LIYU NEWS
10 subscribers
16 photos
1 video
6 files
17 links
Join my channel
ወቅታዊ እና አስገራሚ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል
Download Telegram
አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ሰጥታ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት አንስታለች።

የአሜሪካ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ክርስቲ ኖዬም ለኢትዮጵያ ተሰጥቶ የነበረው የጊዜያዊ ከለላ መብት መነሳቱን አስታውቀዋል።

አሜሪካ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ወደ ሃገራቸው መመለስ ለማይችሉ ዜጎች ጊዜያዊ ከለላ( Temporary protected status) ትሰጥ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያም ይኸው መብት ነበራት።

አሜሪካ ከ1990ዎቹ ጀምሮ በሃገሯ የሚኖሩ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ጦርነትን ጨምሮ በአንዳንድ ምክንያቶች ወደመጡበት ሃገር መመለስ ለማይችሉ ሰዎች ይህንን ከለላ መስጠት ጀምራ ነበር።

ይህ ከለላ የሚሰጣቸው ዜጎችም የሃገራቸው ሁኔታ እስኪሻሻል በአሜሪካ የመኖርና የመስራት መብት ሲሰጣቸው ከአሜሪካ ከመባረር ይጠበቁ ነበር።

አሜሪካ" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ግለሰቦች ደህንነት ላይ ስጋት አይፈጥርም" ያለች ሲሆን በዚህም የተነሳ ይኸው ከለላ መነሳቱን አስታውቃለች።

አሜሪካ ሌሎች በአሜሪካ ለመቆየት ህጋዊ መሰረት ካላቸው ኢትዮጵያውያን ውጪ የኢትዮጵያ ዜጎች በ60 ቀናት ከሃገሯ እንዲወጡ አሳስባለች።

ቀድመው ከአሜሪካ ለሚወጡ የትኬት ወጪያቸው እንደሚሸፈን፣ የ1000 ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥና ለወደፊቱ ህጋዊ የኢሚግሬሽን እድል እንደሚኖራቸው ገልፃለች።

ከፈረንጆቹ የካቲት 13 በኋላ ከለላው እንደሚያበቃ ገልፃ ያለ ከለላው በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደምታስር እና ከሃገሯ እንደምታባርር አስጠንቅቃለች።

አሜሪካ ከሳምንታት በፊት ተመሳሳይ ከለላ የነበራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜጎችን መብትም ማንሳቷ ይታወሳል
Rhetorical Analysis Essay_ an Example of a Web Page Case Study
449.9 KB
Rhetorical Analysis Essay: an Example of a Web Page Case Study
Rhetorical Anal-WPS Office ታህሳስ 6.docx
10.7 KB
Share Rhetorical Anal-WPS Office ታህሳስ 6.docx
Rakhi_Sameer_The_power_of_leadership_storytelling_The_case_of_Mahatma.pdf
186.7 KB
Rakhi-Sameer.-The-power-of-leadership-storytelling.-The-case-of-Mahatma-Gandhi-.pdf
ከ5 ሺህ በላይ የኢትዮጵያ ዜጎች በአዲሱ የአሜሪካ ውሳኔ ተጠቂ ይሆናሉ ተባለ

አሜሪካ ከሰሞኑ ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን ጊዜያዊ የህግ ከለላ ማቋረጧን ተከትሎ 5ሺ ኢትዮጵያውያን የውሳኔው ተጠቂ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

ቀደም ሲል 5001 ኢትዮጵያውያን በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዘመን የህግ ከለላ ተሰጥቷቸው እንደነበርና 263 የሚሆኑ ተጨማሪ ዜጎች አመልክተው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩ ተገልጿል፡፡ 

አሜሪካ በፈረንጆቹ ታህሳስ 12ቀን 2022 በኢትዮጵያ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ለኢትዮጵያ ዜጎች ጊዜያዊ የህግ ከለላ መስጠት መጀመሯ የሚታወስ ሲሆን በሚያዚያ 2024 ዳግም ተራዝሞ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ስደተኛ ጠል ነው የሚባለው የትራምፕ አስተዳደር ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ውሳኔው ለእነዚህ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ከለላ አንስቷል፡፡
የመቂ ከተማ ነዋሪዋ የ10 ሚሊዮን ብር የሎተሪ ዕጣ አሸናፊ ሽልማታቸውን ተረከበች

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ባወጣው የ"ልዩ ዕድል" ሎተሪ የ10 ሚሊዮን ብር ከፍተኛ ዕጣ አሸናፊ የሆኑት የመቂ ከተማ ነዋሪዋ ወ/ሮ ስምረት ኢቲቻ፣ ሽልማታቸውን  በይፋ ተረክበዋል።

ወ/ሮ ስምረት ዕጣው የወጣበትን አጋጣሚ ሲያስታውሱ፣ መስከረም 21 ቀን ከቤተክርስቲያን መልስ ቢሮአቸው ተቀምጠው ሳለ የቆረጡት ትኬት የ10 ሚሊዮን ብር ባለቤት እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። አሸናፊዋ በደስታ ተውጠው በሰጡት አስተያየት "እናቴ እመቤቴ የ10 ሚሊዮን ብር አሸናፊ አድርጋኛለች" በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በበኩሉ፣ ሽልማቱን ለአሸናፊዋ ማስረከቡን ገልጾ፣ መሰል የሎተሪ ዕጣዎች የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ከመቀየር ባለፈ ለሀገር ኢኮኖሚ ያላቸውን ድርሻ ጠቁሟል።Dagu
በ'ፊንቴክ ኢንቨስትመንት' የማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ወሰነ

ሆኖም ችሎቱ ተጠርጣሪዎች ለዋስትና የሚያቀርቡትን የገንዘብ መጠን ለመወሰን ለሰኞ ግንቦት 3/2018 ዓም ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አቃቢ ህግ በበኩሉ አምስተኛ ተከሳሽ ከሆነው መንሱር ጀማል በቀር የዋስትና መብታቸው ቢከበር እንደማይቃወም ለችሎቱ አሳውቋል።

ችሎቱ በበኩሉ አቃቢ ህግ በአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል ዋስትና ጉዳይ ላይ አቃቢ ህግ ያለውን ተቃውሞ በጽሁፍ ለግንቦት ሦስት እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል።
ህወሓት ከሱዳን ጋር አብሮ እየሠራ ነው በሚል በፌዴራል መንግስት የቀረበበትን ክስ አስተባበለ፡፡

ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀጠናውን ለማዳከም ከሱዳን ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው በሚል ያቀረበበትን ክስ በጽኑ አስተባብሏል።

ድርጅቱ፤ ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ “እነዚህን ክሶች ሙሉ ለሙሉ እቃወማለሁ” ብሏል።

ክሶቹን “መሠረተ ቢስ፣ ኃላፊነት የጎደላቸው እና ትኩረትን በሐሰተኛ መረጃ ለማስቀየር የሚደረግ ተደጋጋሚ አካሄድ ማሳያ ናቸው” ሲልም ገልጿቸዋል።
👍1
በህክምና ቁሳቁሶች እጥረት ተራ የሚጠብቁ በርካታ ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና እንዲያገኙ የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ለሶስት የህክምና ተቋማት ተበረከተ

ኢዮብ ተስፋ ለህፃናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ለቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ፣ለጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል 180 ሺህ ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን አበርክቷል ።

በዚህ ወቅት የድርጅቱ መስራች አቶ አበባዉ አንበሣዉ ከደጋፊዎቹ ባገኘው ድጋፍና ትብብር የገዛቸዉን አብረዉት ከሚሰሩ የልብ ሀኪሞች ትብብር ከሜድትሮኒክ ኩባንያ ያገኛቸውን ከ180 ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን አስረክበናል ማለታቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።

ድርጅቱ ለሶስቱ ህክምና ተቋማት ባደረገዉ ድጋፍ በህክምና ቁሳቁሶች እጥረት የተነሳ ተራ የሚጠብቁ በርካታ ህፃናት እና ሌሎች ህሙማን የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የተቋማቱ ሀላፊዎች ተናግረዋል ።

ኢዮብ ተስፋ ለህፃናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት በድንገተኛ የልብ ህመም በ17 ዓመቱ በወጣትነት ዕድሜዉ ህይወቱ ባለፈዉ ኢዮብ አበባዉ አንበሣዉ ስም በወላጆቹና በወዳጅ ዘመድ ትብብር እ.አ.አ በ2021 መጨረሻ በካሊፎርኒያ አሜሪካ የተቋቋመ ድርጅት ነዉ ።
ከ500 ዳቦዎች የተሰራው ቀሚስ ….

ግንቦት 3 2018 ዓ.ም. ምሽት በናይጀሪያ ሌጎስ የተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ማጂክ የተመልካቾች ምርጫ ሽልማት የአፍሪካ ግዙፉ የፊልም እና የፋሽን ምሽት በመባል ይታወቃል።

የአፍሪካ ማጂክ ተመልካቾች ምርጫ ሽልማት (Africa Magic Viewers' Choice Award- AMVCA) የናይጀሪያ ዝነኞችን ጨምሮ ከደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ አፍሪካ አገራት የተወከሉ ስመ ጥር ተዋናዮች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል።

ኤኤምቪሲኤ በአፍሪካ የፊቸር ፊልም፣ የቴሌቪዥን ድራማ እና ዶክመንተሪ ስራዎች የላቀ ጥራት ያላቸው ይዘቶችና የጎላ ስራ ከውነዋል ተብለው በተመልካቾችና በከፍተኛ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተመረጡ ባለሙያዎች የሚሸለሙበት የሽልማት ስነ ስርዓት ነው።

እሁድ ግንቦት 2 2018 ዓ.ም. በናይጄሪያ በተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ፊልሞች አዋርድ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ የፊልም ባለሙያዎች እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ አልባሳት ተውበው ተገኝተዋል።

ከግዙፉ የአፍሪካ የመዝናኛ ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ አማካኝነት በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው በዚህ የፊልም አዋርድ ዝግጅት ላይ የተገኙ ታዋቂ ሰዎች የአህጉሪቱን ባሕል ከማሳየት በዘለለ በአልባሳቶቻቸው ተፎካክረዋል።

በሌጎስ በሚገኘው ኤኮ ሆቴል በተካሄደው ዓመታዊ የአፍሪካ ፊልም፣ ቴሌቪዝን እና ዲጂታል ሥነ ጥበባዊ ስራዎች ሽልማት ምሽቱን ልዩ ውበት ያጎናጸፉት በርካታ አልባሳት መነጋገሪያ ነበሩ።

በዕለቱ ከተገኙት ስመ ጥር ሰዎች ሁሉ ግን የአንዷ ታዋቂ የቴሌቪዥን ተዋናይ አልባሳት የበለጠ መነጋገሪያ ሆና አምሽታለች።
🇪🇹 ኢትዮጵያዊው ገጣሚ በዕወቀቱ ሥዩም በባርሴሎና ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ ሥራዎቹን ሊያቀርብ ነው

በሥነ-ጽሑፍ ሥራዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው ደራሲ እና ገጣሚ በዕወቀቱ ሥዩም ከግንቦት 6 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ በክብር እንግድነት እንዲሳተፍ መመረጡ ተዘግቧል።

📜 በዕወቀቱ ግንቦት 13  በ‘ፓላው ዴ ላ ሙዚካ ካታላና’ አዳራሽ በሚካሄደው የፌስቲቫሉ መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ከመጡ ሰባት ዝነኛ ገጣሚዎች ጋር በመሆን የግጥም ሥራዎቹን ያቀርባል።

📖✍🏼 የኢትዮጵያን ታሪክ ከመረመረበት "ከአሜን ባሻገር" መጽሐፉ ባሻገር፣ "ኗሪ አልባ ጎጆዎች"፣ "በራሪ ቅጠሎች"፣ "የ'ሣት ዳር ሐሳቦች" እና "የማለዳ ድባብ" በሚሉ የግጥም መድብሎቹ የሚታወቀው በዕወቀቱ፤ የሀገረሰባዊ የግጥም ለዛን ከዘመናዊ የፈገግታና የቁም ነገር ስልት ጋር በማዋሃድ የዘመኑ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ተጠቃሽ ባለሙያ ተደርጎ ይወሰዳል።
አስገራሚ የስፖርት ቅጣት

የስላቪያ ፕራግ ደጋፊዎች ለእድሜ ልክ ታገዱ!

የቼክ ሪፐብሊክ ክለብ የሆነው ስላቪያ ፕራግ ደጋፊዎች በደርቢ ጨዋታ ላይ በፈጠሩት ሁከት ምክንያት ከባድ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ቅዳሜ ምሽት በፕራግ ደርቢ ስላቪያ ፕራግ ከ ስፓርታ ፕራግ ጋር ባደረጉት ጨዋታ፣ ስላቪያ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት እየመራ በነበረበት ጨዋታ 97ኛው ደቂቃ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የስላቪያ ፕራግ ደጋፊዎች የሜዳውን አጥር ጥሰው በመግባት በስፓርታ ተጫዋቾች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።

በዚህ ድንገተኛ ጥቃት የስፓርታው ግብ ጠባቂ ያኩብ ሱሮቭቺክን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾች ላይ ድብደባ የተፈጸመ ሲሆን፣ ጨዋታውም ወዲያውኑ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

የክለቡ ዋና ስራ አስፈጻሚ ያሮስላቭ ትቫርዲክ በሰጡት መግለጫ፣ ድርጊቱ "አሳፋሪና የክለቡን እሴት የማይወክል" ነው ብለዋል።

በጨዋታው ቀይ ካርድ የተመለከቱትና የብሄራዊ ቡድን አባላት የሆኑት ቶማስ ቾሪ እና ዴቪድ ዱዴራ እስከ ውድድር ዘመኑ መጨረሻ የታገዱ ሲሆን፤ በሁከቱ የተሳተፉ ደጋፊዎች በዕድሜ ልክ ወደ ስታዲየም እንዳይገቡ ታግደዋል።

የክለቡ አክራሪ ደጋፊዎች መቀመጫ የሆነው የሰሜን መቀመጫም ጊዜ እንዲዘጋ ተወስኗል

የቼክ ሊግ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ስላቪያ ፕራግን ነጥብ የመቀነስን ጨምሮ ሌሎች ውሳኔዎችን ሊወሰንበት እንደሚችል ይጠበቃል።
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሠረት በኦንላይን (Computer-based Testing (CBT) የሚፈተኑ ተፈታኞች በስድስት ዙር የሚፈተኑ ሲሆን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ይፈተናሉ። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የሚፈተኑ ይሆናል።

ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ በሶስተኛ ዙር ላይ የሚፈተኑ ሲሆን የማህበራዊ ሳይንስ በአራተኛ ዙር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚፈተኑ ይሆናል። (ዝርዝሩን ከላይ በምስሉ ይመልከቱት)