💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.58K subscribers
1.29K photos
495 videos
125 files
5.18K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
5 ነገሮችን ከ 5 በፊት ተጠቀም
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ

→ ርዕስ↓

🌐 اغْتَنِمْ خَمسًا قَبْلَ خَمْسٍ

🌐 አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀም

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/4176
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4176
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም – 5 ነገሮችን ከ 5 በፊት ተጠቀም
▪️የአምስት ነገሮች እድል እንዳታስመልጥ‼️

➊ወጣትነትህ ፣ከማርጀትህ በፊት ተጠቀምበት
❷ጤንነትህ ፣ከመታመምህ በፊት ተጠቀምበት
❸ሀብትህ ደሀ ከመሆንህ በፊት ተጠቀምበት
❹ክፍት ሰአትህ መሽቁል ከመሆንህ በፊት ተጠቀምበት
❺ሂወትህ ከመሞት በፊት ተጠቀምበት
◾️ሀፊዝ ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

✅ ኢማን ቀልብ ውስጥ ገብቶ ሰርፃ በፀና ጊዜ፦ የሰውነት አካሎቻችን በሙሉ ለመልካም ስራ ይነሳሳሉ። ምላስንም እንዲሁ በመልካም ንግግር ላይ ትገፋፋለች።
📚 لطائف المعارف [٢٢٥/١]
ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል
~~~~ ~ ~ ~~~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~
ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት!!! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡
ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!

(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)
((ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡)) (አልሐጅ፡ 46)

በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!
ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና!!! አቡበክር አሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች የመጠቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!!!
ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሙት ነው?
ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ ((ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም)) አይደል ያለው ኻሊቁ?
አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
➩◉ዲንህን ➷እስካወቅክ ድረስ ➷አንተን ፊትና አትጎዳህም ➷ፊትና የሚጎዳህ ➷ሀቅ እና ➷ባጢል ተወሳስቦብህ ➷የትኛውን መከተል ➷እንዳለብህ ሲያደናግርህ ➷ጊዜ ነው‼️

📚((مصنف ابن أبي شيبه /٣٦٢٩٢))
ጀግናዬ፦ኢማሙ አሕመድ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ:-
•
"አሏህ የምትወደውን ነገር እንዲያዘወትርልህ ከፈለግክ አንተ አላህ በሚወደው ነገር ላይ ዘውትር"
•
【አል–ቢዳያ ወኒሃያ (10/330)】
ሰኞ እና መውሊድ ገጠመባቸዉ

የዘንድሮው መውሊድ ሰኞን ገጥሞባቸዋል ።
ታላቁ ነብይ ሰኞን ይፆሙት ነበር ። አመት ጠብቀው ልደታቸውን አየአከብሩም ነበር ።
ሰዎቹ ግን
የነቁና የበረቱ ተከታዮች አይደሉምና የነብዩን መንገድ በመተው ነብዩ ከሐላሉ በሚታቀቡበት ሰኞ ሐላሉን አለቅጥ ተሻግረውት አእምሮና ጤና የሚያውከውን ጫት ሲበሉ ይውላሉ ። የነሱ ተከታይነት በመንቀፍ ነው
ማሳሰቢያ ፣ የተወለዱበትን ቀን ጠብቆ በአመት አንድ ቀን መፆምም መሰረት የለውም ።

ነብዩን በስራዎቻችን ከመንቀፍ አላህ ይጠብቀን
t.me/Muhammedsirage
➾ ሸይኹል ኢስላም #ኢብኑ_ተይሚይያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
➺➾➾➾➺➾➺➾➺➾➺
(وأما اتخاذ موسم غير المواسم الشرعية، كبعض ليالي شهر ربيع الأول التي يقال: إنها ليلة المولد، أو بعض ليالي رجب، أو ثامن عشر من ذي الحجة، وأول جمعة من رجب، أو ثامن شوال الذي يسميه الجهال عيد الأبرار، فإنها من البدع التي لم يستحبها السلف، ولم يفعلها، والله سبحانه وتعالى أعلم)
«ሸሪዐዊ ያልሆኑ ክብረ በዓላትን ክብረ-በዓል አድርጎ
#መያዝ ግን ‘የመውሊድ ሌሊት’ የሚባሉትን የተወሰኑ የረቢዐል አወል #ሌሊቶችን ወይም የረጀብ ሌሊቶችን ወይም ደግሞ ዙልሒጃ አስራ ስምንትን ወይም ደግሞ የረጀብ #የመጀመሪያ ጁሙዐን ወይም ደግሞ መሃይማን ‘የደጋጎች ዒድ’ እያሉ የሚጠሩትን #ሸዋል ስምንትን የመሰሉ እነዚህ ሰለፎች እንደሚወደዱ ያልገለጿቸውና ያልተገበሯቸው #ቢድዐዎች ውስጥ ናቸው። ጥራት የተገባው #አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።»
[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/298]
አስተውይ እህቴ‼️
➖➖➖➖➖➖

✅ ለምን ይመስልሻል⁉️
〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ በሸሪአችን ሴት ልጅ፦
➲ነብይ ወይም ረሱል ተደርጋ ያልተላከችው
➲ቃዲ ሆና ፍርድ ሰጪ ያልተደረገችው
➲ኢማም ሆና ሰዎችን የማታሰግደው
➲ለሶላት እንድትጠራ ሙአዚን ያልተደረገችው
➲የሶላት ማእዘን የሆነውን ፋቲሀ ወንዶች ባሉበት ድምፇ ከፍ አድርጋ መቅራትን የተከለከለችው
➲ኢማሙ ቢሳሳት እንድታጨበጭብ እንጂ በድምፅ መመለስ ያልተፈቀደላት
➲በሀጅ ተልቢያ (ለበይከላሁመ ለበይክ) ስትል ድምፃ ከፍ እንዳታደርግ የታዘዘችው
➲በተከበረው ቁርአን ድምፃችሁ አታለስልሱ የተባለው
➡️ለምን ይመስልሻል⁉️

◾️መልሱ፦ የሴቶች ድምፅ ወንዶችን ስለሚፈትንና ስለሚያሳስት ነው። በዚህ ሰበብ ጥፋት ላይ ላለመውደቅ በሩን ለመዝጋት ሲባል ነው።

💢 ታዳ አላፊ አግዳሚው ባለበት፣ የሴት ልጅ አዳኝ ጠላቶች በበዙበት፣ ካፊር ፋሲቅ ሙናፊቁና የሁዳ በግልፅ በሚታይበት በየ ሚዲያው ድምፅሽን የምትለቂው፣ በቪድዮ የምትቀርቢው፣ ከወንዶች ጋር ያለሀጃ እንደፈለግሽ የምታወሪው እህቴ ሆይ ተይ ተመከሪ። ነገ አላህ ፊት ቆመሽ ከመጠየቅሽ በፊት ዛሬውን ተመለሺ። ዝናው፣ ጥቅሙ፣ ዳእዋውም፣ ለሴቶች ያለሽ ተቆርቋሪነቱም ቀርቶብሽ ባንቺ ድምፅም ሆነ በሌላ ነገር ወንዶች እንዳይፈተኑብሽ ማድረግሽ ይህ ትልቅ ጅሀድ ነው። አላህም ያዘዘሽ በዚሁ ነው። ማስተማርና መምከርም ከፈለግሽ ሴቶች ብቻ ባሉበት ወንዶች በማይገኙበት ቦታ ይሁን።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
◼️የተጅዊድ ኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖

↪️ሂዳየቱል ሙስተፊድ
👇👇👇👇👇
【ክፍል 1⃣7⃣】
〰〰〰〰〰

✅ የመድል አስልይ ማብራሪያ
✅ የመዱል ፈርእይ ክፍሎች
✅ መዱል ዋጂብ ሙተሲል


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

🔺ደርሱን ለመከታተል⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/https_Asselfya
↪️አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች “የአላህ መልክተኛ የሰኞን እና የሐሙስን ጾም (ለመጾም በጉጉት) ይጠባበቁ ነበር፡፡”
📚 (ቲርሚዚይ: 745)

✅ሙእሚኖች ለመልካም ነገሮች ጉጉቱ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሰኞ እና ሐሙስን መጾም፤ በየወሩ አስራ ሶስት፣ አስራ አራት እና አስራአምስተኛው ቀን መጾም፤ ዚክር (ተስቢህ ተህሊል ተህሚድ ማብዛት) ፤ ቁርአን መቅራት ፤ በሽተኛን መጠየቅ ፤ ወደተውሂድ ጥሪ ማድረግ ፤ ሰዎችን መልካም ነገር ማስተማር፤ በመልካም ማዘዝ፤ ከመጥፎ መከልከል የዘወትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል፡፡

🔻ሙእሚን አጋጣሚዎችን ይጠቀማል ፤ ጊዜውን ሳያባክን አላህ ለሚወደውና ወደርሱ ለሚያቃርበው ተግባር ይጠቀማል ፤ በቤቱም፤ በመንገዱም፤ በመስጅዱም ፤ በሁሉም ቦታ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ የአላህን ሰዋብ (ምንዳ) ተስፋ ያደርጋል ፤ የአላህን ቅጣት ይፈራል፡፡

https://t.me/joinchat/1dRtOLUW8mpkYzFk
◾️እውነተኛ የነብዩ ወዳጅ ቢሆኑ ኖሮ…
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ መውሊድ አክባሪዎች እውነተኛ የነብይ ወዳጆች ቢሆኑ የነገውን ቀን የአላህ መልእክተኛ ሲያደርጉት እንደነበረው ይፃሙ ነበር እንጂ በነሺዳ፣ በድቤ፣ በውዝዋዜ፣ በእርጥብ እሳት (በጫት) አያሳልፋትም ነበር። ምክንያቱም (المحب لمن يحب مطيع) (ወዳጅ ለወደደው ይታዘዛል) እንጂ አያምፅም። እነሱ ግን ነገሩ በተገላቢጦሽ አደረጉት።

ሀሳን ቢን አጥያ እንዲህ ይላል፦
(ما ابتدع قوم بدعة في دينهم إلا نزع من سنتهم مثلها)
(ሰዎች በዲናቸው ላይ ቢድአን አይፈጥሩም
የቢድአው አምሳያ የሆነ ሱና ከነሱ የተወገደ ቢሆን እንጂ።)
🔺ተመልከት የነገው ቀን ሱናው መፃም ነበር። ይህ ትተው የመውሊድ ቢድአ ሲፈጥሩ ሱና የሆነው ፃም ከነሱ ተወገደ።

አላህም በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»
(ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 31)


➡️ በዚህ የቁርአን አንቀፅ መሰረት የአላህን ውዴታና መሀርታ ለማግኘት እሳቸውን መከተል እንዳለብን ይነግረናል። ይህንን ትሩፋት ለማግኘት የተወለዱበትን ቀን አስመልክቶ የሳቸው ሱና መፃም እንጂ መውሊድ ማክበር አይደለም።

ወንድሜ መውሊድ በማክበርህ ወንጀል እንጂ ምታገኘው አንድም ትርፍ የለምና ከዚህ ቢድአ እራስህን አርቅ።

ለዚህም ነው አዩብ አሰህትያንይ እንዲህ አለ። (ما ازداد صاحب البدعة اجتهادا إلا ازداد من الله بعدا) (የቢድ ባለቤት በቢድአው ላይ ጥረት አይጨምርም ከአላህ መራቁ የጨመረ ቢሆን እንጂ)

➡️ በዚህ መሰረት አህመድ የመዲናው ወይም ሀቢቢ ሀቢቢ ወይም ነብይ ነብይ እያልክ እግርህ እስኪያብጥ ብትደንስ፣ እጅህ እስኪላጥ ብታጨበጭብና ላብ እስኪንጠባጠብህ ድረስ ብትወዛወዝ ወንጀልን እንጂ ምታገኘው አንዳች ጥቅም የለም።

ደሞ አስታውስ መውሊድ ባለማክበርህ ነገ አላህ ፊት ራሱ ብትጠየቅ በቁርአን ስላልተወሳ፣ በሀዲስ ስላልተጠቀሰ፣ ነብዩ ስላላከበሩትና ስላላዘዙት እንዲሁም ሶሀባዎች ስለማያውቁት አላከበርኩም ብለህ መመለስ ትችላለህ። ይህ ሁሉ ነገር እያወቅክና ብዙ ምክር እየሰማህ ባላየ ሆነህ በእልህ በማክበርህ ነገ አላህ ፊት ስትጠየቅ ምን ይሆን መልስህ?

አላህ ከቢድአ፣ ከሁራፋትና ከፊትናው ይጠብቅ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
القارئ إدريس أبكر | إنا أرسلنا نوحا إلى قومه
💭🌸خدمة تلاوات🎧​
▪️ቁርአን የልብ ብርሀን !
✅የዱኒያ የአሄራን ሂወት የሚያቀና ውብ የማይጠገብ የአላህ ቃል ነው።
↪️እናታችን አኢሻ በዘገበቺዉ ሓዲስ የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ትለናለች!

- عن عائشة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم - قال : ( ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها ) . رواه مسلم -
✅የፈጂር ሁለት ረካዎች ከዱኒያ እና በዉስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ።

📚[[ሙስሊም ዘግቦታል]]

💦እኒህ ሁለት ረካአ የተባሉት ከፈጂር ሶላት በፊት የሚሰገዱት ሱናወች ናቸዉ።


▪️ ነብያችን ﷺ አገርም ዉስጥ ሁነዉ መንገደኛም ሁነዉ አይተዋቸዉም ነበር።
ያረቢ አገራችንን ሰላም አድርግልን
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።