ካቦድ ፔጅን በፌስቡክ ፎሎው በማድረግ ቀዳሚ ይሁኑ 💬
Be the first to follow Chabod on Facebook 💬
https://www.facebook.com/profile.php?id=100092577972294

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የእግዚአብሔር ቃል ሲነበብ እንባዬ ይቀድመኛል። እምባዬ የሀዘን አይደለም የደስታ ነው፣ ልብን የሚሞላ ደስታ። የእግዚአብሔርና የበጉ ምስክሮች ያዩትንና የሰሙትን ሲተርኩ ነፍስም አይቀርልኝ። በሕይወቴ የትኛውም ደረጃ ብሆን የማይለዋወጥ የቃሉና የምስክሮቹ ፍቅር እኔነቴን ተቆጣጥሯል። በዚያ መፅሐፍ የማይታየው የክብር አምላክ ይተረካል፣ ለውበቱ መደምደሚያ የሌለው እርሱ በብርሃን ተከቦ ከፀሐይ ይልቅ ሰባት እጥፍ እያበራ ይኖራል ብለው ይመሰክሩለታል፣ ሰማያትን የዘረጋው እርሱ ጎንበስ ቀና እያሉ በሚያመልኩት በእልፍ አእላፋት መላእክት ተከቦ ይኖራል ይሉናል። የእግዚአብሔር ልጅ አለምን ለማዳን ወርዶ እንደሰው ሲመላለስ አብረነው ነበርን ይሉሃል፣ ከጎኑ ሆነን ተራምደናል ታምራቱንና ድንቁን በአይኖቻችን አይተናል ፣ በማንነቱ ተደንቀን በእውነት ይሄስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለን በፊቱ መስክረናል ይሉሀል። ስለሰው ልጆች መከራን ሲቀምስ፣ ለሰው ልጆች ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ በአሰቃቂ መንገድ ራሱን ሲሰጥ ያኔ ነበርን ይሉሃል። ደግሞም በሶስተኛው ቀን ከሙታን ለመነሳቱ ህያው ምስክሮች ነን ይሉሃል፣ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በደመናት በኃይል ከፍ ከፍ ሲል ወደ ሰማያት ወደ ውስጠኛው ሰንጥቆ ሲዘልቅ ቀና ብለን ተመልክተነዋል ይሉሃል...ይኸው ቃል እነዚሁ ምስክሮቹ ወደላይ ከፍ ያለው እርሱ ዳግም በክብር ከመላእክቱ ጋር ተመልሶ ይመጣል ይሉሃል። ዋሃሃህ! እንዴት ያለ ድንቅ ምስክርነት ነው! የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር እና የበጉ ምስክር❤
❤2👍2
ንግሥተ ሳባ የኢትዮጵያ ወይንስ የየመን ንግሥት?
ይህችን ሴት የሂብሩ ቃል (Malkaṯ Səḇāʾ) ማልካት ሳባ ብሎ ይጠራታል። ማልካት ለሚለው ቃል የአማርኛ አቻ ትርጉሙ ንግስት የሚለው ሲሆን ይህች ሴት በሳባውያን ላይ ትገዛ የነበረች ንግስት በመሆኗ ንግሥተ ሳባ ወይንም የሳባውያን ንግሥት የሚለውን ስያሜ አስገኝቶላታል። ሳባውያን ጥንት በደቡባዊ አረብ አከባቢ ሰፍረው ይኖሩ የነበሩ የመናውያን ሰዎች ሲሆኑ በዘመኑ የነበረውን የነገስታቶቻቸውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያሰፈሩበት ጥንታዊ ፅላት በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኝ ኤንሸንት ኦሪየንት ሙዚየም (Ancient Orient Museum) ተመልክቶ ይገኛል። በሀገራችን በኢትዮጵያ በሚነገር አንድ ታሪክ ታዲያ ይህች ሴት የኢትዮጵያ ንግሥት እንደሆነችና ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንጉሥ ሰለሞን ሄዳ ከእርሱ ሚኒሊክ የሚባል ልጅ እንደወለደች፣ ይህም ልጅ ሰሎሞናዊውን መንግሥት በኢትዮጵያ እንዳስቀጠለ ይታመናል። መፅሐፍ ቅዱስ ይህች ሴት ወደ ሰለሞን መውረዷን ቢናገርም ከሰለሞን ግን ልጅ እንደወለደች ፈፅሞ አይነግረንም። በአዲስ ኪዳን ጌታ ኢየሱስ ይህች ሴት ንግሥተ አዜብ/የደቡብ ንግሥት (ከግእዝ ትርጓሜ አዜብ=ደቡብ) እንደሆነች ይጠቁማል(ማቴ 12፥24)። ከዚህ በተጨማሪ መፅሐፍ ቅዱስ ሳባውያን ወንዶች ነገስታቶች እንደነበሯቸው ይነግረናል (መዝ 72፥10)።

