የጅንካ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የሠላም ፎረም JKU student PEASE FORUM🙄🙄🙄
172 subscribers
41 photos
4 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE

• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

• 200, 000  ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ  እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ " ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ  በመሆኑ ነው " ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው #ከወዲሁ_ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት(1/04/2015 ማለዳ 12:00 ሰዓት ) በዩኒቨርሲቲያችን ባተከናወነው የፅዳት መረሃ ግብር ላይ ሙሉ የተማሪዎች አደረጃጀት ማለትም የተማሪዎች ሰላም ፎረም,የተማሪ ፖሊስ, የተማሪዎች ህብረት እንዲሁም በክበባት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን ያሳተፈ ሲሆን የዩኒቨርስቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አለሙ አይላቴ ይህ የፅዳት መርሃግብር በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለዚህ መርሃግብር የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች በቀጣይነት እደሚሟሉ ገልፀዋል። ሰላም ለሁሉም!!!!
Today (1/04/2015 at 12:00 am) in the cleaning program carried out in our university, the entire organization of students, namely students' peace forum, student police, students' union and students in clubs, and the vice president of the university's administration and student services, Dr. Alemu, participated. stated that this cleaning program will continue to be strengthened and the equipment needed for this program will be continuously replenished. Peace for all!!!
ቋንቋ እና የዘር ማንነት ባለቤት የለውም

ሰው ራሱ አስቦ በእውቀቱ ለሚፈጥረው ፈጠራ ምናልባት የተለያዩ ምርጫዎች ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን በደመነፍስ ላገኘው እውቀት ግን ምርጫ የለውም፡፡ ለምሳሌ ሰው ምግብ መመገብ፣ መተንፈስ፣ መዋለድ፣ ውሃ መጠጣትን፣ በአጠቃለይ የሰውነቱን የአሠራር ሥርአት ሰው ፈልጎትና መርጦ ያገኘው አይደለም፡፡ ነገር ግን ዘረመላዊ በሆነ ንድፍ ተቀብሎት በደመነፍስ የሚኖረው ኑሮ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም የሰው አካል ክፍል ራሱ አውቆ የተመደበለትን
ሥርዓት ያለ ሌላ ሰው እገዛ ይፈጽማል፡፡ ደመነፍሳዊ የሆነ ሁሉ አስቀድሞ በተፈጥሮ የተነደፈ የዘረመላዊ ክህሎት የአዕምሮ ቅኝት ነው፡፡ ለምሳሌ አዕዋፍ ጎጆቸውን ሲሰሩ ደመነፍሳዊ ነው:: ይህም በአዕዋፍ ዘረመል ውስጥ አስቀድሞ በተፈጥሮ የተነደፈ የአዕዋፋት የአዕምሮ ቅኝት ስለሆነ ነው፡፡ ማንም ሰው ሲወለድ የዚህ ቋንቋ ተናጋሪ ልሁን ብሎ መርጦ የሚናገረው ቋንቋ የለም፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰብ ይወለድ፣ ተወልዶ ካደገ በኋላ ቤተሰቡን በገበያና በማሕበራዊ ኑሯቸው ያስተሳሰራቸውን ቋንቋ እየተናገረ ራሱን ያገኘዋል፡፡

ስለሆነም ማንም ሰው በግሉ ይሁን በቡድን አንድን ቋንቋ የእኔ ፈጠራ ነው ብሎ ህጋዊ የፈጠራ ባለቤትነት የምስክር ወረቀት የለዉም፡፡ ስለዚህ ሰው  የትኛውንም ቋንቋ ለኑሮው እስካስፈለገው ድረስ የማንንም ፈቃድ ሳይጠይቅ የመናገር መብት አለው፡፡

ቋንቋ ለሰው የተቸረ አንድ ችሎታ ይሁን እንጂ፣ ዘረመላዊ ንድፍን የያዘ ክህሎት ነው፡፡ በመሆኑም እንስሳት ዘረመላዊ የሆነ ክህሎታዊ ንድፍ ስሌላቸው ቋንቋን መናገር አይችሉም፡፡ ቋንቋ የሰው ዘረመላዊ ችሎታ ነው ሲባል የሰውን አጠቃለይ ቋንቋን የመናገር ችሎታን ተጨባጭነት መግለጽ ማለት እንጂ፣ አንድ ቋንቋ ለአንድ ሰው ዘረመላዊ ነው ማለት አይደለም፡፡ አንድ ህጻን ሲወለድ ወላጆቹ የሚናገሩት ቋንቋ በወላጆቹ ዘረመል በኩል ወደ ልጁ አይተላለፍም፡፡ ለልጁ በወላጆቹ ዘረመል በኩል የሚተላለፈዉ ግን እንደ ወላጆቹ ማንኛዉንም ቋንቋን በመልመድ የመናገር ችሎታ ነዉ፡፡ ለምሰሌ፤ አንድ ህጻን በእናቱም በአባቱም ነጭ እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው ሆኖ እንደተወለደ ምንም ቋንቋ መናገር ሳይጀምር ወደ የተኛውም ክፍለ ዓለም ወደሚገኝ አንድ የቋንቋ ተናገሪ ማህበረሰብ ሄዶ ሲያድግ የዚያን ማህበረሰብ ቋንቋ ይናገራል እንጂ፣ የእናቱና የአባቱም ቋንቋ እንግሊዝኛ ስለሆነ በዘረመል ተላልፎበት እንግሊዝኛ ቋንቋን እንዲናገር አያስችለውም፡፡

