💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
✅ውበትን በሜካብ ሳይሆን በኢማን ታገኚዋለሽ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✅አንዲት አማኝ እንስት በጀነት ውስጥ
ከሁረል አይን የበለጠ ቆንጆና በላጭ ናት።

♻️ ኢማሙል ቁርጡቢ :- አት ተፍሲር (16_154)
💢በራስ መተማመን and ተውሒድ❓
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በራስ መተማመን ማለት ከሌላ አካል ምንም ነገር ሣይፈልግ የምንፈልገውን ነገር እራሤ አደርገዋለሁ ወይም አሣካዋለሁ ብሎ ማሰብ ነው ከሌላ አካል ስንል ከፍጡርም ሆነ ከፈጣሪ ማለት ነው።
🔹ከፈጣሪ ከከጀለ ተውሒዱን ጠበቀ
🔹ከፍጡር ከከጀለ ሽርክ ላይ ወደቀ
🔹በእራሱም ከተማማነ ያው ሽርክ ላይ ወደቀ
ምክኒያቱም ፍጡር ሁል ጊዜ ከፈጣሪው ከጃይ መሆነ አለበት ከጃይም ነው።
ለምሣሌ በእኛ ላይ ያሉ ፀጋዎችን እንመልከት፦
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
እውቀትን እና ሐብትን ወደ እራስ ማስጠጋት ማለትም
▪እኔ አዋቂ የሆንኩት ስለተማርኩ ነው ማለት።
▪እኔ ሐብታም የሆንኩት ስለ ሰራሁ ነው ማለት።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በሱረቱል- ቀሶስ አላህ እንድህ ይላል፦
قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلْمٍ عِندِىٓ
ሀብቱን«የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው አለ፡

✅በርግጥ አዋቂ ለመሆን መማር አለብኝ
ሐብታምም ለመሆን መስራት አለብኝ ነገር ግን አንተ 24 ሰዓት ወኢም 24 አመት ስለሰራህ ሐብታም አቶንም አላህ ሐብታም እንድትሆን የረዳህ ቢሆን እንጅ። እውቀትም ቢሆን አንተ አለምን በሙሉ ዙረህ ተሽከርክረህ ስለተማርክ አዋቂ አቶንም አላህ እንድታውቅ ስላደረገህ ቢሆን እንጅ።
🔻እነዚህ ነገሮች በአንተ ጥረት እና ፍላጎት የመጡ ሣይሆኑ የአላህ ፀጋዎች ናቸው። ሀብት ፀጋ ነው እውቀት ፀጋ ነው የፀጋው ባለቤት ዴግሞ አላህ ነው።

በሱረቱል-ነህል ላይ አላህ እንድህ ይላል፦
وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ ٱللَّهِ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فَإِلَيْهِ تَجْـَٔرُونَ
"ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ነው፡፡ ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደርሱ ብቻ ትጮሃላችሁ፡፡
✅ይሕ (አያ) ሁለት ነገሮች ያስተምረናል ...
1.እኛ ላይ ያለው ፀጋ ሁሉ የአላህ መሆኑን
2.ችግር (አደጋ) ቢያጋጥመን በራሣችን መወጣት ሆነ (መዳን) እንደማንችል ያስረዳል።
✅ስለዚህ ሙዕሚኖች ይሰራሉ ( ሰበብ) ያደርሳሉ እንደሚያሳካላቸው በጌታቸው ይተማመናሉ ነገራቸውንም ወደ አላህ ያስጠጋሉ...
‏وَأُفَوِّضُ أَمري إِلَى اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ بَصيرٌ بِالعِبادِ
"ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፡፡ አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና፡፡

በጌታቸው ይመካሉ ልክ አላህ እንዳለው።
وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا
"በአላህም ላይ ተመካ፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡

▪ኢብኑ ተይሚያ እንድህ አሉ፦
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ተውሒድ በነከጠረ ቁጥር ኢማኑ እና በአላህ ላይ መመካቱ እየጠነከረ ይሄዳል። (መጅሙዕ አል ፈታዋ 35‒28)

🔻አንድ ሰው መጥቶ በራሷ
#የምትተማመን ጀግና ሴት ሁኚ ቢለኝ ምክሩን በጭራሽ አልቀበለውም ምክኒያቱም እኔ በጌታዬ በአላህ እንጅ በራሤ በጭራሽ አልተማመንምና።

