Intrance result.neaea.gov.et
2.79K subscribers
601 photos
32 videos
302 files
649 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድረሻ አከላት ጋር መክሯል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትምህርት ሥርዓቱ ን ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፌዴራል እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፈተናው የተሳካ እንዲሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው÷የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ተቋሙ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎችና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን÷በቀጣይ ሁሉንም ተማሪዎች በኦንላይን ለመፈተን ሙከራ ይደረጋል መባሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor