💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.73K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
🔖 َمـا هــي الكلمــــة الطيبــــة ..؟
══
══✺══✺══✺════ 
۞ قـــال الشيخ ابــن العثيميـــن رحمـه الله :
❉ الكلمــــة الطيبــــة قســـمـان :
❶ - طيبة بذاتها .
❷ - طيبة بغاياتها
.

۞ - أما الطيبة بذاتها :
❉ كالذكر [ لا إله إلا الله ، الله أكبر ، الحمد لله ، لا حول ولا قوة إلا بالله ] ..
❉ وأفضل الذكر قراءة القرآن .

۞ - وأما الكلمة الطيبة بغاياتها :
❉ فهي الكلمة المباحة ، كالتحدث مع الناس إذا قصدت بهذا إيناسهم وإدخال السرور عليهم .
❉ فإن هذا الكلام وإن لم يكن طيبا بذاته ، لكنه طيبا في غاياته في إدخال السرور على إخوانك ، وإدخال السرور على إخوانك مما يقربك إلى الله عز وجل " .

❒ شـرح ريـاض الصـالحيـن (290/1)
════✺══✺══✺════ 

t.me/https_Asselfya
አላማ ይኑርህ
Daru tewhid
ህይወት የምትጣፍጠው ፣ ደስታ የምታገኘው እንደፈለክ እንደ እንስሳ ስትኖር ሳይሆን ጠንካራ ሆነህ የአቋም ሰው ስትሆን ነው!!

🎙በኡስታዝ አቡል ዐባስ ሀፊዘሁላህ

       t.me/Darutewhide
🔖 ቁርአን ተጅዊድና á‰ƒáŠ˘á‹°á‰ąáˆ ኑራንያ መማር የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ሴቶች ብቻ ግቡ የምታቀራዉ ሴት ነች መስፈርቱ ይነገራችኋል ....!

t.me/+iPN3KTXRrRIzZWQ8
t.me/+iPN3KTXRrRIzZWQ8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
﴿تَتَجافى جُنُوبُهم عَنِ المَضاجِعِ يَدْعُونَ رَبَّهم خَوْفًا وطَمَعًا﴾


"وتأمل كيف قابل ما أخفوه من قيام الليل بالجزاء الذي أخفاه لهم مما لا تعلمه نفس؟
وكيف قابل قلقهم وخوفهم واضطرابهم على مضاجعهم حين يقوموا إلى صلاة الليل بقرة الأعين في الجنة".

ابن القيم، حادي الأرواح صـ ٥٩٣ || القارئ: محمد خليل القارئ رحمه الله.

#تلاوة
🔖ለአንተ እድገትም ይሁን ውድቀት ወሳኟ ለትዳር ትሆነኛለች ብለህ የመረጥካት ሴት ናት!!

=
t.me/https_Asselfya
13-القواعد الحسان
ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሸይኽ ኣደም
🔖 አዲስ ተከታታይ ደርስ

📚የአል_ቀዋዒዱል_ሒሳን ኪታብ

~ ክፍል - 13

🎙️ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሸይኽ ኣደም

የኪታቡን  Pdf   ለማግኘት* ↓↓↓
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/8593
~ከሴት ልጅ ሀያእ ከተወገደ አበቃ !ጨዋነት
እንደ ወንድ ወይም ከወንድ የባሠች ትሆናለች።

የሀያዕ መወገድ የራሱ ምክንየቶች አሉት
~መቀላቀልን ማብዛት
~ከልጅነት ጀምሮ ከጨዋነትና ከሀያዕ የራቁ አለባበስን መልበስ
👉ከዚያም ይህን ነገር እንድትለምደዉና እንዲትፀናበት ያደርጋታል።

🎙ሼኸ ኢብኑ ኡሰይሚን
~
t.me/https_Asselfya
👍1
ለጋጠ-ወጥ ሙስሊም እህቶቻችን ብቻ አድርሱልኝ


አላማረብሽም...!!
--------------------

አይዞሽ እያሉ የሚያመናቅሩሽ፡
ተጠንቀቂ እህቴ መና-እንዳያስቀሩሽ፡
ይልቅ ዑስታዞችሽ ተውሒድ ሱናን ያቅሩሽ!

ሐቅን የያዘ ሴት አሏህን ይፈራል፡
በአደብ ተሰተሪ ስርዓት ያስከብራል፡
ሐያዕ ውበትሽ ነው ከሰው ጋር ያኖራል፡
ወላሒ አደብ ነው የሴትነት ሞራል፡

ዛሬ ወጣት ሆነሽ አለኝ ብትይ ውበት፡
ጤዛ ነው ይረግፋል ያጠፋዋል ሽበት፡
ይልቅ ተሸፈኝ ኒቃብ ጨምሪበት፡

ለጊዜው ነው እንጂ፤
        አብሮ አይኖር ቁንጂና፡
ጥሩ ልብ ይሩርሽ፤
          አይከስምም በርጂና፡

ሙስሊም ሆነሽ ሳለ አትሁኝ መሳቂያ፡
እምነትሽ አይደለም ወንጀል መደ'በቂያ፡
ስንቶች እህቶችሽ በአንች ተሳቀቁ፡
አፈሩብሽ አወ ከቲክቶክ ለቀቁ፡

ሞጣ እሚባል ቁርበት የሚገለምጥሽ፡
ዮኒ እሚባል ጋኛ የሚገለፍጥሽ፡
ወላጅ የለሽም ወይ የሚቆነጥጥሽ!?


ይሰለቻል አሉ ቁንጂና ቀን በቀን፡
ጥሩ ልብ ይኑርሽ የለውም ሰቀቀን፡

ፈተናውን ታገሽ ሁሉም ነገር ያልፋል፡
ይልቅ ተሰተሪ እምነትሽ ይገዝፋል፡
ነገ ጀናዛ ነሽ ውበትሽ ይጠፋል፡

ዛሬ ላይክና ሸር ዝና ቢያሰክርሽም፡
ነገ ቀብር አለ ተይው ግደለሽም፡
ወላሒ ልንገርሽ አላማረብሽም፡


  «ኑረዲን አል አረብ»

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
【አላማረብሽም】
በኑረዲን አል-አረብ
ዛሬ ላይክና ሸር ዝና ቢያሰክርሽም፡
ነገ ቀብር አለ ተይው ግደለሽም፡
ወላሒ ልንገርሽ አላማረብሽም፡
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
አባካኝነትን እንራቅ
~
ሁሉም ነገር ልክ አለው። እዝነት ልክ አለው። መስዋእትነት ልክ አለው። ዒባዳ ልክ አለው። ቸርነት ልክ አለው። ደግነት ልክ አለው። መልካም ነገር ከልኩ ሲያልፍ ስሙ ይቀየራል። ደግነቱ ሞኝነት ይሆናል። ጥንቃቄው ፍርሃት ይሆናል። ብልህነቱ አጉል ብልጣብልጥነት ይሆናል። ያኔ ውበቱን መልኩን ያጣል። ያኔ ጉዳዩ ወደ ውጉዝነት ተሸጋግሯል ማለት ነው።
ይህ እንዳይሆን ትኩረት መስጠት ይገባል። በልክ መሆን ውበት ነው። በልክ መሆን ጨዋነት ነው። በልክ መሆን ታስቦበት ሲሆን ዒባዳ ነው። በልክ መሆን ሞገስ አለው።
ልክ ማለት ወደ ላይም ወደ ታችም ድንበር አለማለፍ ነው። በአቋምህ ድንበር አትለፍ። በንግግርህ ድንበር አትለፍ። በገንዘብ አያያዝህ ድንበር አትለፍ። በጊዜ አጠቃቀምህ ድንበር አትለፍ። ለሁሉም ነገራችን ለከት ሊኖረው ይገባል። ለምሳሌ ገንዘብ ጋር የተያያዘውን አባካኝነት ላንሳ። ጌታችን አላህ አባካኝነትን ይነቅፋል። እንዲህ ይላል፦
{ وَلَا تُبَذِّرۡ تَبۡذِیرًا (26) إِنَّ ٱلۡمُبَذِّرِینَ كَانُوۤا۟ إِخۡوَ ٰ⁠نَ ٱلشَّیَـٰطِینِۖ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِرَبِّهِۦ كَفُورࣰا (27) }
"ማባከንንም አታባክን፡፡ አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና፡፡ ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው።" [አልኢስራእ፡ 26-27]
በዚህ ቦታ ላይ አባካኝነት ከግልፅ ክልከላ ባለፈ በጥብቅ እየተኮነነ ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው እንዲህ ዓይነቱን ማሳሰቢያ እንደዋዛ ሊያልፈው አይገባም። ስለዚህ፦
* አመጋገባችን ላይ ብክነት እንዳይኖር እንጠንቀቅ። በልካችን እናቅርብ። በልካችን እንመገብ። አላህ አባካኞችን አይወድም።
{وَكُلُوا۟ وَٱشۡرَبُوا۟ وَلَا تُسۡرِفُوۤا۟ۚ إِنَّهُۥ لَا یُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِینَ }
"ብሉ፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና።" [አልአዕራፍ፡ 31]
* ስንታጠብ፣ ውዱእ ስናደርግ፣ እቃ ስናጥብ ውሃ አናባክን። ነብያችን ﷺ በውዱአቸውም በትጥበታቸውም ላይ የውሃ አጠቃቀማቸው የተመጠነ ነበር። በመኖሪያ ቤቶችም ይሁን በመስጂዶች ወይም በሌላ ቦታዎች የውሃ አጠቃቀማችን በልክ ይሁን። ስንጨርስ ቧንቧዎችን በትክክል እንዝጋ። የተበላሸውን እንጠግን።
* ያለ ፋይዳ መብራቶችን አናብራ። በማይፈልግ ቦታና ጊዜ የሚበሩትን እናጥፋቸው። የቤታችንን መብራት፣ ማገዶ፣ ናፍጣ፣ ነዳጅ፣ ሲሊንደር ጋዝ፣ ... ያለ ፋይዳ ሲሰራ አይተን አንለፍ።
* በጥቅሉ ልብሳችን፣ ገንዘባችን፣ ሞባይላችን፣ ኮምፒተራችን፣ ... ሁሉም አይነት ንብረታችን ባግባቡ ሊይያዝ የሚገባ የጌታችን ስጦታ ነው። ያለ አገልግሎት የትኛውም ሃብት ሊባክን አይገባም። ጌታችን ስለዋለልን ኒዕማዎች ከማመስገን ውስጥ አንዱ ፀጋዎቹን ባግባቡ መጠቀም ነው። ይሄ ከደጋግ የአረሕማን ባሪያዎች መታወቂያዎች ውስጥ ነው። የላቀው ጌታ እንዲህ ይላል፦
{ وَٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَنفَقُوا۟ لَمۡ یُسۡرِفُوا۟ وَلَمۡ یَقۡتُرُوا۟ وَكَانَ بَیۡنَ ذَ ٰ⁠لِكَ قَوَامࣰا }
"እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የሆነ ነው።" [አልፉርቃን፡ 67]
ባይሆን አታባክን ማለት ሰስት ማለት አይደለም። አላህ የሰጠንን ፀጋ እሱ በሚወደው ቦታ ላይ ባግባቡ ማውጣት የታዘዝንበት አደራ ነው። ብቻ ሁሉም በልክ ሲሆን ያምራል።
{ وَلَا تَجۡعَلۡ یَدَكَ مَغۡلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبۡسُطۡهَا كُلَّ ٱلۡبَسۡطِ فَتَقۡعُدَ مَلُومࣰا مَّحۡسُورًا }
"እጅህንም ወደ አንገትህ የታሰረች አታድርግ፡፡ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤ የተወቀስክ የተቆጨኽ ትኾናለህና።" [አልኢስራእ፡ 29]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
t.me/IbnuMunewor
👍1
ድክመትህን አላህ ፊት ብቻ ግለጥ። ዓለም ጉልበትህን ብቻ ይመልከት!…

ማንም ድክመትህን እንዳያይ! በመስታወት የሚያዩህ ዓይኖችህ እንኳን የጨፈገገና የተከፋ ፊትህን አይመልከቱ!

ደስታህ ሰዎች በሚዘረጉልህ የእዝነት እጅ ወይም በሚያሳዩህ ፊት ላይ አይቋጠር!…

የሰዎች እገዛም ሆነ ጫና ደስታህን ከፍም ሆነ ዝቅ አያድርጉብህ! የሰዎች መልካም ትድድር ተጨማሪ ነገር ሆኖ የደስታህና የእረፍትህ ምንጭ ቀልብህ ይሁን!

ህይወት ለደካሞች ጠባብ ናት!

t.me/https_Asselfya
~ከታናሽህም ከታላቅህም ተማር!!!!

~
🔖 የማታ ዚክር አትርሱ ...!
~    ~    ~    ~     ~   ~   ~
🌻اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَاْلآخِرَةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِيْنِيْ وَدُنْيَايَ وَأَهْلِيْ وَمَالِيْ. اَللَّهُمَّ احْفَظْنِيْ مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِيْ، وَعَنْ يَمِيْنِيْ وَعَنْ شِمَالِيْ، وَمِنْ فَوْقِيْ، وَأَعُوْذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِيْ.
#አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታንና ጤንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡

አላህ ሆይ! በሀይማኖቴ፥ በዚህች አለም ህይወቴም፥ በቤተሰቦቼም፥ በንብረቴም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ፡፡

አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ  ከኃላዬም፥ ከቀኜም፥ ከግራዬም፥ ከበላዬም ጠብቀኝ፡፡ ከበታቼም እንዳልጠቃ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
~
   
t.me/https_Asselfya
ግማሼ ጓደለ ብለህ በማይሆን ግማሽ ግማሽህን አትሙላ !

=
መልእክት ለሴቶች
Abdul Aziz
ውድ ወንድሜ አብዱል አዚዝ ይባላል አላህ ይጠብቀው ።

ልብ ሰርስሮ የሚገባ ምክር ነው የመከረን
🔖 አቡ ደርዳእ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ

✅ ከወንድሙ ክብር የተከላከለ (የመለሰ) ሰው የውመልቂያማ አላህ ከፊቱ እሳት ይከላከልለታል (ይመልስለታል)።

📚(ቲርሚዚ ዘግቦታል)

t.me/https_Asselfya
የሐጅ ቆይታ ትዝብቴ
~
የአላህ ፈቃዱ ሆኖ በተጠናቀቀው የሂጅራ አመት 1445 ለሐጅ ከተጓዙ ኢትዮጵያውያን ውስጥ አንዱ ነበርኩ። የሄድኩት ለአንድ ወንድሜ አባት የውክልና ሐጅ ለመፈፀም ነው። ምናልባት ለሌላ ጊዜ እንደ ግብአት ካገለገለ በሚል የሐጅ መስተንግዶውና ተያያዥ ሁኔታዎች ምን ይመስሉ እንደነበር ጥቂት ማለት ወደድኩ። ዝርዝር ውስጥ ከመግባቴ በፊት አዲስ አበባ መጅሊስ ውስጥ ያለን አንድን ወንድም በተለየ ማመስገን እወዳለሁ። ስሙ ሃሺም ዐብደላህ ይባላል። ከጉዞ በፊት ጀምሮ እስከ መጨረሻ መረጃ በመስጠት ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል፣ ብዙ አይነት አመሎችን ችሎ ጠብ እርግፍ ብሎ አገልግሏል። ለአዲስ አበባ ሑጃጅ መረጃ ለማስተላለፍ በተከፈተው የቴሌግራም ግሩፕ ላይ ሌላ ሰው ያልለ እስከማይመስል ድረስ በተለየ መልኩ መረጃ መስጠት፣ ማለቂያ የሌለው ጥያቄ መመለስ፣ በስልክና በአካል ማስተናገድ፣ ... ባጭሩ አንድ ሰው እስከማይመስል ድረስ ነበር ሃላፊነቱን ሲወጣ የነበረው። ይሄ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ትልቅ ምሳሌ ነው። ሃሺም በኦንላይን ብቻ ሳይሆን በአካልም በትህትና በፈገግታ ሲቀበል ሲያስተናግድ ሁለት ሶስት ጊዜ አይቼዋለሁ። ባገኘሁት ሰዓት ከሰላምታ ባለፈ ምስጋናየን ሳልገልፅ በመቅረቴ ስለቆጨኝ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ በእጅጉ ማመስገን እፈልጋለሁ። አላህ የልፋቱን ይመንዳው።

ከዚህ በመቀጠል ጥቅል ነገር ለማስቀደም ያክል በሐጁ ጉዳይ ላይ የሚሰነዘሩ ሃሳቦችን በተወሰነ መጠን ተከታትያለሁ። እንደኔ እይታ አንዳንድ በሳል ሃሳቦችን የሰነዘሩ ቢኖሩም ብዙዎቹ ግን በልክ የተያዙ አልመሰለኝም። ደጋፊዎች የመንግስት ካድሬ አይነት ባህሪ ባትይዙ መልካም ነው። በቅድሚያ ተጨባጭ የሆኑ የመስተንግዶ ክፍተቶች፣ በቀጥታ ሲገለፅ የአስተባባሪዎች መዝረክረክ ነበር። ድክመቶች መለየታቸው ለወደፊት የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ግብአት ስለሚሆኑ ሊጎረብጠን አይገባም። በሌላ በኩል አንዳንድ ትችቶች በጣም የተጋነኑ ነበሩ። በቦታውም ላይ ጭምር አንዳንዴ የሚናገሩበት ሰበብ የሚጠብቁ የሚያስመስሉ ሁኔታዎችን አይተናል። ይህንን እንደ መግቢያ ካልኩኝ ከሐጅ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ያለውን ጉዳይ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ብዬ ለሁለት ከፍየ አቀርባለሁ።

