Injibara University
12.6K subscribers
3.26K photos
17 videos
595 files
178 links
Download Telegram
የተሻሻለ የድንች ምርጥ ዘር የማባዛት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የተሻሻለ የምርጥ ዘር ድንችን የማባዛት ሥራ እያከናወነ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ክንዴ ብርሃን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ክንዴ ባለፈው ዓመት የድንች ዘሩን ከሌላ ቦታ በማስመጣትና በማባዛት ለምግብ ፍጆታ እና ለዘር ብዜት አገልግሎት ላይ እንደዋለ ጠቅሰው ከዚህ ምርጥ የድንች ዘርም የግል ድርጅቶችም(NGO) ጭምር በመግዛት ለአርሶ አደሮች ያሰራጩበት ሁኔታ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ በዛሬው እለትም ይህንን ምርጥ ዘር ድንች በአካባቢው ለማባዛት እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የድንች ዘር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ሳይንስ ት/ት ክፍል ኃላፊ የሆኑት መምህር ዘላለም ካሳ በበኩላቸው 1.5 ሄክታር ለድንች ተስማሚ በሆነ መሬት ላይ የዘር ብዜት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው ባለፉት በሦስት ዓመታት የተለያዩ ወረዳዎች ላይ “ጉደኔ” እና “በለጠ” የሚባሉ የድንች ዝርያዎች ላይ የምርምር ስራ ማከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡ በተሰራው የብዜት ሥራም አመርቂ ውጤት የተገኘበት እና ለዘር ብዜት፣ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንዲሁም ለአካባቢ ለፕሮጀክት በመሸጥ ገቢ እንደተገኘበት አስረድተዋል፡፡ ለወደፊቱም ከዩኒቨርሲቲው አልፎ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
መጋቢት 26/2016 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
እንኳን አደረሳችሁ።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ   እንኳን  ለ1445ኛ ዓመት ኢድ-አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ይመኛል።

መልካም በዓል!
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ ያዘጋጀው ልዩ የበዓል መስተንግዶ።
መልካም በዓል!

ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ
Telegram-https://t.me/injiuniversity
Website- https://www.inu.edu.et/
Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni
Email- injibarau@gmail.com
Institution Email -injibarauniversity@inu.edu.et
Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/)
YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity

Explore Your Creative Potential.