እያንዳንዱ ቋንቋ ራሱን የቻለ ዘረመላዊ ቋንቋ ቢሆን ኖሮ ሰው ሁሉ ወደ ተለያየ ሀገራት ሲሄድ የተለያየ ቋንቋን በመልመድ ለመናገር ባልቻለ ነበር፡፡ በመሆኑም ለምሳሌ ከኢትዮጵያ ከየትኛውም አይነት ቋንቋ ተናጋሪ ወደ አሜሪካን ሀገር ይሁን ወደየትኛውም የአውሮፓ ሀገር ሄደው ሲኖሩ የሚኖሩበትን ሀገር ቋንቋ በመልመድ መናገር ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ኑሯቸው ወሳኝ ስለሆነ በሚሰሩበት ስፍራ ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ይናገሩት የነበሩትን ቋንቋ አቁመው የሄዱበትን ሀገር ቋንቋ በመልመድ መናገር ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ ሰዉ የሚናገረዉ ቋንቋ በጊዜና በቦታ ተለዋዋጭ በመሆኑ “የእኔ ቋንቋ” በማለት ሌላውን ቋንቋ በመጥላት ማክረር መገለጫው ቂልነት የሆነ የአእምሮ ቅዠት ነው።

አንድ ሰው አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሚናገራቸው ቋንቋዎች ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዱን ቋንቋ ለይቶ “የኔ ቋንቋ” ማለት፣ ቋንቋውን የብሔር” ማንነቱ መገለጫ ማድረግ
ስለሚናገረው ቋንቋ ሲል ሰውን ከሰው ለይቶ ማግለልና መጥላት ከጀመረ እንደዚህ አይነት ሰው በሚያሳዝን ሁኔታ በአዕምሮ ቅዠት ህመም የሚሰቃይ ሰው ነው፡፡

ማንም ሰው ቋንቋ ያስተላለፈውን አሰተሳሰብ ሊወደው ወይም ሊጠላው
ይችላል:: ነገር ግን ቋንቋን መዉወድና መጥላት ግን ቂልነት ነዉ፡፡ ለምሳሌ፡
በድሃ ሀገራት በዋናነትም በአፍሪካ ውስጥ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራትን አንድን ቋንቋ መሠረት በማድረግ የቋንቋውን ተናጋሪ ህበረተሰብ የቋንቋው ባለቤት እያደረጉ በማቃዠት ”ለብሔር” ማንነቱ በፖለቲካ ፓርቲ ስም ያደራጃሉ፡፡ በመሠረቱ ፖለቲካ በችግር ፈቺነቱ የሰውን ማንነት ማዕከል ያደረገ ሳይንስ እንጂ፣ የብሔር ማንነትን ወይም ቋንቋን ማዕከል ያደረገ የናዚያዊ ወይም የፋሽስታዊ  የአዕምሮ ቅዠት ህመም አይደለም፡፡  የጀርመን ናዚያዊና የጣሊያን ናፋሽስታዊ
አገዛዝ ሲጀመር የተለከፉበት ሰብአዊነት በጎደለው  ማንነታቸው የአዕምሮ ቅዠት ህመም ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ በወንጀለኛነታቸው ተወግዘው ለሚጠፋ ከንቱና ዘለቄታ በሌለው "በብሔር” ማንነት የአዕምሮ ቅዠት ህመም አስተሳሰብ ምክንያት ስንት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ታሪክ ይቁጠረው፡፡

ቋንቋ ሰውን አይጠላም፣ ሰውንም አይጨቁንም፡፡ አስተሳሰብ ግን ሰውን ፣ሊገድል፣ ሊጠላ፣ ሊበቀል፣ ሊጨቁን፣ ነጻ ሊያወጣ፣ የተሻለ የኑሮ ደረጃን ሊያስገኝ ወዘተ. ይችላል፡፡ ለክፉም ይሁን ለመልካም የሰው አስተሳሰብ እንጂ ተጠያቂው አስተሳሰቡን ያስተላለፈበት ቋንቋ አይደለም፡፡ አስተሳሰብ የሚፈጽመው የድርጊት ወንጀል እንጂ ቋንቋ አይከሰስም፡፡

ስለዚህ ቋንቋ የሰው ማንነትን አይገልጽም፡፡  ማንኛውም ቋንቋ የሰው ማንነትን ስለማይሸከምና ባለቤትም ስለሌለው ማንም ሰው እስገፈለገ ድረስ ቋንቋን የመልመድ ሀገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ መብት አለው፡፡ ለቋንቋ ህይወት የሚሰጠው ቋንቋው የተሸከመው አስተሳሰብ እንጅ ቋንቋ ራሱ ብቻውን ሕይወት የለውም፡፡ ቋንቋ ያለሃሳብ አይኖርም፤ በመሆኑም እንስሳት ስለማያስቡ ቋንቋ የላቸውም፡፡ ሰው እንጂ ቋንቋ ዜግነት የለውም፡፡ አንድ ሰው አፍ የፈታበት ቋንቋ ይሁን ሌላ የሚናገረው ቋንቋ ዘረመላዊ አይደለም፡፡ ስለሆነም ቋንቋ ማንነት የለውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በመልኩ፣ በስሙ፣ በዜግነቱና በአሻራው ማንነት በአለም አቀፍ ደረጃ ብቸኛ ስለሚያደረገው የማንም ሰው ማንነት የሌላን ሰው ማንነት ሊሆን አይችልም፡፡

የአንድ ሰው መልካም ይሁን ክፉ ድርጊት የአስተሳሰቡ ውጤት እንጂ የቋንቋው ውጤት አይደለም፡፡ አሰተሳሰብ በአዕምሮ ቅዠት ህመም ይለከፋል እንጂ ቋንቋ በአዕምሮ የቅዠት ህመም አይለከፍም፡፡ አንድን ቋንቋ ጨቋኝ አድርጎ በመፈረጅ ቋንቋውን መናገር እየቻለ ለመናገር መጥላት፣ እንዲሁም አንድን ቋንቋ ሌሎች እንዳይናገሩት ቅስቀሳንና ክልከላን ማድረግ ማሳቀቅ፣ ቂልነት በሆነ በአዕምሮ ቅዠት ነቀርሳ ህመም የመለከፍ ውጤት ነው፡፡

ምንጭ- የብሔር ማንነት ቅዠት
ደራሲ- ሰብስቤ አለምነህ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
ለመላው ኢትዮጵያዊያን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2015 ዓ.ም የገና በአል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በተለይም ለዩኒቨርሲቲያችን የክርስትና እምነት ተከታይ መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ ለማለት እወዳለሁ!!

ኩሴ ጉዲሼ(ዶ/ር), የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
ለክርስትና ዕምነት ተከታይ ተማሪዎች በሙሉ

እንኳን ለ2015 ዓ.ም የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ ፤

እያለ የተማሪዎች ህብረት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
Point‼️ #መልስ

ዩኒቨርስቲዎች መቀበል የሚችሉት 150ሺ አከባቢ ነው። 80 ሺ የተፈጥሮ ሳይንስ እና 70ሺ የማሕበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለው።

ስለዚህ እንደሚታዩት አጠቃላይ ዩኒቨርስቲ የገቡት 30ሺ ብቻ ናቸው። ( 23ሺ NS And 7ሺ SS ) እነዚህ ተማሪዎች በቀጥተ የአንደኛ አመት ተማሪ ይሆናሉ ተብሏል።

ስለዚህ ከ 50% በታች ያመጡ ተማሪዎች 120ሺ የሚሆኑት ዩኒቨርስቲ ገብተው የማካካሻ ትምህርት ተምረው በድጋሚ የመፈተን እድል ይሰጣቸዋል። ( 57ሺ NS and 60ሺ+ SS)

አድል የተሰጣቸው ተማሪዎች ውጤታቸው ዝቅ ባለበት የት/ት አይነቶች ላይ የማካካሻ ትምህርት ይማራሉ። የሚማሩት ግን ዩኒቨርስቲ ገብተው ነው። ከዛ በድጋሚ ይፈተናሉ እና ካለፉ እዛው ዩኒቨርስቲ 1ኛ አመት ይቀጥላሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ልያወጣ ነው። በዚህም መሰረት Freshman Course ልቀር ይችላል።  ኮሌጅ ላይም አዲሱ አሰራር ይተገበራል። ዝርዝር መረጃ በቅርቡ ይደርሱናል።

ሌሎች 700ሺ ተማሪዎች TVET(ቴክንክና ሙያ) ላይ ገብተው ድፕሎማ ይማራሉ ተብሏል።

የቻናላችን ሊንክ👇
https://t.me/+B4iu_KaLsiNjYzc8
https://t.me/+B4iu_KaLsiNjYzc8

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 @ethiouniversity1bot

            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፦

- በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ባ1 ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ብሔራዊ ፈተና አላለፈም።

- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል ነው 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ የታወቀው።

- ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል።

- 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦

👉 ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣
👉 ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣
👉 ባህርዳር ስቴም ት/ቤት  ፣
👉 ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤
👉 የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው።

ምንጭ፦ WMCC
ፎቶ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@TIKVAHETHIOPIA
ከ50% በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች
 አዲስ አበባ----ከ47,980 መካከል 9,491 (19.8%)
 ሀረሪ…………ከ1,849 መካከል 194 (10.5%)
 ደሬደዋ-------- ከ3,726 መካከል 250 (6.7%)
 አማራ………ከ246,675 መካከል 8,810 (3.6%)
 ሲዳማ---------ከ53,478 መካከል 1247 (2.3%)
 ኦሮሚያ…..…327,737 መካከል 6,407 (2.0%)
 ደቡብ………..ከ127,345 መካል 2,533 (2.0%)

#ክልል