💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
በአራት ነገራቶች አማካኝነት የልብ ድርቀት ይፈጠራል‼️
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹 ከልክ በላይ መብላት
🔹ብዙ መተኛት
🔹ብዙ ማውራት እና
🔹 አላስፈላጊ የሆነ መቀላቀል ሲከሰት

↪️እነዚህን ነገሮች ከሚፈለገው በላይ ከተጠቀምናቸው ልባችን መድረቅ እንደሚችል ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ አልፈዋኢድ በተሰኘው ኪታባቸው ላይ አስፍረዋል።ሁሉንም በመጠኑ ለማድረግ እንሞክር ‼️
https://t.me/https_Asselfya
📍خطبة الجمعة
📍የጁሙዓ ኹጥባ
↓↓↓
🌐 የጀነት ፀጋዎችና የጀነት መግቢያ መንገዶች

🌐 نعيم الجنة وسبل الوصول إليها

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/2849
ወንድሜ
〰〰〰
የትም ሆነህ አላህን ፍራው!

በቀን፡በማታ በጫካ፡በገደል በየትም ሁኔታ ላይ ሁን ጌታህ ያይሀል እና አላህን ከመፍራት ወደ ኀላ አትበል፡፡

አላህን በትክክል ከፈራሀው

☞ የእውተኛ መለያ ብርሀን ያደርግልሀል
☞ወንጀልህን ያብስልሀል
☞ ይምርሀል

ሰለዚህ ወዳጄ አላህን በመፍራት ላይ ጠንከር በል አደራ !

አላህ (ﷻ) አንዲህ ይለናል

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَتَّقُوا اللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡

https://t.me/https_Asselfya
#እንዲሁ በተለምዶ ሚስት ብቴድ
በሌላ ሚስት ትተካለች ይባላል፦
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#አንዳንዴ ግን ፍፁም በሌላ ሊተኩ የማይችሉ
ፍፁም የማይረሱ የትዳር አጋሮችም አሉ።

#የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በርካታ ሚስቶች ኖሯቸው ሳለ "በርግጥም አላህ ከኸዲጃ የተሻለችን ፍጹም አልተካኝም" ብለው በግልጽ ተናግረዋል።

#ቀኝ እጅ እና የቁርጥ ቀን ወዳጃቸውም ነበረች ሁሉም ሰው ፊቱን ሲያዞርብኝ እሷ ግን በኔ ፍፁም እምነት ነበራት! ረሱል ﷺ ስለ ኸዲጃ رضيﷲ عنها ከተናገሩት.. !!
💦መስለማ ቢን አብዱል መሊክ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ መልካም ሚስት ለአንድ ሙእሚን ከሁለት አይኑ፣ ከሁለት እጁና ከሁለት እግሩ በላይ አስፈላጊና በላጭ ነች።
📚【 أحسن المحاسن للثعالبـﮯ : ٣٦٨ 】
➡️አንዳትሞኝ ንቃ‼️
〰〰〰〰〰〰〰
አይንናስ ቡዳ ቢይዝህ መልከኛ ነኝ‼️ ወይም ሀብታም ነኝ ‼️ብለህ እንዳታስብ የያዘብህ ምክኒያት ከአሏህ ዚክር በመራቅህ ምክኒያት መሆኑን አስታውል።
የጧት ዚክር
〰〰〰〰

سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ: عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ. (3× إذا أصبح)

‘ ‹‹ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም፡፡ በፍጡራኑ ቁጥር ልክ፤ ነፍሱ በወደደችው ልክ፤ በዙፋኑ ክብደት ልክ፤ በቃላቱ ብዛት ልክ፡፡›› ሦስት ጊዜ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلاً مُتَقَبَّلاً. (إذا أصبح)

‹‹ኣላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን, መልካም የሆነ ሲሳይን, ተቀባይነት ያለውን ተግባርን እጠይቅሃለው፡፡››-

أَسْتَغْفِرُ اللهَ وَأَتُوْبُ إِلَيْهِ. (100× في اليوم)

