"ቃለ እግዚአብሔር "
8.27K subscribers
611 photos
17 videos
7 files
224 links
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
Download Telegram
ተጨማሪ
#ሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

#የዘንባባ_ዝንጣፊ፡-
☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

#የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

#የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡-
☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡
facebook_1714376063595.mp4
8.5 MB
በህማማት ሳምንት ምን ይደረጋል ምን አይደረግም የሚለውን ከአባታችን ከአባ ገብረኪዳን አንደበት።
#የሰሙነ_ሕማማት_ማክሰኞ

#የጥያቄ_ቀን_ይባላል

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡

#የትምህርት_ቀንም_ይባላል፡-

በማቴ. 21፥28፣ ማቴ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ማር.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ሉቃ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱም መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

         "እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
             አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ
   እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሓ ወበሰላም!"
ከማግሥተ ሆሣዕና በኃላ ዕለተ ረቡዕ

ሰሞነ ህማማት

እለተ ረቡዕ
በቅዱስ ማቴዎስና በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላት እንደ ተገለጸው በዕለተ ረቡዕ የሚከተሉት ሦስት ተግባራት ተፈጽመዋል፤

አንደኛ የካህናት አለቆች፣ የሕዝብ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ፈሪሳውያን በጌታችን ላይ ተማክረዋል፤
ሁለተኛ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ሳለ አንዲት የተጸጸተች ሴት ሽቱ ቀብታዋለች፡፡
ሦስተኛ ከዳተኛው ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ለመስጠት ከጸሐፍት ፈሪሳውያንና ከካህናት አለቆች ዘንድ ሠላሳ ብር ለመቀበል ተስማምቷል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሹማምት በጌታችን ላይ ይሙት በቃ ለመወሰን የሰበሰቡት ሸንጐ ‹‹ሲኒሃ ድርየም›› ይባላል፡፡ በዚህ ሸንጐ ላይ በአብዛኛው የተሰየሙት ሰዱቃውያን ሲኾኑ ሌሎቹ ደግሞ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ነበሩ፡፡ ሸንጐው በአጠቃላይ ሰባ ሁለት አባላት
የነበሩት ሲኾን የሚመራውም በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ነበር፡፡ በዕለቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንደሚገድሉት አይሁድ በዚህ ሸንጎ መክረዋል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳም ጸሐፍት ፈሪሳውያንና የካህናት አለቆች በጌታን ላይ የነበራቸውን ጥላቻ ያውቅ ስለ ነበር ‹‹ምን ልትሰጡኝ ትወዳላችሁ? እኔም አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤›› በማለት ጌታችን አሳልፎ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተስማምቷል፡፡

ጌታችን ያስተምር በነበረበት ወቅት የአስቆሮቱ ይሁዳ ከምእመናን ለሚገባው ገንዘብ ሰብሳቢ (ዐቃቤ ንዋይ) ነበር፡፡ ከሚሰበሰበው ሙዳየ ምጽዋት ለግል ጥቅሙ እየቀረጠ የማስቀረት የእጅ አመል ነበረበት፡፡ ይሁዳ ፍቅረ ንዋይ እንደሚያጠቃው ድብቅ አመሉ ጎልቶ የወጣው ጌታችን በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የኾነ ሽቱ በቀባችው ጊዜ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ይሁዳ የተቃውሞ ድምፅ ካሰሙት አንዱ ነበር፡፡ ‹‹ይህ ሽቱ ተሽጦ ለድሆች ቢሰጥ መልካም ነበር፤›› በማለት ያቀረበው አሳብ ‹‹አዛኝ ቅቤ አንጓች›› እንደሚባለው ነበር፡፡ ይሁዳ፣ ሽቱ ሲሸጥ የሚያገኘው ጥቅም ነበረ፤ ሽቶው በጌታችን እግር ሥር ከፈሰሰ ለእርሱ የሚተርፈው የለም፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ያቀረበው አሳብ ተቀባይነት በማጣቱም በቀጥታ ከካህናት አለቆች ዘንድ ሔዶ ጌታንን በሠላሳ ብር ለመሸጥ ተዋዋለ (ማቴ. ፳፮፥፫-፲፮፤ ማር. ፲፬፥፩-፲፩፤ ሉቃ. ፳፪፥፩፮)፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ እንደ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ተምሯል፡፡ በረከተ ኅብስቱን ተመግቧል፡፡ ልዩ ልዩ ተአምራት በጌታችን እጅ ሲደረጉ ዅሉ ተመልክቷል፡፡ ጌታችንም ከሌሎች ሐዋርያት ሳይለየው እግሩን አጥቦታል፡፡ ከዳተኛው ይሁዳ ግን ለሐዋርያነት የጠራውን፣ ተንበርክኮ እግሩን ያጠበውን ጌታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ‹‹የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሔዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት!›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፮፥፳፬)፡፡ ሌሎች ሐዋርያት ከጌታችን ዘንድ ፍቅሩን ገንዘብ ሲያደርጉ ይሁዳ ግን እርግማንን ነው ያተረፈው፡፡ ‹‹ገንዘብ የኃጢአት ሥር ነው፤›› ተብሎ አንደ ተነገረ የኃጢአት ሥር የተባለው ገንዘብ የክርስቲያኖችን ሕይወት ያዳክማልና ምእመናን እንደ ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር እንዳንወድቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ‹‹ይህን ዓለም ቢያተርፍ ነፍሱን ከጐዳ ምን ይጠቅመዋል?›› ተብሎ የተነገረውን ቃል ልብ ማለት ጠቃሚ ነው፡፡

