🕋ISLAMIC ZONE🕋
14.8K subscribers
1.53K photos
167 videos
1 file
535 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሌላኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @hanif_tube
Download Telegram
001 Al-Fatihah
All Islamic channel
ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች እየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አቡበከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም  ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣
2.አንቱን ማየት፣
3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣ በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣ ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!
°
የጁምአ ሱናዎች

1 ትጥበት
2 ዱዓ ማብዛት
3 ሰለዋት ማብዛት
4 የካህፍን ምዕራፍ ማንበብ
5 መስጂድ በጊዜ መግባት
6 ሲዋክ (መፋቅያ መጠቀም)
7 መልካም ልብስ መልበስ
8 ሽቶ መቀባት (ለወንድ)


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
አሰላሙ አለይኩም ዛሬ እስቲ ደስ ያሰኘኝን ታሪክ ላካፍላችሁ ከረታት በአንድ ቀን ባል ሙስቱን እንዲ በማለት ይጀምራል
ባል፦ አስር ሰግደሻል?

ሚስት፡ አይ

ባል፡- ለምን?

ሚስት፡- ከስራ ስለተመለስኩ ትንሽ ደክሞኝ ትንሽ ተኛሁ።

ባል፦ እሺ.........ሂጂ ለዒሻ ሰዓቱ ሳይደርስ አስር እና መግሪብ ሶላት ስገጂ።

በማግስቱ… ባልየው ለስራ ጉዳይ ከተማውን ለቅቋል… በረራው ሊደር ስ ከተባለ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ግን አልደውልም ወይም በሰላም መድረሱን ለማሳወቅ እንደተለመደ ው መልእክት እንኳን አላደረገም። !!

ሚስትየው ባሏን ለማጣራት ትጠራ ለች እሱ ግን አያነሳም‥ እንደገና ደ ወለች; ስልኩ ይደውላል ግን ምን ም መልስ የለም ።

የምትወደውን ባለቤቷን ለመጥራት ከብዙ ሙከራዎች በኋላ መጨነቅ ጀመረች እና ምንም መልስ አላገኘ ችም ለራሷ የሆነ ነገር ተሳስ ቷል ብላ ታስባለች, እሱ በጭራሽ አ ያደርግም. ልክ እንዳረፈ ሁልጊዜ ይደውላል።

ጥቂት ሰአታት አለፉ...እና በድንገት ስልኩ ጮኸ እና ባልየው። ሁሌም የምትጨነቀችው ሚስት፡ በሰላም _ ደርሰሃል ??

ባል፡- አዎ አልሃምዱሊላህ

ሚስት፦ መቼ?

ባል: ከ 4 ሰዓታት በፊት.

ሚስት በንዴት ቃና፡ ከ4 ሰአት በፊት ? እና አትደውልም?

ባል፡ ደክሞኝ ነበርና ትንሽ እንቅልፍ ለመተኛት ወሰንኩ።

ሚስት፡-ብትደውልልኝና እንደደረስክ ብታሳውቀኝ ጥቂት ደቂቃዎች አይጎዳህም ነበር......... በተጨማሪም ስደውልልህ ስልኩ ደጋግሞ ሲጠራ አልሰማህም እንዴ ..??

ባል፡- አዎ ሰምቻለሁ..

ሚስት፡ እና አታነሳም..?? ጥሪዎቼ ለአንተ በቂ ያልሆኑት ለምንድነው .. ??

ባል፦የአንቺ ጥሪዎች ለእኔ አስፈላ ጊ ናቸው ነገር ግን ትላንትና የአዛን ጥሪ አለመመለስሽ የተቸገርሽ አይመስልም ነበር..... የአላህ ጥሪ

ዓይኖቿ እንባ ያዘሉት ሚስት እና ከአጭር ዝምታ በኋላ፡- አዎ፣ አንድ ነገር አለህ አለች....ይቅርታ..... ባል፦ ለምንድነው ይቅርታ የምትጠይቀኝ ?

የአላህን ምህረት መጠየቅ አለብሽ እና ተመሳሳይ ስህተት ለሁለተኛ ጊዜ አትድገ ሚ። እኔ የምፈልገው ከዚህ ምድራዊ ዓለ ም በኋላ አላህ በጀነትም ዳግም እንዲያ ጣምረን ነው። ከዚያን ቀን ጀምሮ ሚስ ትየዋ ማንኛውንም ሶላቷን አታዘገይም።

በእውነት የሚወድህ ወደ አላህ መንገድህ ላይ ወደፊት የሚገፋህ ነው😊


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
قُلْ إِنَّ الْمَوْتَ الَّذِي تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُ مُلَاقِيكُمْ ۖ

"ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት በእርግጥም
የሚያገኛቹ ነው።"

ሁሌም በዝግጅት ላይ ሁን!ሞት ወደአንተ ከመምጣት ምንም ቅሮት የሌለው ነገር ነው።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቁርአን ግብዣ

part(32)

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @Islamic_zonee ለወዳጅ ዘመዶው ያጋሩ ባረከላሁፊኩም
የተከበሩ ወራቶች!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا، مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلَاثَةٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ، وَذُو الْحِجَّةِ، وَالْمُحَرَّمُ، وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ﴾

“አመት አስራ ሁለት ወራት ነው። ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ‘ረጀብ’ ወር ነው።”

ቡኻሪ (3197) ሙስሊም (1679) ዘግበውታል،

ኢብኑ አባስ (رضيﷲ عنهما) እንዲህ ይላሉ፦

“አላህ አራት ወራቶችን ልዩ አድረጎቸዋል። የላቁም አደረጎቸዋል ልቅናቸውንም ከፍ አድርጎታል። በነዚህ ወራት የሚሰሩ ወንጀሎች ከባድ አድረጎቸዋል። እንዲሁም በዚህ ወር የሚሰሩ መልካም ስራዎችን ምንዳቸውን ከፍ አድርጎቸዋል።”

ሊጣኢፈል መዓሩፍ: 207


በሌላ ዘገባ የሙሐረም ወር ፆም

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

ከረመዳን በመቀጠል በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ወር ፆም ነው።

ሙስሊም ዘግበውታል: 1123

ማስታወሻ፦ የሙሀረም ወር ፆም በኢትዮጵያየ ቀን አቆጣጠር ማክሰኞ ሐምሌ 9 ላይ ይሆናል። ከበፊቱ ወይም ከበስተኋላው ያለውን አንድ ቀን ጨምሮ መፆም መዘንጋት የለበትም።