ሀ - ጠንካራ ጎኖች

1- የምዝገባ ሂደቱ ምንም አይነት መጉላላት የሚባል የሌለበት ቀልጣፋ ነበር።
2- ለአዲስ አበባ ሑጃጅ መረጃ ማስተላለፊያና መለዋወጫ የቴሌግራም ግሩፕ መከፈቱም ጥሩ ነው።
3- ጉዞ ሲጀመርም ከቦሌ አየር መንገድ የነበረው የመጅሊስ አስተባባሪዎች ሚና ጥሩ የሚባል ነው።
4- የስልክ የሮሚንግ አገልግሎቱም ቢሆን ከነ ውስንነቱ ጥሩ ነው።
5- መጓጓዣ አውቶቡሶችን በተመለከተ ከሆቴል እስከ ሚና፣ እስከ ዐረፋ፣ ከዚያም እስከ ሙዝደሊፋ የማጓጓዝ አገልግሎት ነበር። የማስተባበር ችግርና መዝረክረክ ጎልቶ የሚታይበት ከመሆኑ ጋር። መጠኑም በቂ አልመስለኝም።
6- የምግብ አቅርቦቱ በአመዛኙ ጥሩና በቂ የሚባል ነው። ክፍተቶች የሉም እያልኩ አይደለም። በዚህ ላይ የሚቀርቡ ትችቶች ግን እንደኔ ምልከታ በጣም የተጋነኑ ናቸው።
7- የተያዙት ሆቴሎች ጥሩ ወይም በጣም ጥሩ የሚባል ደረጃ ያላቸው ናቸው። መገኛቸውም ከመስጂደል ሐራም ብዙ ሩቅ የሚባል አልመሰለኝም። ርቀት አንፃራዊ ነውና እይታችን ሊለያይ ይችላል።
8- አስተባባሪዎችና ሆቴል ላይ አስተናጋጆች በአመዛኙ እንደ ባህሪ ጥሩ ናቸው። በቂ ቁጥር፣ ትጋት፣ አቅም፣ ቅንጅት፣ ቅልጥፍና ያንሳቸዋል ብዬ አስባለሁ። ሳይሰለቹ ስልክ ሲያነሱ፣ የሚናገራቸውን ጭምር ሲያልፉ አይቻለሁ። አንዳንዱ ሰው ለመጣላት የተዘጋጀ እስከሚመስል አቀራረቡ ይከብድ ነበር። የማይመለከታቸውን ጭምር በተደጋጋሚ ሲያዟቸው ሲታዘዙ አይቻለሁ።

ለ - ደካማ ጎኖች

1- የተጋነነ ዋጋ። ዋጋ ስል አጠቃላይ ክፍያውን ማለቴ አይደለም። ይህኛውን ከሌሎች ሃገራት ጋር በማነፃፀር ውድ እንደሆነ የገለፁ ሰዎችን ፅሁፍ አይቻለሁ። ስለሱ ለመናገር የሚያበቃ በቂ መረጃ ባይኖረኝም ትንታኔው አሳማኝ ይመስላል። በራሴ ያየሁት ግን በተሻለ የጊዜ ገደብ ውስጥ ለአየር ትኬት በግል 24ሺ (?) ብር ገደማ የቆረጠ ሰው ያገኘሁ ሲሆን በመጅሊሱ ግን 55ሺ ብር ነው የተቆረጠው። ከእጥፍ በላይ ልዩነት! ይሄ ፍትሃዊ አይደለም። እየበሉን ይሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እያስበሉን ይሁን አላውቅም።
2- የአስተባባሪ እጥረት :- ለተለያዩ ጉዳዮች ሲፈለጉ አይገኙም። እዚያኛው ሆቴል ናቸው ይባላል። እዚያ ሲኬድ ደግሞ ሌላኛው ጋ፣ ...
3- የመጅሊስ አስተባባሪዎች በሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር በኩል ጉዳያችንን ከሚይዙ አካሎች ጋር ፎርማል ግንኙነት ያላቸው አይመስሉም። ብዙ ሑጃጅ አንገት ላይ የሚደረገውን ባጅ በጊዜ ባለማግኘቱ ሲቸገር ፈጣን መፍትሄ ማምጣት አልቻሉም።
4- ሚና ላይ የነበሩ ኸይማዎችና የፍራሽ ሁኔታ ምቾት የሚነሳና ለወረርሽኝ ሊያጋልጥ የሚችል ነበር። በግምት ከ450 የማያንስ ሑጃጅ በአንድ ድንኳን ውስጥ የታጨቀ ሲሆን መሀል ላይ ከምትኖር አንዲት ቀጭን መስመር ውጭ ለእግር መረገጫ የሚሆን ክፍተት አልነበረም። ከዳር እስከ ዳር ተገጣጥመው በተደረደሩ ቀጫጭን ፍራሾች ላይ ታጭቀን ነበር ለቀናት የሰነበትነው። ያውም ሳይበቃቸው ፍራሽ ሳያገኙ ውጭ ላይ የነበሩ ሰዎችን አይቻለሁ። ከአስተባባሪዎች ውስጥ ያለንበትን ሁኔታ የሚታዘብ፣ ተዘዋውሮ "ምን ችግር አለ?" ብሎ የሚጠይቅ አንድም አልገጠመኝም።
5- ሚና ላይ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር ነበር። የሆነ ሰዓት ላይ ምንም አይነት መድሃኒት የለም ተብያለሁ። ለበሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች በበዙበትና ብዙ ህመምተኛ በሚኖርበት ጊዜ ላይ እንዲህ አይነት መዘናጋት ሊኖር አይገባም ነበር። ወደ መካ ከተመለስን በኋላ መድሃኒት እያገኙ እንደሆነና ከኢትዮጵያ የመጣ እንደሆነ ሰዎች ነግረውኛል። ስለዚህ ችግሩ የማስተባበር መሰለኝ።
6- ሰዎች በሚጠፋፉበት ፈታኝ በሆነው 10ኛው ቀን ላይ በጣም ብዙ መንገዶች ላይ አንድም የመጅሊስ አስተባባሪ አላየሁም። አንድም! 
እስከማውቀው ቀድሞ የተሰጠ ማሳሰቢያም የለም። መጨረሻ ማረፊያችን አካባቢ በተወሰኑ ርቀቶች ላይ አንድ አራት አምስት አስተባባሪዎችን አይቻለሁ። በሙቀቱ ምክንያት ስልኬ እየጋለ እየዘጋ ቢያስቸግረኝም በጉግል ማፕ ሎኬሽን የሆነ ያክል ለመጠቀም ሞከሬያለሁ። ግን ስንቱ ይህን ማድረግ ይችላል? በዚህ ቀን ብዙ ሰው ጠፍቶ ነበር። የሞቱም አሉ። አስተባባሪዎች በደረሰው ጉዳት ተጠያቂ እንዳይሆኑ እፈራላቸዋለሁ።
7- የጠፉ ሰዎችን መረጃ ከጤና ተቋማት በቀጥታ ማጣራት አይችሉም ነበር። የአፋልጉን ማስታወቂያ በቴሌግራም ግሩፕ፣ በሆቴሎች በር ላይ በተደጋጋሚ ለቀናት ሲለጠፍ ነበር። መጅሊሱ እንደ ተቋም ከሳዑዲ የጤና ተቋማት ጋር ፎርማል ግንኙነት በመፍጠር በቀላሉ ሪፖርት ማግኘት እየቻለ ቤተሰብ በየ ሆስፒታሉ ፍለጋ መባዘኑ የሚያሳዝን ነበር።

ስለዚህ የአብዛኞቹ ክፍተቶች ሰበብ አስተባባሪዎች ወይም አስተናጋጆች ቦታቸው ላይ መኖራቸውን፣ ሃላፊነታቸውን ባግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን የሚቆጣጠር፣ ቁጥራቸው በቂ መሆን አለመሆኑን የሚገመግም አካል ያለ አልመሰለኝም። ለወደፊት ይሄ ጉዳይ በቂ ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው። በመዘንጋት ወይም የጎሉት ላይ በማተኮር ያልጠቀስኳቸው ደካማም ጠንካራም ነጥቦች ይኖራሉ።