ክርስቲያን ነን በማለት የክርስትናውን ስም በመያዝ እምነታቸውን፣ የቆሙበትን ዓላማ በመገንዘብ የሚለውጡ ሰዎች ዛሬም እንደ ይሁዳ ጌታችንን እየሸጡት እንደ ኾነ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ ለድሆች መመጽወት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ዳሩ ግን በድሆች ስም የሰውን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋል እጅግ የከፋ ኃጢአት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ለገንዘብ ብለው ድሆችን ለረኃብ ለችግር ባልንጀራቸውን ለመከራ እና ለሞት አሳልፈው ሲሰጡ ምንም አይጸጽታቸውም፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ግን ሕይወታችንን ለገንዘብ ፍቅር ሳይኾን ለእምነታችንና ለባልንጀራችን አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል፡፡ በፍቅረ ንዋይ ተጠምደን ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት ለአይሁዳዊ ሸንጐ ምቹ ኾነን መገኘት እንደሌለብን መገንዘብ አለብን
ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል?

ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው።

እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም።

"ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

@KaleEgziabeher
መንፈሳዊ ጉባኤ:
Henok:
❖ ❖ ❖ ጸሎተ ሐሙስ ❖ ❖ ❖
ጸሎተ ሐሙስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ስያሜ ያለው ነው፡፡ ይህም ምክንያቱ በዕለቱ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የተገለጠበት ስለሆነ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህን በሚዘክር ሁኔታ ታስበዋለች፡፡
       ❖ በዚህ ዕለት ምን ተፈጸመ? ❖
√ በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ እለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡
ሌላው በዚህ ዕለት የተፈጸመው ተገባር ሕጽበተ እግር ነው፡፡ወንጌሉ እንዲህ ይላል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ሐሳብ ካገባ በኋላ ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤
ልብሱንም አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡” � /ዮሐ.13፥1-10/ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን ሊከላከል ሞከረ፤ ጌታችን እንዲህ አለው “እኔ የማደርገውን አሁን አንተ አታውቅም በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው” /ዮሐ.13፥10/፡፡ ጴጥሮስ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም ባለው ጊዜ የጌታችን መልስ ይህ ነበር “ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል የለህም” በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ደቀ መዛሙርቱን ሥርዓተ ጥምቀት ፈጸመ ሁለተኛ በቃል ያስተማረውን ትኅትና በተግባር ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሮል፡፡ “ከእኔ ተማሩ እኔ የዋሕ በልቤም ትሁት ነኝና” እንዲል /ማቴ. 11፥29/፡፡ ይህንም ሲፈጽም አሳልፎ ሊሰጠው ያለውን የአስቆሮቱን ይሁዳ አላየውም፡፡
   √ ሌላው በዚህ ዕለት ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጠው ተናገረ በዚህም ማንነቱን ጭምር ለይቶ ነገራቸው፡፡ እንዲህም ብሎ “እጁን በወጭቱ ያጠለቀው እኔን አሳልፎ የሚሰጥ ነው” በዚህ ዕለትም የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ የተቀበለልን የእኛን ሥጋ የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፥36-46፣ ዮሐ.17/
    ❖ የዚህ ዕለት ስያሜዎች፦ ❖
      ☞  ጸሎተ ሐሙስ ፦
የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይለምን የነበረን ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፤ /ማቴ.26፤36-46፣ ዮሐ.17/ በዚህም ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ እየተባለ ይጠራል፡፡
       ☞  ሕጽበተ እግር ፦
ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ወንጌሉ እንደሚል “እራትም ሲበሉ ዲያብሎስ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ በይሁዳ ልብ አሳልፎ እንዲሰጠው ዐሳብ ካገባ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከራት ተነሣ፤ ልብሱንም
አኖረ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም
በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ የደቀመዛሙርቱን እግር አጠበ፡፡”/ማቴ.26፥27/
           ☞  የምሥጢር ቀን ፦
በዚች ዕለት በአልአዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጡ፡፡ ከኅብስቱ ከፍሎ አማናዊ ሥጋ፤ ከወይኑ ከፍሎ አማናዊ ደም አድርጎ ባርኮ ቀድሶ አክብሮ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ /ማቴ 26፥26/ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕብስቱን ቆርሶ ይህ አማናዊ ሥጋዬ ነው ወይኑን ባርኮ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ሥርየት የሚፈሰው ደሜ ነው ብሎ ለደቀመዛሙርቱ ሥርዓተ ቁርባንን በተግባር ያስተማረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት በቃል ያስተማረውን ትምህርት በተግባር እንዴት መፈጸም እንዳለበት ያስተማረበት ዕለት በመሆኑ የምሥጢር ቀን ይባላል፡፡
      ☞  የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ፦
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ የሆነውን የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተበት ነው፡፡ ቀድሞ የነበረውን መስዋዕተ ኦሪት ሽሮ የሐዲስ ኪዳን ደምና ሥጋውን ፈትቶ ስላቀበላቸው የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ /ሉቃ.22፥20/
     ☞  የነጻነት ሐሙስ ፦
በመብል ያጣነውን ክብር በመብል የመለሰበት ዕለት በመሆኑ ጌታችን በሰጠን ሥልጣን ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ መኖር በማብቃቱ የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡
        ❖ሥርዓተ ጸሎተ ሐሙስ ❖
☞ በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ እንደተለመደው ይከናወናሉ ለየት ያለው ሥርዓት መንበሩ /ታቦት/ ጥቁር ልብስ ይለብሳል ጸሎተ ዕጣን ይጸለያል ቤተ ክርስቲያኑ በማዕጠንት ይታጠናል፡፡
በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኰስኰስቶችን ውኃ ሞልቶ ያቀርባል አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ መታጠቢያ፡፡ ጸሎተ አኮቴት የተባለ የጸሎት ዐይነት ተጸልዮ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ /በሊቀ ጳጳሱ/ እጅ ተባርኮ የሕጽበተ እግር ሥርዓት ከካህናት እስከ ምእመናን ከወንዶች እስከ ሴቶች በካህኑ አስተናጋጅነት ይከናወናል፡፡ ሥርዓተ ኅጽበቱ የሚከናወነውም በውኃ ብቻ ሳይሆን የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓቱ ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡
ምስጢሩም ወይራ ጸኑዕ ነው ክርስቶስ ጽኑ መከራ መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም /የሚያጥበውና የሚታጠበው ክርስቲያን/ መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ነው፡፡ የወይኑ ቅጠል በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን የሕይወት መጠጥ ይሆናቸው ዘንድ መስጠቱን ለማዘከር ነው፡፡ ማቴ 26.26 ይህም ሥርዓት ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለምእመናን ለማሳየት ነው ዮሐ. 13፤14፡፡ በቀኝና በግራ የቆሙ ሊቃውንትም ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ እያሉ ይዘምራሉ፡፡
ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን ይቀበላሉ፡፡
የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴው የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ነው፡፡ ደወሉ የጸናጽል ድምጽ ሲሆን በቀስታ ስለሚጮህ ነው፡፡ የድምጽ ማጉያ አይጠቀሙም፡፡ ምክንያቱም ዲያቆኑና ካህኑ ዜማውን በቀስታ የሚሉት ይሁዳ በምስጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም ሲሆን በሌላ በኩል የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማስታወስ ነው፡፡ በመቀጠል ክቡር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡
            ❖  ጉልባን  ❖
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡

ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ
እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ
የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !!!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለጥምና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ አሜን !!!
የዘመኑን ወረርሽኝ በቸርነቱ ያስታግስልን አሜን!!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
መንፈሳዊ ጉባኤ:
Henok:
💦💦የሚገርም ፍቅር💦💦💦

የጌታችን ሕማማት በሊቃውንት
:
☞በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት በማዳኑ፣ ዕዉራነ ሥጋን በተአምራት ዕዉራነ ነፍስን በትምህርት በማብራቱ፣ ልሙጻነ ሥጋን በተአምራት ልሙጻነ ነፍስን በትምህርት በማንጻቱ፣ አጋንንትን በማውጣቱ፣ ሙታንን በማንሣቱና ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ መኾኑን በማስተማሩ አይሁድ ከፍተኛ ቅንአት ዐድሮባቸው ጌታን ይዘው የካህናት አለቃ ቀያፋ ወዳለበት ይዘውት በመኼድ የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ኹሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሐሰት ምስክር ቢፈልጉም ምንም ዐይነት በደል ሊያገኙበት አልቻሉም ነበር፤ በኋላም ሊቀ ካህናቱ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የኾንኽ እንደ ኾነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልኻለኊ” ብሎ ሲጠይቀው፤ ጌታም “አንተ አልኽ፤ ነገር ግን እላችኋለኊ፤ ከእንግዲኽ ወዲኽ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችኊ” በማለት ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው በአብ ቀኝ ያለው የአብ የባሕርይ ልጅ የኾነው ርሱን በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ማለት፡- ዓለምን በማሳለፍ ኀይል ባለው ዕሪና በባሕርይ ክብሩ መጥቶ ታዩታላችኊ በማለት ተናገረው (ማቴ 26፡63-64)፡፡
ያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ በንዴት ልብሱን ቀደደ፤ በዘሌ 21፡10 ላይ “በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ ከወንድሞቹ የበለጠው ካህን ራሱን አይግለጥ ልብሱንም አይቅደድ” በማለት እንዳዘዘው በኦሪት ሥርዐት ካህን በሐዘን ምክንያት ልብሱን ከቀደደና ፊቱን ከነጨ ከሹመቱ የሚሻር ነውና በዚኽም የሊቀ ካህናቱ ኦሪታዊ ክህነት ማለፉን አጠይቋል፡፡
ከዚያ በኋላ ጌታን “ሞት ይገባዋል” በማለት በደረቅ ግንባር ላይ ዐይንን በፈጠረ በርሱ ፊት ላይ ምራቃቸውን ተፉበት፡- ጌታ በኢሳይያስ ዐድሮ በምዕ ፶፥፮ ላይ “ወኢይትሀከዩ ወሪቀ ውስተ ገጽየ ወኢሜጥኩ ገጽየ እምኀፍረተ ምራቅ” (ዠርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠኊ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስኹም) ያለው ትንቢት ሊደርስ ሊፈጸም ምራቃቸውን ተፍተውበታል፡፡ አንድም አዳምን ዲያብሎስ በገጸ ልቡናው ምራቀ ምክሩን እየተፋ ሲኦል አውርዶት ነበርና ለርሱ ካሳ ሊኾን ንጹሐ ባሕርይ አምላክ ተተፍቶበታል፡፡
ከዚያም ራሱን በዘንግ መቱት “ወኲሉ ርእስ ለሕማም” (ራስ ኹሉ ለሕመም ኾኗል) ብሎ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ይደርስ ይፈጸም ዘንድ የሕይወት ራስ ርሱን በዘንግ መቱት (ኢሳ ፩፥፭)፤ አንድም ዲያብሎስ የአዳምን ርእሰ ልቡናውን በበትረ ምክሩ እየመታ ሲኦል አውርዶት ነበርና ካሳ ሊኾን ነበር፤ ከዚያም ፊቱን በሻሽ ሸፍነው “መኑ ውእቱ ክርስቶስ ዘጸፍዐከ” (ክርስቶስ በጥፊ የመታኽ ማነው? ንገረን እስቲ ዕወቀን) እያሉ ዘብተውበታል፤ ይኸውም መተርጒማን እንዳመሰጠሩት አዳምና ሔዋን የአምላክነትን ዕውቀት ዕንወቅ ብለው ሲኦል ወርደው ነበርና ልቡና ያሰበውን ኩላሊት ያመላለሰውን ኹሉን የሚያውቅ ርሱ ላይ በዚኽ ቃል መዘበታቸው ለአዳምና ለሔዋን ሊክስላቸው ነው፡፡
ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት የሚያድሩ ቊጥራቸው ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት የኾኑት ኤልሳቤጥ፣ ቤርዜሊ፣ መልቴዳ በዕለተ ዐርብ በዐይናቸው ያዩትን የጌታን ሕማማት በተናገሩበት ድርሳን ላይ ይኽነን ሲገልጹ፡- “ወሶበ ዘበጥዎ አፉሁ ለእግዚእ ኢየሱስ ሐሙ ከናፍሪሁ ወአስናኒሁ፤ ወውሒዘ ደም ብዙኅ እምአፉሁ…” (ጌታችን ኢየሱስን አፉን በመቱት ጊዜ ከንፈሮቹ ጥርሶቹም ታመሙ፤ ከጌታችንም ከኢየሱስ አፍ ብዙ ደም ፈሰሰ፤ አሕዛብን በሚያጠፋበት ስለቱ (ሥልጣኑ) በኹለት ፊት የኾነ የተሳለ ሰይፍ ከአንደበቱ የሚወጣ ሲኾን (ወደ እኔ ኑ፣ ከእኔ ኺዱ የሚልበት ሥልጣን ገንዘቡ ሲኾን) (ማቴ ፳፭፥፴፩-፵፮)፤ ዳግመኛ አይሁድ ጌታችን ኢየሱስን ፊቱን ፳ ጊዜ በጡጫ መቱት ይኸውም እግዚአብሔር አብን መንፈስ ቅዱስንም በመልክ የሚመስል በባሕርይ የሚተካከል ነው (ዮሐ 10፡30)፤ በጌትነት ክብር በደብረ ታቦር በተገለጸ ጊዜ ተለውጦ እንደ ፀሓይ ያበራ መልኩ ፊቱ ነው (ማቴ ፲፯፥፪)፤ ርሱ የማይጠልቅ ፀሓይ የማይጠፋ ፋና ነውና፤ በወዳጆቹም ላይ ዘወትር የሚያበራ ፀሓይ ነውና (ራእ ፳፪፥፭)፤ ሰነፎች አይሁድም ከምድር ነገሥታት ይልቅ የሚያስፈራ ፊቱን ሲመቱት የጌታችን የኢየሱስ የፊቱ ግርማ ሦስት ጊዜ ወደ ምድር የኋሊት የጣላቸው መኾኑን አላሰቡትም) በማለት በቅንአት የሰከሩ የዝንጉኣን የአይሁድን ነገር አስምረዋል፡፡
ዓለምን ለማዳን ሲል አካላዊ ቃል ክርስቶስ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅም በቅዳሴው ላይ ሲተነትናቸው፡- “በይእቲ ሌሊት እንተ ባቲ ረፈቀ ምስለ አርዳኢሁ መጠወ ነፍሶ ለሞት በፈቃደ አቡሁ ወበሥምረተ ርእሱ…”
(ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በተመጠባት በዚያች ሌሊት በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ ሰውነቱን ለሞት ሰጠ፤ ኹሉን የያዘውን ያዙት ኹሉን የሚገዛውን አሰሩት የሕያው የአምላክን ልጅ አሰሩት፤ በቊጣ ጐተቱት በፍቅር ተከተላቸው፤ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተላቸው ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በዐደባባይ አቆሙት ኀጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾኽ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የግርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን ርሱን (ኢሳ ፮፥፪፤ ራእ ፭፥፭-፲፬)፤ ክፉ ባሪያ እጁን አጽንቶ ፊቱን ጸፋው (ዮሐ ፲፰፥፳፪)
የመላእክት ሰራዊት በፍጹም መደንገጥ ለሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ (ፊልጵ ፪፥፲) ይኽን ያኽል ትሕትና እንደ ምን ያለ ትሕትና ነው?፤ ይኽን ያኽል ዝምታ እንደ ምን ያለ ዝምታ ነው?፤ ይኽን ያኽል ቸርነት እንደ ምን ያለ ቸርነት ነው?፤ ይኽን ያኽል ሰውን ማፍቀር እንደ ምን ያለ ፍቅር ነው?፤ ኀያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው፤ በደል የሌለበትን እንደ በደለኛ ሰቀሉት፤ ሕይወት የሠራውን ከበደለኞች ጋራ ቈጠሩት፤ አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ፤ በአዳም ላይ የሕይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሐሞት ጋራ የተቀላቀለ የኾመጠጠ መጻጻን ጠጣ ወዮ፤ የወልድ መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ኅሊናም ይመታል ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል፤ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ) በማለት ሕማማቱን በስፋት አስተምሮታል፡፡
ወንጌላውያንም እንደጻፉት ጌታችንን አይሁድ ኀሙስ ማታ ከያዙት በኋላ “ወወሰድዎ ለእግዚእ ኢየሱስ እምኀበ ቀያፋ ኀበ ዐውድ ወጎሕ ውእቱ” ይላል በማለዳ ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወደ ፍርድ ዐደባባይ አስረው በማለዳ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ወስደውታል (ማቴ ፳፯፥፲፩፤ ማር ፲፭፥፩፤ ሉቃ ፳፫፥፩፤ዮሐ ፲፰፥፳፰) ይኸውም አዳምን ከመልአከ ገሀነም ፊት አስረው ወስደው አቁመውት ነበርና ለካሣ ሊኾን ነበር፡፡ .