Jano Tube
64 subscribers
100 photos
8 videos
10 files
49 links
Ethiopian Video Sharing Portal
Get up-to-date music videos, movies, news and many more. ለማንኛውም አስተያየት 👉👉👉@Markanl
Download Telegram
ሰው ሆነን ሰዋዊነት ከተሰማን በመተከልም ይሁን በትግራይ ክልል እንዲህ በረሀብ አለንጋ ስለሚገረፉ አጉርሱን እራበን ስለሚሉ በማንነታቸው ስለሚገደሉ ስለሚሰደዱ ህፃናት እናቶች አባቶችን ጉዳይ ሁላችንም ይመለከተናል ! እነዚህን ወገኖች አይቶ ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው :: ምንም በማያውቁት መዘዝ ስንት ወገኖቻችን አሟሟታቸው ይሁን አቀባበራቸው ሳያምር አጥተናቸዋል!
አሁን ደግሞ በየቦታው እንዲህ ሲሰቃዩ ማየት ያማል ብሽሽቁን እና ፖለቲካውን ብሄር እና ስድድቡን ለጊዜው ዘወር አድርገን እንዲህ ስለሚሰቃዩ ወገኖች እናስብ ::
🙏🙏
ትግራይ_ለእርዳታ_ድርጅቶች_ክፍት_
ትሁን_challenge
#ለአዲስ_አበባ_አና_አካባቢው_ነዋሪዎች - የዕይታ ችግር ላለባቸዉ

ዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ፤ ከአድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ የአይን ህክምና ክፍል ጋር በመተባበር #ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በስፔሻሊስት ሀኪሞች ለመስጠት ተዘጋጅቷል። ስልሆነም ማንኛውም የእይታ ችግር ያለበት ሰው በ የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል በመገኘት አና ምርመራ በማድረግ የአገልገሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ::

በቅንነት ላይክ እና ሸር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ !!!
@janovids
ስንቱ በደሀ እንባ
ስንቱ በምስኪን ደም ፣ ዛሬም ይታጠባል
ህዝቡ ፆም ሲጀምር
የሰው ስጋ በልቶ ፣ መቃብር ይጠግባል
ባለጊዜ አያፍርም!
ለፍርድ እንደመቅረብ ፣ ለምርጫ ይቀርባል!!! belay bekele
“አንድ ሰው በትርፍ ጊዜው ብዙ ሙታን ወደተቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ሄዶ በሰዎች መቃብር ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች በማንበብ ላይ ሳለ፣ በአንድ ሰው መቃብር ላይ አንድ ግር የሚል ጽሑፍ አነበበ፡ ጽሑፉ በ”30 ዓመቱ ሞተ፣ በ60 ዓመቱ ተቀበረ” ይላል፡ ጽሑፉ ግር ብሎት ቆሞ ማሰላሰል ጀመረ፡፡ “አንድ ሰው በ30 ዓመቱ ሞቶ እንዴት ለ30 ዓመታት ሳይቀበር ሊቆይ ቻለ?” ይህንን እያሰበ የጽሑፉን ትርጉም የሚያውቅ አንድ ሰው ደረሰ፡፡ “ምን እንደምታስብ ገብቶኛል” አለው ሃሳቡን አንብቦ፡፡

ጥያቄውን በግምት ደርሶበት ኖሮ በቀጥታ መልሱን ነገረው፡፡ “ይህ ሰው እጅግ በጣም የሚያስገርም ራእይና ዓላማ የነበረው ሰው ነበር፡፡ ብዙ ነገሮችን የመስራት እቅድ የነበረውና በዚህም ትጋቱ በሕብረተሰቡ ዘንድ እጅግ የታወቀና ለትልቅ ነገር የሚጠበቅ ሰው ነበር፡፡ ልክ 30 ዓመት ሲሞላው በተለያዩ ውጣ ውረዶች በማለፉ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ዓላማውን ሁሉ ትቶ ከርታታ ሰው ለመሆን በቃ፡፡ የሚቀጥሉትን 30 ዓመታት እንዲሁ በየቦታው ሲንቀዋለል ነው ያሳለፈው፤ ካለምንም ዓላማ፡፡ የጽሑፉ ትርጉም ይህ ነው፡፡ ሰውዬው ሞተ ብለው የሚያምኑት ራእዩን በጣለበትና ጊዜውን በተራ ነገር ማሳለፍ በጀመረበት በ30 ዓመቱ ነው - በአካል ቢኖርም ሞቷል ነው አባባላቸው፡፡ ልክ በ60 ዓመቱ ታምሞ አካላዊ ሞትን ሲሞት ያን ጊዜ ተቀበረ ማለታቸው ነው”

በአካል መኖር ብቻውን ኖሯል አያስብልም ነው ነገሩ፡፡ ህያው የሚያደርገን ራእይና የመኖር ዓላማ እንጂ ቆሞ መሄድ አይደለም፡፡ ቆሞ ለመሄድ በአራት እግር ሆነ እንጂ አህያም ይሄዳል፡፡ አህያ ግን የሰውን ስራ ከማቅለሉ ውጪ የራሱ ራዕይ የለውም፡፡ ስለሌለውም የሌሎች ባሪያ ሆኖ ይኖራል፡፡ በሰው ራእይና ዓላማ የለሽ ህይወት ህይወት ሳይሆን ሞት ነው፡፡ ዓላማ አልባው ሰውም ለመቀበር ነፍሱ ከስጋው እስክትነጠል ይጠበቃል እንጂ ሙትማ ሙት ነው፡፡ ሰውን ህያው የሚያደርገው ህልሙ ነው የሚሉ ይመስላሉ ፀሐፊው፡፡ ልክ ነው! ዓላማ ያለው ሰው መሆንና በዓላማው የሚፀና ሰው መሆን ሁለት የስኬት ቁልፎች ናቸው፡፡

ስኬታማ ሰዎች ባለራዕይ ናቸው፡፡ ለራዕያቸውም ታማኝና ፅኑ ናቸው፡፡ ለፈተናም ሆነ ለየትኛውም ነገር በቀላሉ እጅ አይሰጡም፡፡ እጅ አለመስጠታቸው የህያውነታቸው ምልክት፣ የስኬታቸው ጠቋሚ ነው፡፡

ከዓላማ ውጪ የሚኖር ህይወት ከህይወት አይቆጠርም፡፡ ዓላማ ቢስ ወይም ከባለራዕይነት ወደ ዓላማ የለሽነት የመጣ ሰው ኖሯል ለማለት ከባድ ነው።

ምንጭ፦ “25 የስኬት ቁልፎች” የተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ
በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የምትፈልጉ ከታች የተገለጸውን መስፈርት በሟሟላት እንድትመዘገቡ ይጋብዛል።
📶የምዝገባ ቀን: ከግንቦት 02 እስከ ግንቦት 06 2013 ዓ.ም
📶የምዝገባ ቦታ: ዋናው ግቢ፣ ስድስት ኪሎ በሬጅስትራር ህንፃ ፣ ሁለተኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 203
በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
☘️በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤
☘️በዲፕሎማችሁ ወይም በደረጃ 4 ለምታመለክቱ ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 4 ማቅረብ፤
☘️ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤
☘️ለPreparatory አመልካቾች ከ2007-2012 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፤
☘️ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፤
Programs available at AAU School of Commerce are the following.
1.BA Accounting and Finance
2.BA Business Administration and Information Systems
3.BA Economics
4.BA Logistics and Supply Chain Management
5.BA Management
6.BA Marketing Management
ማሳሰቢያ፡-
የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረ ገጽ https://portal.aau.edu.et/ መሙላት
ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 150 / አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡
ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡
ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ ዲፕሎማ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ ከዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና በተጨማሪም በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡
የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው እና በዲፕሎማ አመልካቾች ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡📶
Announcement for 2020/21 AY New Evening Undergraduate Program Applicants
May 7, 2021

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል

በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

1. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ማቅረብ፤
2. በዲፕሎማችሁ ወይም ደረጃ 4 ለምታመለክቱ ከትምህርት ማስረጃ ጋር የCOC ደረጃ 4 ማቅረብ
3. ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ
4. ለPreparatory አመልካቾች ከ2007-2012 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ¥Qrብ
5. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
ማሳሰቢያ፡-
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረ ገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 150 / አንድ መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
4. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡
6. ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡
7. ለአዲስ አበባ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለማታ ዲፕሎማ የመጀመሪያ ዲግሪ አመልካቾች በሙሉ ከዩኒቨርስቲው መግቢያ ፈተና በተጨማሪም በየትምህርት ክፍሉ ፈተና የሚሰጥ መሆኑን ከወዲሁ አውቃችሁ እንድትዘጋጁ እናስታውቃለን፡፡
8. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
9. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው እና በዲፕሎማ አመልካቾች ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የምዝገባ ቀን፡ ከግንቦት 02 እስከ ግንቦት 06 2013 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
list of available programs for Undergraduate evening applicants

Addis Ababa Institute of Technology

1 . Bachelor of Science in Chemical Engineering

2 . Bachelor of Science in Biomedical Engineering

3 . Bachelor of Science in Civil Engineering

4 . Bachelor of Science in Electrical and Computer Engineering

5 . Bachelor of Science in Information Technology

6 . Bachelor of Science in Mechanical Engineering

7 . Bachelor of Science in Software Engineering

College of Business and Economics

1 . Bachelor of Arts in Accounting and Finance (CoBE)

2 . Bachelor of Arts in Accounting and Finance (Commerce)

3 . Bachelor of Arts in Business Administration and Information Systems (Commerce)

4 . Bachelor of Arts in Economics (CoBE)

5 . Bachelor of Arts in Economics (Commerce)

6. Bachelor of Arts in Logistics and Supply Chain Management (Commerce)

7 . Bachelor of Arts in Management (CoBE)

8 . Bachelor of Arts in Management (Commerce)

9. Bachelor of Arts in Marketing Management (Commerce)

10 . Bachelor of Arts in Public Administration & Development Management (CoBE)

College of Education and Behavioral Studies

1 . Bachelor of Arts in Educational Planning and Management

2 . Bachelor of Arts in Psychology

3 . Bachelor of Arts in Special Needs and Inclusive Education

College of Humanities, Language Studies, Journalism and Communication

1 . Bachelor of Arts in Afan Oromo, Literature and Communication

2 . Bachelor of Arts in Arabic Language and Communication

3 . Bachelor of Arts in English Language and Literature

4 . Bachelor of Arts in Ethiopian Language(s) Literature- Amharic

5 . Bachelor of Arts in French Language and Professional Skills

6 . Bachelor of Arts in Journalism and Communication (Broadcast Journalism)

7 . Bachelor of Arts in Journalism and Communication (Print and Web)

College of Law and Governance Studies

1 . Bachelor of Laws

College of Natural and Computational Sciences

1 . Bachelor of Science in Biology

2 . Bachelor of Science in Chemistry

3 . Bachelor of Science in Computer Science

4 . Bachelor of Science in Information Systems

5 . Bachelor of Science in Mathematics

6 . Bachelor of Science in Sport Science

7 . Bachelor of Science in Statistics

College of Performing and Visual Arts

1 . Bachelor of Arts in Theatre Arts


College of Social Sciences

1 . Bachelor in Social Work Degree

2 . Bachelor of Arts in Archaeology & Heritage Managem
ent

3 . Bachelor of Arts in Geography and Environmental Studies

4 . Bachelor of Arts in Philosophy

5 . Bachelor of Arts in Political Science and International Relations

6 . Bachelor of Arts in Social Anthropology

7 . Bachelor of Arts in Sociology
☀️ ህፃናትን ለምንድነው ፀሐይ የምናሞቃቸው ?


� የፀሐይ ብርሃን በተለይ ደም አልትራቫዮሌት የሚባለው የፀሐይ ጨረር ቆዳችን ላይ ሲያርፍ ሰውነታችን ቫይታሚን ዲ የሚባለውን ንጥረነገር ያመርታል:: ይሄም የራሱ የሆነ ቅደም ተከተል አለው:: አንድ ሰው ፀሐይ አግኝቶ በበቂ ሁኔታ ቫይታሚን ዲ ለማምረት ደሞ ጤነኛ ጉበት እና ኩላሊት ሊኖረው ይገባል::

👉 ቫይታሚን ዲ ጥቅም ምንድነዉ?

📌 ቫይታሚን ዲ በአንጀት ዉስጥ ምግብ ስልቀጣ እና መፈጭት ከተካሄደ በኋላ ካልሲየም የተባለዉ ንጥረነገር ወደ ሰዉነት ዉስጥ እንዲዋሐድ ወይም በደንብ ወደ ሰውነት እንዲቀላቀል ይረዳል ።

📌ይህም ማለት ይሄ ቫይታሚን ሰውነታቺን ዉስጥ ከሌለ ካልሲየም ምግባችን ዉስጥ ቢኖርም እንኩዋን ሰዉነታች ን ዉስጥ ሳይገባ ወይም ሳይዋሐደን በሽንት እና በሰገራ ሊወጣ ይችላል ማለት ነዉ።

♦️የካልሲየም ደሞ ለአጥንት እና ለጥርስ እድገት እና ጥንካሬ በጣም ወሳኝ ንጥረ ነገር ነው::

♦️አንድ ህፃን ሰውነት ዉስጥ የካልሲየም ንጥረነገር እጥረት ካለ አጥንቱ ጥንካሬዉን ስለሚያጣ አጥንቶች ሊጣመሙ ይቺላሉ ፣ ጥርሱም በግዜው ሳይበቅል ሊቀር እንዲሁም በጣም ሊዘገይ ይቻላል::

👉 ህፃናት መቼ ጀምሮ ነው ፀሀይ ላይ መውጣት ያለባቸው ?

📌 ህፃናት በተወለዱ ከ10 ቀን ጀምሮ ፀሀይ ማዉጣት ይቻላል አስፈላጊ ከሆነም ከ5 ቀን በዋላ ሊወጡ ይቺላሉ በተለይ ቢጫ ከሆኑ::

📌ከጠዋቱ 3-5 ሰአት ያለዉ ጊዜ ንፋስ ስለማይበዛው እና ፀሀዩም መጠኑ ያልበዛት ስለሆነ ተመራጭ ሰዓት ነዉ

👉 ህፃናት በቀን ለምን ያህል ጊዜ ፀሀይ ይሙቁ?

📌 ብዙ ጊዜ ህፃናት በቀን ከ20 - 30 ደቂቃ ፀሐይ ካገኙ በቂ ነው :: ሆኖም ይሄ እንደ የቆዳቸው ከለር ሊለያይ ይቺላል ለምሳሌ ጠቆር ያለ ቆዳ እስከ 30 ደቂቃ ሊያስፈልገው ይቺላል ቀይ ቆዳ ደሞ 15 ደቂቃ ብቻ ሊበቃው ይቺላል::

📌 ወላጆች ማወቅ ያለባችሁ ነገር ከፀሐይ የምንፈልገው ዋናው ጨረሩን ወይም ብርሃኑን እንጂ ሙቀቱን አይደለም ስለዚህ በቀጥታ የፀሐዩ ብርሃን ሰውነታቸው ላይ ማረፍ ይኖርበታል:: በመስታወት ዉስጥ ያለፈ ፀሐይ ከሆነ ምንም ትቅም የለውም‼️

📌በተቻለ መጠን አብዛኛው የሰዉነት ክፍላቸው ለፀሀይ ብርሃኑ እንዲጋለጥ ማድረግ ይኖርብናል::

🔴 ጥንቃቄዎች

⚠️ ህፃናት ፀሀይ በሚሞቁበት ወቅት ቫስሊን ወይም ቅቤ መቀባት የፀሃይ ብርሃኑ(ጨረሩ) ወደ ቆዳ ዘልቆ እንዳይገባ ስለሚያደርግ እነዚህን ነገሮች መጠቀም የለብንም ‼️

⚠️ፀሀይ በምናሞቃቸዉ ወቅት አይናቸውን እና ለወንድ ልጆች ብልታቸው አካባቢ በጨርቅ መሸፈን ይኖርብናል::
⚠️ ህፃናት ፀሐይ ላይ ከ30 ደቂቃ በላይ መቆየት የለባቸውም❗️

ህፃናት እስከ መቼ ነው ፀሐይ መሞቅ ያለባቸው?

🔴 ፀሐይ ብርሃን ጨቅላ ህፃናት ጀምሮ እስከ አዋቂ ሰዎች ድረስ ለሁላችንም ሲለዝህ ልጆች በራሳቸው ወተው ፀሀይ እስከሚያገኙ ድረስ ወላጆች ልጆችን ፀሀይ ላይ ማውጣት ይኖርባችዋል:: ከአንድ አመት በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ከቤት ስለምናወጣቸዉ በፕሮግራም ማዉጣቱ አስፈላጊ አይሆንም ፤ በዋነኝነት ህፃናቱ በቀን 20 - 30 ደቂቃ ፀሀይ ማግኘታቸውን እናረጋግጥ።

🔴 የፀሃይ ብርሃን ያላገኙ ህፃናት ምን አይነት ችግር ያጋጥማቸዋል?
👉 የአጥንት መሳሳት እና መጣመም (ሪኬትስ)
👉 ተደጋጋሚ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ)
👉 የጥርስ በጊዜው አለመብቀል
👉 ዝቅተኛ የበሽታ መከላከያ አቅም እና የመሳሰሉት የጤና ችግሮች ሊያጋጥማቸው ይችላል ::

🔴 ክረምት ላይ ፀሐይ ከሌለ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

👉 በውጭው ዓለም በተለይ ምዕራባውያኑ በቂ የ ፀሀይ ብርሃን ስለማያገኙ ለልጆቻቸው ቪታሚን ዲ የሚባለውን ንጥር ነገር በጠብታ መልክ ይሰጧቸዋል ሆኖም ይሄንን በሀገራችን ተግባራዊ ማድረግ በጣም ከባድ ነው ስለዚህ መፍትሄው ፀሐይ በተገኘው ሰዓት ለአጭር ደቂቃም ቢሆን ማሞቅ ይገባል ቢያንስ በሳምንት 4 ቀን ካገኙ በቂ ሊሆን ይቺላል:: እንደ አማራጭ ደሞ የቪታሚን ዲ ጠብታ የምናገኝ ከሆነ ሀኪም አማክረን መጠቀም ይቻላል::

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
The best way to live forever is to be ABEBECH GOBENA! REST IN POWER!
ተአምር ፈልቋል በየመንገዱ

(በእውቀቱ ስዩም)

ዐይኔን ጨፍኜ -እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ - ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጉዋሮ ገብቷል- መርዶ ነጋሪ ::

እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
ርግብ መሬት ላይ -ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ሞልቷል- በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል- በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሰይጣን
ለመደነቂያ፥ ጊዜ ነው ያጣን፤
📖 የ2014 ዓ.ም የድህረ ምረቃ በቀንና በማታ መርሃ ግብር ምዝገባ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 ዓ.ም ለድህረ ምረቃ ትምህርት በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለዚህም የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡

🔑 የአአዩ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተናን በተመለከተ

📌ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ለማመልከት የዩኒቨርስቲዉን የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ቀድሞ መዉሰድ እና ፈተናዉን ማለፍ ግዴታ ነው፡፡
📌የፈተናዉን ግዜ እና ሌሎች መረጃዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዉ ድረ-ገፅ ና ከትምህርት ጥናትና ምርምር ተቋም የፈተና ማእከል ማግኘት ይቻላል፡፡
📌የመፈተኛ ክፍያ ብር 600 በዩኒቨርስቲዉ አካዉንት 1000087392067 ገቢ ማድረግ እና ገቢ ያደረገው የተፈታኝ ስም ያለበት የባንክ ደረሰኝ ለፈተና ማዕከሉ በማስረከብ ለፈተና መመዝገብ ያስፈልጋል፡፡
📌የመግቢያ ፈተናው በኮምፒዩተር የሚሰጥ ሲሆን ፈተናውን በሚመለከት በ አአዩ ድረ-ገፅ አጠቃላይ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
📌 የማመልከቻና መፈተኛ ቀናት፤ ከ ሃምሌ 12 እስከ ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ነው፡፡ ቀድሞ ለተመዘገቡ ቅድምያ ፈተና ይሰጣል፡፡
📌ከዚህ በፊት የዩኒቨርስቲዉን የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና አልፋችሁና ባመለከታችሁበት ፕሮግራም የተማሪ የመታወቂያ ቁጥር የተሰጣችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን የድኅረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና እንደገና መውሰድ ግዴታ ነው፡፡

☘️ የአአዩ የድኅረ ምረቃ ማመልከቻን በተመለከተ

👉🏿 የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.aau.edu.et) መሙላት
👉🏿ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ በክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል፡፡
👉🏿ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን$፣ እንዲሁም ለቀን መርሃ ግብር የትምህርት ወጪዎን /Sponsorship/ የሚሸፍንልዎት የመንግስት መስሪያ ቤት ከሆነ የተፈረመበትና ማህተም የተደረገበት ፎርም አስገብተው እና ሌሎች መረጃዎችን በማከል የኦንላይን ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
👉🏿 የስፖንሰርሺፕ ፎርም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ (https://portal.aau.edu.et/ http://aau.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
👉🏿 ለPhD አመልካቾች የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት እና የMA/MSC ዲግሪና ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
👉🏿 በተጨማሪም ለPhD አመልካቾች ትምህርት ክፍሉ የሚጠይቀውን ማያያዝ ይኖርብዎታል፡፡
👉🏿 ለMA/MSC አመልካቾች የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና CGPA ያለው ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
👉🏿 ምዝገባዎን ለማጠናቀቅ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 የትምህርት እና ሌሎች ማስረጃዎችን በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት ግዴታ ነው፡፡

❇️❇️❇️ ማሳሰቢያ ❇️❇️❇️

🔹 ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡
🔹 የፈተና ግዜንና የትምህርት ፕሮግራም ዝርዝሮችን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (https://portal.aau.edu.et / http://aau.edu.et) ማግኘት እንደምትችሉ ያሳውቃል፡፡
🔹 ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
🔹 የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የመመዝገቢያ ቀን ሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 14 2013 ዓ.ም

የማመልከቻ ቦታ አአዩ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203
#የደመወዝ_ስሌት በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁ

➣ የተጣራ ገቢ ደመወዝ= ሙሉ ደመወዝ ((ሙሉ ደመወዝ*ደመወዙ የተጣለበት ታክስ % የግብር %ቱ ያረፈበት ተቀናሽ ብር) (ሙሉ ደመወዝ*ጡረታ ግብር (7%)))

ለምሳሌ የደርቤ ደመወዝ 6000 ብር ቢሆን
🔧 ሙሉ ደመወዝ =6000
🔧 ደመወዙ የተጣለበት ታክስ= 25% (0.25)
🔧 ደመወዙ ያረፈበት ተቀናሽ ብር = 565
🔧 ጡረታ ግብር = 7% (0.07) ለሁሉም ደመወዝ ስኬል ተመሳሳይ ነው ።
ስለዚህ፦
የተጣራ ደመወዝ = 6000((6000*0.25 565) ( 0.07*6000))
= 60001355
➜ የተጣራ ደመወዝ = 4645 (ይህ በኪስ የሚደርስ ደመወዝ ነው)
👉👉👉ሼር ያድርጉ
👍👍👍ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ
እናመሰግናለን🙏
@janovids
የ14ኛ ዙር የ20/80 እና የ3ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ

#AddisAbaba #Ethiopia