🌸قناة أخوات أهل السنة السلفيات🌸
5.49K subscribers
542 photos
159 videos
13 files
906 links
🌸 አስሰላሙ ዐለይኩን ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ
እንኳን ወደ የአህሉ ሱና ሰለፊያ እህቶች ቻናል በደህና መጡ
ይህ ቻናል በቁርአን እና በትክክለኛው ሱና መሠረት የሚጠቅም ዒልምን ለመማር እና ለማስተላለፍ የተከፈተ ነው
🌿 ተውሒድ መሠረታችን
🌿 ቁርአን መሪያችን
🌿 ሱና መንገዳችን
🌿 ሰለፍ አርአያችን
🌿 ዒልም ሀብታችን
Download Telegram
ሙብተዲዓዎች ላይ አትማሩሩ !!
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ
🚫 «ሙብተዲዓዎች ላይ አትማሩ❗️»

— ለ ነሕው
— ለ ሶርፍ
— ለ ፊቅህ
— ለ ሙስጦለሓል ሐዲስ ብለህ

➡️ እኔ ቀሪአ ማለት(መለመን) አይመቸኝም እነሱ ጋር ደግሞ ሩዝ አለ እያልክ አትጃጃል !

🔹በትርፍ ጊዜህ ጫማ እየጠረክ ሆድህን
አስረህ በሱና ዑለማዎች ተማር !!!

🎙️ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ -ሐፊዞሁ'ሏህ-

↗️ከአጅዊበቱል ሙፊደህ ደርስ ቁጥር 𝟓𝟓 የተወሰደ

⌚ 26:08 ደቂቃ ብቻ !

*በደንብ ይደመጥ !!

✅|| የቴሌግራም ቻናል➡️፦ t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ - قناة الشيخ أبي ذر بن حسن الولوي
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ – ሙብተዲዓዎች ላይ አትማሩሩ !!
ውድ እህቴ ሆይ! ዲንሽ የጀነትሽሸ መግቢያ ወይም የእሳትሽ መግቢያ ነው፤ ስለዚህ እውቀትሽን ከማን እንደምትሰሚ አጥብቀሽ ተጠንቀቂ!ሰለፎች እንዲህ ይላሉ፦«ይህ እውቀት ዲን ነው፤ ስለዚህ ዲናችሁን ከማን እንደምትቀበሉ ተመልከቱ።»ቢድዓ መርዛማ ናት፦ «እኔ እውነትና ውሸትን እለያለሁ» በሚል በራስ መተማመን የሙብተዲዓዎችን (የመንገድ ጠማሞችን) ድምፅ፣ ቪዲዮ ወይም ጹሑፍ በፍጹም እንዳትሰሚ/እንዳታነቢ። ልብ ደካማ ናት፤ ጥርጣሬ (ሹብሃ) አንዴ ልብሽ ውስጥ ከገባች ዲንሽን ያጠፋዋል።የአላህን ቁጣ ፍሪ፦ ዲንሽን የተሳሳተ ዓቂዳ (እምነት) ካላቸው ሰዎች መማር ማለት እራስሽን ወደ ጥፋት መገፍተር ማለት ነው።በሱና ላይ ቁሚ፦ እውቀትን ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች (በቀደምት ሶሐባዎች) ግንዛቤ ላይ ጸንተው ከሚያስተምሩ የሱና ዑለማዎችና መሻይኾች ብቻ ያዢ።እህቴ ሆይ! በዲንሽ ላይ በፍጹም አትደራደሪ! ከሙብተዲዓዎችና ከሰርጦቻቸው (ቻናሎቻቸው) ራስሽን ሙሉ በሙሉ አርቂ!

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
ፈጋግ እያለቹ ቁም ነገሩን አንሱ
📌 ኢማም አቡ ሐኒፋ እና ሌባው (የዲን ምክር)ታሪኩ፦ ታዋቂው ሊቅ ኢማም አቡ ሐኒፋ (ረሒመሁላህ) በጣም ሀብታምና ቸር ነበሩ። አንድ ቀን ሌሊት አንድ ሌባ በድብቅ ወደ ቤታቸው ይገባል። ቤት ውስጥ ያሉትን ዕቃዎች በሙሉ እየፈለገ ሲያይ ግን ምንም የሚሰረቅ ጠቃሚ እቃ አላገኘም። (ምክንያቱም ኢማሙ ሀብታቸውን በሙሉ ለድሆችና ለተማሪዎች ይመጸውቱ ነበር)።የኢማሙ መነቃት፦ ሌባው ዕቃ ሲያገላብጥ ኢማም አቡ ሐኒፋ ነቁ። ሌባው ባዶ እጁን አዝኖ ሊወጣ ሲል ጮክ ብለው ጠሩትና፦ «ወንድሜ ሆይ! በሩን ዘግተህ ውጣ፤ ግን ከመሄድህ በፊት አንድ ነገር ልንገርህ» አሉት።የተደረገው ስምምነት፦ ሌባው ደንግጦ ቆመ። ኢማሙም እንዲህ አሉት፦ «አንተ የመጣኸው የዱንያን ነገር ፈልገህ ነው፣ ግን አላገኘህም። ታዲያ ባዶ እጅህን ከመመለስ ይልቅ የአኼራን ሀብት (አጅር) ይዘህ አትሄድም?» አሉት። ሌባውም ገርሞት፦ «እንዴት አድርጌ?» አላቸው። «እስቲ እዚህ ውሃ አለህ፣ ውዱእ አድርግና ሁለት ረከዓ ሶላት ስገድ» አሉት።የሌባው መለወጥ፦ ሌባውም በኢማሙ ደግነት ተገርሞ ውዱእ አድርጎ መስገድ ጀመረ። ሶላቱን ሲሰግድ ግን ልቡ ተነካና ማልቀስ ጀመረ። ጎህ እስኪቀድ ድረስ ሌሊቱን ሙሉ ሶላት ሲሰግድ አደረ።ማለዳ ላይ የሆነው፦ ጠዋት ላይ የኢማሙ ተማሪዎች ትምህርት ለመማር ወደ ቤታቸው መጡ። ይሄንን ሌሊቱን ሙሉ ሲያለቅስ ያደረውን ሰውዬ አዩትና፦ «ያ ኢማም! ይህ ሰውዬ ማን ነው?» ብለው ጠየቋቸው።የኢማሙ አስቂኝና ጥልቅ ምላሽ፦ ኢማም አቡ ሐኒፋ ፈገግ አሉና እንዲህ አሏቸው፦ «ይህ ሰውዬማ ትናንት ማታ እኛን ሊሰርቀን የመጣ 'ሌባ' ነበር፤ እኛ ግን ልቡን ሰረቅንበትና ለአላህ ታዛዥ አደረግነው!» አሏቸው። ሰውየውም ከዚያ ቀን ጀምሮ ስርቆትን ትቶ የኢማሙ ምርጥ ተማሪና ደግ

ሙስሊም ሆነ።💡 ከታሪኩ የምንማረው (ጠቃሚ ምክር)፦1 ጥበብ የተሞላበት ዳዕዋ፦ ሰዎችን ከስህተታቸው ለመመለስ ኃይልና ጩኸት ሳይሆን፣ እንደ ሰለፎች በጥበብ፣ በለስላሳ አንደበትና በጥሩ ሥነ-ምግባር መቅረብ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ያሳያል።
2 ክፋትን
በበጎነት መመለስ፦ የበደለንን ወይም ሊጎዳን የመጣን ሰው በጥሩ ነገር መመለስ ልቡን እንደሚያረክሰው ያስተምረናል

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
القارئ عبدالعزيز العسيري | وكل إنسان ألزمناه طائره في عنقه
💭🌸خدمة تلاوات🎧
✅ የቁርዓን ግብዧ ⤵️

📖 { وَكُلَّ إِنسَانٍ أَلْزَمْنَاهُ طَائِرَهُ فِي عُنُقِهِ ۖ وَنُخْرِجُ لَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ كِتَابًا يَلْقَاهُ مَنشُورًا }

