💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.73K subscribers
1.27K photos
494 videos
123 files
5.14K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
18-القواعد الحسان
ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሸይኽ ኣደም
🔖 አዲስ ተከታታይ ደርስ

📚የአል_ቀዋዒዱል_ሒሳን ኪታብ

~ ክፍል - 18

🎙️ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሸይኽ ኣደም

የኪታቡን  Pdf   ለማግኘት* ↓↓↓
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/8593
Forwarded from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] (Muhammed Ibnu Fedlu [Abu Nuh])
ይህ የሞባይል መተግበሪያ ተፍሲር ጁዝእ ዐመ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ መልኩ ሙሉ ክፍል ደርስ አጠቃሎ ይዟል።

𑁍ቂርዓት አቅራቢ፦
ሸይኽ ያሲን ሙሳ ጧሂር ሐፊዞሁላህ

𑁍መተግበሪያው ከያዛቸው በጠቂቱ፦

- የድምፅ ማብራሪያ፣
- ቁርአን በፅሑፍ፣
- ሌሎችም...

አፑን በሚከተለው ሊንክ ይጫኑ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.quran.tefsir.ammah
⚠️ሞት ሁሌ አድስ እንግዳ!!

መካሪ እኮ የለም ትልቅ  እንደ ሞት
አንኳኩቶ ይገባል ድንገት ወደ ቤት
ሲመጣ አያማክር በድንገት ከች ነዉ
እቅድ ሲደረድር የተዘናጋዉ ሰዉ
ከመጣ ብኋላ መላሽ የሌለዉ
ችላ ባይ የሆነዉ የኔ ቢጤ ሰዉ
ያኔ ይባንናል የተዘናጋዉ

በደስታ እየኖሩ ድንገት ይመጣና
የደረሰባት ነፍስ ጠጋ ይላትና
የተላኩኝም ነኝ ከላይ ከረበና
እያለ ይላታል እዉነት ይዟልና
፣

አጀል ከደረሠ የለም ወደ ኋላ
ኸይርን አልሠራሁም አይቻል ብኋላ
ቆራጡ ከመጣ ጥፍጥና ቆራጩ
የሚያድነን የለም ፍጡራን ቢንጫጩ
፣

ጨለማዉ ሲመጣ ትልቁ እንግዳዉ
የማይለመደዉ ሁል ጊዜ አድስ ነዉ
ከእንግዶችም በላይ ትልቁ እንግዳ ነዉ
ቀላል ይመሥለናል ሌሎች ቤት ስናየዉ


ነገር ግን  ሲመጣ በዬ ሁሉም ቤት
ያለ ድንጋጤ ያለዉም ጭንቀት
ብርቱ የሆነ ነዉ የማይቀረዉ ሞት
ዱንያ አንዱን አክብራ አንዱን እያስጠማች፡
ሰው ሆይ ልብ እንግዛ ለዚህች ምድር ዘማች፡
እባክህ አስተውል ስማኝ የነገ ሟች!?

ነፍስ ያላትን ፍጥረት ሁሏንም ያጉዛል፡
በማንም ፍጡር ላይ ሽብርን ይነዛል፡
ጀናዛ ተብሎ ሁሉም ይገነዛል፡
ትልቅ አይል ትንሽ ፈሪም አይለይ ጀግና፡
ሁሉንም በተራው ያጉዘናል ገና...

እድሜ አይገድብ ፆታ አይመርጥም ቁንጅና፡
አይፈራም ትልቅ ሰው አያከብር እርጅና፡
ሰውን በአቋሙ በስራው አይመዝን፡
ለሴትም ለወንድም ለወጣት አያዝን፡


ምንም ሀብታም ቢሆን ገንዘቡ ቢቆለል፡
ልመና አያስቆመው በጉቦ አይደለል፡
በአሏህ ከታዘዘ ከተላከ ለኛ፡
መኪና አሽከርካሪ ቢሆን ከብት እረኛ፡


እጂግ የከፋ ሰው ወይ ደግሞ ኸይረኛ፡
ይፈፅማል ትዕዛዝ ሞት የፍትህ ዳኛ፡
መልካም ሥራ ሰርተን ካልሆነን ለአኺራ
ከአፈር በታች ገብተን ስለ እኛ ቢወራ
ስምችን ቢነሳ  በአለም ላይ ቢጠራ


የሠራነዉ ስራ ከሆነ ገለባ
ለአኺራ ካልሆነ ለኛ ምን ሊረባ
ጨለማዉ ተገፎ ቀብር ካላበራ
ምን ሊጠቅም ወሬ ዝናሥ ምንሊሠራ


ደስታን አያገኝም ከአንተ የሸሸ
ይቅር በለኝ ብዬ መጣሁ ተመልሸ
ይቅር ባይ ነህና ከሁሉም በላይ
እጆቸን አንስቸ ዳግም ወደ ላይ
ይቅርታን ጠየኩህ ሀያሉ ጌታዬ
አስጨነቀኝ እና የመጨረሻዬ

ኻቲማዉ ሲያምር ነዉ ስኬታማ ማለት
ኸይር ስራ ሰርቶ ወንጀል ተምሮለት
ይሔ ነዉ ትልቅ ሰዉ ስኬታማ ማለት
ከአዛብ ተጠብቆ የገባ ከጀነት።


✍ኡሙ በህረዲን

=
🔖ከፊል ሰለፎች እንዲህ ይሉ ነበር ፦

‹ሰዎች ሆይ!› አባታችን ኣደም "ዓለይሂ'ሰላም" በአንዲት ወንጀል ምክንያት ከጀነት መውጣቱን እያወቃቹህ!፣ እናተ ደግሞ ወንጆሎቻቹህን እያበዛቹህ ጀነት መግባት ትፈልጋላቹህን! ?

[ሊጧኢፉ-ል'መዓሪፍ ሊብኒ ረጀብ 57]

~
ከአላህ ፍራቻ አንፃር ዐይናችን እንባ ከቋጠረች ሰላም ነን። የደረቀች እንደሆነ ግን አደጋ ላይ ነን።

=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🫵 " ትሄዳለህ! ዛሬ ወይ ነገ! " 🫵

ድንቅ ምክር!👌

🎙ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን
ጋብቻ
ሐጂ መሐመድ ወሌ
🔖ጋብቻ..!

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ወሌ
ረሒመሁላሁ ተዓላህ

t.me/https_Asselfya
አንዳንዴ ......!

አድምጡ ግብዣ ነዉ

=
"ሰው ቅጠ ቢስ ሁኖ ተፈጠረ"

አሏህ ምን ይለኛል? እንበል፡ የመርህና የአቋም ሰው እንሁን፡

ከዚህ በዘለለ ግን ለራሱ ቅጥ ላጣ ሰው፡ ሰው ምን ይለኛል? ብሎ መጨነቁ ተገቢ አይደለም።

t.me/https_Asselfya
ያንቺን አመጡና፡ ለኔ ነገሩና
የኔን ወሰዱና፡ ላንቺ ነገሩና
ተደላድለው ተኙ፡ አለያዩንና

አለ ገጣሚው።

ከገጣሚው ህይወት ትምህርት የወሰደ ሰው፡ ሕይወቱን ሁሉ በጥንቃቄና በብስለት ይመራል፡

በአሏህ ፈቃድም በክፉ አሳቢዎችና አላዋቂዎች ላይ #ተረማምዶ አላማውን ከግብ ያደርሳል።
👍1
سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَـهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتُوْبُ إِلَيْكَ.

~
🔖 የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅና ትሩፋቶቹ

ሸሪዓችን ካበረታታቸውና እኛ ችላ ካልናቸው መልካም ስራዎች ውስጥ ሰዎችን ማስታረቅ አንዱ ነው። 
ኢስላም የፍቅር፣ የአንድነትና የመቻቻል ሀይማኖት ነው። አሏህ በሱረቱንኒሳእ እንዲህ ይላል ፦

۞ لَّا خَيْرَ فِي كَثِيرٍ مِّن نَّجْوَاهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَاحٍ بَيْنَ النَّاسِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡ (ኒሳእ:114)

ረሱልም   ሰዎችን የሚያስታርቅ ሰው ብዙ አጅር እንደሚያገኝ በበርካ ቦታዎች ነግረውናል። ለአብነት ያክል፦
አቡድደርዳእ (ረ.ዐ) ባወራው ሀዲስ ረሱል   <<ከሶላት፣ ከጾምና ከሶደቃ የተሻለን ነገር ልንገራችሁ?>> አሉ። እንዴታ ይንገሩን አሉ ሶሀቦቹ።
ረሱልም   << የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ ነው>>  አሉ።[ ኢማሙ አሕመድ: 27,508 ]

ሰዎችን ለማስታረቅ መዋሸት ይፈቀዳል።
አሙ ኩልሱም (ረ.ዐ) ነብያችን   ውሸትን ለሶስት ነገሮች እንጅ አይፈቅዱም ነበር ትላለች። ከሶስቱ አንዱ ሰዎችን ለማስታረቅ ነው።
[ሶሂሁ ሙስሊም 2605]

አሏህ የተግባር ሰዎች ያድርገን

منقول
t.me/https_Asselfya
💎ብልህ እና አኺራዋን ያስበለጠች እንስት
በትዳር ህይወቷ ለአሏህ ትእዛዝ የሚያግዛትን የሚያቃርባትን እና ልጆቿን በተርቢያ የሚያሳድግላትን ስትዘነጋ የሚያስታውሳትን
ዲኑን ብላ ገንዘብ የለለውን ትመርጣለች
ገንዘብ አያስፈልጋትም አይደለም። ነገር ግን
አሏህ በረዘቃቸው አመስግና ተብቃቅታ የዱኒያን ህይወት ትገፋለቸ።

በዱኒያ ቁሳቁስ የተሸወደችዋ ደሞ ገንዘቡን ውበቱን ብላ ዲን የለለውን ትመርጣለች።

=
t.me/abuUseyminabdurehman
በሚድያ  የሚያስተምሩ፣የሚያቀሩ፣ሙሀደራ የሚያደርጉ፣የሚፅፋ  መሻይኾች፣ኡስታዞችና ወንድሞች. ማበረታታት፣ማጠናከር፣ሞራል መስጠት፣ጠንካራ ጎናቸውን ማጉላት ደካማ ጎናቸውን መደበቅና እንዲያርሙና እንዲያስተካክሉ ጥቆማ በመስጠት የግል ሀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል። እየሰሩ ያሉት ሾል እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም። ግዜ ይፈልጋል።   ግዜ ሰጥተው፣ዋጋ ከፍለው የፃፋትን፣ያቀሩትን፣ዳእዋ ያደረጉትን.  ማንበብ፣መቅራት፣ማዳመጥ ይኖርብናል። ለሌሎችም ሟር በማድረግ ማሰራጨት  ማካፈልም የኛ ድርሻ ነው።  ዳእዋ መሻይኾችላይ ኡስታዞች ላይ ብቻ የተጣለ ግዴታ. አይደለም። ተራው ሰውም በሚችለው.  ሊያግዝ ግዴታው ነው። አሁን አሁን ላይ ሚድያው ከኢስላም ተቃራኒ በሄኑ ነገሮች  ዘመቻ ተከፍቶበታል።ሙዚቃው፣ድራማው፣ዛዛታው፣ነሺዳው፣መንዙማው፣ተራ ወሬው ሚዲያውን እየተቆጣጠረው ይመስላል።  እኛም ያቅማችንን ለትውልድ ኢስላምን ተውሂድን፣ቁርአንን፣ሀዲስን በማሰራጨት ሚድያው ላይ ሰፊ ሚና ሊኖረን ግዴታ ነው።

@AbuHafsaYimam