💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
اللهم اغفر لجميع المسلمين والمسلمات والمؤمنين والمؤمنات الأحياء منهم والأموات اللهم ضاعف لهم الحسنات وارفع لهم الدرجات وكفر عنهم السيئات.
~
ሰለፎች እርስ በርሳቸው እንዲህ ሲሉ አደራ አደራ ይባባሉ ነበር:-

* ለአኼራው ለሚሰራ ለዱንያው አላህ ይበቃለታል።
* በርሱና በ አላህ መሃል ያለውን ያሰተካከለ በርሱና በሰዎች መሃል ያለውን አላህ ያሰተካክልለታል።
* ውሰጡን ያስተካከለ ውጩን አላህ ያስተካክልለታል።

#ማስታወሻ
👍8
🔖ዲን ያላት ሴት የምትባለዋ የትኛዋ ሴት ነች ...??

     ሼኽ ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ፦

🔻ዲን ያላት ሴት የምትባለዋ - የአላህን ትእዛዝ ቀጥ አድርጋ የምትፈፅም፣   የባሏን ሀቅ የምትጠብቅለት የሆነችዋ እና እንዲሁም አልጋውን፣ ልጆቹን፣ ገንዘቡን የምትጠብቅለት የሆነችዋ ነች።

🔹 እንዲሁም አላህን በመገዛት ላይ {በዒባዳ ላይ}} የምታግዘው፣ ሲረሳ የምታስታውሰው፣ ሲዳከም የምታነቃው፣ ሲቆጣ የምታስደስተው የሆነችዋ ሴት ነች፡ ይች ነች ዲን ያላት ሴት የምትባለዋ።

📒 ኪታቡ ዘዋጅ (20)

t.me/https_Asselfya
የምንከታተለው
1- ወደ ጀነት የሚያቀርበን፣ ከእሳት የሚያርቀን ይሁን።
2- ለዲናችንም ይሁን ለዱንያችን የሚጠቅመን ይሁን።

ከዚህ ውጭ ያሉ ለኣኺራችንም ይሁን ለዱንያችን ጉዳት ያላቸው ይዘቶችን የሚለቁትን ሃይማኖታዊም ይሁኑ ሌላ አካውንቶችን፣ ፔጆችን እንራቅ። #ዘወትር ፋይዳ የሌላቸው እንቶ ፈንቶ ከመከታተልም ጥንቃቄ ብናደርግ መልካም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🫵ለባልሽ ያለሽን ቅናት በልክ አድርጊዉ!


ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን፣ አላህ ይዘንላቸው፣ እንዲህ ብለዋል፡-

« من طبيعة المرأة أن تغار على زوجها ، وهذا دليل على محبتها له ..

«ከሴት ባህሪ በባሏ መቅናት ነውይህ ደግሞ ለእሱ ያላትን ፍቅር የሚያሳይ ማስረጃ ነው።

« ولكني أقول : الغيرة إذا زادت صارت غبرة وليست غيرة ، وتتعب المرأة تعباً شديداً  !!

«ሆኖም፣ እንዲህ እላለሁ፡- ቅናት ከመጠን በላይ ከሆነ ከልክ ያለፈ ይሆናል እና እውነተኛ ቅናት አይሆንም፣ እናም ሴትን ከፍተኛ ጭንቀት ያስከትላል!

«لذلك أشير على المرأة أن تخفف من غيرتها ..

«ስለዚህሴቶች ቅናታቸውን እንዲቀንሱ እመክራለሁ።

{ اللقاء الشهري [ ٣١ ] /فتاوى_المرأة }


𝑻𝒆« t.me/abu_reyyis_arreyyis
👍10
(وتزودوا فإن خير الزاد التقوى)

ተሰነቁ።መልካሙ ስንቅ ማለት አላህን መፍራት ነው ይለናል አላህ

አካል ስንቁ መብል እና መጠጥ ነው። ነፍስ ምግቧ ተቅዋ ነው። እናም አካላችን ጠግባ ሩሃችን የተራበች እንዳትሆን እንጠንቀቅ።

#ማስታወሻ
👍7
~አቡ ደርዳአ እንዲህ ይላሉ
#እኔ በጣም የምፈራዉ ነገር የቂያማ እለት ለሂሳብ ስቆም፦ባወከዉ ምን ሠራህ እንዳልባል ነዉ።

  ~
      t.me/https_Asselfya
👍4
قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ

«እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ በላቸው። አላህ ኃጢኣቶችን
በሞላ ይምራል። እነሆ እሱ አዛኝ
መሀሪ ነውና!
[  سورة الزُّمَرِ]


t.me/https_Asselfya
👍3
"ወሀብያ" አግቢ!

ትክክለኛ ወሀብያ የሆነ ወንድ እንኳንስ ገላው በዝሙት የሌላ ሴትን ገላ ሊነካ ቀርቶ፡

~ከአጅነብይ ሴት ጋር አይደባለቅም!
~ከአጅነብይ ሴት ጋር በማህበራዊ ሚዲያ አይለፋደድም አይጀናጀንም!
~አጅነብይ ሴትን አፍጥጦ አያይም!
~አጅነብይ ሴትን ፈፅሞ አይጨብጥም!

ታዲያ ከዚህ በላይ ባሏ ለሷ ያልለው ታማኝነት በምን መልኩ መግለፅ ይችላል?

ሀቂቃ ባሏ እንዲህ አይነቱን ባል እንዲሆን የማትፈልግና የማትወድ ሴት ትኖራለችን?

ስለሆነም ለጌታውም ላንቺም ታማኝ የሆነ ባል ከፈለግሽ፡ ትክክለኛ ሱንይ ሰለፍይ፡ አህባሽ እንደሚለው ደግሞ "ወሀብይ" የሆነውን ወንድ አግቢ!

ፈጅር-ንቁ|አንቁ!

منقل
👍23
"በተውሂድ የታነፀ ሰብእና ቢለምን ከጌታው ነው ቢታገዝም በጌታው ነውአንተ ልጄ ሆይ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ ስትጠይቅ አላህን ጠይቅ ስትታገዝ በአላህ ታገዝ ልጄ ሆይ እወቅ! ህዝቦች ባጠቃላይ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ለንተ በፃፈልህ በሆነ ነገር እንጂ አይጠቅሙህም በሆነ ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሳቡም አሏህ በንተ ላይ በፃፈው ነገር እንጂ አይጎዱህም ብእሮቹ ተነስተዋል! መዝገቦችም ደርቀዋል። የሚለው የነብዩ ሰላለሁ አለይሂ ወሰለም ድንቅ ሀዲስ የህይወት መመሪያው ነው።

[አልሚሽካት:5302]

t.me/https_Asselfya
👍2
ወዳጄ ጠንካራ ሁን!

እዛጋ አንድ እንኳ ለአንተ የሚቆምልህ ስታጣ ራሥህን ታድን ዘንድ ጠንካራ ሁን
👍6
(وَلَا یَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ أَیُحِبُّ أَحَدُكُمۡ أَن یَأۡكُلَ لَحۡمَ أَخِیهِ مَیۡتࣰا فَكَرِهۡتُمُوهُۚ)

ከፊላችሁ ከፊሉን አይማ።አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞቶ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱንም እንደጠላችሁት ሃሜቱንም ጥሉት ብሏል የላቀው አላህ።
የሞተ ሆኖ ሰጋውን መብላትን እርም እንዳደረገባችሁ በህይወት እያለ እሱን ማማትንም እርም አድርጎባቹሃል።ሞቶ ስጋውን መብላት እንደጠላችሁት በህይወት እያለ የሱን መታማትንም ጥሉ።(ተፈሲሩ ጠበሪይ)

ሰውን የሚያማ ሰውን አላህ በሰዎች የሚጠላ እንዲሆን በማድረግ እንደሚፈትነው አመላካች ነውም ይላሉ።ምክነያቱም ሃሜት ተናጋሪ ሃሳቡ የሚያማውን ሰው ሰዎች እንዲጠሉት በማሰብ ስለሆነ ሀሳቡ ተመልሶ በራሱ ላይ ተፈፃሚ ሆኖ ያገኘዋል።

#ማስታወሻ
🔖ሼኸ ሷሊህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

አንድ ሙስሊም ከሌሊት ሶላት ቁጥሩ ቢያንስም እንኳን ሁሌም የሚዘወትርበት የሆነ የተወሰነ ድርሻ ሊኖረው ይገባል

📚الملخص الفقهي(صـ ٩٣)
=
         t.me/https_Asselfya
👍9
«ከምላስህ ይልቅ ተግባር ማንነትን ይገልፃል!!

«እውነተኛ ባልሆነ ማንነታችን ሠዎች ዘንድ መልካም መስሎ ለመታየት ከመጣር ይልቅ እውነተኛ ማንነትን አውቆ ለለውጥ መንቀሳቀስ ምንም ጊዜው ቢረዝም ውጤቱ ግን ታላቅ ነው!!!
🔖ኢማም አላማህ አል-ሰአዲይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፡-

አላህ ለሙእሚን ባርያ ከለገሰው ታላቅ ፀጋ መካከል አንዱ ምርጥ አማኝ ጓደኞችን መስጠቱ ነው።ከአንድ ሰው ቅጣቶች መካከል በክፉ ጓደኞች መፈተኑ ነው። የምርጥ አማኝ  ጓደኝነት ሰውዬውን ወደ ከፍተኛ ደረጃዎች ወደ ጀነት ለማድረስ ምክንያት ሲሆን የመጥፎ ሰው ጓደኝነት ደግሞ ጥሩ ሰዎችን ወደ አዘቅት ወደ እሳት ለማውረድ ምክንያት ነውና።የምርጥ ሰዎች ጓደኝነት ትልቅ ስነምግባር ላይ እና ጠቃሚ እውቀት ላይ ያደርስሃል። የክፉ ሰዎች ጓደኝነት ደግሞ እነዚህን ሁሉ ያሳጣሃልና።

📚[شرح جوامع الأخبار) للسعدي(189)] .

t.me/https_Asselfya
Forwarded from ስለ ቀልባችን
~ከ ወንጀል ዉጤቶች መካከል አንዱ«ስኬትን ማጣት ነው» ይላሉ ኢብኑ አል-ቀይም ረሒመሁላህ፡፡

ወንጀል ባንተ እና በጌታ መካከል እክል ነው፤ ጋሬጣ ነው፣ ግርዶ ነው፡፡ለምነህ ለዱዓህ ምላሽ አታገኝም፣ ሠርተህ ከድህነት አትወጣም፣ አስበህ አይሳካልህም፣ ተወዳድረህ ትሸነፋለህ፣ ለሥራና ለትህምርት ተፈትነህ ትወድቃለህ፣ ምኞትህ አይሰምርልህም፣ ያቀድከው አይሆንልህም፡፡ ምክንያቱም ነገሮች መንስኤና ዉጤት አላቸውና፡፡

የወንጀል ባለቤት ከሆንክ እቆጥባለሁ ብትልም አይሆንልህም፣ ወንጀል ብል ነው፡፡ ኃጢኣት ተምች ነው፤ ኃጢኣት ቫይረስ ነው በልቶ ይጨርስሃል፤ አተንም ፀጋህንም ይበላል፡፡ የኃጢኣት ዉጤቱ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ አየርን ይለውጣል፣ ቤትን ያበላሻል፣ ትዳርን ያደፍርሳል።

ወንጀልህ ሲበዛ ፊትህ ይጠቁራል፣ ኑርህ ይጠፋል፣ ሞገስህ ይገፈፋል፡፡እናም ለአንዳንንድ ነገሮች ጓጉተህ፣ አንዳንድ ነገሮችን ሞክረህ …. አልሳካ  ያለህ እንደሆነ መለስ ብለህ ራስህን ፈትሽ፡፡ ከስኬትህ ያገደ ጋሬጣ ሊኖር ይችላልና ያንን አስወግድ፡፡ ከራስህ ጀምር። ከማሳበብህ በፊት ሁኔታህን መርምር።

አላህ ይርዳን!
👍1
‏قال الإمام #ابن_القيم - رحمه الله - :

اليقين أفضل مواهب الربِّ لعبدِه؛ ولا تثبت قدم الرِّضا إلَّا على درجة اليقين.

[ مفتاح دار السّعادة (ص١٥٥) ]
🔖ኢማን ያልቃል ያለን ግንዛቤ በየጊዜዉ እየሟሸሸ ሊሄድ ይችላል። ከግዜ ርዝመት ጋር የልብ ድርቀት ሊገጥም ይችላል። ኢማናችን ልክ እንደ ልብስ ሊያልቅ ይችላል ።

عن عبد الله بن عمرو  قال: قال رسول الله ﷺ: إن الإيمان ليخلق في جوف أحدكم كما يخلق الثوب، فاسألوا الله أن يجدد الإيمان في قلوبكم

📚 [رواه الطبراني في المعجم الكبير: ،وصححه الألبانيفي صحيح الجامع:

~የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል። 

~በአንዳችሁ ቀልብ ዉስጥ ኢማን ያልቃል።
ልክ ልብስ እንደሚያልቀዉ ኢማን ያልቃል ።አላህ ኢማናችሁን እንዳዲስላችሁ ለምኑት ።

~በየግዜዉ  ዲናችንን ማደስ አንድ ጊዜ ተረድቻለሁ ብለን አለመዘናጋት ለማስፋት መታገል አለብን።

🔖ሼኽ ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ሰዎች ሲያወዲሷቸዉ እንዲህ ይላሉ፦
~በአላህ ይሁንብኝ አሁን ድረስ እስላሜን በየጊዜዉ አድሳለሁ በሁሉም ወቅት ገናየተሟላን የሆነ እስላምን ሰልሜለሁ ማለት አልችልም
من أقوال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله : (وأنا أحلل كل مسلم . وأنا أحب الخير للمسلمين بل لجميع الناس . والله إني إلى الآن أجدد إسلامي كل وقت وماأسلمت بعد إسلاماً جيدا 

~ድናቸዉን ለመጠበቅ ግንዛቤቸዉን ለማስፋት ወደ አላህ ያላቸዉን ቅርበት ለመጨመር ። የበለጥ እታገላለሁ እያሉ ነዉ
~
t.me/https_Asselfya
👍1
نسائمُ القرآن عليلةٌ، تزيحُ الهموم وتسكنُ النّفس وتريح الرّوح.