‘አላህን ምህረትን እምፀ ናለሁ፡፡ወደርሱ በፀፀት እመለሳለሁ፡፡››- በቀን መቶ ጊዜ

اَللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ. (10×)
አላህ ሆይ! በነብዩ ላይ ሰላምታ አውርድ፡፡ ሰላም አስፍንም፡፡›› አሥር ጊዜ .’

https://t.me/https_Asselfya
☞የዱንያን ጭንቀት አትሸከሚ ዱንያ የአላህ ነች
☞ስለ ርዝቅሽም አትጨናነቂ ርዝቅም ከአላህ ነው
☞ወደፊት የሚያጋጥምሽን ችግር አታስቢ በአላህ እጅነው ያለው ሁሉም ነገር

☞ስለ አንድ ሀሳብ ብቻ ተጨነቂ አላህን እንዴት ማስደሰት እንደምትችይ አላህን ካስደሰትሽ ተደስቶብሽ ያስደስትሻል መብቃቂያሽ ሆኖልሽ የደስታን ሀብት ይሰጥሻል ።ከሃብት ሁሉ ትልቅ ሃብት የልብ ሃብት ነው።አቂደን መገንዘብ ነው።ሀላሉን ከሀራም ለይቶ ማወቀና ጠቃሚና ጎጂን መለየትነው።አብሽሪ ሁሉም ነገር ጊዜው ስደርስ በአሏሀ ምርጫ ይመጣልናል።ሪዝቃችን ማንም አይነጥቀንም።ዬትም አያመልጠንም አሏህ የፃፈልን ነገር እሺ
☞ልብሽ በደማበት የህይወት ችግር ተስፋ አትቁረጪ
☞ወደ አላህ ተጣሪ ወደ ኸይር ቀይርልኝ ብለሽ
☞ሀዘን በስግደት ይጠፋል
☞ደስታ በዱአ ይመጣል
ብቻ ምን ልበልሽ

ለነገሮች በጣም ቦታ ሰጠሽ አትጨናነቂ ሰበቡን አድርሺ ከዚያም በጌታሽ አሏህ ተመኪ "በእርሱ የተመካ ሁሌም ኡፍፍፍፍፍፍፍ እንዳለ ነው

https://t.me/https_Asselfya
Audio
✅ምክር ለሴቶች‼️
➖➖➖➖➖➖

✅ ሴቶችን ትዳር አልባ ያደረጉ ዋና ዋና ጉዳዮች፦
〰〰〰〰〰〰
🇸🇦ከቤተሰብ መራቅ
🇸🇦ገንዘብ ማሯሯጥ
🇸🇦ትዳርን መፍራት
🇸🇦የማይገኙ መስፈርቶች


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
በአላህ ፍቃድና እገዛ ዛሬ ከአሱር ሰላት በኀላ ረውደቱል ባዲኢን የ122 ሀዲስ ቂርአት ደርስ ከቀኑ 10:30 ላይቭ በቴሌ ግራም ይተላለፋል። አድራሻ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
የሱጁደሰህው [የመርሳት ሱጁድ]
ምክንያቶች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
በሶላት ውስጥ የመርሳት ሱጁድ የሚፈጸምባቸው ምክንያቶች ሶስት ሲሆኑ፦
❶ኛ፡- መጨመር
❷ኛ፡- መቀነስ እና
❸ኛ፡- መጠራጠር ናቸው፡፡

❶ኛ፡- #መጨመር
መጨመር፡- ማለት አንድ ሰው በሶላቱ ውስጥ ሩኩኡን ወይም ሱጁዱን ወይም ቂያሙን ወይም ቁኡዱን ( መቀመጡን) ከመደበኛ ቁጥሩ በላይ መጨመር ማለት ነው፡፡

