🌸قناة أخوات أهل السنة السلفيات🌸
5.49K subscribers
542 photos
159 videos
13 files
907 links
🌸 አስሰላሙ ዐለይኩን ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ
እንኳን ወደ የአህሉ ሱና ሰለፊያ እህቶች ቻናል በደህና መጡ
ይህ ቻናል በቁርአን እና በትክክለኛው ሱና መሠረት የሚጠቅም ዒልምን ለመማር እና ለማስተላለፍ የተከፈተ ነው
🌿 ተውሒድ መሠረታችን
🌿 ቁርአን መሪያችን
🌿 ሱና መንገዳችን
🌿 ሰለፍ አርአያችን
🌿 ዒልም ሀብታችን
Download Telegram
فضل العلم وآداب طلبه ١
للشيخ طه خضر حفظه الله
ኮርስ

بعنوان:- فضل العلم وآداب طلبه.
የእውቀት ደረጃና የመፈለጉ ስርኣት

⏯ ክፍል ①

🎙በሸይኽ አቡ ዐብደሏህ ጧሀ ቢን ኸድር (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተሰጠ ኮርስ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
فضل العلم وآداب طلبه ٢
للشيخ طه خضر حفظه الله
ኮርስ

بعنوان:- فضل العلم وآداب طلبه.
የእውቀት ደረጃና የመፈለጉ ስርኣት

⏯ ክፍል ②

🎙በሸይኽ አቡ ዐብደሏህ ጧሀ ቢን ኸድር (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተሰጠ ኮርስ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
فضل العلم وآداب طلبه ٣
للشيخ طه خضر حفظه الله
ኮርስ

بعنوان:- فضل العلم وآداب طلبه.
የእውቀት ደረጃና የመፈለጉ ስርኣት

⏯ ክፍል ③

🎙በሸይኽ አቡ ዐብደሏህ ጧሀ ቢን ኸድር (ሀፊዘሁላህ)

በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተሰጠ ኮርስ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444
አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች 1
በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ)
አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች 2
በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች 3
በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች 4
በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
አምሳ ምክሮች ለዲን ተማሪዎች 5
በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
የብቸኛው ቤቴ ..ዋ ነብሴ ፈረውልሽ ተመለሺ
"ኩልሉ ነፍሲን ዛኢቃቱል ማውት..." የጌታዬ ቃል እውነት ነው፣
የዱንያ መሸሻዋ፣ የመጨረሻዋ መስመር
ቀብር ነው።
ያማረው ሳሎኔ፣ የደመቀው ስሜ ዛሬ አበቃለት፣
የብቸኛው ቤቴ... የጨለማው ጉድጓድ ተቆፈረለት።
አፈር ነው ትራሴ፣ የለመድኩት ኑሮ ዛሬ ተቀየረ፣
ማልቀሻው መቃብር፣ በባዶነቴ ላይ በሩ ተዘጋገ።
አህባብና ዘመድ፣ ጀናዛዬን ሰግደው ጥለውኝ ሲመለሱ፣
የጫማቸው ኮቴ እየራቀ ሲሄድ... ነፍሴ ሆይ ምን ይዋጥሽ?
የሙንከርና ነኪር ጥያቄ ሲመጣ፣ ምን ይሆን ምላሽሽ?
ነፍሴ ሆይ... ተመለሺ! ተውባ አድርጊና አልቅሺ፣
"ያ አዩሃል ለዚነ አመኑ ቱቡ ኢለላህ..." የሚለውን የጌታሽን ጥሪ ስሚ።
ከዝንጋታ (ጋፍላ) ውጪ፣ ከአኺራሽ መንገድ አትሽሺ፣
የሩቅ ጉዞ አለብሽ፣ በፈርዶችሽ ላይ ንቂ።
ያ ብቸኛው ቤትሽ፣ ያ ጠባቡ ቀብርሽ፣
በቂ ያደረግሽው፣ ወንጀል እንዳይሆን ጨለማሽ።
የሌሊት ቂያምሽ፣ የቁርዓን ብርሃንሽ፣
ከአላህ እዝነት ጋር፣ እሱ ነው ነገ የሚጠቅምሽ።
ያ አላህ... ያ ረህማን... ያ ረሂም!
በዚያች የብቸኝነት ቤት፣ ቀብራችንን ኑር (ብርሃን) አድርግልን፣
ሁስነል ኻቲማን (ያማረ መጨረሻን) ለሁላችንም ስጠን።
ያረብ
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
ቁጥብ ሴት ከዋጋ ቢስ ወሬዎች እና ሀሜት የራቀች ናት። አንደበታችን የኢማናችን ማሳያ ነው። በአጅነቢይ ፊት ድምፅሽን ከመለስለስ ተቆጠቢ፤ ምላስሽ ግን ሁልጊዜ በአላህ ዚክር እና በኢስቲግፋር የረጠበ ይሁን። በዱንያ ላይ የምንናገረው እያንዳንዱ ቃል ነገ አኼራ ላይ ይመዘገባል

