🕋ISLAMIC ZONE🕋
15.8K subscribers
1.54K photos
178 videos
1 file
548 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሌላኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @hanif_tube

For comment an& promotion
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Islamic_zone_bot
Download Telegram
ለፈገግታ
ምከረው ምክረው

እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ።
በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦

«እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ።

እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ 👋

«ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»  😊

Copied from S.T

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
001 Al-Fatihah
All Islamic channel
ረሱል ﷺ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች እየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ ﷺ አቡበክርንረ.ዐ "ያ አቡበከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም  ረ.ዐ "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ከአንቱን ጋር መቀመጥ፣
2.አንቱን ማየት፣
3.አንቱ ባዘዙዋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ረ.ዐ ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን ረ.ዐ በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"
"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም ﷺ "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"
አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣ በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣ ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ﷺ " እኔም በዱኒያ ላይ
3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣
በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል አ.ሰ.ወ ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ ነብዩም ﷺ "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣
ጅብሪል አ.ሰ.ወ ተመልሶ ወደ ከሄደ በኋላ ረሱልና ﷺ ሱሃቦቻቸው ረዲየሏሁ አጅመኢን ከመቀመጫቸው ሳይነሱ ተመልሶ መጣና አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሱ.ወ. ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም ሱ.ወ እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ሱ.ወ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ﷺ ሱሃቦች ረ.ዐ.አ የወደዱትን ያስወድደን!
°
የጁምአ ሱናዎች

1 ትጥበት
2 ዱዓ ማብዛት
3 ሰለዋት ማብዛት
4 የካህፍን ምዕራፍ ማንበብ
5 መስጂድ በጊዜ መግባት
6 ሲዋክ (መፋቅያ መጠቀም)
7 መልካም ልብስ መልበስ
8 ሽቶ መቀባት (ለወንድ)


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
አሰላሙ አለይኩም ዛሬ እስቲ ደስ ያሰኘኝን ታሪክ ላካፍላችሁ ከረታት በአንድ ቀን ባል ሙስቱን እንዲ በማለት ይጀምራል
ባል፦ አስር ሰግደሻል?

ሚስት፡ አይ

ባል፡- ለምን?

ሚስት፡- ከስራ ስለተመለስኩ ትንሽ ደክሞኝ ትንሽ ተኛሁ።

ባል፦ እሺ.........ሂጂ ለዒሻ ሰዓቱ ሳይደርስ አስር እና መግሪብ ሶላት ስገጂ።

በማግስቱ… ባልየው ለስራ ጉዳይ ከተማውን ለቅቋል… በረራው ሊደር ስ ከተባለ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ግን አልደውልም ወይም በሰላም መድረሱን ለማሳወቅ እንደተለመደ ው መልእክት እንኳን አላደረገም። !!

ሚስትየው ባሏን ለማጣራት ትጠራ ለች እሱ ግን አያነሳም‥ እንደገና ደ ወለች; ስልኩ ይደውላል ግን ምን ም መልስ የለም ።

የምትወደውን ባለቤቷን ለመጥራት ከብዙ ሙከራዎች በኋላ መጨነቅ ጀመረች እና ምንም መልስ አላገኘ ችም ለራሷ የሆነ ነገር ተሳስ ቷል ብላ ታስባለች, እሱ በጭራሽ አ ያደርግም. ልክ እንዳረፈ ሁልጊዜ ይደውላል።

ጥቂት ሰአታት አለፉ...እና በድንገት ስልኩ ጮኸ እና ባልየው። ሁሌም የምትጨነቀችው ሚስት፡ በሰላም _ ደርሰሃል ??

ባል፡- አዎ አልሃምዱሊላህ

ሚስት፦ መቼ?

ባል: ከ 4 ሰዓታት በፊት.

ሚስት በንዴት ቃና፡ ከ4 ሰአት በፊት ? እና አትደውልም?

ባል፡ ደክሞኝ ነበርና ትንሽ እንቅልፍ ለመተኛት ወሰንኩ።

ሚስት፡-ብትደውልልኝና እንደደረስክ ብታሳውቀኝ ጥቂት ደቂቃዎች አይጎዳህም ነበር......... በተጨማሪም ስደውልልህ ስልኩ ደጋግሞ ሲጠራ አልሰማህም እንዴ ..??

ባል፡- አዎ ሰምቻለሁ..

ሚስት፡ እና አታነሳም..?? ጥሪዎቼ ለአንተ በቂ ያልሆኑት ለምንድነው .. ??

ባል፦የአንቺ ጥሪዎች ለእኔ አስፈላ ጊ ናቸው ነገር ግን ትላንትና የአዛን ጥሪ አለመመለስሽ የተቸገርሽ አይመስልም ነበር..... የአላህ ጥሪ

ዓይኖቿ እንባ ያዘሉት ሚስት እና ከአጭር ዝምታ በኋላ፡- አዎ፣ አንድ ነገር አለህ አለች....ይቅርታ..... ባል፦ ለምንድነው ይቅርታ የምትጠይቀኝ ?

የአላህን ምህረት መጠየቅ አለብሽ እና ተመሳሳይ ስህተት ለሁለተኛ ጊዜ አትድገ ሚ። እኔ የምፈልገው ከዚህ ምድራዊ ዓለ ም በኋላ አላህ በጀነትም ዳግም እንዲያ ጣምረን ነው። ከዚያን ቀን ጀምሮ ሚስ ትየዋ ማንኛውንም ሶላቷን አታዘገይም።

በእውነት የሚወድህ ወደ አላህ መንገድህ ላይ ወደፊት የሚገፋህ ነው😊


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
قُلْ إِنَّ الْمَوْتَ الَّذِي تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُ مُلَاقِيكُمْ ۖ

"ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት በእርግጥም
የሚያገኛቹ ነው።"

ሁሌም በዝግጅት ላይ ሁን!ሞት ወደአንተ ከመምጣት ምንም ቅሮት የሌለው ነገር ነው።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቁርአን ግብዣ

part(32)

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @Islamic_zonee ለወዳጅ ዘመዶው ያጋሩ ባረከላሁፊኩም
የተከበሩ ወራቶች!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا، مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلَاثَةٌ مُتَوَالِيَاتٌ : ذُو الْقَعْدَةِ، وَذُو الْحِجَّةِ، وَالْمُحَرَّمُ، وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ﴾

“አመት አስራ ሁለት ወራት ነው። ከነሱ ዉስጥ አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሶስቱ ተከታታይ ሲሆኑ፤ ዙልቂእዳ ዙልሂጃና ሙሀረም ናቸው። ሌላው ደግሞ በጁማዳና በሻዕባን መካከል ያለው የሙደር (ጎሳዎች የታወቁበት)  የ‘ረጀብ’ ወር ነው።”

ቡኻሪ (3197) ሙስሊም (1679) ዘግበውታል،

ኢብኑ አባስ (رضيﷲ عنهما) እንዲህ ይላሉ፦

“አላህ አራት ወራቶችን ልዩ አድረጎቸዋል። የላቁም አደረጎቸዋል ልቅናቸውንም ከፍ አድርጎታል። በነዚህ ወራት የሚሰሩ ወንጀሎች ከባድ አድረጎቸዋል። እንዲሁም በዚህ ወር የሚሰሩ መልካም ስራዎችን ምንዳቸውን ከፍ አድርጎቸዋል።”

ሊጣኢፈል መዓሩፍ: 207


በሌላ ዘገባ የሙሐረም ወር ፆም

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

ከረመዳን በመቀጠል በላጩ ፆም የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ወር ፆም ነው።

ሙስሊም ዘግበውታል: 1123

ማስታወሻ፦ የሙሀረም ወር ፆም በኢትዮጵያየ ቀን አቆጣጠር ማክሰኞ ሐምሌ 9 ላይ ይሆናል። ከበፊቱ ወይም ከበስተኋላው ያለውን አንድ ቀን ጨምሮ መፆም መዘንጋት የለበትም።
📩የጁምዓ ቀን  !!

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

➧«አላህ ዘንድ ከቀኖች ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው»

➧ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ "ሰሂህ" ብለውታል።(1502)

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

➧«በጁምዓ ለሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድበታል።»

➧ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሀሰን " ብለውታል።
[አል ሲልሲለቱ ሰሂሃ: ቁጥር 1407 ]

  "ጁሙዓችሁ እጅጉን በኢባዳ የተዋበ እና መልካም ዱዓችሁ  ተቀባይነት የሚያገኝበት ቀን ያድርግላችሁ  /ያድርግልን !!



የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @Islamic_zonee ለወዳጅ ዘመዶው ያጋሩ ባረከላሁፊኩም
1st Friday of 1446

Ya Allah,bless us with good health.
happiness and success throughout this year.


Say Amin!!!

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
Live stream started
🕋ISLAMIC ZONE🕋
የአሹራ ቀን ጾም 🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ከሰኞ እስከ ሰኞ
=============
📅 ተከታታይ ወርቃማ ቀናት ከፊታችን፦

ሰኞ: የሙሐረም 9ኛ ቀን፣
ማክሰኞ: የሙሐረም 10ኛ ቀን → የዐሹራእ ጾም፣
ረቡዕ : የዐሹራእ ቀጣይ ቀን፣
ሐሙስ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን፣
ጁሙዓህ: የአያሙልቢዽ የመጀመሪያ ቀን (ሙሐረም 13)
ቅዳሜ: አያሙልቢዽ፣
እሁድ: አያሙልቢዽ፣
ሰኞ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን


አላህ አላህ!

እንኳን ተጨማሪ ሰበብ ኖሮት ሙሐረምን ሙሉውን መፆም ይወደዳል።

የቻልን እንጹም፣ ሌላውንም እናመላክት። አላህ ያግራልን።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
📮 """ታላላቅ_ወንጀሎ"""📮


📍
ይህ ልቦና ላላቸው ሰዎች ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ስለ አንዳንድ ትልልቅ ወንጀሎች ባጭሩ ለማስታወስ ያክል፣

የአሏህን ቁጣ መጠበቂያ ይሆነንም ዘንድ ወንድም እህቶቼን የማስታውስበት ነው።

➴አንድ ሙስሊም ትልልቅ ወንጆሎችን መራቁ በትርፍ ዒባዳዎች ወደ አሏህ ከመቃረብ እጅጉኑ የተሻለ ነው፣ እንዳውም ትልልቅ ወንጀሎችን መራቅ ጀነት ለመግባት ትልቁ ምክናየት ነው።

ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ‏( ﺇِﻥ ﺗَﺠْﺘَﻨِﺒُﻮﺍ ﻛَﺒَﺎﺋِﺮَ ﻣَﺎ ﺗُﻨْﻬَﻮْﻥَ ﻋَﻨْﻪُ ﻧُﻜَﻔِّﺮْ ﻋَﻨﻜُﻢْ ﺳَﻴِّﺌَﺎﺗِﻜُﻢْ ﻭَﻧُﺪْﺧِﻠْﻜُﻢ ﻣُّﺪْﺧَﻠًﺎ ﻛَﺮِﻳﻤًﺎ ‏) ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ‏(31 )
አሏህ በተከበረው ቃሉ እንድህ አለ፦
«የምትከለከሉትን ትልልቅ ወንጀል ከራቃችሁ ፣ ጥቃቅን ወንጀሎቻችሁን እናራግፍላችኋለን ፣ የተከበረም መግቢያን እናስገባችኋለን»።
አኒሳእ (31)
➴ትልቅ ወንጀል ማለት ምን ማለት ነው?
☑️ ኢብኑ አባስ እንድህ አሉ:-

«ከባኢር ወንጀል  ማለት አሏህ በእሳት የዘጋው ፣ ወይም በእርግማን ወይ በቁጣ ወይ በቅጣት የዛተበት ማንኛውም ወንጀል ነው»።
📘ተፍሲር ኢብኑጀሪር (4/41)

➴እንኳን ትልቅ ወንጀል ይቅርና ትንሽ ወንጀል የሚናቅ አይደለም ኢብኑ ጀሪር ተፍሲራቸው ላይ የሚከተለውን አስፍረዋል፣
«አሏህን ምህረት ከመጠየቅ ጋር ትልቅ ወንጀል የለም ፣ ትንሽም ወንጀል የለም ከመዘውተር ጋር»።