“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”
— ቆላስይስ 1፥13-14
— ቆላስይስ 1፥13-14
“አብርሃምም፦ ልጄ ሆይ፥ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው...” ዘፍጥረት 22፥8
ክርስቶስ ኢየሱስ በሰው ልጆች ፋንታ ይሰዋ ዘንድ በእግዚአብሔር የተዘጋጀ የመሥዋዕት በግ ነው።
“ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ዮሐንስ 1፥29
ቅዱስ ዳዊት የክርስቶስ ሥጋ በእግዚአብሔር የተዘጋጀ አዲስ ሥጋ መሆኑን ሲናገር “መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድህም፤ ሥጋን አዘጋጀህልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልሻህም።” ብሎ ይናገራል። መዝሙር 40፥6
"ቃልም ሥጋ ሆነ" ዮሐንስ 1፥14
“And the Word was made flesh”John 1:14
ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሥጋ ተደርጓል! አዎ አዲስ ሥጋ በእግዚአብሔር የተዘጋጀ የአዲሱ አዳም ሥጋ።
እንደሰውኛ አብርሃም ከሳራ ዘር ሊያገኝ ባይቻለውም፣ እንደመለኮት አሠራር ግን የእግዚአብሔር ቃል በእምነት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዘር ሆኖለታልና ክርስቶስ ከድንግል ያለወንድ ፈቃድ በእምነት በእግዚአብሔር ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል(ችሎታ) ሲወለድ የአብርሃምን ዘር ይዟል እንላለን። “የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።” ዕብራውያን 2፥16
ይሄ ሥጋ መበስበስን የማያውቅ ቅዱስ ሥጋ ነው!
“...ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።”
መዝሙር 16፥10
ይሄ ሥጋ በአብ ቀኝ መቀመጥ የሚችል ክቡር ሥጋ ነው!
“..ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” ዕብራውያን 1፥3

የእግዚአብሔርን ክብር ልትሸከም ትችላለህ?
የእግዚአብሔርን ክብር ለመሸከም ትሻለህ፣ ነገር ግን ልትሸከመው ትችላለህ?
“በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።”
— ማቴዎስ 9፥16
የመሸከም ችሎታ(Capacity) ሚስጥር ጥልቅ ነው። እግዚአብሔር ያረጀው ልብስ መቀደዱ የባሰ ሊሆን እንደሚችል ያውቃል።
“በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል" ማቴ 9፥17
እግዚአብሔር የአሮጌውን አቁማዳ ችሎታ ያውቃል። እርሱ አዲሱን የወይን ጠጅ የማያኖርበት እንደሚፈነዳ ስለሚያውቅ ነው።
አሮጌው ሰው አዲሱን የወይን ጠጅ መሸከም አይችልም። ይፈነዳል!
አሮጌው ሰው ሲሰቀል አዲሱ ሰው ህያው ይሆናል። ያኔ አዲሱን በአዲሱ መሸከም ይቻላል።
"..ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።” ማቴ 9፥17

