💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
9.68K subscribers
1.29K photos
494 videos
124 files
5.15K links
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Download Telegram
هل فرّق الرسول صلى الله عليه وسلم بين الكفار عندما قاتلهم ❗️
Anonymous Quiz
71%
نعم فرّق بينهم
29%
كلا لم يفرّق بينهم
🔖ሁለቱ ቆንጆ ባህሪያት!

ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿عليْكَ بحسْنِ الخلُقِ، وطولِ الصمْتِ، فوالذي نَفْسِي بيدِهِ ما تَجَمَّلَ الخلائِقُ بِمِثْلِهِما﴾

~“በመልካም ስነምግባር እና በረጅም ዝምታ ላይ አደራችሁንነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከፍጡራኖች በእነሱ (በሁለቱ ባህሪያት) እንደተዋበ አይነት ሰው ማንም የለም።”

📚 አልባኒ በሶሂህ አልጃሚ ውስጥ ሀሰን ብለውታል: 4048

~
t.me/https_Asselfya
"ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ"
~
የልጅ አእምሮ ነጭ ወረቀት ማለት ነው። እኛ ዋዛ የሚመስሉንን ብዙ ነገሮች እንደ ቁምነገር ይይዛል። በልጅነቱ የሰው ጅብ ወይም ጭራቅ የሚባል አለ ብለው ስለነገሩት ካደገ በኋላም እንዲህ የሚባል ነገር አለ ብሎ የሚያምን ብዙ ሰው አለ። በርግጥ ከእድገት ጋር የሚቀየሩ ነገሮች አሉ። ቢሆንም ኋላ ተቀየረም አልተቀየረም ለህፃናት ያልሆነ ነገር እየነገርን አእምሯቸው ውስጥ የተዛባ ነገር እንዳንተክል መጠንቀቅ ይገባል። ከዚህ ጋር የተያያዙ እንደየሃገሩ እንደየባህሉ ብዙ ልማዶች አሉ። ለምሳሌ፦
* ህፃናት ሲጫወቱ "ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ" እያሉ መዘመር። ይሄ ሺርክ ነው።
* ጥርሳቸውን ሲጥቅሉ "አይጢቷ! የኔን ወስደሽ ያንቺን ስጪኝ" ብሎ ጣራ ላይ መጣል። ይህም ሺርክ ነው።
* ጆሮ ደግፍ ሲያዛቸው የሰው ቤት በድንጋይ እንዲመቱ መላክ። በዚህም ውስጥ ትንሹ ሺርክ አለ።
* የቀብር አፈር ቤት ላይ መበተን። ልጆች ውጭ ላይ አጥፍተው ሲመጡ ቤተሰብ እንዳይቀጣቸው ሲፈሩ የቀብር አፈር ይዘው በመምጣት ቤት ላይ ይበትናሉ። በቃ ይህን ሲያደርጉ ቤተሰብ ስለዚያ ጉዳይ አይጠይቅም ብለው ያምናሉ። በዚህም ውስጥ ሺርክ አለ።
መስጠት የፈለግኩት ጥቆማ ነው። እነዚህና መሰል ባህሎች ዛሬ ከተማ ውስጥ በብዛት አይኖሩም። ግን አንዳንዴ የማንጠብቀው ነገር ይዘው እናገኛቸዋለን። ስለዚህ ልጆቻችንን በጨዋታም ይሁን በቁም ነገር፣ በእምነትም ይሁን በልማድ መልክ የተዛባ ነገር እንዳይዙ መጠንቀቅ መልካም ነው። አንዳንዱ በጨዋታ መልክ የሚቀርብ ቢሆንም በሺርክ መቀለድ በእሳት መጫወት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ወሬ በበዛበት ጊዜ ዝምታ "በረሃ ላይ እንደበቀለ ዛፍ" ጌጥ ነው።

t.me/AbuOubeida
t.me/AbuOubeida
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
📓 العبادة لا تُسمَى عبادة ‼️

إلا مع
•••
العبادة لا تُسمَى عبادة إلا مع

التّوحيد .

📓 قال
#الشيخ_عبد_الرزاق_البدر_حفظه_الله :

✔️ والعبادة لا تكون
#عبادة إلا مع التوحيد ، بأن يكون #العبد موحداً لله جل جلاله ، مخلصاً في #عبادته كلها ، بأن تكون #صلاته لله ،وحجه لله ، ونذره لله ، دعاؤه #يتوجه به إلى الله ، توكله على الله ، رجاؤه من #الله ، خوفه من الله ، وهكذا بكل عباداته لا #يصرف منها شيئا إلا لله سبحانه وتعالى...

  {وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ } [البينة:٥].

{أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ} [الزمر :٣]

{وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا} [الجن :١٨]

والآيات في هذا المعنى كثيرة .

📖 شرح القواعد الأربع .
👍1
"እኔ" ገደል እንዳይከተን
~
"እኔ እኔ" ሲበዛ ለሰሚው ያቅለሸልሻል። ድንበርም ያስታል። ለራስ የተጋነነ ግምት ማሳደር ጎንበስ ብሎ ለመማር እንቅፋት ይሆናል። በ "እኔ" የተለከፈ ማንነት ከኢኽላስ ጋር የመጣላቱ እድል ሰፊ ነው። እዚህ ላይ አንድ የሚደንቅ የሶሐቦች ስብእና አለ። ከሚያስተላልፏቸው ገድሎች ውስጥ የራሳቸው ሲሆን ጊዜ "አንድ ሰው እንዲህ አድርጎ" በማለት እንደዋዛ የአንድ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው ጉዳይ በሚመስል መልኩ የሚያቀርቡበት ሁኔታ አለ። ታሪኩ በሌላ አቅጣጫ ሲፈተሽ ግን የራሳቸው ገድል ሆኖ ይገኛል። ሱብሓነላህ!

ኢኽላስን ለማረጋገጥ፣ ስግብግብ ነፍስያን ለማሸነፍ፣ በራስ ፍቅር ክንፍ ከማለት ለመዳን "እኔ፣ እኔ" በሚል ክፉ ስሜት ላይ ጦርነት ማወጅ ያስፈልጋል። ነፍሲያን ጉሮሮዋን አንቆ መያዝ። የኢኽላስ ነገር ለነፍሲያ ፈተና ነው። የአንድ ሸይኽ ደርስ ላይ የሚገርም ገጠመኝ ሰማሁኝ። የሆነ ሰው ሌሊት እየተነሳ ሶላት መስገዱ ማንም ዘንድ አለመታወቁ ይከነክነዋል። እና በብልሃት ሰጋጅነቱን ማሳወቅ ፈለገ። ፋርማሲ ገባና

* "በሌሊት ሶላት ምክንያት ለሚሰማ ድካም የሚሆን መድሃኒት አለህ ወይ?" ብሎ ይጠይቃል።
- "የለኝም" አለው።
* "እሺ ሷሊሖችን ትውዳለህ'ንዴ?" ብሎ ይጠይቀዋል።
- ፋርማሲስቱ ነገሩ ቢገርመው አሳለፈው።
* "ለማንኛውም ሷሊሖችን ውድድ አላህ ይወድሃል" ብሎት ወጣ።

"እኔ" ይሉኝታ ያሳጣል።
"የኔ" ስግብግብ ያደርጋል።
"እኔ ዘንድ" ትእቢት ያወርሳል።

እነዚህ ስሜቶች ልባችንን እንዳይቆጣጠሩ መጠንቀቅ ይገባል። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
" 'እኔ'፣ 'የኔ' እና 'እኔ ዘንድ' ማለት ድንበር እንዳያልፍብህ መጠንቀቅ ይገባል። እነኚህ ሶስት ቃላት ኢብሊስ፣ ፊርዐውን እና ቃሩን ተፈትነውባቸዋል።
👉🏾 'እኔ ከሱ በላጭ ነኝ' የሚለው የኢብሊስ ነው።
👉🏾 'የግብፅ ግዛት የኔ ነው' የሚለው የፊርዐውን ነው።
👉🏾 '(ሀብቱን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው' የሚለው የቃሩን ነው።

➡️ 'እኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'እኔ ባሪያ ነኝ'፣ 'እኔ አጥፊ ነኝ'፣ 'እኔ ምህረትን ለማኝ ነኝ'፣ 'እኔ ወንጀለኛነቴን የማምን ነኝ'፣ ... በሚለው የባሪያ ንግግር ውስጥ ነው።
➡️ 'የኔ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ 'የኔ ወንጀል'፣ 'የኔ ውርደት'፣ 'የኔ ድህነት' በሚለው ውስጥ ነው።
➡️ 'እኔ ዘንድ' የምትለዋ ቃል ያረፈችበት ያማረ ቦታ ደግሞ 'ምሬንም ሆነ ቀልዴን፣ ስህተቴንም ሆነ አውቄ የፈፀምኩኑን ምህረት አድርግልኝ። ይሄ ሁሉ እኔ ዘንድ አለና' በሚለው ውስጥ ነው።"

📖 [ዛዱል መዓድ]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
~ምቀኝነት ከእውቀት ማነስ የሚመነጭ
ትልቅ የአዕምሮ ድህነት ነው!

~
هل يوجد فرق بين مشركي زماننا و المشركين الأولين ‼️
Anonymous Quiz
87%
نعم
13%
كلا
አንድ ሰው እንደት እንደዚህ ደስተኛ ሂዎት ሊኖርህ ቻለ ተብሎ ሲጠየቅ
አላህን በድብቅ ማመጽ ትቸ ብሎ መለሰ!
ብዙዎችን የከበደው. ይህ ነው።

~
سعادة المرأة في تغطية الوجه!!
Audio
ወንጀሎችን መራቅ ተውሂድን ከማረጋገጥ ውስጥ ነው

አጭር ምክር ሙሐመድ ሲራጅ
https://t.me/MedrestuImamuAhmed

https://t.me/Muhammedsirage