❷ኛ፡- #መቀነስ
መቀነስ፡- ማለት አንድ ሰው ከሶላት ማዕዘናቶች ወይም ዋጅባቶች ከመደበኛ ቁጥሩ መቀነስ ማለት ነው፡፡

❸ኛ፡- #መጠራጠር
መጠራጠር ፡- ማለት ሶስት ወይስ አራት ረከዓ ነው የሰገድኩት? ብሎ መወላወል ማለት ነው፡፡

↪️ #መጨመር ጭማሬን አስመልክቶ አንድ ሰው በሶላቱ ውስጥ ሆን ብሎ ሩኩዕ ወይም ሱጁድ ወይም ቂያም ወይም ቁኡድን ከጨመረ አላህና ረሱል ካዘዙት ውጭ በመተግበሩ ሶላቱ ተቀባይነት አያገኝም፡፡
የአላህ መልክተኛ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ቡኻሪና ሙስሊም በተዘገበ ሐዲስ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"من عمل عملا ليس عليه أمرنا فهو رد"
رواه البخاري ومسلم
“የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ እርሱ ተመላሽ ነው፡፡”
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
ከሶላቱ ላይ ረስቶ ቢጨምር ግን ሶላቱ አይበላሽም፡፡ ነገር ግን ከሰላምታ በኋላ የመርሳት ሱጁድ በመስገድ ሊጠግነው ይገባል፡፡
ለዚህ ማስረጃው ኢብን መስኡድ ያስተላለፉት ቡኻሪ እና ሙስሊም የዘገቡት ሐዲስ ነው
ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የዙህር ሶላትን አምስት ረከዓ አድርገው ሰገዱ፡፡ ካበቁ በኋላ “ሶላት ተጨመረ እንዴ? በማለት ተጠየቁ፡፡ እርሳቸውም “ምንድን ነው?!” አሉ “አምስት ረከዓ ነው እኮ የሰገድከው!” አሏቸው፡፡ ወደቂብላ በመዞር እግራቸውን አጠፉ፡፡ ከዚያም ሁለት ሱጁዶችን ሰገዱ፡፡

↪️ #መቀነስ (ማጉደል) ከሶላት ማዕዘናቶች (ፈርዶች) አንዱን ቢያጎድል አማራጮች የሚከተሉት ናቸው።
➲ ከሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ቦታ ሳይደርስ የረሳውን ቀድሞ ቢያስታውስ የረሳውን ማዕዘን ተመልሶ ይፈጽም፡፡
➲ ከሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ቦታ ላይ የረሳውን ቢያስታውስ ሁለተኛውን ረከዓ ላመለጠው ማዕዘን ትክ ያድርግና ሌላ አንድ ሙሉ ረከዓ ይስገድ፡፡
በእነዚህ ሁለት ባህሪያት ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡

ለመጀመሪያው ምሳሌ፡- በሁለቱ ሱጅዶች መካከል ሳይቀመጥ አንድ ሱጁድ አድርጎ ወደቂያም ሄደ ፋቲሃን ሊጀምር ሲል አስታወሰ ወዲያው ይመለስና የረሳውን ሱጁድ ይፈጽም ፡፡ ከዚያም መጨረሻ ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡

ለሁለተኛው ምሳሌ፡- በሁለት ሱጁዶች መካከል ሳይቀመጥ አንድ ሱጁድ ረስቶ ከሁለተኛው ረከዓ ተመሳሳይ ቦታ ላይ አስታወሰ የዚህ ጊዜ የሁለተኛው ረከዓ እንደአንደኛ ረከዓ ተቆጥሮ ሌላ አንድ ረከዓ ይጨምር ከዚያም አሰላምቶ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡

➡️ ማዕዘን ሳይሆን ዋጅብ ነገር ቢያጎድል ለምሳሌ “ሱብሃን ረቢየል አእላ” የሚለውን ዚክር ረስቶ ቢነሳ ሶላቱን ዝም ብሎ ይቀጥል ፡፡ ከሰላምታ በፊት ሰጀደተ ሰህው ያድርግ፡፡ ምክንያቱም ነብያችን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - የመጀመሪያውን አታህያቱ በረሱበት ወቅት ወደሶላታቸው ቀጠሉ እንጅ አልተመለሱም፡፡