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
ጊዜን (ዘመንን) መሳደብ ⏱️

የእለት ተእለት የጋፍላ (የዝንጋታ) ንግግሮቻችን እና አደገኝነታቸው

ብዙዎቻችን ነገር ሲበላሽብን "ክፉ ዘመን!"፣ "የተረገመ ቀን!"፣ "ይህ ኑሮ ያመጣብኝ መዓት!" ወይም "እድለ ቢስ ቀን!" እያልን ቀናትንና ጊዜን እንረግማለን ወይም እንሰድባለን። ይህ በእስልምና በጥብቅ የተከለከለ (ሀራም) ነው።

ለምን ተከለከለ?
ጊዜ፣ ቀንና ሌሊት ምንም ዓይነት የራሳቸው ኃይል የላቸውም። ጊዜን የሚቀያይረው፣ በውስጡ የሚሆነውን በጎም ሆነ መጥፎ ነገር የሚወስነው አላህ (ሱ.ወ) ብቻ ነው። ስለዚህ ጊዜን መሳደብ ፈጣሪን እንደ መሳደብ ይቆጠራል!

ሀዲሰል ቁድሲ ላይ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦

"የአዳም ልጅ (ሰው) ዘመንን በመሳደብ ያስቀይመኛል፤ እኔ ዘመን (ጊዜን ፈጣሪ) ነኝና! ሌሊቱንና ቀኑን እኔው ነኝ የምገለባብጠው።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ትክክለኛው መንገድ፦ መጥፎ ነገር በገጠመን ጊዜ "አልሃምዱሊላህ ዓላ ኩሊ ሃል" (በማንኛውም ሁኔታ ላይ ምስጋና ለአላህ ይሁን) ወይም "ቀደረላሁ ወማሻአ ፈዐለ" (አላህ የሻውን ወሰነ፣ የሻውንም ሰራ) ማለት እንጂ ቀናትን መርገም የለብንም።

2. አላህንና ፍጡርን ማስተካከል

በዕለት ተእለት ሕይወታችን ውስጥ "በመጀመሪያ በአላህ፣ ቀጥሎ በአንተ" ማለት ሲገባን፣ አላህንና ሰውን በእኩልነት ደረጃ የምናስቀምጥባቸው ንግግሮች ወደ ትንሹ ሽርክ ይመሩናል።

"አላህና አንተ ካልረዳኸኝ አይሆንም" ❌ (ይህ ስህተት ነው! "እና" የሚለው ቃል ሁለቱን እኩል ያደርጋል።)

ትክክለኛው አባባል፦ "በመጀመሪያ በአላህ፣ በመቀጠል (ከዚያም) በአንተ እርዳታ" ✅ ተብሎ መነገር አለበት።

"አላህና አንተ ታውቃላችሁ" ❌ (ይህም ስህተት ነው!)

