BE INFORMED FIRST ️ ️
13K subscribers
1.32K photos
485 videos
24 files
552 links
👉መልካም ለማጨድ መልካሙን ይዝሩ!
#መጽሐፍ_ቅዱስ_በድምፅ
#ትምህርት - በጥያቄና መልስ💡
#ጠቃሚ_ምክሮች
#Scholarships 💌

👉 #ዓላማችን
ሰው ሁሉ ማህበራዊ ሚዲያን ለተቀደሰ ዓላማ እንዲጠቀሙ ማበረታታት፡፡

#For any suggestions 👇👇
@Bochu_Unclica
Download Telegram
I am deeply honored to have been invited by the esteemed President William Ruto and First Lady Rachel Ruto of Kenya to share the life-transforming Word of God. I am grateful for their hospitality and the opportunity to minister to the beautiful people of Kenya. To Jesus be the glory for all He did!

#Nairobi #Kenya #Africa #President #BennyHinn
. Be Informed first 👇
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
ቴሪ ፎክስ የካንሰር ህመም ተጠቂ ነበር🤔

👇🏾

ከካንሰር ጋር ግብ ግቡን የተያያዘው ቴሪ ፎክስ ከመሞቱ በፊት ለ143 ቀናቶች 5,373 ኪሎ ሜትር የሚሆን የካናዳ ምድርን በሩጫ ሸፍኗል

የቴሪ ፎክስ የሩጫ አላማ እያንዳንዱ ካናዳዊ ጋር በመድረስ አንድ የካናዳ ዶላር መሰብሰብ ነበር:: በወቅቱ የካናዳ ህዝብ 24 ሚሊየን ነበርና ጉዞውን በጨረሰበት የካቲት ወር 1981 ዓ.ም ላይ 24.7 ሚሊየን ዶላር መሰብሰብ ቻለ

ይህ የተሰበሰበው ገንዘብ በካንሰር ህመም ለሚሰቃዩ እርዳታ እና ምርምር ለሚያደርጉ ደግሞ እገዛ የሚውል ነበር

ቴሪ በሞተ በአመቱ "ቴሪ ፎክስ በጎ አድራጎት" የሚል ድርጅት የተከፈተ ሲሆን በካናዳ ውስጥ የተለያዩ ሩጫ ውድድሮችን በማዘጋጀት ለካንሰር ህክምና የሚሆን ገንዘብ ይሰበስባል

እስካሁን ድረስ በቴሪ ፎክስ ስም 715 ሚሊየን የካናዳ ዶላር ተሰብስቧል

እየሞትክ ነፍስ መዝራት !!❤️🙌🏼

♻️ Share ♻️ Share♻️
BE INFORMED FIRST

@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
. ተንቀሳቀሱ!

ለረጅም ጊዜ በሕልም፣ በራእይ ወይም በዓላማ መልክ በውስጣችሁ አምቃችሁ የቆያችሁት ነገር ካለና እስካሁን ወደፊት መንቀሳቀስ ካስቸገራችሁ፣ አንድን እውነታ ላስታውሳችሁ፡፡

ያንን ነገር ለመጀመር የግድ ጎበዝ መሆን የለባችሁም፡፡ ጎበዝ ለመሆን ግን የግድ ያንን ነገር መጀመር አለባችሁ፡፡

እነዚያ ሌላ ሃገር ያሉት፣ ብዙ ነገር የጀመሩትና የተዋጣላቸው . . . እነዚህ በቅርብ በሃገራችን ያሉት፣ ብዙ ነገር ጀምረው የተሳካላቸው፣ ያንን ነገር የጀመሩት ጎበዝ ስለሆኑ ነው ብላችሁ የምታስቡትን ከእውነት የራቀ ሃሳብ ተወት አድርጉት፡፡

እነዚህ ሰዎች ጎበዝ የሆኑት ያመኑበትን ነገር ባላቸው አቅም አንድ ብለው በመራመድ ስለጀመሩ ነው እንጂ ጎበዝ ስለሆኑ አይደለም የተራመዱት፡፡

1.  እጃችሁ ላይ ባለው ገንዘብ ወይም አእምሯችሁ ውስጥ ባለው እውቀት ጀምሩ!

