🕋ISLAMIC ZONE🕋
15.5K subscribers
1.55K photos
183 videos
1 file
554 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሌላኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @hanif_tube

For comment an& promotion
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Islamic_zone_bot
Download Telegram
ሰለዋትን በነቢዩ ﷺ ላይ:-

«إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ
آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا» (الأحزاب: 56)

«አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሰላትን ያወርዳሉና እናንተ አማኞችም ሆይ! በሱ ላይ ሰላትና ሰላምታን አውርዱ።» ሲል አዝዞናል።
【አል-አህዛብ (56)】

ነቢዩም ﷺ
"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشراً"

«ጁምዓ ቀንና ሌሊቱን በኔ ላይ ሰላትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰላትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰላትን ያወርዳል።» ብለዋልና በዚህ ላይ ልንበረታ ይገባናል።

#የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم
«የቂያም እለት የኔን አማላጅነት የማግኘት ቅድሚያ ያለው ሰለዋትን በብዛት ያወረደ ሰው ነው።» ብለዋልና ሰለዋት በማብዛት አላህ(ሱ.ወ) የነቢዩን صلى الله عليه وسلم ሸፋዓ እንድናገኝ ያደርገናል።

#ነቢዩ صلى الله عليه وسلم
«በኔ ላይ ሰላትን ኣብዙ። አላህ ከቀብሬ ዘንድ የሚሆን መለክን በኔ ላይ ወክሎብኛልና ከህዝቦቼ መካከል አንዱ ሰው በኔ ላይ ሰላትን ሲያወርድ፤  ያ… መለክ  "ሙሀመድ صلى الله عليه وسلم ሆይ እገሌ የእገሌ ልጅ ባንተ ላይ በዚህ ሰዓት ሰለዋትን አውርዷል ይላል።» ብለዋልና ስማችን በነቢዩ صلى الله عليه وسلم ዘንድ እንዲጠራ፣ እንዲወሳ ሰበብ ይሆነናል።

#የአላህ መልእክተኛ ﷺ
« ሰዎች ሰብሰብ ብለው ተቀማምጠው እያለ አላህን አዝዘ ወጀል የማያወሱበት እንዲሁም በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን የማያወርዱ እንደሆን መቀማመጣቸው የቂያም እለት ቁጭት ሳይሆንባቸው አይቀርም።» ብለዋል።
ስለዚህ በሰለዋት መበርታት አለብን አህባብ

والله اعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه وسلم.
በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛን ሰቆቃ ለማስቆም እንዲረባረቡ ጥሪ ቀረበ

የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት ዋና ጸሐፊ ሸይኽ ዓሊ አል ቀራዳጊ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛን ሰቆቃ ለማስቆም እንዲረባረብ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ዋና ጸሐፊው ሙስሊሞች የፍልስጤማዊያንን ሰቆቃ ኃላፊነታቸው ድርብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሸይኽ ዓሊ አል ቀራዳጊ ጥሪውን ያቀረቡት ለመላው ዓለም በተንቀሳቃሽ ምሥል ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ነው፡፡ የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት ዋና ጸሐፊ በመልዕክታቸው ሙስሊሞች ከፍልስጤማዊያን ጎን እንዲቆሙ ሃይማኖታዊ እና ሰብዓዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ሸይኽ ዓሊ በዚሁ ንግግራቸው በጋዛ የሚፈጸመውን ጥቃት ዓለም በዝምታ መመልከቱንም “አሳፋሪ ነው” ሲሉ ኮንነውታል፡፡

እስራኤል በጋዛ በፍልስጤማዊያን ላይ ከመስከረም ወር መጨረሻ አንስቶ በምትሰነዝረው ጥቃት 37 ሺሕ 700 ንጹሐን ተገድለዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል የእናቶች እና ሕፃናት ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡

በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች የጋዛ ሰቆቃ እንዲያበቃ እንዲረባረቡ ጥሪ ያቀረቡት ሸይኽ ዓሊ አል ቀራዳጊ በዋና ጸሐፊነት የሚሠሩበት የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት፣ ዋና መቀመጫውን ኳታር ዶሓ የደረገ ድርጅት ነው፡፡

የዓለም ሙስሊም ምሑራን ኅብረት ከዚህ ቀደም በታላቁ ግብጻዊ የእስልምና ሃይማኖት ሊቅ ሸይኽ የሱፍ አል ቀርዳዊ ይመራ የነበረ ነው፡፡ ኅብረቱ ከመላው ዓለም ከ90 ሺሕ በላይ ሙስሊም ሊቃውንትን በአባልነት መያዙን በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡
🤍ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

“አላህ በባሪያው ላይ መልካምን ከፈለገለት ቅጣቱን በዱንያ ያፈጥንለታል፤ አላህ በባሪያው ላይ መጥፎን ከፈለገለት ወንጀሉን ዝም ይለውና የቂያማ ቀን በወንጀሉ አሟልቶ ይቀጣዋል፡፡"'
ምቀኛ ስትሆን አላማህ ጥላቻ ብቻ ነው።
-------------------------------------------
     «እባብ እና ትል»

እባብ በባህሪው አብሪ እና አንፀባራቂ ትል አይወድም እና ሁሌም ያሳድዳታል።
በጣም የሚገርመውና የሚደንቀው ነገር ደግሞ «ትሏ»ለዕባቡ ስጋትም ጠላትም አለመሆኗ ነው።
...... የሷ አላማና መርህ ድምቅ ብሎ መብራት ብቻ ነው።ነገር ግን አባብ መድረሻ ሲያሳጣት..በዚህ የእባብ ድርጊት የተሰላቸችው አብሪ-ትል ❸ ጥያቄወችን ልጠይቅህ አለችው.....!!?

እሱም በማለት ፈቀደ...!!

❶➤ትሏ=ምግብ ልሆንህ እችላለሁ!?
እባብ=ፈፅሞ ልበላሽ አልችልም ከማልበላቸው ፍጥረታት አንዷ ነሽ አላት......

❷➤ትሏ=የበደልኩህ ያስከፋሁህ ያደረኩህ ነገር አለን !?
እባብ=በፍፁም ደግሞ በምን አቅምሽ ነው የምትበድይኝ....በማለት መለሰላት።

❸➤ትሏ=እኔን በማሸበርህና በማሳደድህ በማስፈራራትህ  የምታገኘው ጥቅም አለን!?

እባብ=ደግሞ ካንች ምን ጥግም ይገኛል።

➤ትሏ ግራ ገብቷት=ታዲያ ለምን ታሳድደኛለህ!?
እባብ=በቃ ፍክት ድምቅ ሽብርቅ ስትይ ማየት አልፈልግም አወ ብርሀን ስታመነጭ በርቀት ስታብረቀርቄ እናደዳለሁ አላት ይባላል።


➥እናማ አንዳንድ ሰወች ልክ እንደ እባቡ ናቸው። የእናንተ ከፍታና ስኬት የሚያማቸው ብሎም ከራሳቸው ስኬት በላይ የሌሎች ውድቀት የሚያስደስታቸው ሰው መሳይ ፍጥረቶች አሉ።

  «አሏህ ልቦና ይስጣቸው»


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
መሃይምነት እንደ እንቅልፍ ነው።
መጀመሪያ የምትጮኸው በቀሰቀሰህ ሰው ላይ ነው።



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
በአላህ ይሁንብኝ…!ምን አልባት ወንጀል ጊዜያዊ የስሜት ትኩሳትን ያቀዘቅዝ ይሆናል። ነገር ግን በዘላቂነት ፀፀትንና የበታችነትን እንዲሁም መረበሽን ያስከትላል!

አላህ እርሱ ከሚጠላው ተግባር ፣ ንግግር እና ሃሳብ የምንርቅ ያድርገን!


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ለፈገግታ
ምከረው ምክረው

እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ።
በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦

«እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ።

እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ 👋

«ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»  😊

Copied from S.T

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
001 Al-Fatihah
All Islamic channel
ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች እየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አቡበከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም  ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣
2.አንቱን ማየት፣
3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣ በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣ ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!
°
የጁምአ ሱናዎች

1 ትጥበት
2 ዱዓ ማብዛት
3 ሰለዋት ማብዛት
4 የካህፍን ምዕራፍ ማንበብ
5 መስጂድ በጊዜ መግባት
6 ሲዋክ (መፋቅያ መጠቀም)
7 መልካም ልብስ መልበስ
8 ሽቶ መቀባት (ለወንድ)


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
አሰላሙ አለይኩም ዛሬ እስቲ ደስ ያሰኘኝን ታሪክ ላካፍላችሁ ከረታት በአንድ ቀን ባል ሙስቱን እንዲ በማለት ይጀምራል
ባል፦ አስር ሰግደሻል?

ሚስት፡ አይ

ባል፡- ለምን?

ሚስት፡- ከስራ ስለተመለስኩ ትንሽ ደክሞኝ ትንሽ ተኛሁ።

ባል፦ እሺ.........ሂጂ ለዒሻ ሰዓቱ ሳይደርስ አስር እና መግሪብ ሶላት ስገጂ።

በማግስቱ… ባልየው ለስራ ጉዳይ ከተማውን ለቅቋል… በረራው ሊደር ስ ከተባለ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ግን አልደውልም ወይም በሰላም መድረሱን ለማሳወቅ እንደተለመደ ው መልእክት እንኳን አላደረገም። !!

ሚስትየው ባሏን ለማጣራት ትጠራ ለች እሱ ግን አያነሳም‥ እንደገና ደ ወለች; ስልኩ ይደውላል ግን ምን ም መልስ የለም ።

የምትወደውን ባለቤቷን ለመጥራት ከብዙ ሙከራዎች በኋላ መጨነቅ ጀመረች እና ምንም መልስ አላገኘ ችም ለራሷ የሆነ ነገር ተሳስ ቷል ብላ ታስባለች, እሱ በጭራሽ አ ያደርግም. ልክ እንዳረፈ ሁልጊዜ ይደውላል።

ጥቂት ሰአታት አለፉ...እና በድንገት ስልኩ ጮኸ እና ባልየው። ሁሌም የምትጨነቀችው ሚስት፡ በሰላም _ ደርሰሃል ??

ባል፡- አዎ አልሃምዱሊላህ

ሚስት፦ መቼ?

ባል: ከ 4 ሰዓታት በፊት.

ሚስት በንዴት ቃና፡ ከ4 ሰአት በፊት ? እና አትደውልም?

ባል፡ ደክሞኝ ነበርና ትንሽ እንቅልፍ ለመተኛት ወሰንኩ።

ሚስት፡-ብትደውልልኝና እንደደረስክ ብታሳውቀኝ ጥቂት ደቂቃዎች አይጎዳህም ነበር......... በተጨማሪም ስደውልልህ ስልኩ ደጋግሞ ሲጠራ አልሰማህም እንዴ ..??

ባል፡- አዎ ሰምቻለሁ..

ሚስት፡ እና አታነሳም..?? ጥሪዎቼ ለአንተ በቂ ያልሆኑት ለምንድነው .. ??

ባል፦የአንቺ ጥሪዎች ለእኔ አስፈላ ጊ ናቸው ነገር ግን ትላንትና የአዛን ጥሪ አለመመለስሽ የተቸገርሽ አይመስልም ነበር..... የአላህ ጥሪ

ዓይኖቿ እንባ ያዘሉት ሚስት እና ከአጭር ዝምታ በኋላ፡- አዎ፣ አንድ ነገር አለህ አለች....ይቅርታ..... ባል፦ ለምንድነው ይቅርታ የምትጠይቀኝ ?

የአላህን ምህረት መጠየቅ አለብሽ እና ተመሳሳይ ስህተት ለሁለተኛ ጊዜ አትድገ ሚ። እኔ የምፈልገው ከዚህ ምድራዊ ዓለ ም በኋላ አላህ በጀነትም ዳግም እንዲያ ጣምረን ነው። ከዚያን ቀን ጀምሮ ሚስ ትየዋ ማንኛውንም ሶላቷን አታዘገይም።

በእውነት የሚወድህ ወደ አላህ መንገድህ ላይ ወደፊት የሚገፋህ ነው😊


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
قُلْ إِنَّ الْمَوْتَ الَّذِي تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُ مُلَاقِيكُمْ ۖ

"ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት በእርግጥም
የሚያገኛቹ ነው።"

ሁሌም በዝግጅት ላይ ሁን!ሞት ወደአንተ ከመምጣት ምንም ቅሮት የሌለው ነገር ነው።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቁርአን ግብዣ

part(32)

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @Islamic_zonee ለወዳጅ ዘመዶው ያጋሩ ባረከላሁፊኩም
የተከበሩ ወራቶች!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا، مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلَاثَةٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ، وَذُو الْحِجَّةِ، وَالْمُحَرَّمُ، وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ﴾

“አመት አስራ ሁለት ወራት ነው። ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ‘ረጀብ’ ወር ነው።”

ቡኻሪ (3197) ሙስሊም (1679) ዘግበውታል،

ኢብኑ አባስ (رضيﷲ عنهما) እንዲህ ይላሉ፦

“አላህ አራት ወራቶችን ልዩ አድረጎቸዋል። የላቁም አደረጎቸዋል ልቅናቸውንም ከፍ አድርጎታል። በነዚህ ወራት የሚሰሩ ወንጀሎች ከባድ አድረጎቸዋል። እንዲሁም በዚህ ወር የሚሰሩ መልካም ስራዎችን ምንዳቸውን ከፍ አድርጎቸዋል።”

ሊጣኢፈል መዓሩፍ: 207


በሌላ ዘገባ የሙሐረም ወር ፆም

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

ከረመዳን በመቀጠል በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ወር ፆም ነው።

ሙስሊም ዘግበውታል: 1123

ማስታወሻ፦ የሙሀረም ወር ፆም በኢትዮጵያየ ቀን አቆጣጠር ማክሰኞ ሐምሌ 9 ላይ ይሆናል። ከበፊቱ ወይም ከበስተኋላው ያለውን አንድ ቀን ጨምሮ መፆም መዘንጋት የለበትም።