🔗ቢጤ የለሽ ወንጀል ፣ አሏህ በተውበት እንጂ የማይምረው ጥፋት ሽርክ ነው"
(አሏህ በሱ ) ላይ ያጋራን እንደማይምር በተከበረው ቃሉ በተደጋጋሚ አስፍሯል።

➴አቡ በክራም አሏህ ይውደድለትና ከመልእክተኛውﷺ  ባስተላለፈው የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንድህ ብለዋል

«የወንጀል ሁሉ ትልቁን ወንጀል አልነግራችሁምን» አሉ እንደታ ንገሩን እንጂ የአሏህ መልእክተኛ አልን
«በአሏህ ላይ ማጋራት ፣ ወላጆችን መበደል ነው»…።አሉ

7️⃣ ሰባቱ አጥፊ አውዳሚ ነገሮችም ከትልልቅ ወንጀል ተርታ ይመደባሉ ቡኻሪና ሙስሊም አቡ ሁረይራን በመጥቀስ ባስተላለፉት የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንድህ ብለዋል፦

➴«((ሰባት አጥፉዎችን ራቁ))
የአሏህ መልእክተኛ ሆይ ምንድን ናቸው ተባሉ
① በአሏህ ማጋራት፣
② አስማት፣
③ አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ አለ አግባብ ማጥፋት፣
④ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣
⑤ አራጣን መብላት፣
⑥ የትግል የጅሃድ እለት መሸሽ
⑦ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ፅዩፍ ሴቶችን መስደብ ነው።» አሉ

ምንጭ:- ቡኻሪ (2766) ሙስሊም (89)
 
ወንጀልን ለመተው የሚጠቅሙን ነጥቦች :

①  ከወንጀሉ አላህ እንዲያወጣህና ለልብህም የተጠላ እንዲሆን አላህን በመማፀን ዱዓን ማብዛት

② በሃዲስ  ላይ ነፍስንና ቀለብን በማስተካከል ዙርያ  የተጠቀሱ  ዱአዎችን ማዘውተር

③ ቁርአንን  በማስተንተን ቀልብን በማስተካከል ኒያ መቅራት

④ ሰላትን  በጥሞናና በመረጋጋት መስገድ

⑤  አላህን በቀልብና በምላስ  ማውሳት

⑥ የቂያማ ክስተቶችን ማስታወስ

⑦ ለወንጀሉ ሊያዳርሱህ የሚችሉ መንገዶችን መራቅ

⑧ ትርፍ ጊዜህን መልካም ተግባራትን  በመስራት ማሳለፍ

⑨ ወንጀሉን ለአላህ ብለህ በመተውህ ምክንያት ልታገኝ የምትችለውን ታላቅ ምንዳና የአላህን ችሮታ  ማስታወስ


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
Forwarded from Hanif Tube
ነገ የአሹራ ፆም ነው
እንፁመው ሌሎችንም እናስታውስ
ይነበብ ይነበብ ይነበብ!!!

አንብባችሁ ስጨርሱ ሼር አድርጉት

✔️  ሞትና ቀጣይ ሂደቶች
 
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ

- መጽሐፎቼ

- ጫማዎቼ

- ልብሦቼ …..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም  እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው  ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣

- ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡

አስቡ ያሄ መልእክት እናንተ ጋር ብቻ እንዲቆይ አትፍቀዱ ለሌሎችም አጋሩ ወይም ሼር አድርጉ በናንተ ምክንያት ሌላ ሰው አንብቦ ቢጠቀም እናንተ የሱ ምንዳ ተካፋይ ናችሁና።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋


ሼር ማድረግን አትርሱ
ምላስ

የሰዎች ጥፋት የሚበዛው አጥንት በሌለው ትንሽ ስጋ ነው።ንግግር ሰዎችን ይገድላል ህያውም ያረጋል..የምትጠቀማቸው ቃላት በህሊናህ ጓዳ ስር ይመዘኑ ከክስረት ይጠብቁሀል።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