💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.67K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.16K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
04 الوسائل المفيدة للحياة السعيدة
  Abu Sufiyan Albenan
―ክፍል (④)
📚الوسائل المفيدة للحياة السعيدة
«ደስተኛ ሕይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች!»
የኪታቡ pdfለማገኘት👇
t.me/https_Asselfya/8029
ኢማሙ ኢብኑል ቀይም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፡-

በተወኩል ላይ ተረከዞቹን ያፀና እራሱንም ወደ አላህ ያስጠጋ እንዲሁም እራሱንታዛዥ ያደረገ ሰው እርካታን ማግኘቱ ቅሮት የለውም።❞

        
    📚مدارج السالكين ٢ / ١٧٣"]
t.me/https_Asselfya
~ አግባ! ብዙዎች አግብተው ሀብታሞች ሆነዋል፤
ድህነትን #ፈርተህ አንተ ግን ፈዝዘሃል

=
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ                【ክፍል ሁለት 0⃣2⃣ ◾️ካፊር እና ፃም ↪️ 【ነጥብ አንድ】👉 ካፊር ቢፃም ፃሙ ተቀባይነት ያገኛልን⁉️ ◾️ካፊር የሆነ ሰው በኩፍሩ እስካለ ድረስ ረመዷንን መጾም ግዴታ አይሆንበትም። ቢፃም ራሱ ረሀብና ጥማት ከማትረፍ ውጪ ተቀባይነት አይኖረውም። ነገር ግን ይህ ማለት ነገ አላህ ፊት አይጠየቅበትም…
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ

#ህፃን (ለአቅመ አዳም) ያልደረሰ ልጅና ፃም

↪️ ክፍል ሶስት《0⃣3⃣

ህጻን ልጅ ብሉግ (አቅመ አዳም) እስኪደርስ ድረስ ፃም ግደታ አይሆንበትም። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋልና።
رُفِع القلم عن ثلاَثَةٍ عَنِ النَّاءِم حتَّ يَستيْقِظ وعنٍِ الصغيرِ يكبُرَ وعنِ المجنُونِ حتَّ يُفِيق
⭕️👉 ከሶስት ሰዎች ላይ ቀለም ተነስቷል
🔹የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ
🔹ህጻን ልጅ ብሉግ (አቅመ አዳም) እስኪደርስ
🔹እብድ እስኪነቃ ድረስ

📚ኢማሙ አህመድ፣ አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይና ዘግበውታል።

⭕️👉 ስለዚህ በዚህ ሀዲስ መሰረት አቅመ አዳም ያልደረሰ ልጅ ቀለም ስለተነሳለት ለምን አልፃምክም ተብሎ ስለማይጠየቅ ፃም በሱ ላይ ግዴታ አይሆንበትም ማለት ነው።

ነገር ግን ህፃኑ ቢፃም የሚችልና ጉዳት የማያመጣበት ከሆነ አስተዳዳሪዎቹ
እንዲጾም ያዙታል። ይህ በማድረጋቸው ልጁ ነገ ትልቅ ሲሆን እንዳይከብደውና እንዳይቸገር ይረዳዋል።

ሶሀቦች የአላህ ሱብሀነሁተአላ ውዳሴ በነርሱ ላይ ይሁንና  ልጆቻቸውን ትንሽ ሁነው ሳለ እንዲጾሙ  ያደርጉዋቸው ነበርበዚህ መልኩ ከፃሙ በኋላ ወደ መስጅድ ይዘዋቸው ይሄዱና ምግብ ትዝ ብሏቸው ማልቀስ ሲጀምሩ መጫወቻ ነገር በመስጠትና በማጫወት ምግብ እንዲረሱና እንዲዘናጉ ያደርጉዋቸው ነበር።

👉ስለዚህ በዚህ መሰረት ህፃናቶች እንዲፃሙ ማድረግና በዚህ ላይ ማለማመድ የሰለፎችን መንገድ ከመከተል ውስጥ አንዱ ነው።

🚫ስህተት 🚫

◾️ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ዲንን አያስተምሩምየወላጅ ትልቁ ሀላፊነት ማብላትማጠጣትና ማልበስ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ሊቀረፍ የሚገባ ትልቅ ስህተት ነው። ልጆች ከምግብ ከመጠጥ ከሌላም ነገር በላይ ዲን ያስፈልጋቸዋል። በዘመናችን ብዙ ሙስሊም ወጣቶች አጫሽ፣ ቃሚ፣ ጠጪ፣ ዱርዬ እየሆኑ ያሉት ከቤተሰብ ክትትልና ዲንን ካለማስተማር የተነሳ ነውብዙ ወጣቶች ጎልማሳነት እድሜ ላይ ሆነው አርካኑል ኢስላም አያውቁም፣ እስልምና የሚያበላሸውን አይለዩም። የነብያቶችና የሶሀባዎች ምንነትም ሆነ ስም አያውቁም። በተቃራኒው የካፊር ፊልም አክተርና ኳስ ተጫዋች አድናቂ በመሆን የመልእክተኛውን ሱና ትተው በፈረንጆች ፋሽንና ዲዛይን ተሸውዶ ይታያሉ። በአብዘሀኛው የዚህ ሁሉ መንስኤ ገና በልጅነታቸው ዲን ያለማሰረተመሰራችን ውጤት ነው።

◾️አንዳንድ ልጆች ለዲናቸው ካላቸው ፍቅርና ለኢባዳ ካላቸው ውዴታ የተነሳ መፃም ይፈልጋሉነገር ግን አንዳንድ ወላጆች በግድ እንዲያፈጥሩ ሲያደርጓቸው ይታያል። ይህም ሌላኛው ሊቀረፍ የሚገባው ጥፋት ነውበመፃማቸው ግልፅ የሆነ ጉዳት የማይደርስባቸው ከሆነና አቅሙ እስካላቸው ድረስ ቢፃሙና ቢለማመዱ የተሻለ ነው። ምናልባትም አንዳንድ ወላጆች ይህን በማድረጋቸው ለልጆቻቸው ያዘኑ መስሏቸው ሊሆን ይችላል። ሀቂቃው ግን ይህ ድርጊት ለነሱ ማዘን ሳይሆን እነሱን መበደል ነው። እውነተኛ የልጅ እዝነት ማለት፦
🔹ቁርአን ማቅራት
🔹ሀዲስን ማስተማር
🔹ሸሪአን ማሳወቅ
🔹በኢስላማዊ ተርብያ ማሳደግና
🔹ኢባዳን ማለማመድ
ነው።

◾️ክፍል አራት ይቀጥላል ኢንሻአላህ
               ፧              ፧
               ፧              ፧
     t.me/https_Asselfya
     t.me/https_Asselfya
Audio
"بُشْرَاكُم اليَومَ جنَّاتٌ"
ደህና እደሩልኝ!
05 الوسائل المفيدة للحياة السعيدة
  Abu Sufiyan Albenan
―ክፍል (⑤)
📚الوسائل المفيدة للحياة السعيدة
«ደስተኛ ሕይዎት ለመኖር የሚያግዙ ነጥቦች!»
የኪታቡ pdfለማገኘት👇
t.me/https_Asselfya/8029
~የበደለንን ይቅር ማለት
መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን
ማስተማር፣ቀናነትን መዝራት
ህይወትን ማደስ ነው።

~
~በሽታ ከሠው ወደሰው እንደሚጋባ ሁሉ
ጤንነትም ከሠው ወደ ሠው ይጋባል።
ጤናማ አስተሳሰብ
ካላቸው ሠዎች ጋር መዋል
ጤናማ ያደርጋል።

~
t.me/https_Asselfya
አብዝቶ የሚታገስ
በዉሳኔዉ አይፀፀትም

~
~ለምን የለይል ሶላት ሲቆም አያድርም ። ምቀኝነት ያለበት ሰው ሰላም የለዉም ።

~
t.me/https_Asselfya
~ወንድ ልጅ ቤት ሊሠራ ይችላል።
ምቹ መኖሪያ የምታደርገዉ ግን ሴት ልጅ ናት።

~
t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ #ህፃን (ለአቅመ አዳም) ያልደረሰ ልጅና ፃም ↪️ ክፍል ሶስት《0⃣3⃣ ህጻን ልጅ ብሉግ (አቅመ አዳም) እስኪደርስ ድረስ ፃም ግደታ አይሆንበትም። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋልና። رُفِع القلم عن ثلاَثَةٍ عَنِ النَّاءِم حتَّ يَستيْقِظ وعنٍِ الصغيرِ يكبُرَ وعنِ المجنُونِ…
⭕️👉ተከታታይ ስለ ረመዷን አህካም ዳሰሳ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
#አቅመ አዳም (بلوغ) የመድረሻ ምልክቶች

↪️{ ክፍል አራት《0⃣4⃣

📍በወንድም ሆነ በሴት ላይ ማንኛውም የሸሪአ ድንጋጌ ግዴታ (ዋጂብ) የሚሆነው አቅመ አዳም ወይም ብሉግነት ደረጃ ላይ ከደረሱ በኋላ ነው። ብዙ ሰዎች ለአቅመ አዳምነት ደርሰው ነገር ግን ምልክቶቹ በደምብ ካለማወቃቸው የተነሳ ገና ህፃን ነኝ በሚል እሳቦት ሶላት ፃምና ሌሎችም ግዴታ የሆኑ ኢባደዎች ላይ ሲዘናጉ ይታያሉ። በአላህ ፍቃድ እነዚህን ምልክቶች በቅደም ተከተል የምንቃኝ ይሆናል።

