Kaffa Zone Revenue Department
112 subscribers
696 photos
3 videos
1 file
91 links
ይህ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ የቴሌግራም ገፅ ነው
Download Telegram
ለታክስ ሕግ ተገዥ ያለመሆን መገለጫዎች

ነሐሴ 25/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

ለታክስ ሕግ ተገዥ አለመሆን ማለት የግብር እና የቀረጥ ግዴታዎችን በትክክለኛው መንገድ አለመወጣት ነው፡፡
ለታክስ ህግ ተገዥ ያለመሆንን ከሚያሳዩ መገለጫዎች ውስጥ፡-
👉ደረሰኝ አለመቁረጥ፣
👉 በግብር ከፋይነት አለመመዝገብ፣
👉 ግብርን በወቅቱ አለማሳወቅ እና አለመክፈል፣
👉 የተሳሳተ መግለጫ መስጠት (ገቢን ማሳነስ እና ወጪውን ማብዛት)
👉 የማይገባውን ተመላሽ መጠየቅ፣
👉 አላግባብ በተደጋጋሚ ኪሳራ ማሳወቅ፣
👉 የግብር ቅናሽ ማድረግ፣
👉 የሽያጭ መመዝገቢያን ማሽን በአግባብ አለመጠቀም በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው ።
1👍1
የተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ የማስረዳት ኃላፊነት እና አዲስ ማስረጃ ማቅረብን በተመለከተ ምን ይላል?

ነሐሴ 25/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 አንቀጽ 59 መሰረት ከታክስ ውሳኔ ጋር በተገናኘ በሚደረግ ማናቸውም የታክስ ክርክር ሂደት የታክስ ውሳኔ ትክክል ያለመሆኑን የማስረዳት ኃላፊነትን እና አዲስ ማስረጃ ማቅረብን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል፡-
ከታክስ ውሳኔ ጋር በተገናኘ በሚደረግ ማናቸውም የታክስ ክርክር ሂደት የታክስ ውሳኔ ትክክል ያለመሆኑን የማስረዳት ኃላፊነት የታክስ ከፋዩ ነው፡፡

በዚህ አዋጅ መሰረት ቅሬታ፣ ይግባኝ ወይም የውሳኔ ማስተካከያ ጥያቄን የሚያቀርብ ታክስ ከፋይ በታክስ ውሳኔ ወቅት ካቀረበው የተለየ አዲስ ማስረጃን ማቅረብ አይችልም፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ ቢኖርም አዲስ ማስረጃ በቅሬታ፣ ይግባኝ ወይም ስህተትን ለማረም በሚቀርብበት ወቅት ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው፦
👉 የማስረጃው አለመታየት በታክስ ከፋዩ የታክስ እዳ ላይ ከፍተኛ ጫናን የሚያስከትል ከሆነ፤
👉 ታክስ ከፋዩ ማስረጃውን ያገኘው የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሰው በኋላ ከሆነ፤ ወይም
👉 ሰነዱ ያልቀረበው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከሆነ፤ ይሆናል፡፡

በዚህ አዋጅ መሰረት “አዲስ ማስረጃ” ማለት የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሰው በኋላ በታክስ ከፋዩ የሚቀርብ አዲስ ሰነድ፤ መረጃ፤ ማስረጃ፤ ፍሬ-ነገር ሲሆን፤
👉 በመጀመሪያው የታክስ አወሳሰን ሂደት ለታክስ ባለስልጣኑ ያልቀረበ፤
👉 ለታክስ ውሳኔ ማስታወቂያው ትክክለኛነት አግባብነት ያለው እና መሰረታዊ የሆነ፤ እና
👉 በተወሰነው የታክስ መጠን ወይም በታክስ ከፋዩ ግዴታ ላይ መሰረታዊ ለውጥ የሚያስከትል ነው፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የተዘጋጀ
በተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ንዑስ አንቀጽ 29 መሠረት ከዲጅታል ይዘት ፈጠራ ከሚገኝ ገቢ ግብር እንዲከፈልበት ተደርጓል