ትክክለኛው አባባል፦ "አላህ ያውቃል፣ ከዚያም አንተ ታውቃለህ" ✅

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
🌹 የነፍስ ጥሪ ለውዷ እህቴ!ውዷ እህቴ ሆይ! ቆም ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? አንቺ የዚህች ኡመት ትልቅ ምሰሶ ነሽ። ያንቺ መስተካከል የትውልድ መስተካከል ነው፤ ያንቺ መበላሸት ደግሞ የኡመቱ መዳከም ነው።እስኪ ወደ ኋላ ተመልሰን የታላላቅ ሴቶችን ታሪክ እንቃኝ፡እናትችን ኸዲጃ (ረ.ዐ)፦ ነቢዩ (ﷺ) በጭንቅ ሰዓት የተጠጉባት፣ በሃብቷና በምክሯ ዲኑን የደገፈች የጥንካሬና የጥበብ ተምሳሌት ነበረች።እናትችን ዓኢሻ (ረ.ዐ)፦ የኡመቱ መምህር፣ የዕውቀት ባህርና ለነቢዩ (ﷺ) ልዩ የልብ አጋር ነበሩ።ፋጢማ (ረ.ዐ)፦ የፅናት፣ የትዕግስትና የሀያዕ (የእፍረት) ተምሳሌት ነበረች። ከሀያዕዋ መላቅ የተነሳ “እኔ ከሞትኩ በኋላ አስከሬኔ በጨርቅ ተሸፍኖ እንኳ የሰውነቴ ቅርፅ ለወንዶች እንዳይታይ” ብላ የተጨነቀች የሀያዕ ንግስት ነበረች።የእኛስ ሀያዕ ዛሬ የት አለ?እህቴ ሆይ! ዛሬ አለም በዘመናዊነት ስም ውበትሽን ለባዕድ ወንዶች እንድታሳይ፣ ክብርሽን በይፋዊ መድረኮች (ሶሻል ሚዲያ) ላይ እንድትዘረግፊ ትገፋፋሻለች። ነገር ግን እውነተኛው ክብርሽና ጌጥሽ አላህን መፍራት (ተቅዋ) እና ሀያዕሽ ነው። ሂጃብሽ ፋሽን ሳይሆን የአላህ ትዕዛዝ እና የውስጥሽን ንፅህና መጠበቂያ ጋሻሽ ነው።ለመመሳሰል ምን እናድርግ?ልብሽን በአላህ ፍቅር ሙይው፦ ሶላትሽን በወቅቱ ስገጂ፣ ቁርኣንን አዘውትረሽ ቅሪ። ልብ በአላህ ዚክር ሲረጥብ ወንጀልን ይጸየፋል።ሀያዕሽን ጠብቂ፦ በአነጋገርሽ፣ በአለባበስሽና በባህሪሽ የነ ፋጢማን ፈለግ ተከተይ። አይንሽን ካልተፈቀደ እይታ፣ ምላስሽን ከሃሜት ጠብቂ።ክብርሽን በሶሻል ሚዲያ አትቀይሪ፦ ላይክና ፎሎወር ለማግኘት ብለሽ ለአላህ ያለሽን ታዛዥነት አታርክሺ። ድብቅነቱ ያማረባት ዕንቁ ሁኚ።እህቴ ሆይ! እኛ እነሱን ሙሉ በሙሉ መሆን ባንችልም፣ ወደ እነሱ ለመጠጋትና እነሱን ለመምሰል የምናደርገው እያንዳንዱ ጥረት በአላህ ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው። ገጣሚው እንዳለው፦"ከመልካም ሰዎች ጋር ተመሳሰሉ፤ እነሱን መሆን ባትችሉም እንኳ! መልካም ሰዎችን መምሰል ራሱ ትልቅ ስኬት ነውና።"

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
ኢብኑ ተይሚያ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"እውነተኛው ምስኪን (ደሃ) ማለት ገንዘብ የሌለው ሰው አይደለም። እውነተኛው ምስኪን ማለት በዚህች ዱንያ ላይ እየኖረ የአላህን ማውሳት (ዚክር) ሳይቀምስና ሳይደሰትባት የሞተ ሰው ነው።"

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✨️ ነጻ የሰለፊዮች ቻናል ግብዣ ✨️

🔴ይህን ቀላል 🤏 ጥያቄ ለመለሰ ነጻ የሰለፊዮች ቻናል ግብዣ አለው ⚡️
♻️ አላህ {سبحانه وتعالى } ስራችንን ሊያሳምርልን እና ወንጀላላችንን ሊምርልን ዘንድ ከኛ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል⁉️
🔹️______________________________🔹️