❤1
ህብረት(Fellowship)
የዮሐንስ መልዕክት ምዕራፍ ፩ መግቢያ
የመልዕክቱ ፀሀፊ የጌታ ደቀመዝሙርና ሐዋሪያ የሆነው ዮሐንስ ሲሆን ከጴጥሮስና ከያዕቆብ ጋር ሆኖ ከሌሎች ሐዋርያት ይልቅ ለጌታ ቅርብ የነበረ ሰው ነው።
ይህ ፀሀፊ አስቀድሞ የጌታን ሕይወትና አገልግሎት በወንጌሉ የፃፈልንና በአስደናቂ መገለጥ የራዕይን መፅሐፍ ያበረከተልን ሰው ነው።
ሐዋርያው በዚህ መልዕክቱ ሀሳቡን ሲጀምር ታላቅ በሆነ የምስክርነት ቃል የጀመረ ሲሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለተገለጠ አስደናቂ ህይወት እየመሰከረ ይጀምራል።
1ኛ ዮሐንስ 1
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን።
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን።
የምዕራፉ መክፈቻ ይህ አስደናቂ ምስክርነት ቢሆንም አጠቃላይ የመልዕክቱ ሀሳብ በዋናነት የሚያጠነጥነው ግን ምስክርነቱ ላይ ሳይሆን የምስክርነቱ አላማ ላይ ሆኖ እናገኘዋለን።
“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥3
"እናንተ ደግሞ [ከእኛ] ጋር ህብረት(fellowship) እንዲኖራችሁ..."
ከክፍሉ እንደምንመለከተው ሐዋርያው አንድን ህብረት (fellowship) በማሳየት ሰዎች ወደዚህ ህብረት እንዲመጡና በህብረቱ ውስጥ ባለ የአኗኗር ስርዓት እንዲኖሩ ያስተምራል።

፩ ዮሐንስ መልዕክት ምዕራፍ ፩
አማኞች ስለጌታ ኢየሱስ በሰሙት ምስክርነት በኩል ወደ አንድ ታላቅ ህብረት (fellowship) ተጠርተዋል።
ሐዋርያው ይሄንን ሀሳብ ሲያብራራ ስላየነውና ስለሰማነው ነገር የመሰከርንላችሁ እናንተም፦ እኛ በማመናችን ህብረት እያደረግንበት ወዳለው ህብረት እንድትቀላቀሉ ነው ብሎ ይናገራል።
፫ "እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን።"
ይህ ህብረት ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ጋር የሚደረግ አስደናቂ ህብረት ነው።
፫ "ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።"
፨ ከአብና ከልጁ ከኢየሱስ ጋር ህብረት ማድረግ!
ሐዋርያው ዮሐንስ ሰዎች በተቀበሉት እምነት ኃይማኖተኞችና ወገኞች ብቻ ሆነው እንዳይቀሩ ጉዳዩ ከመናፍስት አባት ከአብ ከልጁም ከክርስቶስ ጋር የሚደረግ የመንፈሳዊ ህብረት ጉዳይ እንደሆነ ያሳስባል።
ክርስትና ወደጠለቀ መንፈሳዊ ህብረት መቀላቀል ነው!
ሐዋርያው በሕይወታቸው ፍፁም የሆነ ደስታ ወደዚህ መንፈሳዊ ህብረት የደረሱ አማኞች መገለጫ እንደሆነም ያስተምራል።
፬ “ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።”

፩ ዮሐንስ ፩፥፭-፲
ይህ ክፍል በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ያለው ሰው የሕይወት ምልልስ ምን መምሰል እንዳለበት የሚያስተምር ክፍል ነው።
ሐዋርያው ዮሐንስ በዚህ ክፍል ሀሳብ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ሊያደርግ የሚፈልግ ሰው ከሁሉ አስቀድሞ ሊረዳው ስለሚገባ ስለ አንድ መሠረታዊ ስለሆነ መንፈሳዊ ትምህርት በማንሳት ይጀምራል፦
“ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።”
1ኛ ዮሐንስ 1፥5
ከእግዚአብሔር ጋር የሚደረግ ህብረት አንዳች ጨለማ የሌለበት በብርሃን የተሞላ አስደናቂ ህብረት በመሆኑ ወደዚህ ህብረት የሚመጡ ሁሉ ከጨለማ ሥራ የተላቀቁና በብርሃን ለመጓዝ ፈቃዳቸውን የሰጡ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
ሐዋርያው ይህንን ሀሳብ ሲያጠናክር በምሳሌ ፦ “ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን” በማለት ያስረዳል። 1ኛ ዮሐንስ 1፥6-7
በተጨማሪም ሐዋርያው ቶሎ የሚከበንን የኃጢአት ጨለማ በመናዘዝና በንስሃ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም በማስወገድ በብርሃን እንድንመላለስ ያስተምረናል።
“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥9