የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺
ክፍል 37

.
ከቀጠሮው ቦታ በሰዓቱ ለመድረስ ስለፈለኩኝ #07 ሰዓት ላይ ከዶርም ወጥቼ በቶኒ በር ለመውጣት ጉዞ ጀመርኩኝ ። ቶኒ በር ላይ ስደርስ ግን ጥበቃው "ተመለስ" አለኝ በንቀት አይነት ድምፅ ። ደንግጬ ዞር ብዬ አየሁትና 'ምነው ያጠፋሁት ነገር አለ እንዴ ...?' አልኩት በትህትና ። "የለበስከው ልብስ ትክክል አይደለም" ሲለኝ ፡ በሆዴ 'ጌታ ሆይ ቀሚስ ነው የለበስከው እንዳትለኝ ብቻ' እያልኩኝ ዝቅ ብዬ የለበስኩትን ሾፍኩት ። በቅርቡ የገዛሁት አዲሱና የምወደው ጅንስ ሱሪ ነው ። ከላይም ቢሆን ካሉኝ ልብሶች ቆንጆ የምለውን ሸሚዝ ነው የለበስኩት ። ትንሽ እንደ መገረም ሆንኩኝና 'ልብሴ ምን ሆነ አልኩት ...?' በድጋሜ ትህትና በሞላው አነጋገር ። "አትሰማም እንዴ የምትባለውን ፡ ሱሪክ የተቀደደ ነው ። በእንደዚህ አይነት ልብስ ደግሞ መውጣትም ሆነ መግባት አይቻልም" አለኝ ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ ። የተቀደደ ሱሪ እንደሆነ ስለማላውቅ በድጋሜ ዝቅ ብዬ አየሁት ። ሱሪው የተቀደደ ሳይሆን ትንሽ ጭረት ነገር ጉልበት ላይ አለው ። ትንሽ ቦታ ብቻ ነው ክሮቹ የተፈቱት እንጂ ምንም የተጋነነ ነገር የለውም ። እንደውም ከቅርብ እንጂ ከሩቅ መተልተሉ እራሱ አይታወቅም ። በጥበቃው ሁኔታ በጣም ስለተገረምኩኝ 'ኧረ የኔ ወንድም ብዙም እኮ አይደለም የተቀደደው ፡ ደግሞም የምቸኩልበት ቦታ ስላለኝ እንጂ ተመልሼ እቀይረው ነበር' አልኩት በመማፀኛ ቋንቋ ። እሱ ግን ሊሰማኝ ነው ...? ጭራሽ ከተቀመጠበት ተነስቶ "ለምንድነው ስራዬ ውስጥ ገብተህ የምትረብሸኝ ፡ ተመለስ አልኩህ አይደል እንዴ ...?" አለኝ ሸሚዜን ጨምድዶ ይዞት ። ከዚህ በፊትም በተሰጣቸው ትንሹ ስልጣን ተማሪዎች ላይ የሚያደርሱት አንዳንድ ያልተገባ ስራቸው ከዛሬው ጋር ተደምሮ በጣም ስላናደደኝ 'እመለሳለሁ አ ፡ ልቀቀኝ ወደዛ' አልኩትና ወደ መጣሁበት ልመለስ ስል ጊቢውን ከሚጠብቁት የመከላከያ ሰራዊት አባል አንዱ "ና ዌዴዚህ ...!" አለኝ በሃይለኛ ድምፅ ። ቆሌዬ ብቻ ሳይሆን ቆዳዬ ጭምር ነበር የተገፈፈው ። በልቤ 'አቤት የኔ ጌታ ፡ ምን አልከኝ' እያልኩ ድምፁን ወደ ሰማሁበት አቅጣጫ ሄጄ ፊትለፊቱ ሹክክ ብዬ ቆምኩኝ ። Ak4 የሚባለው መሳሪያ ይዟል ። ፊቱ ጠቆር ብሎ የሚያስፈራ ሲሆን ቁመቱ ደግሞ ረዘም ያለ ነው ። ፈራ ተባ እያልኩ ወደላይ እያየሁት 'አቤት ፡ ምን ነበር ...?' አልኩት ። ትንሽ የፌዝ ሳቅ ሳቀብኝና "ጢቤቃውን ሜን ሲቲሌው ኔበር ...?" አለኝ በተወላገደ አማርኛ ። 'ምን አልኩት ፡ ያው ፡ እእእ ፡ ምን መሠለህ ፡ እእእ ፡ ቸኩዬ ስለነበር የምለውን ነገር አላውቅም ነበር ፡ እእእ ፡ እና ካጠፋው በጣም ይቅርታ' አልኩት በየመሃሉ ምራቅ እየዋጥኩኝ ። "ኢሱን ፡ በዴንብ ኢናዎራሌን ፡ ና ፡ ቴኬቴሌኝ አሁን" ብሎኝ ቶኒ አዲሱ በር ላይ ከተሰሩት ወደ አንደኛው ክፍል እየመራኝ ይዞኝ ገባ ። ሰዓቴን ሳየው #07:21 ይላል ። በዚህች ምድር ላይ ከሁሉ በላይ ድንቅ የሚለኝ ነገር የሰዓት ጉዳይ ነው ። መች ነው የሚነጋው እያለን ስንጨነቅ ከቆመበት ንቅንቅ አይልም ። ቀጠሮ ኖሮን ቦታው ላይ ለመድረስ ችግር ሲገጥመን ግን ሰዓቱ እንደ ሴኮንድ መሮጥ ይጀምራል ። የቶኒ በር ገና ያላለቀና በመሠራት ላይ ያለ ስለሆነ ክፍሉ ባዶና ቀለም እንኳን ገና ያልተቀባ ፣ በዛላይ ደግሞ መብራት ጭምር የሌለው ጨለማ ክፍል ነው ። በሩ ላይ የተሰሩት ክፍሎች ለጥበቆች ሻዎር ፣ ልብስ መቀየሪያ ፣ መፀዳጃ እና እቃ ማስቀመጫ ይሆናሉ ተብለው የተሰሩ ቢሆኑም ፡ ለኔ ግን በአሁኑ ሰዓት ከማዕከላዊ አሳንሼ የማላየው አስር ቤት ሆነው እየታዩኝ ነው ። መሳሪያ የያዘው ሰውዬ ...ሰሚራ ትባላለች ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት fashion design ተማሪ ናት ። ቤተሰቦቿ ሙስሊም እሷ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት ። በዚሁ ጉዳይ ነበር በቴሌግራም የተዋወቅነው ። ከሳምንት በዋላ ጊቢ ውስጥ ICT WAP አካባቢ ከምሽቱ #03:00 ላይ ተቀጣጠርንና ተገናኘን ። እያወራን እያለ ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ሁለት ፌደራሎች አንደኛው መሣሪያ ሌላኛው ደግሞ የጎማ ገመድ ይዘው ወደኛ መጡ ። ያለንበት ቦታ እና ሰዓት በትምህርት ቤቱ ህግ መሠረት ወንጀል አይደለም ። ጊቢ ውስጥ እስከ #04:00 ሰዓት ድረስ እንደፈለግን መንቀሳቀስ ይቻላል ። ሲጀምር ያለንበት ቦታ ለመደበቅያነት የሚያመች ሳይሆን ለማንም ሰው የሚታይና ፊትለፊት የሆነ ቦታ ነው ። ፌደራሎቹ ኮስተር ብለው በጥያቄ ያፋጥጡን ጀመር ። "እዚህ ምን እየሰራችሁ ነው ...?" ሲለን አንዱ 'ምንም ፡ ዝምብለን እያወራን ነው' አልኩት ። "ID አምጡ" አለንና ሁለታችንም ሰጠነው ። ትኩር ብሎ አየና ብሔር የሚለውን ፈልጎ አጣ መሠለኝ "ከየት ነው የመጣችሁት ...?" ብሎ የማይመለከተውን ጥያቄ አቀረበልን ። እኔ 'ከአዲስ አበባ' ስለው ሰሚራ ደግሞ "ከመቱ" አለችው ። ሁለተኛው ፌደራል ወደኔ ተጠጋና በእርግጫ እናቴን መታኝ ። ምን እንዳጠፋው ባይገባኝም ዋጥ አድርጌ ዝም አልኩኝ ። ሰሚራ ግን በድንጋጤ ልትጮህ ብላ አፏን አፍና ያዘች ። "አንቺ አፍሽን ዝጊ" አላትና አንደኛው በጥፊ መታኝ ። ጉልበታቸውን እና ስልጣናቸውን ሊያሳዩን ስለፈለጉ ሞኝነታቸውን በልቤ አምቄ ተሸነፍኩላቸው ። ባላጠፋነው ነገር ሁለታችንም "እሺ በቃ አጥፍተናል ፡ ይቅርታ" እያለን መለመን ጀመርን ። ጭራሽ ብሶባቸው በእርግጫ የመታኝ ፌደራል ፀጉሬን ይዞኝ መሬት ላይ ጎተተኝ ። አስቡት እንግዲህ ፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ ውስጥ ፡ ያውም በ FB library እና ICT WAP መሀል በሚገኘው ቦታ ላይ ሆነን ። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ተማሪዎች በቦታው ላይ የሉም ። ለነገሩ ቢኖሩም ከመሸሽ ውጪ ምንም የሚረዱን ነገር አይኖርም ። ሰሚራ እያለቀሰች ነው ። እኔ ደግሞ የፌደራሎቹ ጅልነት አናቴ ላይ ወጥቶ በብስጭት ልፈነዳ ነው ። እነሱ አቅማቸውን እያሳዩን ፡ እኛ ደግሞ ምንም አቅም እንደሌለን act እያደረግን ወደ #10 ደቂቃ ሆነን ። የመፍራት ስሜት አልተሰማኝም ። እነሱ በዚህ ሰዓት ከኛ የሚፈልጉት ከነሱ በታች መሆናችንን እንድናሳያቸው ስለሆነ ፡ እነሱ የሚሉንን ሁሉ አዎ ልክ ናችሁ ፡ እኛ ነን ጥፋተኞቹ እያልን ነው ። ህገ መንግሥት እንጂ ህግ የሌላት ሀገር ፣ ትንሹም ትልቁም ባለው ትንሽ ስልጣን ፈጣሪ ካልሆንኩ የሚልባት ምድር ። በስተመጨረሻ "በቃ ሂዱ ከዚህ" አሉን ID ሳይመልሱልን ። ለሱም ከደቂቃዎች በላይ የሚሆን ከስግደት ያልተናነሰ ልመና አቅርበን መለሱልን ። እንድንሄድ የፈቀዱልን በምን ምክንያት እንደሆነ ሳውቅ ግን በጣም አፈርኩኝ ። እነሱ የሚፈልጉትን ቋንቋ ስንናገር ነበር ደንግጠው የተውን ። እስካሁን በኛ ላይ ሲፈፅሙ የነበረው በሌላ ብሔር ላይ እያደረጉ ያሉ መስሎአቸው ነበር ። ግን በተቃራኒው የሁለታችንም እና የፌደራሎቹ መገኛ ፡ እነሱ በሚያስቡት መንገድ ከአንድ ብሔር ነው ። ደግነቱ እኔ እንደነሱ ብሔር አለመቁጠሬ ነበር ። ፈልገን ባላገኘነው ነገር መኩራትም ማፈርም ጅልነት ነው ። የዚህችን ቀን ትውስታ ቶኒ በር ጭለማ ክፍል ውስጥ ሆኜ ሳስብ ቆየሁና ፡ አሁን ደግሞ ፊትለፊቴ የቆመው መከላከያ ምን ያደርገኝ ይሆን እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ "ተነስ" የሚል የሚያስፈራ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ።
Channel photo updated
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 38


.
ደንግጬ ቀጥ ብዬ ቆምኩኝ ። ቁጭ ብዬ እንደነበር እራሱ አላወኩም ነበር የእጅ battery አበራና ፡ "push up ሲራ" አለኝ ። አንድ ሁለት መስሎኝ ዝቅ ብዬ ተፍ ተፍ ስል እሱ ይበቃል ሊል ነው ...? በግምት ከ #40 በላይ የሚሆን ሰርቼ እጄን ደክሞኝ ስንቀጠቀጥ አይቶኝ አዘነልኝ መሠለኝ "ቤቃ ቴኔስ" አለኝ ። ደስ ብሎኝ ስነሳ "አሁን ዴሞ sit up ጄምር" አለኝ ። እንደዛው ከሃያ ደቂቃ በላይ ሲያፈጋኝ ከቆየ በዋላ "ካውን ቤዋላ እንደቂዲሙ ቲሆኒና ፡ ዋ" አለኝና "ሂድ አውን" ሲለኝ ደስ ብሎኝ ወደ ቶኒ በር በፈገግታ ስሮጥ የቅድሙ ጥበቃ እየሳቀብኝ "መጀመሪያ ሱሬውን ቀይረህ ና" አለኝ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #07:44 ይላል ። ዶርም ደርሼ እስክመለስ #08 ሰዓት ይሆናል ። በ #1 ደቂቃ ውስጥ ደግሞ በ plane እራሱ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል መድረስ አልችልም ። ቢያንስ ከቶኒ እስከ ሆቴሉ ለመድረስ ከ #20 ደቂቃ በላይ ይወስድብኛል ። ጥበቃው እሺ ብሎ ቢለቀኝ ኖሮ #4 ደቂቃ ባረፍድ ነበር ። አሁን ግን ተስፋ በቆረጠ መንፈስ ወደ ዶርም በሩጫ ተመልሼ ሱሪ ቀይሬ ተመለስኩኝና ፡ በባጃጅ ከቶኒ እሸት ፣ ከእሸት ሼል ተሳፍሬ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል ፊትለፊት ስወርድ #08:20 ሆነ ። በበሩ ወደ ሆቴሉ ልገባ ስል የሆቴሉ ጥበቃ ትኩር ብሎ ካየኝ በዋላ "ተስፋዬ ነህ...?" ሲለኝ 'አዎ ነኝ' አልኩት ። "እንካ ይሄ ላንተ ነው" ብሎኝ ሁለቴ የታጠፈ ወረቀት ሰጠኝ ። ገልጬ ለማንበብ ደቂቃ አላባከንኩም ። የህይወት እጅ ፅሁፍ ነው ። አንድ አረፍተ ነገር ብቻ ነው የተፃፈበት ። እሱም "እኔም በጣም እወድሃለሁ" የሚል ነው ። ጥበቃውን የት እንደሄደች ስጠይቀው "ከትንሽ ደቂቃ በፊት ነው በዚህ በኩል በባጃጅ የሄደችው" ብሎኝ ወደ ከዚራ የሚወስደውን መንገድ ጠቆመኝ ። ጥበቃውን አመስግኜ ባጃጅ ውስጥ ገባሁና ወደዚያው አመራሁ ። ከዚራ ስወርድ ግን የት መሄድ እንዳለብኝ ዞሮብኝ ባለሁበት ቦታ ቁጭ ብዬ ለማሰብ ሞከርኩኝ ። ሳወጣ ሳወርድ በስተመጨረሻ አሪፍ ሀሳብ ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ አለልኝ ። በደስታ ብድግ አልኩኝና ስልኬን ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ የነ ህይወት ቤት ላይ የተለጠፈውን የቤት ሽያጭ ማስታወቂያ ፎቶ አውጥቼ ስልኩ ላይ ደወልኩኝ ። እድሜ ለ technology እያልኩ የኔን ድምፅ ወደ ትልቅ ሰው የሚቀይረው option ላይ አደረኩት ። የህይወት አባት ስልኩን አነሱትና ማውራት ጀመርን ። ቤታቸውን ለመግዛት እንደምፈልግና ከዛ በፊት ግን በአካል ቢቻል ዛሬውኑ ተገናኝተን እንድናወራ ጠየኳቸው ። የመሄጃቸው ቀን እየደረሰ ስለሆነ ነው መሠለኝ በደስታ ተስማሙ ። በአቅራቢያቸው ወዳለው ቦታ መምጣት እንደምችል ስነግራቸው ከዚራ እንደሆኑ ነገሩኝ ። ነገር ቀለለ ብዬ #10:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ይዘን ስልኩን ዘጋሁት ። የኔ አላማ እንዳልኩትም ቤታቸውን መግዛት አይደለም ። የህይወት አባት በቀጠሮው ቦታ ላይ ሲገኙ እኔ ሰበብ ፈጥሬ እንደቀረሁ እነግራችኋለሁ ። ከዛን እሳቸው ደግሞ ተናደው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከዋላቸው ተከትያቸው ቤታቸው የት እንደሆነ ማወቅ ። ቤታቸውን ካወኩኝ ህይወትን በቀላሉ አገኘዋት ማለት አይደለም...? ከአንድ ሰዓት በዋላ የቀጠሮው ሰዓት ሲደርስ ከተባባልንበት ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ ተደብቄ ቁጭ አልኩኝ ። የህይወት አባት ልክ በሰዓቱ ወደ ቦታው ከዚህ በፊት በማውቃት የቤት መኪና መጡ....በእቅዴ መሠረት ስልኬን አውጥቼ ለህይወት አባት ደወልኩኝ ። አስቸኳይ ጉዳይ እንደገጠመኝና ለዛሬ እንደማይመቸኝ ስነግራቸው ፡ "ይሁን" የሚል መልስ ቢሰጡኝም ፣ በትንሹም ቢሆን ድምፃቸው ላይ የቅሬታ አይነት ሁኔታ ይሰማል ። ስልኩን ዘጋሁና ተነስተው ወደሚሄዱበት ቦታ ለመሄድ ከተቀመጥኩበት ቦታ ተነሳሁ ። በመኪና ስለሆነ የሚሄዱት እንዳያመልጡኝና ለመከታተል እንዲያመቸኝ ያለችኝን #100 ብር ለባጃጅ ኮንትራት ከፍዬ የግል ሹፌር ቀጥሬያለሁ ። እና አሁን የህይወት አባት በ rava #4 ፊትለፊቴ ፣ እኔ ደግሞ በባጃጅ ከዋላቸው ነኝ ። መኪናቸውን ለገሀር/chemin de fer ወደ ሚወስደው መንገድ እየነዱት ይገኛሉ ። ለገሀር ከጊቢ በጣም ስለሚርቅ ፡ ከኔ ለመሸሽ ከሆነ ሰፈራቸው እዛ ሊሆን ይችላል አልኩኝ በልቤ ። ብዙ ደቂቃ ከተጓዝን በዋላ የህይወት አባት የሆነ ቤት አጠገብ መኪናቸውን አቆሙና ክላክስ አደረጉ ። አኔ ደግሞ ከባጃጁ ወርጄ በሆነ ግንብ ተከልዬ የሚያደርጉትን እያየሁ ነው ። ብዙም ሳይቆይ የቤቱ የውጪኛው በር ተከፈተና የሆነ ህፃን ልጅ እየሮጠ የመኪናውን በር ከፈተና ገባ ። ከዛን መኪናዋ ወደ ውስጥ ገብታ ከፊትለፊቴ ተሰወረች ። የሆነች ሴትም ውጪውን በሁለቱም አቅጣጫ ቃኘችውና በሩን ዘጋችው ። ጠጋ ብዬ ቤቱን በደንብ አየሁት ። ደስ የሚል የቤተሰብ አይነት ቤት ነው ። ህይወት እንደነገረችኝ ከሆነ ምንም አይነት ዘመድና የሚያውቁት ሰው የለም ። ታድያ እነዚህ ሰዎች እነማናቸው ...? የህይወት አባትስ እዚህ ምን ሊሰሩ መጡ ...? ብዙ ጥያቄዎች በጭንቅላቴ ውስጥ ሲመላለሱ ከቆዩ በዋላ የህይወት ስልክ ደወልኩኝ ። እንደተለመደው አይሰራም ። ስለዚህ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ የህይወት አባት ከመምሸቱ በፊት ከቤቱ ወጥተው ሌላ ቦታ የሚሄዱ ከሆነ ጠብቆ መከታተል ። ካልወጡ ደግሞ ተስፋ ቆርጦ ወደ ጊቢ መመለስ ነው ። ከሰላሳ ደቂቃ በዋላ በሩ ሲከፈት ካለሁበት ደንግጬ ተነሳሁ ። የቅድሟ መኪና ተመልሳ ወጣች ። የህይወት አባት መኪናውን አቆሙትና ወርደው በሩ ፊትለፊት የቆሙትን አንዲት ሴትና ህፃን ለጥቂት ሴኮንድ ካወሩ በዋላ ግንባራቸውን ስመው ወደ መኪናው ተመለሱ ። ምናልባት ከጠቀመኝ ብዬ ትንሽ ራቅ ቢልም በስልኬ ፎቶ አንስቻለሁ ። ከዛን መኪናዋ እኛ ወዳለንበት መንገድ መምጣት ጀመረች ። በፍጥነት ባጃጁ ውስጥ ገባሁና ተደበኩኝ ። ሲያልፈን እኛም በሹፌሬ አማካኝነት መከታተሉን ተያያዝነው ። ጭንቅላቴ ግን ያለ እረፍት ያሰላስላል ። እነዚያ ሰዎች ማናቸው ...? ወደ ሰላሳ አምስት ዓመት የሚሆናት ሴት እና አንድ ወደ #4 ዓመት የሚጠጋ ህፃን ልጅ ። በውስጤ ሚስቱና ልጁ ይሆኑ እንዴ እላለሁ ። ግን ሳላረጋግጥ መፍረድም አልፈለኩም ። ብዙ ደቂቃዎችን ከሄደን በዋላ ወደ መጣንበት ወደ ከዚራ ተመልሰን የህይወት አባት አሁንም እንደ ቅድሙ የሆነ ቤት ፊትለፊት መኪናቸውን አቆሙና ከጥቂት ሴኮንድ በዋላ የውጪኛው በር ተከፍቶ መኪናዋ ወደ ውስጥ ገባች ። የድሬዳዋ ሰፈር አሰራር ደስ የሚለው መተጣጠፍ ስለሚበዛው ተደብቆ ለማየት በደንብ ያመቻል ። መኪናዋ ከገባች በዋላ በሩ ላይ አንዲት ቆንጅዬ ሴት ልጅ ቆማ እንደ ቅድሟ ሴትዮ ግራና ቀኙን ስትቃኝ የልብ ምቴ ከዚህ በፊት ታይቶብኝ በማያውቅ ሁኔታ እንደ ፈረስ ይጋልብ ጀመር ። በአካባቢው ከእኛ ውጪ ማንም ስላልነበረ በሩን ወዲያው ዘጋችው ። ልጅቷ ህይወት ናት ፡ አዎ ህይወት ። እኔም ባለ ባጃጁን ሸኘሁትና ወደነ ህይወት ቤት ጉዞ ጀመርኩኝ


ይ..............
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል...................
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 39

የነ ህይወት በር ላይ ደርሼ የእጅ ሰዓቴን ሳይ ከምሽቱ #12:00 ሰዓት አልፏል ። ሰማዩም እየጠቆረ ነው ። እዚህ ከቆየሁ ደግሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ በወቅታዊው ችግር ምክንያት በጊዜ ስለሚዘጋ ማደሪያ አጣለሁ ። ሲጀምር እነ ህይወት ቤት ገብቼ ምን ልላቸው ነው ...? ለማንኛውም አሁን ቤታቸውን ስላወኩኝ የማደርገውን ሁሉ በደንብ አስቤበት ነገ ተመልሼ ብመጣ ነው የሚሻለው ብዬ ወደ ጊቢ ተመለስኩኝ ። ደስ የሚለው ዛሬ ጠዋት ነበር የዘንድሮውን በጀት ዓመት class ያጠናቀቅነው ። final exam ከአስር ቀን በዋላ እንጀምራለን ። መሽቶ ሲነጋ ቁጥር አንድ አላማ ያደረኩት ትናንት የህይወት አባት መጀመሪያ ላይ የሄደበት ቤት መሄድ ነበርና ወደዛው አመራሁ ። ደብተርና ብዕር ይዤ በሩን አንኳኳሁ ። ትናንት የህይወት አባት ስመዋት የነበረችው ሴት ናት ። ሰላምታ ተለዋውጠን "ምን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ" ። እኔም የመመረቅያ ፅሁፌን ድሬዳዋ ላይ እየሰራሁ እንደሆነ ነገርኳትና ምናልባት አሁን ስላለንበት ሰፈር አመሠራረትና ለየት ያለ ታሪክ ካወቀች እንድትነግረኝ ጠየኳት ። የድሬ ሰው ደግም አይደል ...? እሷም "የድሬ ፀሃይ እረፍት የላት መቼም ፡ በር ላይ ከማቆምህ ወደ ውስጥ ብትገባ የተሻለ ይሆናል" አለችኝና ወደ ቤታቸው ጋበዘችኝ ። እኔም ሳላቅማማ ገባሁ ። ሳሎናቸው ውስጥ ስዘልቅ የትናንቱ ህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ carton network እያየ ነበር ። ቁጭ በል አለችኝና "ስለ ለገሀሬ ብዙም አላውቅም ግን አባቶቻችን እንደነገሩን ከሆነ...!" ብላ የሆነ ታሪክ ነገረችን ። የኔ ፍላጎት እሱ ስላልሆነ ብዙም ትኩረት ሰጥቼ አላዳመጥኳትም ። አይኔ ቤት ውስጥ ያሉትን ነገሮች search እያደረገ እያለ አንድ ፎቶ ላይ ፍዝዝ ብዬ ቀረሁ ። ሴትዮዋ ፣ ህፃኑና የህይወት አባት በጣም የሚያምር የቤተሰብ ፎቶ ተነስተው ቁጭ ። ማፍጠጤ የታወቀኝ ሴትዮዋ "ምነው ፎቶው ላይ ፈዘዝክ" ስትለኝ ነበር ። 'አያይ ምንም' አልኳትና ቀጥዬ ወደ ጉዳዬ ለመግባት መንገድ ስለሆነኝ 'ትዳራችሁ በጣም ያስቀናል ፣ ስንት ጊዜያቹ ነው ...?' ስላት ፤ "መጀመሪያ ግን ፎቶው ላይ ያለው ሰው ማን እንደሆነ አውቀሃል...?" አለችኝ ። 'ካልተሳሳትኩኝ ከንቲባው ናቸው አይደል ...!' አልኳት እያወኩ እንዳላኩ እየሆንኩ ። "ልክ ነህ ፡ አሁን ግን የስልጣን ዘመኑ ስላበቃ ከቦታው ላይ በዚሁ ወር ለቋል ። እና ፎቶው ላይ አይተኸው ትዳራችሁ ያስቀናል ላልከው ፡ ባንተ እይታ ሊሆን ይችላል ። እንዳልከውም ግን የኛ ትዳር ያስቀናል ። ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎበታልና ። ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ብላ ትክዝ ስትል ሁኔታው ይበልጡኑ አጓግቶኝ 'ማለት ፡ ምን ተፈጠረ' አልኳት ሰፈፍ ብዬ ። ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ብንን አለችና "ምንድነው የምቀባጥረው ፡ ተወው እርሳው በቃ ዝም ብዬ ነው" አለችኝ መናገር የሌለባትን ነገር እንደ ተናገረች በሚያስታውቅባት አነጋገር ። ጫን ብዬ ከጠየኳት ማንነቴ ላይ ችግር ስለሚያስከትል ተውኩትና እንዳይነቃብኝ ስለ ድሬዳዋ ጥቂት ጥያቄዎችን ጠይቄ አመስግኜ ልወጣ ስል ሴትዮዋ ህፃኑን "አቤል ፡ ቻው አትላቸውም አንግዳውን" አለችው ። ህፃኑም የእናቱን ቃል ተቀብሎ በሚያሳሳ ድምፅ "ቻው" አለኝና ፈገግ ብዬ ወጣሁ ። አንድ ነገር ግን ጥያቄ ሆኖብኛል ። የልጁ ስም ። አቤል ። የህይወት ጓደኛ የነበረው ፣ በሷ ፋንታ የተሰዋው ፣ ያ ምስኪኑ ልጅም ስሙ አቤል ነበር ። ሴትዮዋ ካለችኝ ነገር ጋር ተደምሮ ሁሉም ነገር ዝብርቅርቅ አለብኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ። ምን ማለቷ ነው ...?ሳስበው ሴትዮዋ ልትለኝ የነበረው ስለ ህይወት ሞት ነውና ፤ የህይወት አባት ሚስት ሆና እንዴት በህይወት ፋንታ አቤል መሞቱን እንዳላወቀች ገርሞኛል ። የህይወት አባት ደግሞ ሆን ብሎ በህይወት ፋንታ የተገደለውን ልጅ ለማስታወስ አቤል የሚል ስም ለልጁ እንዳወጣም ይሰማኛል ። ስገምት ሴትዮዋ የህይወትን በህይወት መኖር የምታውቀው ነገር የለም ። ህይወትም እንደዛው ስለዚህ ቤተሰብ ምንም መረጃ የላትም ። ይሄን ያክል ምን ቢፈጠር ነው ግን ከንቲባው በእነዚህ ሰዎች መሀል ድንበር ሰርቶ እንዳይተዋወቁ ያደረገው ። መልሱንም ከራሱና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅ ። ለማንኛውም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው በሚለው ቃል በማመኔ እያተረፍኩኝ ነው ። ይህ አጋጣሚ ህይወት ትኩረት ሰጥታ እንድታዳምጠኝ ይረዳኛል ። ላወራህ አልፈልግም ብትል እንኳን የአባቷን ከሌላ ቤተሰብ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ photo ሳሳያት ደንግጣ ከኔጋር መስማማቷ አይቀርም ። ከሴትዮዋ ቤት እንደወጣሁ ቅድምያ ወደ ፎቶ ቤት ነበር የሄድኩት ። ከዛ መልስ #08:00 ሰዓት አካባቢ ወደ አዲሱ የነ ህይወት ቤት ሄጄ ትንፋሼን ሰበሰብኩና በራቸውን አንኳኳሁ ። ብዙም ሳያስጠብቁኝ በሩ ተከፈተ ። ህይወት ናት ። ልክ እንዳየችኝ ነበር ደንግጣ በሩን በሀይል መልሳ የዘጋችው ። በሩን ክፈቺና እናውራ ስላት ፡ ልትሰማኝ እራሱ ፍቃደኛ ልትሆን አልቻለችም ። እንባ በተናነቀው ድምፅ "ፀባይህ መቼም አይገባኝም ፣ መተሀል ስል ትሄዳለህ ፤ ሄደሃል ስል ትመጣለህ ። ለምንድነው ግን የምታሰቃየኝ ...? እባክህ ላይህ አልፈልግም ፤ ሂድልኝ" አለችኝ ። በቃ ደጋግማ የምትለኝ ቃል ቢኖር "ሂድልኝ" የሚለው ብቻ ነው ። 'እሺ በቃ ይቅርታ' አልኳትና ፎቶ ቤት ሄጄ ከስልኬ ላይ ያሳጠብኩትን የአባቷንና የሌላኛው ቤተሰቡ ፎቶ በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ጊቢ ለመመለስ መንገዴን ጀመርኩኝ ። አስር እርምጃ ሳልራመድ ከዋላዬ "ጥለኸኝ አትሂድ" የሚል ከዚህ በፊት የማውቀው አሳዛኝ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ። ዞር ስል ህይወት ናት ። ቀጥ ብላ ቆማ ወደኔ እያየች ነው ። በጣም ናፍቃኝ ስለነበር በሩጫ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ምን እየተሰማት እንደሆነ መገመት ቀላል ነው ። ሁሉ ነገሯ የሆነው አባቷ እሷ ሳታውቅ ከአንዲት ሴትና ህፃን ልጅ ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ፎቶ ስታይ ልቧ እንደሚሰበር ግልጽ ነው ። ቀና ብላ አየችኝና "እነዚህ ሰዎች ማናቸው ፡ ፎቶውንስ ከየት አገኘህ ...?" አለችኝ ። 'ውስጥ ገብተን ብናወራ አባትሽ ይመጡብን ይሆን ወይስ እቤት ናቸው ...?' ስላት "በቅርብ ሰዓት ስለወጣ ቶሎ አይመጣም ፡ ስለዚህ ወደ ውስጥ ብንገባ ይሻላል ። ሲጀምር መምጣትም ይችላል ። ስለ ሁሉም ነገር ልጠይቀው እፈልጋለሁ" አለችኝና ወደ አዲሱ ቤታቸው አብረን ገባን ። የማውቀውንና ያየሁትን ሁሉ በቅደም ተከተል ስነግራት ፡ ስለ አባቷ የማታውቀው ነገር በመኖሩ በጣም ተገረመች ። "ቆይ እንዴት ይደብቀኛል ፣ ሚስት ቢያገባ እኔ ለሱ የማልደሰት መስሎት ነው ...?" ትላለች አንዴ ወደዚህ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዛ እየሄደች ፡ ያሳጠብኩትን ፎቶ ደግሞ ትኩር ብላ እያየች ። አንዴ ደግሞ ትቀመጥና "ቆይ እሺ ፡ በኛ ምክንያት የአንዲት ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን ማለትስ ምን ማለት ነው ...?" ትልና ድጋሜ ደግሞ ከተቀመጠችበት ተነስታ "በኛ ምክንያት ካለች ፡ በሷና በአባቴ ምክንያት ማለቷ ነው" አለችና ትንሽ እንደ ማሰብ ብላ "የኔ ህይወት እንደዚህ የመሆኑ ጉዳይ ላይ የአባቴም እጅ አለበት ለማለት ፈልጋ ብቻ እንዳይሆን ...?" አለች እኔ ላይ አፍጥጣ ። ለማረጋጋት ብዬ 'በቃ ተረጋጊ ፡ ለጊዜው ስለምንም ነገር በእርግጠኝነት ስለማናውቅ ምንም ማድረግ አንችልም' ስላት "
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 39

የነ ህይወት በር ላይ ደርሼ የእጅ ሰዓቴን ሳይ ከምሽቱ #12:00 ሰዓት አልፏል ። ሰማዩም እየጠቆረ ነው ። እዚህ ከቆየሁ ደግሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጊቢ በወቅታዊው ችግር ምክንያት በጊዜ ስለሚዘጋ ማደሪያ አጣለሁ ። ሲጀምር እነ ህይወት ቤት ገብቼ ምን ልላቸው ነው ...? ለማንኛውም አሁን ቤታቸውን ስላወኩኝ የማደርገውን ሁሉ በደንብ አስቤበት ነገ ተመልሼ ብመጣ ነው የሚሻለው ብዬ ወደ ጊቢ ተመለስኩኝ ። ደስ የሚለው ዛሬ ጠዋት ነበር የዘንድሮውን በጀት ዓመት class ያጠናቀቅነው ። final exam ከአስር ቀን በዋላ እንጀምራለን ። መሽቶ ሲነጋ ቁጥር አንድ አላማ ያደረኩት ትናንት የህይወት አባት መጀመሪያ ላይ የሄደበት ቤት መሄድ ነበርና ወደዛው አመራሁ ። ደብተርና ብዕር ይዤ በሩን አንኳኳሁ ። ትናንት የህይወት አባት ስመዋት የነበረችው ሴት ናት ። ሰላምታ ተለዋውጠን "ምን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ" ። እኔም የመመረቅያ ፅሁፌን ድሬዳዋ ላይ እየሰራሁ እንደሆነ ነገርኳትና ምናልባት አሁን ስላለንበት ሰፈር አመሠራረትና ለየት ያለ ታሪክ ካወቀች እንድትነግረኝ ጠየኳት ። የድሬ ሰው ደግም አይደል ...? እሷም "የድሬ ፀሃይ እረፍት የላት መቼም ፡ በር ላይ ከማቆምህ ወደ ውስጥ ብትገባ የተሻለ ይሆናል" አለችኝና ወደ ቤታቸው ጋበዘችኝ ። እኔም ሳላቅማማ ገባሁ ። ሳሎናቸው ውስጥ ስዘልቅ የትናንቱ ህፃን ልጅ ቁጭ ብሎ carton network እያየ ነበር ። ቁጭ በል አለችኝና "ስለ ለገሀሬ ብዙም አላውቅም ግን አባቶቻችን እንደነገሩን ከሆነ...!" ብላ የሆነ ታሪክ ነገረችን ። የኔ ፍላጎት እሱ ስላልሆነ ብዙም ትኩረት ሰጥቼ አላዳመጥኳትም ። አይኔ ቤት ውስጥ ያሉትን ነገሮች search እያደረገ እያለ አንድ ፎቶ ላይ ፍዝዝ ብዬ ቀረሁ ። ሴትዮዋ ፣ ህፃኑና የህይወት አባት በጣም የሚያምር የቤተሰብ ፎቶ ተነስተው ቁጭ ። ማፍጠጤ የታወቀኝ ሴትዮዋ "ምነው ፎቶው ላይ ፈዘዝክ" ስትለኝ ነበር ። 'አያይ ምንም' አልኳትና ቀጥዬ ወደ ጉዳዬ ለመግባት መንገድ ስለሆነኝ 'ትዳራችሁ በጣም ያስቀናል ፣ ስንት ጊዜያቹ ነው ...?' ስላት ፤ "መጀመሪያ ግን ፎቶው ላይ ያለው ሰው ማን እንደሆነ አውቀሃል...?" አለችኝ ። 'ካልተሳሳትኩኝ ከንቲባው ናቸው አይደል ...!' አልኳት እያወኩ እንዳላኩ እየሆንኩ ። "ልክ ነህ ፡ አሁን ግን የስልጣን ዘመኑ ስላበቃ ከቦታው ላይ በዚሁ ወር ለቋል ። እና ፎቶው ላይ አይተኸው ትዳራችሁ ያስቀናል ላልከው ፡ ባንተ እይታ ሊሆን ይችላል ። እንዳልከውም ግን የኛ ትዳር ያስቀናል ። ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎበታልና ። ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ብላ ትክዝ ስትል ሁኔታው ይበልጡኑ አጓግቶኝ 'ማለት ፡ ምን ተፈጠረ' አልኳት ሰፈፍ ብዬ ። ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ብንን አለችና "ምንድነው የምቀባጥረው ፡ ተወው እርሳው በቃ ዝም ብዬ ነው" አለችኝ መናገር የሌለባትን ነገር እንደ ተናገረች በሚያስታውቅባት አነጋገር ። ጫን ብዬ ከጠየኳት ማንነቴ ላይ ችግር ስለሚያስከትል ተውኩትና እንዳይነቃብኝ ስለ ድሬዳዋ ጥቂት ጥያቄዎችን ጠይቄ አመስግኜ ልወጣ ስል ሴትዮዋ ህፃኑን "አቤል ፡ ቻው አትላቸውም አንግዳውን" አለችው ። ህፃኑም የእናቱን ቃል ተቀብሎ በሚያሳሳ ድምፅ "ቻው" አለኝና ፈገግ ብዬ ወጣሁ ። አንድ ነገር ግን ጥያቄ ሆኖብኛል ። የልጁ ስም ። አቤል ። የህይወት ጓደኛ የነበረው ፣ በሷ ፋንታ የተሰዋው ፣ ያ ምስኪኑ ልጅም ስሙ አቤል ነበር ። ሴትዮዋ ካለችኝ ነገር ጋር ተደምሮ ሁሉም ነገር ዝብርቅርቅ አለብኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት በኛ ምክንያት ምንም የማታውቅ የአንድ ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን" ። ምን ማለቷ ነው ...?ሳስበው ሴትዮዋ ልትለኝ የነበረው ስለ ህይወት ሞት ነውና ፤ የህይወት አባት ሚስት ሆና እንዴት በህይወት ፋንታ አቤል መሞቱን እንዳላወቀች ገርሞኛል ። የህይወት አባት ደግሞ ሆን ብሎ በህይወት ፋንታ የተገደለውን ልጅ ለማስታወስ አቤል የሚል ስም ለልጁ እንዳወጣም ይሰማኛል ። ስገምት ሴትዮዋ የህይወትን በህይወት መኖር የምታውቀው ነገር የለም ። ህይወትም እንደዛው ስለዚህ ቤተሰብ ምንም መረጃ የላትም ። ይሄን ያክል ምን ቢፈጠር ነው ግን ከንቲባው በእነዚህ ሰዎች መሀል ድንበር ሰርቶ እንዳይተዋወቁ ያደረገው ። መልሱንም ከራሱና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅ ። ለማንኛውም ሁሉም ነገር ለበጎ ነው በሚለው ቃል በማመኔ እያተረፍኩኝ ነው ። ይህ አጋጣሚ ህይወት ትኩረት ሰጥታ እንድታዳምጠኝ ይረዳኛል ። ላወራህ አልፈልግም ብትል እንኳን የአባቷን ከሌላ ቤተሰብ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ photo ሳሳያት ደንግጣ ከኔጋር መስማማቷ አይቀርም ። ከሴትዮዋ ቤት እንደወጣሁ ቅድምያ ወደ ፎቶ ቤት ነበር የሄድኩት ። ከዛ መልስ #08:00 ሰዓት አካባቢ ወደ አዲሱ የነ ህይወት ቤት ሄጄ ትንፋሼን ሰበሰብኩና በራቸውን አንኳኳሁ ። ብዙም ሳያስጠብቁኝ በሩ ተከፈተ ። ህይወት ናት ። ልክ እንዳየችኝ ነበር ደንግጣ በሩን በሀይል መልሳ የዘጋችው ። በሩን ክፈቺና እናውራ ስላት ፡ ልትሰማኝ እራሱ ፍቃደኛ ልትሆን አልቻለችም ። እንባ በተናነቀው ድምፅ "ፀባይህ መቼም አይገባኝም ፣ መተሀል ስል ትሄዳለህ ፤ ሄደሃል ስል ትመጣለህ ። ለምንድነው ግን የምታሰቃየኝ ...? እባክህ ላይህ አልፈልግም ፤ ሂድልኝ" አለችኝ ። በቃ ደጋግማ የምትለኝ ቃል ቢኖር "ሂድልኝ" የሚለው ብቻ ነው ። 'እሺ በቃ ይቅርታ' አልኳትና ፎቶ ቤት ሄጄ ከስልኬ ላይ ያሳጠብኩትን የአባቷንና የሌላኛው ቤተሰቡ ፎቶ በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ጊቢ ለመመለስ መንገዴን ጀመርኩኝ ። አስር እርምጃ ሳልራመድ ከዋላዬ "ጥለኸኝ አትሂድ" የሚል ከዚህ በፊት የማውቀው አሳዛኝ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ። ዞር ስል ህይወት ናት ። ቀጥ ብላ ቆማ ወደኔ እያየች ነው ። በጣም ናፍቃኝ ስለነበር በሩጫ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ምን እየተሰማት እንደሆነ መገመት ቀላል ነው ። ሁሉ ነገሯ የሆነው አባቷ እሷ ሳታውቅ ከአንዲት ሴትና ህፃን ልጅ ጋር እየተሳሳሙ የሚያሳይ ፎቶ ስታይ ልቧ እንደሚሰበር ግልጽ ነው ። ቀና ብላ አየችኝና "እነዚህ ሰዎች ማናቸው ፡ ፎቶውንስ ከየት አገኘህ ...?" አለችኝ ። 'ውስጥ ገብተን ብናወራ አባትሽ ይመጡብን ይሆን ወይስ እቤት ናቸው ...?' ስላት "በቅርብ ሰዓት ስለወጣ ቶሎ አይመጣም ፡ ስለዚህ ወደ ውስጥ ብንገባ ይሻላል ። ሲጀምር መምጣትም ይችላል ። ስለ ሁሉም ነገር ልጠይቀው እፈልጋለሁ" አለችኝና ወደ አዲሱ ቤታቸው አብረን ገባን ። የማውቀውንና ያየሁትን ሁሉ በቅደም ተከተል ስነግራት ፡ ስለ አባቷ የማታውቀው ነገር በመኖሩ በጣም ተገረመች ። "ቆይ እንዴት ይደብቀኛል ፣ ሚስት ቢያገባ እኔ ለሱ የማልደሰት መስሎት ነው ...?" ትላለች አንዴ ወደዚህ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዛ እየሄደች ፡ ያሳጠብኩትን ፎቶ ደግሞ ትኩር ብላ እያየች ። አንዴ ደግሞ ትቀመጥና "ቆይ እሺ ፡ በኛ ምክንያት የአንዲት ፍሬ ልጅ ህይወት ሰዋን ማለትስ ምን ማለት ነው ...?" ትልና ድጋሜ ደግሞ ከተቀመጠችበት ተነስታ "በኛ ምክንያት ካለች ፡ በሷና በአባቴ ምክንያት ማለቷ ነው" አለችና ትንሽ እንደ ማሰብ ብላ "የኔ ህይወት እንደዚህ የመሆኑ ጉዳይ ላይ የአባቴም እጅ አለበት ለማለት ፈልጋ ብቻ እንዳይሆን ...?" አለች እኔ ላይ አፍጥጣ ። ለማረጋጋት ብዬ 'በቃ ተረጋጊ ፡ ለጊዜው ስለምንም ነገር በእርግጠኝነት ስለማናውቅ ምንም ማድረግ አንችልም' ስላት "
​​😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 40
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
#ሊጠናቀቅ 1 የመጨረሻ ክፍል ብቻ ይቀረዋል..
ህይወት ለጊዜው ሆቴል ይዤ መረጋጋት ይኖርብኛል ብላኝ ነበር ። እኔ ግን ለብቻዋ እንድትሆን ስላልፈለኩኝ ከሷ ጋር ተቀራራቢ መልክ ካላት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ልጅ ID card ለምኜ ወደ ጊቢ ይዣት ገባሁ ። በር ላይ መታወቂያውን ልብ ብለው ስለማያዩት ማንም በማንም ሰው ID መግባት ይችላል ። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ደንግጣ ነበር ። እንደ high school ጠባብ አይደለም ። በዛላይ ከ #15 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአንድ ጊቢ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዛታቸው ትንሽ ግር ይላል ። ሰዓቱም ወደ ምሽት እየተጠጋ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ለእራት ከጊቢ እየወጣ ነበር ። ለተባበረችን ልጅ Id መልሼ ፡ እኛ እንደነገሩ ጊቢ ውስጥ ካለው ላውንጅ እራት በልተን ከዚህ በፊት ብቻዬን አዘውትሬ የምቀመጥባት ፣ ከማራኪዬ ጋርም ስልክ የማወራባት የነበረው ቦታ ወሰድኳት ። ቦታው ጨረቃን ወለል አድርጎ ከማሳየቱም በተጨማሪ ጭር ያለና ፀጥታ የሰፈነበት ፣ በዛላይ ደግሞ እራስን ለማዳመጥ በጣም አመቺ ነው ። "ሳልማር ዩኒቨርሲቲ ገባሁ አይደል...?" አለችኝ ህይወት በተከፋ ድምፅ ። እንዳይሰማት ብዬ 'እኛ ተምረን ይመስልሻል እዚህ የደረስነው ...? ዩኒቨርስቲ ከገባ ውስጥ #10% አይሆንም ተምሮና በራሱ ጥረት እዚህ የገባው ። አብዛኛው ኮርጆ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ሳያስበው ነው እራሱን እዚህ ቦታ ላይ ያገኘው ። ዞረሽ ብትጠይቂያቸው "እኔ ለቤተሰቦቼ ብዬ ነው የምማረው ፡ እኔ ላይፉን ለማየት ነው የመጣሁት ፣ እኔ ከ famly ርቄ ነፃነቴን ለማግኘት ነው የመጣሁት ፣ ወዘተ ይሉሻል ። አላማ አለኝ ፣ ትምህርቴን ጠንክሬ ጨርሼ ለሀገሬና ለወገኔ እንደዚህ ላደርግ ነው የመጣሁት የሚልሽ በጣት የሚቆጠሩ ልጆች ብቻ ናቸው ። ታዲያ አንቺስ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ባለመግባትሽ ማመስገን እንጂ ማማረር ነበረብሽ ...?' አልኳት ። ደግሞም የምሬን ነው ። የከሰረ ትውልድ ይዛ ፣ ትርፍ ለማግኘት የምትሯሯጥ ሀገር ላይ ነን ። ይሄንን ትውልድ ማስተማር ያለብን physics ፣ chemistry ፣ biology ሳይሆን ትምህርት ምን እንደሆነ ፣ ምን ምን ጥቅም እንዳለው ፣ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር ጭምር ማሳየት አለብን ። ከሁሉ ነገር መቅደም ያለበት ለትምህርት ያለን ፍቅርና ፍላጎት ነው ። እሱ ላይ ከተሰራ ሌላው ሁሉ በራሱ ጊዜ ይመጣል ። ይሄ ትውልድ ትምህርት የሚለውን ቃል እራሱ መስማት አይፈልግም ። በቃ ከሰይጣን በላይ ጠልቶታል ። ስለዚህ የጠላውን ነገር በግድ ተማር ከምንለው ፡ ለምን እንደጠላ መርምረን ፣ ምን ብናደርግ ደግሞ መውደድ እንደሚችል አስበን ወደ ቀልቡ መመለስ የተሻለ ይሆናል ። እንዲሁ ስለ ዩኒቨርስቲ እያወራን እያለ #01:30 ላይ የህይወት አባት እቤት ገብተው አጧት መሠለኝ ስልኳ ላይ ደወሉ ። አንስታው እንድሰማቸው ነው መሠለኝ loud speaker ላይ አደረገች ። "የኔ ህይወት ፡ የት ሄደሽ ነው ፣ ከቤት አጣውሽ እኮ ...?" ሲሏት "አያይ ብዙም አልራኩም ፡ ባሌንና ልጄን አይቼ ለመመለስ ብዬ ነው" አለቻቸው ፈርጠም ብላ ። "ስለምን ባልና ልጅ ነው የምታወሪው ልጄ ...?" አሏት መልሰው ። ህይወትም ትንሽ የፌዝ ሳቅ እንደመሳቅ አለችና "ለካ አልነገርኩህም ፡ ባል አለኝ እኮ ፣ ለዛውም አንድ ቆንጂዬ ህፃን ልጅ ከሶስት ዓመት በፊት ወልደናል" አለቻቸው ። ምንም መልስ የለም ፣ ፀጥ ፡ ሴኮንዱ ይቆጥራል ፡ አሁንም ግን ምንም አይነት መልስ ከህይወት አባት አልመጣም ። ህይወት ዝምታው ሲበዛባት "አየህ ፡ ምንም መልስ የለህም ። ቆይ ግን እስከመች ነበር እኔን ለመደበቅ ያሰብከው ፣ እስከዘላለም ...? ንገረኛ ...? ለማንኛውም ከኔጋር ከምታሳልፈው ቅዳሜና እሁድ ይልቅ ከነሱ ጋር የምታሳልፋቸው አምስት ቀናት የተሻሉ ስለሆኑ እነሱ ይሻሉሀል ። ቆይ ግን ልጅ አለኝ ፣ ሚስት አለኝ ብትል የምቃወምህ መስሎህ ነበር ...?" ስትላቸው "የኔ ልጅ እቤት ተመለሺና እናውራ" ብለው ይማፀኗት ጀመር ። "ሶስት ዓመት ሙሉ እኮ እቤት ነበርኩ ። ያኔ የት ነበርክ ። ለማንኛውም አትፈልገኝ ፣ የተሻለ ቦታ ላይ ነው ያለሁት ። መገናኘት ሲያስፈልገን እራሴው እቤት እመጣለሁ" ብላ ስልኩን ዘጋችው ።ምንድነው ሰው ሁሉ ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ መላክ የመሰለው ፣ እንዴት ነው ሰማዩ እንዲህ ተጠቅልሎ በእጄ የምይዘው መሀረብ ያከለው ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው ፡ መሬት መዞር ትታ በእፎይታ ያቆማት ፣ ምንድነው ጨረቃን ከሰማይ አውርዶ ምድር ያሳረፋት...? እያልኩ አስባለሁ ። ደግሞም አላቆምም መልሼ መላልሼ አሁንም አስባለሁ ። ማነው በመንገዴ ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ ፣ ማንስ ነው ግማሽ ልቤን ሸርፎ የወሰደው ፡ በትልቁ ቆርሶ ፣ መንገደኛው ሁሉ የተከፋ ፊቱን በማን ተነጠቀ ፣ ከጨፍጋጋ ፊት ላይ እንዲህ ያለ ብርሃን እንዴት ፈነጠቀ ፣ ሚሊዮን ህፃናት ከልብ በሚነሳ ስርቅርቅ ድምፃቸው ፡ የት ቢዘምሩ ነው ልቤ ሚሰማቸው ፣ እኮ በምን ምክንያት ይህ ሁሉ ተቀየረ ፣ ያልነበረ ወደነበረ እንዴት ተመለሰ ...? እያልኩ አስባለሁ ። አሁንም አስባለሁ ። ምንድነው እንደዚህ ፊቴን በብርሃን ፡ ከንፈሬን በውብ ሳቅ የሚያጥለቀልቀው ፣ እንዴትስ ነው ከልቤ ኮለል ያለ ሰላም በጠዋት የሚፈልቀው ፣ የጠሉኝን ሁሉ ድንገት መውደዴ ፡ መሬቱን ለቅቄ አየር ላይ መንጎዴ ፡ ምንድነው ምስጢሩ ፣ ቆይ ውስጤን ምን ነካው ...? አለም እንዲህ ጠቦ በእርምጃ የሚለካው ፣ ውቅያኖስ በእፍኝ ተጨልፎ የሚደርቅ ፣ ተራራው በክንዴ ተጎሽሞ የሚደቅ ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው እያልኩ አስባለሁ ። እኔ ደግሞ ቤሳቤስቲን ሳንቲም ኪሴ ሳይጨመር ፣ ዓመት የለበስኩት ልብሴ ሳይቀየር ፣ የዘውትር ጉርሴ ጣዕሙ ሳይነካ ፣ እኔነት እኔ ውስጥ ተቀይሯል ለካ ። እኮ በምን ምክንያት እኔ ተቀየርኩኝ ፣ እንዴት እኔ ነኝ ስል ፡ እኔ ሌላ ሆንኩኝ እያልኩ አስባለሁ ። ለካስ ከህይወት ጋር ስለሆንኩኝ ነው ። ያውም ከአባቷ ተለይታ ከድሬዳዋ ለቃ ከዩኒቨርስቲ የዚህን ዓመት ትምህርት ጨርሼ ስመለስ አብራኝ ወደ ትውልድ ቦታዬ ወደ ሙገር መጥታ ። አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል

✎ የመጨረሻ ክፍል ይለቀቃል....
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​😘የከንቲባው ልጅ😘
ደራሲ ተስፋዬ በትሩ
#የመጨረሻው ክፍል
አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል ። አባቷም ከሚስቱና ከህፃን ልጁ ጋር ወደ አሜሪካ በረዋል ። ከሰኔ #13 እስከ #21 final ፈተና ተፈትነን ስንጨርስ ከመሄዳቸው በፊት አባቷን አግኝቼ አነጋግሬያቸው ነበር ። ስለ ሁሉም ነገር እንዲህ ብለው ነገሩኝ ። "ከአራት ዓመት በፊት ወደ ስልጣን እንደመጣሁ አካባቢ በስራ ላይ አንዲት ሴትን ተዋወኩኝ ። በድሬዳዋ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ናት ። ሁለታችንን አንድ የሚያመሳስለን ነገር ነበር ። እሷ ባሏን እኔ ደግሞ ሚስቴን በሞት አጥተናል ። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ውስጤን ሰርስራ ገባች ። በስራና በኑሮዬ ጭምር ገብታ ታግዘኝና ትረዳኝ ጀመር ። በዚህ መሀል ግን አንድ ችግር ነበር ። እሱም በዙሪያችን ያሉ ሰዎች በኛ ስራና ግኑኝነት አለመደሰት ነበር ። የሚገርምህ ሁሉም በአንድነት ይቺን ምስኪን ከተማ ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ሲስማሙ እሷ ብቻ ነበረች ከጎኔ የነበረችው ። ድሬዳዋ ከተማ በሁለት ክልል መሃል ያለች በመሆኗ በየ አራት ዓመቱ ባለስልጣናት አንዴ ከኦሮሚያ ከአራት ዓመት በዋላ ደግሞ ከሶማሌ ክልል እያለ ተራ በተራ #4 ዓመት እየጠበቀ ስለሚፈራረቅ ሁሉም ባለስልጣናት ሀሳባቸው ድሬን ማልማት ሳይሆን እራሳቸውን ማልማት ነበር ። እኔ ደግሞ ከንቲባ የሆንኩበት ዋነኛው ምክንያት ይህንኑን ስርዓት ለማጥፋት ነበር ። ከዛ በዋላ ያለው ታሪክ ህይወት እንደነገረችህ ነው ። የኛን መንገድ የማይከተሉ ሰዎች በበቀል ተነሳስተው ልጄን ለመግደል ብለው አቤልን ቀጠፉ ። እናም ወጣት ተስፋዬ ባለፈው ተከትለኸኝ ያየሀት ሴት በዛ አስቸጋሪ ጊዜ ከጎኔ የነበረች ጀግና ሴት ናት ። በዛው ወቅት በመሃላችን በተፈጠረው የፍቅር ግኑኝነት ልጅ ፀነሰችልኝና ተወለደ ። ይሄን ሁሉ ታሪክ ደግሞ ለልጄ በጊዜው እንዳልነግራት ለራሷ በጣም መጥፎ ሁኔታ ውስጥ ነበረች ። እንዴት ልጄ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርጎ በጣም የምትወደው ጓደኛዋ ሞቶ ስለራሴ ደስታና ሀሴት እነግራታለሁ ...? ምን አይነት ስቃይ ውስጥ እንደነበረች ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ። አሁን አንተን ስታገኝ ነው እንደዚህ ተቀይራ ያየሀት ። ለማንኛውም ሁሉንም ነገር ወደ ውጪ ስንሄድ ላሳውቃት ነበር የፈለኩት ። ባለቤቴንና ትንሹ ልጄን ከህይወት ጋር አንድላይ አሜሪካ ወስጄ ለሁሉም እውነታውን ልገልጽ ነበር እቅዴ ። እንደምታየው አሁን ሁሉም ነገር ተበላሽቷል ። ልጄም አኩርፋኝ ሸሽታኛለች" አሉኝ በሀዘን ። በስተመጨረሻ ልንለያይ ስንል ያሉኝን ግን እስካሁን ድረስ አምኜ አልተቀበልኩትም ። እንዲህ ነበር ያሉኝ "የህይወትን በህይወት መኖር ከኔና ካንተ ውጪ ማንም ሰው አያውቅም ። ለህይወት በህይወት መኖር ሲባል ይህ ምስጢር እንዲቀጥል እፈልጋለሁ ። እሷን ካንተ ለይቼ ወደ ውጪ ልወስዳት አልችልም ። ስለዚህ ልጄን ላንተ ሰጥቼሃለሁ ። ይዘሃት ወደ ሀገርህ ሂድ ። ከፈለጋችሁ እዛው ፤ ካልሆነም ደግሞ አዲስ አበባ ደስ የሚል ኑሮ መኖር ትችላላችሁ ። ዕድሜያችሁ ከ #20 ስላለፈ እራሳችሁን ችላችሁ መኖር አይከብዳችሁም ። ለብር ደግሞ ብዙም አትጨነቁ ። በባንኳ ውስጥ አንቀባሮ የሚያኖራችሁ በቂ ገንዘብ አለ" ። ታድያ የህይወት አባት እንዲህ ብለው መርቀው ልጃቸውን ሲሰጡኝ እንዴት ብዬ ልመን ...? በሌላ በኩል ደግሞ ማራኪዬ ስለኔ ምን እያሰበች እንደሆነ ለማወቅ በስልክ ሳዋራት "ሙሉ በሙሉ እንደረሳችኝና ሌላ ህንወት እንደጀመረች" ነገረቸኝ ። አሁን ከህይወት ጋር ነኝ ። ከቤተሰቦቼ ጋር አስተዋወኳት ። ለቤተሰቦቼም ሁሉን ነገር ነግሬያቸው ተስማምተን አዲስ አበባ አዲስ ህይወት ከህይወት ጋር ለመጀመር ተዘጋጅተናል ። ልክ እንደባልና ሚስት ሳይሆን እንደ ፍቅር ለመኖር ጉዞ ጀምረናል ። ከህይወት ጋር ስትኖር ፤ በህይወት መኖርህን ትወደዋለህ ። ስለ ህይወት ለማውራት ፣ እኔ ቃል የለኝም ፤ እሷ ካለች አለሁ ፣ ያለዚያ ግን የለሁም ።

ህይወት መዝሙር ነች ፤ ዘምራት
ህይወት ሰቀቀን ነች ፤ ቻላት
ህይወት ተግባር ነች ፤ ተወጣት
ህይወት ሽፍንፍን ነች ፤ ግለጣት
ህይወት ሀዘን ነች ፤ ተቋቋማት
ህይወት ስጦታ ነች ፤ ተቀበላት
ህይወት ውርርድ ነች ፤ ተወራረዳት
ህይወት ትግል ነች ፤ ታገላት
ህይወት ምስጢር ነች ፤ ፍታት
ህይወት ውበት ነች ፤ አጊጣት
ህይወት ጉዞ ነች ፤ አጠናቃት
ህይወት ቃል ነች ፤ አሟላት
ህይወት አጋጣሚ ነች ፤ ተጠቀማት
ህይወት ጀብዱ ነች ፤ ድፈራት
ህይወት ፍቅር ነች ፤ ፈልጋት ።
.
.
.
.
✍🏽~~~ተፈፀመ~~~~✍🏽 ☞ የስው ልጅ መጨረሻው ሲያምር ነውና ፤ ፈጣሪ መጨረሻችንን ያሳምርልን! እኔ አሜን ብያለሁ፡፡

#እኔም የተስፋዬና የህይወት ፍቅር አብቦ ወደሌላኛው የህይወት ምእራፍ እንደሚሸጋገሩ...ትዳራቸው ሰምሮም ፍሬ እንደሚያዩ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ ...አመሰግናለሁ።።😘
Forwarded from ༺Mâřķóñãľ༻
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፈል 1


.
.
.
በጠዋት ከ ቅዱስ ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን የሚወጣው ህይወትን የሚያለመልም የቅዳሴ ዜማ በጆሮዬ አቀጨለና ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ።ከብርድ ልብሱ ውስጥ ሳልወጣ አይኔን ሸፍኜ ይሔን ጥዑም ዜማ እየኮመኮምኩ ሳለሁ "ዮርዲ ቁርስ ደርሷል" የሚል ድምፅ ከተመሰጦዬ መለሰኝ ።ብርድ ልብሱን ከአይኔ ላይ ቀስ ብየ ስገልጠው መጋረጃውን አምልጣ ሰርጋ ከገባችው የጠዋት ፀሐይ ጋር ተጋጨን።ቢጫ ቀለም ከተቃባው ምኝታ ቤት ጋር ፀሐይ ተደምራ ክፍሉን በብርሀን አሽቆጥቁጣዋለች።"ዋው ደስ የሚል እሁድ "አልኩና ከአልጋየ ላይ ወረድኩ። ................ቁርስ እንደነገሩ ከቀማመስኩ በኋላ አንድ ሲኒ ቡና ፉት ብዬ ወደ ክፍሌ ገባሁና ከውስጥ ዘግቼ ቁጭ አልኩ ።ትንሽ በሀሳብ ስባክን ቆየሁና "ደሳለኝ ያለኝ ነገር እውነት ነው እሱን መስማት አለብኝ" አልኩና በውስጤ ከተቀመጥኩበት በወኔ ተነስቼ ከመሳቢያው ውስጥ እስክሪብቶ እና ወረቀት አወጣሁና በድፍረት ጫር ጫር እድርጌ ወደ ኪሴ አስገባሁት ። ወደ መስታወቱ ተገጠቼ ከምስሌ ጋር ተፋጠጥኩ ።"ድፈር ዮርዲ አንተ እኮ የኔ ወንድም ነህ አንተ እኮ ዮርዳኖስ ነህ ታደርገዋለህ" የደሳለኝ ድምጽ ደጋግሞ ጆሮዬ ላይ ደወለ።በረጅሙ ተነፈስኩ እና መስታወቱ ውስጥ ሆኖ የሚያየኝን የራሴው ምስል "ድፈር ዮርዳኖስ ድፈር ካለመናገር ደጅ አዝማችነት ይቀራል " አልኩት ከሌላ ሰው ጋር የማወራ ያሀል ጮህ ብዬ ።ዛሬ ከየት እንደመጣ የማላውቀው የወኔ ካባ በላዬ ላይ ተደፍቷል ።ግቢያችንን ለቅቄ ጉዞ ጀመርኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ተሾመ እባላለሁ ከእናቴ ከ ወ/ሮ አለም አወቀ እና ከአባቴ ከአቶ ተሾመ ታምሩ መስከረም 05,1992ዓ.ም ይችን ዓለም ተቀላቀልኩ ።ለቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነኝ አህቴ ቤዛዊት ተሾመ ።በጣም የምወዳት ታላቅ እህቴ ነች በሊትሌቸር ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በዚህ ክረምት ነው የተመረቀችው።አባቴ ነጋዴ ነው እናቴ የቤት እመቤት።ኑሯችን ከደብረ ማርቆስ 15 ኪ.ሜ እርቃ ከምትገኘው ትንሿ አምበር ከተማ ነው።ሀብታሞች አይደለንም ድሆችም አይደለንም የጎደለን የለም ።ቤተሰባችን ውስጥ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች አሉ።እድሜ ጠገቧ አያቴ እና የቤት ሰራተኛዋ እልፍነሽ።ቤተሰባችን ፍቅር ነው። ፍቅር ማለት የእኛ ቤተሰብ ነው ብል ማጋነን አይሆንም! 2007 ማትሪክ ተፈትኜ ውጤት እየጠበኩ ነው ።ብዙ ጓደኞች አሉኝ።ደሳለኝ ግን ከጓዳኛ በላይ ወንድሜ ነው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከግቢያችን በስተሰሜን በግምት 100 ሜትር ያክል ከተጓዝኩ በኋላ ከአንድ ትልቅ ግቢ ላይ ደረስኩ።ትንሽ ከአቅማማሁ በኋላ "አብርሃም አብርሃም " ብዬ እንደተጣራሁ ያ እንደ ጦር የምፈራው ምዕታተኛው የሔዋን ድምፅ ማነው አለኝ።መልስ አልመለስኩም ልቤ አታሞውን ይደልቅ ጀምሯል። በሩም ተከፈተ ወኔየን ሰብሰብ አድርጌ ቆምኩ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
Forwarded from ༺Mâřķóñãľ༻
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ🔥

😘ክፍል 2


.
.
.
"እንዴ ዮርዲ እንዴት ነህ"አለች ሔዋን።
"አብርሀምን ፈልጌ ነበር "አልኳት ሰላምታዋን አልሰማሁም አሉ።
ጉንጬን ዳበስ አደረገችና "ዮርዲዬ ዛሬ ደግሞ ሰላምታ የለም እንዴ ምን ሆንክብኝ የኔ አስቀያሚ ደህና አይደለህም?"አለችኝ እንደመጨነቅ ብላ።"ሒዊ ምንም አልሆንኩም አብርሃምን ማግኘት ብቻ ነው የምፈልገው" አልኳት አይኗን የመሸሽ ያህል ወደ መሬት አቀርቅሬ።ሔዋን ያለመፈለግ ስሜት ተሰማት መሰለኝ ተበሳጭታ መንቀር መንቀር እያለች አብርሀምን ለመጥራት ወደ ውስጥ ገባች። አብርሀም መጣ።ሳቂታው አብርሀም እሱ ማለት ለመሳቅ የተፈጠረ ፈገግ ለማለት ብቻ የሚኖር አይነት ልጅ ነው።
"ዮርዳኖስ እንዴት ነህ"አለ አብሪሽ ፈገግ ብሎ
"ደህና ነኝ ሁሉ ሰላም ነው አይደል"አልኩት
"ሰላም ነው ። በጠዋት ምን ጎርፍ ጣለህ?
"ውይ አብሪሽዬ ስራ ላይ ነበርክ እንዴ?"አልኩት እንደመሳቀቅ ብዬ
"አረ በጭራሽ ምንም ስራ የለኝም ከዚህ በፊት በዚህ ሰዐት መጥተህ አታውቅም ብዬ ነው" አለኝ
"በል እንግዲያስ ስራ ከሌለህ ከለመድነው ቦታ እንሒድ እማማክርህ ጉዳይ ነበረኝ።"አልኩት
"በደስታ ነዋ እሺ የምልህ"አለ አብሪሽ እየሳቀ።ተያይዘን ከለመድንው ቦታ ሔደን ተቀመጥን።ለብዙ ደቂቃዎች ያህል ስንጨዋወት ቆየን እና።"እሺ ወንድም ዮርዳኖስ ለምን ነበር የፈለግከኝ ?"አለኝ
ትንፋሼን ሰብሰብ አድርጌ ለመናገር ተዘጋጀው "ምን መሰለህ እኔ ሔዋንን አ...ፈ...ቅራ...ታለሁ ለብዙ ጊዜ ልነግራት እወስን እና ድፍረት እያጣሁ ወኔ ከእኔ ገሸሽ እያለ ስቸገር ቆየሁ።"አልኩና የማማጥ ያህል ተጨነቄ ተነፈስኩ።ቀና ብዬ አብርሀምን ስመለከት ደነገጥኩ።ምንም አይነት የስሜት መለወጥ አይታይበትም።አልደነገጠም አልተገረመም አይኔ ጋር የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ሁሉ አይኖቹን አይኔ ላይ ተክሏል።"እንዴ እንደዚህ ተጨንቄ በመከራ ነግሬው አልሰማኝም ማለት ነው"አልኩኝ በውስጤ።ግራ መጋባቴን የተመለከተው አብርሃም "ዮርዳኖስ ሔዋንን እንደምታፈቅራት አቃለሁ"ብሎኝ እርፍ
"አረ በቂርቆስ አትቀልድ "አልኩት
"እሚቀለድበትን ሰዐት እና ቦታ አውቃለሁ ትንሽ ልጅ አይደለሁም"አለኝ ኮስተር ብሎ
"እና ጠንቋይ ትቀልባለህ ልበል?እኔ እኮ ከ ጓደኛዬ ከደሳለኝ ውጭ ለማንም ትንፍሽ አላልኩም።እንዴት አንተ ልታውቅ ቻልክ?"አልከት
"እሱን በሰፊ ፕሮግራም እናወራለን ።አሁን ከእኔ ምን እንደሚጠበቅ ንገረኝ እና እንለያይ ዝናብ ሊዘንብ ይመስላል"አለኝ ሰማዩን ቀና ብሎ እየተመለከተ።
"አብርሀም ለአመታት ያህል እንደወንድም ከጎኔ ውስጥ ከእቅፌ ላይ የነበረችን ልጅ በድንገት ከፊቷ ቆሜ አፈቅርሻለሁ ለማለት ሞራል አጣሁ።አንተን ማስቸገር ካልሆነብኝ ይችን ወረቀት አድርስልኝ?" አልኩት
"እንዴ ዮርዲ እኔ ሌላ ሰው መሆኔ ነው ካላስቸገርኩህ የምትለኝ በል ስጠኝ እና ልሒድ"አለ አብሪሽ ለመሔድ እየተነሳ
"ወረቀቱን ሰጠሁት እና፤ስማ ደግሞ መልሱን ዛሬ ትፃፍልኝ እና መልስልኝ?"አልኩት
"እሺ መልካም እድል 10:00 እንገናኝ"አለና እየሮጠ ሔደ።ሰዓቴን ተመለከትኩ 6:03 ይላል።ቤት ለምሳ ይጠብቁኛል ብዬ ወደቤቴ አመራሁ።የጠዋቷ ፀሐይ ለውሸት ነበር የወጣችው።ቤት ከመግባቴ ትንሿን የአምበር ከተማ ዶፍ ዝናብ በአፍ እና በአፍንጫዋ ያዳፈት ጀመር።ቤተሰቦቼ በዛሬው ሁኔታዬ ሳይወዛጋቡ አልቀሩም ።ምሳ ቀመስኩ እንጂ አልበላሁም።ምሳ ተበልቶ የምሳ ሰዓቱ ቡና ሲጠጣ እኔ ግን እምቢ ብዬ ክፍሌን ዘግቼ አልጋየ ላይ ጋደም አልኩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የማይታለፍ ነገር የለም እነዚህ አርባ አመት ያህል ረዝመው ያስጨነቁኝ አራት ሰዓታት በመከራ አለፉና ጉዴን ለመስማት
ከተለመደው ቦታ ቀደም ብዬ ሔድኩ።ከ30 ደቂቃ ጥበቃ በኋላ አብርሀም በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሲመጣ አየሁት።የሞት መልዕክት ይዞልኝ የመጣ ይመስል ሳየው ልቤ በአፌ እስክትወጣ ያህል መምታት ጀመረች።

ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
Channel photo updated
​​😘ሰሜናዊት ሙሽራ🔥

💞ክፍል 3


.
.
.
ከሁለት አመታት በኋላ ..........................

ከሁለት አመት በፊት ያልታየችው ሔዋን ዛሬ ግን መነጋገሪያ ሆነች።ማንም ያላየውን ውበቷን ተመልክቶ በፍቅሯ የተነደፍው እሱ ብቻ ሳለ፤ዛሬ ግን ስር ስር ባዬች በዙ።ጉድ ተባለ ይችን የመሰለች ልዕልት ከዚህ ጋር ምን ትሰራለች አይመጥናትም አይገባትም ተባለ።እውነት ነው ዮርዳኖስ ቆንጆ የሚባል ባይሆንም ለወንድ ልጅ የሚገባውን ያህል ደስ የሚል ልጅ ነዉ።ፍቅራቸው ያስቀናል ።ማንም ምንም ቢያወራ ሔዋን እኔ የ ዮርዳኖስ ነኝ ከእሱ የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው አለች።ዛሬ ሐምሌ 13 ነው ከሔዋን ገር ፍቅር ከጀመሩ ሁለተኛ አመታቸውን እያከበሩ ነው።ሁለቱም 12ኛ ክፍል ተፈትነው ውጤት እየጠበቁ ነው።ዮርዳኖስ ሶሻል ሳይንስ እርሷ ደግሞ ናቹራል ሳይንስ ነበር የገቡት ።
"ኩራተኛዋ ልዕልት"አለና ዮርዳኖስ ጉንጯን ሳም አደረገጋት።
"ማነው ባክህ ኩራተኛ ያደረገኝ፤እኔ እንደሆኩ ማንንም የማላስከፋ ሩህሩህ ልብ ነው ያለኝ"አለች የጉንዮሽ ስርቅ አድርጋ እየተመለከተችው።ዮርዳኖስን ለማስቀናት ሁሌ የምትናገራት ሽሙጥ መሆኗ ነው።
"እሱን ተይውና ኩራተኛማ ነሽ።ያኔ እስረኛ ክፍል እያለን ለአብርሃም የላኩልሽን ደብዳቤ ምን ብለሽ ነበር የመለስሽልኝ?"አላት
ከአፉ ቀለብ አደረገችና"እኔ ለአንተ መሆን አልችልም አቻህን ፈልግ ደፋር !"አለችና ሳቀች።መቼም ስትስቅ እንኳን የአፍቃሪዋን የጠላቷንም ልብ ያስደነግጣል ።
"ግን ምን አስበሽ ነበር?"አለ
"አንተ ደግሞ፣የሴት ወግ መሆኑ ነዋ በአንድ ጥያቄ እሻ ያለች ብቸኛዋ ሴት እንድባል ፈልገህ ነው እንዴ?"ቀጠለች እና "ደሳለኝ አይመጣም እንዴ?"አለች
"አረ የሱን ነገር ተይው" አለ እንደመሳቅ ብሎ ።
"ምነው ምን ብሎ አናደደህ ደግሞ"አለች ለመስማት እየጓጓች
"አንድ ቀን አነሱ ቤት ደርሰን ስንመለስ ፡አንዲት ቆንጆ ልጅ ከሆነ ሰው ጋር ቆማ ስትሳሳም ተመለከትን።"
"ከዚያስ?"አለች ሔዋን
"ከዚያማ ሞን ቢለኝ ጥሩ ነው "ይቺ ደግሞ ከዚህ ቦርኮ ጋር ምን ትሰራለች አለኝ።እኔም ምነው ዋናው ነገር መፋቀራቸው ነው አልኩት ።ቀለብ አደረገና ፍቅር እውር ያደርጋል የሚባለውን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ አረጋገጥኩ ።አለኝ"
"አንዴት? አልኩት።
"ምን እንዴት አለው እያየኸው ይቺ ቆንጆ ከዚህ ጉርድ በርሜል ጋር፤ሌላኛው የእኔው ጉድ" አለና በስርቆት አየኝ
"ምን ለማለት ፈልገህ ነው ?አልኩት
"ያው አንተ ከሔዋን ጋር ማለት ነዋ"አለና መናደዴን ሲመለከት "ያሉትን ነው"አላለኝም መሰለሸ።
ሔዋን ልቧ እስኪፈርስ ሳቀች እና "በቃ እሱ ግቢ ሔዶ ከመጣ በኋላ ስራው ሁሉ አንተን ማናደድ ሆነ አይደል"አለች ያልጨረሰችውን ሳቋን ለመጨረስ የምትስቅ በሚመስል መልኩ ደግማ እየሳቀች።
"አንቺማ ሳቂ የእኔ አስቀያሚ"አለና ሳም አደረጋት
"በቃ ማታ ከደሳለኝ ጋር ሆነህ ላግኝህ ልደታችንን እናከብራለን"አለች እና ፍዝዝ አለች
"እሺ የእኔ እመቤት ታዛዥ ነኝ የልደት ስጦታዬን እንዳትረሺ"አለ ዮርዳኖስ
"በደምብ ነው ያለህ የዛሬው ልዩ ነው"አለች ፍዝዝ እንዳለች።
ሁኔታዋ አላመረውም ።እንደዛሬው ሁና አይቷት አያውቅም።ከተገናኙ ጀምሮ በስስት ነበር የምትመለከተው።
"እሺ በቃ ግቢ፤ የማታ ሰው ይበለን"ብሎ ከንፈሯ ጋር ማህተም አስቀመጣና ምን ሆና ይሆን እያለ እያሰላሰለ ወደቤቱ ገባ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 4

.
.
.
ዮርዳኖስ ቤት ሲገባ ደነገጠ አፉን ከፍቶ ቀረ።ቤቱ በዲም ላይት አሸብርቋል ።ከበሩ ፊት ለፊት የ ዮርዳኖስ እና የሔዋን ፎቶ በትልቅ መስታወት ተንጠልጥሏል።ከላይ እንኳን ለሁለተኛ አመት የፍቅር ጅማሪያችሁ አደረሳችሁ።የሚል ወረቀት ተለጥፏል።ልቡ ተሸበረ።"ዛሬ የሚፈጠር ነገር አለ እንጂ ካለነገር ልቤ አልፈራም፤ሔዋንም ልክ አልነበረችም"አለ በውስጡ ።እህቱ ቤዛ ወደ ሳሎን ገባች እና "ሰርፕራይዝ"ብላ ከሃሳቡ አባነነችው።
"በቃ ስራ አጥ መሆን እንደዚህ ነው የሚያደርገው? ለአንቺ ስራ ፈጠራ መሆኑ ነው አይደል?እስኪ ይሔን ሁሉ ለደከምሽበት ምንያህል ክፍያ ነው የምትጠይቂኝ?"አለ ዮርዲ ለመቀለድ
ቤዛ አኮረፈች እና ተመልሳ ወደ እናቷ ሔደች ።
"አንተ ምላሳም ሰምቼሃለሁ!አንተን ለማስደሰት ይሔንን ሁሉ ደክማ እንደዚህ ነው መልስህ?"አለች ወይዘሮ አለም እየሳቀች ።
እውነት ነው ቤዛዊት ከተመረቀች ድፍን ሁለት አመት ሞላት።ስራ የሚባል ነገር የለም።ከአባቷ ከአቶ ተሾመ ጋር ንግዱን እያጦጧፈችው ነው።አሁንማ ተስፋ ቆርጣ የስራ ማስታወቂያ ማየት ካቆመች ስድስት ወር ሞላት አረ አንዲያውም የተመረቀችበትን የትምህረት መስክ ሁሉ ሳትረሳው አልቀረችም ።
ዮርዲ ጓዳ ሲገባ እናቱ ምግብ በመስራት ተጠምዳለች።ቤዛ ደግሞ ለምቦጯን ጥላ ተቀምጣለች።
"አንቺ ደግሞ ሰው መቀለድ አይችልም እንዴ?"አለ ዮርዲ ፀጉሯን እንደ ህፃን ልጅ እዬደባበሰ
"አንደኛ ስራ አጥ አትበለኝ፤ሲቀጥል እኔ ስራ አጥ አይደለሁም ነጋዴ ነኝ አሺ።"አለች ኮስተር ብላ።
"እስኪ በእኔ ሞት በስነፅሁፍ ተመርቆ ነጋዴ አይከብድም " አለት ዮርዲ።
"አሱን ከጥቂት አመታት በኋላ በእኔ ቦታ ስትሆን ትነግረኛለህ ወሬኛ"አለች ቤዛ
"አንተ ስራ ፈት ሒድ ወደ ክፍልህ አባትህ እቃ አስቀምጦልሀል"አለች ወይዘሮ አለም
"እእእ ስራ ፈት ብለውማ የሰው ሞራል አይንኩ ወይዘሮ አለም"አለና ጓዳውን ለቆ እየወጣ ዞር ብሎ ቤዛን አየት ሲያደርጋት ነጠላ ጫማዋን አውልቃ ጀርባውን አቀመሰችው።ሳሎኑን አቋርጦ ወደ ክፍሉ እየሮጠ ገባ።
"ደግ አደረግሽ ትንሽ ምላሱን አርፈን እንቆያለን"አለች እና ወይዘሮ አለም ተሳሳቁ።
ዮርዳኖስ ክፍሉ ሲገባ አልጋው ላይ አዲስ ልብስ ተቀምጦለታል።ዋው አለና አንስቶ ተመለከተው።ሰማያዊ ጅንስ ሱሪ እና ብሉ ብላክ አጀ ጉርድ ሸሚዝ።የለበሰውን ሸሚዝ አወለቀ እና አዲሱን ሸሚዝ ለበሰው ።ወደ መስታወቱ ተጠገና ራሱን እየተመለከተ ቁልፎችን ቆለፋቸው።
"አንተ ያበደ ነው ሸበላ ነው የሆንከው
"አለች እልፍነሽ በመስኮት ታይ ኖሯል ልብስ እያጠበች ።
"አረ ተይ አልፊቱ አታሹፊብኝ" አለ ዮርዳኖስ
"አባቴ ይሙት ጋሼ ምርጫ ይችላሉ"አለች እልፍነሽ
"አንቺ ግን እስከ አሁን አጥበሽ አትጨርሽም እንዴ? የዛሬው ደግሞ ከአስራ ሁለት እስከ አስራሁለት ሰዐት ነው እንዴ አጠባው"አለ ዮርዲ
"ምን ባክህ ኬኩን ላዝዝ ሔጄ ነበር ለዛ ነው"አለችው
"የምን ኬክ ነው ቆይ እናንተ ሰዎች እንዴ ዛሬ ምን የተለየ ነገር አለ።እኔና እሷ እኮ የምናከብረው እዛው ከምንገናኝበት የሾላ ዋርካ ላይ ነው።"አለ ተገርሞ
"በል ስራ አስፈታኸኝ" ብላ ወደ ልብስ አጠባዋ ገባች።እሱም መዘነጡን ተያያዘው ።አባቱ የገዛለትን ሱሪ ለበሰው እና አጁን ወደ ኪሱ ሲከተው ኪሱ ውስጥ የሆነ ነገር አገኘ።በፍጥነት አወጣው እና ሲመለከተው ትንሽ ካርቶን ነች።ከፈተው።ውስጡ ሀብል ነበር ።ከካርቶኗ አወጣ እና ሲያይ ተንጠልጣዩ ጋር ኤች H ፊደል አለ።እንዴ "አባዬ ስሜ ጠፋበት እንዴ?" አለና አንገቱ ላይ አንጠልጥለው።ዝንጥ ብሎ ከክፍሉ ወጣ እና ወደ ጓዳ ተመለሰ።
"ትፍ ትፍ ከአይን ያውጣህ ልጄ! አንተ 18ኛ አመትህን እንኳን ስታከብር እንደዚህ አልዘነጥክም።"አለች እና እናቱ ግንባሩን ሳም አደረገችው
"ዛሬ ምሳ ሰዓት የለንም እንዴ 9ኝ ሰዐት አየሆነ እኮ ነው"
"ምነው ራበህ እንዴ" አለች ወይዘሮ አለም
"አይ እንደሱ እንኳን አይደለም ግን አባዬም የለም ብዬ ነው"አለ
"አባትህ እስኪመጣ እኔም እጨርሳለሁ ሒድ ለደሳለኝ ደውልለት የእሱም እቃ ተቀምጦለታል ቤዛ ክፍል አለልህ"አለች ወይዘሮ አለም ።
ዮርዳኖስ ግራ ተጋባ "ቆይ እነዚህ ሰወች ምን አስበው ነው?" ይሔ ሁሉ ሽር ጉድ ምንድን ነው።እናቱ ብዙ የድስት አይነት ደርድራለች ።ማህበር ያለ ነው ያስመሰለችው ።እንዲህ እንደተወዛገበ ወደ ሳሎን ሔደና ለደሳለኝ ደውሎ አሁን እንዲመጣ ነግሮት ወደ ቤዛ ክፍል ሔደና ለደሳለኝ የተቀመጠለትን እቃ አየው። ገረመው የእሱን አይነት ልብስ ነበር የቀመጠው ።ወደ ክፍሉ ይዞት ሔዶ ተቀመጠ።የ ዮርዳኖስ አባት የሁለቱን ጓደኛሞች ፍቅር ሲያወራ ውሎ ቢያድር አይጠግብም።በሁለቱ ልጆች ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ተዛምደዋል። በእድሜ ደሳለኝ አመት ይበልጣል። ደሳለኝ ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ በሶፍትዌር አንድ አመት አስቆጥሮ ነው የመጣው።ዮርዲ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ውጤት እየጠበቀ ነው።
ቀና አለና ከግድግዳው ጋር የተሰቀለውን የሔዋንን ፎቶ ተመለከተ ።"የእኔ ልዕልት ሺ አመት ኑሪልኝ"አለ ፎቶዋ ላይ እንዳፈጠጠ።
ሔዋን ቀይ መልክ ያላት፣አፍንጫዋ ሰልከክ ብሎ የወረደ፣ጥርሶቿ በስርዓት የተቸመቸሙ እና ብርሀን የሚፈነጥቁት አይኖቿ ዛጎል የሚያካክሉ ሲሆኑ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ወርዶ ወርዶ እንደቄጠማ የተነሰነሰ ጡቶቿ የአራት መከራክር ተራራን መስለው የተቀሰሩ።አጠር ያለ ቁመና ያላት እና እና ቀጠን ያለች ሰትሆን ወገቧ ችቦ አይሞላም ወገቧ ተብሎ የተዘፈነላት አይነት ሴት።በአጠቃላይ ውብ የሆነች እንስት ነች።
"አንተ እስከ አሁን አበባውን አልገዛኸውም "አለና ደሳለኝ ዮርዳኖስን ከሀሳቡ አባነነው።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

❤️ክፍል 5


.
.
.
"አፈር ብላ ጥላ ቢስ ሳታንኳኳ ትገባለህ እንዴ?"አለ ዮርዳኖስ
"ሙሽራው ዘንጠሀል ዮርዲ ሙት እንዴት እንዳመረብህ"አለ ደሳለኝ "ባክህ ይሔንን ልበስ እና ማን እንደዘነጠ ትነግረኛለህ።"አለና ዮርዳኖስ አባቱ የገዛላቸውን ሰጠው ።" አረ በለው ማች ማድረግ ግን ፋዘርየ ተቸገሩ" አለ የለበሰውን ልብስ አውልቆ አዲሱን እየለበሰ።
"አሱን ተወው እና በዚህ ተበልጠሀል" ብሎ ዮርዳኖስ ሀብሉን ከሸሚዙ አውጥቶ አሳየው ።
"አንተ ምን ነክቶህ ነው አሱን እኮ ለሔዋን እንድትሰጣት ነው ፋዘርየ የገዛው ፍጠነህ አውልቅ"አለ ደሴ እየሳቀ
"አንተ ደግሞ ይሄን የት አወቅክ? እኔ እኮ ኤች ፊደል ምንድን ነው እያልኩ ነበር ለካ ሔዋን! ነው ምን አይነት ቀሽም ነኝ በናትህ "አለ ዮርዲ ።
"ስማ ፋዘርየ በቃ ብቸኛ ወንድ ልጅ ስለሆንክ እንደዚህ ያቀብጥሀል የእኔ አባት ቢሆን እንኳን ፍቅር የጀመርኩበትን ሊያከብርልኝ እንዳፈቀርኩ ስነግረው ነው ገና ከቤተሰቡ ዜግነቴን የሚነጥቀኝ ።"አለ ደሳለኝ እየሳቀ።ደሳለኝ ለብሶ ጨረሰ እና ወደ መስታወቱ ተጠጋ "እ ዮርዲ እንዴት ነኝ ?"አለ
"ዘናጭ ቁጥር አንድ፤አንተ እኮ ቅጠል ብትለብስም ያምርብሀል"
ብሎ እንደተናገረ አቶ ተሾመ ገባ ።"በለው ውበት መንታ ልጆች መሰላችኋል" አለ
"እንዴ ምንድን ነው አባዬ ራስህን ተመልክተሃል?ቆይ ምንድን ነው ነገሩ ግራ አጋባችሁኝ"እኮ አለ ዮርዲ የአባቱን ሱፍ እያደነቀ
አቶ ተሾመ ሳቀና የያዘውን ሽቶ በላያቸው ላይ አርከፈከፈው ።
"በሉ ወደሳሎን ኑ ምግብ ቀርቧል።"ብሎ ትቷቸው ወደ ሳሎን ሔደ።
"ደሴ የምታውቀው ነገር ካለ ንገረኝ ሰው ሁሉ ምን ሆኗል?"አለ ዮርዲ
"በል ነገር አትፈልፍል ምሳ አልበላሁም መብላት እፈልጋለሁ"አለ ደሳለኝ
"የዛሬ ምሳ በመክሰስ ሰዐት ሆኗል"አለና ወደ ሳሎን ሲገቡ ወለሉ በቄጠማ አብዷል ።ቤዛ እና ወይዘሮ አለም ተመሳሳይ ጥልፍ ያለው ጥበብ ለብሰዋል ።እድሜ ጠገቧ አያቱ የሀበሻ ቀሚስ ለብሰው ሶፋ ጋር ተቀምጠዋል ።እልፍነሽ እንደነገሩ ዘንጣ ረከቦቱ ጋር ተቀምጣለች።ዮርዲ እና ደሴ የዮርዳኖስን አያት ጉልበታቸውን ስመው ተመርቀው ወደ ምግብ ጠረጴዛው ሔደው ከእነ ቤዛ ጋር ተቀላቀሉ ።ወይዘሮ አለም ወደ ደሴ ጆሮ ጠጋ ብላ "መልዕክቴን ለእናት አባትህ አድርሰሀል?"ብላ አንሾካሾከች ።
ደሳለኝ አዎንታውን በምልክት ለገሰ።
ዮርዳኖስ አሻግሮ ሲመለከት ሶስት ካሳ ቢራ ተደርድሮ አየ።"አንተ ደሴ ምንድን ነው ከእኔ የተደበቀው?"አለ ዮርዳኖስ ደሴን ተጠግቶ
"ሊያገባ ነው "አለ ደሴ
"ማነው የሚያገባው ?"አለ ዮርዲ ደንግጦ
"አቶ ተሾመ "አለና ደሴ ሳቀ። አነጋገሩ ስለገረመው ዮርዲ እየተናደደ ቢሆንም ሳቀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምግብ አንደነገሩ ተቀማመሰ እና እልፍነሽ ቡና ልታፈላ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች ።በር ተንኳኳ ። እልፍነሽ ልትከፍት ሔደች
"ቤት ለእምቦሳ"ብለው የደሴ ቤተሰቦች ገቡ ።
"እምቦሳ እሰሩ "ብለው የዮርዳኖስ ቤተሰቦች ሰላምታ ተለዋውጠው ቦታ ስጥተው አስቀምጧቸው ።
"ሙሽራው ና እስኪ ይሔን አስቀምጥ"አለና የደሴ አባት አቶ ሀብቴ የተጠቀለለ ጠርሙስ ለዮርዲ ሰጠው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"አንተ ደሴ 11:30 ሆነ እኮ ሔዋንን እናግኛት"አለ ዮርዲ
"ተረጋጋ ሰዓት አለን ፥ደግሞ ደውላልኝ ነበር ስትጨርስ እንደምትደውል ነግራኛለች።"አለ ደሴ
"እሺ አንተ ግን እኛ ላይ ነው የምታድረው።ያንን ቢራ አመድ ስናደርገው ነው የምናድር።መቼም ምክንያቱ ባይገባኝም ድግስ ተደግሷል ድግሱን ትተህ አትሔድም "አለ ዮርዲ
"ትጠራጠራለህ እንዴ የትም አልሔድም። ሰማ ሳልረሳው ሔዋን የግጥም ደብተርህን አዘጋጅተህ አስቀምጥልኝ ብላለች" አለ ደሴ
"ምነው ለምን ፈልጋው ነው"
"ዘልዛላ ነው በስነ ስርዓት አያስቀምጥም "አለችኝ አለ ደሴ
"አትዋሻ !"አለ ዮርዲ
"ዮርዲ ሙት እንደዛ ነው ያለችኝ"አለ ደሴ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከደቂቃዎች በኋላ የግቢ በር ተንኳኳ ።እልፍነሽ ሔዳ ከፈተችው።
ቤት ውስጥ የነበሩ አይኖች በሙሉ ወደ በሩ ተወረወሩ ።
ዮርዳኖስ ግን አፉን ከፍቶ ቀረ።
"ደሴ ህልም ነው በለኝ ምንድነው የማየው"አለ እየተንተባተበ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​‍ 😋ሰሜናዊት ሙሽራ😋

💞ክፍል 6


.
.
.
"ደሴ ህልም ነው በለኝ።ምንድን ነው የማየው?"አለ ዮርዲ እየተንተባተበ ።
"ሙሽራው አታስፎግራ ቀብረር ብለህ ቁም።ቤተሰብ ትውውቅ መሆኑ ነው"አለ ደሴ ዮርዳኖስን ጠጋ ብሎ
"የምን ቤተሰብ ትውውቅ ?እኔ የሔዋንን ቤተሰቦች አላውቃቸውም?ወይስ የእኔ ቤተሰብ ሔዋንን ከእነ ቤተሰቧ የማያውቅ መሆኑ ነው?አንድ ሰፈር ውስጥ ለብዙ አመታት እኮ ኖረናል።ደሴ አባዬ ምን እያደረገ እንደሆን ምንም ሊገባኝ አልቻለም።"አለ ዮርዲ
"አንተ ፈገግ በል ሔዋን እያየችህ ነው አታስደብራት"አለ ደሴ
ዮርዳኖስ የግዱን ፈገግ ብሎ ለቤተሰቡ ሰላምታ ሰጠ።ሁሉም ቦታ ቦታውን ይዞ ተቀመጠ።የደሳለኝ እናት አና አባት አንድ ሶፋ ላይ፣የሔዋን ቤተሰቦች አብርሀምን ጨምሮ ሌላ ሶፋ ላይ ።ደሴ፣ዮርዲ እና አቶ ተሾመ አብረው ተቀምጠዋል።ቤዛና ወይዘሮ አለም መስተንግዶውን ተያይዘውታል ።እልፍነሽ ቡናውን እያደራረሰች ነው።
ዮርዳኖስ በሀፍረት ሽምቅቅ እንዳለ ቀና ብሎ ሔዋንን ተመለከታት ።በጥበብ አሸብርቃ ሙሽሪት መስላለች።"ሺ አመት ኑሪልኝ የእኔ ልዕልት።"አለ በውስጡ ።አይኑን ከእሷ ላይ መንቀል አልቻለም።የእሱ አልመስልህ አለችው ።ደሴ በጫማው እረገጠ እና "አረ ፍሬንድ ንቃል ምንሼ ነው "አለ ደሴ
"ወይ አፈጠጥኩ እንዴ "አለና በሀፍረት አንገቱን ደፋ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቡናው ተጠጥቶ፣ምግቡ ተበልቶ አሁን ቢራ ተከፍቶ ጨዋታው ደርቷል ።አቶ ተሾመ ደሴን አጁን ይዞ ወደ ኮሪደሩ ወሰደው እና የሆነ ነገር አንሾኳሽከው ተመለሱ።አቶ ተሾመ ሔዶ ሲቀመጥ ደሴ ከምግብ ጠረጴዛው አጠገብ ቆመና አጨበጨበ።ጆሯችሁን አውሱኝ ለማለት ነበር።ሁሉም በፀጥታ ወደ ደሳለኝ ዞሩ።
"በመጀመሪያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለመጣችሁ በአቶ ተሾመ እና በወይዘሮ አለም ስም ምስጋናየን አቀርበዋለሁ ።"ጭብጨባ ተከተለ።
"በመቀጠል ወንድሜ ዮርዳኖስ እንዲሁም እህቴ ሔዋን እንኳን ለሁለተኛ አመት የፍቅር ጅማሪያችሁ አደረሳችሁ እያልኩ ኬኩን እንድትቆርሱ እጋብዛችኋለሁ ።"አለ ደሴ ።ሔዋን እና ዮርዲ በጭብጨባ ታጅበው ወደ ምግብ ጠረጴዛው አመሩ።ኬኩን እየቆረሱ ቤዛ ፎቶ አነሳቻቸው ።ደሳለኝ ምስጋና አበርክቶላቸው ወደ መቀመጫቸው ሸኛቸው ።
"በመቀጠል ወንድሜ ዮርዳኖስ ለሔዋን ስም እንዲያወጣላት እና አንዲዘፍንላት ።እጋብዛለሁ ።"አለ ደሴ ።ጭብጨባ ተከተለ ።
ዮርዲ ያላሰበውን ዱብዳ ነገር ደሴ ሲያወርድበት በድንጋጤ ድርቅ ብሎ ቀረ።ሁሉም መነሳቱን እየጠበቁ እንደሆነ ሲመለከት የግዱን ፈገግ ብሎ ተነሳ ።
"እሺ በቅድሚያ ለዚች ልዕልት ልጅ ስም እንድታወጣላት ዕድል ሰጠሁህ "አለ ደሴ እየሳቀ
ዮርዲ በድንጋጤ ብዛት አፍንጫው ላይ ችፍፍ ያለውን ላቡን በእጁ ሞዠቀ እና መናገር ጀመረ።
"በመጀመሪያ ያላሰብኩት ነገር ስለተፈጠረ መደንገጤን አልክድም ። እንደዚህ አይነት ፕሮግራምም ሰርፕራይዝም አጋጥሞኝ አያውቅም ።ሁላችሁንም ላመሰግን እወዳለሁ ።ሲቀጥል ለዚች እንደ ከዋክብት ለምታበራ ልጅ የሚመጥናት ስም ባይኖረኝም "ሳልዕሳዊት"ብየ አውጥቼላታሉሁ "አለ ዮርዲ
"ትርጉም "አለ ደሴ እየሳቀ
"ትርጉሙ ሶስተኛዋ ማለት ነው "አለ
"ሶስተኛዋ ምን?"አለ የሔዋን አባት አቶ አንድነት
ደሳለኝ ቀለብ አደረገና "እንግዲህ እኔ ሲመስለኝ በአስራ ስምንት አመት ውስጥ ያፈቀራት ሶስተኛዋ ሴት መሆኑ ነዉ።"አለና ሳቀ።የእሱን መሳቅ ተከትሎ ቤቱ በሳቅ ተናጋ።
ዮርዲ ሳቁ ጋብ እስኪል ጠበቀና"እንተ ብቻችንን ስንገናኝ ትነግረኛለህ"አለ ዮርዲ ደሴን በፍቅር ጎሸም አድርጎ ።ቀጠለና"ሔዋን ማለት ለእኔ ከእናቴ እና ከእህቴ ቀጥሎ ያገኘኋት ሶስተኛዋ ሴት ነች ።ስለዚህ ሳልዕሳዊት ።ተናግሮ ሳይጨርስ ጭብጨባ ቀደመው ።
"ዝፈንላት ላላችሁት ሁለት አመት ሙሉ ዘፍኜላት ክር ጨርሻለሁ ።እንደማፈቅራት ንገሩልኝ" አለና ሀብሉን ከደረት ኪሱ አውጥቶ ሔዶ አንገቷ ላይ አደረገላት እና ግንባሯን ሳም አድርጎ ወደ መቀመጫው ተመለሰ።ጭብጨባ ተከተለ።
"አሁን ደግሞ ለአቶ ተሾመ መድረኩን እለቃለሁ ።"አለና ደሴ እየሳቀ ወደ ቦታው ተመለሰ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ ተሾመ ተነሳና መናገር ጀመረ ።"በመጀመሪያ ልጄ ዮርዲ ላመሰግንህ እወዳለሁ ።በአንተ ምክንያት ከሁለት ቤተሰብ ጋር ተዛምጃለሁ።ከሔዋን ቤተሰቦች እና ከደሴ ቤተሰቦች።እኔ እና የሔዋን አባት አቶ አንድነት ተመካክረን ስጦታ ገዝተናል ።እሱም ምንድን ነው እ....እንግዲህ ልቦቻችሁ በፍቅር ተሳስረዋል ።እኛ ደግሞ በቀለበት ልናስተሳስራችሁ ወደድን።"አለና የቀለበት ፓኬቱን ለዮርዳኖስ ሰጠው ።
ቀለበቱን አጠለቀላት እሷም እንደዚሁ ።ቤቱ በዕልልታ እና በጭብጨባ ድብልቅልቅ አለ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ፕሮግራሙ ተጠናቀቀ ።የደሳለኝ ቤተሰቦች እና የሔዋን ቤተሰቦች አመስግነው ወደ እየቤታቸው ተበተኑ ።
ሔዋን፣አብርሃም እና ቤዛ ስፕራይት ይዘው ደሳለኝ እና ዮርዳኖስ ደግሞ ቢራ እየጠጡ።የዮርዳኖስን ክፍል በአንድ እግሯ እስክትቆም ድረስ በሳቅ በጨዋታ አመሹ ።
ሔዋን ስልኳን ተመለከተች 3:08pm ይላል ።"እንግዲህ ሸኙን ሊነጋ እኮ ነው"አለች እየሳቀች
"ገና በሶስት ሰዐት "አለች ቤዛ
"አይ መሽቷል ይሒዱ" አለና ዮርዲ ተነሳ ።ከመሳቢያው ውስጥ ደብተሩን አወጣና "ይሔዉ አዘጋጅ የተባልኩት የግጥም ደብተር"አለና ለሔዋን ሰጣት ።
ተቀበለችው እና በተራዋ አብርሀምን ፖስታ ተቀብላ"ይሔው ስጦታየ "ብላ ለዮርዲ ሰጠችው ።
መሳቢያው ውስጥ አስቀመጠው ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ደሳለኝ እና ዮርዳኖስ ሔዋንን እና አብርሀምን ይዘው እነ ሔዋን በር ደረሱ ።ሔዋን መጀመሪያ ደሴን አቅፋው ደህና አደር አለች እና ወደ ዮርዲ ተመለሰች ።
ዮርዲ ትክ ብሎ ተመለከታት ።እነኛ ውብ አይኖቿ እንባ ቋጥረዋል።
"ምነው እማ ምን ሆንሽብኝ"አለ እንባዋን እየጠረገላት
"ደስ ስላለኝ ነው "አለችው እና ከንፈሩን በከንፈሯ ከደነችው ።
አንገቱ ውስጥ ሆና "ጠብቀኝ"አለችው
"እማ ግን ደህና ነሽ ?"አለ ዮርዲ
"ፖሰታውን ነገ ክፈተው "አለች እና ጥብቅ አድርጋ አቅፋው" ደህና እደር "ብላ እያለቀሰች ከአብርሃም ጋር ተያይዘው ገቡ።

ይቀጥላል
​​‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 7


.
.
.
ከአስር አመት በፊት .....................................
ከኮረብታማው ጥንታዊ አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ግርጌ ድሮ በጣሊያን ወረራ ጊዜ በጣሊያን ይዞታ ውሰጥ የነበረው እና ጣሊያን በአባት አርበኞች ድባቅ ተመታ ሴራዋ ተንኮላሽቶ አፍራ ስትመለሰ ስራ ያቆመው የድንጋይ ወፍጮ እና ሴራሚክስ አምራቹ ሰፊ ግቢ በ1999 ዓ.ም እደሳ ተደርጎለት ስራ ጀመረ ።ባላ ሀብቱ ከአዲስ አበባ መጥቶ የገዛው ሲሆን ስሙ ኢሳያስ ተ/አረጋይ ይባላል ።የደብሩ አስተዳዳሪ እና ጠባቂ የአባ ቶማስ ዘመድ ነው አሉ እየተባለ ጭምጭምታ ይሰማል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጥንታዊው አምበር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተው ሁለቱ ወንድማማቾች ማለትም አብርሀወአጵብሀ ወይም ኢዛና እና ሳኢዛና ኢትዮጵያን ይገዙበት በነበረበት ዘመን ክርስቶስ ከተወለደ 300 አመት ገደማ እንደተመሰረተ አባቶች ይናገራሉ።ቤተ ክርስቲያኗ በግራኝ አህመድ ወረራ ጊዜ የጥፋቱ ገፈት ቀማሽ እንደሆነች እና እንደተቃጠለች አንዳንድ የታሪክ መፅሐፍት አና አፈ ታሪኮች ያስረዳሉ።ከዚህ በተጨማሪ ግን ለአካባቢው ማህበረሰብ እንቆቅልሽ ሆኖበት እየኖረ ያለው ነገር ከደብሯ በሰተ ደቡብ በኩል ያለው ሰፊው ኮረብታማ ቦታ ነው።ቦታው አጅግ የሚያስገርም ከመሆኑ በተጨማሪ ሲቆሙበት የሚያሰማው ድምፅ ለእንግዳ ሰው በድንጋጤ ይገድላል።ቦታው ሲረግጡት የሚያወጣው ድምፅ ከከበሮ አይተናነስም ።ህብረተሰቡ ውስጡ ዋሻ ሰለሆነ ነው አንደዚህ የሚጮኸው ይላሉ ።እውነት አላቸው።አዎ ዋሻ ነው ማረጋገጫው ደግሞ ከኮረብታው ምስራቃዊ አቅጣጫ ወረድ ብሎ ለዋሻው መግቢያ ተብሎ የተሰራ በሚመስል መልኩ ቅርፅ አልባ መስኮት መሳይ ቀዳዳ አለ።በተለምዶ የዘንዶው ዋሻ በር ተብሎ ይጠራል። ጥንት አባቶች እና እናቶች ንብረታቸውን ከጠላት ለማሸሽ የቆፈሩት ዋሻ ነው ይባላል ።ወስጡ መንፈሳዊ የሆኑ እና መነሰፈሳዊ ያልሆኑ ሀብቶች እንደተደበቁ እና በዘንዶ እንደሚጠበቅ ሰፊው ማህበረሰብ ብትጠይቀው የሚሰጥህ መልስ ነው።ወደ ውስጥ ግን ማንም አልገባም ማንም ሊገባ አልሞከረም።ምክንያቱም የዘንዶ እራት መሆን የሚፈልግ የለም።እየተባለ ይወራል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከአምስት አመት በፊት ........................
የሔዋን ትልቅ ወንድም የአቶ አንድነት የግል ልጅ ምናሴ አንድነት ይህን የጥንታዊ ቅዱስ ቂርቆስ አስገራሚውን ኮረብታማ ቦታ ጎብኝቶ የተመለሰ ማግስት የውሀ ሽታ ሆነ።የአካባቢው ኗሪ የዮርዳኖስን ቤተሰቦች ጨምሮ ምናሴ የት ደረሰ ብለው ጠየቁ።የሔዋን ቤተሰቦችም ምናሴ ዲቪ ደርሶት አሜሪካ ሔደ ብለው ተናገሩ ።ኗሪው የአቶ አንድነት ልጅ አሜሪካ ሔደለት ብለው የአቶ አንድነትን ቤት በድግስ አስጨንቀውት ሰነበቱ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከአንድ አመት በፊት .....................................
"እሰኪ ስለ ስደት ምን ትያለሽ ?"ሲል ሔዋንን ዮርዳኖስ ጠየቃት
"ህዝባችን እኮ ኑሮን ለማሸነፍ ቤተሰብ ለመርዳት ራስን ለመለወጥ ብሎ ከእናት ሀገሩ እየወጣ በበረሃ የጊንጥ ሲሳይ በባህር ደግሞ የአሳ ነባሪ እራት እየሆነ ፣ገሚሱ ደግሞ አልሳካለት ብሎ ተጠርዞ ሲመለስ ተስፋ ቆርጣ ፤የዚች ምስኪን ሀገር እጣፈንታ እርሱ ትክሻ ላይ መሆኗን ዘንግቶ በሱስ እየዳከረ የሱን ህይወት አባላሽቶ እሱን እያዩ ለሚያድጉ ታናናሽ እህት እና ወንድሞቹ ነገን እንዳያዩ የአይን ቆብ ሆኖባቸው የተሸከመውን የሀላፊነት ቀንበር ከ ጫንቃው ላይ ጥሎ ለቤተሰብም ለሀገርም ሸክም ይሆናል።ተሳክቶለት የወጣውም በአፍ ብቻ እናት ሀገሬን እወዳታለሁ።ከማለት ውጭ ለዚች ሀገር ምን የፈየደላት ነገር አለ?እንዲያውም የዚች ምስኪን ሀገር ጥሪት ሊያጫርስ ከነጫጭባ ፈረንጅ ባላንጣ ጋር ሆኖ ለወጥመዱ ሽቦ ሲያቀብል ይውላል። እስኪ የእኔን ወንድም ምናሴን ተመልከት ።ለእናት ሀገሬ እሞታለሁ እኔ የምኖረው እሷ ስትኖር ነው ።ጥርኝ አፈሯን ልሼ እንዳደኩ ሁሉ የላስኩባትን ጥርኝ አፈር ወርቅ አድርጌ እመልስላታለሁ እያለ ኖሮ እድል ሲቀናው ይኸው ትቷት ሔደ።ምን አደረገላት?ምንም።ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች በእስኮላር መልኩ ይወሰዳሉ ።ተምረው መጥተው ለዚች ሀገር የፈየዱት ነገር አለ?የለም።የእግሯን እሾህ በመርፌ ለመንቀስ የሞከረ ምሁር እስከ አሁን አላየሁም አልሰማሁም ።በሔዱበት ሀገር እስረኛ ሆነው ይቀራሉ ።እስኪ እሩቅ ሳንሔድ ከዚው ከመንደራችን እንነሳ ።እንዳወቀ ካሴ ምሁር ይባላል ።ሳይንቲስት ይባላል ።ግን ሳይንቲስት ሆኖ ለዚች ሀገር ምን ጠቀማት?ይልቅ በችግር ማቃ የሞተችውን እናቱን ለመቅበር በእልፍ አእላፍ የፈረንጅ ወታደር ታጅቦ።መጣ።አስቀበረ።እንባው እንኳን ሳይደርቅ ነበር አንጠልጥለው የወሰዱት ።ይሔ ዘመናዊ ባርነት አይደለም ?አየህ የአገርህን ሰርዶ በአገርህ በሬ ድሮ ቀረ። የአገርህን ጥሪት የአገርህ ልጆች
አሳልፈው ሰጡ ለፈረንጆች ።ብሎ አገሬው መተረት ከጀመረ ቆይቷል ።ይቺን ሀገረ እግዚአብሔር ይቺን የተስፋ ምድር የቺን የቃል ኪዳን ሀገር ኢትዮጵያን ፤ቀቢፀ ተስፋ በልባችን ያደረብን ወጣቶቿ ከተስፋ መንገድ እየራቅን በትንሳኤዋ ፋንታ ተስፋዋን እያጨለምን እኛ ሌላ ሀገር እንሽታለን ።የእኛን ቤት እያፈረስን ለባዕድ አገር ምሰሶ እንተክላለን ።"ብላ በምሬት ስትናገር ቆይታ "የግል አሰተያየቴ ነው"አለችው።

ይቀጥላል