💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
✅↪️ሰለፍይ ማለት ምን ማለት ነው?? በሰለፎች ጎዳና መጓዝ ግደታ ይሆናልን?
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
አስ ስለፍየቱ " ማለት የሷሀባዎች ፣የታብዕዬች ከተከበረው ክፍለ ዘመን ላይ የነበሩ ሰዎችን አቂዳ የነርሱን ግንዛቤና ባህሪ አጥብቆ መያዝና መጓዝ ማለት ነው።
💎እያንዳንዱ ሙስሊም በዚህ ጎዳና ላይ መጓዝ ግድ ይለዋል።

✅አላህ ሱብሀነሁተዓላ እንድህ ብሏል
وَٱلسَّٰبِقُونَ ٱلْأَوَّلُونَ مِنَ ٱلْمُهَٰجِرِينَ وَٱلْأَنصَارِ وَٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُم بِإِحْسَٰنٍۢ رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ{{التوبة ١٠٠}}

➿➿➿➿➿➿
👉አንዳንድ ሰዎች ሰለፍያን እንደሌሎች አንጃዎች የሚቆጥሩ አሉ። ይልቁንም ሰለፍያ ወደ ቀደምት ሶሃባዎች የምትጠጋ የነርሱን ጎዳና ተከትላ የምትጓዝ ጀመዓ ነች።

ይህን አስመልክቶ ኢብን መስዑድ ረድየሏሁ አንሁ እንድህ ብሏል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በሒወት ያለ አይታመንም መከተል የፈለገ ከአሁን በፊት በሞቱት ይከተል እነርሱም የረሱል ሶሀቦች ናቸው። ልባቸው በጎ እውቀታቸው ጥልቅ የማያውቁትን እናውቃለን ብለው የማይፍጨረጨሩ ናቸው። {ጃሚዕ አል በያኒል ኢልሚ ወፈድሊሂ ገጽ 419((ሚሽካቱል መሷቢህ :-1/67 ))አል ሂልያ :1/305))

✅✅አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ ዓን አስኢለቲል መናሒጀል ጀዲዳህ ከሚለው ኪታብ የተወሰደ
〰〰〰〰〰〰〰〰
📕አዘጋጅ ዶክተር ሷሊህ ብን ፈውዛን ብን ዓብደላህ አል ፈውዛን

✍ቢንት ሰዒድ
🔻የአላህ መልእክተኛ ﷺ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


"አላህ በባሪያው ላይ መልካም ነገርን ሲፈልግ ከመሞቱ በፊት ያጠራዋል ሲሉ ሶሓቦችም፤ የባሪያው መጥራት ምንድነው ሲሉ ጠየቁ? እሳቸውም፤ እስኪሞት ድረስ ለመልካም ስራ ይመራዋል" ይላሉ።

ጦበራኒ ዘግበውታል አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።
ፅኚ በሂጃብሽ !!
🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋🖋
በሱረቱል አህዛብ በደማቅ ተከትቧል፤
ከአንገትሽ ቀናበይ ታሪክሽ ተውቧል፤
ድንቅ ነው ኢስላምሽ ከአምላክ የተሰጠሽ፤
ቅይጥ የሌለበት ጥርት ያለ ሀብትሽ፤
እስኪ መለስ በይ እልፍ አመታትን፤
ትእዝዛ ሲመጣ ወህይ ከአምላካችን፤
እንዴት ነበረ እስኪ ድንቁ ታሪካችን፤
የሂጃቡ አያህ ሲወርድ ለአለማት፤
ያኔ ሲታዘዙ እኒያ ሶሀቢያት፤
ሀገሩን አስዋቡት በጥቁር ቀለማት፤
በኒቃብ በጅልባብ አበሩ በውበት።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
አንቺስ ምንሽ ሞኙ ማማር የምትጠይው፤
በሂጃብ ተውበሽ አምላክሽን ታዘዢው፤
አዎ ታዘዢው ሀያሉን ህልምሽ እንዲሳካ፤
በዱንያም በአኼራም እንድትይ ፈካ፤
አትስጊ በፍፁም ባል ይጠፋል ብለሽ፤
እዝነቱን ፈልገሽ ኒቃብ በመልበስሽ፤
አንቺ ጀግና ሆነሽ ለትእዛዙ ካደርሽ፤
ቤትሽን ያንኳኳል ይቆማል ከበርሽ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ኢልምሽን ተማሪ ጠዋት ማታ ድከሚ፤
ጅህልናን ለመግፈፍ በደሊል ታከሚ፤
በሰላሙ ጊዜ ስንቅሽን ካልሰነቅሽ፤
ጎታችሽ ይበዛል አንችም ትሄጃለሽ፤
ስለዚህ እህቴ ኢልም ላይ ጠንክሪ፤
አሰሱን ገሰሱን ቆሼ ፍርፋሪ፤
እንደ እስፓንጅ አትምጠጭ ፈጣሪሽን ፍሪ፤
አህባሹ ሲመጣ ከአህባሽ አትስፈሪ፤
ከኢኽዋን ዘናጩ ከሱናው ርቆ፤
ላይሽ አልመኝም ያ ውበትሽ ደርቆ፤
ከሙመይእ ለስላሴ እወደድ ባይ ከንቱ፤
ላይሽ አልመኝም ስትቀሪ ከንቱ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ያንቺ መታለልሽ መሸወድ ሳይበቃ፤
ትውልድ ይበላሻል የኢስላም ውድ እቃ፤
የነገውም ተስፋ ያ እንቁ ፀሀይ፤
አንድነት ይሰብካል ከኢኽዋን ስትውይ፤
ከተውሂድን ይርቃል ከሱና ሰማይ፤
ከአህባሽም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል፤
ከተውሂድ ርቆ በሽርክ ይደበቃል፤
በዱአው አሳቦ ከሱስም ይወድቃል፤
ከድቤ ዳንኪራ አጥር ይወሸቃል፤
ከተብሊጉም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል፤
ኡሉህያን ርቆ እድሜውን ይፈጃል፤
በ 3 በ40 ቀን በተብሊግ ፍከራ፤
ወገኑን ሊታደግ ተውሂድ ሳይጣራ፤
እድሜውን ይፈጃል አንድ ውል ሳይሰራ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ለዚህ ሁሉ ስህተት ምክንያቷ አንቺ ነሽ፤
በኢስላም ስር ውለሽ መንሀጅ ስላልገባሽ፤
መሰረት የጣልሽው ካለቦታው ሆኖ፤
ግንቡን አፈረሽው የትም ቀረ ተኖ፤
ሰንደቅሽ ከፍ ብሎ ሁሌም እንዲያምርብሽ፤
እዛም እዛም አትበይ ይለይ መንሀጅሽ፤
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
እውነቱን ልንገርሽ የሂጃብሽን ዋጋ፤
ሊያናግርሽ ያፍራል ካንቺ የተጠጋ፤
መናቅኮ አይደለም ክብር ስላለው ነው፤
ሊቀርብሽ ያልቻለው በሩቁ የሸሸው፤
አንቱታን አተረፍሽ በ15 አመትሽ፤
ድል አጎናፀፈሽ ኒቃብ በመልበስሽ፤
ወለም ዘለም አትበይ ፅኚ በሂጃብሽ፤
ፊትናም አትፍጠሪ ተደበቂ ቤትሽ፤
ምድር ሁኝ ለባልሽ ሰማይ እንዲሆንልሽ፤
ክብርን አጎናፅፊው እሱም እንዲያከብርሽ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ደሞ ሴቶች አሉ ፀጉር የሚቆልሉ፤
ሂጃብ ለበስን ብለው የሚንቀዋለሉ፤
ረሱል ተራግመዋል ብለሽ ስትነግሪያቸው፤
አቦ አታጠባብቂ እነሱን ተያቸው፤
ገና አልሰለጠኑም ኃላ ቀር ናቸው፤
ብለው ያሾፋሉ ሞኛ ሞኝ ናቸው፤
ፀጉር መቆለሉ ደሞም መወጣጠር፤
ቅርፅን ማሳየቱ ሂጃብን መወርወር፤
ይሄ አይደል መስፈርቱ ለትዳርሽ መስመር፤
ይልቅማ አዳምጪኝ ለትዳርሽ ማማር፤
ዘላቂው መፍትሄ በሰላም ለመኖር፤
ሁሌ ለመወደድ ሁሌም ለመፈቀር፤
ሂጃብ ነው ሚስጥሩ ልቀቂው ከላይሽ፤
ሀያእም ተላበሽ አርጊው ጎረቤትሽ፤
ፈላስፋም አትሁኝ ማስረጃን ሰንቂ፤
ለምትሰሪው ስራም ደሊሉን እወቂ፤
ይህንን ካደረግሽ እህቴ እወቂ፤
ፍፁም አትወድቂም የለሽም ነቅናቂ።

https://t.me/aselefey
ጠንካራ ሰለፊያ ላይ ሁን!!
በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን
👆👆👆
#ጠንካራ ሰለፊያ ላይ ሁን!!

