💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ውድ የሱና ወንድሞቼና እህትቼ እነዚህ ከታች የዘረዘርኳቸው ወንድሞች

ይኸነው በማይባል ጉዳይ አክራሪ ውሃብይ ናቸው በሚል ታሰረው ይገኛሉ።

የነዚህ ወንድሞች ሀገር ጃማ ደጎሎ ነው ከታሰሩ አራት ቀናቸው እናም ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት ሊሞት ነው የት እንደታሰሩም አይታወቅ ም ደሴ ወስደዋቸዋል ተብሎ ነበር ደሴም ተፈለገለ አልተገኙም።

1/ አብዱሰላም ከበደ አሰን
2/ ጡሀ አብዱል ባሲጥ
3/ ሙሀመድ ሰማን

ውድ የሱና ወንድሞቼ በቻላችሁት አቅም ትብብራችሁን እንሻለንና እነዚህ ወንድሞች በያላችሁበት ሀገር በቅርብ ወደ አሉት እስረ ቤቶች በመሄድ አጠያይቁልን ስንል በትህትና እጠይቃለን።

የኛ ሰላም መሆን የነሳቸው ጠላቶቻችን ይሄው ኢስላም ስለሆኑ ብቻ መግደሉ ማቃጠሉ አለበቃችው ሲል እያገቱ ማሰሩን ደግሞ ተያይዘውታል ።

አድስ ነገር ካገኛችሁ በዚህ አሳውቁን
➘➘➘➘➘➘➘➘➘
@Abu_Luqman13
+251931786342

ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው


https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Video message
‏
۞ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
۞

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል 1⃣1⃣0⃣➰
〰〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Forwarded from Ibnu Muhammedzeyn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አላህ በሚሰጠን ኒዕማ(ፀጋ) እንደምትሐስዱን(እንደምትመቃኙን) ቀድሞ ቁርኣን ነግሮናል።

{وَدَّ كَثِيرٌ مِّنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَوْ يَرُدُّونَكُم مِّن بَعْدِ إِيمَانِكُمْ كُفَّارًا حَسَدًا مِّنْ عِندِ أَنفُسِهِم مِّن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ الْحَقُّ}
«ከመጽሐፉ ባለቤቶች ብዙዎች እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በኾነው ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ሊመልሱዋችሁ ተመኙ፡፡»[በቀራ 109]

እሄው ሌት ተቀን እኛን ለመመለስ ትጥራላችሁ ትደራጃላችሁ ትለፋላችሁ ግን ደስ የሚለው ብዙዎች ከናንተ ሀይማኖት ነው ወደኛ ሀይማኖት የሚመለሱት‼️

አላህ በሚያወርድልን ኒዕማ እንደምትመቃኙና እንደምጠሉ ገና ሳታሳውቁን በስተፊት ቁርኣን ቀድሞ አሳውቆናል።

{مَّا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَلَا الْمُشْرِكِينَ أَن يُنَزَّلَ عَلَيْكُم مِّنْ خَيْرٍ مِّن رَّبِّكُمْ}

«እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎቹም የካዱት በናንተ ላይ ከጌታችሁ የኾነ መልካም ነገር መወረዱን አይወዱም፡፡»[በቀራ 105]

ያው በምቀኝነት (ልክ እንዳንተ) ፊታችሁ ይገረጣል እንጅ በአማኞች ላይ ሌት ተቀን በዝችም ሆና በዛንኛው አለም የአላህ እዘነትና ፀጋ ከመውረድ አይቋረጥም። በቁጭት ሙቱ‼️
ደግሞ "ጋኒን ተሰብስቦ ይስቅባቸዋል ብዬ…" እያለ ያፊዛል አመድ በዱቂት ይስቃል ነው እንጅ ነገሩ ከናንተ በላይ ጋኒን አለ እንዴ!? እሄ ሳቃችሁ እኮ የሰይጣ ስብስብ ሁላ ‼️

እርኩስ የሳት ማገዶ እንኳን እኛ አንተም በእጅህ የጠረብከውን እንጨት አምልከህ እፀድቃለሁ ብለሃል……

⊰✿◇✿⊱•
✍ t.me/IbnuMuhammedzeyn
Audio
✅የጀግና ሴቶች ተምሳሌት!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

➛ታላላቅ ሴቶች በኢስላም ያበረከቱት ታሪክ!

➛ሴቶች ሸሪአን ማወቅ ምናክል አንገብጋቢና አሳሳቢ እንደሆነ ከሌሎች ቁም ነገሮች ጋር የተዳሰሰበት ምክር!

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
حفظه الله

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
▪ሴቶች ሆይ!!


▪እናንተ የልጆቻችሁ ታላቅ አስተማሪ ናችሁና እናንተ ከምንም በፊት ተውሂድን ተማሩ።

▪ ምንም የሌለው ምንም መስጠት አይችልም እንደሚባለው ፣ አንቺ የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ተውሂድን ካላወቅሽ ለልጆችሽ ምንም መስጠት አትችይም።

▪ሴቶች ሆይ! ልጆቻችሁን በልጅነታቸው ተውሂድን አስተምሩ ።


▪ወጣቶች ሆይ! ከምንም እውቀት በፊት የተውሂድ እውቀት ይቀድማልና ቅድሚያ ስጡት።


➰ተውሂድ እና ሽርክ

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧ማስታወሻ 2/3/4ተኛሚስት ለመሆን 👉 ከመጣደፍሽ በፊት ካንች በፊት የነበረችዉን እህትሽን አያያዙን አጣሪ ከገቡ ቡኋላ ማለቃቀስ ማፊ ፍይዳ። 👉እናማ አትሩጪ አጣሪ!ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታልና! 👉ገብተሺ ሂወትሺ አበላሽተሺ ከመዉጣትሺ በፊት አገባብሺ አስተካክይ እህቱ! 👉ልብ በሉ ሴቶች!!
👉ተጨማሪ ስላገቡ ብቻ ዘላለም ፀንቶ የሚኖር የሚመስላቸዉ ሞኞች አሉ ያላገቡ እህቶቻቸዉ በምላሳቸዉ በአሽሙር የሚወጉ እረ ተዉ ምን አልባች ያንች ትዳር ፈርሶ እሷ አግብታ በትዳሯ ፀንታ ልትኖር ትችላለች ይህ የአሏህ ስራ ነዉና!!

👉እናማ ስላገባችሁ ብቻ አትኮፈሱ እንደዉም ይህን ትልቅ ነኢማ ለለገሳቸዉ አላህ እያመሰገናችሁ ራሳችሁ ዝቅ አድርጉ ላላገቡ እህቶች አላህ እድወፍቃቸዉ ዱዓ አድርጉ!!

👉ዝም ብላችሁ አትንቦጣረሩ አማኝ አይንጠባረርም
ሁለየ ተናናሺ ነዉ!!!
016 ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
♦️አዲስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

▪️كتاب منهاج الفرقة الناجية والطائفة المنصورة

➲ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ

▪️ክፍል አስራ ስድስት
〰〰〰〰〰

♦️የኪታቧን PDF ለማገኘት
➴➴➘➘➷➷➴➴➘➘➷
https://t.me/https_Asselefya1/3725

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/https_Asselefya1
▪በላጭ_ሴት!!
➬➬➬➬➬

➧በተውሒድ በሱና የማትደራደር፡
ፈገግታ የሞላት የማትዞር መንደር፡
ዘመድ ጎረቤቷን ወዳጂና አክባሪ፡
የሀላል ንጉሷን የእውነት አፍቃሪ፡
ሀቅ ላይ የፀናች ጥንቁቅ እንስት የምር፡
የውበት አለቃ ሲያዋት የምታምር፡


➧ሰለፍይ ኮከብ ያች ኒቃቢስቷ፡
መንሀጂና አቂዳ የህነው ርስቷ፡
በመልካምነቷ ሁሉም ሰው የሚያፍራት፡
አሏህ በችሮታው አሟልቶ የሰራት፡
ስትጓዝ በአደብ ሳብ ያለ ቁመቷ፡
ሀያዕ የለበሰች በወጣትነቷ፡


➧ብልጥ አርቆ አሳቢ አስተዋይ የሆነች፡
ሚስትነት የገባት መልካም ሴት ይህች ነች፡
የወንድን ልጂ ህይወት ምትሞላው ሀሴት፡
የዘላለም ንግስት ይህች ነች በላጭ ሴት፡

✍️በኑረዲን_አል_አረቢ حفظه الله

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧ከተውሂድ አርማዎች ➛➛➛➛➛➛➛➛ ➭ክፍል አስራ አንድ ➲3⃣ኛው አንኳር ነጥብ ተውሒድን ማረጋገጥና ማሟላት ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➧ተውሒድን ማረጋገጥ ከፍተኛና የላቀ ደረጃ አለው፡፡ ረሡል صلى الله عليه وسلم በታወቀው ሐዲሳቸው የተውሒድ ባለቤቶች ያለምንም ሒሳብ እና ቅጣት ጀነት እንደሚገቡ አውስተዋል፡፡ ▪️وعن ابن عباس وغيره رضي الله عنهم قال صلى…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ክፍል አስራ ሁለት
➻➻➻➻➻➻➻

➲እነዚህ በሁለቱም ክፍል ያሉ ተውሂድን አረጋጋጭ ሰዎች - ሙቅተሲድና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች - የትንሳኤ ቀን ያለምንም ሂሳብና ቅጣት ጀነትን ይገባሉ፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️ثُمَّ أَوْرَثْنَا الْكِتَابَ الَّذِينَ اصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا ۖ فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِ وَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌ بِالْخَيْرَاتِ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ

➧“ከዚያም እነዚያን ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው፡፡ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አልለ። ከእነርሱም መካከለኛ አልለ፡፡ከእነሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አልለ፡፡ ያ (ማውረስ) ፤ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡” (ፋጢር፡32)

➲ሶስቱም ክፍሎች - ነፍሱን በዳይ ፣ሙቅተሲድ (መካከለኛዎች) እና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች - ዘውታሪ የሆኑ ገነቶችን ይገባሉ፡፡ ሙቅተሲድ እና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች፡ ያለምንም ሂሳብ ጀነት ይገባሉ፡፡

➧ከሽርክ በታች በሆኑ ወንጀሎች ነፍሳቸውን በዳዮች ደግሞ ጀነትን ይገባሉ፡፡ ነገር ግን ነፍሳቸውን የበደሉት ልክ እንደ ሙቅተሲድና በመልካም ቀዳሚዎች ያለምንም ሂሳብና ቅጣት መጀመሪያ ጀነትን አይገቡም፡፡ ይልቁንም ለቅጣትና ለሂሳብ ይቀርባሉ፡፡ በአላህ መሽአ ውስጥ ናቸው፡፡ አላህ ከፈለገ ቀጥቶ ጀነት ያስገባቸዋል ወይም ምህረት
ያደርግላቸዋል፡፡

➧አራተኛው አንኳር ነጥብ የተውሒድ አፍራሽና አጉዳዮች
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➲ተውሒድ የራሱ የሆነ አፍራሽና አጉዳይ አለው፡፡ የተውሒድ አፍራሾች ስራን የሚያሰርዙ ሀይማኖቱን በአጠቃላይ የሚያበላሹ ናቸው፡፡ እነርሱም በአላህ መካድ፣ማጋራትና ጥርት ያሉ ንፍቅናዎች ናቸው፡፡ የክህደት ፣ የማጋራት እና የትልቁ ንፍቅና አይነቶች ከመሰረቱ ተውሂድን ያፈርሱታል ፣ ይንዱታል፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጹ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

➧“ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሃዲዎቹ ትሆናለህ ማለት
ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል
፡፡” (አዝ ዙመር:65)

➲የተውሒድ አጉዳዮች፡ ማለት ደግሞ ተውሒድን ሙሉ በሙሉ የማያበላሽ የማይንድ ነገር ግን የሚቀንስ ነው፡፡ ከነዚህ መካከል ትንሹ ክህደትና ተግባራዊ የሆነው ንፍቅና ናቸው ፡፡

▪️የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው ሐዲስ ተናግረዋል፡-

▪️"آية المنافق ثلاث: إذا حدث كذب ، وإذا وعد أخلف ، وإذا اؤتمن خان"

“የመናፍቃን ምልክት ሶስት ናቸው፡ ሲያወራ ይዋሻል ፣ ቃል ሲገባ ያፈርሳል ፣ ሲያምኑት ይከዳል” ቡኻሪ፡ 33 ሙስሊም፡59

➧ይህ ተውሒድን የሚቀንስ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ከባሪያው ላይ ከተገኙ ተውሒዱን እና ኢማኑን ያጎድሉታል፡፡ ትንሹ ማጋራት ፣ ማጋራትን ሳያስብ በአንደበቱ የማጋራት ቃላትን መናገር ተውሂድን ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ማጋራትን አስቦ ከሆነ ተውሒዱን ሙሉ በሙሉ ከሚያፈርሱት ትልቁ ማጋራት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡

በዚህ ምክንያት እያንዳንዱ አማኝ ሙሉ በሙሉ አፍራሽም ይሁን አጉዳይ ነገሮችን በመራቅ ተውሒዱን መጠበቅ ፣መንከባከብ ይኖርበታል፡፡

▪️ሸይኽ ዓብዱረህማን ብን ሀሰን - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

((የተውሒድ ተቃራኒ ሽርክ መሆኑን እወቅ፡፡ እነርሱም ሶስት አይነቶች ሲሆኑ ትልቁ ማጋራት ፣ ትንሹ ማጋራት እና ድብቁ ማጋራት ናቸው፡፡

▪️ለትልቁ ማጋራት መረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

“አላህ በርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡” አን ኒሳእ፡116

▪️لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

“አልመሲህም አለ፡- “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን
ተገዙ፡፡” እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም
አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡”
አል ማኢዳህ፡72

➛ይህ አይነቱ ማጋራት አራት አይነት ክፍሎች አሉት የሚለውን በቀጣይ ክፍል እናየዋለን።
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል


تأليف: فضيلة الشيخ عبدالرزاق بن عبد المحسن البدر

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】

🖊ام فاروق

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➧ልብ ትዝጋለች ፣ ብረት እንደሚዝገው ሁሉ ማፅጃዋ አሏህን ማውሳትና ቁርኣን መቅራት ናቸው ።
አሏህ ሆይ የአንተን ውዴታ ወፍቀን!✍

▪️صباح الخير اذكار صباح የጧት ዚክርን እንዳረሱ ባረከላህ ፊኩም

🌹መልካም ቀን🌹☕️