💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
من وصايا العلامة العثيمين رحمه الله قال :

.اشتغل أنت بعيوبك وطهر نفسك منها بقدر المستطاع ، وعليك بخاصة نفسك ؛ لأن الإنسان الذي يشتغل بعيوب الناس سوف يتعب ...".

በራስህ ነውር ላይ ተጠመድ፣ ተጨነቅ፣ በቻልከው አቅም ከነውርህ ለመፅዳዳት ሞክር! የራስህ ነፍስ ላይ አደራህን!! በሰው ነውር ላይ የሚጠመድ ሰው መድከሙ አይቀርም....

التعليق على اقتضاء الصراط (٩٢)


https://t.me/https_Asselefya1
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ

🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?!
➫➫➫➫➫➫➫

➲ክፍል ሶስት

➤በአላህ ፍቃድ ከመልካም ጓደኛ አድርገን ልንይዘው ከሚገባ ሰው መካከል የተወሰኑ ባህሪዎችን እንመልከት ኢንሻ አላህ!

➛ከዲን ስትዘናጋ የሚያስታውስህ!!

➲ይህ ማለት አንተን ሸይጧን እና ነፍስያ ወስውሰውክ አንዳንድ ነገራቶችን ከዲን ስትዘነጋ የሚያስታውስክ ማለት ነው ።

➤እንዲሁም ወደ ወንጀል ለመዳፈር ይህ ስትሞክር እጅህን ይዞ የሚከለክልክ ማለት ነው ወንድሜ።

➲ይህ ታላቁ ምርጥ ጓደኛ ማለት ነው ለምን ብትለኝ አንተን ወደዝህ ታላቅ ኸይር እየጠቆመህ ነው እና የጓደኛ ታላቁ ሚስጢር ይህ ነውና ።


➤ሰላት ሲደርስ ወደ መስጊድ እንሂድ ብሎ የሚያስታውስክ ወደ ዳዕዋ ወደ ቅርአት ቦታ ይዞህ የሚሄድ ማለት ነው ይህ ትልቅ የአላህ ፀጋ ነው ።

❷➛በተውሂድና በሱና ላይ የታነፀ!!

➤ይህ ማለት አንድ ሰው ተውሂድ ከለለው ጓደኛ አድርገህ ልትይዘውም አይገባም ምክኒያቱም አንተንም ሊያበላሽክ ይችላልና ተጠንቀቅ።

➲ በተውሂድና በሱና የሰለፎችን መንገድ የሚከተል መሆን አለበት ይህን ካገኘህ ትልቅ ደስታ ነው ላንተ ስለዝህ በተውሂድ በሱና ላይ ራሱም ጠንካራ ሆኖ አንተም የሚያጠነርክ መሆን አለበት ወንድሜ ።


➤ተውሂድን ትቶ ወደ ቀብር ከሄደ ወደ መሻይኾች ከሄደ ወደ ቆሌ እና አድባርን ከለመነ ይሄ ላንተ ጓደኛ ሳይሆን የአላህ ጠላት ነውና አንተም ጠላት አድርገህ ልትይዘው ይገባል ።

➲ብዙ ሰዎች የተውሂድ ሰዎችን ጓደኛ ባለማድረጋቸው የተነሳ ከተውሂዳቸው እና ከሱና ተንሸራተው በመጥፎ ጓደኛ የተነሳ በሽርክና በቢድዓ ላይ ሲዋኙ እናያለን አላህ ይጠብቀን ።

➤ስለዝህ ለዝህ ትልቅ አደጋ እንዳትጋለጥ ዘንድ ጓደኛ አድርገህ የምትይዘው ሰው እይ ወንድሜ እህቴ በደንብ መመልከት ይጠበቅብናል ስንወዳጅ የተውሂድን ሰው እንወዳጅ ።

❸➛ሁሌም ያንተን ደስታ የሚመኝ !!

➲ሁሌም ያንተን ደስታ የሚመኝ ጓደኛ ላንተ ምርጥ ጓደኛህ ነው እንዳያመልጥህ ያዘው ጠበቅ አድርገህ ለምን ይህ እድል ለብዙ ሰዎች ስላልተገኘላቸው ።


➤አንዳንድ ጓደኛ ተብየዎች ከወንድም ከሴትም ያንተን ወይንም ያንቺን ደስታ ሲመለከቱ በጣም የሚከፋቸው አሉ ለምን ?

➲እንዲህማ ከሆነ ጓደኝነታችሁ የጥቅም ወይንም ለግዜው እንጅ ከልብ አልነበረም ማለት ነው ምን ይጠቅማል ይሄማ ማስመሰል የሚሉት ትልቁ በሽታ ውስጥ ገባን ማለት ነው ።

➤አንተ ስትደሰት እሱም የሚደሰት አንተ ሲከፋህ የሚከፋው መሆን አለበት ወንድሜ ሁሌም ስኬትህን የሚመኝ በቻለው ያክልም ከጎንህ የሚቆም መሆን አለበት ይሄ ታላቁ የአላህ ፀጋ ነው አላህ ብቻ ይወፍቀን እንጅ ።

➲አንተ እያዘንክ እሱ ከተደሰት አንተ ጠቦህ እሱ ከሰፋው አንተ ስኬትህን ስታገኝ እሱ ይሄን ሲያይ የሚከፋ ከሆነማ ቶለ ብለህ ከርሱ መራቅ አለብህ ይህ ጓደኛ ሊሆንህ አይችልምና ።

➧ክፍል አራት ይቀጥላል ኢንሻ አላህ...........✍️

✍️አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/abuUseyminabdurehman

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➧እርዚቅሺ የምትበይዉ የምትጠጪዉ እደተፃፈ ሁሉ ባልሺም ተፀፏል ማን እደምታገቢ ተፀፏል!

➛ራስሺን ገላልጠሺ ስለወጣሺ ባል አይገኝም!

➧so ኒቃብ ጂልባብሺ ዉስጥ ተደበቂ ያንቺ ባል አላህ የፃፈዉ ግዜ ሲደርስ ይመጣል!!
‏﴿ يَا حَسْرَةً عَلَى الْعِبَادِ ۚ ﴾
➧እውነተኛ ጓደኝነት ልብ ውስጥ የሚያሳድረው ልዩ ጣእም አለው። ስትገናኝ፣ ስትደዋወል ልብህን አድምጠውማ። ከድብርትህ አትነቃም? የሚስሰማህ እርካታ፣ እፎይታ፣ ሀሴት የለም?
ምናልባት በዚህ ካልተሰማህ ጓደኛህ ሲጎዳ፣ ሲቸገር፣ ሲሞት ምን ያክል እንደተሰማው ልብህን ጠይቀውማ። ከወትሮው የተለየ ስሜት ከሌለህ ግንኙነታችሁ ጓደኝነት የደረሰ አይደለም።
ወይም በሆነ ምክንያት ጓደኛህ ቢርቅህ አትረበሽም? አትጨነቅም? ደግሞ ደጋግሞ ከልብህ አልጠፋ እያለ አትቸገርም? ካልሆነማ ይሄ ትውውቅ እንጂ ጓደኝነት አይደለም።

ጓደኝነት ቦታውን ሲጠብቅ ትልቅ ኒዕማ ነው። ግን ምን ያክል ቦታ እንሰጠዋለን?! ተገቢውን እንክብካቤ ባለመስጠታችን ምክንያት ከስንት ጓደኞቻችን ጋር ተራርቀናል? እስኪ ያለ ተጨባጭ ምክንያት የተራራቅናቸው የድሮ ጓደኞችን እናስብ። አይሰማንም? ክፍተቱ ከየት በኩል ነበር? ተገቢ እርምጃስ ወስደናል?
የጓደኝነት አለም ከግጭት ፍፁም አይደለም። መቀያየም፣ መበዳደል፣ መተማማት ሊገጥመው ይችላል። ሆኖም ግን ሆደ ሰፊነት ካለ ይቀጥላል። ይቅር መባባል ከኖረ ይለመልማል። ቂም፣ ምቀኝነት፣ ትእቢት ባለበት ግን ጤናማ ጓደኝነት ይቀጥላል ማለት ዘበት ነው።

🖊𝑼𝑺𝑻𝑨𝒁 𝑰𝒃𝒏𝒖 𝑴𝒖𝒏𝒆𝒘𝒐𝒓. (𝑯𝒂𝒇𝒊𝒛𝒆𝒉𝒖𝒍𝒍𝒉)

https://t.me/IbnuMunewor

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
""አስተማሪ ጥበበኛ መሆን አለበት""


➧በንግግርህ ለተማሪው ትምህርቱን እንዲወድ አድርግ ጠንካራ ጎበዝ እንዲሆን"
➧ኢማሙ ዘሀብይ ሪሁመሁላህ ኢልም ላይ እንዲጠነክር እንዲወድ እንዲማር ያደረገኝ
➧አንዲት ትንሽ የአስተማሪየ ንግግር ነበረች ይላሉ !! የዘሀብይ አስተማሪ የሆኑት አል-በርዛሊይ እንዲህ አሉት ለተማሪያቸው
"ዘሀብይ "ፁህፍህ የሙሀዲሶችን ፁሁፍ ይመስላል" ይች ንግግር ነች ሙሀዲስ እንዲሆን ያናሳሳችኝ ይላሉ ።


(( الدرر الكامنة)٢٧٨/٤


✍️ምንኛ ያማረ ነዉ ከበሳል አንደበት አሁን ላይ ግን
ስንቶች አስተማሪዎች ናቸዉ የተማሪዎቻቸዉ ሞራል የሚገድሉ በመጥፉ ቃል ከሚወዱት ትምህርት እድርቁ የሚያደርጉት!!አላሁመ ሙስተዓን!


➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ኦለሞች እንደሚሉት! በባል ላይ መህር ሲበዛበት እዕምሮዉ ላይ እና በልቡ ላይ ሚመላለሰው ለሷ ብሎ ብዙ ነገር እንደተሸከመ ነዉ።

فقه النكاح والعشرة بين الزوجين: /٨٨/

ሴቶችዬ ቀለል አድርጉት !!

https://t.me/https_Asselefya1
الشيخ سليمان الرحيلي
➛ጥሎሺ/መህር /ብዙ የከፈለ ባል ፣በመካከላቸው ችግር ሲፈጠር :አንች ከመጀመሪያዉም አድክመሽኛል ይህ ነው ማይባል ገንዘብ ነው ላንች ስል ያዉጣሁት ።

መህሩ በጣም ትንሽ ሆኖ ያገባት ባል:በመካከላቸው ፀብ ሲፈጠር ; ዉድ ብትሆኚማ አባትሺ በትንሽ ጥሎሽ/መህር / አይድርሽም ነበር። የነገሮች ሁሉ መልካሙና ጡሩው #መካከለኛ የሆነ ነገር ነው #መካከለኛ የሆነ ነገር መልካም ፍሬን እንጂ መጥፎ ፍሬን አያፈራም ።

فقه النكاح والعشرة بين الزوجين /٨٨/

https://t.me/https_Asselefya1
قال الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله
➧ጥሎሺን ማስወደድ የዱንያዊ ክብር ወይም ተቅዋን አያሰጥም!!
➘ዱንያዊይ ክብርን ተቅዋን ቢያሰጥ ኖሮ ረሱል ከኛ በፊት ቀድመዉን በተገበሩት ነበር
። ረሱል ﷺ መህርን ሲሰጡ ለሚስቶቻቸው በጣም የወረደም አይደል በጣም ከፍ ያለም አይደለም መካከለኛ  ።  እንዲሁም ልጆቻቸውን ሲድሩ በመካከለኛ መህር ነበር። ይህ ደግሞ የሴቶችን ቦታ ይጠብቃል በባልና ሚስት ያለውን ግንኙነት ያሳምራል!!

فقه النكاح والعشرة بين الزوجين:٨٨/


➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
አድ-ዱሩሱል ሙሂማ الدروس المهمة.apk
110.1 MB
🆕 📲 አዲስ አፕሊኬሽን ተለቀቀ

አድ-ዱሩሱል ሙሂማህ ❞

🎙 በአቡ ኡሰይሚን አብዱረሕማን ዝናቤ የተሰጠውን የ" አድ-ዱሩሱል ሙሂማህ" ሙሉ ደርስ የያዘ የአንድሮይድ መተግበሪያ!

🔰ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
👉https://t.me/almuhajir_app/122
🔰ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ!
━━━━━━
𝐀𝐋-𝐌𝐔𝐇𝐀𝐉𝐈𝐑 | 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐀𝐩𝐩 & 𝐆𝐫𝐚𝐩𝐡𝐢𝐜𝐬

☎️ ስልክ- 0936489716 - ™️ @muhualis

https://t.me/abuUseyminabdurehman/8309
` الاختلاط بين الرجال والنساء

➣የወንዶችና ሴቶች ቅልቅሎሽ
" ልዩ መልዕክት "
⇘ኡኽቲ... ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ ያናግሩሻል፤


⇘ከታላቁ ሊቅ ሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ቢን ባዝ ድንቅ ምክርን ያዘለ ፈትዋ የተቀነጨቡ ጭብጦች [አላህ ይዘንላቸው]

⇘ሒጃብ ምንድነው መረጃውና አስፈላጊነቱን ሁሉ ዳስሰው ተከታዮቹን ቁምነገሮች አስተላልፈዋል፤

☞ ሒጃብሽ አስፈላጊና ግዴታሽ ነው!

⇘ከቅርብ ቤተሰቦችሽና አማቾችሽ [ከአጎትና ከአክስት ልጅ፣ ከባል ወንድም… ] ጭምር ተሸፋፈኚ።
በቀላሉ ስሚያገኙሽ ይበልጥ አስጊው የነሱ መንገድ መሆኑንም ልብ በይ።

⇄ ' ልቡ ንፁህ ነው እንዲህ ያለ ነገር አያስብም ' የሚል ቀጭን ምክንያት ከፊትና አንፃር ቦታ የለውም ።
⇘ባህልና ተለምዶም ከሸሪዓ በላይ ሊሆን አይገባም።

⇘ከወንዶች ጋር ያለ በቂ ሒጃብ ከመቀላቀል ተቆጠቢ።

⇘ተሸፋፍነሽም ቢሆን መህረምሽ (አባትሽ፣ አጎትሽ፣ ወንድምሽን የመሳሰሉ የቅርብ ቤተሰብሽ) በሌለበት ከባዕድ ወንድ ጋር በገለልተኛ ቦታ እንዳትገኚ።


⇘ከወንዶች ጋር ከሚያጋፋሽና ከሚያነካካሽ ቦታዎች ያቅምሽን ያህል ራቅ በይ።

⇘ሸይጣን ባገኘው ቀዳዳ ሊያጠቃሽ አሰፍስፏልና መንገዶቹን አትቅረቢ።

⇘ላሳለፍሽው ህይወትሽ ተውበት አድርገሽ ጌታሽን ምህረቱን ጠይቂው።

⇘የማንንም ትችት፣ ወቀሳና ውዥንብርም አትፍሪ። እንዳሻው ሊዘልብሽ እንጂ አዝኖልሽ አይደለምና።

↳ ለሁሉም ቁርኣናዊና ሀዲሳዊ ግልፅ መረጃዎችን ከነማብራርያው ገልፀውልሻል☞

⇘የክብርሽ በር ክፍት ሆኖ እንዲቀር የሚሟገቱሽ ሰዎች ምን ይሆን ፍላጎታቸው


➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1