2.  የአንድን ሰው ድጋፍ በመጠየቅ የምታገኙት ድጋፍ ትንሽም ሆነ ትልቅ ካመሰገናችሁ በኋላ ከዚያ ጀመሩ!

3.  በማሕራዊ ሚዲያ ላይ ቁም ነገር ለሌላቸው የchat ምልልሶች ረገብ በማለት ያንን ጊዜ ለዓላማችሁ በማዋል ጀምሩ፡፡

የምትችሉትን ያህል በማቀድና አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል በመዘጋጀት ተንቀሳቀሱ!!! ጉብዝናው ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡

መልካም ቀን

✍️ Dr Eyob Mamo
BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
ሰላም ጤና ክብረት ፣ ፍቅር ይስጥልን ውድ ቤተሰቦች ይህ BE INFORMED FIRST የቴሌግራም የቻናላችን ነው🙏

እንኳን ጌታ አነጋላችሁ፤
እንኳን ደህና ሆናችሁ፤
የሰላሙ ንጉሥ በውሎአችሁ ይክብር፤
ማዕበል ወጀቡን ፀጥ ያድርግላችሁ፤
ልባችሁን የሚያውክ ይውደቅላችሁ!🙏
የእናንተ የሆነውን ሁሉ ይባረክላችሁ!


ይህንን እንድታስተውሉ እንንገራችሁ ለዛሬ መብቃት ቀሊል አደለምና
የሚቀድመውን አስቀድሙና የሚከተውን አስከትሉ🥰
መጽሐፉ
“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
— ማቴዎስ 6፥33


መልካም ቀን ተመኘንላችሁ
BE INFORMED FIRST

@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
You must watch this video 📼

. [ 0 ] ZERO!

📟 Duration 4:10 min
💿 Size 4:4 mb
✍️ @Jesuschristinheaven
✍️ @Jesuschristinheaven
______
[ BE INFORMED FIRST CHANNEL ]
. ትዕግስት 🥰

"በህይወትህ ትዕግስተኛ መሆን ከቻልክ የምትፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ወዳንተ ይመጣሉ፡፡
        ምድር ምትባለው ፕላኔት ውስጥም ትልቁን ዋጋ ሚያስከፍለው ትዕግስት ነው፡፡ መታገስ ይከብዳል፡፡ ያ' ጊዜ ሲያልፍ ግን ምንፈልገውን እናገኛለን፡፡መራራውን ጊዜ አልፈህ ጣፋጩን ፍሬ ትበላ ዘንድ ታጋሽ ሁን፡፡ ትዕግስተኞች ከ ጉልበተኞች ይበልጣሉ፡፡" 🙊
  
                #መልካም_ ቀን

BE INFORMED FIRST 🥰
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
እስኪ በሰላም ላሳደረን ፈጣሪ እጃችንን ለምስጋና እንዘርጋ🙏
ሰነፍ አትሁን! 🚫
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Jesuschristinheaven/22073
ሰነፍ አትሁን!

አንዳንዴ ከዚህ ቀደም በላቀ ተነሳሽነት ትሰራው የነበረን ስራ በአግባቡ መስራት ያቅትሃል ፤ ከዚህ በፊት የሚያስደስትህ ተግባር ስሜት አልሰጥህ ይላል፤ አዕምሮህ በወረዱ አሉታዊ ሀሳቦች ይሞላል፤ ምናልባት ከአልጋም መነሳት ሸክም ሲሆንብህ ልትመለከት ትችላለህ። እንግዲ ህይወት አንዳንዴ እንዲ ነችና ቻል ማድረግና ቀስ በቀስ ጊዜውን ማሳጠር ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን አስተውል ይሄ ስሜት ለረጅም ጊዜ ከቆየብህ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደጋግሞ የሚመጣብህ ከሆነ፣ ወደፊት እንዳትጓዝ፣ የተለየ ሀሳብ እንዳታስብ እያደረገህ ከሆነ፣ እያደር አቅም እያሳጣህ፣ ተነሳሽነትህን እየገደለ የጊዜያዊ ስሜትህ እስረኛ ካደረገህ፣ ከየትኛውም ጊዜ በላይ መንቃት ያለብህ አሁን ነው። ስንፍና መነሻው ምቾትን መፈለግ ነው፡፡ ምንም ከባድ ነገር ማድረግ ሳትፈልግ ስትቀር፣ ስሜትህን ማስታመም ስትጀምር፣ ጊዜያዊ ደስታን ስታሳድድ፣ ባለህ ነገር መመቻቸት ሰትፈልግ ስንፍና አሳስሮ ያስቀምጥሃል። ብታስብም አታደርግም፣ መሔድና መጀመር ብትፈልግም አትጀምርም!!!.....።

አዎ! ጀግናዬ..! ሰነፍ አትሁን! እራስህን የስሜትህ ባሪያ፣ የጊዜያዊ ደስታህ ግዞተኛ አታድርገው፡፡ ስንፍናህ ምን እንዳሳጣህ፣ ቸልተኝነትህ ምንያህል ወደኋላ እንዳስቀረህ፣ ትኩረት ማድረግ አለመቻልህ ምን እንዳጎደለብህ ካንተ በላይ የሚያውቅ የለም። ሰነፎች ዓለም ላይ ቦታ የላቸውም፣ ግዴለሾች በምንም መንገድ ተፅዕኖ መፍጠር፣ ደረጃቸውን ማሻሻልና ህይወታቸውን መቀየር አይችሉም፡፡ አንዳንዴ ለእራስህ ብለህ እራስህ ላይ መጨከን ይኖርብሃል። ምቾት እየገደለህ እንደሆነ እያየህ ዝም አትበል፣ ከዓመት ዓመት አንድ ቦታ መገኘት ለእራስህ የምትሰጠውን ስፍራ እያሳነሰ በበታችነት መዓበል እየመታህ እንደሆነ እያየህ ዳግም ቁጭ ብለህ አትጠብቀው፡፡ መንቀሳቀስ ባለብህ ልክ ተንቀሳቀስ፣ ለስንፍናህ መፍትሔ አብጅለት፣ ባለህ አቅም ሁሉ ወደፊት ለመጓዝ ሞክር፣ እራስን መግዛት ተለማመድ፣ ከሚመጣውና ከሚጠፋው ጊዜያዊ ስሜትህ በላይ ለእውነተኛው ማንነትህ፣ ለውስጣዊ ፍላጎትህ መቆም ጀምር።

አዎ! ስንፍናህ እራስህን ከማሳመን በላይ ሰዎችን ለማሳመን

በምትደረድረው የሰበብ መዓት የበለፀገ ነው፤ ስንፍናህ በማያሳድጉህ፣

ምንም ለውጥ በማያመጡልህ ጥቃቅን የጊዜያዊ ደስታን ብቻ በሚያጎናፅፉህ ተግባራት የዳበረ ነው፡፡ ማንም ይክበድም ይቅለልም፣ ይብዛም ይነስም ምንም ነገር ሳይሰራ ሊቀመጥ አይችልም። አንዳንዴ ሀሳብ በራሱ ከተግባራዊ ስራ በላይ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ውስጥህ መፅሐፍ እንድታነብ እየፈለገ አንተ ግን ቁጭ ብለህ ለሰዓታት ቲቪ የምትመለከት ከሆነ፣ ውስጥህ ለሚጠብቅህ የስራ ቃለመጠየቅ እንድትዘጋጅ እየነገረህ አንተ ግን አሁንም ቲክቶክ Scroll እያደረክ ከሆነ በእርግጥ ስራ እየሰራህ ነው፣ ነገር ግን የምትሰራው ስራ የሚገድልህን እንጂ ቀና የሚያደርግህን አይደለም፣ ይበልጥ በራስመተማመንህን የሚያንኮታኩት እንጂ ለእድገትህ ጠብታ ያህል አስተዋፅዖ የሚያበረክትልህ አይደለም፡፡ እራስህን ማስታመም አቁም፣ ስንፍናህን ለመሸፈን ምክንያት መደርደር አቁም፡፡ ሰነፍ ከሆንክ የመጀመሪያው ስንፍናህን የምታሸንፍበት መንገድ ሰንፍ እንደሆንክ አምነህ ከስሜትህ በላይ የሚያደርግህን የህይወት ትርጉም ማግኘት እንደሆነ እወቅ። ስንፍናህ እየገደለህ እንደሆነ አስተውል፣ ግዴለሽነትህ ከፍለህ የማትጨርሰው መዘዝ እያመጣብህ እንደሆነ አስተው፡፡ ስንፍናን ጠል ዲስፕሊን ገንባ፣ ግዴለሽ አትሁን ለገዛ ህይወትህ ግድ ይኑርህ።

ግሩም ድንቅ ቀን ተመኘን!
💐

♻️ Share ♻️share♻️ share♻️
👇👇 JOIN US 👇👇
BE INFORMED FIRST ||ON TELEGRAM
♻️ @Jesuschristinheaven
♻️ @Jesuschristinheaven
እመኑኝ

አለምን በ6 ቀን ሰርቶ የጨረሰ አምላክ የናንተን ሕይወት ለማስተካከል ብዙ ጊዜ አይፈጅም!


መልካም ቀን 💐

BE INFORMED FIRST
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
"Study this Book of Instruction continually. Meditate on it day and night so you will be sure to obey everything written in it. Only then will you prosper and succeed in all you do."
Joshua 1:8

“የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።”

መ.ኢያሱ 1:8

መልካም ቀን ተመኘንላችሁ 💐
BE INFORMED FIRST 👇
@Jesuschristinheaven
@Jesuschristinheaven
Shooting Stars 🌌 ተወርዋሪ ኮከቦች👇
https://t.me/Jesuschristinheaven/22105
ተወርዋሪ ኮከቦች 🌌

ተወርዋሪ ኮከቦች (Shooting Stars) መቼ እንደመጡ ሳናውቃቸው በድንገት ከተከሰቱ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ በድንገት የሚሰወሩ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ ዛሬ እዚህ ተከስተውና ታይተው ባለፉበት ፍጥነት ሌላ ቦታም እንደዚሁ፡፡

ልክ እንደተወርዋሪ ኮከብ ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ የሚሉ ሰዎች በሕይወታችሁ ላይ የሚያመጡት ጉዳትና ክስረት በምንም አይተመንም፡፡ ይህ ክስረት እንዳይደርስባችሁ ከፈለጋችሁ ብቸኛውና ዋነኛው መንገድ ለሰዎች ጊዜን መስጠት ነው፡፡ የሰዎችን እውነተኛነትና “ቋሚ ኮከብነት” ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል ዋነኛው መሳሪያ ጊዜ የሚባለው ነው፡፡

በድንገት በሕይወታችሁ ለተከሰቱ ሰዎቸ ጊዜ እንዲፈትናቸውና እውነተኛ የመነሻ ሃሳባችውንም ሆነ ማንነታቸውን ኩልል አድርጎ እንዲያወጣላች ከፈለጋቸሁ ለሁኔታው በቂ ጊዜን ስጡት፡፡

ጊዜ መስጠት ለሁለት ነገር ይጠቅማችኋል፡-

1. እውነተኛ ሰዎች ብቻ መቆየት የሚችሉበትን ሁኔታ በመፍጠር እውነተኛ ያልሆኑት እንዲያልፉ ያጣራላችኋል፡፡

2. በወቅቱ የስሜታችሁ ሁኔታ ተገፋፍታችሁና ተታላችሁ ውሳኔ ውስጥ እንዳትገቡ እናንተን ያረጋጋችኋል፡፡

ሰዎች “ቋሚ ኮከቦች” ይሁኑ ወይም “ተወርዋሪ ኮከቦች” ይሁኑ ለመለየት ጊዜ መስጠት ማለት የሚከተሉትንና መሰል ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ሳታጋሩ መቆየት ማለት ነው፡፡

የጊዜን ፈተና ላላለፈ ሰው በፍጹም . . .

1. ገንዘብና ንብረት (ቁሳቁስ) አታጋሩ

2. ከፍቅር ጋር የተያያዘ ስሜታችሁን አታጋሩ

3. የግል ምስጢራችሁን አታጋሩ

አንድ ጊዜ እነዚህንና መሰል የግል ሁኔታችሁን ካጋራችሁ በኋላ የሰዎቹ እውነተኛ ማንነት ሲገለጥና በመጡበት ፍጥነት ሲያልፉ፣ የልባችሁን ቁራጭ ቦጭቀው ይዘው ነው የሚሄዱት፡፡ ከዚያም፣ ያንን የተቦጨቀውን ልባችሁን ስታክሙና፣ ቡጫቂውን ይዘው የሄዱትን ሰዎች ስትፈልጉ እድሜያችሁን ታሳልፋላችሁ፡፡

ፈጣሪ የሰላም ሕይወት ይስጣችሁ!

✍️ Dr Eyob Mamo
BE INFORMED FIRST 👇
♻️ @Jesuschristinheaven
♻️ @Jesuschristinheaven
Forwarded from 𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶
"____ የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው÷ ነፍሰ ገዳይም የሆነ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።"
Anonymous Quiz
4%
A. ድሆችን
16%
B. ባልንጀራውን
79%
C. ወንድሙን
2%
D.ሕይወትን
Forwarded from 𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶
“እናንተ ደካሞች __________ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።”
Anonymous Quiz
2%
A. ህይወት
0%
B. መከራችሁ
97%
C. ሸክማችሁ
1%
D. ሰላማችሁ
Forwarded from 𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶
“ማናቸውንም ነገር _____ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
Anonymous Quiz
3%
A. በፍቅር
36%
B. በእምነት 🙏
0%
C. በእንባ 😢
59%
D. በስሜ
2%
E. በተስፋ
The things you don't have are not important now, what's more important is what you do have.

Be Happy In God! & Bless him😃
Thank you lord! 🙏
Thank you Jesus🙏


👇BE INFORMED FIRST👇
@Jesuschristineaven
@Jesuschristinheaven
Forwarded from 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐎𝐍𝐆𝐒 𝐓𝐔𝐁𝐄 (𝐁𝐎𝐂𝐇𝐔 𝐔𝐍𝐂𝐋𝐈𝐂𝐀❶)
#አሳዛኝ_ዜና😭😭😭
ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደሚወደው ጌታ ሄዷል። ኢየሱስን አምላኩ አድርጎ እያገለገሉ መጠራት ዕድል ነው!! የሄደው ወደጌታ ቢሆንም የሚወዱት ሲለይ ያሳዝናልና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን....🙏😭

@Holysongstube
BE INFORMED FIRST ️ ️
#አሳዛኝ_ዜና😭😭😭 ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደሚወደው ጌታ ሄዷል። ኢየሱስን አምላኩ አድርጎ እያገለገሉ መጠራት ዕድል ነው!! የሄደው ወደጌታ ቢሆንም የሚወዱት ሲለይ ያሳዝናልና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን....🙏😭 @Holysongstube