ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
1.03K subscribers
2.95K photos
44 videos
102 files
788 links
ይኽ በፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች የሚለቀቁበት ሚዲያ ነው።
https://linktr.ee/kaletsidkizm
Download Telegram
#የጸሎት_ማሳሰቢያ | #ቃለ_ጽድቅ_ዘመካነ_ሕይወት

የሰንበት የሐሙስ ጸሎት በወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ላልተወሰነ ግዜ የተዘጋ ቢሆንም ይህንን ወቅት አልፈን ከደጉ ዘመን እንዲያደርሰን እና ይቅር እንዲለን እንዲሁም በአገልግሎታችን እንድንበረታ ጸሎት ዋነኛ መሳሪያችን ነውና በየቤታችን ሐሙስ መጋቢት 24/2012 ዓ.ም. የቻልን ሰርክ፣ ካልቻልን ምሽቱ ከ3:00 ወይም ከምሽቱ 6:00 በአንድ ልብና በአንድ ሀሳብ የምንጸልየውን የጸሎት ይዘት ከዚህ በታች ባለው መሠረት እንድንጸልይ ተቀምጦልናልና ሳንዘናጋ እንጸልይ:: የበረታን ደግሞ ጨምረን ብጸልይ መልካም ነው፡፡

ክፍል ፩ ፦
• የዘውትር ጸሎትን---እስከ እናታችን ማርያም ሆይ
• ውዳሴ ማርያም የዕለቱን
• ይዌድስዋን በማድረስ
• ጸሎታ ለማርያም ወስዕለታ ያድኅነነ እምዓተ ወልዳ --- የሚለውን ከዚህ በታች ያለውን መጸለይ
እግዝእትነ (2) ነፅሪ ኃቤነ ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ምስሌነ (3)

ጸሎታ ለማርያም ወስዕለታ ያድኀነነ እምዓተ ወልዳ

ጸሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለሕዝበ ክርስቲያን ይዕቀቦ እምዓተ ወልዳ

ፀሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለነፍሳተ ሙታን ያድህኖ እምዓ ተወልዳ

ፀሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ይዕቀቦ እምዓተ ወልዳ

ፀሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለመምህርነ ይዕቀቦ እምዓተ ወልዳ

ፀሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለመካነ ሕይወት ይዕቀባ እምዓተ ወልዳ

ጸሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለመካነ ሕይወት ይዕቀባ እምዓተ ወልዳ

ጸሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ይዕቀባ እምዓተ ወልዳ

ጸሎታ ለማርያም ወስዕለታ ለአግብርታ ወለአዕማታ ይኩነነ ወልዳ

ኦ ማርያም አዕርጊ ፀሎትነ ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ

በእንተ ማርያም ወላዲትከ ምህላነ ስምዓ በእዝንከ

በእንተ ማርያም ሐፃኒትከ ምህላነ ስምዓ በእዝንከ

በእንተ ማርያም ፀዋሪትከ ምህላነ ስምዓ በእዝንከ

|ሲጨርሱ የራስን የቃል ልመና አድርሶ በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር|

ክፍል ፪ ፦ መዝሙራት

#መዝሙረ ዳዊት 51

አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።

እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።

እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።
እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።

በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።

ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።

የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።

ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።

የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።

አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።

መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።

የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።

አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ።

የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።

#መዝሙር ፻፵
አቤቱ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ስማኝ፤
ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ቃል አድምጥ።
ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣንተቀበልልኝ፤
እጆቼ የሠርክ መሥዋዕትን አነሡ።
አቤቱ፤ ለአፌ ጠባቂ፤ ለከንፈሮቼም ጽኑ መዝጊያን አኑር።
ልቤን ወደ ክፉነገር አትመልሰው፤
ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኅጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤
ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
በጽድቅ ገሥጸኝ በምሕረትም ዝለፈኝ፥
የኅጢአተኛ ዘይትን ግን ራሴን አልቀባም፤ ዳግመኛም ጸሎቴ ይቅር እንዳትላቸው ነውና።
ኅያላኖቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፤ ተችሎኛልና ቃሌን ስሙኝ።
እንደ ጓል በምድር ላይ ተሰነጣጠቁ፤ እንዲሁ አጥንቶቻቸው በሲኦል ተበተኑ።
አቤቱ ጌታዬ፤ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፤ በአንተ ታመንሁ፤ ነፍሴን አታውጣት።
ከሰወሩብኝ ወጥመድ፤ ዐመፃንም ከሚያደርጉ ሰዎች እንቅፋት ጠብቀኝ።
እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ኃጥአን በወጥመዳቸው ይውደቁ።

#መዝሙር ፻፴፭
ሃሌ ሉያ
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
እርሱ ብቻውን ታላቅ ተአምራትን ያደረገ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ሰማያትን በጥበቡ የሠራ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ለጨረቃና ለከዋክብት ሌሊትን ያስገዛቸው፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ከበኲራቸው ጋር ግብፅን የገደለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
የኤርትራን ባህር ፈጽሞ የከፈለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ፈርዖንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር ውስጥ የጣለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ከዓለት ውኃን ያፈለቀ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ታላላቅ ነገሥታትን የገደለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ጽኑዓን ነገሥታትን የገደለ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎን፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
የባሳንን ንጉሥ ዓግን፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ርስት ምድራቸውን፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ለባርያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
እግዚአብሔር እኛን በመዋረዳችን ዐስቦናልና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡
የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤
ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡

#የምናሴ_ጸሎት

ዓለምን ሁሉ የምትገዛ፤
የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ የያዕቆብም የጻድቃን ልጆቻቸውም አምላክ ሆይ፤
ሰማይንና ምድርን ከዓለሞቻቸው ጋር የፈጠርህ፤ በቃልህ ትእዛዝ ባሕርን የገሠጽሃት፤
ቀላዮችን የዘጋህ፤ የሚያስፈራውንም የወሰንህ፤ ይኸውም በተመሰገነው ስምኽ ነው፤
ኀይልኽ ከመገለጡ የተነሳ ኹሉ የሚርድና የሚንቀጠቀጥ፤
ለክብርኽ ከፍተኛነት ፍጻሜ የለውምና፤ የቊጣኽም መቅሠፍት በኃጥአን ላይ ግሩም ነው፡
በትእዛዝህ ለሚሆነው ይቅርታህ ስፍር ቊጥር የለውም፤ ገናና እግዚአብሔር አንተ ብቻ ነህና፤
ይቅር ባይ፤ ከቊጣ የራቅህ፤ ይቅርታህ የበዛ፤ የሰውንም ኀጢአት የምታስተሰርይ አንተ ነህ፡፡
አሁንም፤አቤቱ፤የጻድቃን አምላካቸው አንተ ነህ፡፡
ንስሓን የፈጠርህ ለጻድቅ ሰው አይደለምና፤
አንተን ላልበደሉ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም አይደለምና፤
ነገር ግን የእኔን የኃጥኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመለስ፡፡

🔔
✥✥✥
ሰዓት
✥ተንስኡ ለጸሎት✥

#መዝሙረ ዳዊት 119 164

"ስለ ጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ" ።

በዚህ ሰዓት ይህንን የምታ
የምታደርጉትን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታዬ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ

የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታዬ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ

የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታዬ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ
🔔
✥✥✥
ሰዓት
✥ተንስኡ ለጸሎት✥

#መዝሙረ ዳዊት 118_25
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።

#በዚህ ሰዓት ይህንን የምታዩ የምታደርጉትን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ

የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን

የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን

የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን