Intrance result.neaea.gov.et
1.35K subscribers
544 photos
29 videos
301 files
549 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
ይመዝገቡ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ የፊታችን ቅዳሜ ይጠናቀቃል።

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ ቅዳሜ የካቲት 30/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ870 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
#MoE

የመውጫ ፈተና ኩረጃ እና ሌሎች የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም. ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ውሳኔውን አሳውቋል።

የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሰረዙንና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑ በደብዳቤው ተመልክቷል።

ከየካቲት 6 እስከ 11/2016 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና ከ119 ሺህ በላይ ተፈታኞች ለፈተና መቀመጣቸው ይታወሳል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
2016 GEOGRAPHY GRADE 12 MODEL EXAM.pdf
896.9 KB
😍የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና😍

አዘጋጅ 👉አራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

መንፈቀ አመት👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት 

የትምህርት አይነት👉ሁሉም

አመት 👉2016

ክፍል 👉12

❤️Share


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
ቴሌግራም ላይ ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ maximum security እና privacy level

1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode

2. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።

3. ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate secc ቀንሷቸው።

4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።

5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።

6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።

7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ።

8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።

9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts
የ 12ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ ወር ላይ ልሰጥ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

የ 2016 12ኛ ክፍል መውጫ ፈተና ሰኔ ወር መጨረሻዎች ላይ ለመስጠት እቅድ መያዙን ያገኘነው መረጃ ጠቁሞናል። እስካሁን ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ስለ ፈተናው ቀን ያለው ነገር ባይኖርም ከዚህ በፊት ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ ይሰጣል መባሉ የሚታወስ ነው።

ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናው ቀን እየተቃረበ መሆኑን አውቀው ለፈተናው እንድዘጋጁ እንላለን።

#ETU


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
T.me/unv_info
" የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት እየተገባደደ ነው ፤ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት ይጀመራል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የፀጥታ ችግር በሌላባቸው አካባቢዎች ብቻ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው ሀገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ተካሂዶ መጠናቀቁን የገለጸው አገልግሎቱ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል ብሏል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በዚህ ሣምንት ይከናወናል ብሏል።

የፈተና ዝግጅት ሥራው የሀገሪቱን ሥርዓተ ትምህርት የተከተለ እና ተማሪዎቹን በአግባቡ መመዘን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ተቋሙ ገልጿል።

የፈተናው ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አመልክቶ በቀጣይ #የፈተናው_ሕትመት እንደሚጀመር አሳውቋል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የመስጫ የጊዚ ሰሌዳ ወደፊት ይፋ እንደሚሆንም የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ኢዜአ ዘግቧል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
T.me/unv_info
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በቅርቡ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ መጠናቀቁም ተገልጿል።

የፈተናው ሕትመት በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ለኢሳት የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥም አረጋግጠዋል፡፡

ለ3ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
T.me/unv_info
በ2016ዓ.ም ግንቦት አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ገለፀ።

በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከ43 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል 20 የሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈትኑ ተገልጿል።

የአዊ ብሄ/አሰ ትምህርት መምሪያ ተተኪ ሀላፊ አቶ ፀጋ ተሰማ እንደገለፁት በብሄረሰብ አስተዳደሩ ከሚገኙ 43 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 12ኛ ክፍል ያሏቸው ቢሆንም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ መማር ማስተማር በሚከናወንባቸው 20 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ ሀገራዊ መልቀቂያ ፈተናውን እንደሚያስፈቱኑ ነው የገለፁት።5ሽህ 249 መደበኛ 1ሽህ 613 በግል ተፈታኝ ጨምሮ በድምሩ 6ሽህ 862 ተማሪዎች ፎርም ሞልተው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉም ብለዋል።

እንደ አቶ ፀጋ ገለፃ በነዚህ ት/ቤቶችም ቢሆን በተለያዩ ምክንያቶች ክፍለ ጊዜ የባከነባቸውን በማካካስ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መምህራን ተማሪዎችን ልዩ እገዛ በማድረግ እያዘጋጁ ይገኛሉ። እንደ አንከሻ እና አዘና ያሉ ት/ቤቶች ችግሮችን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎችን በመምረጥ ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል ልዩ የንባብ ክፍል አዘጋጅተው ቅኸዳሜና እሁድን ጨምሮ የማገዝ ስራዎች እያከናወኑ እንደሆነም አቶ ፀጋ ተናግረዋል ።

አስፈታኝ ት/ቤቶች ወቅታዊ ችግሮችን ተቋቁመው ውጤታማ ለመሆን እያደረጉት ያለው ጥረት መልካም እንደሆነ ያብራሩት አቶ ፀጋ በተፈጠረው ችግር የተማሪዎች መፅሐፍ አቅርቦት ችግር እንዳጋጠመና ከዚህ ጋር ተያይዞ የትምህርት ይዘት ለመሸፈን ስጋታ መኖሩን አሳውቀዋል።

ትምህርት መምሪያውም በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚሰጠው ሀገራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በብሄረሰብ አስተዳደሩ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በአካልና በስልክ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አቶ ፀጋ አስታውቀዋል ።

[ዘገባው የአዊ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ነው]

ችን በፍጥነት ለማግኘት ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
T.me/unv_info