Injibara University
13.9K subscribers
3.35K photos
17 videos
597 files
186 links
Download Telegram
የአትክልት ልማት (የአፕል እና ሽቅብ ግብርና/Vertical Farming) የማስተማሪያ እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ሰርቶ ማሳያ ማዕከል ላይ ጉብኝትና ውይይት ተካሄደ፡፡
https://www.facebook.com/share/vQGob3tiiU4p3cmu/?mibextid=oFDknk
#የሀዘን መግለጫ
***
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣ የትምህርት እቅድና ሥራ አመራር
/Educational Planning and Management/ ትምህርት ክፍል፣ 2ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ብርቱካን ጥበቡ ወሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ዩኒቨርሲቲው በተማሪ ብርቱካን ጥበቡ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ፣ የተማሪዋን አስክሬን ወደ ትውልድ ስፍራዋ ሸኝቷል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለቤተሰቦቿ፣ ለጓደኞቿ እና ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሙሉ መፅናናትን ይመኛል!
Forwarded from Yirga Tadesse
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክቶች ግምገማ ተካሄደ።
ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በ2015 ዓ.ም ተጀምረው ባልተጠናቀቁት እና በ2016 ዓ.ም መጀመር ባለባቸው ግንባታዎች ላይ ያተኮረ ከአማካሪ ድርጅቱ እና ከስራ ተቋራጮች ጋር ውይይት አደርገዋል።
ውይይቱን የመሩት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ እንደገለጹት የምክክር መድረኩ ዓላማ በ2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ተጠናቀው አግልግሎት መስጠት የነበረባቸውን ነባር ፕሮጀክቶችን እና መጀመር የነበረባቸውን አዳዲስ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመለየት አሁንም ነባር ፕሮጀክቶች የሚጠናቀቁበትን እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችም የሚጀመሩበትን ስልት ለመቀየስ እንደሆነ አብራርተዋል።
በውይይቱም የበርካታ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ይቀርፋሉ የተባሉት የመምህራን መኖሪያ አፓርትመንቶች እና የአስተዳደር ህንጻዎች በቅርቡ ተጠናቀው ለአግልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እንዲቻል ከአማካሪ፣ ከስራ ተቋራጮች እና ከዩኒቨርሲቲው የሚጠበቁትን ኃላፊነቶች በመለየት እና ልዩ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት መረባረብ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በተጨማሪም የአዳዲስ ፕሮጀክቶች ግንባታ ማለትም የስብሰባ አዳራሽ፣ የመማሪያ ክፍል፣ ተጨማሪ የመምህራን መኖሪያ፣ የሰራተኞች መዝናኛ እና የተማሪዎች ማደሪያ በቅርቡ መጀመር እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ሁሉም አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በውይይቱ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ስራ ተቋራጮች እና የአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የዩኒቨርሲቲውን የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ገመገመ።
በግምገማው ዩኒቨርሲቲው ባለው ነባራዊ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆኖ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መቻሉን፣ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለመጨረስ የተወሰዱ እርምጃዎችን እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን ቦርዱ በጥንካሬ የገመገመ ሲሆን በቀጣይ በትኩረት መሠራት ያለባቸውንም ጉዳዮች ለይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ለሥራ እንቅፋት በሆኑ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች እና ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዲሁም ከዋጋ ግሽበት ጋር ያልተገናዘበው የተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ ቦርዱ ውይይት አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ የሱታና ንግድ እና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝም የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀርቦ በቦርዱ ተገምግሟል፡፡
የሥራ አመራር ቦርዱን ስብሰባ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሰቢ የሆኑት ፕሮፌሰር የሺጌታ ገላው መርተውታል፡፡
ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም