💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
✅ሐያእ (አይናፋርነት) ለሴት ልጅ ትልቁ ሀብቷና ውበቷ ነው!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖


↪️ሐያእ በመሰረቱ ወንዱም ሴቱም ጋር ሊኖር የሚገባው ተወዳጅ ምርጥ ባህሪ ነው። በተለይ መልኩ ግን ሴቶች ዘንድ ወሳኝነት አለው። ይሁን እንጂ ሐያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር አላህ ካዘነላቸው ጥቂት እንስቶች በስተቀር ብን! ብሎ የጠፋ ይመስላል። ሴት ልጅ አይናፋርነት ከሌላት እንዲሁ ባህሪዋ ለባሏ እንኳ አይማርከውም፣ ምክንያቱም አይናፋርነት ለሴት ልጅ ከፈጣሪዋ የተሰጣት ልዩ ውበትና ግርማ ሞገሷ፣ ተፈጥሯአዊ የሆነ ስጦታዋ ነውና። ሀያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር ከብዙ ሴቶች ልብ ድራሹ ጠፍቶ በስመ ስልጣኔ ጋጠ-ወጥ ሴቶች አስባልቱን ከሞሉት ሰነባብቷል። እንዲያውም አንዳንዴ በተቃራኒው ሀያእ የሚባለው ነገር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ዘንድ ይስተዋላል።
"
↪️እህቴ ሆይ! ቁርኣን አንድን ነገር ሲጠቅስ ያለ ምክንያት አይደለም!። ይልቅ ከእኛ መተገበሩ ወይም መጠንቀቁ ተፍልጓል ማለት ነው። ለምሳሌ አላህ ስለ ነቢዩላህ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ስደት ላይ ሆኖ የገጠመውን ሲተርክ እንዲህ በማለት የአንዲትን እንስት አካሄድ አውስቷል:-

فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ

⏯«ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትሄድ ሆና መጣችው፡፡» አል-ቀሰስ 25

ሸይኽ ናሲሩ ሰዕዲ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ ተፍሲራቸው ላይ እንዲህ አሉ:- “ይህ የሚያመላክተው የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት መሆኗን ነው፣ ምክንያቱም አይናፋርነት በላጭ ከሆነው ከመልካም ስነ-ምግባር ነው!፣ በተለይ በሴቶች ላይ።” [ተፍሲሩ ሰዕዲ]

↪️"ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆነ…" በማለት አካሄዷን አውስቷል፣ አላህ ይህን አካሄድ አንቺም ከቤት የሚያስወጣሽ አስገዳጅ ነገር ሲኖር ተግባራዊ እንድታደርጊው ፈልጓል ማለት ነው። አለባበስሽ ሸሪዐው የሚፈልገው አይነት ሆኖ በጅልባብና ኒቃብ የተሰተርሽ ሆነሽ ብትወጪ እንኳን ይህ አይናፋርነት ፈፅሞ ሊለይሽ አይገባም!። ምክንያቱም ሀያእ ከፈጣሪሽ ዘንድ የተቸረሽ ትልቁ ሀብትሽና ውበትሽ ነው!።
"
↪️የነዚያ ጋጠ-ወጦች ጩሃት ሸንግሎሽ በስመ ስልጣኔና ግልፀኝነት ሀያእሽን አትልቀቂው የአንቺ የሙስሊሟ እንስት የፈጣሪዋ ትልቅ ችሮታ ነው!!። ሀያእ የሚባለውን የተፈጥሮ ስጦታሽንና ሀብትሽን ለማቆየት ምናምንቴዎችን ትተሽ ጓደኝነትሽን ሀያእ ካላቸው እህቶችሽ ጋር አድርጊው!። ጓደኛሽ ሀያእ ከሌላት ሙተነቂብ መሆኗ አለያም ከአንቺ በላይ እውቀት ስላላት አትሸንግልሽ!፣ ከቻልሽ ሀያእ እንዲኖራት ምከሪያት! ካልተስተካከለች ግን ራቂያትና ሀያእ ያላቸውንና ዲናቸው ጠንካራ የሆኑ እህቶችሽን ጓደኛ አድርጊ!።
"
↪️ወንድሜ ሆይ! ልታገባ ስታስብ ሀያእ ያላትን ሴት መምረጥ እንዳለብህ አትዘንጋ!። ልታገባት ያሰብካት ሴት ምናልባት ማሻ አላህ አለባበሷ ሸሪዐዊ የዲን እውቀቷም እንደዛው ሊሆን ይችላል፣ ግን ሀያእዋ እንዴት ነው?!። ምክንያቱም ሀያእ ትልቅ ዋጋ አለው!
በዚህ አስቸጋሪ ዘመን ሀያእ የሌላት እንስት ከራሷ የባሰ ሀያእ የሌለውን ትውልድ ቢሆን እንጂ ሀያእ ያለውን ትውልድ ልታፈራ አትችልም!!።

↪️ሀያእ እየጠፋ የመጣ የሙስሊም እንስቶች ትልቅ ሀብት ነው!! እህቴ ሆይ! ትልቁን ሀብትሽን ውበትሽን፣ የፈጣሪሽን ስጦታ ፈልገሽ አጥብቀሽ ያዢው!!

✍🏻ኢብን ሽፋ:

#ውዷ_እህቴ_በሀያዕሺ_በሂጃብሺ_ተዋቢ_አትዝረከረኪ_ቁጥብ_ሁኚ_ውድ_ትሆኛለሺ!!

የተለያዩ ት/ት ሰጪ ፅሁፎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከሌሎት
#join ⤵️ ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
#ሴቶች_እቤታቸው ውስጥ አጫጭር ልብሶችን መልበስ ይፈቀድላቸዋልን❓

✅“በቤቷ ከሆነና ከባሏ ውጭ ሌላ ወንድ የሌለ ካልሆነ በስተቀር አጭር ልብስ መልበስ አይገባትም።

(ባሏ) ከሌላ ሰው ጋር ባለበት ሁኔታ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ እንዲሁም ገላዋን የሚያሳይ ስስ የሆነ ልብስ መልበስ አይፈቀድላትም።

↪️ነቢዩ  “የእሳት ሰዎች የሆኑ  ሁለት አይነት ሰዎች ካሉ በኋላ ለብሰው ያልለበሱ ሴቶች …፣ ጀነትን አይገቧትም። ሽታዋንም አያገኟትም።” ብለዋልና።

በመሆኑም ሴት ልጅ አጭር ልብስ ወይም ጠባብ ወይም ከውስጡ ቆዳን የሚያሳይ ስስ ልብስ ከለበሰች በትክክልም ይህች ሴት “ለብሰው ያልለበሱት ሴቶች” ከተባሉት ትመደባለች።

በላይዋ ላይ ልብስ ስላለ ለብሳለች ይባላል። ልብሱ ግን (ገላዋን ለመደበቅ) ምንም ስለማይጠቅማት አልለበሰችም።”

        ምንጭ ☞⇘⇘
مجموع فتاوى ابن عثيمين (12/268)

ከቻናላችን ከሌሉ
#join በማለት ይቀላቀሉ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
◼️ኢልም በመፈለግ ላይ ፅና‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

◾️قال الإمام_أحمد بن محمد بن حنبل:
💦ኢማምአህመድ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይሉ ነበር፦

📌【أنا أطلب العلم إلى أن أدخل القبر】
✅ እኔ እውቀትን ቀብር ውስጥ እስከምገባ (እስክሞት) ድረስ እፈልጋለሁ (እማራለሁ) ይሉ ነበር።

📚 [شرف أصحاب الحديث ١٣٨]

✅ የሸሪአ እውቀት ተዝቆ የማያልቅ ትልቅ ባህር ነው። እድሜ ልክህ ብትማር ምታገኘው የተወሰነውን ነው። ህይወትህ በዚህ ምድር ላይ እስካለ ድረስ እውቀት በመፈለግ፣ ባወቅከው ነገር ላይ በመስራትና ወደዚህም ዳእዋ ወይም ጥሪ በማድረግ ላይ ቀጥል። እውቀት ልፋትና ጊዜ ይፈልጋል። በአንድ ጀምበር በአቋራጭ ኣሊም አይሆንምና ጅህልና ከላይህ ላይ እስኪጠፋ ድረስ በፅናት ልትጓዝ ይገባል። ኢልም በመፈለግህ አላህ ግዴታ ያደረገብህን ግዳጅ ከመወጣትህ ባሻገር አጅር ምታገኝበት ኢባዳም ጭምር ነውና አቅምህ በቻለው ልክ ሳትሰላችና ሳትዳከም ወደፊት ልትጓዝ ይገባል።

↪️አደራ፦ የሳምን የወርና የአመት ተማሪ ከመሆን ተጠንቀቅ። ልቅናህ ክብርህና ዝናህ ያለው በዚህ ዲን እስልምና ላይ ነውና ዲንህን በማወቅ ላይ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳትል ጠዋት ማታ በመልፋት የዱንያም የአሄራ ስኬት ከሚጎናፀፋ ውድ የአላህ ባሮች መካከል አንዱ ትሆን ዘንድ አንገትህን ደፍተህ ተማር እወቅ።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

👉በግልባጩ ለውዷ እህቴም ይሁን ምክሩ አንቺም አንገትሺን ድፍት አድርገሺ ድንሺን ተማሪ ኦኽታየ አደራ!!


#join በማለት ይቀላቀሉ⤵️⤵️⤵️

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
♨️✅ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ❗️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️
#ክፍል_ስምንት↩️
〰〰〰〰〰〰〰

#ስምንተኛ፡ - አንዲት ሴት ለሆነ ጉዳይ ስትወጣ አጅነብይ የሆኑ ወንዶችን ዘወር ዘወር እያለች መመልከት የለባትም፡፡
ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡-

⫸【وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنِّ】

↪️“ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡” አን ኑር 31
#ዘጠነኛ፡ - የአላህን ትዕዛዝ ማክበር አለባት፡፡

🔷አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯ

⫸【وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الجَاهِلِيَّةِ الأُولَی وَأَقِمْنَ الصَّلَاةَ وَاتِينَ الزَّكاةَ وَأَطِعنَ اللَّه وَرَسُولَهُ إِنَّمَا يُرِيدُ اللَّه لِيُذْهِبَ عَنكُمُ الرِّجْسَ أَهْلَ البَيْتِ وَيُطَهِّرَكُمْ تَطْهِرًا】

↪️“በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም
በማጌጥ አትገለጡ፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡

↪️የነቢዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከእናንተ ላይ እርክስነትን ሊያስወግድና ማጥራትም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው፡፡” አል አህዛብ፡


✅ #የተከበርሽ_እህቴ_ሆይ! ይህ አጠቃላይ ሴቶችን በተለየ ሁኔታ የሚመለከት ሰላም የሚሰጥ ልቅናዋን ጠባቂ ተደርጎ የሚቆጠር ቁርኣንን እና ሐዲስን መሰረት ያደረገ ህግና ደንብ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ሙስሊም ሴት ክብሯ የሚጠበቅበት ፤ ከአደጋ
እራሷን የምትከላከልበት ፤ እድለኛ የምትሆንበትን ታላላቅ አቅጣጫዎችን በመስጠት አላህ ታላቅ ጸጋ የዋለ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡


✅ #የተከበርሽ_እህቴ_ሆይ! ፡ ሙስሊም ሴቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ኢስላም አልቋል

↪️ ለተከበረ ህይዎቷ መስተካከል ዋስትና ወስዷል ፤ መለያዋን ሂጃብ አድርጓል ፤ ሴት ልጅ የአላህን ዲን አጥብቃ እስከያዘች ፤ የጌታዋን ትእዛዝ እስከጠበቀች ፤ መልእክተኛዋን صلى الله عليه وسلم እስከታዘዘች ፤ ለሸሪዓው የተናነሰች እስከሆነች ድረስ ተከብራ ትኖራለች፡፡በዱንያም ይሁን በአኼራ ታላቅ የሆነ ምንዳ ታገኛለች ፡፡

🔺ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋልና!!


#ኢንሻአላህ
#ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል••••••

•
•
•
•

🔷ሙሉውን ማንበብ ከፈለጋችሁ ወደ ቻናላችን
#join በማለት ይቀላቀሉ
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አምስት ➭➭➭➭➭➭➭➭ ➠ይህ አትራፊ የሆነው ንግድ እንጅ ተወጋጅ ፣ ከሳሪ ፣ ጸጋዋና መልካሟ የሚቋረጥ ፣ባለቤቷ በቅርብ እርሷን ትቷት የሚጓዝ የሆነችው ዱንያ ንግድ አይደለም፡፡ባሪያው ከዚህ ከሳሪ የንግድ ውልና ቃልኪዳን ባለቤቶች ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡ ▪️ኢማም አሽ'ሻጢቢይ ረሂመሁላህ ዑለሞች ለዚህ ጉዳይ ምሳሌ እንዳደረጉ ገልጸዋል፡…
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ስድስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

