Ibnu munewor(ኢብኑ ሙነወር)
27 subscribers
1 link
كناشة ابن منور
Download Telegram
ወደ ሱፍያው ካምፕ ልምጣ። ወደ ሌላ ዓለም መሄድ ሳያስፈልገን እዚሁ በሃገራችን ውስጥ በሱፊያው ክፍል ስንትና ስንት ፅንፈኝነት እየተፈፀመ እያየ አሁን ሰለፍያን በፅንፈኝነት እየከሰሰ ያለው የሱፊያ የሚዲያ ክንፍ ትንፍሽ አይልም። ሰለፍያው ላይ እንደሚዘምቱት ቀርቶ በስሱ እንኳ ሱፍዩን ሲነቅፉ አይታዩም። ለሱፍዮች ያላቸው ጭፍን ውግንና አይናቸውን ሸፍኖታል። እንደ ሐሰን ታጁ ያሉ የሳር ውስጥ eባ^ ቦች እራሳቸውን ለዘብተኛና ተራማጅ፣ "ወ^ ሃቢ" የሚሉትን ክፍል ደግሞ አ ^ ው ሬ አድርገው ሲግቷቸው አይናቸውን ጨፍነው ይግጋቱና አርቲ ቡርቲ ይዘው በሳልና አስተዋይ መስለው ሊተነትኑ ይወጣሉ። ሱፍዮች የሚያራምዱትን ፅንፈኝነት እና የሚፈፅሙትን ጥፋት ግን በስሱ እንኳን ሲነቅፉ አይታዩም።

ለነዚህ አስ ^ መሳይ የሱፊያ ጭፍሮች የማይታዩ ግን በሃገራችን ሱፍዮች የተፈጸሙ ጠርዘኛ አካሄዶች ውስጥ ጥቂቶቹን ልጥቀስ፦

1. አሕ ^ ባሽ ሙስሊሞችን አ K ^ ፍረው ባደባባይ በጅምላ ሸሃዳ ሲያስይዙ እንደነበር ይታወቃል።
2. በመንግስት እየታገዙ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በፖሊስ እያስፈራሩ የጉልበት ጠመቃ ሲያካሂዱ ነበር።
3. መስጂዶችን በጉልበት እየነጠቁ የተቃወማቸውን እያሳሰሩ፣ እያስደበደቡ ነበር።
4. በነሱ ሰበብ ብዙ ሙስሊሞች እንደተገደ ^ሉ፣ እንደታሰሩ፣ እንደተሰደዱ የሚታወቅ ነው።
5. በነሱ ሰበብ ሙስሊም ሴቶችን ታፍሰው ከታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ በሌሊት እርቃናቸውን የተለቀቁበት አለ።

6. "ወሃ ^ ብዮች ያረዱት አይበላም፣ ሚስቶቻቸውም ኒካሕ የላቸውም እያለ ፈትዋ የሚሰጠው፣ "እንደ ወ ^ ሀብያ በዓለም ለሙስሊሞች ጠላት የለም" ፣ "ከነሱ iሁድና ነሷራ ይሻላል" እያለ አዳራሽ ሙሉ የሱፍያ ሸሆች ፊት የሚናገረው የነ ይመር ገራዶ ሽፍታ ቡድን "ፅን ^ፈኛ" ተብሎ በነ ሐሰን ታጁ አይከሰስም። ምክንያቱም እነሱ ራሳቸው የዚህ አካሄድ ደጋፊ ናቸው።
7. እነ ኢብኑ ተይሚያና እነ ኢብኑል ቀይም ሙስሊሞች አይደሉም"፣ "ወ ^ ሃብዮች ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፣ ሙስሊሞች አይደሉም" የሚለው የነ ደ ^ጃል አቡበክርን ፈትዋ "የሱፍዮች ፅንፈኝነት" ብለው ሲያወግዙት አታይም።

8. "ወሃ ^ ብዮች ሙስሊሞች አይደሉም" የሚል መፈክር በደማቁ ፅፎ እያውለበለበ፣ ባንድ ድምፅ እያስተጋባ ጎዳና ላይ ሰልፍ የወጣው የኮምቦልቻው የአሕ ^ ባሽ መን -ጋ በነ ሐሰን ታጁና ቅጥቅጦቻቸው ፅንፈኛ ተብሎ አይወገዝም። ምክንያት? ይህንን የፈፀሙት ሰለፍዮች ስላልሆኑ።
9. በሀምሌ ወር 2004 በራስ ሆቴል ከመላው ኢትዮጵያ የተሰበሰቡ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የሱፍያ ሸሆች "ወ - ሀ ^ ብዮች" የሚሏቸውን ሙስሊሞች ከኢስላም አስወጥተው ያወጁበት ፈትዋ አውጥተዋል። ይሄ ስብስብ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ ከፊሎቹን ልጥቀስ:-

- የትኛውም "ወ - ሃ - ቢ ህዝብ ላይ ተፅእኖ ማሳደር የሚችልበት የትኛውም ኃላፊነት (ኢማምነት፣ የመጅሊስ ኃላፊነት፣ ሙአዚንነት፣ አስተማሪነት፣ ኸጢብነት፣ ... ) ላይ እንዳይቀመጥ፣
- ወጣቶች ወደ "ወ - ሃ - ቢያ" ዩኒቨርስቲዎች እንዳይሄዱ ማድረግ፣
- በ"ወ - ሃ - ቢዮች" በኩል የኡዱሒያ ስጋ፣ እርዳታና ድጋፍ ምንም አይነት ሶደቃ እንዳይከፋፈል ማገድ፣
- በ"ወ - ሃ - ቢዮች" በኩል ምንም አይነት የነፃ የሐጅ ድጋፍ ለማንም እንዳይደረግ ማድረግ፣
- የትኛውም የ"ወ - ሃ - ቢያ" ኪታብ ስርጭት እንዳይኖር እገዳ መጣል፣
- ምንም አይነት መርከዝና ድርጅት እንዳይኖራቸው ማድረግ፣
- "ወ - ሃ - ቢዮችን" ማሳደድ፣ ወዘተ. ዝርዝሩ ረጅም ነው።

ይሄ ሁሉ በነ "ሙፍቲ" ዑመር ገነቴ፣ በነ ይመር ገራዶ፣ በነ ደጃ ^ል አቡበክር ሲፈፀም የነበረ ነው። እራሱ "ሙፍቲ" ዑመር ሸገር ሬድዮ ላይ በተላለፈ ምስክርነት ህወሓትን በመጠቀም ሙስሊሞችን ለማስመታት ሲሰሩ እንደነበር አረጋግጧል። እንዲህ አይነቱን ሰው ቢሳካለት ጄኖሳይድ ይፈጽምብናል ብለው ሲከሱት አይታችኋል? የለም! እንዲያውም ይህንን ሰው ክብሩን አልጠበቃችሁም ብለው ነው የሚያለቃቅሱት። እኔ ልቤ የማያምንበትን በዲፕሎማሲ የተቀባባ ቃል መጠቀም አልፈልግም። ቀጥታ ስናገር እንዲህ አይነቱ ሰው ክብሩን ያረከሰው እራሱ ነው። ጠላትን በሙስሊሞች ላይ የሚቀሰቅስ ሰው የትኛው ክብር ነው ያለው? ሀሰት እንዳትሉ እራሱ አረጋገጠ። ምን ቀራችሁ? አጉል መጋጋጥ ብቻ!)

10. በፅንፈኛ ሱፍዮች ደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ላይ የ"ወሃ ^ ብዮች ነው" ብለው መስጂድ አቃጥለው ሲጨፍሩ ነበር። ወረባቦ ወረዳ ውስጥ እንዲሁ መስጂድ አቃጥለዋል። የነ ሐሰን ታጁ ጭፍራ "ለምን?" አላለም።
11. ሆለታ ላይ ኢማም ተገድሏል። ድብደባና በስለት መውጋት ብዙ ቦታ የተከሰተ ነው።
12. ሐሰን ታጁ በሀሰት ወ - ሃ - ቢዮች የመውሊድ ምግብ ላይ መርዝ ጨመሩ ብሎ ግጭት ለመቀስቀስ ሞክሯል። እሱን ፅንፈኛ ብሎ የፈረጀው ግን የለም።
13. ያያያዝኩት ቪዲዮ ላይ የአንዋር መስጂዱ ኢማም ጦሀ "ወ ^ ሃብዮችን በፖሊስ አስደብድቧቸው!'' እያለ ህዝብ የሚቀሰቅስበት ነው። እንዲህ አይነቱ ዱር ^የ ለጥፋቱ ተጠያቂ አልተደረገም። ሌላው ቀርቶ ፅንፈኛ ብሎ እንኳ የሚከሰው የለም።

14. እነ ሐሰን ታጁ እና መሰሎቻቸው "ኢማም" እያሉ የሚያወድሱት ከውሠሪ ሶሐቦችን ሳይቀር የሚወርፍ፣ እነ ኢማሙ ማሊክን፣ ዐብደላህ ብኑ ኢማም አሕመድን፣ እነ ኢብኑ ኹዘይማን የሚያወግዝ፣ እነ ኢብኑ ተይሚያን፣ ኢብኑል ቀይምን እጅግ ስቅጣጭ በሆኑ ቃላት የሚሳደብ ነው ^ረኛነው።

እነዚህና የነዚህ ደጋፊዎች ናቸው እንግዲህ ሰለፊዮችን በፅንፈኝነት የሚከሱት። "ጅብ ማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ" የሚባለው ለንዲህ አይነቱ አካል ነው። እንዲሁ ሚዛናዊ ለመሆን ሳይሆን ለመምሰል ያህል እንኳ በጠርዘኛ ሱፍዮች እና በጠርዘኛ ኢኽዋንዮች የሚፈፀሙ ነውሮችን ሲነቅፉ አይታዩም። አንድ ማንነቱ በቅጡ የማይታወቅ ሰለፊይ ወጣ ያለ ነገር ቢናገር ግን ለማጠልሸት ስለሚፈልጉት በደስታ ነው የሚቦርቁት። የድፍን ሰለፊዮች አቋም አድርገው ሲቀባበሉት ይሰነብታሉ። ባለፈው አንዷን ዶክትሬቷን በዘመቻ እናስነጥቃታለን አሉ እያሉ ሲሳላቁ ነበር ። እንዲሁ ወሬ ከማድመቅ ውጭ ማነው ይህን ያለው ተብለው ቢጠየቁ የረባ ሰው አይጠቅሱም። የገለባ ክምር! አብዛኞቹ የቁርአንና የሐዲስ ማስረጃ ጠቅሰው መናገር ስለማይችሉ እንዲህ አይነት የከረፋ የወያላ አካሄድ የሚሄዱ ቁማ ^ርተኞች ናቸው።

የቀረኝ አለ፣ እመለሳለሁ ኢንሻአላህ
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 27/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ሀይ ሰለም