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መመካትና መተማመን ያለብን በአሏህ ብቻ መሆኑን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
(ولا تكلني إلى نفسي طرفة عين)
«የአይን ቀፀብታ ያክል ወደ ነፍሴ አታስጠጋኝ»

https://t.me/https_Asselfya
📌♻️ ለሱና እህት ወንድሞቻችን ምን ያክል ውዴታ አለን❗️

🔵 قال ايوب السختاني رحمه الله:
〰〰〰〰〰〰〰✍✍✍〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰✍✍✍〰〰〰〰〰〰〰

📌《إنه ليبلغني موت الرجل من أهل السنَة ؛ فكأنما سقط عضو من أعضائي》

📌♻️ አዩብ አሰህቲያኒ (አላህ ይዘንለት) እንዲህ ብሏል።

🔺 የአንድ የአህለሱና (የሱና ተከታይ) የሆነን ሰው ሞት ሲነገረኝ ልክ ከሰውነቴ የሆነ አካል እንደጠፋኝ (እንደወደቀኝ) ያክል ይሰማኛል።

📚 الحلية ٣/٩

📌♻️ የሱና ወንድምህ ከልብህ ውደደው። ዱንያ ከያዘችው ጥቅም ሁሉ እሱ ይበልጣል። የሱና ወንድምህ ክብርህ ነው። በትንሽ በትልቁ ጀርባ ከምትሰጠው ቀርበህ ምከረው፤ ቅረበው፤ አትሽሸው፤ ለጠላቶቹ አሳልፈህም አትስጠው ከነሱ ጋርም ሆነህ አታብርበት ክብሩንም ጠብቅለት። ልትበድለው ልታዋርደው ልትሳለቅበት ይቅርና ሲተች፣ ሲታማ፣ በመጥፎ ሲነሳ ስትሰማ ከሱ ተከላከል። ስህተቶቹን አታጉላ ይልቁንስ ሚደበቅና በራሱ ብቻ ሚቀር ከሆነ ሰትርለት ደብቅለት። አንተ ማለት እሱ እሱ ማለት አንተ እንደሆንክ አስብ። አንድ የሰውነት አካልህ እንደሆነም ቁጠረው። ሁሌም በውስጡ ደስታ ለማስገባት ሞክር። አቅምህ በቻለው እሱን አዛ ከማድረግ ተቆጠብ። በሱና ወንድምህ ላይ አጉል ጥርጣሬን ተው። ስንትና ስንት መልካምነት እያለው በውሉ ባልታወቀ ወሬ ስሙን አታጥፋ። እውነቱን ልንገርህ ሞትኩልህ፣ ያላንተ መኖር አልችልም ከሚልህ ሙብተዲእ ምንም ችግር ቢኖርበት ይህ የሱና ወንድምህ ይሻልሀል።

✍ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
📌♻️ ህይወትህ አላህን ወደ መታዘዝ የማይመራህ ከሆነ ከምድር በላይ ከመሆን ይልቅ ከምድር በታች ላንተ ኸይር ነው።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
✅ቅምም ያለች ምክር✅

👂👂👂👂👂
🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
متن_كشف_الشبهات___عبدالعزيز_الصيني(360p) 20210722_154839
<unknown>
ከሽፉ ሹቡሃት ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ቢን ዓብዱልወሓብ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
የኪታቡ አረብኛ ንባብ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Recitation_of_Al-Qawaa'id-ul-Arba'(360p) 20210718_104310
<unknown>
ቀዋዒዱል አል አርባዕ ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ቢን ዓብዱልወሓብ አረብኛ ንባብ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️የቀራናቸውን ኪታቦች እያስተነተን ስናዳምጠው የበለጥ እንረዳለን! እንድሁም ለሂፍዝ ይጠቅመናል ብየ እላለሁኝ።

ሌሎች ድምጾችን ለማግኘት Join ይበሉ
👇👇👇
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
↪️ ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ
- رحمه الله تعالى -:
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
እንዲህ ይላል

💧አላህን ፈሪ ለመሆን ወንጀል አለመስራት መስፈርት አደለም። ከወንጀል ጥቡቅ መሆንም የግድ አደለም። ነገሩ እንደዛ ቢሆን ኖሮ በኡማው አንድም አላህን ፈሪ አይኖርም ነበር።

