🕋ISLAMIC ZONE🕋
15.5K subscribers
1.55K photos
183 videos
1 file
554 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሌላኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @hanif_tube

For comment an& promotion
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
@Islamic_zone_bot
Download Telegram
وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ(33)

"ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?!"
ሱረቱል ፉሲለት; 33


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሁላቹም ማንበብ ያለባቹ ነገርነው እንዳያመልጣቹ አህባቢ ገራሚ የቀብር ዝግጅት😭😭



በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ።

እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት።

እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል።

እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት....

ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?!

ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው

ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ።

አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?!

ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።"

ዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ናቸው የፃፉት ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር ብታደርጉላቸው እና ከእነሱ ውስጥ አንድ ሰው ቢለወጥ የአጅሩ ተካፋይ ናቹ ባረከላሁ ፊኩም


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
በሀሜት ለተጠመዳችሁ❗️

ከክፉ መጨረሻ ተጠንቀቁ! ሞት  በድንገት ይመጣልና።
ምናልባት በሰዎች መካከል መለያየትና መነታረክ እንዲፈጠር ወሬ በማቀባበል  እየተሯሯጣችሁ ፍጻሜያችሁ ይሆናል። በሞታችሁበት ነገር ላይ ደግሞ የውመል ቂያማ ትቀሰቀሳላችሁ።

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሰበር ዜና ! ተክቢር አላሁ አክበር!!!


እንደ የዓለም ዑለማዎች ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ዘገባ የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ ሌሎች የዓለማችን ሀገራቶችን ሳይጨምር በፈረንሳይ ብቻ 17 ሺህ ሰዎች ኢስላምን መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

"እርሱ ያ መልዕክተኛውን በቀጥተኛው መንገድና በእውነተኛው ሀይማኖት ላይ የላከው ከሀይማኖቶች ሁሉ በላይ ይፋ ይሆን ዘንድ ነው፣ ከሀዲያን ቢጠሉም እንኳን፤"




🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ኢብኑ ቁዳማህ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፡-

•ቀደምቶች(ሰለፎች) ስህተታቸውን የሚነግራቸውን ሰው ይወዱ ነበር።አሁን ግን እኛ ዘንድ በጣም የተጠላ ሰው ስህተታችንን የሚነግረን ነው። ይህ ደግሞ የኢማናችን ድክመት ማሳያ ነው።"

📚[مختصر منهاج القاصدين ٣/ ١٥.]



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
በልጆች ጉዳይ ላይ የነብዩ (ሰዐወ) አደራ👉
🌴<<ሰባት ዓመት ሲሞላቸው ልጆቻችሁን በሰላት እዘዙ አስር ዓመት ሞልቷቸው ካልሰገዱ ግረፏቸው።>>(አቡ ዳዉድ)
🌴<<በልጆቻችሁ መካከል ስጦታን እኩል አድርጉ በመልካም ውለታቸው እናንተን በእኩል ዓይን እንዲመለከቷችሁ እንደምትወዱ ሁሉ።>>(ሙስሊም)
🌴<<ሁለት ሴት ልጆች ኖረውት ለነርሱ የሚያደርገውን እንክብካቤ ያሳመረ አንድም ሙስሊም ሊኖር አይችልም ጀነት የሚያስገቡት ቢሆን እንጂ።>>(ቡኻሪ)
🌴<<አላህን ፍሩ በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ።>>

🌻🌻🌻ልጅህ አንተ ሳታዘው አንተን ተከትሎ የአንተን ምሳሌ ይዞ ወደ መስጂድ ለመሄድ ሲነሳ ከማየት የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር አለ?🌻🌻🌻
🍃ህፃናት ከትችት ይልቅ አርአያነትን ይበልጥ ይፈልጋሉ።🍃


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
﴿صدقةُ السِّرِّ تُطفئُ غضبَ الرَّبِّ،﴾


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስንት Like ይገባዋል በአላህ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የወራሪዋ አይሁድ ዜጎች እህል ውሀ ለራቃቸው ለፍልስጤማውያን የሰብአዊ እርዳታ መኪኖች እንዳይገቡ መንገድ ዘግተው እህሉን እያወረዱ ሲከፋፈሉ ስታይ አንጀትህ ይነዳል። ውስጥህ በብሶት ይቀጣጠላል። 😡😡😡😡😡


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳቹ ማለት....
አላህ سبحان وتعالى
ሰባት ነገሮችን ይወዳል

①☞ተውበት  “አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል”
አል በቀራህ ☞2:222

②☞ ጦሀራ ☞“አላህ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡”
☞አል በቀራህ 2:222

③ ☞ተቅዋ  ❥አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” ☞አተ ተውባ 9:4

④ ☞ኢህሳን  ❥ “አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡”
☞አል ኢምራን 3:134

⑤ ☞ተወኩል ❥“አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”
❥ ☞አል ኢምራን 3:159

⑥ዐድል ❥ “አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡”
☞አል ማዒዳህ 5:42

⑦ ☞ሶብር ☞”አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
☞”አል ኢምራን3:146


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
የ ቂያማ ትናንሽ ምልክቶች አብቅተዋል 😔
1 - የሴቶች መብዛት
2- እራቁታቸውን የሚሆኑ ሴቶች
3- በሙስሊም ሀገራት ከመጠን በላይ ዝሙትና መጠጥ መብዛት
4- ድንገተኛ ሞት
5- በግንባታ መፎካከር
6- ሙዚቀኞች እና ዘፈኖች በስፋት መስፋፋት
7- ብጥብጥ፣ ብጥብጥ፣ ከዚያም አመጽ
8- ወንዶች ሴቶችን መመሳሰል።
የእነዚህን ሁሉ ምልክቶች ገጽታ አላስተዋልክም?

አስበው የሆነ አንድ ቀን ላይ ነቅተህ  ሰዎች በጣም እየጮሁ ልክ ሊጠፉ የተቃረቡ መስለው ፣ ሁሉም በመገረም ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ስትመለከታቸው ።
እሷ ፀሀይ ናት በምዕራብ በኩል እየጠለቀች ነው
ይህ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃለህ!
የተውበት በር ተዘግቷል እና ስራዎች ሁሉ  ወደ አላህ ከፍ ብለው ተነስተዋል።
ጥሩም ሆነ መጥፎ ስራዎች ወደ አላህ ሄደዋሉ
ከዚያ በኋላ የተመላሽ ተውበት ምንም ጥቅም የላትም !!
የትንሳኤ ቀን ዋና ዋና ምልክቶች መካከል፡-

1- ሰባት የአረብ መሪዎች ውድቀት
2- የኢማም ማህዲ መታየት
3- የ መሲሁ ደጃል መታየት
4- የነቢዩ ኢሳ (ዐ.ሰ.ወ)መውረድ
5- ፀሐይ ከጠለቀችበ መውጣት
6- የንስሐ በሮች ይዘጋሉ።
7- አንዲት የምድር አውሬ ሙስሊሞች ላይ ምልክት ስታደርግ ይታያል
8- የ ያእጁጅ እና የ ማእጁጅ መውጣት
9- ለ40 ቀናት በምድር ላይ ጭጋግ ይበዛል እና ሙስሊሞች የቀሩትን ምልክቶች እንዳያዩ ሙስሊሞች ሁሉ ይገደላሉ ።
10 - ታላቅ እሳት
11- የካዕባ መፍረስ
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- ይህንን ዜና በእኔ ስም ያሰራጨ ሰው በቂያማ ቀን በጀነት ውስጥ ቦታ አደርግለታለሁ!!
.
.
የንስሐ ጊዜ አልደረሰምን?
። ሁሉን ቻይ የህነው አላህ እንዲህ ይላል፡- አንተ የአዳም ልጅ ሆይ ኃጢአትህ የ ሰማይ ደመና ያክል የደረሰ ቢሆንና ከዚያም ይቅርታን ብትለምንኝ ይቅር እልሃለሁ ግድ የለኝም።
ጌታችን ሆይ! እኛ ራሳችንን በድለናልና ። አምላካችን ሆይ መልካሙን መጨረሻ ስጠን 🤲