➧የዚህ አንጡራ ሐብት ባለቤት ከአላህ የተሰጠውን ይህን ውድ ጸጋና እውነታ
የማያውቅ
፣ ውስጡ በወህይ ኑር ያላበራ ፣ ምስኪንና ቂል ሆኖ እድሜውን በእንቶ
ፈንቶ የሚያሳልፍ ከሆነ ወደቀብር ዜሮ ሆኖ ተጎትቶ ይገባል፡፡
ወንድሞቸ ሆይ! አኼራ መልካም ስራ ለመስራት ፉክክር የሌለባት ፣በመልካም ስራ ድሓ ለሆኑ ሰዎች የማትመች አገር ነች፡፡

በውስጧ ያስቀደመው መልካም ስራ እንጅ ሊያግዝ የሚችል ውድ የሆነ
ጓደኛ የለም ፣ መዋዋስ የለም ፣ ሶደቃ የለም፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ የመልካም ስራ ድሃ ሆኖ ከጌታው ጋር መገናኘት የለበትም፡፡
ውድ የሆነውንና አላህ የሰጣቸውን የጊዜ አንጡራ ሐብት መልካም ስራ በመስራት ይጠቀሙበት፡፡

▪️ለእርሱም ክብር ይስጡ፡፡

إذا كان رأس المال عمرك فاحترز
عليه من الإنفاق في غير واجب


➧“ተጠንቀቅ! እድሜህ ከሆነ አንጡራ ሀብትህ ፤ ዋጅብ ከሆነው ውጭ አታባክን እባክህ)) ነፍሱን መካሪ የሆነ ሙስሊም አላህ የሰጠውን እድሜ ነገ አላህን ሊያስደስት በሚችል መልካም ስራ ብቻ ያሳልፍ፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን
ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡” አል ሐሽር 18

➧የመልካም ስራ ምንነትና ማረጋገጫ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲በዚህ ክፍል መልካም ስራ ምንድን ነው? አንድ ስራ እንዴት ነው መልካም ሊሆን የሚችለው? ለሚሉ ተገቢ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትና ማብራራቱ የግድ ይሆናል፡፡

➛መልካም ስራ ፡ ማለት ግዴታም ይሁን ግዴታ ያልሆነ አላህና ረሡል صلى الله عليه وسلم ያዘዙትና የሚወዱት ተግባር ነው፡፡ ይህ ሰፊ ሜዳና ሁሉን የሚያስተናግድ በር ነው፡፡ የንግግር እና የተግባር ፤ የውጭና የውስጥ መልካም ስራዎች ሁሉ በዚህ ክፍል ይካተታሉ፡፡

➭ ይህ የንግድ ሜዳ የውድድር
ሜዳ ነው
፡፡ በዚህ ሜዳ ላይ የአላህን ረህመት የሚከጅሉ ፣ ታላቁን ምንዳ ፣ ተጸጽተው በመልካም መመለስን የሚፈልጉ ሁሉ ይሽቀዳደሙ ፣ይወዳደሩ!አንድ ስራ ፍጹም አምልኮ ለሚገባው አምላካችን አላህ እስካልሆነና አፈጻጸሙ
የረሡልን صلى الله عليه وسلم መንገድ እስካልተከተለ ድረስ መልካም ሊሆን አይችልም፡፡


➠ስራን ፍጹም ለአላህ ማድረግ የሁሉም መልካም ስራ መሰረት ነው፡፡ ሁሉም በእርሱ ላይ ነው የሚገነቡት፡፡ መልካም ስራዎች አይነታቸው ቢለያይም ቁጥራቸው ቢበዛም በኢኽላስ
ላይ (ፍጹም ለአላህ በሆነ መልኩ) ካልቆሙ ሰሪው ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡


➻በተመሳሳይ ኢኽላስ ኖሮት ነገር ግን በረሡል صلى الله عليه وسلم መመሪያ መሰረት ካልተፈጸመ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚ የሚሆነው ሁለቱንም - ኢኽላስና ሙታበዓን - አጣምሮ ሲጓዝ ነው፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ

“ስራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ..” አል ሙልክ፡2
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➛ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➧ፅሁፉን በተከታታይ ለማገኘት #Join
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w