ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
1.02K subscribers
2.78K photos
44 videos
102 files
781 links
ይኽ በፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች የሚለቀቁበት ሚዲያ ነው።
https://linktr.ee/kaletsidkizm
Download Telegram
የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚደረግ ሥርዓተ ጸሎት ይጀመራል !!!

በወሊሶ አካባቢ በ"አባ" ሳዊሮስ መሪነት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ "የኤጲስ ቆጶሳት" ሢመትን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሠረት ከእሁድ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እየገቡ የሚገኙ ሲሆን አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት አመሻሽ ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚደረግ ሥርዓተ ጸሎት የሚጀመር ይሆናል።


በርካታ አህጉረ ስብከት የተፈፀመውን የቀኖና ጥሰት አስመልክቶ እንደማይቀበሉት እየገለፁ የሚገኙ ሲሆን መላው ኦርቶዶክሳውያን በአሁኑ ሰዓት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በፍፁም ክርስቲያናዊ ትዕግስት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። በሕገ ወጠሰ መንገድ "ኤጲስ ቆጶሳት" ተብለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር የተላኩት መነኮሳት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሆቴሎች በመዘዋወር እየኖሩ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።


#አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriarch
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox

"ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" ጸሎተ ሃይማኖት
🌿ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።
🌿 “ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።”
— መዝሙር 102፥17

ልዩ የጸሎት መርሐ ግብር
በቤተክርስቲያናችን በተነሳው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት የተዘጋጀ ልዩ የጸሎት መርሐግብር ለወዳጅ ዘመዶ በማጋራት በተጠቀሱት ቀናት እንገኝ።
#አንድ_ፓትርያርክ
#አንድ_መንበር
#አንዲት_ቤተክርስቲያን

🌿 ከጥር 18–20 ቀን 2015 ዓ.ም
ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ
⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ

ኑ በአንድነት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወደ ፈጣሪያችን በጋራ እንጸልይ
🌿ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።
🌿 “ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።”
— መዝሙር 102፥17

ልዩ የጸሎት መርሐ ግብር
በቤተክርስቲያናችን በተነሳው ወቅታዊ ፈተና የተዘጋጀ ልዩ የጸሎትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ለወዳጅ ዘመዶ በማጋራት በተጠቀሱት ቀናት እንገኝ።

#አንድ_ፓትርያርክ
#አንድ_መንበር
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
🌿 ከጥር 25–27 ቀን 2015 ዓ.ም

ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ
⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ

ኑ በአንድነት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወደ ፈጣሪያችን በጋራ እንጸልይ
ቤተ ክርስቲያናችን እንደወትሮው ሁሉ አሁንም መከራ አልተለያትም:: በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ እየተቀበልን ጸንተን መቆም የሚጠበቅብን ሲሆን በሚከተለው መንገድ ደግሞ ቤተ ክርስቲያናችንን እንድናግዛት በአክብሮት እጠይቃለሁ:: (መቼም ጸልዩ ማለት የዲያቆን ሥራ ነው)

የክርስቲያኖች ትልቁ መሣሪያችን እጃችንን ለጸሎት ወደ ሰማይ መዘርጋት ነው:: ዕንባችንም እንደ ራሔል ዕንባ ባሕርን ይከፍላል:: ራሳችንን በንስሓ ካዋረድንና ካለቀስን የማንቀለብሰው ነገር የለም::

የፊታችን ሰኞ የሦስት ቀናቱ ጾም ጾመ ነነዌ ይገባል::

ጾሙ ከመግባቱ አስቀድሞ ኦርቶዶክሳውያን ሁላችን ንስሓ እንግባ:: በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ይህንን ያያችሁ ወንድሞቼና እኅቶቼ ሁላችሁ ንስሓ አባቶቻችሁን ምስክር አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ:: "ጌታ ሆይ ይህ የሆነው በእኔ በደል ነውና ኃጢአቴን ይቅር በለኝ" ብለን አብረን አምላካችንን እንማጸነው::

ከዚህ ንስሓ ጋር የታወጀውን የየነነዌ ጾም ጠዋት በኪዳንና ከሰዓት በቅዳሴ ማታ ደግሞ በጸሎተ ምሕላ በየአጥቢያችን እየተገኘን አምላካችንን እንማጸነው::
የቻልን ሦስቱን ቀናት እስከ ማታ እየጾምንና እየሰገድን የፈጣሪያችንን ምሕረት እንለምን::

በሦስት ቀን ጾም የነነዌን መዓት የመለሰ : በሦስት ቀን ጾም የግብፅን ተራራ ያፈለሰ የነስምዖን አምላክ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመጣ ያለውን እሳት ሁሉ በቸርነቱ ይመልስልን ዘንድ በልባችን ጉልበት እንስገድ::

ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የተለዩትን እንዲመልስልን!
በዚህ ምክንያት የሚጠፉ ነፍሳትን እንዲጠብቅልን!
የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መናወጽ የሚሻውን ሁሉ እንዲያስታግሥልን ወደ ፈጣሪያችን በጋራ እንጩኽ::

በየጊዜው ለችግራችን ስእለት እንደምንሣለው አንድ ጧፍ እንኩዋን ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ስእለት አድርገን እንጸልይ:: አርከ መሀይምናን (የምእመናን ወዳጅ) ለቤተ ክርስቲያንም ቅን መሪን የሚሠጥ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ስለሚማልሉ የዋሃን ብሎ ሰላማችንን ይመልስልን::

"እግዚአብሔር እንዳይቀየማቸው ከመዓትም ተመልሶ ፍጹም ዕረፍትን ይሠጣቸው ዘንድ ስለ በደሉ አባቶቻችንና ወንድሞቻችን እንማልዳለን" በእንተ ቅድሳት

#ነነዌ_ኢትዮጵያ
#ንስሓ_ግቡ
#ትጉና_ጸልዩ
#አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriarch
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox
ሺህ ጉድጓድን ምሶ - ሊቀብረው ለሚያስብ፣
ለካስ ሕዝቡ ዘር ነው - የሚበቅል የሚያብብ፤
+
የአመክንዮው ቀመር - መች እዚህ ሠራና፣
ፈርቶ ይሸሻል ሲሉ - ሰፋ ክርስትና፤
+
ሺህ ቆራጭ ቢላክም - ለመመልመል ግንዱን፣
ቅርንጫፉ በዝቶ - ጫካ አረገው አንዱን፤
+
ምን ዓይነት ግንድ ነው - በጨለማ ዘመን - በሌሊት ያጤዛል፣
መልማዮች ሲፈሉ - ስለት ሲወረወር - ቅርንጫፉ ይበዛል፤
+
አሩሩን ተማምኖ - ኔሮን ቢደነፋም - ሰይፉን እየሳለ፣
የሰማዕትን ደም - በጠጣ አፈር ላይ - ሺህ አማኝ በቀለ፤
+
ንገሩት በጥብዐት - ፍቅር ባለው ድምጸት - ከሰማ ሲመከር፣
እነ ሱስንዮስ - ይህን ክፉ መንገድ - ሞክረውት ነበር፤
+
ይህ ሕዝብ ምስማር ነው - ብርታቱ የላቀ
በተመታ ቁጥር - እጅጉን ጠበቀ።
+++

ዲ/ን ሕሊና በለጠ
የካቲት 1፣ 2015 ዓ.ም.

#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