ለአላህ ብለላቹ ሼር አድርጉ ፊኩም
🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሶላትን አዘግይተህ በምትሰግድ ግዜ.. ናዋፊል (ሱና) ሰላት አስከትል

ዘፈን በሰማህ ቁጥር .. ከቁርኣን አንድ ገጽ አንብብ።

ድምፅህን ወላጆችህ ላይ ከፍ በምታደርግ ግዜ..በስማቸው ሰደቃ ስጥ

አንድን ሰው ስታማ. . እኩለ ለሊት ላይ ዱኣ ኣርግለት።

መጥፎውን ሥራ በመልካም ሥራ አስከትል፤ ጌታህም መሓሪ አዛኝ ነውና።

" إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ "‌‌‏

"በእርግጥም መልካም ስራ መጥፎ ስራዎችን ያስወግዳል"


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ድሮ እኔ ካልሰገድኩ አላህ እንደሚቀጣኝ
እያሰብኩ ነው የደኩት አሁን ግን
አለመስገዴ ቅጣቱ እደሆነ ተረዳሁ😭😭😭


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሶላት አለመስገድ...

«ሶላት ባለመስገድህ የሚጠብቅህን ቅጣት ተወውና አለመስገድህ ራሱ ከአላህ የሆነ ቅጣት መሆኑን ተገንዘብ።

የውዱ ነቢይ ﷺ የመጨረሻው ምክር « ሶላትን አደራ!» የሚል ነበር።» አደራቸውን መብላት በራሱ ለሌላ የከፋ ቅጣት የሚዳርግ ቅጣት አይደለም ትላለህን?


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰዎች በሰሩት ወንጀል ምክንያት ወድያውኑ በቅጣት የምይዛቸው ብሆን ኖሮ...


አድምጡት!!!😭😭


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ነገ እኮ ጁምዐ ነው ሰሉ አለ ነቢይ🫶

اللهم صلى وسلم على نبينا محمد
اللهم صلى وسلم على نبينا محمد

ፈጅር ተነስተን ሱረቱል ካህፍን መቅራት እንዳንረሳ



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
. ሰላት ካልሰገድክ ጀሃነም ትገባለህ ብዬ አላስፈራራህም ነገር ግን ያቺ ውቧን ጀነት ታጣታለህ።‼️


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሐጅِ

ማሳሰቢያ
ለ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) ለሐጅ ተጓዦች

የኢትዮጵያ  እስልምና  ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) በኢትዮጵያ   እና  በሳውዲ አየር  መንገዶች  የሚበሩ  የሐጅ ተጓዦችን ረቂቅ  የበረራ መርሐ ግብር  በጠቅላይ ምክር ቤቱ  የመረጃ ማግኛ  ማስፈንጠሪያ  (ሊንክ )  https://hajj.et/hajj-status አማካኝነት  ይፋ ማድረጉ  ይታወቃል።

በተወሰኑ በረራዎች  ላይ  የበረራ መርሐ ግብር  ለውጥ   የተደረገ  መሆኑ እያሳወቅን   አዲሱን  የበረራ መርሐ ግብር  ከሰዓታት በኋላ  የምናሳውቅ በመሆናችንንና  መረጃውን በቋት ዉስጥ እስከምናስገባ  ድረስ ቋቱን (ሊንኩን) ለጊዜዉ  የምንዘጋ መሆናችንንና እያሳወቅን የተከለሰው  መርሐ ግብሩ ቀድሞ ከተጫነው የበረራ ቀንና ሰዓት  ልዩነት ሊኖረው ስለሚችል  ሑጃጆች  ይህንን ተገንዝባችሁ አዲስ በመረጃ ቋት ማስፈንጠሪያ ሊንክ  የሚጫነውን  መረጃ ብቻ  እንድትጠቀሙ  እናሳስባለን ።

ለቀጣይ የሃጅ መስተንግዶ የተመለከቱ አዳዲስ መረጃዎች ከላይ በተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ እና በ9933 ቀጥታ በመደወል እንድትከታተሉ በዚሁ አጋጣሚ እናስታውሳለን።
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