም እግረ መንገዴን የምርጫ ቅስቀሳ ባደርግ ውስጤ ነበር ። ግን በልደት ቀን ስለ ፖለቲካ አይወራም ። እዛው #MA ሆቴል ምሳ በልተን ፣ ህይወትን ቤቷ ድረስ ሸኘዋትና ጊቢ ውስጥ ስለ ወቅታዊው ችግር ስብሰባ እንዳለና መቅረት እንደሚያስቀጣ ተደውሎ ስለተነገረኝ ለዛው ብዬ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገብቻለሁ ። ስብሰባው #08 ሰዓት ተብሎ #10 ሰዓት ተጀመረ ። ስብሰባውን የተጠሩት ሁሉም የጊቢው ተማሪዎች ሲሆኑ ፤ የተገኙት ግን ስብሰባ የሚወዱ ተማሪዎች (አብዛኛው የ Law ተማሪዎች ናቸው...) ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ባለስልጣናት ፣ የጊቢው አመራር አካላትና የሰሙትን ወሬ ላልሰሙት የሚያወሩ ጋዜጠኞች ናቸው ። የስብሰባው አጀንዳ ፡ ሰሞኑን ጊቢ ውስጥ በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠል ነው ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ተጣሉ የተባሉትን ተማሪዎች ማስታረቅ ግድ ነው ። ስብሰባው ላይ ደግሞ የተጣሉት ተማሪዎች አልተገኙም ። ሆኖም ግን በስተመጨረሻ ያልተጣላነውን እኛኑን አስታርቀውን ለሁለት ሳምንታት የተቋረጠው ትምህርት ነገ እንዲጀምር ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ ። ምሽት ላይ ጓደኞቼ #ማራኪ club ይዘውኝ ሄደው አንድ ሁለት እያለን ቆንጆ ምሽት አሳልፈን ወደ ዶርም ገባን ። እንኳን ተወለድክልን ያላችሁኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ፈጣሪ ውለታ መላሽ ያድርገኝ ። ለዚህች ቀን ያደረሰኝ ፈጣሪ ነውና ከሁሉ በላይና በፊት ምስጋናውን እርሱ ይውሰድ ። ጠዋት ነግቶ ቁርስ ሳንበላ ለ #16 ቀን ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ተጀመረ ። የልደቴ ቀን ግን ለጊቢው እንደዚህ በረከትን ይዞ ይመጣል ብዬ አላሰብኩም ነበር ። በጊቢው ሰላም መሆን ደስ ቢለኝም ትምህርት በመጀመሩ ግን ከፍቶኛል ። አስቡት እስኪ ፡ #2 ሳምንት ሙሉ ስለ ትምህርት ሳናስብ አሳልፈን በአንዴ ወደ ትምህርት ግቡ ሲባል ትንሽ አይከብድም...? እኔ በበኩሌ ለትምህርት የምንዘጋጅበትን ሌላ ሁለት የዕረፍት ሳምንት ቢሰጠን ባይ ነኝ ።በበላይ አካላትና የሀይማኖት አባቶች በየክፍሉ አስቸኳይ ስብሰባ ተደረገና ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ ወደ ፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ እንድንነጋገር ተደረገ ። እንደ ዕድል ሆኖ እኛ ክፍል የደረሰው የጊቢው president ናቸው ። ስሜን ማን እንደነገሯቸው አላውቅም ፤ "ተስፋዬ እስቲ ኢትዮጵያዊነት ላንተ ምንድነው...?" አሉኝ ከዛ ሁሉ ተማሪዎች እኔን መርጠውኝ ። መጀመሪያ ስሜን ሲጠሩ ደንግጬ ነበር ። ከተነሳሁ በዋላ ግን የኢትዮጵያ አምላክ እረድቶኝ ሰይጣን ይዞት ፀበል እንደ ገባ ሰው መለፍለፍ ጀመርኩኝ ። 'እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም' ብዬ ንግግሬን ስጀምር ሁሉም አፈጠጡብኝ ። 'አይገርማችሁም ፡ እናንተም ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ። በልባችሁ ፡ "አሜሪካዊ ናችሁ በለን" እንደ ምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ። ሁልሽም ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተወለድሽ ብቻ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ተሳስተሻል ። ትንሽ እንኳን አናፍርም ...? ፡ ለዚች ክብርት ሀገር ብለው የሞቱ ስንቱ ደግና አንበሳ አባት ፡ ስንቷ ሩህሩና ጀግና እናት በተጠሩባት ፤ እኛ በዘር በሀይማኖት እየተባላን ፡ ከነሱ እኩል ኢትዮጵያዊ ተብለን ስንጠራ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጠንም ...? ፡ እኔ በበኩሌ ስማቸውን ጠርቼ ከማልጨርስና ከማልጠግብ የሀገራችን ባለውለታዎች እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ መጠራት አልፈልግም ። እስቲ ለዚች ሀገር ሲሉ የሞቱትን ጀግኖች እናስባቸው ። አፄ ቴዎድሮስና በላይ ዘለቀ የሞቱት ለአማራ ክልል ነው ...? ፡ ጀነራል ታደሳ ብሩና ገረሱ ዱኪ የሞቱት ለኦሮሚያ ክልል ይመስላችኋል ...? ፡ አቡነ ጴጥሮስስ የሞቱት ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው ...? ፡ ነው ወይስ አሚር የሞተው ለእስልምና ይመስላችኋል ...? ። እንደዛ ካሰብባችሁ ተሳስታችኋል ። እነሱ በጊዜያቸው ክልል የሚል ድንበር አልነበራቸውም ። በሀይማኖት መከፋፈል ሀሳቡም አልፈጠረባቸውም ። እነሱና እነሱን የመሰሉ ስንቶቹ ለዚች ክብርት ሀገር ኢትዮጵያ ብለው እንጂ ለዘራቸው አልነበረም ጥብቅናቸው ። ምን ነካን ጎበዝ ...? ፡ ጠላት ከውጪ ሲመጣብን አንድላይ ሆነን እንዳልመከትን ፡ ዛሬ ላይ እርስ በእርስ መጫረስ ምን የሚሉት ጉድ ነው ...! አሁንም ሳስበው ጥላቻው የኛ አይመስለኝም ። እናም ወገኖቼ ፡ የኛን አንድነት የማይፈልጉትን አንድ ላይ ሆነን በፍቅር እንመክታቸው ። ጥፋታችንን የሚፈልጉትን ተቃቅፈን እናሳፍራቸው ። እንደ ክልልና ሀይማኖት ሳይሆን ፡ እንደ ሰው አስበን ኢትዮጵያን ከጥፋት እናድናት ። ያኔ እኔም እናንተም ልክ እንደ ቀደምቶቻችን ኢትዮጵያዊ ተብለን እንጠራለን ። ክልል ሳይሆን ሀገር ስላስረከብናቸው ልጆቻችንም ይኮሩብናል' ብዬ ቁጭ አልኩኝ ። እናንተ ፡ እህህህ የሚለኝ አጣሁ እንጂ እተነትነው የለ እንዴ ...? ። ሁሉም ተራ በተራ የሚሰማቸውን ከተናገሩ በዋላ ፕሬዚዳንቱ "እስቲ ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ምንድነው ትላለህ ወጣት ተስፋዬ" አሉኝ በድጋሜ ።ይቀጥላል......


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺
🔥ክፍል 34

.
የጠዋቱን ክፍለ ጊዜ እስከ #5 ሰዓት ተማርኩኝና በግብዣዬ መሠረት ምሳ ሰዓት ላይ ወደነ ህይወት ቤት ሄድኩኝ ። አባትና ልጅ ደስ በሚል ፈገግታ እሷ ከውጪ ከአጥሩ በር ፣ አባቷ ደግሞ ከቤቱ መግቢያ በር ላይ ተቀበሉኝ ። አባቷ በኔና በእሳቸው መካከል ስለነበረው ግኑኝነት በሙሉ ስለነገሯት ከህይወት ጋር ምንም አይነት ድብብቆሽ መጫወት አይጠበቅብንም ። ምሳ እኔም ስላልበላሁ ፣ እነሱም እየጠበቁኝ ስለነበር የምግብ ጠረጴዛውን ከበን የቀረቡትን የምግብ አይነቶች መርጠን አነሳንና ለመብላት ተዘጋጀን ። አባትና ልጅ ምግቡን ባርከው ተጎራርሰው መብላቱን ቀጠሉ ። እኔ ደግሞ ስርዓቴን ጠብቄ ብቻዬን እየበላሁ ነው ። ማን ያውቃል ምናልባት የወደፊት አማቼም ሊሆኑ ስለሚችሉ በወግ ልማዳችን መሠረት ሰብሰብ ብዬአለሁ ። ምግቡም አለቀና ፣ ጨዋታ ጀመርን ። ስለ ትምህርት ፣ ቤተሰቦቼ ፣ ወቅታዊ ጉዳይ ፣ ምን ያላወራነው ነገር አለ...! በስተ መጨረሻ ህይወት "መጣሁ ተጫወቱ" ብላ ተነስታ ወደ ኩሽና