💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
▪️اللهم أنت أصلحت الصالحين، فأصحلنا حتى نكون صالحين.

مالك بن دينار / #كتاب_التوبة صـ ٧٥

➲«አላህ ሆይ! ሷሊሆችን ሷሊህ እንዲሆኑ የረዳሀቸው አንተ ነህና!
እኛንም ከሷሊሆች እንድንሆን ሷሊህ አድርገን።»

ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሂመሁሏህ)

[ኪታቡ ተውባ ገፅ (75)]
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዷን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
➲ የቁርአን ልቅናና ክብር
➲ የቁርአን መገለጫዎች

《ክፍል 3⃣0⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➧የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

【مَنْ صلَّى عليَّ صلاَةً، صلَّى اللَّه علَيّهِ بِهَا عشْرًا】

➲በኔ ላይ አንድ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ በአስር እጥፍ አድርጎ ያወርድበታል።
📚 رواهُ مسلم
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
سورة_الكهف_في_صفحة_واحدة_للجوالات.pdf
626.5 KB
👉ሱረቱል ካህፍ በ pdf መልኩ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
♦️አላህ ቀርተው ከሚጠቀሙበት ያድርገን
https://t.me/https_Asselefya1
سورة الكهف كاملة للقارىء عبدالله الجهني
🔁 سورة الكهف 🔁

➲የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፦
【من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين】

▪️የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል።
📚 صحيح الجامع - رقم : (6470)

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ኹጥባ_በአሏህና በመልዕክተኛዉ ፊት አትቀሙ!
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ

لَاتُقَدِّمُوا بَينْ يَدَيِ اللهِ وَرَسُولِهِ
በአሏህና በመልዕክተኛዉ ፊት አትቀደሙ!

🕌 ደሴ አል-አዝሓር መስጂድ

📅 يوم الجمعة 17 رجب 1443 الموافق 18/02/2021

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማ
↓↓↓
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4892
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4892
••
أَعْظَمُ حُقُوق البَشَر هُوَ ⁧#حقُّ_الوَالِديْنِ؛
لِأَنَّ اللهَ جَعَلهُ فِي المَرْتَبَةِ الثَّانِيَةِ بَعْدَ حَقِّهِ."

📍‏ تَفْسِيرُ سُورَة النِّسَاء | ŘŹ1 Řľ903 ⁧
الشيخ الوالد ابن_عُثَيمِين ⁩رَحِمَهُ الله

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዷን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
➲ የቁርአን ስንቀራ አስፈላጊ አደቦች
➲ አስደናቂ የቁርአን መገለጫዎች

《ክፍል 3⃣1⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
✅አድስ ተከታታይ ፅሁፍ 〰〰〰〰〰〰〰〰 ➲ከተውሂድ አርማዎች ➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አንድ ➲“ተውሒድ” የዲኑ መነሻም መድረሻም ፤ ውስጡም ውጩም ነው፡፡ተውሒድ የመልእክተኞች ሁሉ የመጀመሪያም የመጨረሻም ጥሪ ነው፡፡ ተውሒድ “ላኢላሃ ኢል'ለሏህ” ለሚለው ቃል ትርጉም ነው፡፡ ለተውሒድ ሲባል ፍጥረታቶች ተፈጠሩ ፣ መልክተኞች ሁሉ ተላኩ ፣ መጽሓፎች ሁሉ እንዲወርዱ ተደረገ፡፡ በተውሒድ ምክንያት…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሁለት
➻➻➻➻➻➻

✅የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➧ተውሒድ፡ ከፍተኛ ደረጃና ቦታ የሚሰጠው መሆኑን የሚጠቁሙ በርካታ መለያ ባህሪያትና ትሩፋቶች እንዳሉት እወቅ፡፡ ከእነርሱ መካከል አስሩን እንደሚከተለው እጠቁምሃለሁ፡፡

➲አንደኛ፡- የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደሚጠቁመው እኛ የተፈጠርንበት እና
የተገኘንበት ዋና ዓላማ ለተውሒድና ተውሒድን ለማረጋገጥ ብቻ ነው
፡፡


▪️وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ጅንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ (ዓላማ) አልፈጠርኳቸውም፡፡” አዝ ዛሪያት፡56

➧“ኢልላ ሊየዕቡዱን” ፡ የሚለው የቁርኣን ቃል ትርጉም “እኔን (በአምልኮት) ብቸኛ ሊያደርጉኝ” ማለት ነው፡፡ በዚህ ዓለም የተፈጠርንበት ዋና ዓላማ ለቀልድና ለጨዋታ ሳይሆን ለተውሒድ ሲባል ነው፡፡

➭አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ልቅ አድርጎ
ሊተወን ሳይሆን እርሱን በብቸኛነት ልንገዛው ፈጠረን ፤ እርሱን በአምልኮ ብቸኛ ልናደርግ አስገኘን፡፡ የተውሒድ ሁኔታ ላቅ ያለ ለመሆኑ ከማስረጃ በኩል በዚህ ይብቃ፡፡


➲ሁለተኛ፡- ተውሒድ የነብያቶችና የሩሡሎች ጥሪ መሽከርከሪያ ምህዋር ነው፡፡ አላህ የላከው ማንኛውም ነብይ የጥሪው ትኩረትና መቆሚያ መሰረቱ ተውሒድ ነው፡፡ ለዚህም በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡

▪️አላህ በተከበሩት ቁርኣናዊ አንቀጾች የሚከተለውን ተናግሯል፡

◀وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ

➧“በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡” አን ነሕል (36)

▪️وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

➧“ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡” አል አንቢያእ፡(25)

▪️وَاسْأَلْ مَنْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رُّسُلِنَا أَجَعَلْنَا مِن دُونِ الرَّحْمَٰنِ آلِهَةً يُعْبَدُونَ

➧“ከመልክተኞቻችንም ካንተ በፊት የላክናቸውን (ተከታዮቻቸውን) ከአልረህማን ሌላ የሚገዟቸው የሆኑን አማልክት አድርገን እንደሆነ ጠይቃቸው፡፡” አዝ ዙኽሩፍ (45)

۞ وَاذْكُرْ أَخَا عَادٍ إِذْ أَنذَرَ قَوْمَهُ بِالْأَحْقَافِ وَقَدْ خَلَتِ النُّذُرُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

“የዓድንም ወንድም (ሁድን) ሕዝቦቹን በአሕቃፍ ባስጠነቀቀ ጊዜ አውሳላቸው፡፡ በስተፊቱና በስተኋላውም ብዙ አስፈራሪዎች በእርግጥ አልፈዋል
፡፡ “ከአላህ በስተቀር አትግገዙ ፣ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁና” በማለት (ባስጠነቀቀ ጊዜ)፡፡ አል አህቃፍ፡21

➲“ኑዙር” ማለት መልክተኞች ማለት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩትም ይሁን ወደኋላ የመጡት መልክተኞች “ከአላህ በቀር አትግገዙ” በሚለው አላማ ላይ አንድ ሆነዋል፡፡

➧ተውሒድ ፡ የነብያቶች እና የሩሡሎች ጥሪ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቦቻቸው ከመልእክተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያደምጡት ቃል የተውሒድን ቃል ነው፡፡ ወደአላህ ጥሪ ሲያደርጉ አንድ ብለው የሚጀምሩት በተውሒድ ነው፡፡
〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

تأليف: فضيلة الشيخ عبدالرزاق بن عبد المحسن البدر

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ⑦⑦➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➻ክፍል አስራ ሁለት ➲እነዚህ ሰዎች መቃብር ውስጥ የተነባበረና የማያቋረጥ ምንዳ ማግኘታቸው በጣም ያስገርማል፡፡ ይህ ነው ከሞት በኋላ ያለው ሁለተኛው እድሜ፡፡ በዚህ ተቃራኒ በምድር ላይ ሌሊት እና ቀን እየተንቀሳቀሱ - አላህ ይጠብቀንና - መልካምን ስራ ሳይሆን ሐጢያትን የሚያስመዘግቡ አሉ፡፡ ሱብሃን አላህ! የሁለቱን ልዩነት ተመለከታችሁ!…
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል አስራ ሶስት