📎 ምንጭ :- ከላይ ካለው ቪዲዮ 👆
Forwarded from đšÄ•đš đš‘đšŽđšŽđš & ŝūññã𝚑
👍👍👍👍👍👍👍👍

🔴አስደሳች ሰበር ዜና🔴

✔️በታላቅ ጉጉት በሚጠበቀው ዓለም አቀፍ የዳእዋ ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡ
▫️አሊሞች
▫️መሻኢኾች
▫️ኡስታዞችና
▫️ዳኢዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ‼️

📹🎥በኦንላይን የሚተላለፈው የዚህ ብርቅዬ ፕሮግራም እንቁ ተሳታፊዎች ⬇️

❶ የተከበሩ ሸይኽ ዶክተር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ጉፈይሊ... ከሪያድ/ሳውዲ

❷ ሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን .... ከባህር ዳር

❸ ሸይኽ አብዱልሀሚድ... ከስልጤ/ለተሞ

❹ ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ሙሐመድ … ከአዲስ አበባ

❺ ሸይኽ ጡሃ ኸድር.... ከአዲስ አበባ

❻ ሸይኽ ሙሀመድ ጀማል.... ከኮምቦልቻ

❼ ሸይኽ  አቡዘር ሐሰን... ከኮምቦልቻ

❽ áˆ¸á‹­áŠ˝ ሙሀመድ ሀያት... ከሀራ

❾ ሸይኽ ሁሴን ከረም... ከሀራ

❿ ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ.... ከባህር ዳር

➀➀ሸይኽ መህቡብ... ከወራቤ

⓵⓶ ሸይኽ  ሰይፋሏህ… ከምስራቅ ስልጤ

⓵⓷ ሸይኽ ሙባረክ... ከወልቂጤ

⓵⓸ ሸይኽ አህመድ... ወረታ/ከአዲስ አበባ

⓵⓹ ሸይኽ ሙሀመድ ሲራጅ… ከሀሮ

⓵⓺ ኡስታዝ ሙሀመድ ኢብራሂም... ከመዲና

⓵⓻ ኡስታዝ ሰልማን... ከመዲና

⓵⓼ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን.... ከአዲስ አበባ

⓵⓽ ኡስታዝ አብዱልቃድር ሐሰን...  ከአዳማ

⓶⓪ ኡስታዝ  ሙሀመድ እባቡ... ከቻግኒ

⓶⓵ ወንድም አቡ ሷሊህ አል ኡስይሚን ኢልያስ… ከኩዌት

🎙የፕሮግራሙ መሪዎች ⬇


1️⃣ áŠĄáˆľá‰łá‹ ባህሩ ተካ.... ከአዲስ አበባ

2️⃣ኡስታዝ አብዱረህማን ሰኢድ....  ከመርሳ

3️⃣  ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን... ከደሴ

4️⃣  ኡስታዝ አቡበክር ዩሱፍ … ከባህር ዳር

5️⃣  ኡስታዝ ሪድዋን ዳውድ… ከባህር ዳር

[ሁሉንም አሏህ ይጠብቃቸው]

📌ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት:-

🗓 ቀን - መስከረም 16

🕑 ሰአት - ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ መገባደጃ

💎የሚተላለፍባቸው ቻናሎች:-

📱Telegram
https://t.me/bilalmesji
Imo

💬https://s.imoim.net/RKt0rh?from=copy_link

▫️▫️▫️🎀🎀▫️▫️▫️
〰ሰለፍይነት ያብባል
ተውሂድ ይነግሳል
〰
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
✨ የልብ ብርሃን — ሸሪዓዊ እውቀት! ✨ውድ ወንድምና እህቶቼ... አላህ (ሱ.ወ) መጀመሪያ ያወረደው የቁርአን አንቀፅ "አንብብ" (إِقْرَأْ) የሚል ነበር። ይህ የሚያሳየው ዲናችን ለእውቀት የሰጠውን ትልቅ ቦታ ነው።"እንደ ጅህልና ጠላት የለም!" ወላሂ ይህ ትልቅ እውነት ነው። በዲኑ ጃሂል (አላዋቂ) የሆነ ሰው ዒባዳው የተስተካከለ አይሆንም፣ በትንሽ ሹብሃ (ብዥታ) መስመሩን ይስታል።ስለዚህ ወንድሜ... እህቴ... እራሳችሁን በሸሪዓዊ እውቀት ወጉት!ቁርአንን በተጅዊድና በተፍሲር ለመቅራት ጊዜ ስጡ።የነብዩን (ﷺ) ሀዲስና ፊቅህን ተማሩ።አቂዳችሁን (እምነታችሁን) አስተካክሉ።ዱንያም በአኺራም ስኬታማ የሚሆነው በእውቀት የተገነባ ትውልድ ብቻ ነው። በየቀኑ አዲስ የዲን እውቀት

ለመጨመር እንጣጣር።🤲 "ረቢ ዚድኒ ዒልማ" (ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ጨምርልኝ) በሉ!

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
Forwarded from áŒŒá‰łá‹Ź ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!
🌊✨ ጥያቄ ! ✨🌊

📖❓ በሸሪዓችን «ቢድዓቱል ሐሰና» (ጥሩ ቢድዓ) የሚባል ነገር አለንዴ?

👇 ትክክለኛውን መልስ በመንካት የሚመጣላችሁን የሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ! 📲🌊
ሙብተዲዓዎች ላይ አትማሩሩ !!
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ
🚫 «ሙብተዲዓዎች ላይ አትማሩ❗️»

— ለ ነሕው
— ለ ሶርፍ
— ለ ፊቅህ
— ለ ሙስጦለሓል ሐዲስ ብለህ

➡️ እኔ ቀሪአ ማለት(መለመን) አይመቸኝም እነሱ ጋር ደግሞ ሩዝ አለ እያልክ አትጃጃል !

🔹በትርፍ ጊዜህ ጫማ እየጠረክ ሆድህን
አስረህ በሱና ዑለማዎች ተማር !!!

🎙️ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ -ሐፊዞሁ'ሏህ-

↗️ከአጅዊበቱል ሙፊደህ ደርስ ቁጥር 𝟓𝟓 የተወሰደ

⌚ 26:08 ደቂቃ ብቻ !

*በደንብ ይደመጥ !!

✅|| የቴሌግራም ቻናል➡️፦ t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ - قناة الشيخ أبي ذر بن حسن الولوي
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ – ሙብተዲዓዎች ላይ አትማሩሩ !!
ውድ እህቴ ሆይ! ዲንሽ የጀነትሽሸ መግቢያ ወይም የእሳትሽ መግቢያ ነው፤ ስለዚህ እውቀትሽን ከማን እንደምትሰሚ አጥብቀሽ ተጠንቀቂ!ሰለፎች እንዲህ ይላሉ፦«ይህ እውቀት ዲን ነው፤ ስለዚህ ዲናችሁን ከማን እንደምትቀበሉ ተመልከቱ።»ቢድዓ መርዛማ ናት፦ «እኔ እውነትና ውሸትን እለያለሁ» በሚል በራስ መተማመን የሙብተዲዓዎችን (የመንገድ ጠማሞችን) ድምፅ፣ ቪዲዮ ወይም ጹሑፍ በፍጹም እንዳትሰሚ/እንዳታነቢ። ልብ ደካማ ናት፤ ጥርጣሬ (ሹብሃ) አንዴ ልብሽ ውስጥ ከገባች ዲንሽን ያጠፋዋል።የአላህን ቁጣ ፍሪ፦ ዲንሽን የተሳሳተ ዓቂዳ (እምነት) ካላቸው ሰዎች መማር ማለት እራስሽን ወደ ጥፋት መገፍተር ማለት ነው።በሱና ላይ ቁሚ፦ እውቀትን ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች (በቀደምት ሶሐባዎች) ግንዛቤ ላይ ጸንተው ከሚያስተምሩ የሱና ዑለማዎችና መሻይኾች ብቻ ያዢ።እህቴ ሆይ! በዲንሽ ላይ በፍጹም አትደራደሪ! ከሙብተዲዓዎችና ከሰርጦቻቸው (ቻናሎቻቸው) ራስሽን ሙሉ በሙሉ አርቂ!

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
ፈጋግ እያለቹ ቁም ነገሩን አንሱ
📌 ኢማም አቡ ሐኒፋ እና ሌባው (የዲን ምክር)ታሪኩ፦ ታዋቂው ሊቅ ኢማም አቡ ሐኒፋ (ረሒመሁላህ) በጣም ሀብታምና ቸር ነበሩ። አንድ ቀን ሌሊት አንድ ሌባ በድብቅ ወደ ቤታቸው ይገባል። ቤት ውስጥ ያሉትን ዕቃዎች በሙሉ እየፈለገ ሲያይ ግን ምንም የሚሰረቅ ጠቃሚ እቃ አላገኘም። (ምክንያቱም ኢማሙ ሀብታቸውን በሙሉ ለድሆችና ለተማሪዎች ይመጸውቱ ነበር)።የኢማሙ መነቃት፦ ሌባው ዕቃ ሲያገላብጥ ኢማም አቡ ሐኒፋ ነቁ። ሌባው ባዶ እጁን አዝኖ ሊወጣ ሲል ጮክ ብለው ጠሩትና፦ «ወንድሜ ሆይ! በሩን ዘግተህ ውጣ፤ ግን ከመሄድህ በፊት አንድ ነገር ልንገርህ» አሉት።የተደረገው ስምምነት፦ ሌባው ደንግጦ ቆመ። ኢማሙም እንዲህ አሉት፦ «አንተ የመጣኸው የዱንያን ነገር ፈልገህ ነው፣ ግን አላገኘህም። ታዲያ ባዶ እጅህን ከመመለስ ይልቅ የአኼራን ሀብት (አጅር) ይዘህ አትሄድም?» አሉት። ሌባውም ገርሞት፦ «እንዴት አድርጌ?» አላቸው። «እስቲ እዚህ ውሃ አለህ፣ ውዱእ አድርግና ሁለት ረከዓ ሶላት ስገድ» አሉት።የሌባው መለወጥ፦ ሌባውም በኢማሙ ደግነት ተገርሞ ውዱእ አድርጎ መስገድ ጀመረ። ሶላቱን ሲሰግድ ግን ልቡ ተነካና ማልቀስ ጀመረ። ጎህ እስኪቀድ ድረስ ሌሊቱን ሙሉ ሶላት ሲሰግድ አደረ።ማለዳ ላይ የሆነው፦ ጠዋት ላይ የኢማሙ ተማሪዎች ትምህርት ለመማር ወደ ቤታቸው መጡ። ይሄንን ሌሊቱን ሙሉ ሲያለቅስ ያደረውን ሰውዬ አዩትና፦ «ያ ኢማም! ይህ ሰውዬ ማን ነው?» ብለው ጠየቋቸው።የኢማሙ አስቂኝና ጥልቅ ምላሽ፦ ኢማም አቡ ሐኒፋ ፈገግ አሉና እንዲህ አሏቸው፦ «ይህ ሰውዬማ ትናንት ማታ እኛን ሊሰርቀን የመጣ 'ሌባ' ነበር፤ እኛ ግን ልቡን ሰረቅንበትና ለአላህ ታዛዥ አደረግነው!» አሏቸው። ሰውየውም ከዚያ ቀን ጀምሮ ስርቆትን ትቶ የኢማሙ ምርጥ ተማሪና ደግ

ሙስሊም ሆነ።💡 ከታሪኩ የምንማረው (ጠቃሚ ምክር)፦1 ጥበብ የተሞላበት ዳዕዋ፦ ሰዎችን ከስህተታቸው ለመመለስ ኃይልና ጩኸት ሳይሆን፣ እንደ ሰለፎች በጥበብ፣ በለስላሳ አንደበትና በጥሩ ሥነ-ምግባር መቅረብ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ያሳያል።
2 ክፋትን
በበጎነት መመለስ፦ የበደለንን ወይም ሊጎዳን የመጣን ሰው በጥሩ ነገር መመለስ ልቡን እንደሚያረክሰው ያስተምረናል

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
القارئ عبدالعزيز العسيري | وكل إنسان ألزمناه طائره في عنقه
💭🌸خدمة تلاوات🎧
✅ የቁርዓን ግብዧ ⤵️

📖 { وَكُلَّ إِنسَانٍ أَلْزَمْنَاهُ طَائِرَهُ فِي عُنُقِهِ ۖ وَنُخْرِجُ لَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ كِتَابًا يَلْقَاهُ مَنشُورًا }

🎙️ القارئ عبدالعزيز العسيري