ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
1.03K subscribers
2.92K photos
44 videos
102 files
787 links
ይኽ በፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች የሚለቀቁበት ሚዲያ ነው።
https://linktr.ee/kaletsidkizm
Download Telegram

#ስለ_ጌታችንና_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተመሰሉ_ምሳሌዎች

ነቢያት ሱባኤ እየገቡና ምስጢር እየተገለጠላቸው ስለ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት ተናግረዋል ምሳሌም መስለዋል፡፡ ከተመሰሉት ምሳሌዎች በጥቂቱ ለመመልከት እንሞክር፡፡

#የዳዊት_መሰንቆ፡- ከዳዊት መሰንቆ የሚወጣው ድምጽ ሕሙማን ይፈወሱ ነበር፡፡ በዚኽም መሰንቆው የእመቤታችን የድንግል ማርያም ከመሰንቆው የሚወጣውም ድምጽ የጌታችን ምሳሌ ኾኗል፡፡ ከመሰንቆው በሚወጣው ድምጽ ሕሙማን እንደተፈወሱ ከድንግል ማርያም በተወለደው በመድኃኔዓለም ድኅነተዓለም ተገኝቷል፡፡

#ምስራቅ፡- ምስራቅ የእመቤታችን ፀሐይ የጌታችን ምሳሌ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ጸሐየ ጽድቅ› እንዲል፡፡

#ሶምሶን፡- ሶምሶን በሕይወቱ ካጠፋቸው በሞቱ ያጠፋቸው እንደሚበዙ ጌታችንም በሕማሙ በሞቱ ሠራዊተ ጽልመትን አጥፍቷልና፡፡

#ገራህተ_ሙሴ፡- ሙሴ ጌታችንን ፊትህን ላይ እወዳለኹ ባለው ጊዜ ጌታችን ‹ዘር ካልተዘራባት ምድር የበቀለች ስንዴ ብትሰዋልኝ እታይኻለኹ› ብሎታል (ዘፀ 33፡12-23)፡፡ በዚኽም ገራህት የእመቤታችን፣ ስንዴ የጌታ ምሳሌ ሲኾን የጌታችን ቃል ምስጢር ‹‹ከድንግል ተወልጄ መስዋዕት ኾኜ አድንኻለኹ›› የሚል ነው፡፡

#ዮሴፍ፡- ዮሴፍ ወንድሞቹ ተመቅኝተውት በ20 ብር ሸተውታል (ዘፍ 38፡28)፤ ጌታችንንም ደቀመዝሙሩ ይሁዳ በ30 ብር ሸጦታል፡፡ የዮሴፍ ወንድሞች ከሸጡት በኋላ ልብሱን በጠቦት ደም ነክረው ለአባቱ አሳይተውታል፡፡ በዚኽም ልብሱ የትስብእት ዮሴፍ የመለኮት ምሳሌ ይኾናል፡፡ ደሙ ከልብስ እንጂ ከዮሴፍ አለመገኘቱ ሕማምና ሞት ለትስብእት እንጂ ለመለኮት ላለመኖሩ ምሳሌ ነው፡፡

#ይስሐቅ፡- ይስሐቅ አባቱ እንደሚሰዋው እያወቀ በእጁ እሳት በጀርባው እንጨት ተሸክሞ እንደተከተለው ጌታም የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ ቀራንዮ ወጥቷልና ይስሐቅ የጌታ ምሳሌ ኾነ፡፡

#ከራድዮን፡- ሰው ሲታመም ከራድዮን ወይም ዖፍ ጸዓዳ ወደተባለው ወፍ ይወስዱታል፡፡ ሰውየው የሚሞት ከኾነ ፊቱን ይመልስበታል የሚድን ከኾነ ደግሞ ቀርቦ አፉን ከአፉ ጋር ቀጥሞ እስትንፋሱን ይቀበለውና ይድናል፡፡ በዚኽም ከራድዮን የጌታችን፣ ሕማሙ የአዳም፣ ቀርቦ እስትንፋሱን መቀበሉ ደግሞ ጌታችን የአዳምን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ የተፈረደበትን መከራ ተቀብሎ ለማዳኑ ምሳሌ ነው፡፡

ውድ አንባቢያን እነዚኽን ስንተቅስ ኹሌም ቢኾን ምሳሌ ከተመሰለለት ነገር የሚያንስ መኾኑን በማስታወስ ነው፡፡


🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳
ይኽ የፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ቻናል ነው። 👇👇👇
@kaletsidkzm @kaletsidkzm