🎙️ القارئ عبدالعزيز العسيري
ውድና የተከበርሽ እህቴ ሆይ... አላህ (ሱ.ወ) የሰጠሽን ውድ የህይወት

እድሜ በከንቱ አታባክኚው። ሴት ልጅ

በቤቷ ውስጥ ብዙ ስራዎችን

ስለምታከናውን "ለዲኔ ጊዜ የለኝም" ልትል ትችላለች። ነገር ግን ጎበዝ ሙስሊም ሴት ጊዜዋን በአግባቡ ትጠቀማለች!ምስጢሩ በጣም ቀላል ነው፦

1/ 🌸እጆሽ በስራ ላይ ሲሆኑ፦ ቤት ስታጸጂ፣ ምግብ ስታዘጋጂ ወይም ልጆችን ስትንከባከቢ ጆሮሽ የዲን እውቀት ይቅሰም。 ጠቃሚ ደርሶችንና የዑለማዎችን ሙሀደራዎች በስልኮሽ ከፍተሽ አዳምጪ።

2 /🌸ምላስሽ በዚክር ይውለብለብ፦ "ሱብሃነላህ፣ አልሀምዱሊላህ፣ ላኢላሀ ኢልለላህ፣ አላሁ አክበር" እያልሽ ምላስሽን በዚክር አርጥቢው። የልብ እረፍት ታገኛለሽ።በዚህ መልኩ በአንድ ጊዜ ሁለት ታላላቅ ተግባራትን ትፈጽሚያለሽ፦ የቤት ስራሽንም ትጨርሻለሽ፣ ለአኺራሽም ከፍተኛ

አጅር ታፍሻለሽ።እህቴ ሆይ! ጊዜሽን በፌስቡክና በቲክቶክ ላይ በከንቱ አታስልፊ። ስራሽን ወደ ዒባዳ ቀይሪው!

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
የጁሙዐ ኹጥባ
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ
♦️| ወሳኝ የጁሙዐ ኹጥባ !

« ተውሒድ እና ሺርክ »

🎙️ ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ    - ሐፊዞሁ'ሏህ -

🕌 በ ኮምቦልቻ ከተማ ሰላም መስጂድ

🗓 መስከረም /𝟏𝟓 / 𝟐𝟎𝟏𝟗
                                 
|| የቴሌግራም ቻናል፦https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የወጣቶች ሚና
ኡስታዝ ሙሐመድ ኪርማኒይ
♦️| አዲስ ሙሓደራ ከ"ملتقى" ቁ.026

● ርእስ፦ "የወጣቶች ሚና ኢስላምን በማሰራጨት ረገድ"

🎙ኡስታዝ ሙሐመድ አል-ኪርማኒይ
           -ሐፊዞሁ'ሏህ- ከዱና


🕌 በሰለፊዮች መገናኛ ግሩፕ የተደረገ ሙሓደራ!

🗓 ረቢዑ'ሣኒ 15 - 1448

|| #የመገናኛው_ግሩፕ፦
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
በሶላት ውስጥ ኹሹዕ (ልብን መሰብሰብ) ✨ውድ ወንድም እና እህቶቼ! ሶላት የዕለት ተዕለት

የሕይወታችን መረጋጋት እና ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር የምንገናኝበት ታላቅ መድረክ ነው። ነገር ግን ብዙዎቻችን ሶላት ላይ ስንቆም ልባችን በዱንያ ሃሳብ፣ በስራ

ወይም በሶሻል ሚዲያ ወሬ ይበታተናል። የሶላት እውነተኛ ጣዕምና ፍሬ የሚገኘው ግን ኹሹዕ (ልብን ሰብስቦ በአላህ ፊት መተናነስ) ሲኖር ብቻ ነው።📖 አላህ

(ሱ.ወ) በቁርአኑ እውነተኛ ስኬታማ ሙዕሚኖችን ሲያወድስ መጀመሪያ የጠቀሰው ይህንን ነው፦"እነዚያ በሶላታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች (ተናናሾች) የሆኑት ምእመናን በእርግጥ እረዱ (ስኬታማ ሆኑ)።" (አል-ሙዕሚኑን፡ 1-2)


ነቢያችን (ﷺ) ደግሞ ሶላት ላይ ስለሚሰርቀው ሸይጣን (ኽንዘብ) ሲያስጠነቅቁን፣ ልባችን ሲበታተን በአላህ እንድንጠበቅ እና ወደ ግራችን ሶስት ጊዜ ቀስ ብለን እንድንተፉ

አስተምረውናል። [ሙስሊም]📌 በሶላታችን ላይ ኹሹዕን ለማምጣት የሚረዱ

4 ወርቃማ መንገዶች፦

1️⃣ ቀድሞ መዘጋጀት፦ አዛን ሲል ጀምሮ ስራን አቁሞ በጥሩ ውዱእ እና በዱዓ ወደ ሶላት መዘጋጀት።

2️⃣ የመጨረሻ ሶላት እንደሆነ ማሰብ፦ ሶላት ላይ ስንቆም ይህች ሶላት የዚህች ዱንያ የመጨረሻችን ሶላት ልትሆን
እንደምትችል አስቦ መስገድ።

3/ የምናነበውን ማስተዋል፦ በቁርአን ቅራቴአችን እና በዚክራችን ላይ የምንላቸውን ቃላቶች ትርጉም
ለማስተዋል መሞከር።

4️⃣ ርጋታ (ጡመእኒናህ)፦ በሩኩዕ፣ በስጁድ እና በመሃል ባሉ መቀመጦች ላይ ሳያፈጥኑ እያንዳንዱን አካል አረጋግቶ መስገድ።⚠️ ውድ እህቴ! ውድ ወንድሜ! ሶላት ዝም ብሎ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይደለም፤ የነፍስ ማረፊያ እንጂ። ነቢያችን (ﷺ) ቢላልን "ቢላል ሆይ! በሶላት አሳርፈን" ይሉት ነበር። ሶላታችን የጭንቀት ማረፊያ እንዲሆን ዛሬውኑ ኹሹዕን ለመለማመድ እንጣር።አላህ ሶላታቸውን በተሟላ ኹሹዕ ከሚሰግዱት እና ጀነትን ከሚወርሱት ሳሊህ ባሮቹ ያድርገን

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
➻ውዱ ሸይኽ ዶ/ር ሁሰይን ብን ሙሀመድ (ሀፊዛሁሏህ) ጀምረዋል

ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም

አድ ና ሸር በማድረግ  የአጅሩ ተከፋይ ይሁኑ!! 👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
. Click the link to join us! https://s.imoim.net/tBLAMO?from=other


በቴሌግራም
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bilalmesji?videochat
🌟 የሰለፊያ አንድነት 🌟
የተውሂድ ሰንደቅ ዓላማው ሲያበራ፣
የሱናው መሻኢኽ ቆመዋል በአንድ ጋራ።
አንድነታቸው ውብ ልብን የሚያረሰርስ፣
የሰለፊያ መንገድ የሀቅ ምንጭ የሚፈስ።
ከትውልድ ትውልድ ሳይናወጽ የኖረው፣
በጽናት ቁመው ነው ሀቅን ያደመቁት ሰው።
የቢድዓን ጨለማ በዕውቀት እያጠፉ፣
የሰለፊያን ብርሃን ለዓለም አተረፉ።
እንዴት ያሚያምርበቸው በአንድነት ሲቆሙ፣
ለኡማው መከታ መመኪያ ሲሆኑ።
ልዩነት ሳይበግራቸው በሱና ተባብረው፣
የሰለፊያ ውበት በምድር ላይ ደምቆ የታየው
አለህ ይጠብቅልን እስከ መጨረሸ አለህ በሱነ ለይ የፅነልን
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
🎙ወንድም አቡበከር '

📖 ይህ ወንድማችን ሞቷል፣ አላህ ይርሀመው። ቲላዋውን በማሰራጨት፣ ስንቁን እናብዛለት
Forwarded from áŒŒá‰łá‹Ź ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!
🌸 ጥያቄ 🌸
📖 ወደ አድ ሕዝቦች ተውሒድን እንዲሰብክ የተላከው ነብይ ማነው?
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
✅ ትክክለኛውን መልስ በመጫን

📲 ወደ ሰለፊዮች ቻናል ይቀላቀሉ!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌸እህት ዓለም ሆይ! በዚህ በፈተናና በዱንያ ውክውክ በበዛበት ዘመን፣ ለልብሽ እውነተኛ እረፍትና ብርሃን የምታገኚው ወደ አላህ ቃል (ወደ ቁርአን) ስትመለሺ ብቻ ነው። የሰለፎች ታላቅ አርአያ የነበሩት ዑስማን ኢብኑ ዐፍዋን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይሉ ነበር፦ "ልቦቻችን (ከወንጀልና ከፊልም/ከወሬ) ንጹህ ቢሆኑ ኖሮ፣ ከጌታችን ቃል (ከቁርአን) መቼም ቢሆን አይጠግቡም ነበር!"አንቺ የሰለፎች ወራሽ የሆንሽው ጽኑ እህቴ ሆይ! በየቀኑ ከቁርአን ጋር ያለሽ ግንኙነት ምን ይመስላል? ማህበራዊ ሚዲያዎችን (ቲክቶክና ቴሌግራምን) ለማየት በየሰዓቱ የምንጓጓውን ያህል፣ የልባችን መድኃኒት ለሆነው ለቁርአን ጊዜ እንሰጣለን?ቁርአን እኮ፦በዱንያ ላይ ሳለሽ ልብሽን ከጭንቀትና ከፈተና የሚጠብቅሽ፣በኒቃብሽና በሱናሽ ላይ እንድትጸኚ ጥንካሬ የሚሆንሽ፣ዛሬ ይሁን ነገ መምጫውን የማናውቀው ታላቁ እንግዳ (ሞት) መጥቶ ወደ ቀብር ስንወርድ በዚያች ጨለማ ቤት ውስጥ ብርሃን ሆኖ ከጎናችን የሚቆም እውነተኛ ጓደኛችን ነው።ስለዚህ እህት ዓለም፣ የቁርአን ገጾችን በየቀኑ በማንበብና በውስጡ ያለውን ትእዛዝ በተግባር በመኖር ልብሽን አርጥቢ። በጽናት በሱና ላይ ሆነሽ ለአኺራሽ ታላቅ ስንቅ ሰብስቢ! 👑

https://t.me/https_Nissa_aselefyea
https://t.me/https_Nissa_aselefyea
ፈጋግ እያለቹ
አንድ ሰውዬ ሶላት ሲሰግድ በጣም ይፈጥናል፤ ሱጁድ ወርዶ ወዲያው ይነሳል። ልክ ሶላቱን ጨርሶ እጁን ዘርግቶ ረዥም ዱዓ ማድረግ ይጀምራል።
ይህንን የታዘበ አንድ ጓደኛው ቀረብ ብሎ፦ "ለመሆኑ ቅድም ሰማይ ላይ የነበረውን አምቡላንስ አየኸው?" አለው።
ሰውየውም ደንግጦ፦ "አላየሁም፣ ምንድነው የሆነው?" ሲል ጠየቀው።
ጓደኛው፦ "ቅድም አንተ ሶላት ስትሰግድ ጂብሪል ለአንተ ሰላምታና መልካም ምኞት ይዞ እየወረደ ነበር፣ ነገር ግን አንተ ሱጁድ አድርገህ የተነሳህበት ፍጥነት በጣም ስለበረታ መልእክተኛው ሳይደርስብህ አምቡላንስ ተጠርቶለት ወደ ሰማይ ተመለሰ!" አለው ይባላል። ሀሀሀሀ (ሶላትን በእርጋታ መስገድን ለማስታወስ)