💠 ወንድ ልጅ አቅመ አዳም (ብሉግ) መድረሱ የምናውቅባቸው መንገዶች

◼️አንድኛ፦ መንይ (የዘር ፈሳሽ)

~አንድ ሰው ተኝቶም ይሁን ሳይተኛ በየትኛውም መልኩ መንይ (የዘር ፈሳሽ) ከወጣው ከዛን ሰአት ጀምሮ የሸሪዓ ድንጋጌዎች በሱ ላይ ግዴታ ይሆንበታል። ምክንያቱም ይህ ሰው አቅመ አዳም መድረሱ ከሚያሳዩ ምልክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የዘር ፈሳሽ ተገኝቶበታልና።

⭕️👉 ለዚህም መረጃው የአሏህ ሱብሀነሁተአላ ንግግር ነው
📌وَإِذَا بَلَغَ ٱلْأَطْفَٰلُ مِنكُمُ ٱلْحُلُمَ فَلْيَسْتَـْٔذِنُوا۟ كَمَا ٱسْتَـْٔذَنَ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ
ከእናንተም ሕፃናቶቹ ኢህቲላም (የዘር ፈሳሽ ሚያዩበት) ጊዜ ከደረሱ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት (ታላላቆቹ) እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡
📚 ሱረቱ አኑር (59)

🔹በሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
غُسلُ الجُمُعَةِ واجبٌ على كُلِّ مُحتلمٍ
ኢህቲላም (የዘር ፈሳሽ) የማየት ደረጃ ላይ በደረሱ ሁሉ የጁሙዓ ትጥበት ግዴታ ነው

📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

◾️ሁለተኛ፦ "ብልት አካባቢ ፀጉር ማብቀሉ"

~ይህ ፀጉር ከርዳድ ያለ ልስላሴ የሌለው ብልት አካባቢ የሚበቅል ሲሆን ይህም አንዱ ቡሉግነት የመድረሻ ምልክት ተደርጎ ይቆጠራል።

⭕️👉 ለዚህ መረጃው አጢያ አልቁረዝይ ፡፡የተባለው ሰሀብይ የተናገረው ንግግር ነው። እሱም እንዲህ አለ፦ "የቁረይዛ ዘመቻ ግዜ በመልእክተኛው ላይ ቀረብን የዘር ፈሳሽ ማየት ደረጃ ላይ የደረሰ ወይም ብልቱ አካባቢ ፀጉር ያበቀለ ሰው ይገደል ነበር ብልቱ አካባቢ ፀጉር ያላበቀለ ሰው ይተው ነበር።
📕ኢማሙ አሕመድና ነሳዒይ የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ ነው።

⭕️👉በኑ ቁረይዛዎች ከየሁድ ጎሳ የሆኑ አደገኛ የኢስላም ጠላቶች ነበሩበዚህ በበኑ ቁረይዛ ዘመቻ ጊዜ የተማረኩት እንዲገደሉ ተወስኖ ስለነበረ ለአቅመ አዳምነት ያልደረሱት ግን ይተው አይገደሉም ነበር። ለአቅመአዳምነት ለመድረስ በብልቱ ላይ ፀጉር ማብቀሉ ያለማብቀሉ ታይቶ ካበቀለ ትልቅ ስለሆነ ይገደላል። ካላበቀለ ደሞ ህፃን ነውና ይተው ነበር።

◾️ሶስተኛ፦ አስራ አምስት {15} አመት መሙላት

ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች ውስጥ አንዱ ካልታየ አስራ አምስት አመት እስኪሞላው የሚጠበቅ ይሆናልይህ እድሜ ላይ ሲደርስ ግን ቡሉግነቱ ስለሚረጋገጥ በሸሪአ ዋጂብ የተደረጉ ኢባዳዎችን የመስራት ግዴታ ይኖርባቸዋል።

▪️ ለዚህም መረጃው፦
⭕️👉አብደላህ ኢብኑ ኡመር እንድ አለ:- የእሁድ ዘመቻ ጊዜ በዘመቻው ላይ እንድሳተፍ መልእክተኛው ሰለሏሁአለይሂ ወሰለም ዘንድ ቀረብኩኝ። የዛኔ እድሜዬ 14 ነበር። ነገር ግን ለጅሀድ መልእክተኛው አልፈቀዱልኝም። በቀጣዩ አመት ላይ የኸንደቅ ዘመቻ ግዜ መልሽ ቀረብኩኝ። የዛኔ አስራ አምስት አመት ሞልቶኝ ነበርና ዘመቻ ላይ ተፈቅዶልኝ ተሳተፍኩ።
📚( ቡኻሪ ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል።)

~ሴት ልጅ አቅመ አዳም (ብሉግ) መድረሷ የምናውቅባቸው ምልክቶች፦

◼️አንድኛ፦ መንይ (የዘር ፈሳሽ)
◾️ሁለተኛ፦ "ብልት አካባቢ ፀጉር ማብቀሏ"
◾️ሶስተኛአስራ አምስት {15} አመት መሙላት
◾️አራተኛ፦ ሀይድ (የወር አበባ) ማየት

~ ከላይ ያየናቸው ወንድ ልጅ አቅመ አዳም (ብሉግ) መድረሱ ከሚጠቁሙ ምልክቶች ውስጡ አንዱን ካየች ቡሉግ መድረሷ የሚታወቅ ሲሆን ከወንድ በተጨማሪ ሀይድ ማየት ይገኝበታል።

⭕️👉አንድ ሴት ልጅ በየትኛውም የእድሜ ክልል ደረጃ ላይ ሀይድ ካየች ብሉግነት የመድረሷ ምልክት ስለሆነ በግዴታነት የተደነገጉ የተለያዩ የኢባዳ አይነቶች መፈፀም በሷ ላይ ግዴታ ይሆናል።

⭕️👉ማሳሰቢያ!!
    
①)–አንድ ሰው ብሉግ ደረጃ ደረሰ ለማለት የግድ ሁሉንም ምልክቶች መታየት አለባቸው አይባልም። ይልቁንስ አንዱን ምልክት ከታየ በቂ ማረጋገጫ ነውና በኢባዳ ላይ የተገደደ ይሆናል።
②)–አንድ ሰው አቅመ አዳምነት ደረሰ ለማለት የግድ አስራ አምስት አመት የሚጠብቁ አሉ ይህ ስህተት ነው። አንድ ሰው የዘር ፈሳሽ ካላየ፣ ፀጉር ካላበቀለ፣ ሴቷም ሀይድ ካላየች ያለው አማራጭ አስራ አምስት አመት መጠበቅ ነው። ነገር ግን በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ አንዱን ምልክት ቀድሞ ከታየ ያ በቂ ነውና ብሉግ ደረሰ ይባላል።
③)–አንድ ሰው ረመዷን ውስጥ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ብሉግ መድረሱን ካረጋገጠ መጀመርያውኑ ፃሞ ከነበረ በዛው ፃሙን ይቀጥላል። ፃመኛ ካልነበረ ደሞ ከዛ ሰአት ጀምሮ ከምግብና መጠጥ መታቀብ ይኖርበታል ነገር ግን ቀዷ የማውጣት ግዴታ የለበትም።
            ፧              ፧
            ፧              ፧
    t.me/https_Asselfya
   
t.me/https_Asselfya
~ጣፋጭ ቲላዋ

በቁርአን እንገሠፅ

~
ውድ ወንድሞችና እህቶች መቸም አዝካረ ሶባህ እንደማትረሱ ተስፋ አለኝ ።
ዚክር የደረቀችን ልብ ያረጥባል የረጠበች ልብ ይበልጥ ወደ አላህ እንድትቀርብ ያደርጋታል።


🖊ወንድማችሁ አቡ ዓኢሻ ነኝ
https://t.me/Abuebrahim22322
~አላህ ጋ መገናኘትን የወደደ አላህ ከሱ ጋ መገናኘትን ይወዳል።ከአላህጋ መገናኘትን የጠላ አላህም ከሱጋ መገናኘትን ይጠላል።

የአላህ መልእክተኛ ይሄን ሲሉ እናታችን አኢሻ እንድህ አለች ፦ሞት ጥላቻ ነዉን?ሁላችንም ሞትን እንጠላለን አለቻቸዉ የአላህ መልእክተኛ ይህ አይደለም አሏት።ነገር ግን አማኝ ጣራ ሞት ሲደርስ በአላህ ራህመት ፦በአላህ ዉዴታ በጀነት እፊቱ ተመስሎለት ቁጭ ይልለታል።ስለዚህ አላህን መገናኘት ይወዳል። በዚ ተቃራኒ ጠማማዉ ጣራሞት ሲደርስ ፊለፊቱ ጀሀነም የአላህ ቁጣ ቅጣት ስለዚህ አላህን መገናኘት ይጠላል።አላህም ከሱጋ መገናኘትን ይጠላል።

إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُوا۟ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسْتَقَٰمُوا۟ تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا۟ وَلَا تَحْزَنُوا۟ وَأَبْشِرُوا۟ بِٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ

~