💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
📓 العبادة لا تُسمَى عبادة ‼️

إلا مع
•••
العبادة لا تُسمَى عبادة إلا مع

التّوحيد .

📓 قال
#الشيخ_عبد_الرزاق_البدر_حفظه_الله :

✔️ والعبادة لا تكون
#عبادة إلا مع التوحيد ، بأن يكون #العبد موحداً لله جل جلاله ، مخلصاً في #عبادته كلها ، بأن تكون #صلاته لله ،وحجه لله ، ونذره لله ، دعاؤه #يتوجه به إلى الله ، توكله على الله ، رجاؤه من #الله ، خوفه من الله ، وهكذا بكل عباداته لا #يصرف منها شيئا إلا لله سبحانه وتعالى...

  {وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ } [البينة:٥].

{أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ} [الزمر :٣]

{وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا} [الجن :١٨]

والآيات في هذا المعنى كثيرة .

📖 شرح القواعد الأربع .
👍1
"እኔ" ገደል እንዳይከተን
~
"እኔ እኔ" ሲበዛ ለሰሚው ያቅለሸልሻል። ድንበርም ያስታል። ለራስ የተጋነነ ግምት ማሳደር ጎንበስ ብሎ ለመማር እንቅፋት ይሆናል። በ "እኔ" የተለከፈ ማንነት ከኢኽላስ ጋር የመጣላቱ እድል ሰፊ ነው። እዚህ ላይ አንድ የሚደንቅ የሶሐቦች ስብእና አለ። ከሚያስተላልፏቸው ገድሎች ውስጥ የራሳቸው ሲሆን ጊዜ "አንድ ሰው እንዲህ አድርጎ" በማለት እንደዋዛ የአንድ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ። ታሪኩ በሌላ አቅጣጫ ሲፈተሽ ግን የራሳቸው ገድል ሆኖ ይገኛል። ሱብሓነላህ!

ኢኽላስን ለማረጋገጥ፣ ስግብግብ ነፍስያን ለማሸነፍ፣ በራስ ፍቅር ክንፍ ከማለት ለመዳን "እኔ፣ እኔ" በሚል ክፉ ስሜት ላይ ጦርነት ማወጅ ያስፈልጋል። ነፍሲያን ጉሮሮዋን አንቆ መያዝ። የኢኽላስ ነገር ለነፍሲያ ፈተና ነው። የአንድ ሸይኽ ደርስ ላይ የሚገርም ገጠመኝ ሰማሁኝ። የሆነ ሰው ሌሊት እየተነሳ ሶላት መስገዱ ማንም ዘንድ አለመታወቁ ይከነክነዋል። እና በብልሃት ሰጋጅነቱን ማሳወቅ ፈለገ። ፋርማሲ ገባና

* "በሌሊት ሶላት ምክንያት ለሚሰማ ድካም የሚሆን መድሃኒት አለህ ወይ?" ብሎ ይጠይቃል።
- "የለኝም" አለው።
* "እሺ ሷሊሖችን ትውዳለህ'ንዴ?" ብሎ ይጠይቀዋል።
- ፋርማሲስቱ ነገሩ ቢገርመው አሳለፈው።
* "ለማንኛውም ሷሊሖችን ውድድ አላህ ይወድሃል" ብሎት ወጣ።

"እኔ" ይሉኝታ ያሳጣል።
"የኔ" ስግብግብ ያደርጋል።
"እኔ ዘንድ" ትእቢት ያወርሳል።

እነዚህ ስሜቶች ልባችንን እንዳይቆጣጠሩ መጠንቀቅ ይገባል። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
" 'እኔ'፣ 'የኔ' እና 'እኔ ዘንድ' ማለት ድንበር እንዳያልፍብህ መጠንቀቅ ይገባል። እነኚህ ሶስት ቃላት ኢብሊስ፣ ፊርዐውን እና ቃሩን ተፈትነውባቸዋል።
👉🏾 'እኔ ከሱ በላጭ ነኝ' የሚለው የኢብሊስ ነው።
👉🏾 'የግብፅ ግዛት የኔ ነው' የሚለው የፊርዐውን ነው።
👉🏾 '(ሀብቱን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው' የሚለው የቃሩን ነው።

➡️ 'እኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'እኔ ባሪያ ነኝ'፣ 'እኔ አጥፊ ነኝ'፣ 'እኔ ምህረትን ለማኝ ነኝ'፣ 'እኔ ወንጀለኛነቴን የማምን ነኝ'፣ ... በሚለው የባሪያ ንግግር ውስጥ ነው።
➡️ 'የኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'የኔ ወንጀል'፣ 'የኔ ውርደት'፣ 'የኔ ድህነት' በሚለው ውስጥ ነው።
➡️ 'እኔ ዘንድ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ ደግሞ 'ምሬንም ሆነ ቀልዴን፣ ስህተቴንም ሆነ አውቄ የፈፀምኩኑን ምህረት አድርግልኝ። ይሄ ሁሉ እኔ ዘንድ አለና' በሚለው ውስጥ ነው።"

📖 [ዛዱል መዓድ]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
~ምቀኝነት ከእውቀት ማነስ የሚመነጭ
ትልቅ የአዕምሮ ድህነት ነው!

~
هل يوجد فرق بين مشركي زماننا و المشركين الأولين ‼️
Anonymous Quiz
87%
نعم
13%
كلا
አንድ ሰው እንደት እንደዚህ ደስተኛ ሂዎት ሊኖርህ ቻለ ተብሎ ሲጠየቅ
አላህን በድብቅ ማመጽ ትቸ ብሎ መለሰ!
ብዙዎችን የከበደው. ይህ ነው።

~
سعادة المرأة في تغطية الوجه!!
Audio
ወንጀሎችን መራቅ ተውሂድን ከማረጋገጥ ውስጥ ነው

አጭር ምክር ሙሐመድ ሲራጅ
https://t.me/MedrestuImamuAhmed

https://t.me/Muhammedsirage
Forwarded from أَبُوْ سَهْلَة مُصْطَفَى سَعِيْدٍ الْجُنَيْدِي
ቆንጆ ግጥም ማሻአላህ

#አስመሳይ #አግብቼ

አስመሳይ አግብቼ ግራ ከምጋባ፣
ተደብቄ ልኑር ልቅር ሳላገባ።
ተመሳሳይ ኮፒ በመቅረቷ አልባባም፣
እምነት አሰዳቢ ፍፁም አላገባም።
የአላህን ትዕዛዝ ሂጃቧን አድርጋ፣
ከተጨማለቀች ከአጂነብይ ሰው ጋ፣
እሷን አላገባም ከቶ ቁሜ ልቅር፣
በብቻየ አለም ውስጥ ተደብቄ ልኑር።

አቂዳየ እያለ ምን አለው ካለችኝ፣
እስልምናየን ይዤ ድሃ ካረገችኝ፣
መስፈርቷ ከሆነ ቤት ና መኪና፣
ኒቃቢስትም ብትሆን ብትሄድ ተሸፍና፣
ትቅርብኝ ይች ልጂ እኔ አላገባትም፣
ኪታቤን አዝየ ሄዳለሁ የትም።

እውቀት ፍለጋየን አቀጣጥላለሁ፣
እምነት አሰዳቢ ለምን አገባለሁ።
ጀግና የጀግና ልጂ በመንሀጂ ያደገች፣
በሰለፎች አሰር አምራ የደመቀች፣
አላህ ከገጠመኝ ውብ ትዳር ፈላጊ፣
አስተዋይ መካሪ ንደት አረጋጊ፣
የሙብተዲ ጥላት ጦረኛ ተዋጊ፣

ሽርክን አፈራራሽ የተውሂድ ምርኮኛ፣
የቢድአ ካንሰር የሱና ሱሰኛ፣
እምነቷ ሲደፈር የሚያንዘረዝራት፣
ከእግር እስከ ራሷ ንደት የሚወራት፣
በአቂዳዋ ታጋይ ጀግና አርቆ አሳቢ፣
የእህቶቿ ሞደል በሂጃብ ተዋቢ፣

ከመጥፎ ከልክላ በመልካም ላይ አዛዢ፣
ውዲ ባልተቤቷን በፍቅር አደንዛዢ።
ለረጂሙ ጉዞ ስንቋን የሰነቀች፣
በተውሂድ በሱና በሀቅ የደመቀች።
ከመንሀጀ ሰለፍ ሁሌ የማትለወጥ፣
ያወራ ቢያወራ ልቧን የማትሰጥ።

ይህችን መሳይ ሞደል ታስፈልገኛለች፣
እህትም ፣ባልተቤት እናት ትሆናለች።
ችግሩ እሷ ግን የት አለች የት አለች፣
ልፈልግ በዱኣ ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም፣
እምነት አሰዳቢ አልለማመጥም፣
ተውሂድ ያልገባት ልጂ አርፋ አትቀመጥም።

ያ አላህ
እኔንም አድርገኝ ከነጓደኞቼ፣
ቀጥ ብየ የምሄድ አንተኑ ፈርቼ።
ሀቅ የምገልፅበት ስጠኝ እምቅ ወኔ፣
ተውሂድ ላስተምረው ይጠቀም ወገኔ።
ጀግናይቱ የት አለች ለባሽ ጥቁር ካባ፣
ብቸኝነት ይብቃኝ አትፈትነኝ ላግባ።
.     ╭─•••─═••••••═─•••─╮
.    🌺 እንኳን ደህና  መጡ 🌺     
.     ╰─•••─═••••••═─•••─╯
❝አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ❞

«ስለ ቀልባችን» የቻናሉ ዓላማ ምንድን ነው?
|
~በዚህ ዘመን በብዙ የዓለም አካባቢዎች ላይ በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ የአላህ ፍራቻ ሁኔታ ወርዶ ታይቷል፡፡ የዚህ ሁሉ መንስኤው የግሎባላይዜሽንና ቴክኖሎጂ ተጽእኖ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ የኢንተርኔት መስፋፋት፣ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በኩል የሰዎች በእጅጉ መቀራረብ ደግሞ ጉዳዩን የበለጠ አወሳስቦታል፡፡ በዚህም ምክንያት የብዙው ሰው ቀልብ አደገኛ በሆነ የኢማን ድርቅ በመመታቱ መጥፎና ጥሩን መለየት ተስኖታል፡፡ ይህ ሁኔታ ወደፊትም በዚሁ መልኩ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይመስላል፡፡

•የዚህ ቻናል ዓላማውም ይህን ድርቀቱን ለመቋቋምም ሆነ ለማከም ሰበብ ይሆን ዘንድ አላህ ያገራልንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከ ቁርኣን እና ከሀድስ መድሐኒቱን ለመጠቆም ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው።

Ⅱ-ስለሆነም በዚህ ቻናል ላይ፦
➜ ልብ የሚያረጥቡ አጫጭር ፁሁፎች፣
➜ ከ ቀልባችን ጋር የተያያዙ የሙሓደራ ፕሮግራሞች፣
➜ ከ ረቃኢቅ እና ከ አደብ ጋር የተያያዙ የቂርኣት ደርሶች፣
➜ አጫጭር የሆነ የሰለፎች ንግግር ከነ ትርጉሙ፣
➜ አጫጭር የቀደምቶች ታሪኮች፣
➜  በቻናሉ በቀጥታ ስርጭት ብሮድካስት የሚደረጉ መሰናዶዎች…

☞እንድሁም የተለያዩ ቁም ነገር አዘል ፕሮግራሞችን በሰፊው ለመስራት አስበናል።―ኢንሻ አላህ!―
t.me/Sle_Qelbachn
t.me/Sle_Qelbachn
👆አስተማማኝ ሂፍዝ ለመሀፈዝ
ከሚረዱን ነገሮች 5ቱን
ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ
~እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

👉እርካታ ሲለካ በዚክር ነዉ ለካ!!

=
~ትዳር ማለት ከመጥፎ ነገር  ከዝሙት ያልተፈቀደ ከማየት ያልተፈቀደ ከመንካት የምንቆጠብበት የአላህን ድንጋጌእንጂ!ሚስትህን እያስቀየምክ በሚዲያ እየዋሸህ ሌሎችን ልብ እምሠርቅበት የስዳዶች መድረክ አይደለም።

~ትዳር ማለት እሾህ ያለዉ አበባ ነዉ።ፍሬ እንዲያፈራልህ ከፈለክ የእሾሁን ዉጋት መታገስ አለብህ።እሾሁ አንዳንዴ ያለመግባባት ሲሆን ያኔ ታጋሸ ሁን። አበባ እዉነተኛ ፍቅር ሲሆን እዉነተኛ ባልሆነ አበባዉን ቅዘም ፍሬዉ የአብራክህ ክፋይ ልጆች ሲሆኑ ለልጆችህ እዉነተኛና ጀግና አባት ሁነህ በተርቢያ አሳድገህ የፍሬዉ ባለቤት ሁን።

=

t.me/https_Asselfya