➤እነዚህ ደረጃዎች የሰው ልጅ ጸጸቱ ጥቅም የማያስገኝበት ነገር ግን የሚጸጸትባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ዓቅለኛ የሆነ ሰው ስራ በሚሰራበት በዚህ ምድራዊ ዓለም ነገሮችን ከወዲሁ ያስተካከል፡፡ ሳያስበው ይህችን ዓለም ከመልቀቁና አላህ ሂሳብ ሳያደርገው በፊት ነፍሱን ከወዲሁ ራሱ ሂሳብ ያድርግ፡፡

▪️አላህ ሱበሃኑሁ ወተአላ በሐዲስ አልቁድስ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

◀"يا عبادي، إنما هي أعمالكم أحصيها لكم ثم أوفيكم إياها، فمن وجد خيرا فليحمد الله، ومن وجد غير ذلك فال يلومن إلا نفسه"

➲“ባሮቸ ሆይ! ይህ ስራችሁ ነው ፣ ለእናንተ ሙሉ በሙሉ ቆጥሬ እይዘዋለሁ ፤ ከዚያም ሙሉ ዋጋዋን እሰጣለሁ፡፡መልካምን ያገኝ ሰው አላህን ያመስግን ፤ ከዚህ ውጭ ያገኘ ደግሞ ነፍሱን እንጅ ሌላን እንዳያማ፡፡” ሙስሊም፡2577


➲ከሰለፎች አንዱ ጓደኛውን ለመምከር ፈልጎ ወደመቃብር ይዞት ሄደ። ከመቃብሮች መካከል አንዱን እየጠቆመ “በዚህ ቦታ ብትሆን ምን ትመኛለህ” አለው፡፡ እርሱም “ከሰራሁት ውጭ መልካም ለመስራት አላህ ወደዚህ አለም እንዲመልሰኝ እመኛለሁ”በማለት ምላሽ ሰጠው፡፡ “አንተ በአሁኑ ሰዓት ልክ እንደተመኘኸው ነህ” በማለት መለሰለት፡፡

➲ ይህ ማለት አንተ አሁን የምትገኘው በዚህ የዱንያ ዓለም ውስጥ ነው፡፡ዓቅለኛ የሆነ ሰው ደግሞ ትንሳኤ ቀን ደርሶ ሂሳብ ከመደረጉ በፊት ነፍሱን ሂሳብ ያደርጋል ፤ ከመመዘኑ በፊት ነፍሱን ይመዝናል፡፡

➲እያንዳንዱ የአላህ ባሪያ ወንጀልን ይጠንቀቅ፡፡ “ወንጀል ከዚህ አትራፊ ንግድ
አዘናግታ ኪሳራ በሆነ ንግድ እንዲጠመድ ታደርገዋለች፡፡ ከቅጣት ይህ ብቻ ለእርሱበቂው ነው”
አል ጀዋቡል ካፊ፡ ገጽ (248) ጤንነትን እንለምናለን፡፡

➧አላህ ከንግግርም ይሁን ከተግባር እርሱ ለሚወደውና ለሚቀበለው እንዲገጥመን ፤ በኢማን ውበት እንዲሸልመን ፣ ከጥመትና ከማጥመም አርቆ የሐቅ መሪም ተመሪም እንዲያደርገን በመልካም ስሞቹ ፣ በከፍተኛ መገለጫዎቹ እማጸነዋለሁ፡፡

➧አትራፊው የንግድ ማዕከላት የሚለው ፅሁፍ በዚህ ተጠናቀቀ! እኔም መልካም ስራዎችን ሰርተው ከከሰሩት አላህ እንዳያደርገን እያልኩ ፁሁፌን በዚህ ጨረስኩ!!✍

▪️ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】
〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰

➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Kitabu Tewhid #55
Ibnu Munewor
* ደርሱ:- ኪታቡ ተውሒድ
* ክፍል:- 5⃣5⃣
* ርእስ:-
باب من الإيمان بالله الصبر على أقدار الله
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዷን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
➲ ቁርአን ስንቀራ ልንጠብቃቸው የሚገቡ ስነስርአቶችና አደቦች

《ክፍል 3⃣2⃣》

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w