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በዚሁም መሠረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ማለት አንድ ግለሰብ፣ ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግሎቶችን፣ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም የገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ ነው።

ይህም የሚከተሉትን ገቢዎች ያካትታል፦

ሀ) ማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣
ለ) የምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣
ሐ) የአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች
መ) የደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ የገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ
(ክራውድ ፈንዲንግ)፣
ሠ) የአባልነት ክፍያዎች፤
ረ) የዲጂታል ወይም የአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣
ሰ) ለማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች እና
ሸ/ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎች፡፡
የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ስለመፍታት

ነሐሴ 27/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 አንቀጽ 61 የታክሱ ባለስልጣን የታክስ አለመግባባትን በመስማማት ለመፍታት ያለውን ስልጣን በተመለከተ የሚከተለውን ይላል፡-

👉 የታክሱ ባልስልጣን የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ስልጣን ተሰጥቶታል።
👉 ማናቸውም በስምምነት የሚፈታ የታክስ ያለመግባባት በጽሁፍ የሚደረግ እና የተስማሚ ወገኖች ፊርማ ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
👉 የታክስ አለመግባባቶችን በመስማማት የመፍታት ስልጣን የሰጠው ድንጋጌ ቢኖርም የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ጉዳዩ በማስማማት ሊታይ አይችልም፦
1. የታክስ ማጭበርበር ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ ታክስን የመሰወር ድርጊት መኖሩ ወይም ሌላ ከታክስ ጋር የተገናኘ ወንጀል መኖሩ ሲጠረጠር፤
2. በማስማማት የሚደረግ ስምምነት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት እና ከሚመለከታቸው የታክስ ሕጎች ጋር የሚጋጭ ሲሆን፤
3. ከሁለቱ ወገኖች አንዱ በሽምግልና ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ካልሆነ።
👉 ሚኒስቴሩ የአስማሚውን የትምህርት እና ሙያ ደረጃን ጨምሮ የመስማማት ሂደት የሚመራበትን ሥርዓት የሚወስን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ያወጣል፡፡
በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ

ነሐሴ 27/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ፣ የግብር ክፍያ የመጨረሻ ጊዜ ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

በመሆኑም የግብር ክፍያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት እስከ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም. ድረስ ግብራችሁን እንድትከፍሉ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በአክብሮት ያሳስባል።
የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያን ለማስተካከል የሚያስችሉ ምክንያቶች

ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 አንቀጽ 96 መሰረት በታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ላይ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችለው፦

👉 የስሌት ወይም የሂሳብ ስህተት ያለ ከሆነ፤
👉 በታክስ አወሳሰን ወቅት ያልታየ አግባብነት ያለው ማስረጃ ወይም በዚህ አዋጅ መሰረት የቀረበ አዲስ ማስረጃ ያለ እንደሆነ፤
👉 የታክስ ውሳኔው አስገዳጅ ከሆነው የታክስ ህጎች ትርጉም ጋር የማይጣጣም ከሆነ፤ ወይም
👉 ታክስ የመክፈል ግዴታን በመወሰን ረገድ የተሳሳተ ውጤት የሚያስከትል ሌላ ስህተት ካለ ነው፤
በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ

ነሐሴ 28/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ፣ የግብር ክፍያ የመጨረሻ ጊዜ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

በተጨማሪም ለቁርጥ ግብርና የአከራይ ተከራይ ግብር ከፋዮቻችን የግብር ውሳኔ ያልደረሳችሁ ከዛሬ ጀምሮ በየወረዳችሁ በሚገኘው ገቢ ተቋም በመገኘት የግብር ክፍያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት እስከ ነሐሴ ዓ.ም. ድረስ ግብራችሁን እንድትከፍሉ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በአክብሮት ያሳስባል።