🔶ደቡብ ክልል በስልጤ ዞን በውልባራግ ወረዳ በደመቄ ቀበሌ
በዋቤራ ዐብዱልዐዚዝ መስጅድ የተደረገ ሙሐደራ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)
https://t.me/aselefey
Audio
👉አጭር ምክር ቃኢዳ ኑራንያና ቁርአን ለሚቀሩ ወንድም እህቶች

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
የዱዓ አንገብጋቢነት!
በሸይኽ ዐብዱልሐሚድ
# ቆይት ታለ ወሳኝ የሆነ ሙሐደራ!

ርዕስ፦ #የዱዓ አንገብጋቢነት #በታላቁ #በረመዷን ወር!

➡️ ዱዓ እንዴት ማድረግ እንዳለብን እና ምን መጠየቅ እንዳለብንም ተጠቅሷል።
•≈≈≈≈≈≈≈≈•📓🖇📓•≈≈≈≈≈≈•

🎙 #በሸይኽ #ዐብዱልሐሚድ አል– ለተሚይ[ሀፊዘሁላህ]

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ

📲 👇

https://t.me/aselefey
«ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም! ይልቁንስ በአንተና በአላህ መካከል ያለውን አሳምር! ለሰወች ደንታ አይኑርህ»።
ኢማሙ ሻፊዒ (ረሂመሁሏህ)

ምንጭ፦📗ጦበቃቱ ሻፊዒያህ (184-2)
ቢድዓ
ኢብኑ ሙነወር
ተውሒድ/ዐቂዳ/
ሐዲስ //ሙሐደራ ከሱና ኡስታዞች እንለቃለን ወደ ቻናሉ ይቀላቀሉ 👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻👇🏻

منهج السلفية منهج الحق والنجاة في الدنيا والأخيرة

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና
https://t.me/aselefey
ዲን ያላት ሴት የምትባለዋ የትኛዋ ሴት ነች ...??
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሼኽ ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ፦

✅🔻ዲን ያላት ሴት የምትባለዋ - የአላህን ትእዛዝ ቀጥ አድርጋ የምትፈፅም፣ የባሏን ሀቅ የምትጠብቅለት የሆነችዋ እና እንዲሁም አልጋውን፣ ልጆቹን፣ ገንዘቡን የምትጠብቅለት የሆነችዋ ነች።

🔹 እንዲሁም አላህን በመገዛት ላይ {በዒባዳ ላይ}} የምታግዘው፣ ሲረሳ የምታስታውሰው፣ ሲዳከም የምታነቃው፣ ሲቆጣ የምታስደስተው የሆነችዋ ሴት ነች፡ ይች ነች ዲን ያላት ሴት የምትባለዋ።

📒 ኪታቡ ዘዋጅ (20)
ሃፊዝ ኢብኑ ረጀብ (ረሒመሁላሁ) አኽላቅ {{ስነምግባር}} ሁለት አይነት ነው ይላሉ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
👉.ከአላህ ጋር ያለ ስነምግባርና
👉ከሰዎች ጋር ያለ ስነምግባር ነው።
✅🔹ከአላህ ጋር ያለን ስነምግባር እሱን በብቸኝነት ልትገዛና በእርሱ ላይ ቅንጣትንም ላታጋራ ነው።

↪️ከሰዎች ጋር ያለ ስነምግባርወደ እነሱ ጥሩ ልትውል ነው። ፈገግ ልትልና የተለያዩ ጥሩ ስነምግባሮችን ልታሳይ ነው።


↪️ ታድያ ይህ እንዲህ ከሆነ አንድ ሰው እነኚህ ሁለት የስነምግባር ችግሮች ካሉ መጀመሪያ ማስተካከል ያለበት ከዓላህ ጋር ያለውን ስነምግባር ነው።

🔻 ምክንያቱም ትልቁ አህላቅ {{ስነምግባር }}ከዓላህ ጋር ያለን አህላቅ ነው።አላህን በብቸኝነት ማምለክና በሱ ቅንጣትን አለማጋራት

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና
https://t.me/https_Asselfya
የልጆች ሓቅ በኢስላም ምንድን ነው
በኢብኑ ሙነወር
ወሳኝ #ሙሐደራ

ርዕስ  â†ˇâ‡Łâ†ś
የልጆች #ሐቅ በኢስላም

🎙 በኡስታዝ #ኢብኑ_ሙነወር ሀፊዘሁሏህ

↪️ የልጆች ሐቅ የሚጀምረው ከትዳር በፊት ነው! ምክንያቱም ጥሩ ሚስት መምረጥ ከሐቃቸው ነውና

↪️ በርካታ ቁም ነገሮች ተዳሰውበታል።
ይደመጥ
Audio
🔁 سورة الكهف 🔁
🔺ማራኪ የሱረቱል ከህፍ ቂርአት
🎙القارئ محمد صديق المنشاوي
✅✍ውዷ እህቴ ሀያዕ ካለሽ ከማንም በላይ ውድ ነሽ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሀያዕ ማለት ጨዋነት አይን አፋርነት መተናነስ ማለት ሲሆንሀያዕ የኢማን ግማሽ ነው።

↪️አንድ ሴት ልጅ ሀያዕ ካላት መልካም ሥነ—ምግባርን ትላበሳለች።

💎መልካም ሥነ —ምግባርን ስንል
👉 በንግግሯ :-
👉በአለባበሷ :-
👉በአይን አይናፋርነቷ።
👉ሁሉ ነገሯ ያማረና የተዋበ ልቧ በኢማን የታነፀ ይሆናል ።

↪️ሴት ልጅ በአለባበሷ እራሷን ከወንጀል ጠብቃ ሌሎችንም ወንጀልውስጥ እዳይገቡ ተምሳሌት ትሆናለች ።

🔹ሀያዕ ያላት ሴት መረጋጋትን ትጎናፀፋለች እሱም ሰኪና ይባላል።

👉አላህ ሱብሀነሁተዓላ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል

አላህም በመልክተኛው ላይና በምእመናኖቹ ላይ
እርጋታውን አወረደ ""

🔺አንዲት ሴት በሀያዕ ከታነፀች ከብዙ ክፉ ነገሮች እራሷን ታድናለች።
🔺ሀያዕ ከሌላት ግን መልካም ነገሮች ሁሉ ከእርሷ ይርቃሉ
🔺ልቦቿ ይደርቃል ኢማን ታጣለች አይናፋርነት አይኖራትም። የፊትናና የወንጀል መንስዔ ለእሷም ለሰዎችም አጋላጭ ትሆናለች።
↪️የሴቶች አህዋል መስተካከል የህብረተሰብ የመስተካከል ሚስጥር ነውና።
↪️ሀያዕ ከአላህ ዘንድ ተቅዋን ይጨምራልናል
↪️ከመልካም ባህሪዎች ያደርገናል
↪️በመጥፎ ሰዓትም በደስታ ጊዜ አላህ በትእግስት ታመሰግናለች።
فَصْبر صبْرًا جميلا
🔺መልካም ትግስትን ታገስ።
✍ቢንት ሰዒድ

Join us👇
@menhajselefiya123
@menhajselefiya123
🔻"ረሱል(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
↪️የተራበን መግብ
↪️የተጠማን አጠጣ
↪️ሰዎች መልካም እንዲሰሩና ከመጥፎም እንዲከለከሉ እዘዝ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
↪️ይህን ማድረግ ካልቻልክ ምላስህ መልካም ይናገር።
✅አለዝያ ዝም በል¡>>
هل يجوز للمرأة أن تعمل مذيعة
Shaik Abu Zer Hassen
◾️ሴት ልጅና ሶሻል ሚድያ
➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ሴት ልጅ ዜና አቅራቢ ሆና ስራ መስራቷ እንዴት ይታያል⁉️
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
↪️ ሴቶች በራዲዮ ጣቢያ በቴሌቪዥንና በዩቱብ ቻናል ስርጭት መቅረብ⁉️
@UstazAbuzarhassenAbutolha
@UstazAbuzarhassenAbutolha
👉እነዚህና ሌሎችም መሰል ነጥቦች የተዳሰሱበት ምክር ነው።

🎙በሸይኽ አቡዘር ሀሰን (አቡ ጦልሓ)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
✅ነፍሱ ከዒባዳ መሰላቸቷን ያስተዋለ፤ኢስቲግፋር ያብዛ። ማንኛውም ሰው ዒባዳን መፈፀም የሚሳነው በሰራው ወንጀል ምክንያት ነው።
أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ، وَأَتُوبُ إِلَيْهِ.
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya