ፍትህ ለሙስሊሞች
31 subscribers
214 photos
18 videos
22 links
Islamic news
............ hadis
And so on
Download Telegram
በሃገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር የፊታችን
እሁድ ይካሄዳል!
በመጪው እሁድ ሰኔ 5/2014 በአዲስ አበባ ስቲዲዮም ለሚካሄደው ዓለም
አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር በርካታ እንግዶች እየገቡ ይገኛሉ ።

ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራው ይህ ውድድር ከ56 በላይ ሀገራት
የሚወዳደሩበት ሲሆን ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል ።

ውድድሩን በዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነትና በአገሪቱ ከሚገኙ
የተለያዩ የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ታላላቅ ድርጅቶች ጋር በመተባበር
የሚካሄድ ነው:
ውድድሩ በሦሥት ዘርፎች የሚካሄድ ሲሆን በአዛን በቁርአን ሒፍዝና በ30ጁዝዕ
የድምጽ ውድድር ይካሔዳል።

እስካሁን ድረስ ባለው መረጃም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተወዳዳሪዎች ዳኞች
እንዲሁም ታዳሚዎች እንደገቡና እየገቡ መሆኑን ተገልጿል።
በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ ሁላችንም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ
ስታድየም በመገኘት የሃገራችንን ስም ከፍ አድርገን ለአለም ልናስተዋውቅ
ይገባል::
በሃገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል!

በመጪው እሁድ ሰኔ 5/2014 በአዲስ አበባ ስቲዲዮም ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር በርካታ እንግዶች እየገቡ ይገኛሉ ።

ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራው ይህ ውድድር ከ56 በላይ ሀገራት የሚወዳደሩበት ሲሆን ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል ።

ውድድሩን በዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነትና በአገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ታላላቅ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚካሄድ ነው:

ውድድሩ በሦሥት ዘርፎች የሚካሄድ ሲሆን በአዛን በቁርአን ሒፍዝና በ30ጁዝዕ የድምጽ ውድድር ይካሔዳል።

እስካሁን ድረስ ባለው መረጃም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተወዳዳሪዎች ዳኞች እንዲሁም ታዳሚዎች እንደገቡና እየገቡ መሆኑን ተገልጿል።

በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ ሁላችንም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም በመገኘት የሃገራችንን ስም ከፍ አድርገን ለአለም ልናስተዋውቅ ይገባል::

ለበለጠ መረጃ
በዚህ ይደውሉ
0911755245
0911723051
ከካይሮ እስከ ራባት፣ ከማራካሽ እስከ ዶኻ የአረብ ተወላጆች የሆኑ እግር ኳስ
ወዳጆች በሙሉ መላው ትዊተርን Abubeker በሚለው ስም
አጥለቅልቀውታል።
.
- "ይሄ ልጅ በኛ 4 ተከላካዮች መሃል ሰፊ አስፋት መስራት ይችላል!" ...
- "እውን አቡበከር ናስር ከፈርናንዶ ቶሬስ አይበልጥም?" ...
- "ይሄ የላቀ ብቃት ያለው ልጅ ያደገው የጥበበኞች መፍለቂያ በሆነው በፈረንሳዩ
ሞናኮ ክለብ ካልሆነ ለዘላለም መገረሜ ይቀጥላል። ...
.
- "አቡበከር ሲጫወት ካየህ ፕልይስቴሽን እንዳይመስልህ! እመነኝ እወነተኛ
ጨዋታ ነው።" ...
- "የዚህ ልጅ አጨዋወት ተዓምራዊ አስማት ነው እንጂ ችሎታ ብቻ
አይደለም።" ...
- "ይሄ ቀጭን ልጅ ለ4ቱ ተከላካዮቻችን መንፈስ ሆኖባቸው አመሸ" ...
.
አረቦቹ በትዊተር ላይ ስለአቡበከር ከፃፉት ጥቂቱ ነው።
ፍርድ ያውቃል ንጉሴ
<<እናቴም አባቴም መስዋት ይሁንልሁ ያ ረሱሉሏሕ [ሰ.ዓ.ወ]>> የኳታር
ብሔራዊ የእግርኳስ ክለብ ከግጥሚያ መክፈቻ ጫዎታ በፊት ያሳዩት ባነር!
ነብዩ ሙሐመድን በሰደበው የሕንድ ገዢው ፓርቲ መግለጫ በማውገዝ
ድምፃቸውን አሰምተዋል
የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድድ 2022 እሁድ በድምቀት
ለሚከናወነው የፍጻሜ ውድድር ለማለፍ በዛሬው ዕለት የማጣሪያ ውድድር
ይከናወናል።
በዛሬው ዕለት የማጣሪያ ውድድር የሚያልፉ ተወዳዳሪዎች እሁድ
ለሚከናወነው የፍጻሜ ውድድር የሚያልፉ ይሆናል።
የቁርአን ውድድሩን ትኬቶች በሁሉም የሂጅራ ባንክ ቅርንጫፎች ማግኘት
ይቻላል!
እየገዛችሁ! እየተገባበዛችሁ!!!
የነጃሺ፣ የቢላል፣ የኡሙ
አይመን ሀገር የፊታችን እሁድ
በአዲስ አበባ ስታዲየም
በቁርዓን ትደምቃለች! የቁርዓን
ባለቤቶችን እንድናልቃቸው
ባስተማሩን ነብይ ላይ ሰለዋትን
እናውርድ!ﷺ
እሁድ በስቴዲም ለሚደረገው አለም አቀፍ የቁርዓን ኺፍዝ ውድድር የማጣርያ
ውድድሩ በዛሬው እለት እየተካሔደ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ
ዑለሞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የማጣርያ ውድድሩ በቁርዓን ተከፍቷል። መረጃዎችን ከምስል ጋር ወደናንተ
ማድረሳችንን እንቀጥላለን።
የፌዴራል መጅሊስ ጊዜያዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ
በድረዲን ለእንግዶቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ
ይገኛሉ።