አመራች ። አባቷም ከዚህ በፊት በደምብ አስብበት ብለው የጠየቁኝን ጥያቄ አስታውሰውኝ መልስ መጠበቅ ጀመሩ ። ማታ በዚሁ ጉዳይ እንቅልፍ አልተኛሁም ነበር ። ሳወጣ ሳወርድ ፣ በሀሳብ ስሄድ ስመለስ ነው ያነጋሁት ። በብዙ አቅጣጫ ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ወደ ውስጥም አስቤ ልቤን በደንብ ለማዳመጥ ሞክሬ ነበር ። ጭንቅላቴ ውስጥ 'ሂድ ፡ ቅር ፣ ሂድ ፡ ቅር' የሚል ድምፅ ከጩኸት በላይ እየተሰማኝ እንዲሁ ፍዝዝ ብዬ ነው ያደርኩት ። ስለ ማራኪዬ በደምብ አሰብኩኝ ። ስልኬን ካላነሳች ፣ txt ካልመለሰች ፣ በጓደኞቿ በኩል ላገኛት ስሞክር ካልተሳካልኝ ፣ ታድያ በሷ ላይ የቀረኝ ተስፋ ምንድነው ...? ብዬ በጣም ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ከማንምና ከምንም በላይና በፊት አሰቀድማ እኔን ነው የምታምነው ያልኳት ልጅ ፤ እምነቱ ቀርቶብኝ ስልኬን እንኳን ለአንድ ደቂቃ የማንሳት አቅም አጣች ። ሁለታችንም ቃል ነበረን ። በማንምና በምንም አይፈርስም ብለን የተሳሰርንበት ቃል ። በመሃላችን ስለሚፈጠረው ማንኛውም ነገር ፣ ከሰዎች ምንም ይምጣ ምንም ፣ ከሁለታችን አፍ ሳንሰማ ላንከዳዳ ቃል ተግባብተን ነበር ። አሁን ግን ሁለታችንም ስለተፈጠረው ነገር ምንም ሳንባባል ፣ ለመባባልም ጊዜ አጥተን ተለያይተናል ። በሷ ተስፋ ለመቁረጥ ጫፍ ላይ ደረስኩኝ ፤ ግን አልቆረጥኩም ። "ልጅ ተስፋዬ" አሉኝ የህይወት አባት ። ከእንቅልፍ እንደሚባንን ሰው ከሀሳቤ ነቃሁ ። "ምነው ጥለኸኝ ጠፋህ እኮ" አሉኝ አስከትለው ። እኔም ፈራ ተባ እያልኩ 'አያይ እዚሁ ነኝ ፤ የትም አልሄድኩም' አልኳቸውና ለጥያቄያቸው መልስ ልሰጥ ስል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ። ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ ከፈትኩት ። የማላውቀው ቁጥር ነው ። "ማራኪዬ እንዴት ነህ ...? ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ ። እየውልህ ፡ በሰዓቱ ባንተ በጣም ተናድጄ ስለነበር ስልክህን ላለማንሳትና መልዕክትህን ላለመመለስ ለራሴ ቃል ገባሁ ። ጠልተህኛል ብዬ ጠላሁክ ። እንደውም ከጊዜ በዋላ ያንተን መልዕክት ላለማየት ብዬ ስልክ ቀየርኩኝ ። ለዛም ነው አሁን በአዲሱ ስልክ ቁጥሬ የማወራህ ። አንተ ምናልባት ረስታኛለች ብለህ ታስብ ይሆናል ። ማራኪዬ ፡ ስላንተ ላለማሰብና ላለማውራት ለራሴ ቃል ገብቼ ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ስላንተ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም" ይላል መልዕክቱ ።በስንት መከራና ጭንቀት በስተመጨረሻ ፡ ለአባቷና ለህይወት ልክ እሺታዬን ላበስር ስል ረስታኛለችና ልርሳት ፣ ትታኛለችና ልተዋት ያልኳት ማራኪዬ "ልረሳህ አልቻልኩም" የሚል መልዕክት ልካልኝ ለእሺታ የተዘጋጀውን አፌን ቆለፈችው ። በድንገት 'መሄድ አለብኝ' ስላቸው ተደናግጠው "ምነው የተፈጠረ ችግር አለ እንዴ ...?" አሉኝ የህይወት አባት ። 'አያይ ምንም ችግር የለም' ብዬአቸው ተነሳሁ ። በሁኔታዬ ግራ ቢጋቡም በዝምታ ሸኝተውኝ ባሉበት ፍዝዝ ብለው እያዩኝ ከቤታቸው ከህይወት ጋር ወጣሁ ። "ምን ሆነሃል የኔ ጌታ...?" አለችኝ ህይወትም ። ስልኬን ሰጠዋትና መልዕክቱን አስነበብኳት ። አንብባ ስትጨርስ "እና ለዚህ ነው እንደዛ ባንዴ ተደናግጠህ የተነሳኸው ...?" ስትለኝ ፤ 'ታድያ በዚህ ሰዓት ከዚህ በላይ የሚያስደነግጥ ምን አለ ...?' አልኳት ። "ደስ ብሎሃል አይደል ...?" አለችኝ ቀጥላ ። እኔ ግን ያለሁበትን ሁኔታ እንዴት እንደ ምገልፀው ግራ ገብቶኛል ። መደሰት ይኑርብኝ መከፋት ፣ ማልቀስ ይኑርብኝ መሳቅ ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን አላውቅም ። ግን አንድ ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ እየተመላለሰ ይገኛል ። 'መሄድ የለብህም ፡ ለማራኪክ የገባኸውን ቃል አስታውስ ፣ ከዚህ በፊት አንቺ የልጆቼ እናት ነሽ ያልካትን አስታውሰህ ወደሷ ተመለስ ፣ መጀመሪያም ዝምታዋ ነበር እንድትሄድ ያስወሰነህ ፡ ይኸው አሁን ከአንደበቷ ሰምተሃል ፡ ስለዚህ ከህይወት ጋር ወደ ውጪ መሄድ የለብህም' ይለኛል ። ይሄን ውሳኔ ተቀብዬ ለህይወት ማሳወቅ ደግሞ ለኔ ከሞት በላይ ያስፈራኛል ። ዝም ብላ ካየችኝ በዋላ "ከኔጋር መሄድ አትፈልግም አይደል ...?" አለችኝ ። አይኖቿን እያየሁ መመለስ ስለከበደኝ 'አላውቅም ህይወት ፣ አላውቅም' አልኳት አንገቴን ደፍቼ ። "ስሜትህ ይገባኛል ። ማራኪክ አንተጋ ምን ያክል ቦታ እንዳላት መገመት አይከብደኝም ። ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፈሯን የሳምካት ልጅ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልም ላይ የምታውቀውን የፍቅር ህይወት በእውን ያሳየችህ ሴት ፣ በፍቅርም ለሁለት ዓመታት ርቀት ሳይበግራችሁ በስልክ ብቻ እያወራችሁ ያልተለያያችሁ ጥንዶች ፣ በስልክም ከአምስት ሺህ በላይ መልዕክት የተፃፃፋችሁ ፣ በየ ሳምንቱም ተደዋውላችሁ የምታወሩ ፣ በመሃላችሁ በተፈጠረው አለመነጋገር ምክንያት ብቻ ለወራት ሳታወሩ ብትቀሩም በስተመጨረሻ ግን ረስታኛለች ብለክ የደመደምከው ነገር በተቃራኒው ከልብህ ከማንም በላይ የምትወዳት ፍቅርህ "ልረሳህ አልቻልኩም" ስትልክ ምን እንደ ሚሰማክ አውቃለሁ ። አንተ ለሷ ያለህ ስሜት ፡ እኔ ላንተ ያለኝ ስሜት ስለሆነ በደንብ ይገባኛል ። ሲጀምርም አባቴ ከኛ ጋር ሂድ ማለት አልነበረበትም ። እኔኮ በጣም ደህና ነኝ ። አንተን ባጣ እራሴን የማጠፋ መስሏችሁ ነው ...? በፍፁም እንደዛ አላደርግም" ። አለችኝና እስኪጨንቀኝ ድረስ ጥብቅ አርጋ አቅፋኝ ፣ ጉንጬንም ስማኝ በቆምኩበት ትታኝ ወደ በሩ ሄደች ። በሩ ጋር ስትደርስ ዞር ብላ አየችኝ ። ፊቷ በእንባ ተሸፍኗል ። ልቤን ስትበላኝ ወደሷ ሄጄ ላቅፋት ስል ወደ ውስጥ ገብታ በሩን ዘጋችው ። እኔም ሰፈራቸውን ለቅቄ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሁ ። መልዕክቱ በተላከልኝ ስልክ ላይ ደወልኩኝ ። ነገር ግን ቴሌ "አሁን ማግኘት አይችሉም" አለችኝ ። እስከ ምተኛበት ሰዓት ድረስ ደጋግሜ ብደውልም ሊሰራልኝ አልቻለም ። ምን እየተካሄደ ነው ...? መልዕክት ልኮ ስልክ ማጥፋት ምን የሚሉት ጉዳይ ነው ...

ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​🌺የከንቲባው ልጅ 🌺

🔥ክፍል 35
.
ጠዋት እንደተለመደው ወደ ክፍል ሄጄ እስከ ምሳ ሰዓት ተምረን ፣ ቶኒ ምሳ በልተን ወደ ዶርም ገባሁ ። Telegram መጠቀም በጣም ስለምወድ ስልኬን አወጣሁና ገባሁ ። ትናንት በተላከልኝ ፣ መልሼ ስደውል እምቢ ባለኝ ስልክ ቁጥር አዲስ መልዕክት ተላከልኝ ። "እንዴት ነህ የኔ ጌታ ፡ በመጀመሪያ የሚያናድድህ ነገር አድርጌ ከሆነ በጣም ይቅርታ ። ትናንት ያንን መልዕክት እኔ ነኝ አዲስ ሲም ካርድ አውጥቼ የኩልህህ ። ሁለት ልብ ሆነህ ሳይክ በመሀል ተጨነኩና እንዲቆርጥልህ ብዬ እንደዛ አደረኩ ። ስለ ፍቅር ካንተ አንድ የተማርኩት ትልቅ ነገር ቢኖር 'እራስ ወዳድ መሆን የለብንም' የሚለው ነው ። እኔም እራስ ወዳድ መሆን አልፈለኩም ። ከኔ ይልቅ ለማራኪክ የበለጠ ስሜት እንዳለህ በትንሹም ቢሆን አውቅ ነበር ። ትናንት ግን ሙሉ በሙሉ አረጋገጥኩኝ ። መልዕክቱንም እኛው ቤት እያለህ ልልክልህ የፈለኩት ፊትህ ላይ ምን አይነት ስሜት እንደሚፈጠር ለማየት ነበር ፤ ደግሞም አየሁት ። አውቃለሁ ምናልባት አንተ ትናንት ስትመጣ ከናንተጋር እሄዳለሁ ልትለን ይሆናል ። እንደዛ የምታደርገው ደግሞ የማራኪክ ፍቅር ሳይወጣልህ ፣ ለኔ ስትል ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው ። ይሄ ደግሞ የኔን ራስ ወዳድነት አጉልቶ ያሳያል ። አንተ በህይወቴ ከመጣህ ጀምሮ እንደ አዲስ መኖር ጀመርኩኝ ፣ ብዙ ነገር አደረክልኝ ። አንተ ያደረክልኝ ነገር ላንተ ምንም መስሎ ሊታይህ ይችላል ። ለኔ ግን ብዙ ነገር ነው ። ብቻዬን ነበርኩኝ ፤ ያውም እስር ቤት ውስጥ ። አንተ ግን መተህ ፈታኸኝ ። ፈተኸኝም ዝም አላልከኝም ፤ አለሜን አሳየኸኝ ። በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ዓመታት ተዘግቶብኝ በፊልም ፣ በመፅሐፍ እና በሙዚቃ የማውቀውን አለም እጄን ይዘህ አሳየኸኝ ። በልቦለድ ላይ የምመኘውን ገፀባህሪ አለበስከኝ ። እናቴ ሰጥታኝ ሰዎች የነጠቁኝን ህይወት መልሰህ ሰጠኸኝ ። ታውቃለህ ፡ ካንተ ጋር ያሳለፍኳት እያንዳንዷ ቅፅበት አሁንም ድረስ ፊቴ ላይ እየተመላለሱ እንደ አዲስ ነፍሴን ወደ ሰማይ ይልኳታል ። ልለይህ መቼም አልፈልግም ነበር ። ይህ ግን ሊሆን አይችልም ። ከዚህ በዋላ እንደ በፊቱ ልጫንህ አልፈልግም ። እኔ ያንተ ብሆንም ፤ አንተ ግን የኔ አይደለህም ። በግድ ደግሞ የኔ ላደርግህ አልሻም ። ምናልባት የፈጣሪ ስራ አይታወቅምና ወደፊት አንድ ቀን አንተን ለኔ ካለ ተመልሰን ልንገናኝ እንችላለን ። ይህ ደግሞ የኔ የወደፊቱ ብቸኛው ምኞቴ ነው ። አሁን ስለኔ ይቅርና ካንተ አንድ የምፈልገው ነገር አለ ። ማራኪህን በጣም ትወዳታለህ ። እሷን እንደ ቀድሞህ ለመመለስ ደግሞ የሚቻልህን ማድረግ አለብህ ። ለፍቅር የሚከፈለውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ከፍለህ የራስህ እንድታደርጋት እፈልጋለሁ ። ይሄን ካደረክ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው ። ከዚህ ውጪ ግን ከሶስት ዓመት በዋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ እመጣለሁ ። ያኔ ግን ብቻህን ሆነህ ካገኘሁክ የእናቴን ቀን ይስጠኝ አለቅህም ። ድል ባለ ሰርግ አግብቼህ የራሴ አደርግሃለሁ ። እስከዚያው ግን ፈጣሪ መላዕክቶቹን ልኮ ይጠብቅህ ። መልሼ እስካገኝህ በጣም ትናፍቀኛለህ የኔ ጌታ" ይላል መልዕክቱ ። ባለሁበት ደንዝዤ ቀረሁ ። እንደምንም ወደ ራሴ ተመለስኩና ፡ ከዶርም ወጥጬ ወደነ ህይወት ቤት በረርኩኝ ። ቤታቸው በር ላይ ስደርስ ግን ...ያጋጠመኝ ፡ ህይወትን ለማግኘት ተስፋ አስቆራጭ የሆነ ነገር ነው ። ቤታቸው ላይ በትልቁ በፖስተር ተደርጎና በር ላይ ደግሞ ወረቀት ላይ ማስታወቂያ ተፅፎ ተለጥፏል ። "for sell ፡ የሚሸጥ ፣ kan gurguramu" የሚል በሶስት ቋንቋ የተፃፈ ነው ። ከስር ደግሞ ስልክ ቁጥር ተፅፎበታል ። ይሄ ማለት እነ ህይወት ቤቱን ለቀው ወጥተዋል ማለት ነው ። ምናልባት ካሉ ብዬ በሩን በደንብ አንኳኳሁ ፤ ግን ሰሚ የለም ። የህይወት ስልክ ላይ ደወልኩ ፤ ጭራሽኑ አይሰራም ። ተስፋ በቆረጠ አንጀቴ ወደ መጣሁበት ልመለስ አንድ እርምጃ ሳነሳ ከበራቸው ስር የሆነ ፖስታ አየሁኝና ዝቅ ብዬ አነሳሁት ። ገና ስከፍተው የህይወት እንደሆነ በእጅ ፅሁፏ አወኩኝ ። "እዚህ እንደምትመጣ ስላወኩኝ ነው ይሄን ደብዳቤ የፃፍኩልህ ። አየህ አንተ አሁንም ድረስ ሁለት ልብ እንደሆንክ ነው ያለኸው ። ትናንት እንደ ማራኪክ ሆኜ መልዕክት ስልክልህ ወዲያውኑ ፊትህ ተቀያይሮ አባቴ ጋር ጥለኸኝ ሄድክ ። አሁን ደግሞ መልዕክቱ የተላከልህ ከማራኪክ እንዳልሆነ ስትረዳ ወደኔ ሮጠህ መጣህ ። እየወቀስኩህ አይደለም ። እራስህን በደንብ እንድታዳምጥ ስለፈለኩኝ ነው ። አንተ በሁለት ሰዎች መካከል ቆመህ ልብህ እንደ pendulum ወደዛ ወደዚህ እያለብህ ነው ። ይሄ ደግሞ ላንተም ጥሩ አይደለም ። መወሰን አለብህ ፣ መቁረጥ አለብህ ፤ ለዛ ደግሞ ጊዜው አሁን ነው ። ማንንም ጣልቃ ሳታስገባ ከራስህ ጋር የራስህ የሆነ ንግግር አድርግ ። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን አንድ መቶ አንድ ጊዜ አስብ ። ሁሉንም መርምር ፤ የሚበጀውን ደግሞ ምረጥ ። ያኔ ያንተ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰው ልብ ያርፋል ። በዚች ምድር ላይ ከአስከፊ በሽታዎች ሁሉ የላቀ ህመም ፤ ቁርጡን ሳያውቁ ዝም ብሎ በተስፋ መቀመጥ ነው ። አገኘው ይሁን ፡ አጣው ይሁን ...? ፣ የኔ ይሁን ወይስ የሌላ እያሉ ቀን ከለሊት ያለ እረፍት ማሰብና መጨነቅ የህመሞች ሁሉ አስከፊው ህመም ነው ። እኔ ደግሞ የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆን አልፈልግም ። ወይ አንተን ብቻ ማሰብ ወይም ደግሞ አንተን እስከነ መፈጠርህ መርሳት ይኖርብኛል ። ይሄን ደግሞ ለማድረግ ያንተ እርዳታ ያስፈልገኛል ። አንተ በኔ ላይ ያለህ ተስፋና ለኔ ያለህ ፍቅር ለውሳኔዬ ይረዳኛል ። ለዚሁ መልስ ደግሞ ከመሄዴ በፊት አንድ ዕድል እሰጥህና ለመጨረሻ ጊዜ እንድንገናኝ አደርጋለሁ ። የማገኝህ ያንተን የመጨረሻ ውሳኔ ለማወቅ ብቻ ነው ። ያንቺ ነኝ ወይም ያንቺ አይደለሁም የሚለውን እንድታሳውቀኝ ብቻ ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ ግዴታ ቃል ማውጣት አይጠበቅብህም ። ሰኞ #08:00 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ። በቦታው ላይ በሰዓቱ ከተገኘህ ከኔጋር ለመሆን ፍቃደኛ እንደሆንክ እቆጥረዋለሁ ። ከኔጋር ለመሆን ካልፈለክ ግን ወደ ቦታው መምጣት እራሱ አይጠበቅብህም ። ለብዙ ደቂቃ የምጠብቅህ እንዳይመስልህ ። ባልኩህበት ቦታና ጊዜ በተስፋ እጠብቅሃለው ። እስከዚያው ግን በአካልም ሆነ በስልክ መገናኘት የለብንም ። ከሁሉም ነገር ተገልለህና ብቻህን ሆነህ በንፁህ ህሊናና ልብ በደንብ አስበህበት ላንተም የሚበጀውን ውሳኔ ትወስናለህ ብዬ አስባለሁ ። ስለሁኔታው አባዬ ምንም አያውቅም ። ይሄንን የማደርገው ከሱ ተደብቄ ነው ። ስላንተ ሁሉንም ነገር ነግሬው በጣም ተናዷል ። ፍቅረኛ እንዳለህ ሲሰማ ፊቱ እንዴት እንደተለዋወጠ ብታየው አታውቀውም ። ካሁን በዋላ እንዳገኝህ እንደማይፈልግም ነግሮኛል ። እንደ ምንገናኝ ካወቀ ምን እንደሚያደርግ አላውቅም ። ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ ። እስከዚያው ግን ... ። #ህይወት"

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺
🔥ክፍል 36

.
