💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.56K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
አንድ ወንጀል ሌላ ወንጀል ይበልጠዋል። አንዱ የከፋ ሲሆን ሌላው የቀለለ ይሆናል። ሆኖም ግን ማንኛውም ወንጀል የአላህን ቁጣ የሚያስከትል ከመሆኑ አንፃር መጠንቀቅና መራቅ አለብን። የወንጀሎች ሁሉ ቁንጮና ዋና ሽርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ነው።

♻️ ሶላት መተው ግን፦
◾️ዝሙት ከመስራት
◾️የሰውን ነፍስ ከማጥፋት
◾️መጠጥ ከመጠጣት
◾️ከስርቆትና ማጭበርበር
🇸🇦የበለጠና የከፋ ወንጀል ይሆናል።


http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
01 ኢና ኩና ሺ ጃሂሊያ ሊሸይኽ ሷሊሕ አል—ፈውዛን
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ዛሬ ሰኞ የቀጥታ ስርጭት የኪታብ ደርስ

📚📚 ኪታብ = ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ

አዘጋጅ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን

⌚️⌚️ በሳምንት ③ ጊዜ ምሽት 3:00 ቡሓላ

🎤🎤 በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)

ትምህርቱን ለመከታተል በቀጥታ 👇
👇
https://t.me/UstazKedirAhmed
የዊትር ቁኑት ዱዓ

« يقوم يصلي إن أراد ذلك »

اَللَّهُمَّ اهْدِنِيْ فِيْمَنْ هَدَيْتَ، وَعَافِنِيْ فِيْمَنْ عَافَيْتَ، وَتَوَلَّنِيْ فِيْمَنْ تَوَلَّيْتَ، وَبَارِكْ لِيْ فِيْمَا أَعْطَيْتَ، وَقِنِيْ شَرَّ مَا قَضَيْتَ، فَإِنَّكَ تَقْضِيْ وَلاَ يُقْضَى عَلَيْكَ، إِنَّهُ لاَ يَذِلُّ مَنْ وَالَيْتَ، [وَلاَ يَعِزُّ مَنْ عَادَيْتَ]، تَبَارَكْتَ رَبَّنَا وَتَعَالَيْتَ.

↪️🔻አላህ ሆይ! ሌሎችን እንዳቀናኸው እኔንም አቅናኝ፡፡ ለሌሎች ጤና እንደሰጠኸው ለእኔም ስጠኝ፡፡ ለሌሎች ዋቢ እንደሆንክ ለኔም ዋኒ ሁነኝ፡፡ በሰጠኸኝ (ፀጋ) ረድኤትህን ጨምርልኝ፡፡ ከወሰንከው ክፉ ነገር ጠብቀኝ፡፡ አንተ ትወስናለህ፡፡ በአንተ ላይ አይወሰንብክም፡፡ አንተ የተወዳጀኸው አይዋረድም፡፡ አንተ ጠላት የሆንከው ክብር አይጎናፀፍም፡፡ የተቀደክና ልዑል ነህ፡፡

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَعُوْذُ بِرِضَاكَ مِنْ سَخَطِكَ، وَبِمُعَافَاتِكَ مِنْ عُقُوْبَتِكَ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْكَ، لاَ أُحْصِيْ ثَنَاءً عَلَيْكَ أَنْتَ كَمَا أَثْنَيْتَ عَلَى نَفْسِكَ.

.↪️💦አላህ ሆይ! በእርካታህ ከቁጣህ÷ በይቅር ባይነትክ ከቅጣትክ እጠበቃለሁ፡፡ በአንተ ከአንተ እጠበቃለሁ፡፡ አንተ ራስክን ያወደስከውን ያክል ላወድስክ አይቻለኝም፡፡

اَللَّهُمَّ إيـَّاكَ نَعْبُدُ، وَلَكَ نُصَلِّيْ وَنَسْجُدُ، وَإِلَيْكَ نَسْعَى وَنَحْفِدُ، نَرْجُوْ رَحْمَتَكَ، وَنَخْشَى عَذَابَكَ، إِنَّ عَذَابَكَ بِالْكَافِرِيْنَ مُلْحَقٌ. اَللَّهُمَّ إِنَّا نَسْتَعِيْنُكَ وَنَسْتَغْفِرُكَ، وَنُثْنِيْ عَلَيْكَ الْخَيْرَ، وَلاَ نَكْفُرُكَ، وَنُؤْمِنُ بِكَ، وَنَخْضَعُ لَكَ، وَنَخْلَعُ مَنْ يَكْفُرُكَ

🎀↪️አላህ ሆይ! አንተን ብቻ እናመልካለን፡፡ ላንተ እንሰግዳለን፤ እናጎበድዳለን፡፡ ወደአንተ እንሮጣለን፤ እንገሰግሳለን፡፡ እዝነትህን እንቻለን፡፡ ቅጣትህን እንፈራለን፡፡ ቅጣትህ ከሀድያንን ያገኛል፡፡ አላህ ሆይ! እርዳታህን እንጥይቅሀለን፡፡ ምህረትህን እንማፀንሃለን፡፡ እናወድስሃለን፡፡ አንከድሀም፡፡ ባንተ እናምናለን፡፡ ላንተ እንንበረከካለን፡፡ አንተን የካደህን እንተዋለን፡፡
https://t.me/https_Asselfya
سورۃ الناس
<unknown>
#በዳሩል_ሐዲስ_መድረሳ ለኮድ 1 ተማሪዎች የሚሰጥ ተከታታይ ቅርአት ከተወሰነ የተጅዊድ ማብራሪያ ጋር ፨

>>>>>>>>>>>>>><<<<<<<<<<<<


⤴️ ክፍል #ሁለት


🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
https://t.me/https_Asselfya
የወንጀል ቅጣት ሙእሚን ከሆነ ሰው ላይ እንዴት ልትወገድ ትችላለች?
———
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-
“ግልፅ የሆኑ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎች የወንጀል ቅጣት ከባሪያው በአስር ምክንያቶች እንደሚወገድ አመላክተዋል።
① መፀፀት (ተውበት) ማድረግ። ይህ በሙስሊሞች መካከል ሙሉ በሙሉ ስምምነት ያለበት ነው።
② ኢስትግፋር ማድረግ።
③ ወንጀል እንዲታበስ ምክንያት የሚሆኑ መልካም ስራዎችን መስራት።
④ የሙእሚን ዱዓ ለሙእሚን ቅጣትን ይመልሳል። ለምሳሌ በጀናዛው ላይ መስገዳቸውን ይመስል።
⑤ ለሟች ከሚሰሩ መልካም ነገሮች መስራት፣ ሶደቃና የመሳሰሉ ነገሮችን ማድረግ ሰበብ ይሆናል።
⑥ በእለተ ትንሳኤ ለወንጀለኞች የነቢዩ ﷺምና የሌሎችም ምልጃ (ሸፈዓ) ማግኘት።
⑦ አላህ ወንጀልን የሚያብስባቸው በዱኒያ ላይ የሚደርሱ የተለያዩ መከራዎች።
⑧ በቀብር ውስጥ የሚደርስበት ፈተና ጭንቀትና ፍርሃት።
⑨ የቂያማ ሁኔታዎች፣ ጭንቀትና መከራዎቿ።
10, የአላህ እዝነት፣ ከባሪያው ያለ ምንም ምክንያት ይቅር ባይነትና ምህረት።”
[ምንጭ:- መጅሙዕ አልፈታዋ]
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ


#join ⤵️
https://t.me/https_Asselfya
{{‍የጥዋት ዚክር}}


أَصْبَحْنَا وَأَصْبَحَ الْمُلْكُ لِلَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرُ. رَبِّ أَسْأَلُكَ خَيْرَ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَخَيْرَ مَا بَعْدَهُ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا فِيْ هَذَا الْيَوْمِ وَشَرِّ مَا بَعْدَهُ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْكَسَلِ وَسُوْءِ الْكِبَرِ، رَبِّ أَعُوْذُ بِكَ مِنْ عَذَابٍ فِي النَّارِ وَعَذَابٍ فِي الْقَبْرِ.

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
↪️ማለዳ ላይ ለመድረስ ነቅተናል፡፡ በዚህ ሰዓት ሉዓላልነት የዓላማት ጌታ የሆነው አላህ ነው፡፡ ምስጋና ከአላህ ነው፡፡

💦 ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋሪ የለውም፡፡ ሉዓላዊነት የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የርሱ ብቻ ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ የዚህን ቅና የቀጠዩን /የሌሊቱን/ መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡

↪️ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ /ከሌሊቱ/ ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ።
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀 pinned «የጧት ዚክር سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ: عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ. (3× إذا أصبح) ‘ ‹‹ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም፡፡ በፍጡራኑ ቁጥር ልክ፤ ነፍሱ በወደደችው ልክ፤ በዙፋኑ ክብደት ልክ፤ በቃላቱ ብዛት ልክ፡፡›› ሦስት ጊዜ اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ…»
رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا وَهَبْ لَنَا مِنْ لَدُنْكَ رَحْمَةً ۚ إِنَّكَ أَنْتَ الْوَهَّابُ

«ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፡፡ ከአንተ ዘንድ የኾነን ችሮታም ለኛ ስጠን፡፡ አንተ በጣም ለጋስ ነህና፡፡»🖋
አንዳንድ ሴቶች ሀያዕ ሲባል መንገድ ላይ ሲሄዱ አንገት መድፋት & ሰዎች ስለኔ ጥሩ አመለካከት እንድኖራቼው ዝቅ ማለት ብቻ ይመስላቼዋል።

★ሀያዕ ( አይፋርነት) ማለት አሏህ ማይፈልግበት ቦታ አለመገኜትና ከቆሻሻ ነገሮች ሁሉ መፅዳትንም ያካትታል።
🗞 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት

💦ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". صحيح الجامع ، رقم 1133

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

عن ابن عباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐
«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች በበለጠ ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐

1. ጾም፦ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት፦ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكر

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤
«ከነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።

ከተክቢር አደራረግ መካከል፤
الله أكبر ، الله أكبر لا إله إلا الله ، والله أكبر ولله الحمد
“አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች መካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት የተሳሳተ አፈፃፀም ነው።

3. ሐጅና ዑምራ፦ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء إلا الجنة" متفق عليه.
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ፦ በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን ይሰጣሉ፤

- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው። የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ (ተቅዋ) ነው።

- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

- ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል
ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

- የአላህ መልዕክተኛ እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል።

- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

- ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

- በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ሆኖም ይህ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም።

የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል።

አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ
ህዳር 23/ 2004 ዓ.ል

https://t.me/https_Asselfya
አኺራ እና ዱንያ
MuhammedSirage M.NUR
ሙሐደራ‼️
=======
#የልብ መድረቅ
#አኺራ እና ዱንያ!

በተወዳጁ ኡስታዛችን፦

🎙#Muhammedsirage M.NUR አሏህ ይጠብቀው።
----------------
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
*ልቦናን ማስተካከል

💦ምስጋና ለአላህ ይገባው ። በእርሱ እመካለሁ ፣ ወደርሱ ተፀፅቶ እመለሳለሁ ።

↪️ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ
አምላክ የሌለ መሆኑን ፣ ሙሐመድ የአላህ
አገልጋይና መልክተኛ መሆናቸውን ፣ እሰከ እለተ ሞታቸው ድረስ ህዝብን በትክክል
የመከሩና የተሰጣቸውን አደራ በአግባቡ የተወጡ መሆናቸውን ፤ መልካም ነገር ኖሮ
የተውት ፣ መጥፎ ነገር ኖሮ ያላስጠነቀቁት አንድም ነገር የለም ብየ በእርግጠኝነት
እመሰክራለሁ። በእርሳቸው ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሶላትና
ሰላምታ ይስፈን።

↪️ከዚህ በመቀጠል፡

💧ማንኛውም ሙስሊም ከጎኑ አብራው የማትነጠለውን ልብ ትኩረት ሰጦ
ማስተካከል የመጀመሪያ ተቀዳሚ ስራው ሊያደርግ ይገባል፡፡ ልብ ለተግባራችን ወይም
ለአካል እንቅስቀሴያችን ሁሉ መሰረት ነች። ለሰራዊት መሪ እንደሚያስፈልገው ሁሉ
የአካላችን መሪ ልባችን ነች። ልብ ካማረች አካላችን ሁሉ ያምራል። ልብ ከተበላሸች
ደግሞ አካላችን ሁሉ ይበላሻል፡፡


↪️ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሁሉ ልብ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጣት እንደሚገባ የአላህ
መልክተኛ ሰላሏሁ አለይሂ ወሰለም በበርካታ ሐዲሶቻቸው ላይ ተናግረዋል፡፡ ልባቸውን ወደትክክለኛው ጎዳና
እንዲመራላቸውና ጤናማ እንዲያደርግላቸው አላህን በብዛት ተማጽነዋል።
ረሡል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የሚከተሉትን ዱዓዎች ዘወትር ያደርጉ ነበር፡-
" اللهم اجعل في قلبي نورا"
“አሏህ ሆይ! በቀልቤ ውስጥ ብርሃንን አድርግልኝ።” (ቡኻሪ፡ 6316, ሙስሊም፡ 763)
II
"اللهم إني أعوذ بك من قلب لا يخشع"
“አላህ ሆይ! (አንተን) ከማይፈራ ልብ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡” (ሙስሊም፡ 2722)
II
"اللهم نق قلبي من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس"
“አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከቆሻሻ አንደሚጸዳው ልቤን ከወንጀል አጽዳልኝ።” ( ቡኻሪ፡ 6375,
ሙስሊም፡ 589)
"اللهم آت نفسي تقواها وزكها أنت خير من زكاها أنت وليها ومولاها"
“አላህ ሆይ! ከነፍሴ ጥንቃቄዋን ስጣት ፤ (ከሐጢያት) አጥራት ፤ ከሚያጠሯት ሁሉ
በላጭ ነህና ፤ አንተም ጠባቂያዋ ጌታዋ (አምላኳ) ነህና።" (ሙስሊም 2722 )

ይቀጥላል

↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
የሸህ አልባንይ ያማረ ቂርአት
↪️የጥዋት ዚክር↩️

اَللَّهُمَّ عَافِنِيْ فِيْ بَدَنِيْ، اَللَّهُمَّ عَافِنِيْ فِيْ سَمْعِيْ، اَللَّهُمَّ عَافِنِيْ فِيْ بَصَرِيْ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ. اَللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوْذُ بِكَ مِنَ الْكُفْرِ وَالْفَقْرِ، وَأَعُوْذُ بِكَ مِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ، لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ. (3×)

💦አላህ ሆይ አካሌን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ አላህ ሆይ ጆሮዬን ጤናማ አድርግለኝ፡፡ አላህ ሆይ ዓይኔን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አላህ ሆይ ከክህደትና ከድህነት በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከቀብር ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከቀብር ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሶስት ጊዜ።

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَاْلآخِرَةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِيْنِيْ وَدُنْيَايَ وَأَهْلِيْ وَمَالِيْ. اَللَّهُمَّ احْفَظْنِيْ مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِيْ، وَعَنْ يَمِيْنِيْ وَعَنْ شِمَالِيْ، وَمِنْ فَوْقِيْ، وَأَعُوْذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِيْ.

↪️ አላህ ሆይ በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታንና ጤንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ በሀይማኖቴ፥ በዚህች አለም ህይወቴም፥ በቤተሰቦቼም፥ በንብረቴም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡ አላህ ሆይ ነውሬን ሸፍንልኝ፡፡ አላህ ሆይ ከፊት ለፊቴ ፥ ከኃላዬም፥ ከቀኜም፥ ከግራዬም፥ ከበላዬም ጠብቀኝ፡፡ ከበታቼም እንዳልጠቃ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ’

اَللَّهُمَّ عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَاْلأَرْضِ، رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيْكَهُ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِيْ، وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ وَشِرْكِهِ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِيْ سُوْءًا أَوْ أَجُرُّهُ إِلَى مُسْلِمٍ.

🔻 ሩቅንም ቅርብንም የምታውቅየሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንክ አላህ ሆይ! የሁሉም ነገር ጌታ ነህ፡፡ የሁሉም ነገር የበላይ ተቆጣጣሪ ነህ፡፡ ከአንተ ሌላ የሚመለክ ሀይል የለም፡፡ ከነፍስ ክፉ ነገር፣ ከሸይጣንና አጋሮቹ ተንኮል፣ በራሴ ወይም በአንድ ሙስሊም ላይ ክፉ ነገር እንዳልጽምም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ’

بِسْمِ اللهِ لاَ يَضُرُّ مَعَ اسْمِهِ شَيْءٌ فِي اْلأَرْضِ وَلاَ فِي السَّمَاءِ وَهُوَ السَّمِيْعُ الْعَلِيْمُ. (3×)

↪️ በአላህ ስም፣ እርሱ (አላህ) ከስሙ ጋር (በስሙ የተጠበቁትን) በሰማይም በምድርም ምንም ነገር አይጎዳቸውም፡፡ እርሱ ሰሚም አዋቂም ነው፡፡ ሦስት ጊዜ፡

رَضِيْتُ بِاللهِ رَبًّا، وَبِاْلإِسْلاَمِ دِيْنًا، وَبِمُحَمَّدٍ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نَبِيًّا. (3×)

💦 በአላህአምላክነት በኢስላም ሀይማኖትና በሙሀመድስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ነብይነት ረክቻለሁ፡፡” ሦስት ጊዜ.

يَا حَيُّ يَا قَيُّوْمُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغِيْثُ، أَصْلِحْ لِيْ شَأْنِيْ كُلَّهُ وَلاَ تَكِلْنِيْ إِلَى نَفْسِيْ طَرْفَةَ عَيْنٍ.

↪️አንተ ህያዉ የሆንክ አምላክ ሆይ! አንተ ራስክን የቻልክ አምላክ ሆይ! በእዝነትክ እታገዛለሁ፡፡ ጉዳዩን ሁሉ የተስተካከለና መልካም አድረግልኝ፡፡ ለቅፅ በት እንኳ እኔን ለራሴዉ ብቻ አትተዎኝ፡፡’

↪️በተወኩልበዚክርበዱዓያልተገነባች ልብ በነፍስያና በሸይጧን ተንኮል ትሽበባለች
↪️ለጭንቀትና ለሀሳብ ትጋለጣለች
🌹
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
#ከሒጃቢስቷ ሴት የሚጠበቁ ነገሮች

↪️ከልብሽ አድምጪኝ ውድ እህቴ!
አንዲት የተሟላ ሒጃብን የለበሰች ሴት ከወሲብ ቀስቃሽ ተግባሮች መፅዳት አለባት።
ቀጥሎ ያሉትን ነገሮችም አጥብቃ መያዝ አለባት፡፡

→①/ ዕይታዋን ዝቅ ማድረግ (ዓይኖቿን ሰበር ማድረግ)፣ በባዳ ወንዶች ፊት
አለመቅለስለስ፣ አለመሽኮርመምና አለመቅበጥ፣

→②/ ከባዳ ወንዶች ጋር አካላዊ ንኪኪን ማስወገድ፤

→③/ ከቤቷ የምትወጣው ላስገዳጅ ነገር መሆን አለበት የወጣችበትን አስገዳጅ ነገር ፈጽማ ቶሎ ወደቤቷ መመለስ አለባት፣

→④/ ወደራስዋ ትኩረትን ለመሳብ ምንም ዓይነት ጥረትን ከማድረግ መቆጠብ አለባት፤

→⑤/ ኮስመቲከስ ተጠቅማ፣ ቀለማ ቀለምና ሽቶ ተቀባብታ፣ ተኳኩላና ተጋጊጣ ከቤት ከመውጣት ፈጽሞ መታቀብ አለባት፡፡

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
አስርቱ ውድ ቀናቶች


🇸🇦የአስሩ ቀናቶች ብልጫ
🇸🇦ታላላቅ የኢባዳ ስብስቦች
🇸🇦በነዚህ ቀናት የሚሰሩ ስራዎች
🇸🇦የኡለማዎች አጭር ምክር


◾️ሼር በማድረግ ሰዎችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
💦በተከበሩት የዙል_ሒጃ 10 ቀናት ነፍሲያህን አሸንፈህ መልካም ስራዎችን መስራት እንኳ ቢያቅትህ በነዚህ ቀናት ወንጀልን ከመዳፈር ከመቼውም በላይ ተጠንቀቅ!

↪️መልካም ስራ እጥፍ ድርብ ምንዳ የሚያሰጥበት ወቅት ላይ የሚሰራ ወንጀልም ቅጣቱ ከሌላ ጊዜው ቅጣት ይልቅ ከባድ ነው የሚሆነው!
መጠነኛ ዳዕዋ ስለ ዒልም
<unknown>
አዲስ ዳዕዋ

👆 #የዒልም_ትሩፋቶች

▶️ ከተጠቀሱ ነጥቦች መካከል ፦

የዑለማኦች ደረጃ

እውቀትን ከማን ነው የምንወስደው

እውቀትን ለማግኘት ምን ምን ማሟላት ይኖርብናል ?

ሼር እናድርግ

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
ጥሩ ህልም እንድታዩ ሊጠቅማቹ ከቻለ


💦የምእመናን እናት አኢሻ ረዲየላሁ አንሀ ልትተኛ ስታስብ ይህንን ዱአ ትል ነበር።
.
"اللهم إني أسألك رؤيا صالحة ، صادقة غير كاذبة ، نافعة غير ضارة "

ትርጉሙም

"አላህ ሆይ መልካም ፣ እውነተኛን ውሸት ያልሆነን ጠቃሚ ጎጂ ያልሆነን ህልም እጠይቅሀለው።"

📚ኢብን ሀጀር እና ኢማመ ነወዊ ጠቅሰውታል ሰነዱም ሰሒህ ነው ብለውታል