↪️ #መጠራጠር፦ መጠራጠር ማለት ጨመርሁ ወይስ ቀነስሁ? ብሎ መወላወል ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ሶስት ሰገድሁ ወይስ አራት ረከዓ ሰገድሁ ብሎ ቢወላውል ከሚከተሉት ሁኔታዎች አይዘልም፡-
መጨመር ወይስ መቀነስ ከሚለው ከሁለቱ እርግጠኝነቱ ያመዘነውን ይውሰድና ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡
ከሁለቱ አንዱ ሚዛን ካልደፋለት ግን እርግጠኛ የሆነበትን ይውሰድ እርሱም አነስተኛው ቁጥር ነው፡፡ ሶስት ወይስ አራት ሰገድሁ? ካለ ሶስትን ይውሰድና አራተኛውን ረከዓ ሞልቶ ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ይስገድ፡፡

ማጠቃለያ፦
➲ ከዋጅብ ነገሮች አንዱን ዋጅብ ከተወ ወይም ከረከዓዎች ቁጥር አንዱ አመዛኝ አልሆንለት ብሎ ከተጠራጠረና አነስተኛ የሆነውን ቁጥር ወስዶ ከሰገደ ሰጀደተ ሰህው ከሰላምታ በፊት ተፈጻሚ ያደርጋል፡፡
➲ ከሶላቱ ላይ ረከዓ ከጨመረ ወይም ተጠራጥሮ ከሁለቱ አንዱ አመዛኝ ከሆነለት ከሰላምታ በኋላ ሰጀደተ ሰህው ያደርጋል፡፡
مجموع الفتاوى محمد بن صالح العثيمين (1/ص
https://t.me/https_Asselfya
👉በዘመናችን ትልቁ ፈተና
〰〰〰〰〰〰〰〰
ሁለት የሰለፍያን መንሀጅ የሚከተሉ ጥንዶች አለመገናኘታቸው ነው።

➡️የቢድአ ሰወች ምሳሌ⬅️
➖➖➖➖➖➖➖➖
↪️የቢድአ ሰወች ሱና ጋ ያላቸው ምሳሌ

ወርቅና አጥንት እንደተጣለለት ውሻ ማለት ናቸው ‼️
💦ሱና ወርቅ ነች ብልሆች እንጂ አያነሷትም
🔻ቢድአ ጥንብ ነች ውሾች እንጂ አያነሷትም ‼️
✅ፍቅርን በትዳር ውስጥ ፈልጉት.......
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
💢ኢስላም በፍቅር ዙሪያ ከማንም የማይዋሠው ግልፅ እና የማያሻማ አቋም አለው። ለዚህ ነው በታላቁ መለዕኮታዊ መፅሐፍ (በቁርዓን) ውስጥ ስለፍቅር እና ተያያዥ ነጥቦች በተደጋጋሚ የተወሣው።

🔺በመሠረቱ ቁርዓን ፍቅር እና ውደታን
በተለያዬ ቃላቶች በስፋት ገልፆታል ለምሣሌ፦
▪መወዳ
▪ሁብ
▪ሸገፍ
▪ወልይ እና ሌሎችም..

♻️ፍቅር በትዳር ውስጥ ሲሆን፦ ደስታ፤ ሐሴት፤ እርካታ፤ የልብ መረጋጋት፤ እርስ በርስ መተማመን፤ እንድሁም እዝነት(ራሕማ) ....አለው።
🚫ፍቅር ከትዳር ውጭ ሲሆን ደግሞ፦ የልብ ሕመም (ስቃይ) ፤ከሸይጧን ፈተና ላይ መውደቅ፤ በስሜት መነዳት፤ ወንጀልን መዳፈር፤ አላህን ማመፅ ፤ ከአላህ መራቅን፤ ያስከትላል።

❎ፍቅርን ከጋብቻ በፊት አትግባበት❗️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ተሳስተህ (አዳልጦህ) ከገባህበት ግን መድሃኒቱ አንድ እና አንድ ብቻ ነው - እሱም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፦
#የፍቅር መድሃኒቱ ያፈቀርካትን ሴት ማግባት ነው።

👁‍🗨ግን ፍቅር ምንድን ነው❓
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ፍቅር መልካም ተግባር ነው፤ፍቅር የምናደርገው ድርጊት ነው፤ፍቅር ስሜት አይደለም፤ፍቅር የራስን ስሜት እና ፍላጎት ማሟላትን አይወክልም፤ትክክለኛው ፍቅር ላፈቀሩት እና ለወደዱት ሰው በቅን ልቦና የሚያከናውኑት ተግባር ነው።ፍቅር የደግነት ተግባር ነው መልካም ቃላትን መናገር ለአፈቀሩት ሰው መራራት እና ማዘን፤መርዳት እና ማመስገን ፈገግ ማለትን እና ማገዝን የሚወክል ቃል ሲሆን ሌሎችም መልካም ተግባራትን ያካትታል።


https://t.me/https_Asselfya
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Photo
የወንድና የሴት ጀናዛ አስተጣጠብ ۞
ሥነ_ስርዓት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
.1 ሰውዬው ለመሞቱ ማረጋገጫ መውሰድ ከዋናዎቹ
ማረጋገጫዎች
አምስቱን እንመለከታለን

* የአይን ተከፍቶ መቅረት
* የአፍንጫ መጣመም
* የልብ ምት መቆም
* ከእግር ጫፍ የሚጀምር እያለም ወደ ላይ የሚሄድ ከፍተኛ የሆነ
ሙቀትና ወደ ቅዝቃዜ መለወጥ
* የእግር መደራረብ
እነዚህ በአብዛኛው ሰው ላይ የሚስተዋሉ ናቸው ::
ከዚህ በመቀጠል

.2 ሰውነትን ማላላት ይህም ሲባል እጁን የሰዓት ማሰሪያ ቦታ እና
ክንድ ላይ ማንቀሳቀስ ዓይንንም ወደታች መግጠም ወይም
መሸፈን ::

.3 እግርን ጉልበት ላይ ማንቀሳቀስና ማላላት ይህም በኋላ ላይ
ለማጠብ ስናንቀሳቅስ እንዳያስቸግረን ይረዳል

.4 የምናጥብበትን ቦታና የምንገለገልባቸውን እቃዎች ማዘጋጀት።
.5 ሶስት ሰው ሁለቱ የቅርብ ቤተሰብ አንዱ በጣም ሚስጥር
ጠባቂ የሆነ ያየውን የማያወራ
.6 ሁለት የውሃ ባልዲ ከነመቅጃው
.7 ንጹህ ለብ ያለ ውሃ
.8 ሽርጥ፣ጎንት፣ሁለት ፎጣ፣መቀስ ፣ሜትር፣ሽቶ፣የመጠባበቂያ
ጨርቅ፣ (ኸፋዛ)፣የስቲንጃ ጨርቅ፣ጥጥ፣የከፈን ጨርቅ ፣
እንዳስፈላጊነቱ የአፍ መሸፈኛ
.9 ሲድር ፦ ሲድር ማለት የቁርቁራ ዛፍ የቅጠሉ ዱቄት ማለት
ሲሆን በሱ ማጠቡ
1ኛ. ሱና ነው
2ኛ. እንደ ሳሙና ጠቃሚ በመሆኑ
3ኛ.ሰውነትን የማለስለስ ባህሪ አለው ። ሲድር ካልተገኘ ሳሙና
፣ሻምፖ፣የዱቄት ሳሙና እንጠቃማለን።
.10 ካፉር፦ ካፉር ማለት በሲድር ካጠብን በኋላ የምናለቃልቅበት
የማጽጃ አይነት ነው።
ከጥቅሞቹ መካከል በአደጋ የሞተና የደም ፍሳሽ ላለው የደሙን
መጠን ይቀንሳል ተባይን ያዳክማል፣መጥፎ ሽታ ወይም ጠረን ካለ
ያስወግዳል፣አይጥ አይጠጋውም። ካፉር ካልተገኘ ንጹህ ውሃን
እንጠቀማለን።
۞ ያዘጋጀነውን ሽርጥ እንለብሳለን ፣ ጓንቱንም እናጠልቃለን
፣አፋችንን እንሸፍናለን።
۞ 1ዱን ፎጣ ከደረቱ እስከ ጉልበቱ እንሸፍናለን ወይም
በለበሰው ልብስ ላይ እንደርባለን።
۞ ይህ ከሆነ በኋላ ማንኛውንም ሰው በራስና በእግር በኩል
መቆም የለበትም ።አውረቱ እንዳይታይ ማለት ነው
۞ ልብሱ መውለቅ ከቻለ እናወልቃለን ። ካልተቻለ እንቀዳለን
የቀደድነውን ልብስ ጀናዛውን ሳናንገላታ እናወልቃለን
۞ እጆችን በድጋሚ እናንቀሳቅሳለን። የሟችን እራስና ትከሻ
በመያዝ ቀና በማድረግ ሆዱን እንጫናለን ። በዚህ መልኩ 3 ጊዜ
እናከናውናለን።
۞ በመቀጠል ያዘጋጀነውን የእስቲንጃ ጨርቅ ግራ እጃችን ላይ
በመጠቅለል ባዘጋጀነው ንጹህ ውሃ በሟቹ በስተግራ በኩል
በመቆም በእግር መሀከል እጅን በመላክ ሌላኛው ሰው በደረቱ
በኩል ቁልቁል ውሃን በማፍሰስ የእስቲንጃውን ትጥበት ለ3 ጊዜ
እንደግማለን ። ይህ ሆኖ ካልጸዳ ለ5ኛ ጊዜ በዚህም ካልጸዳ 7
ዊትር እያደረግን እናጸዳለን
۞ በመቀጠል ለሟች ውዱዕ እናደርጋለን። ቀኝ እጁን በግራው
ላይ በመጫን ሶስት ሶስት እያደረግን አፍ አፍንጫ ፣ፊት፣እጅን
እስከ ክርን ፣እራስንና ጆሮን ማበስ ፣ቀኝ እግር ከዚያም ግራ እግር
በማጠብ ውዱን እናጠናቅቃለን።
۞ በመቀጠልባዘጋጀነው ባልዲ በአንዱ ላይ የሲድር ዱቄት፣
ሳሙና ፣ሻምፖ እንዳይጓጉል አድርገን እንበጠብጣለን። ሲበጠበጥ
በሚገኘው አረፋ ከአንገት በላይ በደንብ አድርገን ሁለት ጌዜ
እናጥባለን ።
۞ የሰውነት ክፍል አስጠጣጠቡ በቀኝ በኩል በመጀመር የቀኝ
ሙሉ ሰውነትን በሚገባ እናጥባለን ። ከግማሽ ደረት እስከ
ጉልበት ያለውን ክፍል ሳይገልጡ እጅን ወደ ውስጥ በመላክ
እስከ እግር ጣት እናጥባለን ።
۞ ከዚያም ወደ ግራ ጎን ማንጋለልና የቀኝ ጀርባውን በሲድር ውሃ
ማጠብ ከዚያም ወደነበረበት በመመለስ ልክ እንደ ቀኙ ክፍል ግራውንም ማጠብ ።


አሏህ መጨረሻችንን ያሳምርልን ሼር አድርጉት

↪️↪️↪️↪️↪️
https://t.me/https_Asselfya
ወጣቶች እንደሚተናኮሏትና እንዳስቸገሯት በመናገር
ለወንድሟ አቤት ያለችውን እህት ኢስላማዊ አልባሳት መሸጫ ወስዶ ለፊትና የማያጋልጥ ኢስላማዊ ልብስ ገዛላትና መልበስ ጀመረች። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ አሁንም ወጣቶቹ ያስቸግሩሻል? በማለት ጠየቃት። የእህቱ ምላሽ፤ "በአላህ ይሁንብኝ ይህንን ልብስ ከገዛህልኝ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ያከብረኛል" የሚል ነበር። ወንድሟ ይህን ሲሰማ እንዲህ አላት « የሚፈታተን ልብስ በመልበስ አንቺ ነበርሽ ማለት ነው የምትለክፊያቸው። እነሱ ቢሆኑ ኖሮ የጨዋ ልብስ ከለበስሽ በኃላም ማስቸገራቸውን ይቀጥሉ ነበር»።

[ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﻗُﻞ ﻷَِّﺯْﻭَاﺟِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺗِﻚَ ﻭَﻧِﺴَﺎءِ اﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻳُﺪْﻧِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻦَّ ﻣِﻦ ﺟَﻼَﺑِﻴﺒِﻬِﻦَّ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺃَﺩْﻧَﻰٰ ﺃَﻥ ﻳُﻌْﺮَﻓْﻦَ ﻓَﻼَ ﻳُﺆْﺫَﻳْﻦَ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ اﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًا ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ] الأحزاب 59

«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» አል አህዛብ 59

አላህ ሆይ! እህቶቻችንን የፊትና ምክኒያት ከመሆን ጠብቃቸው። ከሸይጣን ወታደሮች ሁሉ ሰትራቸው። የትክክለኛ ሂጃብን ውበት አሳያቸው።

وَآعْبُدُواْ ﷲ وَلاَ تُشْرِكُواْ بِهِ شَيْءً وَبِاْ لْوٰلِدَيْنِ اٍحْسانً.
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
➷💎"ሀያዕ ከ ኢማን ነዉ
ይህ ምክሬ ላንቺ ለኔም ነው!"
ውዷ እህቴ ሆይ ተሸፈኚ

በሀያዕሽም ንግስት ሁኚ
🌸➖➖➖➖➖➖🌸
【ምክር ለሙስሊሟ እህቴ➧


https://t.me/menhajselefiya123
♻️ከልጅ በፍት የሸሪአን እዉቀት እናስቀድም!!!!!

♻️እህቴ ሆይ የሸርአን ትምርት በደንብ ሳትማሪ ማለትም ግደታ ማወቅ ያለብሺን ሳታቂ
🗝 ልጂን መዉለድ አትመኚ ማለትም የወለድሺዉን ልጂ ምን ልታስተምሪዉ ነዉ??

🗝እማ የለኢላሀኢለለህ ማዕና እና ሸርጥ ንገርኚ!!!!
🗝እማ ተዉሂድ ማለት ምን ማለት ነዉ?
🗝እማ ሺርክ ማለት ምን ማለት ነዉ?
🗝እማ እኛ ምንከተለዉ ፍላሲፎቺን ነዉ ሰለፎቺን ብይልሽ

💲ምን ትይዋለሽ አንቺ ምንም የማታቂ ጃሂል ከሆንሽ

💲እነዚንና ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ቢጠይቅሽ ምን ይሆናል መልስሽ????

✅ወይም አህለል ቢደአ ጋር ሂዶ ተምሮ ሲመጣ

💲 አላህ እኮ
እሁሉም ቦታ ነዉ በዛቱ ያለዉ ኡሥታዝ ብሎኛል
ብለሽ ትክክል ነዉ ወይስ አይደለም የምትይው??

✅እናም አትዉለዱ ማለቴ ሳይሆን ልጂን ከምትፈልጉ አዉ መዉለድን ከምትጓጉ በላይ የሸርአን እወቀት ለመማሪ ጓጉ : ትጉ ጣሩ የታገለ ሰዉ የሚፈልገዉን ከማግኘት አይወገድም ።
القرآن الكريم والسنة:
عن أبي أيوب الأنصاري رضي الله عنه قال :
عن النبي ﷺ قال :

((مَنْ قَالَ لَا إلَهَ إلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ ، لَهُ المُلْكُ ، وَلَهُ الحَمْدُ ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شيء قَدِيرٌ عَشْرَ مَرَّاتٍ كَانَ كَمَنْ أعْتَقَ أرْبَعَةَ أنْفُسٍ مِنْ وَلَدِ إسْمَاعِيلَ))

متفق عليه.
Audio
◼️መጥፎ ጓደኛ መያዝ አይብ ነው‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅የመጥፎ ጓደኛ አደገኝነትና ጉዳት
🔺
✅ጓደኛ ስትመርጥ ወሳኝ ጥንቃቄ
🔻
✅የጓደኛ ተፅእኖ በህይወት ላይ
🔺
✅የጥሩ ጓደኛ አስፈላጊነት


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw