🕋ISLAMIC ZONE🕋
15.5K subscribers
1.55K photos
183 videos
1 file
554 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሌላኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @hanif_tube

For comment an& promotion
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Islamic_zone_bot
Download Telegram
ላንተ ነው ኢላሂ😭😭😭


እግር የለውም ሀጅ ከማደረግ አላገደውም


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
በ ሀገረ ኦርዶን አንድ ህፃን ልጅ የሃማስ ቃል ኣቀባይን አቡ ኡበይዳ አስመስሎ ሲናገር ታይቷል።



በኢድ ቀናችን የተበደሉትን የፍልስጤም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን እናስታውሳቸው።


ኢድ ሙባረክ 👍


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
Forwarded from Hanif Tube
ከአዲስ አበባ እና አካባቢዋ አዲስ አበባ ስታዲየም የኢድ ሰላት ለመታደም ለመጣችሁ ምእመናን በሙሉ።

በዘንድሮው የ1445ኛ ዓመተ ሂጅራ የኢድ አልአድሀ በዐል ጀምሮ የኢድ ሰላት ሰአትንበማስተካከል 2:30 እንዲሆን በማድረግ ከዚህ ቀደም ይፈጠር የነበረውን በርካታ ሰጋጆች ሳይሰግዱ የሚመለሱበትን ሁኔታ በአንፃራዊነት የተሻለ ማድረግ ተችሏል።

በትናንትናው እለትም ከፍተኛ ምክር ቤቱ የሰላት ሰአትን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ከጠዋቱ 2:30 ሰላት እንደሚጀመር ያሳወቀ ቢሆንም ሰአቱን ለመቀየርና 2:00 ለማድረግየሚያስገድድ ምክንያት ገጥሟል።
ይህም ቢሆን ማህበረሰቡ ከተጠራበት ሰአት በጣም የቀደመ ስለሚሆን ቢያንስ 2:15 እንዲሰገድ ተወስኖ ከሰአቱ ቀደም ብሎ
ለማሳወቅ ተሞክሯል።

በመሆኑም የእለቱ የኢድ ሰላት ከጠዋቱ 2:20 ጀምሮ እንዲሰገድና የኤፍ ኤም 97.1 ቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍ ሆኗል።
ይሁንና በመግለጫው የተጠቀሰው ሰአትባለመጠበቁ ምክንያት ከየአካባቢው ወደ ስታዲየም በመምጣት ላይ ሆናችሁ ሰላት ላመለጣችሁ በሙሉ ምክር ቤታችን ታላቅ ይቅርታን ይጠይቃል።

በድጋሚ ዒድ ሙባረክ


@Hanif_tube
በሶስቱ የአያሙ አት-ተሽሪቅ ቀናቶች ዱዓ ማብዛት የተወደደ ነዉ ።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ዛሬ፣ ነገና ከነገ በኋላ እነዚህ ቀናቶች የመብላት፣ የመጠጣት፣ አላህን የማውሳት ቀናቶች ናቸውና አትፁሙ።]


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
"በሀሜት ለተጠመዳችሁ❗️

ከክፉ መጨረሻ ተጠንቀቁ! ሞት  በድንገት ይመጣልና።
ምናልባት በሰዎች መካከል መለያየትና መነታረክ እንዲፈጠር ወሬ በማቀባበል  እየተሯሯጣችሁ ፍጻሜያችሁ ይሆናል። በሞታችሁበት ነገር ላይ ደግሞ የውመል ቂያማ ትቀሰቀሳላችሁ።"


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ይነበብ! ይነበብ! ይነበብ!

አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ በቀድሞ ስሙ ትዊተር በአሁኑ ስሙ ደግሞ ኤክስ (X) ስለ አንድ ሰው ታሪክ እያነበብኩ ነበር እና ይህን ታሪክ ሁሉም ሰው እንዲያነበው በእውነት እፈልጋለሁ ፣እና ልብ ብሎ ሚያዳምጥ ጆሯችሁን ስጡኝ በአረብኛ ነው ግን "ኢንሻአላህ" የምችለውን ሁሉ እሞክራለሁ
ከመጀመራችን በፊት አንድ ነገር ማለት የምፈልገው ነገር አለ።

ሁለት ዓይነት ሕልሞች አሉ ከአላህ (ሱ.ወ) የሆነ ህልም እና ከሸይጣን የሆነ ህልም

ከአላህ ዘንድ ያሉ ሕልሞች ምናልባት ከመጥፎ ነገር ያስጠነቅቁዎታል ወይም አስደሳች ዜና ይሰጡዎታል እናም አንዳንድ ጊዜ ሙስሊም ሲሞት እና ዕዳ ሲኖርባቸው በህልም መልክ ለቤተሰብ አልፎም ለ ጓደኛ ምልክት በሚሆን መልኩ በህልም ይመጣል ወደ ታሪኩ እንግባ

ባለታሪኩ ሲናገር እንዱህ በማለት ይጀምራል "እኔ  የ21 አመቴ ወጣት ስሆን ጓደኛዬ ከጥቂት ወራት በፊት በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ" አላህ ይዘንለት

"መልካም ‎ስነምግባር ነበረው የማይወደውም የለም ወላጆቹ ጭምር እና ለሁሉም ያለውን ክብር፣ ደግነት እና መልካም ስነምግባር ሁሉም ይመሰክራል።"

"በሞቱ ሁሉም ሰው ተደናግጧል፣ ማለት ምንችለውም አልሀምዱሊላህ ብቻ ነው። እሱ ከሞተ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እየተሰቃየ እና በጀሃነም እየተቃጠለ በህልሜ አየሁ። በአላህ እምላለሁ ሁልጊዜ  ባየሁት ነገር በጣም እየፈራው ነው ከእንቅልፌ የምነቃው።

"እና ለምን እንዲህ እንደሆነ አላወኩም

"እውን ግን ይህ ነገር እሱ ላይ እየሆነ ነው?"
እራሴን እጠይቃለው


በአላህ እምላለሁ።ሁሉም የሚያቀው ሰው
ስለበጎነቱ ይመስክር ማንም ሰው ስለሱ መጥፎ ነገር የማውራት አቅም የለውም


ቅዠቶቹ በተደጋጋሚ መጡብኝ
እርዳታ ፈልጎ ይመስላል..

የሰማያትንና የምድርን ፈጣሪ በሆነው አላህ እምላለሁ ጩኸቱ ትክክል እንዳልነበረ፣ ጩኸቱ በጣም አስፈሪ ነበር

ከአእምሮዬ ሊጠፋ አልቻለም
ለሱ ይሆን ዘንድ ሶደቃህ ስጠሁ ዱዐም አረኩለት ምንም አይነት ወንጀል ቢሰራ ምናልባት አላህ እሱን ይቅር ይለዋል። በማለት

ነገር ግን ምንም ነገር ባደርግ ምንም ለውጥ አልመጣም ምንም አልተፈጠረም።

ቅዠቶቹ ሊለዩኝ አልቻሉም።

"የተሰቃየበት አሳፋሪ ምስል በአእምሮዬ ተቀርቅሯል  አንድ ሰይድ ከጆሮውና ከአፉ እንዲሁም ከጥፍሩ ስር ወጣ። ሰይድ ሚባለው ፈሳሽ ነገር ሲሆን ከ ደም ጋር የተቀላቀለ ነገር  ነው." እሱ ነገር ከአእምሮዬ  ሊጠፋ አልቻለም

"መተኛትን ጠላው እሱን ሲያሰቃይ ላለማየት እንቅልፌን አልተኛም ነበር

ከዱዓ እና ከሶደቃ በስተቀር ምንም  ነገር ማድረግ አልቻልኩም ወደ ሼኽ መሄድ ፈልጌ ነበር
እነዚህ ሁሉ ምን እንደሆኑ ንገረኝ ህልሞች ያብራራሉ? ብዬ ለመጠየቅ ግን ሁሉም
ከሸይጣን ብቻ እንደሆነ እና እሱ እንዳልሆነ ተስፋ አድርጌ በመቃብሩ ውስጥ እየተሰቃዩ አይደለም በማለት ሼኽ ጋር መሄዱን ተውኩት ።

ከዚያ ከሁለት ቀን በኋላ እሱ እየተሰቃየ  ቅዠት አየው ወደኔም መጣ"

ሁለት ግዙፍ ፍጡሮች አፅም ወዳለበት እና ሰዎች ወደ ሚቀጠበት ቦታ ይጎትቱታል።
እዛም ያሰቃዩታል የቀለጠ ብረት በጆርሮው ይጨምሩበታል በሰቀቀን ይጮሀል
በድምፁ ውስጥ አስከፊ ህመም ይታያል

እጆቹ ተቃጥለዋል እንዴት ብዬ ፈራሁ አሰቃቂ ነበር"

በመጨረሻም በህልም አናገርኩት፡ "ስሙን ጠርቼ ለምን እንዲህ ያደርጉብሃል? ወላጆችህን ስታከብር እና ሰላትህን ስትጠብቅ ለምን እንዲህ ያደርጋሉ? ምን አይነት ኃጢአት ብሠራ?" ነው አነጋገረኝ እና እንዲህ አለኝ፡ "ሙዚቃ ያ"* ሙዚቃ! ከሞትኩ በኋላ መቃብር ውስጥ ከገባሁ በኋላ ቀብሬ ውስጥ እየተሰቃሁ ያለሁት ዘውታሪ በሆነ ወንጀል ነው ሁሌ እንደተሰቃየሁ አንድም ቀን እረፍት አላየሁም እሄ ሁላ በ ሙዚቃ የተነሳ ነው አለኝ

"ይህን ብቻ ነው የማስታውሰው

ከዚያም እንደገና ጎተቱት። የእሱ እይታ ልቤን ሰበረው ። የስቃይ  ጩኸት ነበር ሚጮሀው
በየምሽቱ ባንኜ እንድነቃ የደርገኝ ነበር፣
ኃጢአቱ ሙዚቃ መሆኑን አወኩኝ ።
ነገር ግን ዘውታሪ የሆነ ወንጀል ሲል አልገባኝም ምን ማለቱ ነው?
ለቀናት ስለሱ እያሰብኩ እራሴን አጨናነኩኝ

" ከዚያም አልሀምዱሊላህ አንድ የInstagram አካውንት እንበረው አስታወስኩ
በዛ ላይም ዘፈኖች፣ ሙዚቃ፣ ይለቅ ነበር
ምን ያህል ተከታይ እና ላይክ እንደለው ሳይ ልቤ ተሰበረ

ማንም ግን መሞቱን አያውቁም!! ዘውታሪ የሆነ ወንጀል ሲለኝ እሄን ማለቱ ነው። ሰደቀቱል ጃሪያ ወይም ዘውታሪ የሆነ ሰደቃ እንዳለ ሁሉ ዘውታሪ የሆነ ወንጀል አለ

ሚለቃቸውን ዘፈኖች ሰው ባዳመጠው ልክ ነበር እሱ ወንጀል ሚያገኘው በዛም ሚቀጣው
በጣም ያሳዝናል

ነገር ግን "ስለ እሱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም ስለ ይለፍ ቃሉ (Password)፣ኢሜሉ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም ነገር ግን እሱ አሁንም እየተሰቃየ እነደሆነ ሳስበ መፍትሄ  ፍለጋ ሄድኩ።

ነገር ግን ወላሂ ምንም መፍትሄ ማግኘት አልቻልኩም በእነዚህ ቀናት ውስጥ እፎይታ አግኝቼ አላውቅም ነበር

መተኛት እሰኪያቅተኝ ድረስ እጨነቅ ነበር የኔ ጥፋት  እንደሆነ ተሰማኝ እንደዛ እያረገ መሆኑን እያወኩ ምንም አላልኩትም ነበር ተው ይቅርብህ አላልኩትም ነበር በቻ አላህ ረድቶኝ ወደ አካውንቱ ገብቶ ሁሉንም መደለት ሚችል ሰው አገኘው በመጨረሻም ስለ ሁኔታው አስረድቼው ሁሉንም ነገር ደለተው

ከረጅም ጊዜ በኋላ ጊዜ አካውንቱን ካዘጋሁ በኋላ የእንቅልፍ እፎይታ አገኘሁ ምንም ቢሆን ግን ያየሁትን ህልም እንዴት ሲሰቃይ እንደነበር መቼም አልረሳውም። ያ ነገር ለኔ ዘፈን እንድጠላ ከበቂ በላይ ነበር ከዛን ቀን በኋላ ሰምቼም አላቅም የተረዳሁት ነገር ይህ ዓለም ፈተና ብቻ መሆኑን ነው።

ይህ ነገር አብዛኞቻችን ላይ አለ ጓደኛችን ምንም ውንጀል ቢሰራ መምከር ብሎ ነገር አልፈጠረብንም ለምን? የነብዩ ኡመት ሚለየው በበጎ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል አልነበር እሱን የት ጣልነው መች ነው እርስ በርስ ምንደራረሰው አላህን ልንፈራ ይገባል አብሶ በ ዘፈን ሰው ሁሉ ሀላል በሚመስል መልኩ ሁሉም ጋር አለ ምን ያህል ልባችንን እንደሚያደርቀው ወላሂ..

ማለት ሚቻለው አላህ ሰምተው ከሚጠቀሙት ከሚሰሩበትም ያድርገን አሚን🤲

COPIED FROM Y.N


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
👨‍👩‍👧‍👦 አያመ ተሽሪቅ! 11,12,13

ከበሺር ቢን ሰሂም ተይዞ፡ ነቢዩ (▫️) ስለ አያመ ተሽሪቅ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا يدخلُ الجنَّةَ إلاَّ نفسٌ مسلمةٌ، وإنّ هذِهِ الأيّامَ أيّامُ أكلٍ وشربٍ..﴾

“ነፍሱ ሙስሊም የሆነች ቢሆን እንጂ ጀነትን አይገባም። እነዚህ ቀናቶች ደግሞ የመብያና የመጠጫ ቀናቶች ናቸው።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 1407


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
'
ወንጀል ሰርተን አላህን በማመፃችን ልናዝን ሲገባን ይሄኮ ቀደር ነው (ስለተፃፈ ነው) እያልን እስከ መሟገት ድረስ እኮ ነው የወረድነው😭😭😭


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ስለዓረፋ ሲነሳ ተያይዞ የማይረሳው የአባታችን ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ታዛዥነት ሁላችንም ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። በሰዓቱ አባት ልጁን ለማረድ ሲወስን የሁኔታው ከባድነት አያጠራጥርም። ነገር ግን የኢስማኢል (ዐ.ሰ) ምላሽስ ምን ሆኖ ይሆን? እርዱ እንደሚፈፀም እርግጠኛ በሆኑበት ቀፅበት የተናገሩት የመጨረሻ ንግግራቸው ምን ነበር? ዛሬ.... ታዛዥነትን ከሳቸው አንፃር እንየው እስቲ

{...... የኢስማኢል የመታረጃ ጊዜያቸው ሲቃረብ አባታቸውን እንዲህ በማለት መከሩ።

"አባቴ የምፈልጋቸው ነገሮች አሉ:-

~እጆቼን ና እግሮቼን አጥብቀህ እሰራቸው። ስቃይ ሲበረታብኝ እንዳላስቸግርህና የጌታዬን መብት እንዳላጎድል ይረዳኛል።
~ደሜ እንዳይረጭብህ ልብሶችህን በደንብ ሰብስብ።
~ቢላዋው በደንብ ሳለው፤ ነብሴ ቶሎ እንድትወጣ አንተም ቶሎ እንድትገላገል።
~ልብሴን ይዘህ ወደ እናቴ ሂድ ለመፅናናት ይረዳት ይሆናል።"

       ኢብራሂም(ዐ.ሰ) አነዚህን ቃላት ከልጃቸው አንደበት ሲሰሙ ዓይኖቻቸው በእንባ ተሞሉ።አብዝተው አለቀሱ። እንዲህ አሉ:-

      "የአላህን ትዕዛዝ እንድፈፅም ምን ያህል አገዝከኝ?" ቀጥለው እጆቻቸውን ወደ ሰማይ አንስተው ዱዐ አደረጉ:-

     "ጌታዬ ባለሁበት ሁኔታ ትዕግስትን አላብሰኝ! እንግዲህ ምንም አልቀረኝም። አርጅቻለሁና እዘንልኝ!"

ኢስማዒልም አሉ:-

"ጌታዬ ትዕግስትንና ፅናትን አላብሰኝ። አባቴ ሆይ የጀነት በሮች ተከፍተዋል።"

መላኢካዎች በነገሩ ግራ ተጋብተው ተደናግሯቸው ሱጁድ በመውረድ አላህን ይማፀናሉ። <<ጌታችን ሆይ! ነብይህ ያንተን ፍቃድ ሊሞላ ለመሰዋት ተጋድማል!... እዘንላቸው >>ይላሉ።

     "አባቴ! ከፍቅር ማሳያዎች አንዱ አለመዘግየት ነው! በላ የታዘዝከውን ቶሎ ፈፅም!"

እዩ ታዛዥነት በረቢ 🥺

ዒድ ሙባረክ


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ጓደኛን በንግግሩ ሳይሆን በስራው እወቀው ወዳጅን ደሞ በምላሱ ሳይሆን በእንክብካቤው እወቀው።

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
🥀| እንኳን ደስ አላችሁ |😍
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
:
#ድሆች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

➣ከሀብታሞች አምስት መቶ አመት በፊት ጀነት ትገባላችሁ፡፡

:
#በሽተኞች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

➣ከታገሣችሁና ምንዳችሁን በአላህ ላይ ከተሣሰባችሁ ወንጀላችሁ እንደ ደረቅ ቅጠል ይረግፍላችኋል፡፡

:
#ሚስቶች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

➣ባላችሁን ካስወደዳችሁ፣ ሶላትን ከሠገዳችሁ፣ ፆምን በትክክል ከፆማችሁ.. ቀጥታ ጀነት ትገባላችሁ፡፡

:
#ወጣቶች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

➣በአላህ ዒባዳ ላይ ካደጋችሁ የትንሣኤ ቀን በረህማን ጥላ ሥር ትሆናላችሁ



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
●○●○●○●○●○●○●○●○●

◾️የጁመዓ ቀን ሱናዎች


♦️ገላን መታጠብ
♦️ሽቶ መቀባት ለወንዶች
♦️ሲዋክ መጠቀም
♦️ጥሩ ልብስ መልበስ
♦️ሱረቱ ከህፍን መቅራት
♦️በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
♦️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት


اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد

http://t.me/islamic_zonee

●□●□●□●□●□●□●□●□●
በአላህ ይሁንብኝ…!ምን አልባት ወንጀል ጊዜያዊ የስሜት ትኩሳትን ያቀዘቅዝ ይሆናል። ነገር ግን በዘላቂነት ፀፀትንና የበታችነትን እንዲሁም መረበሽን ያስከትላል!

አላህ እርሱ ከሚጠላው ተግባር ፣ ንግግር እና ሃሳብ የምንርቅ ያድርገን!


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
እየሱስ/ኢሳ ተሰቅሏል ወይ ?

“ሳትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም፤ እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም አለ።”
  — ዮሐንስ 7፥34
ምን መሰላችሁ እንደ እኛ ( እስልምና) አስተምህሮ ኢሳን(እየሱስን) 0.ሰ አልሰቃሉትም፣ አልገደሉትምም ይህን የእስልምና አስተምህሮ የራሳቸው መፅሀፍ ያረጋግጠዋል ከላይ የተጠቀሰው አንቀፅ አንዱ ምሳሌ ነው
ፈልገውታል ግን አላገኙትም  እሱ ወዳለበት (ወደ ሰማይ) ሊወጡ አይችሉም
አላህ እንዲህ ይላል

وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ኢናሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
በዘንድሮ ሐጅ ከ1ሺህ በላይ ሁጃጆች አላህ ይዘንላቸው በሃይለኛ ሙቀት የተነሳ ህይወታቸው አልፏል

ከሞቱት 5ቱ ኢትዮጵያኖች ናቸው


አላህ ይዘንላቸው ስራቸውን ይቀበላቸው


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የካእባ ቁልፍ ዋና ያዥ እና የሶሃባው የኡስማን ኢብኑ ጠልሃ (ረ.ዐ) 109ኛ ተከታይ ቤተሰብ የነበሩት ሼኽ ሳላህ አል-ሻይባ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

አላህ ይዘንላቸው ስራቸውን ይቀበላቸው
(እንቅልፍ)
💥ከአሏህ ተኣምሮችና ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ፀጋዎች መካከል አንዱ እንቅልፍ ነው
💥አሏህ የሰላምና የጤና እንቅልፍ የሰጠውን ሰው ማንም ሊነፍገው አይችልም

☀️እንዲህ ዓይነቱን እንቅልፍ እርሱ ለነፈገው ሰው ደግሞ ማንም ሊሰጠው አይችልም!
በመሆኑም በፈለጉት ሰዓት ተኝተው በፈለጉት ሰዓት መነሳት ትልቅ ምስጋና የሚያስፈልገው የጌታችን አሏህ ኒዕማ ነውና ከልብ الحمد لله  ማለት ያስፈልገዋል
እንቅልፍ ትንሹ ሞት ነውና በዛው እንደተኙ አለመቅረትና ዳግም ተነስቶ አላህን ለመገዛት መብቃትም ሌላው ተጨማሪ ምስጋና የሚያስፈልገው ፀጋ ነው! ለዚህም ነው ሙስሊሞች ልክ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ:-
(("الحمد لله الذي أحيانا بعد ما أماتنا"))
( ከገደለን በኋላ ዳግም ህያው ያደረገን ጌታ አሏህ ይመስገን) የሚሉት
💥 ሆኖም በዲናችን ሁሉም ነገር ገደብና አደብ(ሥርኣት) አለው
☀️የእንቅልፍ አደብ(ሥርኣት) እንቅልፍ አደቡ ከተጠበቀ ትንሹም በረካ ይሆናል፣ ለጤናም ተስማሚ ከመሆኑ አልፎ የህሊና ሰላምን ይለግሳል!
☀️የእንቅልፍ መጠን-
እንቅልፍ ሲበዛ ቀልብ ይደርቃል፣ ከመድረቅም አልፎ ይሞታል
የሰውነት መወፈርንና መጫጫንንም ያስከትላል!
💥ለአኺራችን ስንቅ የምንሰንቅበትን ውድ ጊዜያችንንም ያባክናል፣
ግዴለሽነትንና ስልቹነትንም ያስከትላል!
☀️ጥሩ እንቅልፍ ማለት:- አንተ መተኛት ስለፈከግክ የምትተኛው ሳይሆን  ሰውንነትህ መተኛት ሲያስፈልው የምትተኛው እንቅልፍ ነው!
☀️ጥሩ የእንቅልፍ ሰዓት ማለት-
ከዒሻዕ ሶሏት በኋላ የሌሊቱ መጀመሪያ ላይ የሚተኛ እንቅልፍ ነው።
☀️በቀኑ ክፍለ-ጊዜ የተወሰነ ሰዓት አረፍ ማለት ሱናና ጠቃሚ ሲሆን፣ ለዚህም የተመረጠው ወቅት የቀኑ መሀል ነው
💥ከፈጅርና ከዐሱር በኋላ መተኛት ተገቢም ጠቃሚም አይደለም
☀️ምናልባት ማታ ያልተኛ ሰው ከሱብሂ በኋላ ጸሐይ እስክትወጣ ጠብቆ ከዛ መተኛት ይችላል!
በተቻለው ያህል ሱብሂ እንደተሰገደ ላለመተኛት መሞከር ይኖርበታል!
☀️ በየትኛውም ሰዓት ሲተኙ ውዱዕ ማድረግ ከእንቅልፍ በፊት የሚደረጉ ዚክሮችን ማለት ፣ፊትን ወደ ቂብላ ማዞር፣በቀኝ ጎን  ዞሮ መተኛት፣
እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ ዚክርና ቁርኣንን ማብዛት ተገቢና ከሙእሚኖች ባህሪ ነው
☀️እንቅልፍ ጨርሰው ሲነሱም ፊትን በእጆች ጠረግ ጠረግ ማድረግና ከላይ የተጠቀስውን ዚክር ማለት ሱና ሲሆን ፣እንደባነኑ ከፍራሽ ፈጥኖ መነሳት አይመከርም
ወሏሁ አዕለም