ከነሐሴ 30/2018 በኋላ አስተዳደራዊ ቅጣት እና ወለድ ታክሎበት እንደምትከፍሉ እናሳስባለን።

ግብሮን በጊዜ ይክፈሉ ከአላስፈላጊ ቅጣት እና ወለድ ራሳችሁን ጠብቁ።

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ

ነሐሴ 28/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ፣ የግብር ክፍያ የመጨረሻ ጊዜ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

በተጨማሪም ለቁርጥ ግብርና የአከራይ ተከራይ ግብር ከፋዮቻችን የግብር ውሳኔ ያልደረሳችሁ ከዛሬ ጀምሮ በየወረዳችሁ በሚገኘው ገቢ ተቋም በመገኘት የግብር ክፍያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት እስከ ነሐሴ ዓ.ም. ድረስ ግብራችሁን እንድትከፍሉ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በአክብሮት ያሳስባል።

ከነሐሴ 30/2018 በኋላ አስተዳደራዊ ቅጣት እና ወለድ ታክሎበት እንደምትከፍሉ እናሳስባለን።

ግብሮን በጊዜ ይክፈሉ ከአላስፈላጊ ቅጣት እና ወለድ ራሳችሁን ጠብቁ።

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ።
በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ

ነሐሴ 29/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

በካፋ ዞን ለምትገኙ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች በሙሉ፣ የግብር ክፍያ የመጨረሻ ጊዜ ሊጠናቀቅ 1 ቀን ብቻ ቀርተዋል።

በተጨማሪም ለቁርጥ ግብርና የአከራይ ተከራይ ግብር ከፋዮቻችን የግብር ውሳኔ ያልደረሳችሁ ከዛሬ ጀምሮ በየወረዳችሁ በሚገኘው ገቢ ተቋም በመገኘት የግብር ክፍያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት እስከ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም. ድረስ ግብራችሁን እንድትከፍሉ የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ በአክብሮት ያሳስባል።

ከነሐሴ 30/2018 በኋላ አስተዳደራዊ ቅጣት እና ወለድ ታክሎበት እንደምትከፍሉ እናሳስባለን።

ግብሮን በጊዜ ይክፈሉ ከአላስፈላጊ ቅጣት እና ወለድ ራሳችሁን ጠብቁ።

የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ።
የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ተጠቃሚ ታክስ ከፋይ የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩበታል፦

ነሐሴ 29/2018 (የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ)

የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ ለሚያደርገው ማንኛውም ሽያጭ የተመዘገበ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መስጠት አለበት፡፡

የታክስ ባለስልጣኑ በማንኛውም ሰዓት በታክስ ከፋዩ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ላይ ፍተሻ በሚያከናውንበት ጊዜ ተገቢውን መረጃ የመስጠት፣ የባለስልጣኑ ሠራተኞች ሥርዓቱን እንዲያዩ/እንዲፈትሹ ፈቃድ የመስጠት እና ለሂደቱ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

በግብይት ወቅት ገዥው በደረሰኝ ላይ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ፣ የመታወቂያ ቁጥር ወይም የስልክ ቁጥር እንዲመዘገብለት ከጠየቀ መመዝገብ ግዴታ አለበት፡፡

የተፈቀደው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ከታክስ ባለስልጣኑ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምዝገባ ሥርዓት ጋር መገናኘት በማይችልበት ጊዜ የተደረጉ ግብይቶችን በሙሉ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምዝገባ ሥርዓት ጋር እንደተገናኘ በ72 ሰዓት ውስጥ መመዝገቡን እና ለገዥው ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መስጠቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡

📌 ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ በባለስልጣኑ ያልተፈቀደ ማንኛውንም አይነት የሶፍትዌር ለውጥ እና ማሻሻያ ማድረግ አይችልም፡፡
Did you follow our social media accounts
Anonymous Poll
100%
Yes
0%
No