↪️ ነገር ግን ከወንጀሉ የቶበተ አላህን ፈሪ ይሆናል። ወንጀሉን ሚያስምር ሌላ መልካም ስራ የሰራም ሰው አላህን ፈሪ ሚለው ውስጥ ይገባል።》

📓📔 |[ሚንሀጁ ሱና (٧ / ٨٢) ]
📌✅ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ የሚባል ዚክር‼️

📌✅لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرُ، اَللَّهُمَّ لاَ مَانِعَ لِمَا أَعْطَيْتَ، وَلاَ مُعْطِيَ لِمَا مَنَعْتَ، وَلاَ يَنْفَعُ ذَا الْجَدِّ مِنْكَ الْجَدُّ.

↪️ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡አንድ ነው፡፡ አጋርም የለውም፡፡ ስልጣን የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የሚገባው ለርሱ ብቻ ነው፡፡ አላህ ሆይ! አንተ የሰጠኸውን ነገር የሚከለክል የለም፡፡ የከለከልከውን የሚሰጥ የለም፡፡ የክብር ባለቤትከአንተ ዘንድ ክብሩ ቅንጣት አይፈይደውም፡
አላውቃትም በለኝ
▬▭▬
አላውቃትም በለኝ እንድነግርህ እኔ፣
አላውቃትም በለኝ ላስረዳህ በወጉ፣
ያችን የስደት እንሰት አይገባትም ያልከው የተውሂድ ማረጉ፣
ትማራለች በጣም ልንገርህ ካሁኑ፣
ትማራለች በጣም ተውሂድ ትማራለች፣
ቤተሰብ ልቀይር ወይም ልትቀየር በርግጥ ተሰዳለች።
°°~~__~~°°__~~__°°
አይሆንም ነበረ በርግጥ መሰደድ፣
አይሆንም ነበረ በርግጥ ያለመህረም
#ከቤት_መራመድ፣
ያም ሆነ ያም ሆነ ወታለች በግድ፣
እናም አንተ ወንድሜ አትበላት ጥርዝ፣
እሷም አትከፋ ልቧ አይመረዝ፣
ይልቅ ጠቁምላት ተውሂድን ትያዘው፣
ይልቅ ተርጉምላት አትበላት ጥርዝ፣
በማይሆናት ታሪክ ልቧ አይመረዝ፣
°°~~__~~°°__~~__°°
#ወይ አንተ ወንድሜ ልንገርህ ሚስጥሩን፣
አላውቃትም በለኝ ላስረዳህ ትርጉሙን፣
አላውቃትም ብሎ መናገር ትልቅ ነው፣
ጥርዝ ጥርዝ ማለት በጭፍን ምንድነው፣
አይወክልም እሷን ያችን ስደተኛ፣
ተውሂድ ትማራለች በትርፍ ጊዜዋ በጭራሽ ሳተኛ፣
አይወክልም እሷን ያችን የተውሂድ ሊቅ፣
አታውቃትም በቃ አርፈክ ተቀመጥ፣
°°~~__~~°°__~~__°°
አንች የዱባይ እንሰት የስደት እህቴ፣
አዳምጭኝ ልንገርሺ ያውም ካንደበቴ፣
አያውቅሺም አይደል? ያ የወንድ አልጫ ፣
ሁሌም ያደረገው የስልኩን እስቶሬጅ #የሴት_መቀመጫ፣
°°~~__~~°°__~~__°°
አታስቢ ለሱ ይልቅ በርቺ እህቴ፣
ተውሂድን ቅሰሚው ያው ከፊት ለፊቴ፣
አታውቀኝም በቃ ውጣ ከመስመሬ፣
ተውሂድን ተምሬ ልግባ ወዳገሬ፣
ብለሺ መልሺለት ለዛ ለተንኳሹ፣
ለዛ ለቦዘነው ጫትቤት ለሚያመሹ፣
°°~~__~~°°__~~__°°
አንች የስደት እንሰት ያረቢቷ ቆንጆ
እንድህ ጥርዝ ያሉሺ ከየት የመጣነው ከምን ተኮረጀ፣
አላውቅም በይና ንገሪው መልስሺን፣
እሱም አይጠጋ በደንብ ታወቀ ተውሂድ መማርሺን፣
መስፈርቱ ሌላነው ሊናገር ያሰበው፣
ተውሂድ ያልተማረ ሰው ማደናገር ነው፣
°°~~__~~°°__~~__°°
አላውቅህም በዪው ንገሪው መስፈርቱን፣
ተውሂድን ንገሪው ያዙርልሺ ፊቱን፣
እረ ምን ልንገርህ አዳምጠኝ በይና፣
አይደንቀንም በይው የኛ መሰደድ፣
ይልቅ ተርጉሚለት ወየት ነው ያለከው
በይና ጠይቂው ይልሻል በረንዳ፣
ጥርዝ ከማለትህ ይልቅ ተነስና በል መስጂድ ተው ሂዳ፣
አይወድም ይችችን መጣሺበት ባይኑ፣
አልገባሺም ነበር አህባሽ ነው ፊቱኑ፣
አህባሺ ከሆነማ አልፈርድም በለኝ፣
ትረሳኝ የለወይ ጫታችሁ ሲገኝ።
°°~~__~~°°__~~__°°
እናልህ ወንድሜ ልቋጨው ነገሩን
ድሮም አውቀዋለሁ አህባሺና ኢኽዋን ሰው መሳደቡን፣
ብየ ነበር እንጂ ያለኝ ሰለፍያ መቸ እኔ ሳወራ የንዳንተን አምሳያ፣
ይመክራኛል በቃ ያ የተውሂድ ነብር፣
መረጃን በመጥቀስ ሰው ሳያደናግር፣
°°~~__~~°°__~~__°°
አንተ የተውሂድ ጀግና የነቢ ወራሺ ፣
አንተ የተውሂድ ጀግና የተውሂድ አንበሳ አንተ የት ሂደህ ነው ዳዓዋ ሊያደርግልኝ አህባሹ ተነሳ፣
በል ንቃ ተንግዲህ ንገረኝ ሀቄን፣
እኔም ልተናፈስ ካወኩ መስፈርቴን፣
አያውቁም አይደለ እኒያ ሰለፍዮች ፣
የውሸት መረጃ አህባሺም ወትውቺ ጥርዝ ጥርዝ በይ ያላንድ መረጃ።
➲➲➲
እናም ይበቃኛል ነገርኩ ሀሳቤን ፣
እኔም አቁሚያለሁ ያላንዳች መረጃ ጥርዝ መሳደቤን ።

ለእህቶቼ አድርሱልኝ ባረከላሁ ፊይኩም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📝በወንድም ኢዘዲን
➬➬➬
https://t.me/https_Asselfya
Audio
✅ማራኪ ቲላዋ
➖➖➖➖

🌷 سورة الزخرف
📚ቁርኣን የሚያዳምጥ ሰው "ከሚቀራው ሰው ጋር እኩል አጅር(ምንዳ) ያገኛል።

𒊹︎︎︎ሼኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ

نور على الدرب (٣٥١/٢٦)


ወተህ ላትመለስ ትችላለህና ተዘጋጅ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
በየትኛው ሀል ሆነህ እንደምትሞት አታውቅምና!!

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ምርጫዬ ሷሊህ ነው
〰〰〰〰〰〰〰
ሳይኖርም ልዩነት በመካከላችን
በፍቅር ተሞልቶ የሱናው ቤታችን
ሷሊህ ሷሊህ ልጆች ሲሰጠን ጌታችን
ሱናን ስንከተል እስከ ልጆቻችን
በቁርአን በሀድስ ታንፃ ቀልባችን
ስንሰራ እኖራለን ለዛኛው ቤታችን‼️

https://t.me/https_Asselfya
Audio
"ሲህር እና መዘዙ"
~~〰〰〰〰
🎙በዑስታዝ ባህሩ ተካ አላህ ይጠብቀው

👉ጉራገኛ እምትችሉ አድምጡ።

"الرقية الشرعية"
መንፈሳዊ ህክምና በቁርዓን እና ሓዲስ

#በኡስታዝ አቡ ሙዓዊያ ሰኢድ ሙሐመድ ኑር
📌ይቀላቀሉን

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
አትቅረቡ እህቴን
🍂🍂🍂🍂🍂
ያቺን ሂጃቢስቷ ያቺን ጅልባብ ለባሽ፣
ያቺን ቆራጠኛ አትንኳት በጭራሽ፣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
አትቅረቡ እህቴን አጠቁሙባት፣
ባያችኀት ቁጥር ስም አታውጡላት፣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ይመስላቹሀል እንጂ ይዟቹ ጅህልና፣
የተሸፈነችው የማታምር ሆና፣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
በል እንደው ቆንጆ ነት ኒቃቢስቷ ጀግና፣
አትምጡብኝ ምትል ከለላ ለዲኗ፣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
የኔ እህትኮ ባላት ምትብቃቃ፣
ሁሉን ላግኝ አትል አደለች ሞልቃቃ፣
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ለ'ናትና አባቷ ታዛዛዥኮ ናት፣
ለታናናሾቿ ሁለተኛ እናት፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿
እህቷን ነይ ምትል ተማሪ ዲንሽን፣
ጌታሽን ታዘዢ ሸፍኚ ጌጥሽን፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿
ለወንድሟ አዛኝ ለሱ ተቆርቋሪ፣
ጥፋት ስታይበት ናትኮ መካሪ፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿
ከአጅነቢ ጋራ አትልከሰከስም፣
መዝናናትም ብላ ስትዞር አትውልም፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿
ካልሆንኩኝ አትልም ዘመናዊት ሴት፣
በሶሻል ሚድያው ፎቶ ልፖስት፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿
እርም የሆነውን ታውቀዋለችና፣
መሆን አትፈልግም ለወንድሟ ፊትና፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿
ትንንሽ ወንጀልን የማትዳፈር፣
የማትታለል ናት በሰው ንግግር፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿
ማታውቋት እንደሆን አሁን እወቋት፣
የስድቡን መአት አትልቀቁባት፣
➿➿➿➿➿➿➿➿➿
https://t.me/https_Asselfya
ልጁ፦ ሲሸነግላት ላንቺ ብዬ እሞታለሁ አላት
እሷም፦ እውነትህ ከሆነ ለተውሂድና ለሱና ሙት አለችው።

ልጁ፦ ኧረ ከፈለግሽ አንገቴ ልሰጥ እችላለሁ አላት
እሷም፦ መጀመርያ ከቁርጭምጭሚትህ በታች የሚጎተተው ልብስህ ለመቀስ ስጥ አለችው።

ልጁ፦ ያላንቺ መኖር አልችልም እኮ አላት
እሷም፦ በአላህ ከተመካህ ያለማንም መኖር ትችላለህ አለችው።

እሱ፦ ህይወቴ ያላንቺ ባዶ ነው አላት
እሷም፦ ለቀቅ አድርገኝ ሆ ፈጣሪህ አደረከኝ እንዴ አለችው።

✅ማሳሰቢያ
👉ከኒካህ በፊት የሚደረደሩ የቃላት ሽንገላዎች እንዳይሸውዱን። ከኒክህ በፊት ሞትኩልሽ ታመምኩልሽ የሚለው አካል በጁ ካደረገሽ በኋላ ደና አደርሽ ደና ዋልሽ ላይልሽ ሁላ ይችላል።
【ፍቅር፦ ፍቅር የሚሆነው በሀላል መንገድ ላይ ሲሆን ብቻና ብቻ ነው】

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
♦️ሱረቱል አስር
〰〰〰〰〰
📌📌📌በዉስጡ የተዳሰሱ ነጥቦች

🔺የግዜ አሳሳቢነት
🔺ስል ኢልም
🔺አንድ ሰው ባወቀው መስራት እናደለበት
🔺ስለ ዳዕዋ
🔺ስለ ሶብር

🎙አቡ አዩብ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
👍1
💦የተሸፈነ ነገር ዉስጥ እዉነተኛ ዉበትን ታገኛለህ አየሽ አንች እንቁ እንስት የመሸፈን ዋጋ ለዚህም ነው ላቅ ያለዉ ጌታችን እንድንሸፈን ያዘዘን

እሸትን በቀሎ በሸትነቱና ከማሳ ወደ ቤት ገብቶ ተገላልጦ ደርቆ ስታየዉ ለአይን እይታ የሚስበው እስኪ የትኛው ነው ????

ሱበሀነክ ያኢላሂ አልሀምዱሊላህ አላ ኒዕመተል ኢስላም

ወላሂ ነፃነትም በሉት ዘመናዊነትም ብቻ ባሻችሁ ሰይሙት በመሸፈን ዉስጥንጅ በየትኛውም መንገድ አይገኝም

▶️የሂጃቧን ንግስት የኒቃቧን ጀግና ፣
መቅናትስ በሷ ነው የጌታዋን ትዕዛዝ አክባሪ ናትና ፣

▶️አንተም አኺ አረህማን ወፍቆህ እሷን ካገባሀት ፣

ታድለሀልና ጌታህን አመስግን ማንም የማያያት የግልህ ካዝና ናት፣

🌸🌸ኒቃቢስቷ🌸🌸
〰〰〰〰〰〰〰
♻️ማስመሰል የሌለዉ ያልተበረዘዉ፣
እዉነተኛ ዉበት ያንቺ ብቻ ነው ።

የመሸፈንን ዋጋ የሚያዉቀዉ የተሸፈነ ብቻ ነው አላህ ይወፍቃችሁ ያረብ

የተሸፈናችሁም አላህ እስቲቃማውን ይስጣችሁ!!

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
✍ማስታወሻ
➖➖➖➖➖
✅በየቀኑ እና ለረጅም ሰዓት ሶሻል ሚዲያው ላይ ተጥዶ መዋልም ሆነ ማደር መልካም አይደለም።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹ዕድሜና ጊዜን ይፈጃል። ዕድሜ ማለቁ የማይቀር የሚቆጠር እስትንፋስ ነው። እስትንፋስህን በዉድ ዋጋ እንጂ አትሽጥ።

👌ራስህን ከትልቅ ቦታና ዉጤት ለማድረስ ብልህ ሁን። አንዳንዴም ከግርግሩ ሜዳ ገለል ብለህ ዉስጥህን የምታይበት ጊዜ ይኑርህ።

👉 ዛሬ ላይ ሥራ የሚያስፈቱ ነገሮችም ሰዎችም በዝተዋል። ዩ ቱዩቡና ሶሻል ሚዲያው፣ ዜናዉና የፖለቲካ ወሬው… ሰዎች ረጅም ጊዜ ሰጥተው ሰዓታቸውን የሚፈጁበት ነገር ሆኗል።

↪️በዚህ ዓይነቱ ጊዜ ነቃ በል። በመሃል የሚወስዱህ ነገሮች ቢኖሩ እንኳ "ዋናውን ሥራህን" አትጣል። ሰዎች በብዛት ስለተጠመዱበትና ስለሠሩት ብቻ አንድ ነገር ምርጥ ነው ማለት አይደለም ።

👌 ባይሆን ከብዙዎች ለየት በል። በዝምታ ሥራ። ለዱንያም ለአኺራም ብዙ ትርፍ ሊያስገኙልህ በሚችሉ ነገሮች ላይ አተኩር።

✅የሚዲያው ዓለም ባህር ነው። ሁሉ ነገሩ ይስባል። ሁሉ ነገሩ እዩኝ ይላል። ያዘናጋሃል፣ ጠልፎ ያስቀርሃል፣ ገብተህ መውጫው ይጠፋሃል።

↪️ ከዚህ አንፃር ጠንካራ እና ራሱን መቆጣጠር የሚችል ብርቱ ሁን። ከገባህም በቀላሉ መውጣት የምትችል ጎበዝ ሁን።

🔺በዚህም በዚያም ልብህ አይሰረቅ። የሚስቡና የሚያስፈልጉ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም እጅግ በሚጠቅሙህ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩር።

🔹 ያብለጨለጨ ሁሉ ወርቅ አይደለም። ደምቆ ርዕሱ የተፃፈ ዜና ሁሉ ፍሬ ላይኖረው ይችላል። እናም ጥቂት ብትዘናጋ እንኳ ቶሎ ብለህ ወደ ዋናው ጣቢያህ ተመለስ።

ዋናው ጣቢያችን የቁርአንና ሐዲሥ አስተምህሮ ነው❗️
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 5⃣5⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

↪️የትዳር አስፈላጊነትና ጥቅም
↪️የጥሩ ትዳር መሰረቶች
↪️ከትዳር መሸሽና አደጋው


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw