"ቃለ እግዚአብሔር "
8K subscribers
628 photos
20 videos
7 files
227 links
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
Download Telegram
Henok Asrat:
🔰 #ሱባዔ_ለምን? 🔰

1⃣እግዚአብሔርን ለመማፀን

     ምንም የምንጠይቀው /የምንማጸነው/ ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኘው መልስ አይኖርም። አንድ ሰው ለገባው ሱባዔ መልስ ወዲያውኑ ሊያገኝ ይችላል ወይም ደግሞ መልሱ ሊዘገይ ይችላል። በዚህ ጊዜ  ከተሐራሚው ትዕግስት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ “ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ  አልተሰጠኝም” በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም። እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበትና ለሚማጸነውም መልስ የሚሰጥበት የራሱ ጊዜ አለው።

2⃣ #የቅዱሳንን_በረከት_ለመሳተፍ

     ቅዱሳን በሚጋደሉበት ቦታ “ከወንዶችና ከሴቶች ይልቅ የሚበልጥ ስም እሰጣቸዋለሁ” ኢሳ 56፥6 በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለገባለቸው ሱባዔ በመግባት በረከታቸውን መሳተፍ ይቻላል። #በጾመ_ነቢያት_የነቢያትን_በረከት_ለመሳተፍ_በጾመ_ፍልሰታ_የእመቤታችንን_በረከት_ለመሳተፍ_ሱባዔ_መግባት_የነበረና_ወደ_ፊትም_የሚኖር_የቤተ_ክርስቲያን_ሥርዓት_ነው። ነቢዩ ኤልሳዕ መምህሩን ኤልያስን በማገልገል የኤልያስ በረከት በእጥፉ በኤልሳዕ ላይ አድሮበታል። ይህን አብነት በማድረግ በየገዳማቱ በትሕርምት የሚኖሩ መናንያንን ያገለገሉበትን ገዳም አባት በረከት በእጥፍ እየተቀበሉ ለሌሎችም የሚያቀብሉ አባቶች በየገዳማቱ አሉ። 1ነገ 2፥9

3⃣ #የተሰወረ_ምስጢር_እንዲገልጥልን
ቅዱሳን በየራሳቸው ያዩት ራእይ ምስጢር ሲከደንባቸው የራእዩ ምስጢርና ትርጉም እንዲገለጥላቸው ሱባዔ ይገባሉ። እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምስጢር ይገልጥላቸዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዕዝራ የመጽሐፍትን ምስጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ቢገባ የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ዳግም መልሶ ለመጻፍ ችሏል። መዝ 8፥1 በዘመነ ብሉይ የነበሩ ነቢያትም በዘመናቸው የነበሩ ነገሥታት ራእይ አይተው ነገር ግን ምስጢሩ የተሰወረባቸውን ለመተርጎምና ምስጢሩን ለመረዳት ሱባዔ ይገቡ ነበር። ዘፍ 41፥14-36 ፣ ዳን 4፥9 ፣ ዳን 5፥4 ፣ ዳን 5፥25 በዘመነ ሐዲስ በስፋት የሚወሳው ቅዱሳን ሐዋርያት ከነሐሴ 1 – 14 ተሰውሮ የነበረውን የእመቤታችንን ትንሣኤ ለማየት የገቡት ሱባዔ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
ሰውን የሚያረክሱትን ነገሮች የትኛዎቹ እንደኾኑ እንረዳ እና አንዴ ከተረዳንም በኋላ እንራቃቸው፡: በቤተ ክርስቲያን ውስጥ፤ አብዛኛዎቹ ሰዎች የውጫቸው ንጹህ ኾኖ መታየት እንደሚያሳስባቸው እናያለን፤ ነገር ግን ስለ ንጹህ ልብስ እንጂ በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ ልባቸውን ስለማቅረብ አያስቡም፡፡ እጃችሁን ወይም አፋችሁን አትታጠቡ እያልኩ አይደለም ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ በመልካም ተግባርና በጎነት ብትታጠቡ ይሻላል፡፡

ስለሌሎች መጥፎ መናገር፤ ጸያፍ ቋንቋ መጠቀም፤ ተገቢ ባልኾኑ ቀልዶች መሳቅ እነዚህ ነገሮች ልብን ያቆሽሹታል፡፡ እንግዲያው፣ ከእነዚህ ነገሮች አንዱንም ካላደረጋችሁ፤ በቅን ልብ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ትችላላችሁ፡፡ እነዚህን ነገሮች ካደረጋችሁ ግን ጸሎታችሁ ትርጉም አይኖረውም፡፡ ርኩሰት የተሸከመ ምላስህንም በውኃ ማጠብህ ትርጉም አይኖረውም።

ይህን አስቡ በእጃችሁ ላይ ጭቃ ወይም እበት ቢኖርባችሁ ለመጸለይ ትደፍራላችሁ? በጭራሽ። ነገር ግን የእጅ መቆሸሽ ከልብ መቆሸሽ በላይ የሚያጸይፍ መሆን የለበትም፡፡ ለምንድነው አላስፈላጊ ለኾኑ ነገሮች ትኩረት የምትሰጡት እና አስፈላጊ የኾኑትን ችላ የምትሉት? “አትጸልዩ ነው ወይ የምትለን" ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። አይ፤ መጸለያችሁን ማቆም የለባችሁም፣ ግን በዚህ ቆሻሻ ሁኔታ ውስጥ መሆን የለበትም፡፡

“ሳላውቅ ኃጢአትን ብሰራ፣ ስህተት ካደረኩ ምን ማድረግ አለብኝ?" እራስህን አጽዳ፡፡ እንዴት? ተጸጸት፣ ለድሆች ስጥ፣ የሰደብከውን ስው ይቅርታ ጠይቅ፣ የበደሉህንም ይቅርታ አድርግላቸው፡፡ እግዚአብሔርን አብዝተህ እንዳታስቆጣ አንደበትህን አጽዳ፡፡

በእጆቹ ጭቃ የያዘ ሰው እግርህን ቢይዝና ገንዘብ ቢጠይቅህ፣ አትሰማውም፤ እንዲያውም ልትገፋው ትችላለህ፡፡ ታዲያ ለምን በዚህ መንገድ ወደ እግዚአብሔር ትቀርባለህ? የሚጸልዩ ሰዎች አንደበት የእግዚአብሔርን ጉልበት እንደሚነካ እጅ ነው፡፡ ስለዚህ አንደበታችሁን አታርክሱ፣ አለዚያ እግዚአብሔር ጸሎታችሁን አልሰማም ይላል፡፡ አንደበት የሕይወትና የሞት ኃይል አለው። ቃላትህ ሊያጸድቁህ ወይም ሊያስኮንኑህም ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ምላስህን ከዓይኖችህ የበለጠ በጥንቃቄ ጠብቅ።

አንደበት ለንጉሥ እንደ ፈረስ ነው፤ በእርሱም ላይ ልጓም ቢደረግበት፣ ከተቆጣጠሩት እና ከገሩት ለንጉሡ የታመነ ይኾናል፡፡ ነገር ግን እንዲሁ እንዲሮጥ ከፈቀድክ የዲያብሎስ መሳሪያ ይሆናል፡፡ አንደበትህን አታርክሰው፣ በየዋህነት እና በትህትናም አስጊጠው::

ለእግዚአብሔር የሚገባውን አድርጉ፣ አንደበታችሁ በመልካም ቃላት ይሞሉ፤ መልካም ቃል ከስጦታ ይሻላልና፡፡ ለድሆች በደግነትና በቅንነት መልሱ፡፡ የቀረውን ጊዚያችሁን ስለ እግዚአብሔር ሕግጋትና ትምህርቶች በማሰብ አሳልፉ፡፡ ንግግሮቻችሁ ኹሉ በልዑል እግዚአብሔር ህግጋት የተገሩ ይሁኑ፡፡ ራሳችንን አስጊጠን ወደ ንጉሡ እንውጣና በእግሩ ሥር እንውደቅ፣ በአካል ብቻ ሳይኾን በአዕምሯችንም፡፡ ወደ ማን እንደምንሄድ፣ ለምን ዓላማ እና ምን ማከናወን እንደምንፈልግ እንመርምር፡፡ ሱራፌልና ኪሩቤል በዓይናቸው የማያዩት፤ ግርማውን መሸከም ያቃታቸው፣ መዳረሻ አልባ ብርሃን ወደሆነው ወደ እግዚአብሔር እንሄዳለን፡፡ ከገሃነም ለማምለጥ፤ ለኃጢአታችን ይቅርታ ለመጠየቅ፤ ከቅጣት ለመራቅ እና ወደ መንግሥተ ሰማያት (እና በረከቶቿ ኹሉ) ለመግባት ወደ እርሱ እንሄዳለን፡፡

ምንጭ፦
(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ ገጽ 60-62 #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
Henok Asrat:
🔰 #ሱባዔ_ለምን? 🔰

1⃣እግዚአብሔርን ለመማፀን

     ምንም የምንጠይቀው /የምንማጸነው/ ነገር ሳይኖር ሱባዔ ብንገባ የምናገኘው መልስ አይኖርም። አንድ ሰው ለገባው ሱባዔ መልስ ወዲያውኑ ሊያገኝ ይችላል ወይም ደግሞ መልሱ ሊዘገይ ይችላል። በዚህ ጊዜ  ከተሐራሚው ትዕግስት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ “ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ  አልተሰጠኝም” በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም። እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበትና ለሚማጸነውም መልስ የሚሰጥበት የራሱ ጊዜ አለው።

2⃣ #የቅዱሳንን_በረከት_ለመሳተፍ

     ቅዱሳን በሚጋደሉበት ቦታ “ከወንዶችና ከሴቶች ይልቅ የሚበልጥ ስም እሰጣቸዋለሁ” ኢሳ 56፥6 በማለት እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለገባለቸው ሱባዔ በመግባት በረከታቸውን መሳተፍ ይቻላል። #በጾመ_ነቢያት_የነቢያትን_በረከት_ለመሳተፍ_በጾመ_ፍልሰታ_የእመቤታችንን_በረከት_ለመሳተፍ_ሱባዔ_መግባት_የነበረና_ወደ_ፊትም_የሚኖር_የቤተ_ክርስቲያን_ሥርዓት_ነው። ነቢዩ ኤልሳዕ መምህሩን ኤልያስን በማገልገል የኤልያስ በረከት በእጥፉ በኤልሳዕ ላይ አድሮበታል። ይህን አብነት በማድረግ በየገዳማቱ በትሕርምት የሚኖሩ መናንያንን ያገለገሉበትን ገዳም አባት በረከት በእጥፍ እየተቀበሉ ለሌሎችም የሚያቀብሉ አባቶች በየገዳማቱ አሉ። 1ነገ 2፥9

3⃣ #የተሰወረ_ምስጢር_እንዲገልጥልን
ቅዱሳን በየራሳቸው ያዩት ራእይ ምስጢር ሲከደንባቸው የራእዩ ምስጢርና ትርጉም እንዲገለጥላቸው ሱባዔ ይገባሉ። እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምስጢር ይገልጥላቸዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዕዝራ የመጽሐፍትን ምስጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ቢገባ የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ዳግም መልሶ ለመጻፍ ችሏል። መዝ 8፥1 በዘመነ ብሉይ የነበሩ ነቢያትም በዘመናቸው የነበሩ ነገሥታት ራእይ አይተው ነገር ግን ምስጢሩ የተሰወረባቸውን ለመተርጎምና ምስጢሩን ለመረዳት ሱባዔ ይገቡ ነበር። ዘፍ 41፥14-36 ፣ ዳን 4፥9 ፣ ዳን 5፥4 ፣ ዳን 5፥25 በዘመነ ሐዲስ በስፋት የሚወሳው ቅዱሳን ሐዋርያት ከነሐሴ 1 – 14 ተሰውሮ የነበረውን የእመቤታችንን ትንሣኤ ለማየት የገቡት ሱባዔ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
#ፍልሰታ_መጣች 🙏
"ሕፃኑም ወጣቱም ወንዱም ሴቱም ዕድሜው የገፋውም ሁሉም በፍቅር የሚፆሟት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና በረከት የሚታፈስባት፣ ፍቅረ እግዚአብሔር በሰው ልቡና የሚሰለጥንባት ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሚያይልባት #የንሰሐና_የምህረት_ጾም_ጾመ_ፍልሰታ_መጣች 🙏

በዓለም ያሉ ወደ ቤተክርስቲያን በቤተክርስቲያን ያሉ ወደ ገዳማት የሚገሰግሱባት ጾመ ፍልሰታ መጣች🙏

የተዋህዶ ልጆች እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ 🙏

💚💛❤️ ለሀገራችን ምህረትን ፣ ሰላም እና ፍቅርን የድንግል  ማርያም ልጅ ያድልልን የበረከት የምህረት የይቅርታ ፆም ይሁንልን 💚💛❤️
ፆመ ፍልሰታ የእመቤታችን እረፍት ትንሳኤና እርገት ሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ እመቤታችን በተለያዩ ጊዜያት ሞትና ትንሣኤዋን ለሐዋርያት የገለጸችበትን ምስጢር ከነሐሴ 1-16 ድረስ ምእመናን በጾም በጸሎት ተወስነው የልጇን ቸርነት የእርሷን አማላጅነት በሱባኤ ይማጸናሉ፡፡ የሱባኤው ወቅት ሲፈጸም “እመቤታችን በእውነት ተነሥታለች” ብለው በደስታ የጾሙን ወቅት ይፈጽማሉ፡፡ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን ቅዱስ ያሬድ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል” በማለት ገልጾታል፡፡
በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ 64 ዓመታት ያህል ቆይታ አርፋ ተነሥታ በክብር አርጋለች፡፡ ይህንን የትንሣኤና ዕርገት ዐቢይ ምሥጢር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “ተንሥአ እግዚኦ” ውስተ ዕረፍትከ፡፡ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፡፡ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ.131፡8/፤ እንዲሁም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” /መዝ.44፡9/ ሲል የተናገረው ቃለ ትንቢት በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና የጸናች የቅድስት ድንግል እመቤታችንን ዕረፍት፣ ትንሣኤ፣ ፍለሰት /ዕርገት/ ያስገነዝባል፡፡ /ራእ.11፡19/
እመቤታችን ታቦተ እግዚአብሔር መሆኗን አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ሲገልጽ “ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ” ሲል አመስግኗታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በትርጓሜያቸው ይህንን ቃለ ትንቢት ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ከገለጣት “ንግሥተ ሰማይ፤ የሰማይ ንግሥት” /ራእ.12፡1/ ጋር በማገናዘብ የእመቤታችንን ሁለንተናዊ ክብርና ልዕልና አምልተውና አስፍተው ገልጸውታል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ “… በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው፡፡….. ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል” /ራእ.14፡13/ ብሎ እንደመሰከረው እመቤታችን ከዕረፍቷና ዕርገቷ በኋላ የመጨረሻ ወደ ሆነው ክብር መሸጋገሯ ያስረዳል፡፡
ይህንን ክብርዋን በመረዳት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር “ወበእንተዝ ናዐብየኪ ኩልነ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ንጽሕት ኩሎ ጊዜ፡፡ ንስአል ወናንቀዐዱ ኀቤኪ ከመ ንርከብ ሣህለ በኀበ መፍቀሬ ሰብእ፤ ሁልጊዜ ንጽሕት የምትሆኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ስለዚህ ነገር እናከብርሻለን፣ እናገንሻለን፡፡ ሰውን ከሚወድ ልጅሽ ዘንድ የቅርታንና ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ሁል ጊዜ ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን፡፡ በማለት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ሁል ጊዜ ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን፡፡ በማለት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣትን ልዩ የቃል ኪዳን ጸጋና አምላካዊ ክብር እያመሰጠሩ ያመሰግኗታል፡፡ ሊቁ “ቀስተ ደመና ማርያም ትእምርተ ኪዳኑ ለኖኅ፣ ዘእግዚአብሔር ሤመኪ ለተዝካረ ምሕረት ወፍትሕ፣ ህየንተ ቀስፋ ለምድር ወአማሰና በአይኅ፡፡ ብሎ እንዳመሰገናት፡፡
እመቤታችን በአጸደ ሥጋ ሳለች ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ በመዋዕለ ሥጋዌ ላደረገው የድኅነት ዓለም ጉዞ ምክንያት ነበረች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ባርነትና ስደት ለማጥፋት ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የሰው ልጆችን ያሳደደ ሠይጣን በሄሮድስ አድሮ ሲያሳድደው ልጇን ይዛ በመሰደድ ለድኅነታችን ምክንያት ነበረች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ባርነትና ስደት ለማጥፋት ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የሰው ልጆችን ያሳደደ ሠይጣን በሄሮድስ አድሮ ሲያሳድደው ልጇን ይዛ በመሰደድ ለድኅነታችን ምክንያት ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራእዩ እንዳየው፤ “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ እርስዋም ፀንሳ ነበር፡፡ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች፡፡ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ፡፡ ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስልሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች ”/ራእ.12፡1-6/
የጴንጤዋ ማርያም

የ ዘጠኝ ወር ልፋት እንዲሁ “አትወልጂም“ በምትል በአንዲት ቃል ሲጠቀለል ምን ይባላል??እድሜ ልኬን ተስዬ ለምኜ ያገኘኋት የማህፀኔ ፍሬ እንደ እፉኚት ከወለድሻት ትገልሻለች መባልስ ምን ማለት ነው??ፈጣሪስ ገና ወጥታ እሹሹሩ ካላልኳት፤ ካላጠባኋት፤ካልሳምኳት፤ካልታቀፍኳት ከገዛ ልጄ ጋር እንዴት ፀብ ውስጥ ይከተኛል???

ለምን ይሄ ሁሉ መከራ በኔ እንደመጣ ባላውቅም እግዚአብሔር ብዬ የለመንኩት አምላክ እንደሌለ ግን አረጋግጫለሁ። ቢኖርማ ለምን ሰጥቶ ይነሳኛል??ለምን ሰምቶ ዝም ይለኛል??ደግ ከሆነስ ነብሴና ልጄን ሚዛን ላይ አስቀምጦ እንዴት ይተወኛል??ጨካኝ ቢሆን እንጂ....

ሲስ (ባሌ) ጠዋት ዜናውን ከሰማ ጀምሮ ትንፍሽ አላለም።አላማረረም።አላለቀሰም። ግን ደሞ ከኔ በላይ እየታመመ እንዳለ ፊቱ ጥቁር ብሎ በመሀል በመሀል ከፊቱ ባለች ጠባብ መስታወት ያየኛል።ከኋላ የተቀመጥኩት ጎኑ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ሕመሙን እንዳልጨምርበት ብዬ እንጂ ከአጠገቡ ስርቅ አይወድም።ያለወትሮው መኪናዋን ቀስ እያለ ነው ሚነዳት ሆስፒታል እንድንደርስ ሁለታችንም አልፈለግንም።ያላየናት ልጃችንን ገድለን እራሳችንን ለማትረፍ የምንጣጣር ራስ ወዳድ መሆናችን ተሰምቶን ይሁን?...አላቅም። ብቻ ግን የቀጠሯችን ሰዓት ደርሷል ሰዓቱ 9 ሰአት አናቱ ላይ ይላል።ከፊት ደሞ ከእንጦጦ ኪዳነምህረት አስቀዳሽ ምእመናን ቅዳሴ ጨርሰው ከቤተክርስትያኗ እየወጡ መንገዱን ዘግተወታል።ፍዝዝ ብዬ የሚተራመሠውን ሕዝብ እያየሁ የመኪናችን መስታወት በስሱ ሲንኳኳ ብንን ብዬ ዞርኩ።ጭርጭስ ያሉ አሮጊት በመስታወቱ አጮልቀው እያዩኝ የማልሰማውን ነገር እየለፈለፉ ሳይ መስታወቱን ዝቅ አደረኩት

ልጄ እስከ ሽሮሜዳ አድሺኝ እባክሽ እግሬ እምቢ ብሎኝ...

ምንም ሳላወራ በሩን ከፍቼላቸው ተጠጋው። ሲስ ሁኔታውን ከማየት በቀር መልስ አልሰጠም።እማማ መላእክቱን እየጠሩ ይመርቃሉ...

ሚካኤል አለሁ ይበልሽ..እመቤቴ በሰላም ትገላግልሽ...የማህፀንሽን ፍሬ እዪ....ወልደሽ ሳሚ....የጭንቅ አማላጇ ትቅረብሽ....ከለላ ትሁንሽ....ምጥሽን ታቅለው..

እማማ ይተውኝ!!እኔ ለልጅ አልታደልኩም!!ልጄን በማህፀን ገድዬ የቀበርኩ ነኝ!!እማማ ፈጣሪዬ አሳይቶ ነሳኝ(ሳላውቀው የሚታገለኝ እንባ ከአይኔ አምልጦ ጉንጬ ላይ ተንደረደረ።

ውይ ውይ እኔን አፈር ይብላኝ።ይቅር በይኝ ልጄ እኔማ መመረቄ ነው የሆድሽን መች አውቄ? በይ አይዞሽ አታልቅሺ እንዲህ መርቄሽማ ድንግል አታሳፍረኝም ከሆስቢታሉ በፊት አንድዜ ደጇን እርገጩ እሷ መላውን ታውቃለች በሉ እንመለስ...

እማማ እግዜር ይስጦት ግን አይሆንም እኛ በጌታ ነን ሃይማኖታችን አይፈቅድም በምናቀው ተማፅነናል በዛላይ ሰዓቱ ረፍዷል ትንሽ ከቆየን ሚስቴን አጣታለሁ!!

አይ እንግዲ በጌታ የሆነ በናቱ ቢማፀነው ምን ይከፋል??እሺ በሉኝ.. በተአምሯ ትደሰታላችሁ በሱባኤዋ አታሳፍራችሁም ስላችሁ??

እማማ ይውረዱ ሽሮሜዳ ደርሰዋል!!(ሲስ ብስጭት ያለ ይመስላል እንዲህ ሰው አውርቶ አያውቅም።ጴንጤ ብሆን እንኳ እማማ ያመጡትን ሀሳብ ተቀብዬ ለመጨረሻ ጊዜ ልሄድ ፈልጌ ነበር ባምጥ ማርያም ማርያም ይባል የለ?ጨንቆኝ ብሄድ ምን ችግር አለው??በዚህ ሰዓት ማንም ምንም ቢል ልጄን ለማዳን ምንም እሆናለሁ...

ሆስፒታል ደረስን።ነብሴን መርጩ ልጄን የምጥልበት ሰርጀሪ ክፍል ለመግባት እግሬን እየጎተትኩ ሳለሁ ግን እግርና እግሬ መሀል ቀጭን ፈሳሽ እየተንሸራተተ ተሰማኝ።ትንሽ ቆይቶ ሆዴን ሲቆርጠኝ በትንሹ አቃሰትኩኝ።ጩኸቴ ጨመረ።ከዛ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ ከሰርጀሪ ክፍል በአልጋ እየጎተቱኝ ማዋለጃ ክፍል ሲያስገቡኝ፤ብዙ ሴቶች ከበው እየጮኹ ግፊ ግፊ ግፊ እያሉ ሲያበረቱኝ፤ሳቃስት፤ሳለቅስ፤ስወራጭ ማርያም ማርያም ሲባል በደቂቃወች ውስጥ የህፃን ድምፅ ስሰማ ብቻ ትዝ ይለኛል።በእውኔ ይሁን በሕልሜ ታሪክ ተቀይሮ ልጄን ሲያሳቅፉኝ ባለማመን እያየኋቸው የሞት ሞቴን አወራሁ....

እንዴት??እንዴት ሆነ ዶክተር??አትወልጂም ተብዬ??(ዶክተሩ ሚመልሰው ጠፍቶት አይን አይኔን ሲያየኝ በሩ ተከፍቶ ሲስ እየሮጠ ገባ ማን እንደሆነ ባላቅም በእልልታ ታጅቦ ሲቀርበኝ እኛን የመረቁኝ አሮጊት ከስሩ ብቅ ሲሉ አየኋቸው።የእናትነት ፈገግታቸው እያበራ...

አይ አንቺ...አታሳፍሪኝምኮ!!ቀየርሽው አደል!!እሺ አልሺኝ አደል??ሰማሺኝ አደል??አማላጄዋ.. እናቴዋ.. የኔ ገራገር.. እመ ልቤ.. እሰይ እሰይ እሰይ...(እማሆይ ግንባሬን እየሳሙኝ በመሀል እልልታቸውን አቀለጡት

እማማ እንዴት መጡ ግን??

ተአምሯን ላይ ነዋ!!እንደምታደርገው አውቃለሁኮ...አየሽ ዳቤዋን የቀመሰ.. ይጣፍጥ የለ??(እኔና ሲስን አፈራርቀው እያዩን

የምን ዳቤ እማማ? መች ያቀመሱንን??

አይ ልጄ ተው አትዋሽ ከኔ ብትሰውር ከሷ አይሰወርም።ልጄ ስታለቅስብኝ አንተም እንቢ ስትለኝ ከደብሯ ቆርሼ የያዝኩትን ዳቤ..

አዎ እማ በልቼዋለሁ!!ሲስ ትክክል ናቸው...አንቺ ካለሽ እቺን ድርጊልኝ፤የተሳሉሽ የደረሰላቸው እውነት ከሆነ አሁን ለኔም ድረሺ፤አዋልጂኝ ቅረቢኝ ብዬ እየተሣልኩ እማማ ጥለው የወጡትን ዳቤ በልቻለሁ።ሲስ እሷ ናት የሰማቺኝ ኪዳነምህረት ናት ያዋለደቺኝ(ሳቅና እንባ የቀላቀለ ፊቴን እያየ ሲስ መጥቶ እቅፍ አደረገኝ እማማ እልልታቸውን እያቀለጡት

አየሽ እንዲያው እኛ ተለያየንባት እንጂ "የጰንጤዋ ማርያም የኦርቶዶክስዋ ማርያም ብሎ ነገርኮ የለም"ማርያም እናቴ ብሎ ለጠራት የሁሉ ናት።ለተማፀኗት ለተማመኗት አደለም ላልጠሯት ለማያውቋትም አማላጅነቷን ለማያምንም ትደርሳለች።ለውሻም ትራራለች።አንቺማ ጣድቋን ቆርሰሻል በላኤሰብኮ በስሟ ጥርኝ ውኃ ሰጥቶ ነው የዳነባት።ቆይንጂ ደሞ...እናንተ ቅድም እናት ብሆን አደል አዝናችሁ በመኪና የሸኛችሁኝ??እናንተ ያዘናችሁልኝ ልጇ አምላኳ የሆነ ድንግል ብትጠይቀው እንዴት እምቢ ይላል?ብትማልደው እንዴት ይጨክናል?? ኃጢአታችን ከአምላክ ቢከልለን በማርያም በኩል ግን ይታረቀናል።"ስለ ሔዋን የገነት በር ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን"የተባለውኮ ለዚህ ነው።የተደመደመ ተስፋ በአማላጅነቷ እንደሚለመልም ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሲነግረን እኮ ነው።እየውልሽ እኛ ጎራ ፈጥረን እንጂ እሷኮ ለነውራችን መጋረጃ፤ለእንባችን መሀረብ፤ ለመንገዳችን ስንቅ፤ለቤታችን ውብት፤ለጭንቃችን ደራሽ ናት።እንግዲህ በሉ እኔ ወደቤቴ ልሂድ...

እማማ መች ነው ተመልሰው ሚመጡት??(በስስት እያየኋቸው) እንግዲህማ እናት አትለፋም ልጅ ነው እንጂ ሚመጣው።እዚያው ኪዳነምህረት ደጇ ላይ ብትመጪ እኔንም ወለላዬንም ታገኚናለሽ (ከንፈራቸውን ሸብበው በስሱ ጥርሳቸውን እያሳዩኝ

እማ ማርያምን መጣለሁ!!አልኳቸው። ከልቤ ነው ልጄንም"የማርያም"ብያታለሁ።

@KaleEgziabeher
#እንኳን_አደረሳቹ_አደረሰን_የተዋህዶ_ልጆች_በሙሉ😘🙏
✝️🌿👉 #ቡሄ_ጅራፍ_ማስጮህ
✝️🌿👉 #ችቦ_ማብራት
✝️🌿👉 #ሙልሙል_ዳቦ - ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው⁉️
#ደብረ_ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን ፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው።
✝️🌿💚💛
ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡ #በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ ( #ቡሄ#ጅራፍ ማስጮህ ፣ #ችቦ ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
✝️🌿💚💛
#ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣  ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
✝️🌿💚💛
" ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ " አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ ሙልሙል / ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
✝️🌿💚💛
✝️🌿👉 #ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው / ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ / በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው
ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
✝️🌿💚💛
#አንድም እንደ #ሐዋርያት_የምስራችሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው " ቢሄ በሉ " የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል
ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡
✝️🌿💚💛
#መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት
በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡
✝️🌿💚💛
✝️🌿👉 #ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡
✝️🌿👉 #ጅራፍ
የጅራፍ ምሳሌነት በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
✝️🌿💚💛
✝️🌿 #የመጀመሪያው_ምሳሌ - ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
✝️🌿 #ሁለተኛው_ምሳሌ -  ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና
በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡
✝️🌿💚💛
የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡
✝️🌿💚💛
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡
✝️🌿💚💛
ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
✍️   ቅዱሱ ተራራ ✍️↲(፪ኛ ጴጥ፩÷፲፯-1፲፰ )

ደብረታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡
ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላት መካከል የደብረታቦር በዓል አንዱ ነው፡፡
     በእስክንድርያ ግን ዐበይት በዓላቶቻቸው ፯ ናቸው፡: በዚህም ምክንያት ከዐበይት በዓላት ውስጥ አስገብተው ደብረታቦር አይቆጥሩትም ፡ይሁን እንጂ በበዓልነቱ አይከበርም ማለት ግን አይደለም።

      ደብረታቦር ወይም የታቦር ተራራ ጌታ በምድረ እስራኤል እየተዘዋወረ በማሰተማር ላይ በነበረበት ዘመን ነሐሴ ፲፫ ቀን ብርሃ መለኮቱንና ክብረ መንግስቱን የገለጠበት ታሪካዊ በዓል ነው፡፡ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚስተምረውና ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር፡(ማቴ ፲፯÷፬) ይህን በዓል ከቅዱስ ዮሐንስ በቀር ፫ቱም ወንጌላውያን በየወንጌሎቻቸው መዝግበውታል(ማር፬÷፪ ፲፫ ፤ ሉቃ ፱÷28-36)
     ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም “ ከገናናው ክብር ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ከምስጋናን ተቀብሎአልና እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህ ድምጽ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን” በማለት የተገለጸውን ምስጢር ታላቅነት መስክሮአል(፪ኛ ጴጥ፪÷፲፯-፲፰፣በዓላት በዲ.ን ብርሃኑ አድማስ)
     ቅዱሳን ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን ካዩ በኋላ የቃላቸው ትምህርት የእጃቸውም ተአምራት ብቻ ሳይሆን የልብሳቸውም ቁራጭ ጥላቸው ጋኔን ያወጣ ድወይ ይፈውስ ነበር( ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ)
      ይህ ተራራ ከገሊላ ባሕር በምስራቅ ደቡባዊ በኩል ፲ ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 572 ኪ.ሜ ከፍታ አለው፡፡የታቦር ተራራ በሐዲስ ኪዳን በግልጽ ባይጠቀስም በብሉይ ኪዳን ግን ተጠቅሶ እናገኘዋለን(መሳ ፬÷፮-፲፬) ቅዱስ ዳዊትም “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡ ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፡፡ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች(መዝ 88÷12-13) ይላል፡፡ በደብረታቦር ዲቦራም ዘምራበታለች፡፡

      ጌታችን በቂሣርያ ሐዋርያትን “ሰዎች የሰው ልጅን ማን ብለው ይጠሩታል “ በማለት በጠቃቸው ቀን የቀሩት ደቀ መዛሙርት በተራራው ሥር ትቶ ሦስቱን ( ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በተራራው ላይ ሳሉ የጌታችን መልክ ተለውጦ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፡ልብሱም እንደ በረዶ የነጻ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ብርሃነ መለኮቱንና ክብረ መንግስቱን ገለጠ(ሉቃ9÷29)
በደብረታቦር ተራራ ፭  ነገር ተከናውኗል፤
ሙሴና ኤልያስ ሲነጋገሩ ተሰምቷል፡፡
      -መልኩ ተለወጠ (ወተወለጠ አርአያሁ በቅድሜሆሙ) (ማቴ ፲፯÷፪) በዚህ ሰዓት በሐዋርያት ላይ ያደረ ሥጋዊ መንፈስ ራቀ፡ በውስጣቸው ያለው የጨለማ ፍርሃት አሰወገደላቸው( ጥርጥርን አለማመን እነዚህን ነገሮች ሀሉ ከልቡናቸው አስወገደላቸው፤ ፡የእግዚአብሔርን ክብር እንዲያስታውሉ አእምሮቸው ብሩህ ሆነ፡፡በደመና ውስጥ ሁኖ የምወልደው የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን የሚል ቃል ተሰማ ( ዝንቱ ወእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ወሎቱ ሰምዕዎ) ደመና የእግዚአብሔር የክብሩ ምሳሌ ነው፡፡

      ልብሱ እንደ በረዶ ነጻ ( ወአልባሲሁኒ ኮነ ከመ ፀዓዳ)
ጌታችን በደብረ ታቦር ተራራ የብሉይና የሐዲስ ኪዳ ሰዎችን ( ነቢያትና ሐዋርያትን ) አንድ አደረጋቸው፡፡ እሱ አምላካችን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ነውና ፡፡ሌላው ምስጢር ሙሴና ኤልያስ የተጠሩበት ሙሴ ነህ ይላሉ ኤልያስ ነህ ይላሉ ሲሉት እርሱ አምላከ ሙሴ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ሊያሳይ ነው፡፡
       ከነቢያቱ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ “ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም ( ዘዳ 33÷28) በተባለው መሠረት “እባክህ ክብርህን ( ፊትህን) አሳየኝ ይህ ካልሆነማ ባለሟል መባሌ ምኑ ላይ ነው (ዘጸ33÷18-23) የሚለውን የባለሟልነት ጥያቄውን ሙሴን ከሙታን አስነስቶ ስለክብሩ የቀናውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ ክብሩን አሳይቷቸዋል የሙሴን ጸሎት ሳይረሳ ልመናውን ፈጸመለት፡፡
በጀርባ የተመሰለው ከ5500 በኋላ የተፈጸመው ምስጢረ ሥጋዌ ነው፡፡
          ሙሴና ኤልያስ መሆናቸው በምን ይታወቃል?

   ሙሴ ብልቱትነቱ ኤልየስም በፀጉርነቱ አንድም በአነጋገራቸው ታውቋል፡፡ ሙሴም የእኔን የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ይልሃል እግዚአ ሙሴ ይበሉህ እንጂ ኤልየስም የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ይልሃል እግዚአ  ኤልያስ ይበሉህ እንጂ ሲሉ ተሰምተዋል፡፡
       አንደድም ምውት ለሕያው ሕያው ለምውት ሲጸልዩ ተስምተዋል፡፡ አንድም ሙሴ እኔ ባሕር ብከፍል ጠላት ብገድል ደመና ብጋርድ መና ባወርድ እስራኤላውያንን ከክፋታቸው መመለስ አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማደን ይቻልሃልና፡፡
    ኤልያስም እኔ ሰማይ ብለጉም እሳት ባዘንብ እስራኤላውያንን ከክፋታቸው መመለስ አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማደን ይቻልሃልና ሲሉ ተስምተዋል ( አንድምታ ወንጌል ማቴ ምዕ.፲፯)
        ፍጻሜው ግን ደብረታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት፡፡ሕጋውያንም ደናግልም እንዲወርሷት ለማጠየቅ ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ኤልያስን አመጣ፡፡
ይህ በዓል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በተለይም በምእመናን ዘንድ የተለየ ስም አለው( ቡሄ ይባላል)፡፡
   ቡሄ ማለት መላጣ ( ገላጣ) ማለት ነው፡፡ በሀገራችን ክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በደብረታቦር በዓል አካባበር ስለሆነ “ቡሄ “ ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ሊቃውንት "ቤሄ ከዋለ የለም ክረምት ደሮ ከጮኸ የለም ሌሊት”እንዲሉ(የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ- 127-128)
- ሕፃናት የሚያጮሁት ጅራፍ ጩኸት ድምፅ የድምፀ መለኮት ጅራፍ ሲጮህ ማስደንገጡን የሦስቱ ሐዋርያት ምሳሌ ሲሆን  መደንገጣቸው በድምፀ መለኮቱ መደንገጣቸውን መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
   - በአንዳንድ ቦታዎች የቡሄ ዕለት ማታ ችቦ ያበራሉ በደብረታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡
- ምእመናን በድበረታቦር ክብሩን አየን ዛሬም ያ ክበሩ ለገለጥን ያስፈልጋል፡፡ እገዚአብሔር ክብሩን የገለጠበት ያ ተራራ ዛሬ የእኛ አካል ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔር ክብሩና ጥበቡ የሚገለጥበት ማዳኑ የሚታይበት የተባረከ ሕይወት ሊኖረን ይገባል

- የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ
    እንኳን አደረሰን
መንፈሳዊ ጉባኤ:
#ጷግሜን_ለምን_እንጾማለን?

#ጷግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

#በመጠመቃችን_የምናገኘው_ጥቅም_ምንድን_ነው?

#ጷግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል፡፡

#ጷግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያት_ይከፈታሉ ጸሎታችን በሙሉ ያርጋል፡፡

/ዩ ትዩብ ላይ የለቀኩትን ትምህርት በጽሑፍ ቃል በቃል አቅርቤላችኃለሁ/

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደሚታወቀው ወርኃ ጳግሜ፤ ኢትዮጲያን ብቸኛዋ ባለ አሥራ ሦስት ወራት ሀገር ያደርገች ልዩ ወር ናት፡፡ ታዲያ ይህችህ በሦስቱ ወንጌላውያን አምስት ፣ በዘመነ ዮሐንስ በአራት ዓመት ስድስት ቀን የምትሆነው ጳግሜ፣ ብዙ ምስጢር እና ልዩ ጥቅም የላት ወር ናት፡፡

#ጳግሜን_ለምን_እንጾማለን?

የጳግሜ ወር በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የዓለም ፍጻሜ መታሰብያ ወር ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ ጳግሜ የዓመታት መሸጋገሪያ፤ ጨለማው የክረምት ወቅት፤ ወደ ማብቂያው እና የሚያልፍበት፤ እንደ ሆነ ሁሉ፤

ዳግም ምጽዓትም ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፤ ከጊዜያው ወደ ዘላለማዊ መሻጋገሪያ በመሆኑ ጳግሜ የእለተ ምጻት ምሳሌ የሆነችው፡፡ በዚህም ምክንያት የኦርቶዶክስ አማኞች የጳግሜን ወር በሱባኤ በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ፡፡ በገዳም ያሉ አባቶች ጳግሜን በዝግ ሱባኤ ያሳልፋሉ፡፡

በእግርጥ ጳግሜ ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ባትካተትም፤ ጳግሜን በግዴታ ሳይሆን በውዴታ ብንጾም የበረታን ሱባኤ ብንይዝባት፣ የቻልን በታቅቦ ብናሳልፋት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡

አንደኛ በፈቃዳችን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በሱባኤ ብናሳልፍ ጸጋና በረከት ያሰጠናል፡፡ ሁለተኛው ጳግሜ የአዲስ ዓመት መቀበያ የዋዜማ ቀናት በመሆኗ፤ አዲሱን ዓመት በጾም፣ በጸሎት በሱባኤ ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት፣ የረድኤት ይሆንልናል፡፡

አዲሱን ዓመት በተለይም በዋዜማው በመዝናናት፣ በመጨፈር፣ በመጠጣት እና በመዘሞት ከምንቀበል፤ በጸሎት ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት ዓመት፣ ያሰብነው ያቀድነው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሳካበት ይሆናል፡፡

ቅድም እንዳልኩት የገዳም አባቶቻችን የጳግሜን ወር፤ መንፈሳዊ ጥቅም ስለሚያውቁ፤ በፈቃዳቸው በታላቅ ሱባኤ ሆነው ስለ ሀገር፣ ስለ መጪው አዲስ ዓመት መልካምነት ፈጣሪን ይማጸኑበታል፡፡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን እና፣ እነሱ የሄዱበትን መንገድ ተከትለን፤ እንደ እነሱ ልንጠቀም ያስፈልጋልና፤ ወርኃ ጳግሜን በጾም በጸሎት እና በሱባኤ ብናሳልፍ እንጠቀማለን፡፡

በተለይ በአሁኑ ጊዜ እኛም፣ ሀገራችንም ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንም የገጠመን ፈተና፣ እጅጉን ከባድ ነውና እግዚአብሔር እንዲታረቀን፣ ገጸ ምህረቱን እንዲመልስልን፣ ወረርሽኙን እንዲያጠፋልን፣ ለቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንና ለሀገራችን ጽኑ ሰላም እና አንድነት እንዲሰጥልን ወርኃ ጳግሜን እንደ በፊቱ በመብላት በመጠጣት ሳይሆን በጾም በጸሎት ብናሳልፍ ጥቅሙ ለእኛው ነው፡፡

#ጳግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

#በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

እንደሚታወቀው ብዙዎቻችን ወርኃ ጳግሜን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜን የምንጠመቅበት ዋናው ምክንያት ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር የተያያዘ ነው፡፡  

በዚህ በጳግሜ ወር በዓለም ላይ ያሉ ውቅያኖሶች፣ ባህሮች፣ ወንዞች፣ ኩሬዎች ጸበሎች በአጠቃላይ ውሃዎች ሰማይ ተከፍቶ፣ በመላክእት የሚባረኩበት ስለሆነ፤ ጳግሜን የቻልን ጸበል ቦታ ሄደን፣ ወይም በአከባቢያችን ጸበል ካለ እዛም ሄደን፤ መሄድ ባይመቸን፣ ቤታችን ውስጥ ባለው ውኃ ብንጠመቅ እንባረክበታለን፣ ከበሽታችንም እንድንበታለን፡፡

በጳግሜ ጸበል፣ እንኳን የሰው በሽታ፤ በሽታ ያለው እህል፣ በሽታው ይለቀዋል፡፡  ገበሬው ከጳግሜ ወዲያ ነው የሚጠፋውንና የማይጠፋውን እህል የሚለየው፤ በተለይ ዘንጋዳ ጳግሜ ላይ ነው በደንብ የሚያስታውቀው፡፡

በአባባልም ‹‹ዘንጋዳ እና ቡዳ ከመስከረም ወዲያ›› ነው የሚያስታውቀው ይባላል፡፡ የሚገርመው አባቶቻችን ጳግሜ ሦስት ሌሊት ስድስት ሰዓት በተለይ ፏፏቴ ያለው ወንዝ፤ ውሃው ሲቆም ያዩታል፡፡

ቀድሞ አባቶቻን ይህንን ተአምር ለማየት ጳግሜ ሦስት ሌሊት በተለይ ፏፏቴ ያለበት፣ ትልቅ ወንዝ ዳር ሄደው ያድሩ ነበር፡፡ ውሃው ቀጥ ብሎ ሲቆም ሰማይ ሲከፈት ያዩ ነበር፡፡ ጳግሜን በተለይም ጳግሜ ሦስት፣ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በአሉ ስለሆነ፤

በዚህ ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ውሆችን የሚባርክበት፤ እና ለሰው ልጆች በፈጣሪው ጸጋ፤ ድህነት እና ፈውስ የሚያሰጥበት ቀን ስለሆነ ብንጠመቅ ከበሽታችን እንድናለን፡፡

በመጸሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራ 5 ቁጥር 4 ላይ ‹‹አንዳንድ ጊዜ  የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ፣ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኃላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር›› ይላል፡፡

የጌታ መልአክ ‹‹ውኃውን ያናውጥ ነበር›› የተባለው፤ ከሰማይ ወርዶ ውኃውን ይባርከው ነበር ለማለት ነው፡፡ ውኃውም የሚናወጠው የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ሲባርከውና እና በመጠመቂያው፣ ለፈውስ ደጅ የሚጠኑት፣ ህሙማን ውሃው በመልአኩ መባረኩን የሚያውቁት ውኃው ሲናወጥ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ቀድሞ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል፤ በዓለም ላይ ያሉትን ውሃዎች ሁሉ ስለሚባርካቸው፤ ብንጠመቅባቸው እንፈወሳለን፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅዱሳን መላእክትም ውኃውን ይባርኩታል፡፡

ጳግሜ ሦስት ይህ ብቻ አይደለም ሊቀ መልአኩ ያስለመደን ነገር አለ፡፡ ይህም ሁል ጊዜ ጳግሜ ሦስት ሌሊት፣ ጠዋት፣ ከሰዓት አልያም ማምሻ ላይ ይዘንባል፡፡ ይህ ከሰማይ የሆነ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ጸበል ነው፡፡

በልጅነታችን ጳግሜ ሦስትን ‹‹ሩፋኤል አሳድገኝ›› እያልን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜ ሦስት በዘነበው ውኃ መጠመቅ ትልቅ መታደል እና ፈውስ ነው፡፡ በደዌ ይሰቃይ የነበረው ኢዮብም በዚህ ሳምንት ነው ተጠምቆ ነው የዳነው፡፡

የሚገርማችሁ በዚህ በከተማ ብዙም ስለማይታወቅ ነው እንጂ፤ በገጠር እና በክፍለ ሀገር የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነው ዝናብ በእቃ ይቀዳና ይቀመጣል፡፡ በተቀዳው ጸበል ቦሃቃው ይረጭበታል፣ በውሃው እህሉ ይቦካበታል፣ ቤቱ ደጁ ይረጭበታል፡፡

ይህም የሚሆነው የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነበው ውኃ የሰላቢ መንፈስን ስለሚያርቅ ነው፡፡ የሰላቢ መንፈስ ከቤታችን የእህል በረከት የሚያሳጣ፣ ለአንድ ወር ያሰብነውን ለሳምንት የማያዳርስ፣ ለዓመት ያልነው በሦስት ወር እንዲያልቅ የሚያደርግ፤ ክፉ መንፈስ ስላለ ይህን ያርቅልናል፣ በጸበሉ በረከት እህል አስቤዛውን ያበረክትልናል፡፡

እንደምታውቁት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ በመጀመሪያዋ እለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክት ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው

ቅዱስ ሩፋኤል ራማ ላይ ነው ከነ ሠራዊቱ ያረፈው ወይም የከተመው፡፡ በራማም መናብርት ተብለው ለሚጠሩት አሥሩ ነገድ አለቃ ወይም መሪ ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሟል፡፡ በኃላም መጋብያን በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ተሹሟል፡፡

ስለዚህ ጳግሜ ሦስት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሲመት ወይም የሹመት በዓሉ ነው፡፡

ይህንንም እራሱ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በመጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15 ላይ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› በማለት ተናግሯል፡፡
የስሙንም ትርጉም ስንመለከት ‹‹ሩፋ›› ማለት ሐኪም ማለት ነው፡፡ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለትነው፡፡ ሌላው መልአከ ሰላም ወጥዒና ወይም የሰላም እና የጤና መልአክ ይባላል፡፡

የሰው ልጆችን ከተያዙበት ከተለያዩ በሽታውች በጸሎቱ፣ በአማልጅነቱ እንዲፈውስ ስልጣን እና ጸጋ የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው፡፡
ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለት መሆኑን ነብየ

እግዚአብሔር ቅዱስ ሄኖክ በመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 10 ቁጥር 13 ላይ ‹‹በበሽታ ሁሉ ላይ፣ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ፤ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዲሁም እዛው መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 6 ቁጥር 3 ላይ

‹‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መልእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው››  በማለት እግዚአብሔር ለቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የወጣውን፤ ቁስል እና ደዌ፤ ይፈውስ ዘንድ ስልጣን እንደሰጠው፣ ሐኪም እንዳደረገው ነግሮናል፡፡

እንዲሁም ፈታሄ ማሕፀን ይባላል፡፡ እንኳን በምጥ የተያዙትን ሴቶች፣ እናቶች፤ ቀርቶ እንስሳት እንኳን ምጥ ሲፀናባቸው፣ ስሙን ከጠሩት ይፈታቸዋል፡፡ ይህ መልአክ በተለይ ለሴቶች እጅጉን ረዳታቸው ነው፡፡ ከፀነሱበት ጊዜ አንስቶ እስኪወልዱ አይለያቸውም፡፡

በተለይ በእርግዝናቸው ጊዜ ስሙን እየጠሩ፣ መልኩን እየጸለዩ፣ ጸበሉን እየጠጡ እየተዳበሱ፣ ከተማጸኑት ጭንቀታቸውን ያቀላል፣ በሰላም ያዋልዳቸዋል፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ስለ ቅዱስ ሩፋኤል እንዲያሳውቃቸው፣ ክብሩን እንዲገልጽላቸው ጠየቁት፡፡ ጌታም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሩፋኤልን እንደሚመጡ አዘዛቸው፡፡ እነሱም መጡ፡፡

ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ስለ ራሳቸው ከተናገሩ በኃላ ጌታም ቅዱስ ሩፋኤልን ‹‹ክብርህን ንገራው›› አለው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምስጢር ነገራቸው፡፡

በተለይም ስሙን ለሚጠሩ፣ መታሰብያውን ለሚያደርጉ፣ በጸሎቱ ለሚማጸኑ፣ እንደማይለያቸው፣ እንደሚረዳቸው፣ ክብር እንደሚያሰጣቸው ለሐዋርያት ነግሯቸው ወደ ሰማያት አርጓል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያትም በወቅቱ ወንጌልን ሲያስተምሩ፣ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል ክብር እና በእሱ የሚገኘውን መልአካዊ እርዳታ፣ ለምዕመናኑ በደንብ አስተምረዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ልቦናን ደስ የሚያሰኝ፤ ባለ መድኃኒት ፈዋሽ፤ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው፤ በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ፤ የሰውንም ይሁን እንስሳን ማሕፀን የሚፈታ፤ አዋላጅ፣ ምጥን የሚያቀል፣ ታላቅ መልአክ ነውና እንጠቀምበት፡፡

ስለዚህ የቅዱስ ሩፋኤል ቀን የዘነበውን ዝናብ በዕቃ ቀድታችሁ አስቀምጡ፡፡ ያንንም ጸበል ቤታችሁን፣ ደጃችሁን፣ እንዲሁም የሥራ ቦታችሁን እርጩበት፣ እየቆጠባችሁ እህል ስታቦኩ አብኩበት ጠጡት ተጠመቁበት፡፡ ብዙ በረከት እና ፈውስ ታገኙበታላችሁ፡፡

እህል እና ገንዘብ የሚሰልብባችሁን የሰላቢ መንፈስ ያርቅላችኃል፡፡
ውጭ ሀገር ያላችው እህት ወንድሞቼ ጸበል መጠመቅ ስለማይመቻችሁ፤ ውኃ አቅርባችሁ፣ ያስለመዳችሁትን ጸሎት ውሃው ላይ ጸልያችሁ ‹‹አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል›› ባርክልኝ ብላችሁ ቤት ውስጥ ተጠመቁ ጠጡት፡፡

ጳግሜን መጠመቅ ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የነበረ እና በየአመቱ ጳግሜን መጠመቅ የሚናፈቅ ጊዜ ስለሆነ ተጠቀሙበት፡፡ በዚሁ አጋጣሚ እኛም እንጦጦ ማርያም ጳግሜን የጸበል አገልግሎት ስለምንሰጥ መጥታችሁ መጠመቅ ትችላላችሁ፡፡

#ጳግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያትይከፈታሉ_ጸሎታችን_በሙሉ_ያርጋል፡፡

ጳግሜ ሦስት ርህወተ ሰማይ ይባላል፡፡ ርኅወተ ሰማይ ማለት የሰማይ መከፈት ማለት ነው፡፡ ይህም የሰማይ መስኮቶች ወይም ደጆች የሚከፈቱበት እለት ነው፡፡ ርኅወተ ሰማይ ወይም የሰማይ መከፈት ሲባል፤ በሰማይ መከፈት እና መዘጋት ኖሮበት ሳይሆን፤

ቅዱሳን መላእክት የሰውን ልጆች ጸሎት፣ ልመና፣ ያለ ከልካይ፤ ወደ እግዚብሔር የሚያሳርጉበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ እንዲሁም ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገበ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ ነው ርኅወተ ሰማይ የተባለው፡፡

በእርግጥ በንስሐ ሆኖ ለሚጸልይ ሰው ለእርሱ ሁሌም የሰማይ ደጅ የተከፈተ ነው፡፡ ከዓመት ተለይታ ጳግሜ ሦስት የሰማይ መስኮቶች፤ ወይም ደጆች በሙሉ ተከፍተው፣ የምዕመናን ጸሎት በተለየ ሁኔታ የሚያርግበት ጊዜ እንደ ሆነ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስትያንም ይነግሩናል፡፡

ስለዚህ በዚህም ቀን ማለትም ጳግሜ ሦስት ያስለመድናቸውን ጸሎቶች፤ አንዳንዶቻችንም ያቋረጥናቸውን ጸሎቶች፤ በርትተን ብንጸል ቅድመ እግዚብሔር ይደርሳል፡፡

በዚህችም ቀን የጸለይነውን ጸሎቶች፤ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅዱሳን መላእክት ቅድመ እግዚብአብሔር ያሳርጉልናል፡፡ በዚህችም እለት የእግዚአብሔር ምህረት እና ቸርነት ለሰው ልጆች የሚወርድበት ታላቅ እለት ነው፡፡

አባቶቻችን እንደሚነግሩን ከሆነ፤ ጳግሜ ሦስት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ፤ ያስለመዱትንና ሌሎችንም ጸሎቶች ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ እነሱ ማድረግ ባንችል፤ የበረታን ሌሊት ስድስት ሰዓት፤ የቻልን ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተን ጸሎት ልንጸልይ ይገባናል፡፡

#ጳግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደምታውቁት ያለንበት ጊዜ አጋንንት ተፈቶ የተለቀቀበት፣ ሰው በክፋት ከአጋንንት ያልተናነሰበት አንዳንዴም የሚበልጥበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ በተለይ ብዙ ምዕመናን በመተት በድግምት እድላቸው ተወስዶ፣ ሕይወታቸው ባዶ እየተደረገ ነው፡፡

አጋንንት ጎታቾች እና መተት መታቶች ጳግሜን በሰው ላይ የሚመትቱትን መተት የሚያድሱበት ስለሆነ ጸበል በርትተን ብንጠመቅ እድሳታቸው ይሽራል፣ መተታቸውም ይከሽፋል፡፡ ስለዚህ በዚህ በወርኃ ጳግሜ በመተት እና በድግምት የምትሰቃዩ ወገኖቼ በርትታችሁ ጸበል ተጠመቁ ጠጡ፡፡

ምክንያቱም ዓመቱን ሙሉ በእድላችን ሲመተት ወደ እና ሕይወት ሲጎተት የነበረው አጋንንት ጳግሜን በርትተን ከተጠመቅን አጋንንቱ አዲሱን አመት አይሻገርም፡፡

በተመተተብን መተት እና በበላነው ድግምት ውስጣችን በተለይ ሆዳችን፣ እንዲሁም መላ አካላታችን ላይ ደዌ ሆኖ የተቀመጠው አጋንንት ይለቀናል፣ ውስጣችን ያለው የደዌ መተት ይሻራል፡፡
እንዲሁም በአውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን በቅዱስ ዮሐንስ ስም አስታከው ዛር አንጋሾች፤ ለዛር ደም የሚያፈሱበት፣ የሚገብሩበት ጊዜ ነው፡፡

አዲሱን አመት ደም በማፍሰስ፣ ለዛር በመገበር ስለሚቀበሉ ጸበል መጠመቁ ከእዚህ ችግር እናመልጣለን፡፡ በተለይ ቤተሰባችሁ በቅዱስ ዮሐንስ የሽፋን ስም ‹‹ለዓውደ ዓመት ነው፣ ለአድባር ነው፣ አዲስን ዓመት ለመቀበት ነው፣ የእናት አባታችን የአያቶቻችን አምላክ እንዳይጣላን ነው፣

በአዲሱ ዓመት ጠላታችን ደሙ እንዲፈስ ነው፣ ደም የምናፈሰው የእኛን ጦስ ይዞ እንዲሄድ ነው›› በማለት ገብስማ፣ ወሰራ፣ ባለ ነጠላ ዶሮ፤ ነጭ፣ ቀይ በግ እያሉ ያረዱትን እንዳትበሉ፡፡

አውቃችሁ በዮሐንስ ስም ለዛር የተገበረለትን ብትበሉ በደም የገባውን ዛር፤ በጸበል ለማስወጣት ትቸገራላችሁ፡፡ በቤታችሁ፣ በአከባቢያችሁ እንደዚህ አይነት ክፉ ልማድ ካለ ተቃወሙ፣ ለማስተው ሞክሩ፡፡ የእነሱ እዳ ነው ነገ ለእናንተ የሚተርፈው፡፡

በተረፈ ይህችን ወርኃ ጳግሜን እንደ አባቶቻችን እንድንጠቀምባት አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል ይርዳን፡፡
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
🌿🍂🌿🍂🌿

84 ዓመት

     መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሀና 84 ዓመት ቀንና ለሊት በፆምና በፀሎት፣ እለት እለት እያገለገለች ከቤተመቅደስ አትለይም ነበር ይላል። "እለት እለት" ሊያውም ቀንና ለሊት። ይሄ ሁሉ ዓመት ፈተና ሳይኖር ቀርቶ አይደለም።
   እኛ አንድ ግዜ እንመጣለን አንዴ እንቀራለን፣ ቀላል በሆኑ ምክንያቶች ወደኋላ እንቀራለን።
    ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በመኖሯ ምን አመጣላት እኛስ ብንኖር ምን እናገኛለን ለሚለው መልስ - እመቤታችን ጌታን ይዛው በ40 ቀኑ ወደ ቤተመቅደስ ሲመጣ ሀና እሱን ለማየት በቃች። በዚያች ቅፅበት የሌለ ሰው እኮ አያገኘውም።
    ሚል 3 - የምትጠባበቁት ጌታ ድንገት በመቅደሱ ይገለጣል ይላል። መቅደሱ እኮ ሁሌም ቤቱ ነው ድንገት ይገለጣል ማለት ፀጋ የሚሰጥበት፣ ክብር፣ ኃይል የሚያድልበት፣ እለተ በረከት አለው።
ስንመኘው የነበረው፣ እግዚአብሔርን ስንለምነው የነበረውን ነገር ሊሰጠን ሲመጣ እኛ ደግሞ ከቤቱ እንዳንጠፋ።  በትጋታችን ልክ ዋጋ እንቀበላለን።
    በክርስትያን ህይወት ከሁሉ ከሁሉ ምን ይቀድማል? የሚቀድመው ቤ/ክ መምጣት ነው! ሳይመጡ መማር የለም፣ ሳይመጡ ማወቅ የለም፣ ሳይመጡ ንስሃ የለም፣ ሳይመጡ ቁርባን የለም፣ ሳይመጡ መለወጥ የለም። የአንድ ክርስቲያን የመጀመሪያው ስራው ወደ ቤ/ክ መምጣት ነው። ከመጡ ነው ማወቅ መሻሻል ያለው።

@KaleEgziabeher