ስልክ ቁጥሩ ከጠቀመኝ ብዬ ቤታቸው ላይ የተለጠፈውን ማስታወቂያ በስልኬ ፎቶ አነሳሁትና ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመለስኩኝ ። #10 ሰዓት ላይ class ነበረኝና በፍጥነት ቁና ቁና እየተነፈስኩ ክፍላችን ደረስኩኝ ። #20 ደቂቃ አርፍጃለው ። ሆኖም ግን አስተማሪው ተንበርከክ ሳይለኝ አስገባኝ ። የ machine element መምህራችን ህንዳዊ ዜጋ ነው ። ያው የሱ ትምህርት ትርጉም በስለሺ እስኪመጣልን ድረስ ምንም እየገባን አይደለም ። ድንጋዩ ማነው እንዳትሉኝ እንጂ ድንጋይ ላይ ውሃ እያፈሰሰ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ሰውዬው ከሚያወራቸው ነገሮች አንዲት እንኳን አትሰማም ። ከሱ እንግሊዝኛ ይልቅ የ shah rhuk khan ህንደኛ በስንት ጣዕሙ ። ደግሞ መቸክቸክ አይደክመውም ። አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ጊዜ black board እያጠፋ እየፃፈ ፡ እኛንም ያለ ሞያችን ደራሲ አርጎናል ። እኔ ለሰባቱም ትምህርቶች ትበቃለች ብዬ የገዛዋትን አንዷን ባለ #50 ወረቀት ደብተር እሱ በአንደኛው ቀኑ ነበር ብቻውን መሃል ላይ ያደረሳት ። anyways ግን ከህንድ የሚመጡት አስተማሪዎች ይሄን ሁሉ km አቋርጠው የሚመጡበት ምክንያት አይገባኝም ። ሀገር ውስጥ አስተማሪ ጠፍቶ ነው እንዳንል ስንቱ ተመርቆ ስራ ጠፍቶ እቤት ውስጥ ተጎልቷል ። የማስተማር ብቃት ፈልገውም ከሆነ የኛዎቹን የሚበልጡበት አንድም የተለየ ብቃታቸው አይታየኝም ። እንግሊዝኛቸው ግራ የሆነ ። ከኛ ጋር መማር ማስተማሩ ላይ በቋንቋ ካልተግባባን ምኑን ተማርን ። በቋንቋም ብንግባባ ደግሞ የትምህርት አሰጣታቸው የህፃን ጨዋታ ነው ። ሰሌዳው ላይ የሀገር Note ይፅፉና እሱኑ መልሰው ያነቡልናል ። አለቀ ፡ ደቀቀ ። እኛ ማንበብ ከብዶን ነው እንዴ የመጣነው ...? እንዳልኩትም ራጅ ኩማር ሰሌዳው ላይ የቸከቸከውን አንብቦልን መጨረሻ ላይ quiz ፈተነን ። ከፈለጋችሁ ከደብተር ላይ ስሩ ሲለን እኔ ደግሞ የትልቅ ሰው ምክር አይናቅም ብዬ እሱ እንዳለን ከደብተር ላይ copy paste አደረኩት ። ድፍን ምስር ሳልበላ የደፈንኩት የመጀመሪያው ፈተና ሆኖም በ UNESCO ላይ ተመዝግቦልኛል ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ከ class መልስ ወደ ዶርም ገባሁ ። እንዲህ ደክሞኝ እያለም ግን የያዘኝ ሱስ ሊያስተኛኝ አልቻለም ። high school እያለሁ በጣም ሱሰኛ ነበርኩኝ ። ቤተሰብ እንኳን እስኪማረርብኝ ድረስ የጦፈ ሱስ ውስጥ ገብቼ ነበር ። የተያዝኩት #9ነኛ ክፍል እያለሁ ነው ። ያለሱ አይሆንልኝምና ቤተሰቦቼ በጣም ስለሚያዝኑብኝ ከነሱ ተደብቄ እጠቀም ነበር ። ለሱሴ የሚሆን ገንዘብ አላጣም ። ያለኝን ብር በሙሉ እሱላይ ነበር የማጠፋው ። እንደምንም እየቆጠብኩም ቢሆን ከወር ወር ያደርሰኛል ። campus ስገባ ደግሞ እሱኛውን ሱስ ትቼ ሌላ ሱስ ውስጥ ወደኩኝ ። ይሄ ደግሞ ጭራሽ ከድሮው ሱሴ የባሰ ሆነብኝ ። ስራዬ ሁሉ እሱ ብቻ ነው ። ማጥናት ፣ መማር ፣ ምናምን የለም ። ሙሉ ሰዓቴን እሱ ላይ ነው የማሳልፈው ። ዛሬ ግን ለመተው አስቤአለሁ ። ከቻልኩ እስከነጭራሹ ላለመጠቀም ፤ ካልሆነም በየቀኑ ላለመጠቀም ወስኛለሁ ። ብዙ መጎዳትን እንጂ ጥቅምን አላገኘሁበትም ። ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ገንዘቤን ለ tele መገበር ብቻ ነው ። #9ነኛ ክፍል እያለሁ የጀመረኝ የ facebook ሱሴ ካምፓስ ስገባ ወደ telegram ተቀይሮ ይሄው አይኔ እስኪጠፋ ድረስ ስበላ ፣ ስጠጣ ፣ ስማር ፣ ስሄድ ፣ ስቀመጥ ፣ ስተኛ ፣ ብቻ ምን አለፋችሁ #24 ሰዓት ከስልኬ ጋር እንደተቃቀፍኩ ነው የምውለው ።የሰው ልጅ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ፈጥሯል ። ለኔ ግን እስካሁን ድረስ ወደር ያልተገኘለት ፣ የትኛውም ፈጠራ የማይተካከለው ነገር ቢኖር #መተኛት ነው ። እዚጋ አንድ ጊዜ ተረጋጉና ሌላ አለም ውስጥ ሳትገቡ በፊት ነገሩን ላስረዳችሁ ። "መተኛት" የሚለው ቃል ተኛ ፣ ደቀሰ ፣ ወገቡን ፈተሸ ፣ አንሶላ ውስጥ ገባ ፣ አሸለበ እና ከመሳሰሉት የግሪክ ግሶች የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም ያው ግሪኮች ከላይ ያሉት ነው ። መተኛት በሶስት ይከፈላል ። አንደኛው ፦ የህዝብና ቤት ቁጠራን ለማባዛት የሚተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ባልና ሚስት ። ሁለተኛው ፦ ፈጣሪ የማይወደው ፡ እኛ ሰዎች ግን ደስ ብሎን የምንተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ከጋብቻ በፊት ወንድና ሴት የሚተኙት ። ሶስተኛው እና ወሳኙ መተኛት ደግሞ ብቻህን በር ዘግተህ ለጥ የምትለው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ተስፋዬ የሚተኛው ። እና ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስተኛ ነው የዋልኩት ። እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ አልጋ ሂዱ ፤ እሱም ያሳርፋችዋል የተባለ ይመስል ለምሳና ለእራት ብቻ ነበር ከአልጋዬ ላይ የወረድኩት ። አልጋም ላይ ብውልም ግን ምንም አልተኛሁም ። ማሰብ ፣ ማሰብ ፣ እንደገና ማሰብ ። ብዙ ካሰብኩኝ በዋላ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ በራሴ አፈርኩኝ ። ፍቅር እውር ያደርጋል የሚሉት ተረት በኔ ላይ ሲደርስ አየሁኝ ። ቆይ ከነ ህይወት ጋር ለመሄድ ሳስብ እንዴት ቤተሰቦቼን ዘነጋዋቸው ...? ዝም ብዬ እንደ በግ ለማንም ምኑንም ሳልተነፍስ እብስ ብዬ ልጥፋ ነበር እንዴ ...! አባቷ እንኳን ይሁን የኔን ስም process ውስጥ ለማስገባት ብለው ነው አስቀድመው ከመሄዳቸው በፊት የኔን ውሳኔ ለመስማት የፈለጉት ። እኔስ ምን አስቤ ነው ...? anyways አሁን ግን መሄድ እንኳን ብፈልግ መሄድ የማልችልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ። ይሄን ደግሞ ለህይወት እንዳልነግራት ስልኳንና በሯን ዘግታብኛለች ። የማገኝህ አብረኸኝ እንደምትሄድ ከወሰንክ ብቻ ነው ብላኛለች ። ለዚህ ብዬ ከቀጠሮው ቦታ ከቀረሁ ለዘለዓለም ከህይወት ጋር መቆራረጤ ነው ። በቦታው ላይ ተገኝቼ አልሄድም ካልኳት ደግሞ ቅስሟን መስበር ይሆንብኛል ። ልክ በቀጠሮው ቦታ እንደተገኘሁ ስታየኝ በቃ አብሮን ሊሄድ ወስኖ ነው የመጣው ብላ በደስታ ታብዳለች ። እኔ ደግሞ በተቃራኒው እንደቀረሁ ስነግራት ከመቅረቴ ይልቅ በቦታው ላይ መገኘቴ ይበልጡኑ ያሳብዳታል ። እንደማልሄድ ነግሬያት ለምን እንደቀረሁ ቁጭ ብላ ምክንያቴን የምትሰማኝ አይመስለኝም ። ብትሰማኝም ግን ለመቅረት ምክንያት የምደረድር ነው የሚመስላት ። ሁሌም ህይወት በኔ ላይ እንዲህ ነች ። መምረጥ የማልችላቸውን ሁለት ነገሮች ፈትፍታ ታቀርብልኛለች ። እኔ ደግሞ የትኛውን መጉረስ እንዳለብኝ አላውቅም ። ለአንድ በሽታ ሁለት መዳኒቶች ቀርበውልኝ የትኛውን እንደ ምውጥ ግራ ገብቶኛል ። ሁለቱም እኔን የማዳን ትልቅ ሀይል አላቸው ። ነገር ግን ሁለቱም በአንድ ላይ አይወሰዱም ። የግድ አንዱን መምረጥ ይኖርብኛል ። የቀጠሮው ቀን ደረሰ ። ህይወት #08 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ባለችኝ መሠረት ዛሬ በቦታው ላይ በተስፋ እንደምትጠብቀኝ አውቃለሁ ። አሁን የቀረው የኔ ወስኖ መሄድ ወይም የኔ ጨክኖ መቅረት ብቻ ነው ።
"ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፡
ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፣
ልቤ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ፡
ከቶ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ።
ስቋጥር ስፈታ ፡ ሳሰላስል ፡ አንዱን ይዤ ፡ አንዱን ስጥል ፣
ዞሬ ዞሬ ከሁለት ሰው ፡ መምረጥ አንዱን ተቸግሬአለሁ